ናዝራዊ Tube @nazrawi_tube Channel on Telegram

ናዝራዊ Tube

@nazrawi_tube


ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On Utube sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN

Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

ናዝራዊ Tube (Amharic)

ናዝራዊ Tube የቲምፕላተው ናዝራዊ እንደተመለሰ የአገር እና ራስን በመስዋዕት የተለየ እና ለእግዚአብሔር የተለየ መረጃ። ከዚህ በኋላ ይህ ቲምፕላተ ከመሬት እና የሰውም በግልጽ የተመለሱ መረጃዎችንና እንዴት እንደሚጠቅምም የተነሳ መረጃዎችን አስተካክሏል። የናዝራዊ Tube ቲምፕላተ በኢትዮጵያ ያላቸውን ሀብት በመስራት መረጃ እንደሆነ ድብቅ እና አለብን ማድረግ ያስፈልገዋል። በእያንዳንዱ እና በእያሳረንና በእያንዳንዱ መረጃዎች ከሀብት ውስጥ ስብስብ ላይ ያጋጃቸዋል። አንዱን ከሌሎች መልእክተኞች እንዲለወጥ ድብቅ ማስመለስ ይችላል። ናዝራዊ Tube ቲምፕላተ በኢትዮጵያ አሰራር ላይ በእጅጎ ቢስ ሊሞሩ እና ከወደቁት ጋር የሚያርጉት መረጃዎች አስማማኝ ነው። ናዝራዊ Tube ቲምፕላተ ከበኣሜሪካ ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ጋር የምንኖረውን መረጃዎችን ለመፅሀፍ ይችላል።

ናዝራዊ Tube

11 Jan, 18:34


.              ጥያቄ
በአስቆሮቶ ይሁዳ ቦታ የተተካው ደቀመዝሙር ማትያስ ነው?
እውነት✔️ ወይስ ሀሰት✖️

ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ገራሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።

ናዝራዊ Tube

07 Jan, 14:32


ልዩ የገና በዓል መልዕክት በወንድም በረከት በየነ
https://youtube.com/watch?v=8W-Gsbm2TtI&si=9Ye2oz8CclaUVMPh

ናዝራዊ Tube

05 Jan, 16:05


ደረሰ🤩🤩🤩ደረሰ🤩🤩🤩ደረሰ🤩🤩🤩

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶች የልደት መታሰቢያ በዓል (ገና ) ደረሰ🥳

በዓሉን ድምቅ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀን እንገኛለን🎁

የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉን በዓሉ አብረን ድምቅ ብለን እናሳልፋለን🎅🏾
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ናዝራዊ Tube

04 Jan, 19:24


.        የመዝሙር ጥያቄ
    💿ይህ መዝሙር የማነው?💿
                       👇
🎶የምትራራልኝ የምትወደኝ🎶
🎶ከማንም ይልቅ የምትቀርበኝ🎶
🎶ምትጠብቀኝ ጠዋት ማታ🎶
🎶ጠላቴን በድብቅ የምትመታ🎶
🎶ምትበቀልልኝ ደም መላሼ🎶
🎶ስምህ ብሩክ ይሁን ወንድም ጋሼ🎶

ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ጠቃሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።

ናዝራዊ Tube

31 Dec, 17:21


ደረሰ🤩🤩🤩ደረሰ🤩🤩🤩ደረሰ🤩🤩🤩

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶች የልደት መታሰቢያ በዓል (ገና ) ደረሰ🥳

በዓሉን ድምቅ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀን እንገኛለን🎁

የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉን በዓሉ አብረን ድምቅ ብለን እናሳልፋለን🎅🏾
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ናዝራዊ Tube

30 Dec, 06:52


በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር መጽሐፍ ሙሉ ዳሰሳ #bereket #beyene
https://youtube.com/watch?v=kiTsp7Rd5Ec&si=fSOJRVwFf_mlDjWN

ናዝራዊ Tube

23 Dec, 19:09


ክፍል #2 |የሕይወት ዘመን ምህረትና ቸርነት | የመጽሐፉ የመጨረሻ ክፍል| #bereket #beyene
https://youtube.com/watch?v=NYNUP7Jy5jg&si=Lgu-bz_ICQ_S0SMW

ናዝራዊ Tube

16 Dec, 18:48


በኔ ይሁንባችሁ ይኼን ቪዲዮ ብታዩ ትልቅ ትምህርት ታገኛላችሁ

ናዝራዊ Tube

16 Dec, 17:46


📱▶️⬇️
https://youtu.be/z7eRZUrhOhg?si=arlSuuo6MrGfBSGq

ናዝራዊ Tube

08 Dec, 15:44


https://youtu.be/iMNpMJpTYG0?si=6m9PHsiGlWwbcHjs

ናዝራዊ Tube

24 Nov, 17:22


ትባረኩበታላችሁ ገብታችሁ አድምጡ

ናዝራዊ Tube

24 Nov, 08:18


ገበታና ቅባት | ምዕራፍ 5 | በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር መጽሐፍ #bereket #beyene #amharic...
https://youtube.com/watch?v=OxIc8TAFNG0&si=faCdkQLKQHgbX8T9

ናዝራዊ Tube

21 Nov, 18:08


የዛሬው እንድትባረኩበት የመረጥኩት የዩቱብ ቪዲዮ 🖥
👇
https://youtube.com/watch?v=7YkoGuIqjHM&si=bpVVAIA1iQQD_RFD

ናዝራዊ Tube

14 Nov, 17:23


https://youtu.be/dHaNLVY2nuU?si=87Hv6H4k9laglKYS

ናዝራዊ Tube

14 Nov, 17:23


https://youtu.be/_CHKVUzXdOs?si=o1_WeRIlBTsacpSd

ናዝራዊ Tube

11 Nov, 15:59


በቅርቡ ወደ ጌታ የኼደው የሰሎሞን ጥላሁን ረዥም ጊዜ ወዳጅ የኾነው ምኒሊክ አስፋው ሰሎሞንን እንዲህ ዘክሮታል፦ 👇
https://hintset.org/articles/sew-yemikebrebetn-aymertm/

ናዝራዊ Tube

11 Nov, 00:01


https://youtu.be/3CyrH9V132M?si=9s6xfB5swv8psHoC

ናዝራዊ Tube

09 Nov, 19:28


የክርስቶስ መስቀል የእግዚአብሔርን ወስን የለሽ ፍቅር የሚያሳይ ዘመን የማይሽረው የቤተ ክርስቲያን ዐርማ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ሞት በአንድ ጊዜ ካህናን የመስዋዕት በግ በመሆን ከኀጢአት ርግማን ዋጀን። በጨለማ የሰይጣን አገዛዝ ሥር የኾነችው ዓለም ለምታሰማው የተስፋ ጩኸት መልሱ ይኸው የመስቀሉ ፍቅር ብቻ ነው።

