[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል አርባ ዘጠኝ ]
🕊
[ ስለ አጽንዖ በአት ጥቅም ተናገረ ! ]
🕊
❝ በአንድ ወቅት አንድ እኁ ሊያየው እንደ መጣና ፦ “አባቴ ሆይ ፣ ሕሊናቶቼ 'ሕሙማንን ጠይቅ ፣ እነርሱን እርዳ' ይሉኛል ፣ ይህ ታላቅና ደገኛ ትእዛዛ ነው ተብሏልና” ብሎ እንደ ነገረው ስለ አባ መቃርዮስ ተነገረ፡፡
አባ መቃርዮስም ትንቢታዊ የሆነ ነገርን እንዲህ ሲል ተናገረው ፦ “ ታምሜ ጠይቃችሁኛል ያለው ሐሰት የሌለበት የባለቤቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው፡፡ የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ ከራሱ ጋር አንድ ባሕርይ አድርጎታልና ፡ ከኃጢአት በስተቀር የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጓልና ፣ ነገር ግን እኔ የምልህ ፣ ልጄ ሆይ ፣ ሕሙማንን ከመጠየቅ ይልቅ ለአንተ የሚሻልህ በበአትህ መቀመጥ ነው ፤ ወደ ኋላ ላይ በበአታቸው ጸንተው በሚገኙት ላይ የሚያሾፉበትና የሚቀልዱበት ዘመን ይመጣልና።
ያኔም አባ እንጦንስ እንዲህ ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት ይፈጸማል ፦ እብድ ያልሆነ ሰው ካዩ በእርሱ ላይ ይነሡበትና "እንተ እብድ ነህ” ይሉታል ፣ ምክንያቱም እንደ እነርሱ ስላልሆነና በአኗኗሩ እነርሱን ስላልመሰለ ነው፡፡ እናም የእኔ ልጅ ሙሴ ወደ ጨለማው ባይገባ ኖሮ በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፈባቸውን የቃል ኪዳኑን ጽላት ባልተቀበለ ነበር እልሃለሁ፡፡ ❞
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
† † †
💖 🕊 💖