ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አባለት:
የህግ ባለሙያ (ጠበቃ ) ቴዎድሮስ ባዩ እርቅይሁን የፌደራል ጠበቆች ማህበር አባል ሲሆኑ ከታህሳስ ወር/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባጋጠማቸው ስትሮክ (የነርቭ ችግር ) የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በኮሪያ ሆስፒታል እያገኙ ቢቆይም በግራ ጭንቅላቱ ክፍል ደም መፍሰስ እና የመንቀጥቀጥ ህመም የተነሳ የበሽታው ሁኔታ ከበድ እያለ በመምጣቱ ወደ ሌላ የነርቭ ህክምና ማዕከል ገብተው እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በየጊዜዉ የሚጠየቁት የህክምና ወጪ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ከነ ማስረጃ አያይዘው ካቀረቧቸው ሰነዶች መገንዘብ ተችሏል ።
በመሆኑም ጠበቃዉን ለማገዝ የምትፈልጉ እና የምትችሉ የማህበሩ አባላት በስልክ ቁጥር 0973883341 (ባለቤቱ ) ወይም 0911716643 ደዉላችሁ ማግኘት የምትችሉ ስሆን እንዲሁም በባንክ አካዉንታቸዉ ገቢ ለማድረግ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000206886866 ላይ ድጋፍ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
የማህበሩ ጽ/ቤት
ጥር 5/2017 ዓ.ም
አ/አበባ