መልህቅ @zanchor Channel on Telegram

መልህቅ

@zanchor


"ይህም ተስፋ እንደነፍስ መልሕቅ አለን!" ዕብ 6:19

▣ በግል ሊያገኙኝ ከፈለጉ ➾ @agyap101 or @abesus
▣ ግሩፕ➾ @LOVE_Of_WISDOM

ቻነሉና ግሩፑ የሚመሩባቸውን የአዲስኪዳን መርሆች ከቀጣዮቹ ክፍሎች ማግኘት ትችላላችሁ።

Titus 2 : 2, 6 - 8
1 Peter 3: 8 - 12
James 3: 13 - 18

መልህቅ (Amharic)

መልህቅ - እናቴን፣ ህላዊ እና አስትዮይስ መዝገብ ላይ መነሻን አስመልሷል። ይህም ተስፋ እንደነፍስ መልሕቅ አለን! በእጅጉ የሚያሳይ ታሪክ ፋን ፖርኖውማን ዘርፍ መልእክተኞች እንዳበረታቸው ዋና ቪንቷስ ሚድያ እሳት አካሂዳቸው። ከእናቴን ሚድያዎች እንዳልነበሩባችሁ ስሜትን መልእክት ጥሰዉን። እሳት አካሂዳቸው።

መልህቅ

20 Nov, 18:29


sewoch #SHELFEGNAW Live lay new.

Ketef beluna enmar.

https://vm.tiktok.com/ZMhW51sM7/

መልህቅ

17 Nov, 08:58


ከሥላሴ በኋላ 18ኛው እሁድ

የእለቱ የወንጌልና የመልእክት ክፍል

ማቴዎስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።
²² እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
²³ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።
²⁴ እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
²⁵ እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
²⁶ እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
²⁷ እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
²⁸ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።

1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
² እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።
³ ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
⁴ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
⁵ ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?

መልህቅ

16 Nov, 09:54


ስምምነቱ ይዞት የሚመጣው ጣጣ - EO vs OO

የሆነ ጊዜ ላይ ኦርየንታል እና ኢስተርን ኦርቶዶክስ ተስማሙ ማለት ይህ ግዴታ ፕሮማክስ መሆንን የሚያስገድድ ነው ብያቹ ነበር። ምክንያቴን እስኪ በተዋቀረ መልኩ ላስቀምጥ። ቀጣዩን አመክንዮ ተከተሉ!

P1 ➾ ኢስተርን ኦርቶዶክስ ኦርየንታል ኦርቶዶክስን በነገረ-ክርስቶስ ላይ ተሳስታለች በማለት አናቴማታይዝ በማድረግ ከክርስቶስ አካል የተለየች መናፍቅ አድርጋ ትቀበላለች። በዚህም አቋሟ ከ1000 አመታት በላይ ኖራለች ፤ ዛሬም ድረስ አለች።

P2 ➾ ኦርየንታል ኦርቶዶክስ ኢስተርን ኦርቶዶክስን በነገረ-ክርስቶስ ላይ ተሳስታለች በማለት አናቴማታይዝ በማድረግ ከክርስቶስ አካል የተለየች መናፍቅ አድርጋ ትቀበላለች። በዚህም አቋሟ ከ1000 አመታት በላይ ኖራለች ፤ ዛሬም ድረስ አለች።

P3 ➾ ከጥቂት አመታት ጀምሮ በሁለቱ ቤተእምነቶች መሀከል በተደረጉ ውይይቶች አማካኝነት የደረሱበት ስምምነት ልዩነቶቻቸው የቃላትና የአገላለፅ እንጂ የእምነት አቋም ልዩነት (on the Substance of the Faith) እንዳልሆነና በዚሁሉ አመታት ውስጥ ሁለቱም አንድና ተመሳሳይን አቋም ያምኑ እንደነበር ነው።

P4 ➾ ይህ ስምምነት የመጣው በጭራሽ አንድኛው አካል ተሳስቶ የነበረ መሆኑን አምኖ ከዛ ተቃራኒውን አቋም ለመቀበል ፍቃደኛ ሆኖ አይደለም። ይልቁኑ ሁለቱም ጎራ ሙሉ ለሙሉ ትክክለኛነታቸውን አጥብቀው ይዘው ነው ስምምነቱ ላይ የደረሱት።

