"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ" @ortoteach Channel on Telegram

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

@ortoteach


ኑ መልካሙን መልካሙን እናውጋ፣እናውራ

መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ (Amharic)

እያንዳንዱ ሰው ከአድማጮችና ሽመልናዎች ጋር ስለ አስተማሩ ለየትኛውም እንደዚሁ ምን ያህል ተደመናል። ይህንን ቦታዎች በአሮጌ እና ምስራቅ ምንጭ አሉ። የምን እንደሆነ ይጠቁሙና መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ በሆነ። "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ" ለምን ተጠቅመን፣ ይህ በጣም ስንፈልገው አንድ ሁሉ ስለ አስተማሩ ያሉ ልዩ መምህር የሆነ። እናውጋ፣ እናውራ! ይህ ስራዎች በመኖሪያ ስሜ መግለጫዎች ላይ የሚገኙበት ሁሉ በመገበጽ ብቻ እንደሚቀርቡ የተሻለ-ሄደ ለሚፍሮዉ ግንኙነትና ስምምነት የሚመጣ ሰዉ ነህን! በዚህ ምክንያታ ለመጠቀም ከዚሁ የተሻለ፣ ለሌሎች ሴቶችና ሰውም እናውጋ፣ እናውራ አይደለም!

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ጨለማ ሲበዛ ድንጋይ ይደበቃል፣ ከዋክብት ግን ይደምቃሉ።
መከራ ሲበዛ ቅዱሳን ይገለጣሉ፣ ኃጥአን ግን ይደበቃሉ።
ጨለማ ለኮከብ መድመቅያው ነው ለድንጋይ ግን መደበቅያ ነው።
መከራ ለክርስቲያን መድመቅያው እና መብዣው ነው።
ክርስቲያንን የሚያበዛው መከራ ነው። ክርስቲያንን የሚያሳንሰው ኃጢአት ነው።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ጥር 21 ድንግል ማርያም በ 64 አመቷ ያረፈችበት እለት
የጥንት ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ትንሳኤ በዓይናቸው ያዩትንና የተማሩትን እንዲህ ይመሰክራሉ!
....................
1. # ኢቮድየስ_ዘአንጾኪያ (የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር) :- ይህ ታላቅ አባት ከጴጥሮስ ጋር አብሮ የነበረ፣ የድንግል ዕረፍትዋ በዓይኑ የተመለከተ፣ የትንሳኤዋም ሕያው ምስክር የሆነ ነው! ያየውምን ነገር በሙሉ "Homily on the Dormition of the falling asleep of Mary" በተባለው ክታቡ እንዲህ ይተርካናል!
...........
(ነሐሴ) ወር በአስራ ስድስተኛው ቀን ጠዋት በተመሳሳይ ምሽት በብርሃን ሰዓት፣ ጌታችን በታላቅ ክብር ወደኛ መጣ! ሰግደንም አመለክነው! ጌታም "ለምን ታዝናላችሁ?" ሲለን፣ አባቴ ጴጥሮስም "በእናትህና በሁላችን እመቤት ሞት፣ ከሞተችም ብኋላ ስጋዋን ስላላሳየሀን ነው" አለው! ጌታም ወደ መቃብሩ በመጣራት የድንግል እናቱን ስጋ በማስነሳት፣ ነፍስዋንም እንደገና ወደ ስጋዋ በማስገባት ልክ ቀድሞ በስጋ እንደምናውቃት በስጋ አየናት። መድኃኒታችንም ለስለስ ባለ ድምፅ "እነኋት ውድ እናቴን" አለን። ይህ የሁላችን እመቤት እና የወላዲተ አምላክ የሕይወትዋ መጨረሻው ይህ ነው በጦቢ(ጥር) ወር 21ኛ ቀን። ትንሳኤዋ ደግሞ በሜሶሪ (ነሐሴ) ወር በ16ኛው ቀን ነው> በማለት ከቀብሯ ተገኝቶ ትንሳኤዋን አይቶ ይመክረናል።
.............
2.ቅዱስ # ቴዎዶስዮስ_ዘእስክንድርያ (535 ዓ.ም)
አባታችን ቴዎዶስዮስ ስለ ትንሳኤዋ ሲንፕግረን <የነበሩበት ቦታ በእሳት ተሞላ። ጌታም በኪሩቤል ላይ ሆኖ የድንግልንም ነፍስ በእቅፉ በሰማያዊ ልብስ አጊጣ ይዟት ተገለጠ። ሐዋርያትም በፍርሐት ተሞልተው መሬት ላይ እንደ ሞቱ ሆኑ። እርሱ ፍርሐታቸውን አጥፍቶ እንዲህ አላቸው "እናንተ ደቀመዛሙርቴና ደናግል ሆይ፥ የእናቴን ክብር ታዩ ዘንድ ተነሱ።" እንዲህ ብሎም ወደመቃብሩ ጮሀ "ለእኔ መቅደስ የሆነሽኝ አንቺ ቅድስት ስጋ ሆይ፣ የእኔ የዘላለም ድንኳን የሆነችኝን ይህቺን ነፍስ ውሰጂ" ... ጌታ እነዚህን ቃላት ሲናገር መቃብሩ በዚያ ቅፅበት ተከፈተ... ከዚያም ብኋላ የከበረው የድንግል ስጋ ተነሳ፤ ነፍስዋንም አከበረቻት። ሁለት ወንድማማች ከተለያየ ሀገር እንድሚመጡ እንዲሁ ተባበሩ አንድም ሆኑ> ብሎ ወደ ትንሳኤዋ ይወስደናል።
.............
3.ቅዱስ # ዮሐንስ_ዘደማስቆ (675-749)
ይህ ቅዱስ አባትም <እርስዋ ልጅን ስትወልድ ድንግልናዋ እንደተጠበቀ እንዲሁ ስጋዋ ከሞትም ብኋላ ከመበስበስ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የተገባ ሆነ። ፈጣሪን በሕፃንነቱ በደረቷ እንዳቀፈችው እንዲሁ በመለኮታዊው ድንኳን (ሰማያዊ መቅደስ) ትኖር ዘንድ ተገባት! የእግዚአብሔር እናት የልጇ የሆነውን ነገር (ትንሳኤ) ታገኝ ዘንድ በፍጥረት ሁሉም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ ተብላ ትመሰገን ዘንድ ሆነች> ይለናል።
.............
4.ቅዱስ # ጌርማነስ_ዘቁስጥንጥንያ (8ኛ ክ.ዘ)
ይህ አባት ደግሞ <አንቺኮ እንደ ተፃፈው በውበት የተገለጥሽ፣ ድንግል የሆነ ስጋሽም ቅዱስና ንጹሕ፣ መላውም የእግዚአብሔር ማደርያ ነው። ስለዚህም ጠቅልሎ አፈር ሆኖ ከመቅረት ነጻ ሆነ (ቀረ) ምንም እንኳን አሁንም ሰው ብትሆኚ ሥጋሽ ወደ ማይበሰብስ ሰማያዊ ሕይወት (አካል) ተቀየረ! አሁንም ስጋሽ በሕይወትና በክብር፣ ሳይጎድፍና ሳይጎድል በፍፁም ኑባሬ አለ!> እያለ ከእናቱ ከእናታችን ጋር ያወጋል። በአባቶቻችን እምነት ያፅናን!
.... የትንሳኤዋ በረከት ከወደቅንበት ኃጢኣት ያንሳን!

