***
በዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት ሆስፒታሉ የጤና አገልግሎትን ከማሰፋት እና አለምአቀፍ ግንኙነትን ከመፍጠር አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “ኸርት አታክ ኢትዮጵያ" ከተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከውጭ በመጡና በሀገር ውስጥ ሙያተኞች ለ87 የልብ ታካሚዎች ነጻ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤግዝኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደምም በነበረዉ ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ባለፉት ሁለት ዙሮች 154 ታካሚወችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዉ በተጨማሪም በልምድ ልውውጥ እና በጥናትና ምርምር በጋራ ለመስራት ውይይት እየተካሄደ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አመላክተዋል።
የልብ ህክምና አገልግሎት ዘመቻው ለ3ኛ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ የልብ ታካሚዎች ሀምሌ ወር በሚካሄደው 4ኛ ዙር ዘመቻ የቀዶጥገና ህክምና አገልግሎቱን ያገኛሉ ተብሏል።