በየትኛውም መልኩና መለኪያ “ጥሩና የተሻለ የሚባለው ማኅበራዊ ለውጥ፣ ሰውን ምሉእ አያደርግም። ሕግ “ነጩና ጥቁርኑ” (በአገራችን ዐውድ ደግሞ ‘ብሔሮችን) በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ያስቀምጥ ይሆናል፤ ኾኖም አንዱን በሌላው ልብ ውስጥ አያስቀምጥም! እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ክርስቶስን በብቸኛና የመጨረሻ መፍትሔነት ለዓለም የሰጠው፣ የክፋት ኹሉ ቋት የኾነውን የሰው ልጅ ልብ እንዲያው በጸጋው አዲስ ለማድረግ ነው። የሰውን ልብ መቀየር የሚችለው ወንጌል ብቻ ነው። ስብከታችንም ይኸው መጥምቁ ዮሐንስ ያመለከተው "የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ" ብቻ ይኹንልን።

አሜን!

The cross is the focal point of Christ’s mission—it is the irreducible mark of the Christian faith. The world is crying out for hope and lasting peace, yet the root cause of everything that has gone wrong in the world is sin. As Scripture says, “For all have sinned and fall short of the glory of God.”

No amount of "humanization" or even the most perfected "democracy" can transform the evil and deceitful human heart. These systems, no matter how well-intentioned, are always short of the “ideal.” ONLY the selfless love of Christ, demonstrated on the cross, can change the human heart.

Though the world may ignore, push aside, or even disparage the reality of sin and the transforming message of the cross, God’s final and ultimate solution to the human heart remains His Son’s death on the cross. This is the heart of the gospel. Just like John the Baptist did, the church is called to point to Jesus—the Lamb of God—to a world enslaved by sin and under the power of Satan. We are called to boldly and unashamedly proclaim that humanity's only hope is found in the crucified and risen Christ.

May we declare none other than the crucified and risen Christ.

Amen!
Dr. Girma Bekele
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

07 Nov, 16:55


ቤታችን ፈራሽ ድንኳን ነው!

" ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና" ( 2 ቆሮ 5:1)።

ጳውሎስ በዚህ ክፍል ጊዜያዊውን እና ደካማውን የሥጋዊ አካላችንን ተፈጥሮ ከሚጠብቀን ዘላለማዊና አስተማማኝ ሰማያዊ ሕልውና ጋር በማነፃጸር ተናግሯል።

“ ምድራዊ ማደሪያችን” አሁን ያለውን ሟች ሥጋችንን የሚያመለክት ነው፣ እሱም “ድንኳን” ተብሎ ተገልጿል። ይህ ዘይቤያዊ አገላለጽ የአካላዊ ህልውናችንን ጊዜያዊነት እና ጥራት የሌለው መሆኑን የሚያጎላ ነው:: ይህም የሀብታም ይሁንየድሃ : የምሁርም ይሁን የጨዋ : ወይም የሊቅ ይሁን የደቂቅ ሰውነት ቋሚ መዋቅሮች የሌሉት እንደ ድንኳን የሆነ በቀላሉ ሊፈርስ የሚችል መሆኑን ያሳያል።

በክርስቶስ ላመኑት ግን “በእግዚአብሔር የተሠራው አዲሱ ሕንጻ” ፣ ዘላለማዊ የሆነውን አካል ወይም በሰማይ የምናገኜውን ሕይወት ይወክላል፣ ይህም ከምድር ሰውነታችን ደካማነት ጋር ይቃረናል። ይህ የህንፃ "ግንባታ" ከዚህ ህይወት በኃላ በቋሚነት የምንወርሰውን ዘላለማዊ ህይወት የሚያጎላ ምሳሌ ሲሆን :ይህም ዘላለማዊ “ቤት” “በእጅ ያልተሠራ” ነው::በባህሪውም በመለኮት የተፈጠረ እንጂ እንደ ምድራዊ ነገሮች የሚይፈርስ ወይም የሚጠፋ ቤት አይደለም።

አውዳዊ ትርጉም

ጳውሎስ እየተናገረ ባለበት አውድ ውስጥ የሚያጎላው ሃሳብ አሁን ባለው ሕይወታችን የሚያጋጥመንን መከራ እና ምዋቲነት ነው። በ2ኛ ቆሮንቶስ 4-5 ሰፊ አውድ ውስጥ፣ ጳውሎስ እኛ ክርስቲያኖች ልንታገሰው ስለሚገባ ፈተና እና መከራ በበቂ ተናግሯል፣ በተጨማሪም የዘላለም ሕይወት ተስፋ እና የወደፊቱን ትንሣኤ አበክሮ አሳይቷ።

ሓዋርያው በእነዚህ ሁለት ምእራፎች የሚነግረን ዋና ነገር ምድራዊ አካላችን ሊበሰብስ እና ሲጠፋ ፣ በአንፃሩ ደግሞ ከመከራ፣ ከሞት እና ከመበስበስ ነጻ የሆነ ዘላለማዊ እና የተከበረ አካል ማረጋገጫ እንዳለን ነው። ይህ የወደፊት ተስፋችን በምድራዊ ፈተናዎች ለመጽናት የመጽናናት እና የማበረታቻ ምንጭ ነው።

በክፍሉ "በድንኳን" እና "በህንፃ" መካከል ያለው ንጽጽር በርካታ ቁልፍ ጭብጦችን ለማጉላት አገልግሏል ፡-

1.አካላችን እንደ ድንኳን ጊዜያዊ እቃ ሲሆን በሰማይ ያለው በእጅ ያልተሠራ ግን የዘላለም ቤት : ቋሚና አስተማማኝ ነው።

2. ድንኳን በቀላሉ የሚሰበር እና የሚጠፍ ሲሆን፣ ነገር ግን “ሕንፃው ጠንካራ እና ዘላቂ የሆነ ነገር ነው።

የንፅፅሩ እውነታ የሚያጠናክረው በምድራዊ ህላዌ፣ በማይለወጥ ሁኔታ እና በሰማያዊ ህላዌ መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠናክር ሲሆን ይህም አስተማማኝ እና ዘላለማዊ መሆኑን ያሳያል።

ጳውሎስ ይህንን ዘይቤ ሲጠቀም እኛ ክርስቲያኖች ትኩረታችንን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ እንድናደርግ ለማበረታታት ነው:: አሁን ያለንበት የሚያስቃትት የህይወት ትግል ምንም ያህል ከባድም ቢሆንም ነገር ግን የጊዜ መከራ ተብሏል ፣ በፊታችን ግን በትንሳኤ የማይጠፋ እጅግ የላቀ ነገር ይጠብቀናል።