C1 ➾ ሁለቱም ቤተእምነቶች አንድ አቋምና እምነት የነበራቸው ከሆኑና ልዩነታቸው የአገላለፅና የቃላት ብቻ ከነበሩ ከ1000 አመታት በላይ አንዳቸው አንዳቸውን በከፋ ምንፍቅና እንደተሳሳቱ አድርገው ማየታቸው ስህተት ነበር ማለት ነው።

C2 ➾ ሁለቱም ቤተእምነቶች አንዳቸው አንዳቸውን እንደተሳሳቱ አድርገው ማየታቸው ብቻ ሳይሆን በዚህ ላይ ቆመው አንዳቸው አንዳቸውን አናቴማታይዝ ማድረጋቸው ስህተት ነበር ማለት ነው። አናቴማው የወጣው አንዱ ሌላውን ተሳስቷል ብሎ ስለተቀበለና ስላመነ ብቻ ስለሆነ።

C3 ➾ ስለዚህ እነዚህ ቤተእምነቶች ወደአንድነት ከመጡ ከ1000 አመት በላይ አንዳቸው አንዳቸውን በከፋ ምንፍቅና እንደወደቁና እንደተሳሳቱ አድርገው ማየታቸውና በዛም ላይ ቆመው በቤተእምነት ደረጃ ማውገዛቸው ስህተት እንደነበር ሁለቱም ቤተእምነት መቀበል ግድ ይላቸዋል።

(አስተውሉ! በዚህ ሁሉ ዘመን ውስጥ አንዳቸው አንዳቸውን ሲያወግዙ አንዲቷ ፣ ቅድስት ፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት ቤተ/ክ እያወገዘች እንደሆነ አድርገው ነው ራሳቸውን ይመለከቱ የነበረው።)

C4 ➾ ከ C3 በመነሳት አንዲት ፣ ቅድስት ፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት የሚሏት ቤተ/ክናቸው እንደተሳሳተች ማመን ግድ ይላቸዋል።

እንዲያ ከሆነ ቀጥለን ሌላ ለእኛ ጠቃሚ የሆነ ሙግት ላቅርብ :

P1 ➾ የኦርየንታልም ሆነ የኢስተርን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዲቷ ፣ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ/ክ ልትሳሳት እንደማትችል ያምናሉ ፣ ያስተምራሉ። ከፕሮቴስታንቱም የሚለያቸው መሠረታዊ አስተምህሯቸው ነው።

P2 ➾ ኦርየንታል እና ኢስተርን ኦርቶዶክስ ተስማሙ ማለት ለ1000 አመታት አንዲት ፣ ቅድስት ፣ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ/ክን ናት የሚሏት ቤተ/ክናቸው ተሳስታ እንደነበር መቀበል ግድ ይላቸዋል። (C4)

C1 ➾ ኦርየንታል እና ኢስተርን ኦርቶዶክስ ተስማሙ ማለት ኢስተርንም ሆነ ኦርየንታል ኦርቶዶክስ ግዴታ መሆን አይቻልም።


እንግዲህ ያሉት አማራጮች ካቶሊክ ፣ የአሲሪያ ቤተ/ክ እና ታሪካዊ ፕሮቴስታንት ብቻ ናቸው። ያው ችግሩ ግን ካቶሊኩንም ፕሮውንም.. ሁሉንም አውግዘው ስላሉ ባዶ ሜዳ እንደመቅረት አይደል ?

ብቸኛው መፍትሄ ታሪካዊው ፕሮቴስታንቲዝም ነው የሚሆነው። አለበለዚያ ሽሽታቸው ወደ ሮም ይሆንና በፊሎኩዌ ፣ በፓፓል ኢንፋለቢሊቲ ፣ በኢማኩሌት ኮንሰፕሽን ፣ በትራንሰብስታንሼሽን እና በሌሎችም ጭራሽ በማይቀበሏቸውና በሚያወግዟቸው አስተምህሮዎች ስር ራሳቸውን አስገዝተው ለመኖር ይገደዳሉ ማለት ነው። በአጭሩ ኮስቱ እጅግ ከባድ ነው።

ለዚህም ነው ሁለቱ ቤተእምነቶች ወደአንድነት መጡ ማለት ምንምኳ እኛ በዚህ ደስ ቢለንም ነገር ግን ሊሸሹት የማይችሉት መራር እውነት በጭራሽ ከዚያ ወዲያ ኦርቶዶክሳውያን ሆነው መቀጠል አለመቻላቸው ነው።

@zanchor
@zanchor

መልህቅ

14 Nov, 19:55


👆👆

እየተማርን ሰዎች 😁 ለዘመዶቻችን (ሸልፌክስ ጎረቤት ብሏቸዋል) አድርሱላቸው!

...

መልህቅ

14 Nov, 19:54


ሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚሰሩ ጎረቤቶቻችን መረጃ ለመስጠት ያህል…ያው አብዛኛው የማንበብ ልምድ የለውም የሆነ ጊዜ ከሰማ እሱን እያመነዠገ፣ በየ ሶሻል ሚዲያው እንደ አዋቂ የሰማውን እያስተጋባ ከሚኖር የእውቀት አድማሳቸውን መረጃ በመስጠት ላስፋ ብዬ ነው 😁😁
1 የህጻናት ጥምቀት የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች ሉተራን፣ ፕሬስባይተሪያን፣ አንግሊካን/ኤፒስኮጳል፣ ሜቶዲስት፣ ፒውሪታንስ….
ስለዚህ ሁሌ አንዴ የሰማቹትን ከምታስተጋቡ ከሉተራን ውጪ እነዚህ ቤተ እምነቶች የህጻናት ጥምቀትና በጥምቀት በኩል ጸጋዎች እንደሚተላለፍ እንደሚያምኑ ከዛሬ ጀምሮ እወቁ😀
2 አፖስቶሊክ ሰክሴሽን የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች..።
አንግሊካን/ኤፒስቆጳል፣ የተወሰኑ ሜቶዲስቶችና የተወሰኑ ሉተራኖች።
በፕሮማክሱ አፖስቶሊክ ሰክሴሽን ያላቸው ቤተ እምነቶች የሉም ስትሉ እንዳልሰማችሁ ቀድሜ ነገርኳችሁ😁
3 ካልቪኒዝምን የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች….
ፕሬስባይቴሪያን፣ ኮንቲነንታል ሪፎርምድ፣ አንግሊካን/ኤፒስቆጳል በኮንፌሽን፣ የተወሰኑ ሜቶዲስቶች፣ ፓርቲኩላር ባፕቲስቶች
በየ ሶሻል ሚዲያ ያገኛችኋትን እውቀት ከሪፎርምድ ባፕቲስቶች ውጪ ያሉትን ሌሎችን እንግዳውስ ከዛሬ ጀምራችሁ እወቁ 😁

4 በሴቶች አገልግሎት፣ በነቢያትና በሃዋሪያት፣ በሌሎችም የጸጋ ስጦታ ላይ በኮንፌሽኖቻቸው መሰረት strict የሆኑ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች…..
ኮንፌሽናል ፕሬስባይቴሪያን፣ ኮንፌሽናል ሉተራን፣ ኮንፌሽናል ባፕቲስቶች፣ ኮንፌሽናል ኤፒስቆጳል፣ ኮንፌሽናል ኮንቲነንታል ሪፎርምድ ቤተ እምነቶች
ስለዚህ ከላይ የነገርኳችሁን ቤተ እምነቶች ከፔንቲኮስታል፣ ኢቫንጄሊካል በብዛት፣ ነን ዲኖሚኔሽናል ቤተ እምነቶች ጋር ለያይተህ ውዳሴህንና ነቀፋህን በተነሳው ርእስ ላይ አቅርብ ውዱ ጎረቤታችን 😀
5 ኮንሰርቫቲቭ ሉተራን ነህ ተብሎ አይጠየቅም ይልቁን ኮንፌሽናል ሉተራን ነህ? ነው የሚባለው😁
ማሳሰቢያ፤ ከላይ የጻፍከው እኛን ምን ይመለከተናል? ትለኝ ይሆናል ሎል አይጠቅምህም አንብበህ ማውራት ስለማትችል መንገዱን እያቃለልሁልህ ነው 😁
ደግሞ እቀበተ እምነት ስሰራ በእውቀት ማድረግ እፈልጋለሁ ለምትል አስተዋይ ጎረቤታችን እባክህን ኮንፌሽኖቻችንን አንብብልን😄