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ለምን ይመስላችዋል ማህተባችንን እግራችን ላይ ያላሰርነው?
. ምክንያቱም ሰው፣እግር ቢቆረጥ ስለማይሞት ነዉ። ለምንስ እጃችን ላይ አላሰርንም?
. ምክንያቱም እጃችን ቢቆረጥ ስለማንሞት።
. ግን አንገታችን ላይ አስረናል ይህም ማለት ሰው፣አንገቱ ቢቆረት ይሞታል።
. ለክርስትናችን ህይወታችንን አስከመስጠት ድረስ፣እንታመናለን።
. ስጋን የሚገሉትን አንፈራም ይልቁን ነፍስንም ስጋንም በገሀነም ሊያጠፋ የሚቻለውን የድንግል ማርያም ልጅን እንፈራለን እንጂ።
. እናንተ ግደሉን፣እኛ እየሞትን እንበዛለን ምክንያቱም የያዝነው የቀራኒዮ አሸናፊውን የድንግል፤ማርያምን ልጅ ክርስቶስን ነው።
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በአንድ ወቅት ከተናገሩት

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


መድኃኔዓለም ሆይ!
አቤቱ አቤቱ ስንልህ በከንቱ እንዳንጠፋ ጠብቀን🙏🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ!
ጥቁር ልብስ

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ ከ ሰኞ እስከ እረቡ (ከጥር 29 እስከ የካቲት 1) ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ ከቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምህረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላለፈ።
ሼር በማድረግ ላልሰሙት የተዋህዶ ልጆች አሰሙ