አሜን !
ነብዩ ኢሳይያስ
☑️ @nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

06 Nov, 12:21


"በሞት ጥላ መካከል" በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር መጽሐፍ |ክፍል 4| #bereket #beyene #prot...
https://youtube.com/watch?v=b3j0xyTSvGM&si=nUCjxidsm4O9-0e-

ናዝራዊ Tube

04 Nov, 14:56


💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
በመዝሙሮቹ የተባረካቹበት እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

ናዝራዊ Tube

04 Nov, 05:33


"በሞት ጥላ መካከል" በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር መጽሐፍ |ክፍል 4| #bereket #beyene #prot...
https://youtube.com/watch?v=b3j0xyTSvGM&si=nUCjxidsm4O9-0e-

ናዝራዊ Tube

02 Nov, 18:15


👆 ይህችን መልዕክት ያያችኋት አልመሰለኝም... እስቲ ድጋፋችሁን አሳዩና አበረታቱን 😊

ናዝራዊ Tube

02 Nov, 18:09


“ራሷን ያለስስት በመሥዋዕትነት የሰጠቸ የቪተንበርግ የማለዳ ኮከብ”
በዶክተር ግርማ በቀለ

ስለተሐድሶ ዝክር ስናስብ፣ ዋጋ በመክፈል፣ በስደትና መከራ ለባሎቻቸው የብርታትና የጸጋ ዐቅም የሆኑ ታላላቅ ሴቶችንና ልጆቻቸውን ልናስብ፤ ስለ እነርሱም እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባል። የወንጌል አገልጋዮች፣ ቀን ሲጨለምባቸው፣ ብቻቸውን ሲሆኑ፣ መሄጃ ሲጠፋባቸው፣ እንደ ተወሳሰብ የሸማኔ ማግ ሕይወት ውሏ ሲጠፋባቸውና እንደ ኤርምያስ፤ "ችግርና ሐዘንን ለማየት፣ ዘመኔንም በውርደት ለመፈጸም፣ ለምን ከማሕፀን ወጣሁ?" በማለት በአገልግሎትም በሕይወትም ሲመረሩ (ኤር. 20፥18)፣ ሚስቶቻቸው ጽኑ፣ የማይለወጥ የሕይወት አጋርና ክፉውን ጊዜ የማለፈያ ጸጋ ናቸው።

መሉውን ለማንበብ 👇

https://telegra.ph/የሉተር-ባለቤት-ካታሪና-ቮን-ቦራ-ታሪክ-11-02

ናዝራዊ Tube

01 Nov, 15:57


🎺ናዝራዊ ትዩብ ተመልሷል!😊

☑️ከዚህ በኋላ በቻናላችን፦
📝እናንተን ያስተምራሉ የምንላቸው ሀሳቦች አድነን እናመጣለን።

🎧ልክ እንደ በፊቱ የሚባርኩ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮችን እናቀርባለን።

ℹ️ ወቅታዊ በሆነ ቤተክርስቲያን በተመለከተ የምትማሩባቸውን ሀሳቦች እናንሸራሽራለን።

🖥 በዩቱብ ላይ ድንገት ወደ እናንተ ያልመጡ እንደሆነ ስብከቶች፣ ዶክመንተሪዎችና ሌሎች ያስተምራሉ ብለን የምናስባቸውን ቪዲዮ ሊንኮች እንለቃለን።

በዚህ ሀሳብ ላይ ያለችሁን ስሜት በreaction (👍👏) ከታች ከገለጻችሁልን ሌሎችንም እንጨምራለን...

💬እስቲ ሀሳብም ካለ አጋሩን... በተጨማሪም የምንለቃቸውን መልዕክቶች ሼር አድርጉ ተባረኩ።

ናዝራዊ Tube

01 Nov, 15:01


የያዕቆብ ኹለት ምዕራፎች

የዐዲስ ኪዳን ጸሓፍት በእምነትም ኾነ በተፈጥሮ ምክንያት የሚመጣን መከራ አስመልክቶ በቂ የኾነ ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖ አስፍረውልናል። በተለይ በቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው መከራ ምክንያት ወደ ተለያዩ የሮም ግዛቶች ተበትነው አሁንም ከመከራ ዳፋ ሊያመልጡ ላልቻሉት አይሁድ አማኞች መጋቢያዊ መልእክቱን የጻፈው ጻድቁ ያዕቆብ (James the Just)፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባቸው እንደ ሙሉ ደስታ እንዲቈጥሩት ሲያሳስብ እንመለከታለን። እንዲህ እንዲያስቡ የሚለምናቸውም፣ የሚደርስባቸው ፈተና ምሉእና ፍጹም እንዲሆኑ ወይም ክርስቶስን ወደ መምሰል እንዲያድጉ ስለሚረዳቸው መሆኑን ጨምሮ ያስረዳል።

እንዲህ የሚለው የያዕቆብ መልእክት ከሌሎች ሐዋርያት ትምህርት ጋራ ስምሙ ነው። ጳውሎስም ይሁን ጴጥሮስ ስለዚሁ ጕዳይ ሲጽፉ፣ የመከራ የመጨረሻ ዓላማ የክርስቶስን መልክ መጐናጸፍ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ቅዱሳን እንዲታገሡና ደስ እንዲሰኙ ያሳስባሉ። ያዕቆብ ግን ከዚህ በተጨማሪ አንድ የሚያነሣው ጕዳይ አለ፤ በምዕራፍ አንድ ውስጥ መከራን እንዲታገሡ ካሳሰበ በኋላ፣ በምዕራፍ ዐምስት ውስጥ ግን፣ በአማኞቹ ላይ የግፍ ጽዋ ለሚያፈሱ ባለ ጠጎች የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ተቃረበ ያመላክታል።

ያዕቆብ እንደ ብሉይ ነቢያት፣ በአማኞች ላይ የሚደርሰው የመከራ ሒሳብ በእግዚአብሔር ሳይወራረድ እንደማይቀር ይናገራል። በርግጥ ቅዱሳን እምነታቸው እየተሠራበት ይሆናል፤ እግዚአብሔርም እየተጠቀመበት ይሆናል፤ መከራ አድራሺዎቹ ላይ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ መገለጡ አይቀሬ ነው። ይህን የያዕቆብን ሐሳብ ሳነብ፣ ቤተ ክርስቲያን አንድም በአማኞች ላይ ስለሚደርሰው መከራ ጤነኛ የኾነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ለምዕመኗ መስጠት እንዳለባት የመልእክቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ  ሲያመላክተኝ፣ ዐምስተኛው ምዕራፍ ደግሞ፣ መከራ አድራሺዎቹ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚገለጥ ነቢያዊ ድምፅ ማሰማት እንዳለባት እረዳለሁ።

