Mereb Media (መረብ ሚዲያ) @natnael_mekonen Channel on Telegram

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

@natnael_mekonen


ውድ የትግል አጋሮቸ ውድ ኢትዮጵያውያን አሁን ያለንበትን
ችግር ታሳቢ በማድረግ ከ facebook በተጨማሪ
በቴሌግራም አዳዲስና ወቅታዊ የማንቂያ መረጃዎችን ላደርሳችሁ ይሄንን ቻናል ከፍቻለው ስለዚህ እኔ ከማደርሳቹ በተጨማሪ በአካባቢያቹ ያሉ ኩነቶችን ታደርሱኝና በ ፌስቡክ እንዲሁም በቴሌግራም ለሰፊው ህዝብ የማደርስላቹ ይሆናል!!!!!!!!!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!

ድል ለኢትዮጵያውያን

Mereb Media (መረብ ሚዲያ) (Amharic)

Mereb Media (መረብ ሚዲያ) ከዚህ ፈዚዝ መሰረት በመነጋገር ያላቸው የትግል አጋሮችን ላይ ስለተሠራችሁ ከ Facebook በቴሌግራም እና ፌስቡክ ለሁሉ ህዝብ የሚደርስባቸው የማንቂያ መረጃዎችን ታደርሱንና ለአባቶችና ልጆች የኢትዮጵያ ትኑር ማለት። ኢትዮጵያ ድል ለቀጣይ የኢትዮጵያውያንን ስለሆኑ ለማንቂያዎች ምን ይጠብቁ የሚሉትን አዳዲስ ውስጥ ታደርጉን።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

16 Nov, 19:02


ህዳር 7/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም
አንደኛ ክፍለ ጦር ኤሌኮፍተር መቶ ጥሏል።
============================
በትናንትናው እለት ብርሃኑ ጁላ ባህር ዳር ስለመጣ እርሱን  ታርጌት ያደረገ እንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ሰዓት ዛሬ የጠላት አየር ኃይል መንቀሳቀስ ጀመረ።
ንጋት 11 :00 አካባቢ ከባህር ዳር የድሮን ማዘዣ ጣቢያ አንድ ድሮን ወጥቶ የተለመደውን የንጸሃን ጭፍጨፋ ሊፈጽም እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ሰምተን ስንጠባበቅ ነበር።

ረፋድ 4:10 ገደማ ደግሞ ከተመሳሳይ ቦታ ተነስቶ ወደ ደ/ጎንደር አቅጣጫ ሁለት ኤሌኮፍተር መጓዛቸውን የ1ኛ ክፍለ ጦር ይሰማና በአመራሮች በኩል ስምሪት ሳይሰጣል።
ከአሰሳ እየተመለሱ የነበሩ ኤሌኮፍተሮችን በተሰጠው ስምሪት መሰረት የ1ኛ ክፍለ ጦር ለዚህ ተልዕኮ የተመደቡ ልጆች አንደኛውን መተው ጥለውታል።ከአዴት አቅጣጫ ተመቶ ከበላይ ዘለቀ ኤርፖርት ደቡባዊ አቅጣጫ ወድቋል።
ፓይለቱን ጨምሮ ውስጥ ላይ የነበሩ ሌሎች ማረጋቸውን ያላወቅናቸው ትልልቅ አመራሮች ሙተዋል።

     በቅርቡ መቶ መጣል ሳይሆን ድሮን፣ ኤሌኮፍተር ...እንማርካለን!!!

  ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

16 Nov, 16:09


“ሂሊኮፕተሯን በከባድ መሳሪያ መተን ጥለናታል!” -የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ ፋኖ አስረስ ማረ

“ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከባህርዳር ኤርፖርት ተነስተው የተለመደውን የንፁሃን  ጭፍጨፋ ሲያደርጉ ከዋሉ በኋላ ከወጡበት ስምሪት ሲመለሱ ባህርዳር ኤርፖርት ለማረፍ ዝቅ ብለው በሚበሩበት ወቅት የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር በረጅም ርቀት መሳሪያ ለመምታት ባደረገው ርብርብ አንደኛዋ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ችሏል:: በዚሁ ምክንያት የተመታችዉ ተዋጊ አውሮፕላን የሲቪል አውሮፕላን ማኮብከኮቢያው ላይ ተከስክሳለች።

በስፍራው የነበረው የመከላከያ ምዕራብ ዕዝ እስታፍ ሙሉ ኤርፖርቱን በቁጥጥሩ ስር በማዋሉ ምክንያት የእሳት አደጋ መኪኖች እና አምቡላንሶችም ወደ ስፍራው እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አብራሪውን ጨምሮ በረራው ላይ የነበሩት በሙሉ መሞታቸው ተረጋግጧል። መደበኛ በረራም ተቋርጧል:: የአብይ አህመድ ወራሪ ጦር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርቶችን እና የሲቪል አውሮፕላኖችን ለሰራዊቱ መጠቀም ካላቆመ ፋኖ የበረራ ክልከላ (No Fly Zone) ወደ ማወጁ ይሸጋገራል።”

#Amhara #Ethiopia

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

16 Nov, 13:59


ተጨማሪ መረጃ!

ባህር ዳር ላይ የወደቀችው ሄሊኮፕተ በፋኖ ሃይሎች ጥቃት ተመታ እንደወደቀች የተረጋገጠ ሲሆን በውስጡ የነበሩ ሰዎች ዝርዝር ከመላምት በቀር ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

16 Nov, 13:40


ሰበር ዜና፡-

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ይዛ ነበር የተባለች አንዲት ሄሊኮፕተር በባህርዳር በላይ ዘለቀ ኤርፖርት በፋኖ ሃይሎች ተመታ ወድቃለች የሚል መረጃ የደረሰን ሲሆን መረጃውን አጣርተን የምንመለስ ይሆናል፡፡


ምንጭ፡-አማራ ታይምስ

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

20 Oct, 20:06


ይሄ ኤርድሮፕ ቴሌግራም ካምፓኒ ያስተዋወቀው ፕሮጀክት ነው! አንድ ጓደኛ Invite ስታደርጉ 1$(አንድ ዶላር) ይከፍላል! ቴሌግራም ገፃቸውን ስትቀላቀሉ ደግሞ 0.1$ ዶላር ይሰጣል። የ “X” አካውንታቸውንም በተመሳሳይ 0.1$ ይከፍላችኋል።

ስሩበት! ሊንክ👇

https://t.me/fadewalletbot/app?startapp=2c4c7873604c400ca7d6493232e917d2

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

13 Oct, 17:05


ሰበር ዜና!

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለጦር የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ ወደሆነችው ወልደያ ከተማ አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ ወልደያ ከተማ መግባቱን ሰምተናል!

የጀግና ዘር!

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

11 Oct, 19:17


ባለፉት ቀናት...!

-የመከላከያ አዛዥ የሆነ መቶ አለቃ  ከነ አጃቢዎቹ እና ከነመሳሪያዉ የአማራ ፋኖ በጎንደር ካራማራ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል፡፡

-የኢቲቪ  የአባይ ፕሮግራም ክፍል አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ምኒልክ ፋኖን ተቀላቅሏል።

-የቀድሞው የአማራ ልዩ ሀይል የጣና 29ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበረው ተወዳጁ አርቲስት ሙሉቀን ከተማ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ተቀላቅሏል።

-የባህል አቀንቃኙ አርቲስት ሞላ ሰጥአርግ የአማራ ፋኖ በጎጃምን ተቀላቅሏል!

#Amhara #Ethiopia

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

09 Oct, 12:11


መረጃ!

