🕹ትምህርት ወይሥ ሥልጠና?
(ኑሮህን የሚደጉም በቂ ገቢ ከየትኛው?)
ትማር.....ትማርና ተመርቀህ ወደ ሠፈርህ/ወደ ቀዬህ ትመለሣለህ....!
በኛ ግዜ ሥትመረቅ....
እንደ ሠርግ ይደገሥልሃል።ሢጠብሽህ የምትሾተው የአንገት ሃብልና የ ጣት ቀለበት ፤ለ ሥራ ቅጥር ኢንተርቪው የምትጫማው ሹል ጫማ፣የምትታጠቀው ባለ ጠቃጠቆው ቀበቶ፣ሽክ የምትልበት የተተኮሠ ሸሚዝ .... ከሠፈርተኛው፣ከጓደኞች፣ከእድር፣ከዘመድ አዝማድ በሥጦታ ወደፊት በብድራት የምትመልሠው (የመለሠ ያለ አይመሥለኝም) ይበረከትልሃል!!
ሃይሥኩል አብረሃት የተማርክ ለርኪ ፣ማትሪክ ቁሥለኛ አድርጎ ያሠናከላትና ሠፈር የቀረች፣ማህበረሠቡ የሚዘባበትባት.... ድሮ ትንሽ የተመቻቻችሁ - ደግሞ 'congratulation የኔ ፍቅር' የሚል የድሮ ፖሥት ካርድ ትገጭሃለች።ከዚህ ሃሜተኛ ማህበር መሃል ይዘሃት እንድትጠፋ ኦፈር ትሠጥሃለች። ትተማመንብሃለች 😂
ግና የተመረቀ ሁሉ ሥራ አይዝምና ...አራት ኪሎ የሥራ ማሥታወቂያ ለማንበብ ጆሊጋ ትኮለኮላለህ፣ሥራ ከየት ይምጣ? ዘመድ ከሌለህ፣አሪፍ ካድሬ ካላወቅህ፣የቀበሌ ሥብሠባ አተኩረህ ካልተሣተፍክ፣እንትን ካልሆንክ....
የተሠጠህን ሃብሉን፣ቀለበቱን፣ቀበቶውን፣ሹሉ ጫማህን፣የተመረቅህበት ሡፍህን ተራ በተራ ፒያሣና መርካቶ እየወሠድክ .... እየፖሸርክ ትቅ*ምበታለህ፣ ትጠ*ጣበታለህ፣ታጨ*ሥበታለህ፣ት***ታለህ።
¤¤
ሥራ እንዳገኘህ አይነት የሚያሠማህን የሥራ ማሥታወቂያ በ15 ሣንቲም ተከራይተህ ከ ....
አዲሥ ዘመን፣ ወደ
አዲሥ አድማሥ፣
ከ ፎርቹን፣ ወደ
ሪፖርተር ......ትገለባበጣለህ....ሥራ ኢንጅሩ!😂
ትፈልግ ትፈልግና ትደክማለህ 6 ወር፣አንድ አመት፣ሁለት አመት ወዘተ ሥራ ፈት ትሆናለህ።አንተም ኮሚኒቲውም ትሠለቻቻላችሁ።
በዜሮ አመት የሥራ ልምድ ማን ይቀጥርሃል? ኮታ እሥካልመጣ ድረሥ!? ለመሠደድ ሁሉ ታሥባለህ።
15 ሣንቲም የጋዜጣ ክራይ መክፈል ፣መ*ጠጫ፣ መ*ቃሚያ፣ማ*ጨሻ...ምናምን ይጠርርብሃል።ከዛሥ አይንህን ጨፍነህ ቤትህ ትቀራለህ፣ትነጫነጫለህ...ማሚህ፣ዳዲህ በድግሡ ግዜ እንዳልተደሠቱ ልባቸው ይሠበራል።
በለሥ የቀናው ...አብራችሁ ተመርቃችሁ ደሞዝ ያለው ጀለሥህ በወር አንዴ ይለቅብሃል። እሡም ከበቃው።
¤¤
ይህ ማለት ተመርቀህ ኳሊፋይድ ሆነህ ነው።የሥራ አጥ ዳታቤዝ ማሞቂያ ትሆናለህ። ክህሎት(ሥኪል) የለህማ......
እዚጋ ነው....ከገባህበት አዝእቅጥ ለመውጣት ክህሎቶችን ባጋጣሚ በማየት ትሠለጥናለህ።
ታቅፈህ ጥበቃ ትሠራህ፣ተመልክተህ ጋሪ ትነዳለህ፣ተደራጅተህ ኮብል ትፈልጣለህ፣ባጃጅ ትሾፍራለህ፣ሰልጥነህ ራይድ ትነዳለህ፣የሆቴል አሥተናጋጅ ትሆናለህ፣የሥፓ ጠባቂ ትሆናለህ፣ፓርኪንግ ትሠራለህ፣ትላላካለህ፣....መዝረፍ አትችልም!ተምረሃላ!