የሚያሳዝነው እውነታ ግን፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ኹለቱም አለመሆናቸው ነው። ቤተ ክርስቲያን በምድራችን ላይ እንደ አሸን ስለ ፈላው መከራ ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖ በመስጠት የምዕመናንን እምነት ከመፈራረስ ስትጠብቅ አትታይም፤ ያለ አግባብ በሕዝቡ ላይ የመከራን ውሃ የሚግቱት አካላት ላይም እግዚአብሔር ፍርዱን እንደሚገልጥ ነቢያዊ ድምፅዋን አታሰማም፤ መጋቢያዊም ኾነ ነቢያዊ ሚናዋ የሳሳ ይመስላል። ያዕቆብ መጋቢያዊውንም ነቢያዊውንም ሚና ምሳሌያዊ በኾነ መንገድ አስቀምጦልናል፤ ፈለጉን እየተከተልን ያለን ምን ያኽሎቻችን እንሆን?

fanuel brhane
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

01 Nov, 06:37


#ተሓድሶ
#አጭር_ታሪክ
የ16ኛው ክፍለ ዘመን ተሓድሶ አነሳስ ምን ይመስል እንደነበረ ታሪክን ለሚወዱ እንሆ!

💙"አይታችሁ ከወደዳችሁት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቪዲዮዎችን በየጊዜው አስፍተን ለመስራት የምንበረታታ ይሆናል!" ብለዋል የቪዲዮው አዘጋጆች

🖥 https://m.youtube.com/watch?v=MnCo5NUt1No

ናዝራዊ Tube

31 Oct, 17:52


🎉Happy Reformation Day!

Today, we celebrate the courage and conviction of those who sought to bring the church back to the truths of God’s Word. May we continue to be reformed by the Scriptures, standing firm in faith, and spreading the good news of

1. Sola Scriptura - Scripture Alone
2. Sola Fide - Faith Alone
3. Sola Gratia - Grace Alone
4. Solus Christus - Christ Alone
5. Soli Deo Gloria - To the Glory of God Alone

May these truths guide us, inspire us, and bring us closer to Christ as we reflect on His grace and love.

©ChristianBookSh
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

30 Oct, 17:49


ትንሽ ስለ ሰሌ:

"ትንሽ ስለ ሰሌ" ልበለው እንጂ ስለ እኔም ነው፤ ምክንያቱም ሰሌ በእኔ የሕይወት መንገድ ውስጥ ብዙ ነው፡ አሻራው አይለቅም፡፡

አንዳንድ ሰዎች በሕይወታችን ልክ እንደ milestone ከኋላ የመጣነውን ርቀት ከፊት ደግሞ ምን ያህል ርቀት እንደሚቀረን ጠቋሚዎች ናቸው፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሰለሞን ነው፡ ስለትጋቱ፣ ለእግዚአብሔር ስለነበረው ቅናትና፣ ቤተሰቡን እንደ አይኑ ብሌን ስለማየቱ ለሁሉም የተገለጠ ስለሆነ ምንም ማለት አያስፈልገኝም፡ ነገር ግን በእኔ ሕይወት ዘወትር እያሰብኳቸው እንድኖር የምገደዳቸውን ነገሮች ጥሎብኝ አልፎአል፡ በመሰረቱ ሰለሞን በሕይወታቸው አሻራውን የጣለባቸው ሌሎች ብዙዎች እንደሚኖሩ ጥርጣሬ የለኝም።

ከሰሌ ጋር የተዋወቅነው የሃያሦስት አመት ልጅ ሆኜ በምሥራቅ መሰረተ ክርስቶስ የ ሀ መዘምራን ቡድን ውስጥ ሳለሁ ነበር፡ ወዲያው ነበር ንግግሩ ረገጥ ያለና ቃላቶቹ ጠጠር ያሉ መሆናቸውን ያስተዋልኩት፡ ሰሌ በጣም ትጉህና ከልቡ የተሰጠ ሰው ከመሆኑ የተነሳ ወዲያው ነበር የመዘምራን ቡድናችን መሪ የሆነው፡ መሪ ብቻ ሳይሆን እንደ አባትም ነበር፡ ካረፈድን በር ላይ ቆሞ ገና ከሩቅ ሲያየን በየስማችን እየጠራን “አትሮጡም እንዴ" እያለ ነበር የሚያስገባን፡፡

በደንብ ስንግባባና ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን መነጋገር የጀመርን ጊዜ ነበር ነገረ-መለኮት ትምህርት ቤት እንድገባ ያበረታታኝና ETCን የተቀላቀልሁት፡ ETC ገብቼ እንኳን ከአስተማሪዎቼ በላይ ይከታተለኝ የነበረው እርሱ ነበር፡፡

አንድ ቀን ወደ መዝሙር ጥናት ሲመጣ እስካሁን የማስታውሳት ውብ ቡናማ ሳምሶናይት ይዞ መጣ፡ እኔም ከቀረቤታዬ የተነሳ እንደማያደርገው እያወቅሁኝ “ሰሌ እስቲ ይህችን ሳምሶናይት ስጠኝ” ብዬ ጠየቅሁት፡ ከሳምሶናይቷ በላይ የማልረሳውን መልስ ነበር የመለሰልኝ፣ እንዲህ ሲል፤

“እኔ ካሁን ካሁን ብትቀደድብኝ ምን እሆናለሁ ብዬ እየተጨነቅሁ ነው አንተ ስጠኝ ትለኛለህ?”

ለዓንድ ነገር መጨነቅ ያለብኝ ሳይቀደድ በፊት መሆኑን አስተምሮኝ አልፎአል።

አጥቢያ ቤተክርስቲያኔ ለሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ስትጠራኝ በዋነኛነት እንዲያናግረኝ የተመደበው ሰሌ ነበር - በዚያ ወቅት የአጥቢያችን ሽማግሌ ነበር፡ በተቀጠርኩበት ቀን ቢሮ ስገባ ቤተክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዳገለግል እንደምትፈልግ ሲነግረኝ አይኑ በእንባ ተሞልቶ ነበር፡ ምክንያቱ ይገባኛል፡ ብዙ አብረን ስላሳለፍንና ከነበረን ቅርርቦሽ የተነሳ ልብ ለልብ ስለምንተዋወቅ ቤተክርስቲያን በዚያ እድሜዬ ለዚህ ትልቅ አገልግሎት ስትጠራኝ ከነበረው ደስታ የመነጨ ነበር።