ከሉተራንና ከሉተር ያለፈ እውቀት ስለ ፕሮማክሱ እንዳስጨበጥኳችሁ ተስፋ አለኝ 😙

መልህቅ

13 Nov, 10:09


ከላይ ለለቀቅኩት ርዕሰ ጉዳይ ተጨማሪ ማጥሪያ ሀሳቦች

ከላይ ትላንት በለቀቅኩት ክታብ ውስጥ 'ልጁ ስለሚያወራው ነገር አያውቅም' ብዬ ስደመድም 'አልተረዳኸውም' ወይም 'በስህተት ነው የተረዳኸው' ለምትሉኝ በእርግጥም እንተደረዳሁት የሚያስረግጥልን በቪድዮው ውስጥ የተናገራቸውን አራት መሠረታዊ ነገሮችን ናቸው።

#አንደኛ ➾ ሉተር እና ሉተራኑ በ Invisible Church እሳቤ አያምኑም ፤ ከእነርሱም በኋላ ነው የመጣው ማለቱ። #ስህተት!

#ሁለተኛ ➾ የ Invisible Church እሳቤን የተቀበልነው እንደው በሶላ ስክራፕቱራ አማካኝነት የተለያየ አስተምህሮ እዚም እዛም በዝቶብን ሁሉም ቤተ/ክን ነኝ እያለ ሲያስቸግረን ሁሉንም ለማካተት ስንል የፈጠርነው እንደሆነ አድርጎ ስላስቀመጠው። #በጣም_ስህተት!

#ሶስተኛ ➾ ሉተርም ሆነ ሉተራኑ ልክ እንደሱ በ Ecclessiological Exclusivism እንደምታምን አድርጎ ማስቀመጡ (ከላይ በሶስተኛ ነጥብ ላይ የተቀመጠው ማለት ነው) #ይህም_ስህተት

#አራተኛ ➾ የInvisible Church ን እሳቤ ለመቃወምና ስህተት ለማድረግ ብሎ ቤተ/ክ የምትታይ እንደሆነች መሞገቱ #ይሄ_ደግሞ_የባሰበት_ስህተት

አራቱም ነጥቦች ጉዳዩን ፈፆሞ አለማወቁን እጅግ ጮኸው ይናገራሉ። እኔ ከላይ የ Visible እና Invisible Churchን ምንነት ተርጉሜ ከዛም Distiniction ኡም ምን ላይ እንደቆመ ያብራራሁትን ማብራሪያ ተመልክታችሁ እርሱ ደግሞ እንዴት ተረድቶት እንዳስቀመጠው ጎን ለጎን አስቀምጣችሁ ተመልከቱ። ጨርሶ አይገናኙም።

ታድያ ግን አንዲቷ ቅድስት የሐዋርያት ቤተ/ክርስቲያን የቷ ነች ? በአጭሩ መልሱስኪ ? ለምትሉን ..

አንዲቷ ቅድስት የሐዋርያት ቤተ/ክ (in the strictest sense) በእርግጥም የማትታየዋ ቤተ/ክ ነች። ይህች የማትታየዋ ቤተክርስቲያን ግን በሚታዩ ሰዎች ህብረት መሀከል በሚሰበከው ወንጌልና በቅዱሳት ምስጢራት አገልግሎት ምልክትነት በተለያዩ ቦታዎች Instantiate ተደርጋለችና በዚህ በእርግጥም የምትታይ ሆና ትታወቃለች። ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ Marks of the Church ባሉበት ሁሉ እውነተኛዋ ያቺ አንዲቷ የጌታ ቤተ/ክ በዛ እንዳለች እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

የምንቃወመው መሠረታዊ ነገር አንዲትን የምትታይ ህብረት ጠቁመን አንዲቷን ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ/ክን በዛች ህብረት ብቻ አጥረንና ገድበን ማስቀመጥን እና በተጨማሪም በዛች ባለንባት በምትታየዋ ህብረት ብቻ ገድበን ባጠርነው አጥር ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ጠቅልሎ የዳኑ የእግዚአብሄር ህዝቦች አድርጎ ማሰብን ነው።

@zaNchor
@zaNchor

መልህቅ

10 Nov, 09:29


የዕለተ እሁድ የወንጌል እና የመልዕክት ክፍል


ማቴዎስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁴ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
⁴⁵ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤
⁴⁶ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።


1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ ጳውሎስ ወንድሙም ሶስቴንስ፥
² በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤
³ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
⁴ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤
⁵-⁶ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።
⁷ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤
⁸ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።
⁹ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

መልህቅ

10 Nov, 07:10


Recommendation

#የየሹዋ_አፖለጀቲክስ_ሚኒስትሪ ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ-መለኮታዊ ፍልስፍናዊ ፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን የሚያቀርብ ፤ በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን የሚመክት ፤ የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር የሚመረምር ሚንስትሪ ነው።


ትጠቀሙበታላችሁና ቴሌግራሙንም ዩቱዩቡንም ተቀላቀሉት።

➾ @Yeshua_Apologetics_Ministry
➾ https://youtube.com/@yeshuaapologetics?si=10wK_60IZloSe-ZI

...

መልህቅ

04 Nov, 15:31


...

እስኪ እቺን 👆 ቮይስ አድምጧት። ከሰባት ወር ምናምን በፊት ነበር የለቀቅኩት። ከዛ ደግሞ በስፋት ለመረዳት ከታች ያለችውን ሊንክ በመጫን ለማንበብ ሞክሩ።

ከሰሞኑን ጉዳዮች አንፃር ጥሩ ነገር ይሰጣቹሀል። በዚህም መንገድ መሞገት የጀመርነው ዛሬ እንዳልሆነም እንድትረዱ ይረዳቹሀል።

https://t.me/ZANCHOR/955

...

መልህቅ

04 Nov, 15:29


ከቤተ-እምነታችሁ ለተነጠለ እና ሀሳብ ላይ ብቻ ላለ ፕሮቴስታንቲዝም አትቁሙ! እርሱ የለምና!

ከዚህ በፊት በፅሁፍ ባቀርበውም በዚህ መልኩ ደግሞ ማስቀመጡ ለብዙዎቻችሁ ሊጠቅም የሚችል ይሆናል በማለት ነው!

#share
@zanchor
@zanchor

መልህቅ

02 Nov, 12:28


ብዙ ጊዜ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን እነዚህ ክፍሎች ላይ መሠረት በማድረግ ሙግት ሲያዋቅሩ ይሰማል። ሙግታቸውም ክፍሎቹ ላይ ሉተራኑ በቅዱሳት ምስጢራት ላይ  ከእነርሱ የተለየ አቋም ያላቸውን በጠነከሩ አገላለፆችን በመጠቀም የሚያወግዝ ስለሆነ እዛ ላይ መሠረት በማድረግ ከዛም እነዚህን ወደሪፎርምድ ካምፕም ቤተእምነቶች ፕሮጀክት በማድረግ እነርሱንም የሚመለከት በማድረግ በመሀከላችን በዚህ ልኬት ልዩነት እንዳለና አንድነትን ክሌም ልናረግ እንደማንችል ለማስረገጥ ነው።

ከላይ ላለው ሙግታቸው ግን አራት ነጥቦችን መረዳት ከበቂ በላይ መልስ ይሆናል።

1 ➾ እነዚህን የጠነከሩ ንግግሮች ሙሉ ለሙሉ መረዳትም ሆነ መፍታት ያለብን ፀሀፊዎቹ ከፃፉበት ከዛ ታሪካዊ አውድ አንፃር ብቻና ብቻ ነው።

