የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court) @federalfirstinstanc Channel on Telegram

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

@federalfirstinstanc


የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court) (Amharic)

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ እባኮትን በዚህ ቦታ ያጋሩ። በእርስዎ ቅናሾ አገናኝ ስለ መተግበር፣ ስለ በዓል፣ ማህበረሰብ እና የምርምር ሥራዎች፣ ከተሞች፣ ሴራዎች እና ከትክክለኛ ዓይነትን በፍላጎት ለማድረግ ለመልኩ እንዲህ ትልቅ መልእክቱን እንመለከት።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

28 Nov, 11:15


የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የተፈጸመው ስምምነት ለፌዴራል ተቋማት ብቻ ሳይሆን ለክልሎችም መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው በተፈጸመው ስምምነት ላይ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክቡራን ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና ከቤተሰብ ችሎት ጋር ለሚገናኙ ሰራተኞች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የስምምነቱን ውጤታማነት ለመጨመርና የማህበረሰቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

28 Nov, 11:15


ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የኗሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት ፈጸመ፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የኗሪት አገልግሎት ኤጀንሲ የፍቺ እና የጉዲፈቻ ውሳኔዎች መመዝገብ የሚያስችላቸውን ስምምነት ህዳር 19/2017 ዓ.ም በጋራ ፈጽመዋል፡፡
ስምምነቱ ከመፈጸሙ አስቀድሞ ለስምምነት በሚያበቁ ሁኔታዎች ላይ የጋራ ጥምር ኮሚቴ ተዋቅሮ የዳሰሳ ጥናት ሲደረግ እንደቆዬ እና በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት የስምምነት ሰነድ መዘጋጀቱን በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ስምምነቱ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር እና በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለመየሁ የተፈጸመ ሲሆን የፍርድ ቤቱ እና የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት የፍ/ቤቱ ፕሬዘዳት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር በንግግራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የኗሪት አገልግሎት ኤጀንሲ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ስምምነቱ የፍርድ ቤቶችን ጫና በመቀነስና የመረጃ ጥራትን በመጨመር ደረጃ ያለው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ በትኩረትና በቁርጠኝነት የምንሰራበት ይሆናል ብለዋል፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

28 Nov, 11:08


የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ ጸደቀ
*************

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።
ደንቡ በጸደቀበት ወቅት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ እንደተናገሩት የዳኝነት አከፋፈል ሥርዓቱን ለማዘመን፣ ሥርዓቱም አጭር፣ ቀልጣፋና ለከፋዩ ያመቸ እንዲሆን ለማስቻል ሕጉን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች እስከ አሁን ድረስ ሲጠቀሙበት የነበረው የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል የህግ ክፍል ማስታወቂያ ደንብ በ1945 ዓ.ም የወጣና ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በደንቡ ያልተሸፈኑ በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ወቅቱን ያገናዘበ የዳኝነት ክፍያን መወሰኛ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በተጨማሪም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁን ከደረሱበት ወቅታዊ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ተመጣጣኝ የሆነ የዳኝነት ክፍያ ለማስከፈል የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ ደንቡ ተዘጋጅቷል።
ደንቡ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቂ ውይይት የተደረገበትና የሀገር ውስጥን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባትና የሌሎች ሀገራትንም ልምድ ታይቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል ። መረጃዉ የኢትጵያ ፕሬስ ድርጅት ነዉ፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

