Ethiopian Law™ ⚖ የኢትዮጵያ ሕግ™ @ethiopianlaw_s Channel on Telegram

Ethiopian Law™ ⚖ የኢትዮጵያ ሕግ™

@ethiopianlaw_s


Join us / ይቀላቀሉን👇
#የኢትዮጵያ_ህጎች_እንዲሁም_አዋጆች
#የሕግ_መማሪያ_መፅሀፍት
#የሕግ_ማብራሪያዎች
#በpoll_መልክ_የሚለቀቁ_የመውጫ_ፈተናወች_በብዛት_ይቀርቡበታል
#የታዋቂ_መምህራን_ትምህርቶችን_ያገኛሉ🤝
ለጥያቄ @Ethiopian_law_s_bot
For legal materials @Ethiopianlawlegalmaterialsbot

Ethiopian Law ⚖ የኢትዮጵያ ሕግ (English)

Are you interested in learning more about Ethiopian law and legal practices? Look no further than the 'Ethiopian Law ⚖ የኢትዮጵያ ሕግ' Telegram channel! This channel, with the username @ethiopianlaw_s, is dedicated to providing valuable insights, updates, and discussions on various legal topics relevant to Ethiopia. Whether you are a legal professional, student, or simply someone interested in understanding the legal system in Ethiopia, this channel is the perfect resource for you. Join us to access a wealth of knowledge on Ethiopian laws, legal principles, and case studies. Engage in meaningful conversations with fellow members and stay informed about the latest legal developments in the country. Don't miss out on the opportunity to expand your understanding of Ethiopian law and connect with like-minded individuals. To join the channel, simply click on the link provided and start exploring the world of Ethiopian law today! #የኢትዮጵያ_ህጎች_እንዲሁም_አዋጆች #የሕግ_መማሪያ_መፅሀፍት #የሕግ_ማብራሪያዎች #በpoll_መልክ_የሚለቀቁ_የመውጫ_ፈተናወች_በብዛት_ይቀርቡበታል #የታዋቂ_መምህራን_ትምህርቶችን_ያገኛሉ🤝 For personalized legal materials, don't forget to check out @Ethiopian_law_s_bot. Stay informed, stay engaged, and stay empowered with Ethiopian law!

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

10 Nov, 17:58


በሌላ ሰው ገንዘብ በራስ ስም ቤት ስለመግዛት
--------------------
ከሳሽ ተከሳሽ በኃይል የያዘብኝን ቤትና ቦታ ለቆ እንዲወጣ ይወሰንልኝ የሚል ክስ ሲያቀርብ ሊለቅልኝ ይገባል የሚልበት ምክንያት በተከሳሽ ስም ቢገዛም የከሳሽ ነዉ በሚል ከገለጸ ከሳሽ ከቤቱ ጋር በተያያዘ መብትና ጥቅም ያለዉ መሆኑን በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ የቀረበ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። ተከሳሽ ከሳሽ ምንም ዓይነት የባለሀብትነትም ሆነ የባለይዞታነት መብት ባይኖራቸዉ ያቀረበዉ ክስ ነዉ በሚል ያሚያቀርበዉ መቃወሚያ ከሳሽ በእርግጥ በቤቱ ላይ መብት ያለዉ መሆን ያለመሆኑ በክርክር ሂደት ተጣርቶ እልባት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ ከሚባል በስተቀር ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለዉም ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ባለመሆኑ ከመነሻዉም በመጀመሪያ መቃወሚያነት ሊቀርብ የሚገባዉ አይደለም።
ሰ/መ/ቁ 216702 ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓም የተወሰነ
source:- Minda Girma Law Office

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

10 Nov, 16:07


ለብድር ውል ዋስትና ይሆን ዘንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣነት ሲሰጥ: የመያዣ ውሉ ከተፃፈበት ቀን አንስቶ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት አድራሻ ባለው በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ካልተፃፈ በቀር ምንም አይነት ውጤት የማያስገኝ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3052, 3053, በመጥቀስ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 33295 ቅጽ (7) ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ስለሆነም ይህን የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል ለመገልገል ብሎም በሕግ ፊት ውጤት እንዲኖረው ተጠቃሚው በሚመለከተው የመሬት አስተዳደር አካል ውሉን ማስመዝገብ ይጠበቅበታል::
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