ሰሜን ሸዋ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለ ጦር በምንጃር እና በረኸት ወረዳዎች በእያንዳንዳቸው ለአራት ቀናት ውጊያ ላይ ናቸው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ደግሞ ዛሬ የዓባይ ምንጭ የሆነችውንና የብልጽግና ሰራዊት ብዙ ግፍ የፈጸመባትን ሰከላ-ግሽ ዓባይ መቆጣጠሩን ገልጿል።

የፋኖ ኃይሎች ትናንት ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ መግባታቸው ይታወቃል። በጎጃም ዳንግላ እና አሽፋ መገንጠያ አካባቢዎች ደግሞ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።

#Amhara #Ethiopia

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

07 Oct, 16:48


„በጥፋት ሀይሉ አመራሮች ላይ እርምጃ እንወስዳለን“ - የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር

ዛሬ ረፋድ በነ ዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከ10 በላይ የሆኑ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ሹመኞችን በማንሳት ይወክሉኛል ባላቸው ሰዎች መተካቱ ገልፆ የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም በአቶ ጌታቸው የሚመራም የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ይህንን ሹም ሽር ባደረጉት አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ዛሬ አመሻሽ ባወጣው መግለጫ ‚ህገወጥ‘ ሲል በጠራውና በነ ደብረፅዮን የሚመራው ቡድን ይፋዊ የመንግስት ግልበጣ መፈፀሙን አውጇል ማለቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

ጊዝያዊ አስተዳደሩ አክሎም ቡዱኑ መንግስትነት በምንና እንዴት እንደሚገኝ ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ትግራይን የሁከትና የብጥብጥ ማእከል ለማድረግ ያለውን ፍላጎት ለማሳካት ነው እንዲህ አይነቱ ወሳኔ የወሰነው ያለ ሲሆን ጊዝያዊ አስተዳደሩም እንዲህ አይነቱ ህግ አልበኝነት እንደማይታገስና በህገወጥ ቡዱና አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለፅ ለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት ጥፋት በነ ደብረፅዮን የሚመራው ቡድን ነው ተጠያቂው ሲል ገልፆል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

07 Oct, 16:47


Update

“አቶ ጌታቸው ረዳን ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነት አንስቻለሁ” የዶ/ር ደብረጺዮን ቡድን

በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ያሉትን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ አምስት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ከስልጣን አንስቻለሁ ሲል አስታወቀ።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ “የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት የሚሆኑትን አመራር ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመነጋገር አሳውቃለሁ” ሲል ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በካቢኔ አባልነት እና የተለያዩ ቢሮ ሃላፊ ሁነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ባለስልጣናት ከዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ “ምንም አይነት አመራር መስጠት፣ ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም” ሲል ገልጿል።

ይህንንም “መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት፣ የትግራይ የፀጥታ አካላት፣ የፌደራል መንግስቱ እና ክልሎች፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ሌሎች የሚመለከቱ አካላት እንዲያውቁልን እናሳስባለን” ብሏል።

በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ከስልጣናቸው አንስቻቸዋለሁ ባላቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ምትክ አዲስ ተሿሚዎችንም አስታውቋል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

07 Oct, 11:30


ሰበር ዜና፡-

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ፕሬዝደንት በመሆን ተሾሙ፡፡

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

05 Oct, 12:38


«ዝምታ ነው መልሴን ለአንድ አመት ሞከርኩት» -ክብርት ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ይበቃዎታል አንድ አመት ብዙ ነው!

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

04 Oct, 14:10


ሰበር ዜና


የአማራ ፋኖ በጎጃም የደንበጫ፥ፍኖተ ሰላም እና ጅጋ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

02 Oct, 16:35


ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ መንገድ ዝግ ነው!

ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቀው የተሽከርካሪዎች እገዳ አዋጅ በሁሉም የአማራ ግዛቶች ተግባራዊ እንደሚሆን እና ለዚህም ተፈፃሚነት ከወዲሁ ዝግጅታቸውን መጨረሳቻው የሁሉም እዝ የክፍለ ጦር እና የብርጌድ አመራሮች እያሳወቁ ነው።

የተሽከርካሪ ባለነብርቶች እና አሽከርካሪዎችም ይህንን አዋጅ በማክበር እንድትተባበሩ አደራ አዘል ማሳሰቢያዎች ተላልፈዋል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

01 Oct, 18:32


መካከለኛው ምስራቅ ወደየት ያመራል ?

በእስራኤልና ፍልስጤም ሃማስ መካከል የጀመረው ጦርነት መፍትሄ ሳያገኝ ቀርቶ ችግሩ አድማሱን አስፍቶ ቀጠናው መታመሱን ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።

የቀጠናው ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ነው።

ከሰሞኑ ደግሞ በእስራኤል እና በሊባኖስ ሄዝቦላህ መካከል የነበረው ግጭት ተባብሶ በርካቶች ሞተዋል ፤ ተጎድተዋል።

የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነርሰራላህ እና ሌሎችም ቁልፍ ሰዎች በእስራል ጥቃት መገደላቸው ሁኔታውን እጅግ አስከፊ አድርጎታል።

ከዚህ ቀደም እስራኤል በቀጣናው የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ስታስጠነቅቅ የነበረችው ኢራን ወደ እርምጃ ገብታለች።

ዛሬ የእስራኤል ከተሞች በሳይረን ድምጽ ሲናወጡ ነው ያመሹት።

ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች።

የሀገሪቱ ዜጎችም ህይወታቸውን ለማዳን ወደ አደጋ መከካከያ ስፍራዎች እንዲገቡ ተደርገው ነበር።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥበቃ 250 ሚሳኤሎች መተኮሱን አመልክቷል።

የእስራኤል ጦር ከኢራን በኩል የባላስቲክ ማሳኤል መወንጨፉን አረጋግጧል።

የእስራኤል ጦር አሁን ላይ ከኢራን በኩል የሚያሰጋ ጥቃት እንደሌለና በየመጠለያው የተሸሸጉ መውጣት እንደሚችሉ አመልክቷል።

የኢራን እርምጃ ከዚህ ቀደም እንደተፈራው ሁኔታውን እጅግ ወደከፋ ሁኔታ ሊያስገባው እንደሚችል ተሰግቷል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

30 Sep, 19:36


ልዪ መረጃ

በአማራ ክልል ሰፊ መሰረት እንዳለው የሚነገርለት የቀድሞው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ያሁኑ ፀደይ ባንክ አ.ማ በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ከተማዎች ባሉ ቅርንጫፎቹ ላይ ማንነታቸው በጉልህ ባልታወቁ አካላት ከአምስት በላይ ቅርንጫፎቹ ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ከውስጥ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ባንኩ በአጠቃላይ ከ90 ሚሊዮን ብር ያላነሰ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ:-አማራ ታይምስ

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

30 Sep, 17:48


የጭንቀት እርምጃው ክልሉን አዳርሷል!

በቆቦ፣በወልድያ፣ በደሴ በኮምቦልቻ ወዘተ የመንግስት ሠራተኞች፣ መምህራን፣ ሀኪሞች፣ ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች፣ የብልጽግና አመራሮች ... ከየቤታቸው እየታደኑ ወደ እስር ሲጋዙ ውለዋል። ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ የኾነ ይመስላል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

28 Sep, 12:25


#Update: ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አረጋግጧል

ሂዝቦላህ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በለቀቀው መግለጫ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አስታውቋል።

ቀደም ሲል የእስራኤል ጦር በኢራን የሚደገፈውን የሂዝቦላ ታጣበቂ ቡድን መሪ በትላንትናው ዕለት በቤሩት በፈጸመው ጥቃት መግደሉን መግለጹ ይታወሳል።

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

23 Sep, 08:16


ሰበር ዜና ከጀግኖቹ ምድር ሸዋ!!!

👉በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በሚዳና ሬማ ወረዳ በሬማ ከተማ መሽጎ የነበረውን ወራሪ የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በስሩ ያሉ ብስጌዶችን በማቀናጀት በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ዓመቱን ሙሉ በፋኖ ቁጥጥር  ስር የከረመችውን የጀግኖቹ መንደር የሆነችውን ሬማ ከተማን እና ህዝቡን ነፃ አውጥቷል። የወታደር ቁመና እና ስነ-ምግባር የሌለው ወራሪው የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ዛሬን ጨምሮ በሬማ ከተማ መሽጎ በነበረበት ወቅት በተወሰደበት ተደጋጋሚ እርምጃ ከ 70% በላይ ሰራዊቱን ያጣ ሲሆን ከ 60 በላይ የሚሆኑ አባላቱ እስከ ወዲያኛው አለም ሲሸኙ፣ ከ 45 በላይ ከባድ ቁስለኛ እና እስከ ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ ብቻ 75 የሚሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር የቀስተ ንህብ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።


"የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር የቀስተ ንህብ ብርጌድ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሀላፋ ፋኖ መ/ር ይድነቃቸው ማሙዬ"

    ድል ለአማራ ህዝብ!!!
    ድል ለአማራ ፋኖ!!!

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

23 Sep, 08:12


ወደ ሱዳን ሸሽተው የሄዱ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች መተማ ለሚገኙ ፋኖዎች ስልክ ደውለዋል።

ወታደሮቹ ለፋኖዎች ምን አሏቸው? ዜናውን አድምጡ👉
https://youtu.be/bWCilnd5GLQ?si=sFKW4Zz24J19U61Z

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

22 Sep, 09:24


እነሆ በዚህ ወቅት አትራፊ ከሆኑ የኢንተርኔት ስራዎች ውስጥ ኤርድሮፖች(Air drops)  ተጠቃሽ ናቸው፡፡Dogs,Hamster  አሁን ደግሞ የቢትኮይን መገበያያው ባይናንስ ካምፓኒ(Binance officially)  የራሱን ኤርድሮፕ ይዞ የመጣ ሲሆን  binance moonbix ይባላል፡፡በመሆኑም እንደ Hamster,dogs እና ሌሎችም የመጀመሪያውን ዙር ከመጨረሱ በፊት በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ከወዲሁ ኮይን ሰብስቡ ክፍያ በባይናንስ አካውንትዎ ይሆናል ፡፡ https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startapp=ref_1464251641&startApp=ref_1464251641


#Mereb Media😇😇

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

22 Sep, 09:14


#ከድሮን ጭፍጨፋ ለመዳን የሚያስችሉ ዘዴዎች

1ኛ. በአንድ  ወይም በቡድን ሁኖ አለመጓዝ!

2ኛ. ከ5 ሰው በላይ ሁኖ አለመጓዝ!

3ኛ. ራሱን በቅጠል/በጫካ መሸፈን!

4ኛ. ከ25ሜትር  በታች ባለ የጎንዮሽ ርቀት አለመጓዝ!

5ኛ. ሲቀመጡ በዛፍ ጥላ ስር መሆን አለብን (ድሮን በጥላ ስር ያለን ብዙ ጊዜ ማንበብ  አይችልም)!

6ኛ. የሚያፀባረቁ ምንጣፍ/አንሶላ አለመጠቀም!

7ኛ. ሲቀሳቀሱ በጨለማ/ጧት/በደመና ይጓዙ!

8ኛ. ካሉበት ቦታ ጋ የሚመሳሰሉ ልብስ ይልበሱ!

9ኛ. በአንድ መንገድ ሁሌም አለመጓዝ!

10ኛ. ከመሄዳችን/ከመጓዛችን በፊት ጫካ የሆኑ ቦታወችን መምረጥ!

11ኛ. በአንዴ ብዛት የወታደር ስቅ መጫንና መጓጓዝ የለበትም!