14 Nov, 10:56


ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
**********************************************
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስትራሮችን አወዳድሮ ለመሾም ጥቅምት 08 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ተወዳዳሪዎች ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሲሆን፣ ቅሬታ ያላችሁ አመልካቾች ከ27/02/17 ዓ.ም እስከ 3/03/17 ዓ.ም ድረስ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በስራ ሰአት በአካል በመቅረብ ቅሬታ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጹሁፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እገልጻልን፡፡
ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ለጹኁፍ ፈተና የተመረጡ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር
ተ/ቁ
ሙሉ ስም ከነአያት
1. ዓለሙ ኤና አዳም
2. ሙለታ ገለታ ዲንቃ
3. አማረች ሰብስቤ ወ/ፃዲቅ
4. ትዕግስት ፋንታሁን አበራ
5. ስንታየሁ መስፍን አሻግሬ
6. አረጋሽ ነጋሽ አበራ
7. ትርጋሸዋ ዘሪሁን በየነ
8. ሊዲያ ሀይሌ ገብረሰንበት
9. ቆንጅት ሀይሉ ሰሙ
10. ጂማ ኢሳ የሱፍ
11. ይትባረክ ናሁአዳም አምባዬ
12. ባህርነሽ ሙርሻ ወ/ገብርኤል
13. ሱራፌል ገ/ሚካኤል አበበ
14. ኤደን አበበ አበራ
15. ሙላት ይሄነው አሰፋ
16. ሜሮን ገዳሙ ተክሌ
17. መሰረት አምባው ያለው
18. ወገኔ መንግስቱ ገ/እግዚያብሄር
19. ፈለቀ መለሰ ዘርጋው
20. ተመስገን አሸብር ሽፈራው
21. መስፍን ረጋሳ ቤኛ
22. ጸዳለ ነሲቡ በጋሻው
23. እየሩሳሌም ሙሉዓለም መሸሻ
24. ታሪክ ፋንታሁን ተስፋዬ
25. ግሩም ስለሺ ታደሰ
26. ታከለ ታደሰ ካሳ
27. ዘላለም ብርሃኑ ወርቁ
28. በላይ መካሻ ንጉሴ
29. ፍቅሩ ተክሌ ገ/የሱስ
30. ቤዛዊት ብ/መስቀል
31. ኤልያስ አሸብር ፍቅሬ
32. እንዳልካቸው ተካ ዋኬኔ
33. ጽዮን ግርማ ወርቁ
34. መሀመድ ጀማል ሲራጅ
35. ባንቺአምላክ ይመር አዲሱ
36. ፈትለ ዳምጠው ሀምዛ
37. እንግዳወርቅ ገ/ህይወት አይዳኝ
38. ሀብታሙ የሸዋሉል ዘበነ
39. ነጅሚያ ብድሩ ከድር
40. ደሳለኝ አባይ ጋሻው
41. አበባው ተሰማ ዘገዬ
42. አማኑኤል ገ/ወልድ አሻሞ
43. አክሊሉ አበበ ሸንኮር
44. ሀይማኖት ገብሬ ደሴ
45. ሄኖክ ታደሰ አባተ
46. አየለ ዘላለም በላይ
47. ጀሚላ ሙዘሚል ጀማል
48. ዘርአጽዮን ገበየሁ አስፋው
49. እያኤል ተመስገን አሼቦ
50. ገብረተንሳይ ተክለሀይማት
51. ሰናይት ወርቁ አዘናጋ
52. ራሔል ፍቅሩ ክፍሉ
53. ካሳ መንግስቴ ይማም
54. አብይ ፀጋዬ አበባየሁ
55. ድባብነሽ ገመቹ ወርዶፋ
56. ፋንታነሽ ተበጀ ተሰማ
57. ዘላለም ቻላቸው አንዳርጌ
58. ጽዮን ግርማ ወ/ማርያም
59. ሮቤል ማሞ በርሄ
60. ቴክታ ቴዎድሮስ ተሰማ
61. ጥሩነሽ ገለና ቢራቱ
62. ታጁራ ተክሌ ታንቶ
63. እስከዳር አራጋው ተሰማ
64. ቤተልሄም ሲሳይ መሸሻ
65. አበበ ሙሊሣ ዲንቃ
66. ጽጌሬዳ በቀለ ፈለቀ
67. ልዑልሰገድ ከበደ ወ/ሰንበት
68. መላኩ በላይ መስፍን
69. ሰብለ ታገሱ ንማ
70. ሀይማኖት ዝውገ ይሰማ
71. ፀጋዬ ጫላ ሜጋሮ
72. ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ በለጠ
73. ሰላማዊት አስራት ወልዴ
74. ሪሃና ጀማል አህመድ
75. ሁሉአመል ወ/ፃዲቅ
76. ዘሪሁን ሰለሞን አለሙ
77. ከድር ሚዴሶ ቦንክ
78. ሹረሙ መርዳሳ ከባ
79. አስናቀች ሂርጳሳ ጫላ
80. ቤተልሄም ወ/አረጋይ አልታየም
81. መሳይ እርገጣቸው ለማ
82. ዳንኤል አንጎሴ ነገሬ
83. አዳነች ታምሩ ወ/ሚካኤል
84. ፍጹም አብርሃም ውበት
85. ቃልአብ ይርጋለም አበበ
86. ሰሎሜ ረታ አለሙ
87. እመቤት ሀብታሙ ደራ
88. ጌጤ ከበደ ለገሰ
89. እየሩሳሌም ከበደ ካሳ
90. ማርያማዊት መለሰ ታደሰ
91. ሙሉጌታ አየለ ሞላ
92. ሁሴን ወልደ አበራ
93. ህይወት ተክሌ ወልዴ
94. አበራ አረፈዓይኔ አደሙ
95. ያብስራ ጀማነህ በቀለ
96. ራሄል ተካ ቆጭቶ
97. ቅድስት መንግስቱ ገ/ስላሴ
98. አንተነህ ጌታቸው ተፈራ
99. ዘላለም ቻለው ዳምጤ
100.ውብዓለም ዳጉ ምህረቱ
101. ቅድስት መኮንን ሀይሌ
102. ቤተልሄም ብርሃኑ አንሼቦ
103. ተሬሳ በየነ ተፈራ
104. ሄዋን ተስፋዬ ለገሰ
105. መገርሳ ኢተፉ ቡጤ
106. አልማዝ በትሩ ሀይሉ
107. መልካሙ ጎሳዬ ወ/አፈራሽ
108. ፅዮን ደረጃ ሲሳይ
109. ሲራክ ሲሳይ አሸኔ
110. ሜላት እንግዳወርቅ መልሴ