በግምት የሃያ አምስት አመት ወጣት በሆንኩበት ጊዜ በአጥቢያችን የተዘጋጀውን የፋሲካ አዳር አድረን ጠዋት ወደቤታችን ስንበተን እኔና እርሱ ከገርጂ መገናኛ ድረስ በእግራችን እየተጫወትን እናዘግም ነበር፡ ሐሳቡ እንዴት እንደመጣልኝ ባላውቀውም “ሰሌ እስቲ ምከረኝ” ብዬ ከልቤ ጠየቅሁት፡ ሰሌ ሲጫወትም ይጫወታል ሲመክርም ከልቡ ነበር የሚመክረው፡ ከገርጂ እስከ መገናኛ ድረስ ነበር የሚንቆረቆር ምኩሩን ያጠጣኝ፡ በተለይ እርሱ ካለፈበት የሕይወት መንገድ በመነሳት የለገሰኝ ምክሮች ወርቆች ነበሩ፡ ከመከረኝ ምክር ሁሉ የማልረሳት ግን “ይልዬ የትኛውም ነገር ቸኩለህ ከሚበላሽብህ ዘግይተህ ቢቀርብህ ይሻላል” የምትለዋ ናት።

የመዘምራን ቡድናችንን እንደ ተቀላቀለ ነበር ለሚጠይቀው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ሁሉ መልስ እሰጠው የነበረው፡ ምንም ያንሳ ምን ብቻ እኔ ጋር መልስ አይጠፋም ነበር፡ ብልህ ስለነበር አንድ ቀን እሁድ ማለዳ ሻይ ጠጥተን ለአምልኮ እየገባን ልክ ከግቢው በር ስንደርስ እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ፤

“ይልዬ አዳምና ሔዋን ግን መንግስተ ሰማይ ይገባሉ እንዴ?”

የዛን ቀን ጌታ ረድቶኝ ነው መሰል አድርጌ በማላውቀው መልኩ “ኧረ እኔ አላውቅም” አልኩት፡ እርሱም መለስ አድርጎ በሚራራ ዓይን በእንግሊዝኛ አፍ፤

“Now you became matured” አለኝ፡
ሰው አለማወቁን ሲያውቅ አንድ የመብሰል ምልክት ነው እንደማለቱ ነበር።

ሰሌ የትኛውንም ነገር “እንካ ሥራ” ተብሎ ቢሰጠው ከእርሱ በኋላ ሌላ ሰው የተሻለ አድርጎ እንዳይሰራው አድርጎ ነበር የሚሰራው፡ በነበርንበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለገንዘቡ ለጉልበቱና ለጊዜው ሳይሳሳ የሚለፋ ወንድም ነበር፡፡

በአጥቢያአችን፣ ምናልባት ካልተሳሳትኩ ደግሞ በፕሮቴስታንቱ ማህበረሰብ ዘንድ ሰርግ ማለት ጋብቻ ማለት እንጂ ድግስ ማለት እንዳልሆነ ያሳየን ሰለሞን ይመስለኛል፡ ሰርጉ እሁድ ሲሆን የተደረገው ከበዛ የወሰደው አሥራ ስምንት ደቂቃ ብቻ ያህል ነበር፡ ይኼ የሚያሳየው ሰሌ ምን ያህል ትራፊ ለሆነው ነገር ሳይሆን እንቡጥ ወይም አንኳር ለሆነው ነገር ግድ የሚለው ሰው መሆኑን ነው።

ሰሌ የትኛውም አውድ ውስጥ ገብቶ ለመቀላቀል የማይቸግረው ሰው ነበር፡ አጥቢያችን ውስጥ ከሊቅ እስከደቂቅ ሁሉ የሚወደውና ሁሉንም ደግሞ የሚወድ ውድ ሰው ነበር፡ እጅግ ብዙ የምለው ነገር ነበረኝ ነገር ግን ከላይ እንደጠቆምኩት ስለ ሰሌ ሳይሆን ስለ እኔ እንዳይመስልብኝ ብቻ ትቼዋለሁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ሰዎች ገና ብዙ የሚሮጡት ሩጫና የሚዋጉት ውጊያ እያለ ለምን ከእጃችን ላይ አፈትልከው እንደሚያመልጡን አይገባኝም፡ ሁላችንም ብንሆን በሰው አቆጣጠር ሰሌ ያለጊዜው እንደሄደ ነው የምናስበው፣ ነገር ግን ከጊዜ ውጭ ሆኖ ጊዜን የፈጠረና ጊዜን የሚቆጣጠረው ጌታ ለምን ይህን እንዳደረገ እርሱ ብቻ ነው የሚያውቀው።

ከአምስት ቀን በፊት በዓልጋ ላይ እያለ ከአንድ ወንድም ጋር አይተነው ነበር፡ በአይኔ ያየሁትን ለማየት ቢከብደኝም ሰሌ በቀኝ እጁ በእርሱ ትክክል እንድንቆም ስለፈለገ ወደ ግድግዳው እያሳየን "እዛ ጋር ቁሙልኝ" አለ፡ ከዛም እንዲህ አለ፤

"አሁን እዚህ የምታዩት ሰው የደከመ፣ ቆዳው የተሸበሸበ፣ ሽበት የወረሰው ሰው ነው"

እውነት ለመናገር ግን ያለው ሁሉ ትክክል ቢሆንም የመንፈሱን ጥንካሬ ለመግለጽ ግን ቃላት ያንሰኛል፡ ምንም እንኳን ስለሥጋው ድካም ቢናገርም ከቆሮንጦስና ከሮሜ ደብዳቤዎች እየጠቀሰ ስለ ትንሣኤ ይናገር የነበረው እውነት ግን ውስጡ ምን ያህል እንደ ካሌብ ጠንካራ እንደነበር ነው የሚያሳየው: ምንም እንኳን ውጫዊው ሰውነቱ ቢደክምም የውስጥ ሰውነቱ ግን ብርቱ ነበር፡፡

የእዚያኑ ቀን ነበር አንድ እህት ሰሌ ምን እንዳለ ለሌሎች ሰዎች ስትናገር አጠገባቸው ስለነበርሁ ጆሮዬ ጥልቅ ብሎ የገባው፡

"ወገኖች ቀድሜአችሁ ወደክብር ልገባ ነው"

አለ ብላ ስትነግራቸው ሰማሁና፣ ለራሴ እንዴት ያለ መታደል ነው አልኩኝ።

በዚህም ይሁን በዚያ ሁላችንም ሰሌ የሄደውን መንገድ ከመሄድ አንቀርም፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ለሰሌ አታልቅስ፣ ካለቀስህ ለራስህ አልቅስ፡ ሰሌ መልካሙን ገድል ተጋድሎ ሩጫውን ጨርሶ ሄዷል፡ በሥጋ ስለተለየን ብናዝንም እንደ እውነቱ ግን እድለኛ ነው።