12ኛ. ከድሮውን እይታ ውጭ መሆን!

13ኛ. በገቢያ, ሰበት ቀን,እቁብ,በመኪና, በጋራ ,በሀዘንና በሌሎች የማህበር አኗኗር አብሮ አለመገኘት(መበትን ያስፈልጋል)!

14ኛ. ሲራመዱና ሲቀሳቀሱ በዝግታ ይሁን ም/ቱም ሲፈጥኑ በቀላሉ ድሮውን ሰለሚያየን!

15ኛ. ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ በጥንቃቄ ይሂዱ!

16ኛ. በእንቅስቃሴ ወቅት በደንብ መረጃ መለዋወጥ!

17ኛ. አካባቢውን መቃኘት!

18ኛ. የድሮን እቆስቃሴ መኖሩን ወደ ሰማይ በማየት በደንብ ማረጋገጥና መዘጋጀት ቦታ ለመያዝ!

19ኛ. አንዴ በድሮን ከመታን በኋላ እኛ ቁስለኛ ወይም አስክሬን ለማሳት አለመሄዴ ም/ቱም ከዛው ላይ እኛን ድጋሜ ሊመታን ስለሚችል!

ድል ለአማራ ፋኖ 💪

አማራ ያሸንፋል 💪

#ሼር በማድረግ ለሁሉም ቀጠና የአማራ ፋኖ አድርሱት

መረብ ሚዲያ

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

22 Sep, 09:09


ውድ ተከታታዮቻችን መረብ ሚዲያ ወደ ተሟላ ሚዲያነት ማደጉት ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡


መረብ ሚዲያ🎉🎉🎉😇😇😇😇

Mereb Media (መረብ ሚዲያ)

22 Sep, 09:06


ሰበር ዜና!

በላስታ ቀጠና ልዩ ስሙ ድብኮ አከባቢ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት አንድ የሻለቃ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ በርካታ የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!

ደፈጣ ጥቃት የተፈፀመበት ይህ የአገዛዙ ኃይል ከሰሞኑ ወደ አማራ ክልል የገባ መሆኑም ነው የተነገረው።

ከሌሎች የሃገሪቱ ክፍል ተወጣጥቶ ወደ አማራ ክልል ላስታ ላሊበላ ቀጠና እየገባ የነበረው አዲስ የገዢው ቡድን ወታደር ላይ ትናንት መስከረም 11/2017 ዓ/ም አመሻሹን በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት አንድ የሻለቃ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ጥቃቱ በተፈፀመበት አከባቢ የነበሩ የአይን እማኞችንና የፋኖ አባላቱን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው በጋሼና እና በላሊበላ ከተማ መካከል በሚገኙ ልዩ ስማቸው ድብኮ እና ግራኝ አምባ በተባሉ አከባቢዎች ላይ ሲሆን፡ በዚህም በገዢው ቡድን ኃይል ላይ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት መድረሱን አማራ ፋኖ በወሎ የአሳምነው ኮር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

በዚህ ጥቃት አንድ የሻለቃ አዛዥ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፡ 12 የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያና ሦስት መገናኛ ራዲዮን በፋኖ እጅ መግባቱን ነው የኮሩ ቃል አቀባይ የገለፀው።

"የደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው የአገዛዙ ወታደሮች ከሰሞኑ ነው ወደ አማራ ክልል የገቡት፡ የመጀመሪያውን ጥቃት አድርሰንባቸዋል" ያለው የኮሩ ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው፡ "ገዢው ቡድን እያስገባው ያለው ኃይል ካለን የተዋጊ ኃይል ብዛት አንፃር ያሉብንን አንዳንድ የትጥቅ ጉድለቶችን ያሟላልናል" ሲል ተናግሯል።

እንሆ ተጨማሪ ዝርዝር👉
https://www.youtube.com/watch?v=zzPmtWimA4Q

2,744

subscribers

390

photos

40

videos