እነዚህ ፅሁፎች የተፃፉት ሪፎርሜሽኑ ከፈነዳ በኋላ ሉተር በዛ ጊዜ ለነበሩ ተቃዋሚዎቹ ነው። በአጭሩ በታሪኩ ውስጥ ሶስት አካላት አሉ። ሮማ ካቶሊክ ፤ ማጄስቴሪያል ሪፎሮመርስ ርና ራዲካል ሪፎርመርስ። እነዚህን ሶስቱን መቀላቀል የለብንም። እንደሚታወቀው በዚህ ጊዜ የሉተርና የእርሱ ፈለግ ተከታይ የሆኑት ሀዳስያን (Magesterial1 Reformers) ተቃዋሚዎች ካቶሊኮች ብቻ ሳይሆኑ በሌላ ጥግ ደግሞ ራዲካል ሪፎርመርስ ጭምር ናቸው። ራዲካል ሪፎርሜሽኑ በጠቅላላው በአናባፕቲስቶች ሊወከል ይችላል። የአናባፕቲስት እንቅስቃሴ Monolitic ሳይሆን በContinental Europe የተነሳና የተለያዩ አቋምና እምነት ያላቸውን አካላት የሚመለከት ነው። እነዚህም በ Ecclesaiological, Eschatological እንዲሁም Political ጉዳዮች ላይ ከሮም ጋር ብቻ ሳይሆን ከMagesterial Reformers ጋር የተጣሉና የተጣበዩ ነበሩ። ከተጠቀሱት ጉዳዮች በዘለለና ባለፈ መልኩ ደግሞ የዚህም ምክንያቱ በአስተምህሮ መለያየታቸው ብቻ ሳይሆን ገና ከጅምሩም እነርሱ ካሰቡት የተሀድሶ እሳቤ ጋር ፍፁም የሚቃረኑና የሚያሰናክሉ ናቸው ብለው ስለሚያስቡ ነበር። ሉተር Anabaptists, Schwenckfeldians, New Arians, and Anti-Trinitarians ብሎ በዝርዝር ያስቀምጣቸዋል።

ስለዚህ የመጀመሪያው ነጥብ እነዚህን ክፍሎች ስንተረጉም ከሞላ ጎደል ያን ሁሉ ውግዘትና ቅዋሜ የደረሰባቸው እነማን ናቸው የሚለውን ባሉበት ታሪካዊ አውዱ ስንመለከት ከላይ የተጠቀሱት ራዲካል ሪፎርመርስ ሆነው እናገኛለኝ። እነርሱን ደግሞ ሉተርና ሉተራኖች ብቻ ሳይሆኑ የሪፎርምድ ካምፕ ቤተእምነት አምድ የሆኑት Mageterial Reformers ራሳቸው ጭምር ናቸው።

ይህ ማለት በሉተራኑ እና በሪፎርምዱ መሀከል ልዩነት የለም ማለት አይደለም። እንዲሁም እንደዚህም አይነት ጠንካራ አገላለፆቾች ለእነርሱም አይጠቀሙምም ማለት አይደለም። ነገር ግን ሁሉን በየአውዱ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ለማስቀመጥ ነው።

2 ➾ የፀሀፊዎቹ ባህሪ ከግምት መግባት አለበት። በተለይ በኮንኮርዱ የካተቱ 98 - 99 % የሚሆኑትን እነዚህን አገላለፆች ከሉተር እንደማግኘታችን ከሉተር ማንነትና አፕሮች አንፃር እነዚህን መመልከት እጅጉን አስፈላጊ ነው። ሉተር እጅግ ፕለሚካል አፕሮች የነበረውና በጊዜው ከሚቃወማቸው ሰዎች አንፃር ከነበረው ከስነመለኮታዊና ፖለቲካዊ ልዩነት የተነሳ Theological Rhetorics አብዝቶ የሚጠቀምና በዚህም ምክንያት ጠንካራ አገላለፆችን ያሉት ሰው ነው። ይህንን እሱ ላይ ከተሰሩ ባዮግራፊዎች መረዳት እንችላለን።