እኔና አንተ አሁን ያልሞትነው በኋላ ስለምንሞት መሆኑን አትርሳ።

ብንሞትም በሕይወት ብንኖርም ስለ ሁሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

30 Oct, 16:52


የዛሬው ተሸላሚ!!!
አገልግሎቱ ሕይወቱ፣ ሕይወቱም አገልግሎቱ የነበረው፣ የሰሜን አሜሪካው ሕብረታችን አምበልና የኢዮቤልዩው ፊት መሪ እንዲሁም የተዋጣለት አስተባባሪ፣ የነገረ መለኮት ሊቅ፤ የሰላምና ዕርቅ ምሩቅ፣ ምርጥ ጸሐፊና የአዲስ ቃላት ነዳፊ ዛሬ ወደናፈቀው ጌታ ሄደ። "መንግሥተ ሰማይ እውን ነው" ማለትን የሚያዘወትረውና "ዝግጁ ነኝ!" ሲለን የሰነበተው የትውልዳችን ትልቁ ሰው መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን ለሽልማቱ ተጠራ። አላመነታም፤ ብድግ ብሎ ሄደ። ነፍስህ በሰላም ዐርፋለችና ሶል አሁን ከሕመም ነፃ ነህ፣ እኛን ግን በብርቱ ታጎድለናለህ። ለነገሩ ጉዳታችን የጀመረው "ከከበራ ወደ ሥራ!" ብለኸን ሳትጨርስ የታመምክ ቀን ነው።

አለማየሁ ማሞ
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

30 Oct, 16:45


መልካም እረፍ ይሁንልህ ጋሽ ሶል...

እንደ አንተ አይነት ሰዎች ቢቆዩልን መልካም ነበር... ብቻ እግዚአብሔር ልክ ነው በሚያደርገው ሁሉ።

መጽናናትን ለወዳጅ ዘመዶቹ እንመኛለን...

@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

28 Oct, 19:03


አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? (ዘዳግም 10 : 12 - 13 )

1) አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትፈራው
2) በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ
3) እንድትወድደው
4) በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እንድታገለግለው
5) መልካም እንዲሆንልህ፣ ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞችና ሥርዐቶች እንድትጠብቅ

ስለዚህ . . . (ዘዳግም 10 : 16-22 )

1) የልባችሁን ሸለፈት ግረዙት
2) ከእንግዲህም ወዲያ ዐንገተ ደንዳና አትሁኑ
3) ወላጅ ለሌላቸውና ለመበለቶች ፍትሕ አድርጉ፤ ለመጻተኛውም ፍቅር አሳዩ

ለምን? (ዘዳግም 10 : 17-19 )

1) አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ስለሆነ
2) የጌቶች ጌታ፣ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ ስለሆነ
3) አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና
4) እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳልና

ስለዚህ . . .

1) እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና መጻተኛን ውደዱ
2) አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ
3) አምልከውም
4) ከእርሱም ጋር ተጣበቅ - (በማያቋርጥ የመታዘዝ ሕይወት)
5) በስሙም ማል - (በልብ፣ በሥራና በቃል የተገለጠ የኪዳን ሕይወት)

* እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ (ኤሎሂም) ነው። አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ ሰባ ነበሩ፤ አሁን ግን አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንደ ሰማይ ከዋክብት አብዝቶሃል።”
(ዘዳግም 10 : 21- 22 )

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸጋህን ስጠን።🙏🏽

አሜን!
Dr. Girma bekele
☑️ @nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

27 Oct, 16:26


ናዝራዊ Tube pinned «☑️እግዚአብሔር ስለ ስሙ ሲል እግዚአብሔር እንዴት የእስራኤልን ህዝብ እንደታገሰ... 👇ኑ አብረን እንማር https://youtu.be/Jd2FD0R41TA?si=pb0scsirX-TtgPQL»

ናዝራዊ Tube

27 Oct, 16:26


☑️እግዚአብሔር ስለ ስሙ ሲል እግዚአብሔር እንዴት የእስራኤልን ህዝብ እንደታገሰ...
👇ኑ አብረን እንማር

https://youtu.be/Jd2FD0R41TA?si=pb0scsirX-TtgPQL

ናዝራዊ Tube

20 Oct, 13:33


"ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ"
እግዚአብሔር ስለ ስሙ ምን ያህል እንደሚጠነቀቅ በዚህ ቪዲዮ አብረን እንማር።

👇
https://youtu.be/9x_h9mHMzcs?si=-JkiC8Fzh0UrvgW8

ናዝራዊ Tube

16 Oct, 19:59


መልካም ዜና!

ጳውሎስ እና መሲሓዊው ምስጢር የሕትመት ብርሃን አይቶ አንባብያን እጅ የሚገባበትን ቀን እየተጠባበቀ ነው። ፈላጊዎች ለመግዛት ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ እያሳሰብን፣ የምትችሉ ጥቅምት 17፣ ከ 9 ሰዓት ጀምሮ፣ በEGST ተገኝታችሁ እንድታስመርቁ እንጋብዛለን። በዕለቱ፣ ከዚኽ መጽሐፍ በተጨማሪ፣ በአክሊሉ ኩማ የተጻፈው የዮሐንስ ወንጌል ማብራሪያ እና የዶክተር ተካልኝ ዱጉማ የማቴዎስ ወንጌል ማብራሪያ የኦሮምኛ ትርጉም ይመረቃሉ- ለአንባብያን በመልካም ዜና ላይ መልካም ዜና!

መልዕክቱን በማጋራት ያግዙን።
@thefaithofthefathers

ናዝራዊ Tube

13 Oct, 16:55


"የነፍስ መመለስ" ምዕራፍ 3 ክፍል 1 በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር መጽሐፍ #bereket #beyene #pr...
https://youtube.com/watch?v=QnOy1kN00_k&si=W3PtZGSprC_zKy8v

ናዝራዊ Tube

06 Oct, 19:21


ሁላችንም በቃላችን የምናውቀው መዝሙር 23፡2 “በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።” የሚለው ክፍል በዚህ ቪዲዮ ወንድማችን በረከት በየነ እራሱ የጻፈውን መጽሐፍ ተንተርሶ ቆንጆ ማብራሪያ ሰጥቶአል...
በተለይ በዚህ ዘመን ያለን ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲህ ያለ መረዳት ቢኖረን ጥሩ ነው... እስቲ ከታች ያለውን የዩትዩብ ልንክ ተጠቅማችሁ ተከታተሉት... እንደ እኔ በብዙ ታተርፋላችሁ...

