።።።።።።።።።።።።።
የአዲስ አበባበ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሰብአዊ መብት ድርጊት መረሃ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በ11ዱም ክፍለከተሞች ፖሊስ መምሪያ እስረኞች አያያዝ ዙሪ ባደረገው ጉብኝት መሰረት ሪፖርት አቅርቧል።
ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ በአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢበ፣ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ኮሚሽነር ሐሰን ነጋሽ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የፖሊስ ኮሚሽንናየአስራ ከንዱ ክፍለከተሞች ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
አቶ ተክሌ በዛብህ ሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ከማህበረሰቡ አስተሳሰብ ጀምሮ እስከተቋማት ግንባታ ድረስ ዳሰሳ ጥናት በማድረግ ችግሮች ላይ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ኃላፊው አክለው አሁን ያለንበት ወቅት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ምዕራፍ በመሆኑ ዓቃቢያነ ሕግ፣ዳኞች ፣ ፖሊስ አጠቃላይ የፍትህ አካላቱ ጠርቶ ማለፍ ያለበት ወቅት ላይ ስላለን መብት ጥሰትን ጨምሮ ነዋሪው የሚያነሳቸው ቅሬታዎች በቸልታ የማይታለፋ በመሆናቸው በተቋማቱ ብርቱ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነም አንስተዋል።
አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ በአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢበ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳይ በአንክሮ ሊታይ የሚገባ ነገር ነው ብለው ተሸራርፎ ሲገኝ ግን የሀገር ስም ሊያጠለሽ የሚችሉ ናቸው በማለት ሰብዓዊ መብት በአያያዝ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ነው በማለት በሁሉም ፖሊስ ተቋማት ወጥ የሆነ አሰራር ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል።
ወይዘሮ ሰላማዊት በላቸው በ11ዱም ክፍለከተሞች በተደረገ የእስረኞች ጉብኝት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ጉብኝቱ አንድ እስረኛ 48 ሰአታት ውስጥ ፍርድ ቤት ማቅረብ ፣የተጠርጣሪዎችን ዋስትና መብት ፣ንጹ የመጠጥ ውሃ ፣ የቀለብ አገልግሎት ፣ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም አካላዊ ነጻነት ላይ በታዩ የሰብአዊ መብቶች ግኝት ዙሪያ ሪፖርት አቅርበዋል።
ኮሚሽነር ሐሰን ነጋሽ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በተቋሙ የሚመጡ ወቀሳዎችን በጥናት ላይ ተመርኩዘን ችግሩን በመለየት እርምጃ ለመውሰድ የሚያግዙ ናቸው ብለው በእኛ ዘንድ የሚቆዩ ታሳሪዎች ከእኛ የተሻለ ቅርብ ስለሌላቸው የእስር ቤት ንፅህናን እና ጥበትን በተመለከተ ቀሪ ስራዎችን በትኩረት በመስራት በቀጣይ የተሻሻሉ ጉዳዮች ዙሪያ የሚንወያይ ይሆናል ብለዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ስራ አስኪያጅ አቶ መስዑድ የድርጅቱን አጠቃላይ ለቤቱ አቅርበው፤ስለሰብዓዊ መብቶች ምንነት እና ወቅታዊ ጉዳይላ ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።