👇
#ቀብድ
ቀብድ በውል ማድረግ እና አለማድረግ መካከል "በው" ላይ ያለ መፍትሔ ነው።
ቀብድ ካልተፈፀመ መቀጠል ያልፈለገ ወገን withdraw ያደርጋል እንጂ ውል cancel አያደርግም።
ሁለት ምክንያቶች በኢትዮጽያ ውስጥ ቀብድን "double-ውስብስብ" አድርገውታል።
1ኛ/ በርካታታ ተቀራራቢ ፅንሰ-ሀሳቦች መኖራቸው
ለመጥቀስ ያክል:
down payment
Penalty clause
Promise to sell
Liquidated damage
የውል ማስከበሪያ
non-performance of contract
ተመሳሳይነታቸውና ልዩነታቸው ለሌላ ቀን ይቆየን። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ቀብድ ከተጠቀሱት ውስጥ አንዱም ስር አይወድቅም
2ኛ/ የቀብድ ህጉ "ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ ግንባታ" መሆኑ። በርካታ ድንጋጌዎች ሊጨመሩበት ይገባ ነበር።
ተጀምሯል ግን ገና ግንባታው 50% እንኳን አልደረሰም።
የፅንሰ-ሀሳቡ መወሳሰብ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ መሠረታዊ ገፅታው በከፊል ለመረዳት ያግዘናል።
ይኸውም ቀብድ እንዲኖር condition እና time period የግድ ናቸው።
በቤት ሽያጭ ምሳሌ እንመልከት (ልብ በሉ ምሳሌው የቤት ሽያጭ እንጂ የቤት ሽያጭ ውል አይደለም። ምክንያቱም ቀብድ በውል ማድረግ እና አለማድረግ መካከል ያለ ነው ብለናል)
so, አንድ ሰው 20 ፎቅ ያለው ህንፃ መግዛት ይፈልጋል። እንደ ባለሞያ ሳይሆን እንደ ገዢ አይቶት ወዶታል። ግን ደሞ ህንፃው ለታለመለት አገልግሎት እንዲውል የሚረዱ መዋቅሮች እንዳሉት በቅድሚያ ማረጋገጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በቅድሚያ በባለሞያ inspection ተደርጎ sewage system, አሳንሳር: ሽንት ቤቶች የሚሰሩ መሆናቸው: በርና መስኮት ያልተሰባበሩ መሆናቸው እንዲሁም በርካታ ግልፅ እና latent defects እንደሌሉት በአንድ ወር ጊዜ (time period) በባለሞያ ተመርምሮ report እንዲቀርብ የሽያጭ ውሉ "የሚፈጠመው" ሪፖርቱ ላይ ተመስርቶ እንደሆነ (conditiin) ከሻጭ ጋር ይስማማሉ።
ግን ደሞ ሻጭ እንድ ወር ሙሉ የገዢን ባለሞያ ውጤት መጠበቅ አይፈልግም። በመሀል ጥሩ ዋጋ የሚያቀርብ ሌላ ገዢ ሊያገኝ ይችላል። በሌላ አነጋገር ገዢ የምር የመግዛት ሀሳብ እንዳለው ማረጋገጥ ይፈልጋል። ለዚህ ደሞ መፍትሔው ቀብድ ነው።
እንበልና ገዢ የአጠቃላዩን ዋጋ 10% ቀብድ ለመክፈል ተስማምቶ ከፈለ።
በሁለቱ መካከል የቀብድ ስምምነት መኖሩ ህጋዊ ውጤቱ የሚከተለው ነው።
1/ ገዢ በአንድ ወር ጊዜ ህንፃውን ካላስመረመረ የከፈለው ለሻጭ ይቀራል።
2/ የ inspection report ቀርቦ ገዢና ሻጭ የተስማሙበትን ደረጃ የሚያሟላ ከሆነ ሻጭ አና ገዢ ወደ ቀጣዩ ሂደት መግባት ማለትም የህጉን ፎርማሊቲ የሚያሟላ ውል አድርገው ገዢ የከፈለው ቀብድ እንደ ቅድሚያ ክፍያ ተወስዶለት የቀረበትን ከፍሎ ማጠናቀቅ ቫጭም ህንፃውን ማስረከብ አለበት።
3/ በቁ 2 መሠረት ሁለቱ የተስማሙበት የ inspection report ቀርቦ ገዢ መቀጠል ፈቃደኛ ካልሆነ የከፈለው ቀብድ ለሻጭ ይቀራል።
4/ በቁጥር 2 ሻጭ ለመቀጠል ፈቃደኛ ካልሆነ (የአንድ ወር ጊዜ ሳይጠናቀቅ ወይም ሪፖርቱ ቀርቦ ሪፖርቱን ገዢው ከተቀበለው በኋላ ሀሳቡን ከቀየረ) ገዢ የከፈለውን እጥፍ አድርጎ ይመልሳል።
5/ ሻጭ የአንድ ወር ጊዜ ካለቀ በኋላ የቀብዱን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ከስምምነቱ የመውጣት መብቱን ያጣል። ጊዜው ካለቀ በኋላ በመካከላቸው አስገዳጅ ውል ይመሠረታል። ስለሆነም እንደውሉ እንዲፈፅም ይገደዳል።
6/ ቀብድ ለገዢ የከፈለው ተመልሶለት withdraw የማድረግ መብት ይሰጣል።
(ይሄኛው ነው በእኛ አገር የቀብድ ህግ ብዙም ዕውቅና ያላገኘው)
ይኸውም በሪፖርቱ መሠረት የቤቱ ደረጃ ሁለቱ ከተስማሙበት በታች ከሆነና ገዢ ቤቱን መግዛት ካልፈለገ የከፈለው ይመለስታል። ቀብድ ሁል ጊዜ የገንዘብ መወረስ እና እጥፍ ክፍያ አይከተለውም። ለዚህም ነው 'ሁኔታ' እና የጊዜ ገደብ ከቀብድ አላባውያን መሠረታዊ የሚሆኑት።
የጊዜ ገደብ እና ሁኔታ ከሌለ "ሲጀመር ቀብድ ለምን አስፈለገ?" የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ አይቻልም። በተጨማሪም በግልፅ "ቀብድ" ተብሎ ክፍያ ቢፈፀምም የጊዜ ገደብ እና ሁኔታ ከሌሉ ክፍያውን ከቅድሚያ ክፍያ መለየት የሚቻልበት መንገድ የለም።
ቀብድ የውል "በው" ላይ ያለ መፍትሔ ነው። ከዓመትና ሁለት በኋላ የቀብድ ክርክር የሚደረግ ከሆነ መግቢያው ላይ እንደተገለፀው ፅንሰ-ሀሳቡ double ውስብስብ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው።