Pursuing Holiness @reformedn Channel on Telegram

Pursuing Holiness

@reformedn


You can find old series by searching
The Pilgrims Progress (30 parts)
Reflection on 1st Peter (13 Parts)
Intro to the book of Job (5 Parts)
ኑዛዜ ፩- ፩፪
መፅሀፈ ምሳሌ (12+)
For daily devotions follow posts by https://t.me/WongeluMinistries

Pursuing Holiness (English)

Are you seeking to deepen your spiritual journey and grow in holiness? Look no further than the 'Pursuing Holiness' Telegram channel, with the username @reformedn. This channel offers a treasure trove of old series that will inspire and uplift you on your path towards righteousness. Dive into classics such as 'The Pilgrims Progress' with 30 parts, 'Reflection on 1st Peter' with 13 parts, and 'Intro to the book of Job' with 5 parts. Additionally, you can explore content in Amharic with 'ኑዛዜ ፩- ፩፪' and 'መፅሀፈ ምሳሌ' with 12+ parts. For daily devotions, make sure to follow the posts by Wongelu Ministries at https://t.me/WongeluMinistries. Join us on this journey of pursuing holiness and let the wisdom and teachings shared on this channel guide you towards spiritual growth and fulfillment.

Pursuing Holiness

21 Nov, 03:50


የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር
እንዳይወድቅ አይፈራም
እንዳይጠፋ አይፈራም

How unspeakably wonderful to know that all our concerns are held in hands that bled for us?!
Newton

Pursuing Holiness

20 Nov, 03:04


የማለዳ ረሀብ: Lesson from George Mueller

የሰው ልጅ ተኝቶ ሲነቃ ይርበዋል። አካላዊ ረሀብ ለሁሉም ሰው ሁሌ የሚኖር ባይሆንም ግን ነፍስ ይሄ ነው ማትለው ጠኔ እንዲኖራት አድርጎ እግዚአብሔር ሰርቷቷል። የምንፈልጋቸው ነገሮች ማለቂያ የላቸውም- one after the other we want and want and want and want. ስልክ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ እንቅልፍ፣ ቁርስ ፣ ወሬ..

George Mueller ከአስር ሺህ በላይ ወላጅ ያጡ ህፃናትን የተንከባከበ ጀግና ነው። በሚፅፈው journal ላይ በ 1841 May 7, ያስተዋለው ሀሳብ እጅግ ጠቃሚና በተደጋጋሚ መነበብ ያለበት ነው። በአጭሩ ሀሳቡ ይህ ነው " በየዕለቱ ቀኔን ስጀምር ታላቁና ቅድሚያ የምሰጠው ስራዬ ነፍሴን በእግዚአብሔር ማስደሰት ነው።" መደሰትን እንደ ስራ ለማናይ ሰዎች እንግዳ ሀሳብ ሊሆን ይችላል።

ምናልባትም ቅድሚያ በመስጠት እኖርለታለው የምንለውን ጥሪ ይቃረንብን ይሆናል። እግዚአብሔርን ማገልገል፣ ወንጌል መመስከር፣ የተጨነቁትን ማፅናናት፣ በጨለመው አለም እንደ ብርሀን ልጆች መመላለስና የመሳሰሉት መንፈሳዊ ጥሪዎችና ብዙ በጎነት የሞላባቸው አላማ ብለን የምንኖርላቸው ነገሮች አሉ። But none of these are “the first and the primary thing. Filling up is more important than pouring out. በቅድሚያ ነፍስ በእግዚአብሔር ተደስታ ረሀቧ ጋብ ማለት አለበት።

ረሀብ እንዴት ወደ ፍስሀ ይወስደናል ካልን ደግሞ መብላችንን እራሱ እግዚአብሔር በማድረግ ነው። በዚህ መረዳት ወደእግዚአብሔር የሚመጣ ሰው ከእግዚአብሔር ለመቀበል ተዘጋጅቶ ይቀርባል። ሰው በባህሪው ስራን በማሳካትና በማጠናቀቅ ይረካል። We enjoy achieving even small things. እግዚአብሔር ጋር ስንመጣ ግን ረሀብተኛ ሆነን እርሱን በመቀበልና በማጣጣም እንድንረካ ይፈልጋል።

Mueller “The first thing the child of God has to do morning by morning is to obtain food for his inner man.” ሲል ምግብ የሚሰጠውን ተፈጥሯዊ ጥቅሞች የሚገልፁ ቃላትን ማሰብ አለብን። ጥሩ ምግብ ሀይልና ሙቀት ይሰጣል። It brings nourishment and refreshment. ይሄንን የነፍስ መብል ደግሞ ከቃሉ ነው የምናገኘው።

“What is the food for the inner man? Not prayer, but the word of God. Every verse, to get blessing out of it . . . for the sake of obtaining food for my own soul. Having chewed on one bite and savored it, I go on to the next words or verse, turning all, as I go on, into prayer for myself or others, as the word may lead to it, but still continuously keeping before me that food for my own soul is the object of my meditation. “not the simple reading of the word of God, so that it only passes through our minds, just as water runs through a pipe, but considering what we read, pondering over it, and applying it to our hearts.”

እንደዚህ የተረጋጋ፣ ያልተጣደፈ፣ የተብሰለሰለ የቃል ጥናት በራሱ ወደፀሎት ይመራናል።ፀሎት ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ምላሽ ነው።

“I speak to my Father and to my Friend about the things that he has brought before me in his precious word. Meditation soon leads to a response. Now, having heard our Father’s voice all the way down into our souls, we find ourselves able to really pray and to actually commune with God.

እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል በሰራልን ስራ ምክኒያት የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን we can have a communion woth God.God speaks first in his word, and we receive his words with the hunger, delight, and unhurried pace that fits the word of our Father and divine Friend. Then we speak humbly yet boldly in response, adoring our God, confessing our sins, thanking him for his grace and mercy, and petitioning him for ourselves, our loved ones, and even those who seem like enemies.

ይሄ ህብረት ሰዎችን ለማገልገል የሚደረግ ዝግጅት አይደለም። ምናልባት እግዚአብሔር leftover እንዲኖር ከፈቀደ ካጣጣምነው ውስጥ ለሌሎች እናካፍል ይሆናል ግን ለማካፈል ብለን አይደለም የምንበላው። The point, and prayer, is soul-satisfying communion with Christ.

Mueller testifies that this gave him the help and strength, “to pass in peace through deeper trials, in various ways, than I had ever had before.” When days turn out to be the worst of days in many ways we can say with Mueller “How different when the soul is refreshed and made happy early in the morning!”

(From Desiring God Article)

Pursuing Holiness

19 Nov, 18:23


This world is not my home, I’m just a-passing through,
My treasures are laid up somewhere beyond the blue;
The angels beckon me from heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

O Lord, You know I have no friend like You,
If heaven’s not my home, then, Lord, what will I do?
The angels beckon me from heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

They’re all expecting me, and that’s one thing I know—
My Savior pardoned me, and now I onward go;
I know He’ll take me through though I am weak and poor,
And I can’t feel at home in this world anymore.

I have a loving Savior up in glory-land,
I don’t expect to stop until I with Him stand;
He’s waiting now for me in heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

Just up in glory-land we’ll live eternally,
The saints on every hand are shouting victory,
Their songs of sweetest praise drift back from heaven’s shore,
And I can’t feel at home in this world anymore. 🎶

Pursuing Holiness

16 Nov, 03:54


በየማለዳ
እንደንቁህ ተማሪ በተዘጋጀ ልብ፣ የአለምና የስጋ ጩኸት ባታከተውና አንተን ለመስማት በናፈቀ ጆሮ እንጠብቅህ። በቃልህ ውስጥ የተገለጥከውን አንተን ለማየት የሚጓጉ አይኖችን ስጠን። በፍርፋሪ የማይጠግብ..ግቡ አንተና አንተ ብቻ የሆነ ቁርጠኛ ፈላጊዎች አድርገን። እረፍትንና ሀይል የሚሆነንን ፀጋ ልትሰጠን በክርስቶስ በኩል አንዴ ፈቅደሀልና አቤቱ ስንፍናችንን ገስፀህ አንተን ከአንተ እንድማር ቀልባችንን ወደእግርህ ስር ዘንበል አድርገው።

“ልዑል እግዚአብሔር ...በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።”ኢሳይያስ 50፥4

Gracious Father, since our whole salvation depends on our true understanding of your holy word, grant that our hearts freed from worldly affairs may hear and understand your holy word with diligence and faith so that we may rightly discern your gracious will, cherish it and live by it with all earnestness to your praise and honor. (Martin Bucer)

Pursuing Holiness

12 Nov, 13:34


Jesus Christ and his ways are better than silver and gold, rubies, and all desirable things.

The glory of his Deity,
the excellency of his person, his
all-conquering desirableness,
ineffable love,
wonderful undertaking,
unspeakable condescensions,
effectual mediation,
complete righteousness,
lie in their eyes,
ravish their hearts,
fill their affections,
and possess their souls.

Owen

Pursuing Holiness

11 Nov, 05:51


“እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።”
— መዝሙር 11፥7

Glorious incentive and motivation for holiness.

Pursuing Holiness

08 Nov, 19:34


አንድ አለ። አንድና ብቸኛ የሆነ በዚህ ምድር ላይ ማንንም መበደል የማይችል ቅዱስ አምላክ አለ። የማይስት፣ የማይሳሳት። ፍፁም የሆነ። እንከን የለሽና ነውር አልባ ነው። እርሱ ሀጥያትን ሊያደርግ አይቻለውም። ስለዚህ ይበድለኝ ይሆን ብሎ ስጋት የለም እርሱ ዘንድ። ቅድስናው አስተማማኝ ነውና ያሳርፋል። አለት ነው። ቀላል ያስደግፋችኋል! ነገር ሲዘባረቅባችሁ ራሱ በጭፍን ብትከተሉት በወጀቡ አሳልፎ ማንነቱን ይገልጥላችኋል እንጂ በማዕበል ስትጠፉ ዝም አይልም።

አባት ነው። አባትነት ሁሉ የሚሰየምበት። በምድር ላይ አሉ የሚባሉ ደጋግ አባቶች ጫፉ ጋር የማይደርሱበት ቸር ነው። ቁጣም ቅጣትም ፍቅርም መግቦትም ትዕግስትም ሁሉ የማይነጥፈው ሳትለምኑት የሚያስፈልጋቹን የሚረዳ