10 Nov, 06:56


የቀጠለ👇👆
ይህ ብቻ ሳይሆን የአንዳንድ ሁነቶች መፈጠር ኑዛዜ ፈራሽ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይኸውም፡-
የልጅ መወለድ
ኑዛዜ ያደረገ ሰው ከኑዛዜው በኋላ ሌላ ልጅ ቢወልድ እና ልጁ ውርስ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነ ተቃራኒ ቃል ቢኖር እንኳን ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡ ሆኖም ተናዛዡ ልጅ መወለዱን ቢያውቅም ኖሮ ስጦታውን አያስቀርም ተብሎ የሚገመት ከሆነ ዳኞች በኑዛዜ የተሰጡት ስጦታዎች በከፊል ወይም በሙሉ እንዲፀኑ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም ልጁ የሚያገኘው ግን በማናቸውም ምክንያት እጅግ ቢያንስ ከሀብቱ ሶስት ሩብ ማነስ የለበትም የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 904&905፡፡
ሶስት ሩብ ማለት ምን ማለት ነው?
ከኑዛዜ በኋላ የተወለደ ልጅ የሚያገኘውን የውርስ ድርሻ በተመለከተ የፍትሐብሔር ህጉ በአማርኛ ቅጂው ግልፅነት ይጎድለዋል፡፡ አማርኛው ከውርሱ ሀብት ሶስት ሩብ በሚል ሲያስቀምጥ እንግሊዝኛው “three fourths of the share which he would receive in the intestate succession” ማለትም ውርሱ ያለኑዛዜ ቢሆን ያገኝ ከነበረው ሶስት አራተኛ ማነስ እንደሌለበት ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ ሶስት አራተኛ ከጠቅላላ ውርሱ መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡
➢ የጋብቻ መፍረስ የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 906
ለባል ወይም ለሚስት ጥቅም ተብሎ በኑዛዜ ተካቶ ከሆነ ጋብቻው በሞት ሳይሆን በሌላ ምክንያት ከፈረሰ ኑዛዜው ውድቅ ይሆናል፡፡👇ምሳሌ
አቶ አባተ እና ወ/ሮ ይመኙሻል ለ10 አመታት በጋብቻ ኖረዋል፡፡ በተጋቡ በ8ኛ አመት አቶ አባተ ኑዛዜ ሲያደርጉ ከጋራ ንብረታቸው ላይ ከእርሳቸው ድርሻ ግማሹ ለባለቤታቸው እንዲሆን ይናዘዛሉ፡፡ ሆኖም በ10ኛ አመት አቶ አባተ እና ወ/ሮ ይመኙሻል በመሀላቸው በተፈጠረ አለመግባባት በፍቺ ይለያያሉ፡፡ የተለያዩት በፍቺ በመሆኑ ለወ/ሮ ይመኙሻል የተደረገው የኑዛዜ ስጦታ ውድቅ ሆኗል ማለት ነው፡
Join us👇
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

09 Nov, 11:10


የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነታቸው ምን ያህል ነው? ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው ?

አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ።

1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም።

2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው።

3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው።

4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች ሟሟላት።

◼️ የመንደር ውል ሕጋዊ ነው ?

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ።

◾️ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው ?

አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ።

ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው።

እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው።

◼️ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው ?

በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል።

◼️በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው ?

በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት።

ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው ?

እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም :: የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ ሰጥቷል።

በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቍ 21448)

በሌላ በኩል ደግሞ የመንደር ውል በውል አዋዋይ ፊት እስካልተመዘገበ ድረስ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቁ 83674)

ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈራረሙ ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል::

🟢 ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ?

አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም።

ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል።

በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል።

በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር ከሰረ ማለት አይደል?