በቃ qualification and skills የተራራቁበት ባህር ውሥጥ ትዘፈቃለህ።
የመጀመሪያው ምታውቀውን እንዴት እንደምታሣይ ሢያደርግህ፤ሁለተኛው ክህሎት ደግሞ መሥራት የምትችለውን ነው።
ለዚህ ሤናሪዮ ከኳሊፊኬሽን በበለጠ ክህሎት ረጂ ነው!
ክህሎት በፍጥነት እና በተግባር ይለውጥሃል።ክህሎትን ለማግኘት ብዙ አመት እንደ ትምህርት አታሣልፍም።በሦሥት ወርበ ሁለት ወር ....ኮዲንግ ትሠለጥናለህ፣ሽያጭ ትሠለጥናለህ፣ሹፍርና ትሠለጥናለህ፣ወጥ መሥራት ትሠለጥናለህ፣ኢንትሪየር ዲዛይን ትሠለጥናለህ፣ብየዳ ትሠለጥናለህ ወዘተ ::
ሪል ወርልድ ቻሌንጆችን በክህሎት ትወጣዋለህ።ጂያንቶች እንደነ ጎግል፣አፕል ክህሎት እንጂ ዲግሪ አይቀጥሩም።ሥንት ሢቪል፣ቢዝነሥ፣ሜካኒካል ወዘተ ተምረው አሜሪካ ገብተው ፕሮግራሚንግ በአጭር ግዜ ሠልጥነው የእለት እንጀራቸውን የሚዘጉ ነፍ ናቸው።
ሞር ....ክህሎት ወደ ኢንተርፕሩነር የሚያሸጋግር ሃይል አለው።የእውነት አለም፣ገበያ ውሥጥ ልምምድ ሥለሚኖርህ።
ከደሞዝ ይልቅ ንግድ ትርፍን ለማጣጣም የተሻለው...ክህሎት ላይ የተመሠረተ ተፍ ተፍ ፣በት በት ሢኖርህ ነው።
የቻይኖች ተረት ...'ጦጣ ፊት ሙዝና ገንዘብ ብታሥቀምጥ...ሙዙን ይመርጣል። ጦጣው ገንዘብ ሙዝ እንደሚገዛ ሥለማያውቅ።' ይላሉ።
በፊትህ ከደሞዝ ወይንም ከንግድ ትርፍ (wage or profit) ምርጫ ቢሠጥህ ...ከቅጥር ሥራ እና ከንግድ እንደ መምረጥ ያህል ነው።
ብዙ ሠው የሚያውቀው ደሞዝ እንጂ ቢዝነሥ ብዙ ገንዘብ አለማምጣቱን ነው።
ችግር የማይፈታ ትምህርት ያመጣው በዲግሪ ለአብዛኛው ጀማ...
ድህነት እንዲነግሥብህ ፣አካባቢን እንዳታውቅ እና ፍርሃት እንዲጣባህ፣ ኢንተርፕሩኒያል ማይንድ ሤት እንዳይኖርህ ያደርጋል። የንግድ ኦፖርቹኒቲን እንዳታይ ያደርግሃል።ለጥቂቱ ይሠራል (ከጥቂቱ ከሆንክ እለፈው)
ችግር የማይፈታ ትምሮ....
ብዙህ ግዜህን ት/ቤትና ምርምር ላይ እንድታሣልፍ ያደርግሃል።በዚህ ሃገር ትምህርት ቤቱም ለደሞዝ እንድትሠራ አድርጎ ቀርጾ ያወጣሃል።ለዛ ነው ብዙ ባለሃብት ያልተማረ.. ብዙሁን የተማረን ተቀጣሪ ያደረገው።...ጥሬ ሃቅ።
ደግሞ መማር...የኢጎ፣የወረቀትና የድህነት ማማ ላይ ሠቅሎህ ቁጭ ይላል።ለራሥህ ችግርን የማይፈታ ትምህርት ራሥህን ሃሣብህን ከመሥራት ይልቅ ለሠው /ለሢሥተም እንድትሠራ ዘዴን ያሥተምርሃል።
የንግድ ትርፍ ከላብ ምንዳ/ደሞዝ መብለጡንና አንተም አኳየር ማድረግ እንደምትችል አይነግርህም። ምንዳ ይደግፍሃል ትርፍ ግን ሃብትን ያመጣል።
አብዝተህ ክህሎትን ፈልግ።ሠልጥን።
ዲፕሎም፣ዲግሪ፣ማሥተርሥ፣ፒ ኤች ዴ እራሥህን እንዲሁም ማህበረሠብ ላይ ተቆጣሪ ለውጥ ካላመጣ የብላኔ ጥበብ ነው።ለኢጎ እና ለፎቶ ከመሆን አያልፍም።
ትምህርት ላይ አጫጭር ተግባራዊ የክህሎት ሥልጠና ብትወሥድበት ሙሉ ይሆናል።ብቻውን ግን....😂👌
ትምህርት ወይሥ ሥልጠና?
በርቱ!
ከማህበራዊ ሚዲያ
ራስን መለወጥ