የልቡ ስፋትና ለልጆቹ ያለው ፍቅር ተብራርቶ የማያልቅ ደግ ነው። እንጥፍጣፊ ታክል ክፋት የለበትም። የሚበልጠው የለምና ቅንዓትም ሆነ ፉክክር አያጠቃውም። ሰው አይደለምና አይዋሽም። እውነት ነው። ህይወት ነው።

እመኑት ብቻ እንጂ እርሱ ለዘለዓለም ታማኝ ነው። አንድንም ሰው አሳፍሮ ፣ ከድቶ አያውቅም። አሉ የሚባሉ ብረት መዝጊያ ባሎች ከርሱ ጋር ሲነፃፀሩ ይወይባሉ። እርሱ ለወደደው ራሱን ሳይሰስት ይሰጣል። የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ይወዳል። ዘለዓለማዊ ምህረቱ የማይሸፍነው ጉድ የለም።

እንደርሱ ያለ ማንም የለም። ምሳሌ የለውም። እርሱ እርሱ ነው። ከማን ታወዳድሩታላችሁ? ይሄ ሲገባችሁ ብቻ ነው በእንባ "ከአንተ ወደማን እንሄዳለን?" የምትሉት። እግዚአብሔርን ማወቅ ነው ህይወት። እርሱን በማወቅ የሚገኘውን ደስታ የሚተካከል ምንም የለም። ለዚህ የከበረ እድል ብዙ ዋጋ ተከፍሎልናል። ተራ በሆነ ከንቱ ወሬ ጉብዝናችንን አናባክነው።
Focus.
Look at God.
Look at God as He is revealed in His word.

Pursuing Holiness

07 Nov, 05:17


እግዚአብሔር ሆይ

በፍትህ ጉዳይ ያለን ብቸኛ መፅናኛ እንደ ዳኞች ፍርደገምድለት ቢሆን ጥንት በጠፋን ነበር። ነገርግን የክፋትን ሀይል የሚገድብ ሉዓላዊ እጅህና በዘመን ፍፃሜ ሁሉን የሚያስተካክለው ምጡቅ ፍርድህን በመታመን እንፅናናለን። እንጂማ objective ሆኖቹ ህጉን በመተርጎም ፍረዱ የተባሉት ግፍና አመፅ በርክቷል። ሀይ ባይ ያጡ ብዙ የህግ የበላዮች አሉ። አንዳንዶቹ ለገንዘብ በተሸጠ ህሊና ሌሎቹ ደግሞ አንተ ብቻ በምትረዳው የስልጣን ስካር ምክኒያት ንፁሀንን ይበድላሉ። በዳዮችን ነፃነት ይሸልማሉ።

ይሄንን በቅርበት እንደሚመለከት ሰው ቃልህ እንደሚለው ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ እንደተቀጠረለትና በፃዲቁ በአንተ ፊት ሁሉ እንደሚቀርብ ዘወትር አስታውሰን። መርማሪ አይኖችህንና ሁሉን አወቅ ችሎትህን የሚረታ ፍርደገምድል የዛኔ አይኖርም። ስለዚህም ተመስገን። እስከዚያው ድረስ ለእውነት የተቻለውን ዋጋ ሁሉ መክፈል እንድችል አበርታን። ቆራጦች አድርገን። አንተ ሁልጊዜ ከሀቀኞች ጋር ትቆማለህና ተጠያቂነታችን በዋናነት ለአንተ ይሁን።

ጌታዬና ጠበቃዬ ክርስቶስ ፤ በፍርድ ቀን የምትታይልኝ ፅድቄ፣ የአመፄን ዋጋ ከፍለህ አመፃዬን የከደንክልኝ ዋሴ። ብዙ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል። ዘለዓለም አንተነሰ የማወድስበት መዝሙር ይሄ ነው። ታርደሀልና! ዋጅተኸኛልና! I pray that I die before I take this for granted. ይሄን ተዓምር ከመልመድ ጠብቀኝ።

ደግሞም በአንተ ለመዋጀቴ evidence የሚሆን መልካምን ስራ በህይወቴ ይብዛ። ጣቶቼን ለዚህ አሰልጥናቸው። ለፅድቅ ስራዎች ወይንም ለመንፈስ ፍሬዎች የሚያስፈልገኝን ordinary means of grace ወይንም ፀጋህን የምቀበልበት መሳርያዎች ሰጥተኸኛል። ፀሎት፣ የቃል ጥናት፣ የቅዱሳን ህብረት፣ የጌታ እራት ና ሌሎችንም መንገዶች አሳድጄ በመጠቀም በየዕለቱ የምኖረውን ህይወት እንዲቀይረው እማፀንሀለው። በፍርድ ቀን vindicate የምደረግበት፣ አንተን የማስደስትበት ምስክርነቴ ይብዛልኝ።

