የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን @eaa_123 Channel on Telegram

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

@eaa_123


ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን (Amharic)

ሰላም ይህን ሴቶችና ወንዶች ፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ቴሌግራም አካውንት ትክክለኛ መረጃ ይሆናል። የቴሌግራም በተግባር በሌላም አክስት ለማስመለሻ አይኖርም፡፡ የማንኛውም ቴሌግራም በአንድ አካውንት እንደአካው የሚል መሆኑን ማወቅ ይቻላል። ይህ ሴቶችና ወንዶች በሚገኘው ትክክለኛ መረጃ እንደተመረጡ ከሆኑ በፊት ከዚህ ቴሌግራም መንገድ ይጻፉ።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

11 Jun, 09:34


የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለማዕከላዊ ማእከል አመራሮችና ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፤
አዳማ ግንቦት 30/2016
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ሰልጣንና ተግባር በብቃት በመፈጸም በግብርናው ዘርፍ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር እየሰራ ሲሆን በሰራዎቹ በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የባለሙያዎችን አቅም በተለያዩ መንገዶች መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን በመገንዘብ በስሩ ላሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ኤፍታህ ሆቴል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ የተደራጀ እና እየተገነባ ያለ ተቋም እንደመሆኑ መጠን በየደረጃው ያሉ አመራሮችንና ሰራተኞችን አቅም በመገንባት በተመደቡበት የስራ መደብ ላይ ውጤታማ በመሆን በአዲስ መንፈስ እና ተነሳሽነት የባለስልጣኑን ተልዕኮ በብቃት ይወጡ ዘንድ አቅምን የሚገነባ ስልጠና መሰጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ ከዚህ በፊት ለባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰው አሁን እየተሰጠ ያለው ስልጠና ይህንኑ ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ድሪባ አክለውም በበጀት ዓመቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቀዳቸውን ተግባራት በውጤታማነት ለመፈፀም በተጠያቂነት መንፈስ በመደጋገፍና በመተባበር ተግባራትን በብቃት መፈፀም ተገቢ ስለሆነ ስልጠናውን በንቃት መከታተልና የስራ መመሪያ በማድረግ በቀጣይ ለስራ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
በመቀጠልም ቲም ቢውልድንግ በሚል ርዕስ ላይ ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣን መ/ቤታችን የእንሰሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሚድ ጀማል ሲሆኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አሰፈጻሚ ወ/ሮ መሰረት አበባው ደግሞ ስለ ስትራቴጅክ ምንነት እና የባለስልጣኑን የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድን ለስልጠና ተሳታፊዎች አቅርበዋል::
በመጨረሻም በቀረቡ የስልጠና ርዕሶች ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ የግልፅነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በአሰልጣኞች ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ከተደረገ በኋላ በስራ ሂደት አጋጠሙን ላሏቸው ችግሮች ደግሞ በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ እንዲሰጥበት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የተዘጋጀው ስልጠና የእርስ በእርስ መማማሪያና የተግባቦት መድረክ እንደመሆኑ መጠን ባለሙያዎች ያገኙትን እውቀት መሬት ማስነካት እንዳለባቸው ገልፀው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንም በመጠቀም የራሳቸውን አቅም በመገንባት ስራዎቻችንን በብቃት መፈጸምና ተቋማችንን የማዘመን ስራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

29 May, 15:42


https://www.youtube.com/watch?v=XrNCrKkNv-Q

1,616

subscribers

1,097

photos

7

videos