https://youtube.com/watch?v=VqAQ00f4U9s&si=lS7VQ43SYqSICTgu


@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

03 Oct, 18:41


በጋሽ ሙላቱ ታዬ ሕልፈተ ሕይወት ልቤ አዝኗል። የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን እንዲሁም የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በመሩበት ወቅት በጥቂቱ ከእርሳቸው ጋር የማገልገል ዕድል ጌታ ሰጥቶኝ ነበር። አስተዋይ፣ ትሑት፣ ልበ ሰፊ፣ የጸሎት ሰውና በብዙ ረገድ ምሳሌነት የነበረው ሕይወት በመኖር በአብያተ ክስቲያናት ዘንድ የተመሰከረላቸው ትልቅ የእግዚአብሔር ሰው ነበሩ። በወጣትነቴ ሕይወታቸው አካሄዴን በብዙ መልኩ ቅርጽ ካስያዙት ፊተኛ መሪዎች መካከል አንደኛው ነበሩ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ አባቶች እያጣን ነው። ጋሽ ሙላቱን ማጣት በብዙ ያጐድላል። በዚህ ዓመት መግቢያ ላይ ለመጐብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር። በሕመም ውስጥም ኾኖው ለቤተ ክርስቲያንና ለእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ይጸልዩ ነበር። ልዑል እግዚአብሔር እንደ እርሳቸው ያሉ ብዙ አባቶች ይስጠን፤ ለእኛም ለክብሩ እንደሚገባ የምንኖርበትን ጸጋ ያብዛልን።

የጋሽ ሙላት ሕይወት ዝክር በልባችን ይኖራል። መልካሙን ገድል ተጋድለው በታማኝነት፣ ባልተቆጠበ ትጋትና በፍቅር ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል። በዚህ እንጽናናለን። ውድ ባለቤታቸው ወንጌላዊት ቀለም፣ ልጆችቻቸውና ወዳጆቼ ሂሩት፣ ዶ/ር ሰምዖን፣ ሰብሊ፣ መቅዲ፣ ሃይሚ፣ መላው ቤተ ሰብና ቤተ ክርስቲያን፣ የመጽናናት ኹሉ አባት የኾነው እግዚአብሔር ያጽናናቸሁ። በርቱ!

"እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፏልና።” (ራእይ 21:4)

አሜን!

Dr. Girma bekele
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

02 Oct, 13:04


“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።”
  — መዝሙር 23፥1

በዚህ ክፍል መሰረት "የሚያሳጣኝም የለም” የሚለውን የዳዊትን አባባል እንዴት ነው የምንተረጉመው

🗣️ዳዊት "የሚያሳጣኝም የለም" ሲል

✔️ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ይሰጠኛል ማለት ነው?

✔️ እግዚአብሔር የምንፈልገውን ሁሉ በጠየቅን ቅጽበት ቢሰጥን ምን ይሆን ነበር?

✔️ ፍላጎት እራሱ ምንድነው ?

✔️ እግዚአብሔር የሚሰጠን የምንፈልገውን ወይስ የሚያስፈልገንን?

✔️ አስፈልህጎት ምንድነው?

እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮችን በዚህ ቪዲዮ ላይ አብረን እንማር
በዩቱብ ገብታችሁ ተመልከቱ 👇
💻 YOUTUBE 🖥

ናዝራዊ Tube

01 Oct, 18:34


ሰውዬው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃውን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው '' የምንወዳቸውን እና የምናከብራቸው ጎረቤቶቻችን አብረውን እንዲበሉ  ሂድና ጥራቸው'።

ልጁም ወደ ጎዳና ወጥቶ እንዲህ ሲል መጮህ ጀመረ እባካችሁ የአባቴ ቤት በእሳት ስለተያያዘ ለማጥፋት እርዱን ድረሱልን !!!
  ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጥቂት ሰዎች መጡ  ሌሎች የእርዳታ ጩኸቱን እንዳልሰሙ ሆነው ቀሩ የመጡት ሁሉ ግን በሉ ጠጡ።
 
ባየው ነገር የተደናገጠው አባት ወደ ልጁ ዞሮ እንዲህ አለ '' የመጡትን ሰዎች እኔ አላውቃቸውም ከዚህ በፊትም አይቻቸው አላውቅም። ስለሆነም  ወዳጆቻችን ቤተሰቦቻችን እና የስራ ባልደረቦቻችን የታሉ?'' ልጁም ከቤታቸው ወጥተው የመጡት ሰዎች ቤታችን ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ጩኸት ሰምተው ሊረዱን እንጂ በቤታችን የተዘጋጀውን ፓርቲ ሊካፈሉ አይደለም። ግብዣችን እና እንግዳ ተቀባይነታችን ሚገባው ለነዚ አይነቶቹ ነው አለ'።

📌ሁሉም የምትወዷቸው እና የምታከብሯቸው ሰዎች እውነተኛ  ወዳጃችሁ ላይሆኑ ይችላሉ።  እውነተኛ ወዳጅ ማለት በተቸገራችሁ እና የእነርሱ ድጋፍ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ከጎናችሁ ሚሆኑ ናቸው።  ወዳጅ ይስጣቹ

✍️Samuel N Tola
📱 @nazrawi_tube 💻

ናዝራዊ Tube

27 Sep, 19:34


ብዙዎች በቃል ደረጃ፣ “መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” ይላሉ፤ እውነታው ግን ሌላ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡት በቤተ እምነታዊ መነጽራቸው ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ዶግማቸው ይሟገታሉ እንጂ ዶግማቸውን በቅዱሳት መጻሕፍት ሊፈትኑ ፈቃደኛ አይደሉም። በዚህ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን ለቤተ እምነታዊ ትውፊታቸው ተገዢ ያደርጋሉ።

ሔኖክ ኢሳይያስ
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

22 Sep, 13:03


"የእግዚአብሔር እረኝነት" ምዕራፍ 1 ክፍል 2 #bereket #beyene
https://youtube.com/watch?v=6XyAQj_86mc&si=b_9OtAPw6fVkWs6D

ናዝራዊ Tube

18 Sep, 05:36


“ጭንቅላታችንን ከሚበጠብጠው የኀጢአታችን ጩኸት ይልቅ ልባችንን የሚያሳርፈው የእግዚአብሔር የይቅርታ ድምፅ ከፍ ብሎ ይሰማል”

ዲ. ኤል. ሙዲ
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

15 Sep, 13:03


ምዕራፍ 1 "በእግዚአብሔር ቤት የመኖር ምሥጢር" #bereket #beyene
https://youtube.com/watch?v=tdqNjfELJxE&si=tvAwxzBv_Cq5lZ7Z

ናዝራዊ Tube

12 Sep, 06:53


እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ።
አዲሱ አመት ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር ይሁንልን!