ጌታ ሆይ: የምንኖርበት አለም ሁሉ በአይኑ መልካም እንደመሰለው የሚኖርበት፣ አንድ አስከፊ ግፍ አይተን ይሄ ነው የክፋት መጨረሻ ስንል ከዚያ በእጥፍ ወደሚብስ ማጥ ውስጥ የሚከት አይነት አዙሪት ነው። እንደእንስሳ በደመነፍስ የሚኖሩ ሰዎች ህይወት በዚህ ምድር ብቻ እንደምታበቃ ሁሉ ክፋትን እንደውሀ ይጨልጣሉ። ዳኞችን በሀይልም ሆነ በገንዘብ መግዛት ስለቻሉ ብቻ ከፍርድ ያመለጡ መስሏቸው በ'ሰላም' ይኖራሉ። ከእነርሱ መሀል ስለነፍሳቸው eternal state የሚያስተውል የለም። ጌታ ሆይ ይሄን ማስተዋል ስጣቸው። የሚጠብቃቸው ፍርድ እንዳለ እንዲገነዘቡ። ሞት የሚባል ለሁሉ የማይቀር ክስተት መሸጋገርያ እንደሆነ የሚነግራቸው የሚሰሙትን ሰው አስነሳ። ፈቃድህ ከሆነ ለክፋት የተጉትን ያክል በአንተ ተዋጅተው የፅድቅ መሳርያዎች አድርጋቸው። አልያም ከክፋታቸው የሚገቱበትን መንገድ አንተ ፍጠር።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ለሁላችንም የሰጠኸንን ሀላፊነት በአግባቡ እንድንወጣ እርዳን። ጌታ ሆይ ነገን ዛሬ ላይ ለማወቅም ሆነ ለመቆጣጠር ከመድከም ሰውረን። የሰጠኸንን የዛሬ ቀን በደስታ፣ በትጋት to its fullest መኖር ይሁንልን። በፍርድ ቀን የምንጠየቀው ስለእቅዳችን ሳይሆን ባለን ጊዜ ስለሰራነው ስራ ነውና ስንፍናችንን ገስፀው። ደስታችን በአንተ ነውና ለከት ያለፈ ሀዘናችንን አንሳልን። የምናደርገውን ነገር ሁሉ including our joy ለአንተ ክብር ማድረግን አስተምረን።

Pursuing Holiness

04 Nov, 03:59


Father, what we know not, teach us; what we have not, give us; what we are not, make us for the sake of your Son our savior. (Old Anglican Prayer)

Pursuing Holiness

02 Nov, 20:22


መክብብ 3:16-22 (Part 6)

የፍትህ መጓደልና የሚጠበቅብን ምላሽ

"ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤ በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤ በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር።"

አለማችን በሚያሳዝን ሁኔታ በክፋትና በተዛባ ፍትህ የተሞላ ነው። ይህን ሀቅ መቀበል በእርግጥ ከባድ ነው። Its unsettling. የተበደለ ሰው መፍትሄ ፍለጋ የሚሄድበት ፍርድቤት የበዳዮች ማጎርያ ሲሆን መሄጃ ማጣት ሰውን ይከበዋል። ለነገሩ ፈራጅ መሆን ለፈላጭ ቆራጭነት ያጋልጣል። የህግ የበላይነት አስከብራለው ብሎ የማለ ሰው ከህግ በላይ ሆኖ በሰው ቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳል። ሀይ ባይ የለም። "የዳኛ ነፃነት" እና "ገለልተኛነት" በተባሉ መርሆች ከተጠያቂነት ያመለጡ ብዙ ወንበዴዎች አሉ።

"እኔም በልቤ “ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣ እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል” ብዬ አሰብሁ።"

ነገርግን ምንም ያህል ሰው ከህግ በላይ ሆኖ ፍትህን እንደፈለገ ቢያጣምም ወደ እውነተኛው ዳኛ ፊት የሚቀርብበት ጊዜ አለ። አስባችሁታል? ማንኛውም ድርጊት! No exceptions. Every deed will be judged. ስለፍርድ ሲነሳ metaphor እንጂ እውነታዊ ትዕይንት የማይመስለን ሰዎች እንኖር ይሆናል። መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ በግልፅ ስለፍርድ ቀን ሲያወራ ግን ለትርጉም ክፍት የሚያደርገው አይመስለኝም። እዚህ ላይ ቆም ብለን ስለእኛ በፍርድ ቀን የሚታይልንን ምትካችንን ኢየሱስ ማመስገን ተገቢ ነው። ያ ብቻ ሳይሆን የእኛን ሞት ሞቶ ፅድቁን እንዳስቆጠረልን ያመንን ሁሉ የእምነታችንን እውነተኛነት የሚመሰክረውን ፍሬ በማፍራት ለፍርድ ቀን የማናፍር ፃድቃን ለመሆንም መትጋት አለብን።

እንዲህም ብዬ አሰብሁ፤ “ሰዎች፣ እንደ እንስሳት መሆናቸውን ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል። የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው። ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ።የሰው መንፈስ ወደ ላይ መውጣቱን፣ የእንስሳ እስትንፋስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር መውረዱን ማን ያውቃል?”

ሞት equalizer ነው። እዚህ ጋር የምናየው የዘገየውን ፍርድ ነው። እንደእንስሳ የሰው ልጅ act የሚያደርግባቸው ቅፅበቶች በርካታ ናቸው። ይሄንን ሁሉ ሰው አያስተውልም። እግዚአብሔር ሰውን በገዛ አይኑ የወደደውን እንዲያደርግ የሚለቀውና ፣ የሚገድብ እጁን የሚከለክልበት ጊዜ አለ። በዚያን ጊዜ ሰው ምን ያህል መዝቀጥ እንደሚችል ይገንዘብ። ያንን የራሱን ወራዳነት በማየትም በዙሪያው ያሉት ሰዎች ለራሳቸው ሲተው ጊዜ ምን ያህል እንደሚወርዱና እንዴት ሊበድሉት እንደሚችሉ ሊያስብ ይገባል። እንደእንስሳ የሚኖሩና ግፍ የሚፈፅሙ ሰዎች አስተሳሰብ 'ወደላይ' ከፍ አይልም። As if all there is to life is earth ነው የሚኖሩት። እዚህ ጋር አኗኗር ወይንም የኑሮ ዘይቤንና ድርጊትን ከሀሳብና እውቀት ነጥለን ማየት እንደሌለብን እንማራለን። ሰባኪው የሚገልጣቸው ሰዎች ከእንስሳ ብልጫ እንደሌላቸው ስለሚኖሩ መንፈሳቸው ወደላይ ትውጣ አትውጣ አያውቁም። የመጨረሻው ሀረግ "Who of them knows/ከእነርሱ መሀከል ማን ያውቃል?" ተብሎ መተርጎም ይችላል። ስለዚህ ሰባኪው የሰውን ዘላለማዊነት እየተጠራጠረ ሳይሆን የእነርሱን ignorance እያሳየን ነው።

ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለ ሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው?

ለዚህ ምላሻችን ሊሆን የሚገባው ምንድነው? ዕጣ ፈንታችንን አለመጣላት። እግዚአብሔር ከሰጠን ሀላፊነት ጋር አለመጋጨት። በደስታ በስራችን መፅናት። ደግሞም ነገሮች ለወደፊት ከዚህ ይሻሻሉ አይሻሻሉ የምናውቀው ነገር ስለሌለ ነብይ ፍለጋ አንድከም። ነገን እስክንደርስበት የሚያሳየን የለም። ይልቅስ የተቸረን ዛሬ ላይ ሆነን የምናደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆን እንበርታ። Live in the moment ተራ ቱሪናፋ አይደለም። የጠቢብ motto ነው። አንዴ ትናንት አንዴ ነገ ላይ መንጦልጦል ትርፉ የአዕምሮ ዝለት ነው። አስተዋይ በህልም ቅዠትና በማይጨበጥ ትዝታ ሳይሆን ዛሬ ላይ በእጁ ባለው ይደሰታል።

Pursuing Holiness

01 Nov, 07:56


አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና.. መዝሙር 75፥1

Pursuing Holiness

01 Nov, 06:17


Why a Shepard put oil on His sheep? Psalm 23

Sheep can get their head caught in briers and die trying to get untangled. There are horrid little flies that like to torment sheep by laying eggs in their nostrils which turn into worms and drive the sheep to beat their head against a rock, sometimes to death. Their ears and eyes are also susceptible to tormenting insects. So the shepherd anoints their whole head with oil. Then there is peace. That oil forms a barrier of protection against the evil that tries to destroy the sheep. Do you have times of mental torment? Do the worrisome thoughts invade your mind over and over? Do you beat your head against a wall trying to stop them? Have you ever asked God to anoint your head with oil? He has an endless supply! His oil protects and makes it possible for you to fix your heart, mind, and eyes on Him today and always! There is peace in the valley!

@Mahi_Yoni

Pursuing Holiness

31 Oct, 05:18


ሀጥያት ማለት መጥፎ/የተከለከለን ነገር መስራት ብቻ አይደለም። ሀጥያት በመሰረቱ ሀይል ወይንም አገዛዝ እንጂ የሆኑ የወንጀል/ vice ክልክል ድርጊቶች ብቻ አይደለም። ማምለክ እንደሚገባን አላመለክንም.. ለእርሱ ሊኖረን የሚገባ መሰጠት የለንም...በእርሱ መደሰት ሲገባን ሀሴትን ፍለጋ ሌላ ሌላ ጋር እንቅበዘበዛለን (አሁንም)....ካሰብንበት መናዘዝ ያለብን የሀጥያት መገለጫዎች መሀል የሚገዝፈው ያደረግነው ስህተት ዘይ ጥፋት ሳይሆን ያላደረግነውና ያልኖርነው ህይወት ይመስለኛል....

Pursuing Holiness

28 Oct, 07:40


ወንድሞች ሆይ፤ በተጠራችሁ ጊዜ ምን እንደ ነበራችሁ እስቲ አስቡ። በሰው መስፈርት ከእናንተ ብዙዎቻችሁ ዐዋቂዎች አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ኀያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከትልቅ ቤተ ሰብ አልተ ወለዳችሁም።

ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔር ብርቱዎችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ። እግዚአብሔር የተከበረውን እንደሌለ ለማድረግ፣ በዚህ ዓለም ዝቅ ያለውንና የተናቀውን ነገር፣ ቦታም ያልተሰጠውን ነገር መረጠ፤ ይኸውም ማንም ሰው በእርሱ ፊት እንዳይመካ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኖአል። እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።
1 ቆሮ 1:26-31

Pursuing Holiness

27 Oct, 04:45


እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ከጊዜ ውጪ ትኖራለህ። ለሁሉ ጊዜ አለው። ከአንተ በቀር። አንተ ዘለዓለማዊ ስለሆንክ ስራህም እንደራስህ የፀና ነው። ጊዜ በአንተ ላይ ተፅዕኖ ስለሌለው ግን እርግፍ አድርገህ አልተውከውም. You pick and choose the best time to do your will. Your timing is perfect. Even when I fail to notice it in the moment.