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


<<ቆማችሁ ነፃነታችሁ ከሚረክስ
ሙታችሁ ስማችሁ ይቀደስ>>
ኢትዮጵያዊ ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ።

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


🕯🕯🕯
ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ በቀኝ ጎንህ ሦስት በግራ ጎንህ ሦስት ሆነው ለሠረፁት 6ቱ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ፡፡
ቅዱሱ አባት ሆይ፤ እኔ ልጅህ የአንተን በረከት እፈልጋለሁና የቀን ጉዳይ ጥሎኝ ለእርዳታ በምፈልግህ ጊዜ በነዚያ በክንፎችህ ፈጥነህ ድረስልኝ፡፡
መልክአ አቡነ ተክለሃይማኖት
የተክልዬ ምልጃና በረከት አይለየን🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


፤ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
፤ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
፤ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።
፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
፤ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
የሉቃስ ወንጌል ምዕ2 ቁ7-20
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


እንኳን ለቃና ዘገሊላ አደረሳችሁ🙏
ቃና ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ /2/ በዛ በሠርግ ቤት
ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ
ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ
.........................................
እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙበት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊት ዓለም
አንቺ ደረሽለት ሆንሽው አማላጅ
.......................................
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው አመቤታችን ነሽ
.............................................
የጌታ አምላክነት የተገለጠበት
ምንኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት
ዛሬም የኔ ህይወት ወይኑ ጎድሏልና
ድረሺ እመቤቴ ርህሪተ ህሊና
.......................................
ውሃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን።

ድንግል ማርያም ዛሬም በህይወታችን የጎደለውን ትሙላልን🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ጥር 10 #ከተራ
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! #መልካም_በአል!
#ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
@ orthodox tewahido

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ጥር 18🕯🕯🕯
የቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በዓል ነው
አጥንቱ የተበተነበት ደሙ የፈሰሰበት
70 ነገስታት ያፈሩበት እለት ነው
ጥር 18 " ዝርወተ ዓጽሙ " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ:: በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት:: በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ "እንዲል:: እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይሕቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው:: ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ:: የሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን ሼር በማድረግ ላላወቁት አሳውቁ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሹ በመከራ ግዜ ፈጥኖ ይድረስልን
አጥንታችንን ለመፍጨት ደማችንን ለማፍሰስ የተነሱትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያፍዝዝልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


በመልአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን🙏
ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም። ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም። ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ። ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃለህን አሰማኝ።🙏
መልክአ ገብርኤል
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

10 Feb, 19:30


ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ! ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኝልን ነሽ፤ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

07 Dec, 16:04


የቀደሙት ኣባቶቻችን ጥቁር ውሻ ይግዛህ ብለው ይረግሙ ነበረ ፡፡
እርግማኑ እውን እንዳይሆን እንጸልይ🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

30 Nov, 05:33


እንኳን ለፅዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

30 Nov, 05:33


ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም። ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም።
ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ። ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃለህን አሰማኝ።
መልክአ ገብርኤል

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

25 Nov, 05:31


እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡
የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡
(መልክአ ኪዳነ ምህረት)
ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን🙏

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

24 Nov, 15:59


ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

21 Nov, 11:37


ሚካኤል ሆይ መብረቅን ለተጎናጸፈ መልአካዊ ረቂቅ ርእስህ ሰላም እላለሁ። ተፈጥሯቸው ከእሳት የሆነ የሰማያውያን የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው የምትሆን ሚካኤል ሆይ በኃጢአት ተሰነካክዬ ወድቄ እንዳልፍገመገም አንተን ድጋፍ አድርጌአለሁና። ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።
ሚካኤል ሆይ የችግረኛውን ሁሉ ጸሎት ፈጥነው ለሚሰሙ አዕዛኖችህ ሰላምታ ይገባል። የይቅርታ መልአክ ሆይ ችግሬን አቃልልኝ ጭንቀቴን አስወግድልኝ ምክርን ትለግሰኝ ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እንዳደረኩህ አንተም ልጅ አድርገኝ።🙏
መልክአ ቅዱስ ሚካኤል
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

20 Nov, 19:08


፤ አቤቱ፥ አንተ ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።
፤ ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
፤ አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
፤ ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወድዱ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይጐስቍሉም።
፤ እሰይ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።
፤ አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር። እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ።
፤ እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል፤ አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 40ቁ11.17)