🌹…………ክፍል 50 ………..🌹
የመጨረሻ ክፍል
" ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣ ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ።
መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት። ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ።
ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም።
"ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ።
አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ ታመምኩ ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ።
ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና
"ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት።
ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቀልቀል ወረደ።
ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ•••
"ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ።
ፉቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች።
ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት።
እሷም እህቴ ነች።
የምኖረው ልኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር።
የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ።
ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም።
ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው።
"ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ ብትንትኑ ወጣ።
ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም።
ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ።
ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ እየጠበኩ ነው።
መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ ልጅ እግር በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ። አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና•••
"እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት።
ወረቀቱ ላይ የተፃፈው ••••
"ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም"
የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ። .
.
.
.
•••••••ተፈፀመ ••••••••
.
.
.
.
ለነበረን ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ ❤❤
.
.
ቤተሰቦቼ በሌላ ልብ ወለድ እንገናኛለን። በአጠቃላይ በታሪኩ ላይ ጠቅለል ያለ ሀሳብ አስተያየታችሁን ፣ ወደፊት ቢስተካከል የምትሉትን ነገር ሁሉ በኮሜንት መስጫው ስር እንደምታስቀምጡ ተስፋ እናደርጋለን 🙏🏻
https://vm.tiktok.com/ZMkkFephM/