ምንም ያህል ብጥር የአንተን እቅድ መለወጥ እንደማልችል ገብቶኛል። ትንሽነቴን አሁንም በውሉ በመረዳት እንዳድግ እርዳኝ። ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርገህ የምትሰራውን አንተን እንዳምን እርዳኝ። በኔ ጊዜ ካልሆነ ብዬ ትዕግስት ሳጣ ታግሰኸኛል። አሁንም የአንተን ጊዜ በሚያስረሳ መንገድ ከሰዎች የሚሰበክልኝን "ጊዜው የ....ነው" ልፈፋ እንዳልሰማ አድርገኝ።

በዚህ ጊዜ መሆን የነበረብኝ እያሉ ከንቱ ቁጭት ውስጥ ከመግባት ጠብቀኝ። Helo me to trust and rest in Your timing.

ከሰው ህይወት የማይቀሩ ክስተቶች ሲገጥሙኝ ለምን እንደምበረግግ አላውቅም። ሰው መሆንን በሚገባ ገና embrace አላደረኩትም መሰለኝ። ሞትን አለመድኩትም፣ የደስታና ሀዘን መፈራረቅ ያነጫንጨኛል። የተለየሁትን እስከመጨረሻው መቅደድና መለየት ገና ምን እንደሆነ አልገባኝም። ከስንቱ ትናንት ጋር እንደተሰፋሁ አለሁ። በጦርነት ከመከበቤ የተነሳ የሰላምን ጠዓም ዘንግቼዋለው። ሰው ብቻ'ነቴ እንዳልገባኝ ሁሉ ላልታሰቡ ክስተቶች መዘጋጀት አለመቻሌ እስካሁን ያበሽቀኛል።

ህይወት በእርግጥም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ሆና አየር ላይ ብትቀር አሳሳቢ ነበር። That would actually justify my anxiety. ነገር ግን አንተ አለህ። ሁሉን በስርህ የምታስተዳድር ሉዓላዊው ንጉስ ከዘለዓለም እስከዘላለሙ ብቻህን ጊዜንና በጊዜ ውስጥ የሚያልፉትን ሁሉ ትቆጣጠራለህ። So why do I worry about anything? ያንተን ጥበብና ረቂቅነት እንደሚያውቅ ሰው መንግስትህን እንዳስብ አድርገኝ። ወደ እረፍቴ ውሀ ምራኝ።

You have given me a sense of eternity. That brings its own burden and blessings to my life. በየዕለቱ ያሉትን ጥቃቅን moments ስኖር ዘላለማዊ ህይወቴ ላይ ያላቸውን አንድምታ እንዳገናዝብ አግዘኝ። Routine ከመሰለኝ ተራ ድርጊቶች በስተጀርባ ብዙ እየተሰራ ያለ እውነታ እንዳለ በማሰብ እንዳልሰንፍ ትጋትን ጨምርልኝ።

በምደክምበትና በምኖረው ህይወት ውስጥ ያሉትን ጥቃቅን ደስታዎች እንዳጣጥም ፍቀድ።ደስታ የአንተ ችሮታ ነው። ያለአንተ ፈቃድ ተድላን የቀመሰ የለም። በልፋት ሀሴት ማድረግ የአንተ ስጦታ ነው። በቀኝህ ፍስሀ አለና grant your joy to me. Help me to enjoy the simple things in life.

እንዳከብርህ፣ እንድፈራህ ስለራስህ የሆነ ባህሪይ ስትገልጥ ለገባኝ መረዳት ተገቢውን ምላሽ መስጠትን አስተምረኝ። አንተ አንተን ነህ። አትቀየርም። አትለወጥም። ህይወት እንድትቀጥል ያሰብክበትን ዕቅድ ከኔ ጋር ተማክረህ አታሻሽለውም። የኔ ምላሽ ይልቁንም መሆን ያለበት በገባኸኝ በተገለጥክልኝ ልክ ዝቅ ማለትና የሚገባህን መፈራትና ክብር መስጠት ነው። ዘላለማዊነትህ ደግሞ ትልቅ በረከት ነው። ልትወደስበትም ይገባል። Because it means that all your graces and mercies to me are eternal. ሀሳብህን ቀይረህ አትተዋቸውም። ተመስገን።

You are a righteous judge. ተጠያቂነት ስለሚባለው ፅንሰሀሳብ አንተ ባትኖር አናውቅም ነበር። ማንም ለማንም የማይመልስበት ምድር ውስጥ ስላላኖርከን ተመስገን። ከአንተ ጋር አኩኩሉ ተጫውቶ የማይገኝ የለም። በጊዜው የምትሻውን ሁሉ መልሰህ በማምጣት የሸሸ የመሰለውን ትይዘዋለህ። በዚህ መረዳትም አሳርፈኝ። ፍትህ ምን እንደሆነ ካልገባቸው ዳኞች ፅድቅን በመጠበቅ disappointed ከመሆን አድነኝ።