ከዚህ በዘለለ ሌላው ሉተር በስነመለኮቱ አለም ሲስተማቲሺያን እንዳልነበርም መረዳት አለብን። ይህም ማለት ምንምኳ ስነመለኮት ተማረና በዩኒቨርሲቲም የተከበረ አስተማሪ የነበረ ቢሆንም ግን ብዙ ሊቃውንት እንደሚያስቀምጡት በአካዳሚክ ዘርፉ More of Mystical Theology ላይ የሚያዘነብል እንደሆነ ይነገርለታል። ለዛም ነው ከሉተርና በሱ ጊዜ ከነበሩ አንዳንዶች ሰዎች ይልቅ የሉተራኑን አቋም ከሱ የተቀበሉ ወይም ቀጥለው በመጡ ሉተራን ሊቃውንት (እንዲሁም ስኮላስቲክስ) እጅጉን በጠነከረና በተብራራ መልኩ ንፅፅራዊ በመሆነ መንገድ ያስቀመጡት። ለዚህ እንደ Martin Chemitz, Johan Gerhard ... ያሉትን Divines መጥቀስ እንችላለን። ይህ ማለት ምንምኳ ሉተር አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ መሠረትን ቢጥልም ነገር ግን እርሱ በደንብ ቆይቶ ሳያስብባቸውና ሳያጠራቸው ያለፋቸው ጉዳዮች ቀጥለው በመጡ ሊቃውንት በጥልቀት ተሰርቶባቸው እናገኛለን። ከዚህ ከአንፃር እነዚህን አገላለፆች ከነበራቸው ታሪካዊ አውድ አንፃር ከመርጎም በዘለለ እነርሱ ላይ ብቻ ቆመን ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ወደደረሱበት ድምዳሜ መድረስ በጭራሽ አለመቻላችንን መረዳት አለብን። Non-Sequiter Fallacy ይሆንብናል።

ይህም ወደ ቀጣዩ ሶስተኛ ነጥብ ያመራናል።

3 ➾ ከላይ እንዳልኩት ሉተርን የተኩ ሉተራን ሊቃውንት ከሉተርና ከእርሱ ጋር ከነበሩ ሊቃውንት ላይ ቆመው ከእነርሱም ደግሞ ይልቁን በጠለቀና በጠነከረ መልኩ አቋማችንን ያስቀመጡ ናቸው። ከእነዚህም አልፈን ደግሞ የ 17ተኛ ክፍለዘመን ሉተራን ስኮላስቲኮችንም መመልከት ግድ ይለናል። በእነዚህ ሊቃዎንት መሀከል የምመለከተው ነገር ምንምኳ ለአናባፕቲስቱ እንቅስቃሴ ልክ እንደነሉተር አብረው የሚያወግዟቸውና የሚቃወሟቸው ቢሆኑም ነገር ግን በሪፎርምድ ካምፕ ውስጥ ያሉትን ቤተእምነቶች በጭራሽ ከራዲካል ሪፎርመርስ ጋር በአንድ ጫማ ውስጥ አያስቀምጧቸውም። ይልቁኑ ምንምኳ በመሀከላችን ልዩነቶች ቢኖሩም እንዲሁም ደግሞ ልዩነቶቹም ዳውን ፕሌይ መደረግ የሌለባቸውና እጅግም ጠጣር መሆናቸውን አጥብቀው ቢቀበሉም ነገር እነዚህ ልዩነቶች ከእግዜር መንግስት አውጥቶ አልዳኑም የሚያስብሉ አድርገው አይመለከቷቸውም። በአጭሩ የሚያለያዩንን ጉዳዮች Theological Triage ሲሰሩላቸው በጭራሽ 1st Order አያደርጓቸውም። ይልቁኑ ለእነርሱ እጅግ ከባድ Hetrodoxy ናቸው። ስለዚህ እነዛ አገላለፆች ካላቸው ታሪካዊ አውድ አንፃር ብቻ የሚመለከቷቸው ናቸው እንጂ የቤተእምነት አቋም አድርገው የሚያስቀምጧቸው አይደሉም። ይህን መረዳት እጅጉን አስፈላጊ ነው።