@nazrawi_tube 🌐

ናዝራዊ Tube

08 Sep, 09:19


https://youtu.be/poR_n-pkiAg?si=fSw8FElQX_CXCVbO

ናዝራዊ Tube

25 Aug, 10:22


https://youtu.be/QVS8FPsYdQM?si=jHboXqWCNnhLt4r3

ናዝራዊ Tube

20 Aug, 15:49


ያልባከነ ዕድሜ፦ የወ/ሮ አመለወርቅ አበበ ግለ ታሪክ
ወንድዬ ዓሊ እንዳዘጋጀው

የወ/ሮ አመለወርቅ አበበ መግቢያ ሐሳብ፦

". . . የዚህች መጽሐፍ ቀዳማይ ዓላማ፦ በቸርነቱ በተለገስኩት ረዥም ዕድሜ ያሳለፍኳቸውን የሕይወት ገጽታዎች ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለሰውም ጥቅም ይሆን ዘንድ ምስክርየቴን ለትውልድ ማስተላለፍ ነው።

ሰዎች ከዚህ ዓለም መለኪያ ተነስተው ስኬታማነቴን ደጋግመው ይነግሩኛል። አዎ! አልተሳሳቱም ይሆናል፤ እኔም ስኬታማ ሕይወት እንዳሳለፍኩ አስባለሁ። ይሁንና የስኬቴ ምንጭ በአምላኬ ሁሉን ቻይነት ላይ መደገፌ መሆኑን ላለውና ለሚመጣው ትውልድ መናገር ነው፤ ሁለተኛው ነጥቤ ነው።

በሦስተኛ ደረጃ፦ በትልቁ ማለም፣ ላለሙትም ሕልም፣ ጨክኖ፣ በነፍስም ተወራርዶ ቢሆን ፅናትን ለትውልዱ በተለይም ለሴት ወገኖቼ ማስተላለፍ ነው። . . ."

©zenebe Gebrehana
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

20 Aug, 07:52


#የሕይወት_ዘመን_ታማኝነት!

ዋጋ ለከፈሉለትና መከራ ለተቀበሉለት እምነት በሕይወት ዘመን ኹሉ በጽናት መቆም እንጂ፣ ስለ እምነት መከራ መቀበልና ዋጋ መክፈል ብቻውን የእምነት አርበኛ አያስቢልም። መጋቢ (ዘማሪ) ተስፋዬ ጋቢሶ ለእምነት ዋጋ የከፈለና በመከራ ያለፈ የእምነት አርበኛ ብቻ ሳይኾን፣ ዋጋ ለከፈለለት እምነት በሕይወት ዘመኑ ኹሉ በጽናት የቆመ አባት ነው።

በድፍረት፣ "የእምነት አባቶች" ብለን በመጥራት ፈለጋቸውን እንዳንከተል በርካታ አባቶችን ዝና፣ ገንዘብ፣ ስምና ክብር አማልሏቸዋል። ለበርካቶች፣ "አባትነት" ማለት በየጥሻው እንደ አሸን ለፈሉ ሐሳውያን ዕውቅና መስጠትና መድረካቸውን ማሞቅ፣ እንጂ ዋጋ የከፈሉለትን የወንጌል እውነት ከማመቻመችና በመደባለቅ መጠበቅ አይደለም።

መጋቢ (ዘማሪ) ተስፋዬ የእምነት፣ የጽናት፣ የታማኝነት፣ የጤናማ ወንጌል ትምህርትና ዝማሬ ተምሳሌት ነው።

መጋቢ (ዘማሪ) ተስፋዬ ጋቢሶ ትሕትናው አስደንጋጭ ነው። ታይታ አይወድም። ውዳሴ ይፈራል። ስሙ ቶሎ ቶሎ ከተነሣ ይጨንቀዋል። አግኝተነው ለታሪክ ማስታሻነት ፎቶ እንነሣ ብንለው በጀ አይልም።

መድረክ አይንቅም። ቦታና አገር አይመርጥም። ጤናማ ወንጌል የሚሰበክበት የትኛውም መድረክ ላይ ጊዜ ካለው ይገኛል። አሜሪካና ጋምቤላ፣ እንግሊዝና አፋር፣ አዲስ አበባና ሐረር ለመጋቢ ተስፋዬ አንድ ናቸው። ለርሱ አገልግሎት መለኪያው የቦታው/አገር ሥልጣኔ፣ የሕንጻ ስፋትና የሕዝብ ብዛት ሳይኾን፣ የመድረኩ ጤናማነት ነው። በርካቶች የተሻለ ስፍራና አገር ብለው ወዳመኑበት ከተማና አገር ፈልሰዋል። ርሱ ግን እስካኹን አዋሳ በታማኝነት ያገለግላል።

ከጥንት እስከ ዛሬ፣ ዘመን ሲለወጥ፣ ጊዜ ሲለወጥ፣ አዘማመር ሲለወጥ፣ አሰባበክ ሲለወጥ፣ የአምልኮ ዘይቤ ሲለወጥ፣ ትሕትናው፣ አገልግሎቱ፣ እምነቱ ያልተለወጠ የእምነት አርበኛና አባት ኾነህ ስለተገኘኽ እናመሰግናለን። ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥልን!!

alex zetse'at
@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

09 Aug, 17:15


ድምፅሽን ከልቅሶ፣ ዐይኖችሽን ከእንባ ከልክይ፤ ድካምሽ ያለ ዋጋ አይቀርምና!

ኤር. 31፥16

ናዝራዊ Tube

31 Jul, 16:49


ወንጌላትን በአንድ ወር አንብቦ ለመጨረስ የሚረዳ በየቀኑ 3ምዕራፍ ያንብቡ🙏

@nazrawi_tube

ናዝራዊ Tube

24 Jul, 09:17


ሕይወት እንደ ጤዛ 😥

ሕይወት ለቅጽበት ታይቶ እንደሚጠፋ ጤዛ ናት። አለሁ ማለት ከንቱ የሚሆንበት አጋጣሚም ብዙ ነው። ይልቁንም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ የጅሞላ ሞት ሲያጋጥም ብዙ ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ በከንቾ ቀበሌ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድንገት የተከሰተ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው ናዳ የሆነውም ይኸው ነው። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የበርካታ ሰው ሕይወት ጠፍቷል። የሟቾች ቁጥር ወደ 229 መድረሱ ተገልጿል፡፡ ያሳዝናል! ከናዳው ጋብታ በኋላ እንኳ ለነፍስ አድን ተግባር በሥፍራው የተሠማሩ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸው ተነግሯል። ይኼም ልብ ይሰብራል። እንግዲህ ምን እንላለን፤ እግዚአብሔር የሟች ቤተሰቦችን እና የአከባቢውን ሕዝብ በማጽናናቱ ይጎብኝ።

©ሽመልስ ይፍሩ
@nazrawi_tube