Pursuing Holiness

23 Oct, 05:19


መክብብ 3: 1-15 ( Part 5)

ጊዜና በጊዜ ላይ የሌለን control

1-8: ለሁሉም ጊዜ አለው

የህይወትን ከንቱነት በምሳሌ ማስረዳቱን ሲቀጥል በቀጥታ ወደጊዜ ትንተና ይገባል።
መቀበል ያለብን 2 ነገሮች: እኛ በጊዜ የተገደብን ነን። እግዚአብሔር ግን አይደለም። እኛ የምንሰራው አስቀድሞ እንዳለው አላፊ ጠፊ ነው። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ግን ፅኑ ነው (3:14) ስለዚህ አንድ መፅሀፍ ቅዱስ አስተማሪ እንዳለው እድገት ወይንም መብሰል ማለት ትንሽነትን መገንዘብ ነው። "Part of growing up is learning to grow small."

በዚህ ምዕራፍ መጀመርያ የምናገኘው ግጥም በህይወት ውስጥ ያሉ ወቅቶች/ seasons summary ነው። የግጥሙ ጥልቀት አቅም ላለው ብዙ የሚያመራምር ነው። አንዳንዶቹ ቃላት ሆን ተብለው እንደተመረጡ ያስታውቃሉ። ለምሳሌ የመጀመርያው list መወለድና መሞት መሆኑ intentional ነው። ልደትና ሞት የአንድ ሰው ህይወት አጥር ናቸው። ሁሉንም ሰው የማይምሩ እውነታዎች ስለሆኑ የአንባቢን ትኩረት ለመሳብ ያገለግላሉ። የተቀሩት ዝርዝር ቃላት የሚከተሉት ይሄ ነው የሚባል order or pattern ያለ አይመስልም። ሰባኪው በዚያም ውስጥ ሊያስተላልፍ ያሰበው ነገር ያለ ይመስለኛል።

መወለድ መሞት፣ መትከል መንቀል ፣ መግደል ማዳን፣ ማፍረስ መገንባት፣ ማልቀስ መሳቅ ፣ ሀዘን ጭፈራ፣ ድንጋይ መጣል ድንጋይ መሰብሰብ፣ መተቃቀፍ መለያየት፣ መተቃቀፍ መለያየት፣ መፈለግ መተው፣ ማስቀመጥ አውጥቶ መጣል፣ መቅደድ መስፋት፣ ዝምታ መናገር፣ መውደድ መጥላት፣ ጦርነት ሰላም። እነዚህ ሁሉ በሰው ህይወት ውስጥ አይቀሬ ወይንም inevitable የሆኑ፣ በሆነ መንገድ ልንዘጋጅላቸው የማንችል unpredictable ክስተቶች ናቸው።

በአጭሩ ሰባኪው እንድንረዳ የሚፈልገው ነገር ህይወትን የምንቆጣጠር በሚመስለን ልክ ስልጣን እንደሌለን። እንዲሁም ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም ህይወት የሚከስምበት ወቅት እንዳለ ነው። ህይወት ብቻ ሳይሆን ለመቅደድ ጊዜ አለው ሲል it implies that there will be situations in life where we choose or are forced to move on accepting ‘loss’ saying “Let it be”. ባሉን የቤተሰብ፣ ወዳጅነት ፣ የስራ እና ሌሎች relationships ያለንን አቅም አሟጠን ጨርሰንም ግኑኝነቱን ማከም አንችል ይሆናል። ይህም የህይወት አንዱ እውነታ ነው።

9-11:ጊዜና ዘለዓለም

ከላይ በተነተነው ግጥም ላይ ሁለት ምልከታዎች:

1, The best we can do is simply respond to the inevitable and also the unpredictable events within a finite lifetime. ስለዚህ ሰራተኛ ከጥረቱ የእግዚአብሔርን እቅድ አያስቀይርም። Infact verse 10 makes the point that we have this pressure/ burden to respond to life. በሚያደክም ሁኔታ ጫናውን ከመሸከም ውጪ አማራጭ የለንም። We can't just be passive and do nothing. ትግል እንቀጥላለን እንጂ..

2 , Yes, life is beautiful. በህይወት tragic ነገሮች ሳይቀር የሆነ አይነት ውበት አለ። ነገርግን ሰው ከዚህ ለተሻለ ነገር ተፈጥሯል። ዘለዓለም። ይሄንን ሀቅ መረዳት ህይወትን ያከብዳል እንጂ አያቀለውም (unfortunately). We have this compulsive drive to transcend our mortality. But all we can clearly see is the micro moments of our lives. የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ስራዎች ማወቅም ሆነ መገንዘብ አንችልም።ነገርግን ዘላለማዊነትን በልባችን እግዚአብሄር አኑሯል። ስለዚህ ፍንጭ ቢኖረንም ስለጊዜ እና ስለዘላለም ገና ብዙ ያልገባንና የማይገባን ነገር አለ።

12-15: አሁን: የእግዚአብሔር ስጦታ!