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረጉ የሽያጭ ውሎች በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን  በአዋዋይ ወይም ፍርድ ቤት ፊት መከናወን ይገባቸዋል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ; የማረጋገጥ መስፈርት ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዲኖረው ብቻ መከናወን ያለበት ሳይሆን ውሉ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት እንዲኖረውም ጭምር መከናወን ያለበት ነው፡፡
#tebekasamuel 
#ጠበቃ_ሳሙኤል_ግርማ

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

09 Nov, 07:14


ኑዛዜ ፈራሽ ወይም ውድቅ የሚሆንባቸው ምክንያቶች

ኑዛዜ ህግን ተከትሎ ባለመደረጉ ወይም በሌሎች ምክንቶች ፈራሽ ሊሆን ይችላል፡፡ ለአብነት፡-አንድ
ኑዛዜ ተጠቃሚውንና ጉዳዩን ካላመላከተ ወይም አፈፃፀሙን የማይቻል ከሆነ ፈራሽ ነው (የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 865)፡፡ለምሳሌ፡👇
አቶ ጫላ አምስት ልጆች አሏቸው፡፡ አድሜአቸው እየገፋ በመምጣቱም እሳቸው ካለፉ በኋላ በውርስ የተነሳ ግጭት እንዳይፈጠር በማሰብ ኑዛዜ አዘጋጁ ፡፡ ነገር ግን በኑዛዜአቸው ላይ እያንዳንዳቸው 20% ይውሰዱ ከማለታቸው ውጪ የኑዛዜተጠቃሚዎቹን አልገልፁም፡፡ ይህን መሰል ኑዛዜ ፈራሽ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች በአንድ ፅሁፍ ላይ ቢናዘዙ ፈራሽ ይሆናል የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 858
የኑዛዜው ቃል ለህግ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ከሆነ ፈራሽ ይሆናል የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 866
👉ምሳሌ
ወ/ሮ አለምነሽ ልጃቸው አቤል የሸክላ ሥራ የተሰማራ መሆኑ ደስተኛ አላደረጋቸውም፡፡ በዚህም ባደረጉት ኑዛዜ ወንድማቸው አቶ ብርሀኑ ልጃቸው ይህን ሥራ እንዳይሰራ የሚያደርገው ከሆነ ብር 300,000 እንዲሰጠው ቢናዘዙ ይህ ኑዛዜ ልጃቸው በፈለገው የሥራ ዘርፍ የመሰማራት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ ፈራሽ ይሆናል ማለት ነው፡፡
አንድ ሰው ኑዛዜ ያደረገው በሀይል ከሆነ ወይም ተገዶ ከሆነ ፈራሽ ይሆናል የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 867
👉 ምሳሌ
ወ/ሮ ብርሀን ስድስት ልጆች አሏቸው፡፡ ሁሉም ልጆቻቸው በውጪ ሀገር የሚኖሩ ሲሆኑ እሳቸው ከሀገር መውጣት ስለማይፈልጉ በአዲስ አበባ ከተማ ይኖራሉ፡፡ በእርጅና እና በጤና ችግር ምክንያት የሰው እርዳታ እያስፈለጋቸው ሲመጣ የእህታቸው ልጅ ወደ ሆነች ሄልን ጋር ሄደው መኖር ይጀምራሉ፡፡
ይህን እንደጥሩ አጋጣሚ የወሰደችው ሄለን ኑዛዜ አድርገው የውርስ ተጠቃሚ እንዲያደርጓት በተዳጋጋሚ እንደምትገላቸው ታስፈራራቸዋለች፡፡ በዚህም ምክንያት ኑዛዜ አድረገው የኑዛዜ ተጠቃሚ አደረጓት፡፡በዚህ የሀይል ድርጊት የተደረገ ኑዛዜ ፈራሽ ነው፡፡
ይቀጥላል .....
Join us 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

07 Nov, 19:03


ክፍት የስራ መደብ ለህግ ተመራቂዎች
ሸር ላይክ በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ
https://t.me/Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

07 Nov, 16:32


Bahir Dar university school of law students are participating on The All Africa International Humanitarian Law Competition by representing Bahir dar university and our country, Ethiopia. Surprisingly they passed to the semi final.
Wish you the best!
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


International humanitarian law ppt
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


የፌደራል የቤተሰብ ህግ ይዘት እና አተገባበሩ.pdf
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Criminal code Hateta ze Mikniat
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Principles of Ethiopian criminal law
By_ Elias N. Stebk
JOIN US FOR MORE BOOKS
Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

06 Nov, 18:17


Join 👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s

Ethiopian Law የኢትዮጵያ ሕግ

05 Nov, 11:13


Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s