ስለዚህ ሶስተኛው ነጥቦ በአጭሩ ኮንኮርዱ ራሱ ሲተረጎም እንደፈለጉ ከየትም እየመጡና ወደፈለጉት እያዞሩ የሚተረጎም ሳይሆን ኮንኮርዱን የእምነት መግለጫቸው አድርገው በተቀበሉና ባብራሩት ማህበረሰብ ውስጥ ባለው አቀባበልና በዛም የትርጓሜ አጥር በኩል ብቻ የሚተረጎም መሆን አለበት። ስለዚህ የኦርቶዶክሱ ወቀሳና የሙግት አካሄድ ይህን ያላማከለ ነውና ተቀባይነት አይኖረውም።

4 ➾ የመጨረሻው ነጥብ በቅዱሳት ምስጢራት ላይ ከተቀመጡት እነዚህ አገላለፆች ውስጥ ቅዱስ ቁርባንን በሚመለከት የተቀመጠው ጭራሹኑ የሪፎርምድን ካምፕ ቤተእምነት አቋም የሚመለከት አለመሆኑ ነው። በአቋም ደረጃ ራሱ ኮንኮርዱ ስህተት ነው ከሚለው አቋም ፍፁም የተለዩ ናቸውና። ይህንንም ከግምት እናስገባ። ይህ ማለት ግን አሁንም በሁለቱ መሀከል ልዩነት የለም ፤ ልዩነታቸውም ተራ ነው ማለት አይደለም። በእርግጥም ጠጣርና የለያያቸው ልዩነት አለ። ነገር ግን ስለዚህ ስፔሲፊክ ክፍል ስናወራ ሪፎርምዶችን አልመለከትም።

በአጭሩ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ልዩነቶችን በማሳየት እኛን ስህተት ለማድረግ የሚሄዱት ሩቅ መንገድ እንደው ልፉ ሲላቸውንጂ እኛ ላይ የጠጠርን ውርወራ ያህልኳ አቅም የሌለው የሾቀ የሙግት አካሄድ ነው። በዚህ በጭራሽ ልባችሁ አይውረድ።

@zanchor
@zanchor

መልህቅ

02 Nov, 12:27


ተመልከቷቸውስኪ 😁

ከዛ ከታች ያለውን ያንብቡ!

መልህቅ

01 Nov, 11:57


እቺን ተጋበዙልኝስኪ! ወሳኝ ውይይት ነች! 😁

https://vm.tiktok.com/ZMhCNQNo6/

መልህቅ

30 Oct, 09:04


ወርሀ ሪፎርሜሽኑ እንዲህ እንዲያ እያለ ተገባዶ ይኸው ሊያልቅ አንድ ቀን ብቻ ቀረው። 😁

በሚያሳዝን ሁኔታ በዚህኛው አመት ምንም አላልኩበትም። ያው ስለሪፎርሜሽኑ ስናነሳ የምናወሳቸው ብዙ ነገሮች አሉ። የተሀድሶው Formal Cause እና Material Cause ተደርገው የሚቆጠሩት ቀንደኞቹ ጉዳዮች ሶላ ስክሪፕቱራ እና ሶላ ፊዴ ቢሆኑም እነርሱ ላይ ቆሞ ለተሀድሶው መከሰት ምክንያት የሆኑ ሌሎች ብዙ ጉዳዮችም አሉ።

ተሀድሶው ወደኋላ የምንመለከተው ብቻም ሳይሆን አሁን ላይም የሚያስፈልገንም ጭምር ነው።

ስለዚህ ምን አሰብኩ መሰላችሁ ነገ Oct 31 ሰብሰብ ብለን ከሁለቱ መሰረታውያን ጀምረን ሌሎቹንም በምንችለው እያነሳን እያወጋን እናከብራለን። አሁን ላይ ካለንበትም ሁኔታ አንፃር እንዴት መቀጠል እንዳለበትም እንመካከራለን።

3 ሰአት እንጀምራለን! በተቻለ አቅም ለመገኘት እና ሌሎችም ስንዲገኙ ሼር ለማድረግ ሞክሩ። ያው ጥያቄዎችንም ለመቀበል ክፍት ስለሆነ ስፔሻሊ ኦርቶዶክስ ወንድሞች በአክብሮት ተጋብዛቹሀል። 😁