ቁጥር 12&13 ከምዕራፍ 2: 24-26 ጋር ይመሳሰላል። ምላሻችን ስለጊዜ ሞን መሆን አለበት? አሁን የተሰጠንን ህይወት አሁን በደስታና በሀላፊነት መኖር። እና ደግሞ የህይወትን መሰረታዊ ደስታዎች በአመስጋኝነት ማጣጣም አለብን። መብልና መጠጥ በድጋሚ ተጠቅሰዋል። እነዚህ ነገሮች የስጋ ክፉ ምኞት ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ችሮታ ናቸው። በድካሙ ርካታን እንዲያገኝ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። This is also stated like a testimony. He knows that these things make life good and that they are Gods gifts. ስጦታ/ ችሮታ ደግሞ earn ያደረግነው ሳይሆን በለጋስነቱ የተሸለምነው common grace ነው።

ቁጥር 14: "እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ ምንም አይጨመርም፤ ከእርሱም ምንም አይቀነስም፤ ሰዎች ያከብሩት(ይፈሩት) ዘንድ ይህን አደረገ።” We cant change the way life is, with all its seasons. ምንም ያህል ብንለፋና ብንጥር እግዚአብሔር ህይወትን በዚህ መልኩ ሰፍቶ ወስኖታል። What we can do is bow our souls before Him. Fear God because His deeds are eternal.

እዚህ ላይ ሌላ የምንማረው ነገር የእግዚአብሔር ማንነት ወይ ባህሪ የሚገለጥልን ለሆነ አላማ መሆኑን ነው። Who God is evokes human response. ዘለዓለማዊነቱና የአላማው ፅኑነት እንድንፈራው ሊያደርገን ይገባል።

ቁጥር 15“አሁን ያለው ከዚህ በፊት የነበረው ነው፤ ወደ ፊት የሚሆነውም ቀድሞ የነበረ ነው፤ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል።” ሰው የማይፈልጋቸውን ነገሮች ከህይወቱ ለማጥፋት ይጣጣራል። ለአፍታ ይሳካለትም ይሆናል። ግን እግዚአብሔር በጊዜው የሚመልሳቸው እንደሞት አይነት አይቀሬ ክስተቶች አሉ። የእግዚአብሔርን መኖር ላለመቀበል ሰው ምንም ያህል አኩኩሉ ቢጫወት፣ የክርስቶስን ምስክሮች ወይ ደግሞ የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች እየሸሸ ቢኖር፣ በፍጥረት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን እውነት ቢያፍን..ለጊዜው ነው። There will come a time, when God will require an account.

Pursuing Holiness

22 Oct, 05:57


ከማይደረስበት
ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ፀድቀሻል አለኝ..
ካለሁበት ሸለቆ
ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አ'ርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ...
እዩልኝ እዩልኝ..ደግነቱን እዩልኝ።
አስቱ 💙

Pursuing Holiness

19 Oct, 18:46


ወሰን የሌለው ትዕግሰት..
“ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ።” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥16

እግዚአብሔርን ስለ ትዕግስቱ ማን አመስግኖት ይዘልቃል? The fact that He waits for us ወደቀልባችን እስክንመለስ.. ከውድቀታችንም ከስኬታችንም ተምረን ያለ እርሱ ህይወት ትርጉም የለሽ መሆኗ ያለጥርጥር እስኪገባን ድረስ መታገሱ..

ስንቅበዘበዝ፣ አትሂዱ ወደተባልንበት ስንደረደር፣ ጎስቁለን ደግሞ እንደጠፋው ልጅ ተስፋ ቆርጦ ወደተስፋችን ቶሎ እንደመመለስ when we try to make it by ourselves until we recover enough to pretend like we can be fine without him.. ያኔም አይ የልጅ ነገር እያለ ይታገሳል፣ ነፍሳችንን የሚመልሳት (restore) የሚያደርጋት እርሱ ብቻ እንደሆነ እንዲገባን ይታገሳል።

Its hard for me to believe that whenever I ask for forgiveness for the millionth time on the same sin, His attitude isn't "ኤጭ..ደግሞ መጣች። አሁንም?... I taught you this lesson በቅርቡ እኮ.. ከመቼው ተመልሰሽ ገባሽበት.."

የእርሱን ትዕግስት በጥሩ ሁኔታ የሚያንፀባርቅ template የለንም። ቤተሰብ ብንል ጓደኛ ትዕግስት መሳይ ነገር ቢኖረውም ገደብ አበጅቶ ነው። ተሟጦ ያለቀ ዕለት ምንም ማስተባበያ የለውም። "ቆረጠልኝ" ካለ አበቃ። እግዚአብሔር በኛ በልጆቹ ቢቆርጥለት ምን ይውጠን ነበር?

ለእኛ extended የሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት እራሱ ጌታ ኢየሱስ ነው። ወሰን የለውም። አይነጥፍም። የእስከዛሬው ነው አይደል የሚገርመን? ገና እስከፍፃሜው የሚሸከመን ራሱ ነው።


"ደግሞም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ “አንድ ሰው በወይኑ ዕርሻ ቦታ የተተከለች አንዲት የበለስ ተክል ነበረችው፤ እርሱም ፍሬ ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም። የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው። እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤ ለከርሞ ካፈራች መልካም ነው፤ አለበለዚያ ትቈርጣታለህ።’ ሉቃስ 13:6-9

በለሲቱን አትቁረጣት
ለአንድ አመት ታገሳት
🎶 ቤቲ ተዘራ