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

24 Oct, 05:14


የ2016 ዓ.ም የፍርድ ቤቱ የዳኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ተካሄዶ ለክቡራን ዳኞች ውጤቱ ተገለፀ
******************************************
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ባወጣው የዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ቁጥር 09/2015 መሰረት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ከጥቅምት 1/2016 እስከ ሐምሌ 30/2016 ባለው ጊዜ የተካሄደው ምዘና ውጤት ለዳኞች የማሳወቅ ተግባር ተከናውኗል፡፡
በመመሪያው መሰረት የዳኞችን የስራ አፈጻጸም 12 አካላቶች የሚመዝኑ ሲሆኑ እያንዳንዱ መዛኝ የሚሰጠውም ውጤት በመመሪያው ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በዚሁ አግባብ 160 የፍርድ ቤቱ ዳኞች የስራ አፈጻጸማቸው ተመዝኖ ከመቶ ውስጥ ያገኙት ነጥብ በጥቅሉ ሲቀመጥ፡-
97 ዳኞች ከ90 በላይ
56 ዳኞች ከ81-90
4 ዳኞች ከ70-80 ነጥብ አምጥተዋል፡፡
የፍርድ ቤቱም ክቡራን የበላይ አመራሮችም መመሪያዉ በሚያስቀምጠው አግባብ እያንዳንዱ ዳኛ ያገኘውን የምዘና ውጤት በአካል በመግለጽ በውጤቱ ላይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት መስማማት ተችሏል፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

18 Oct, 08:12


የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)

13 Oct, 13:14


ዓመታዊ የአስተዳደር ሰራተኞች በዓል እና የችሎት መክፈቻ ስነ ስርዓት ተከበረ፡፡
***********************************************
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ሰራተኞች ዓመታዊ በዓልን እና የችሎት መክፈቻ ስነ ስርዓትን ክቡራን ፕሬዝዳንቶች፣ ተጠሪ ዳኞች፣ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዋች እና በሁሉም ምድብ ችሎት የሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ግቢ ጥቅምት 02/2017 በደማቅ ሁኔታ አክበሯል፡፡ በፕሮግራሙ ከፍተኛ ዉጤት ላመጡ ሰራተኞች እዉቅና እና ሽልማት የተሰጣቸዉ ሲሆን በጡረታ ለተሰናበቱ ሰራተኞችም ምስጋና ተበርክቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ ላይም የፍርድ ቤቱ የበላይ አመራሮች የአስተዳደር ሰራተኞች ለዳኝነት ስራው ውጤታማነት እያበረከቱት ላለው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል።

2,495

subscribers

1,377

photos

21

videos