ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

@tewahdotisfafa


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ፥ በርሷም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳቹ እረፋት ታገኛላችሁ፤ኦቶዶክስ ተዋሕዶ ትኑር ለዘላዓለም አሜን💚💛❤️🕊
ት.ኤር 6፥16
💚እውነት ተፈትና
ሀሰት ብትበዛም ፈተና
እውነት ግን አንድናት፨

አስታየት ለመስጠት-ያናግሩን
📥🕯🕯
@Melaku_23
@Melaku_24 📥

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

22 Oct, 18:00


Channel photo updated

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

15 Oct, 23:30


አስደናቂው የቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን መፅሐፍ ምርቃታ አሐቲ ድግል፨
http://sharevideo1.com/v/NnkyakFxVUtlQTQ=?t=ytb&f=sy
🔥Trending video shared via VidMate🔥
🎉Best downloader for video and image on YouTube, WhatsApp status, Facebook, Instagram...
🎉Platform for FREE latest movies🎥🎥
👇Download VidMate Now!👇
https://www.vidmateapp.com/?subpub=sharing

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

09 Oct, 02:41


ፍቅሯ ልዬ ነው ደግነቷ🌿🌿🌿
እናቴ አርሴማ ሰማዐቷ😍🥰

'ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቁመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትሆን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው።አምላጅነቷ አይለየን🤗❤️
  🌺ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ🌺

መስከረም  29 ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ሰማዕትነት የተበለችበት ቀን ነው። እንኳን አደረሳችሁ።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ትሰውረን።🙏

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

03 Oct, 05:30


ያንደበቴ ጣፋጭ ውዳሴ
========///========

ያንደበቴ ጣፋጭ ውዳሴ
ምፅናናብሽ ታዛለ ነፍሴ
ከመቅደስሽ ፍቅር ተምሬ
ማርያም ማርያም ይላል ከንፈሬ

ልመናዬን ሰምተሻል
በረድኤት ቀርበሻል
በፍቅርሽ ተሸልሜ
አረፍኩኝ ከሸክሜ{፪}

ቃሌ ነው በተሰማ
ተማፅኖዬን ሳሰማ
በዙፋኑ ቀኝ ሆነሽ
ድንግል ታስምሪናለሽ {፪}

ማግኝት ማጣት አይደለም
ልመናዬ በአለም
አድይኝ ማስተዋሉን
እንድረዳው መስቀሉን {፪}

አይመራኝም በትሬ
ድንግል ቆመሽ ከበሬ
ምርኩዜ ብዬሻለው
አንቺን እደገፋለው {፪}

https://t.me/maedot_ze_orthodox

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

02 Oct, 05:41


"ከግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም /ድርሳነ መስቀሉ ትርጓሜ በርእሰ አባ ኪዳነ ማርያም!

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

02 Oct, 05:39


"በልዩ መንበሯ አገሯ ግሸን ማማሯ //፪//
ማማሯ ማመሯ አገሯ ግሸን ማማሯ// ፪//
👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 15:11


Channel photo updated

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 15:06


እንኳን አደረሳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን

" ንግስቲቱ#ግሸን_ደብረ_ከርቤ "

ከደሴ ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ 82 ኪሎ ሜትር በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው ዳግማዊት እየሩሳሌም በመባል የምትታወቀው ግሸን ደብረ ከርቤ ከእምነትና ከአስተዳደር ጋር የተቆራኙ ታሪኮችን ይዛለች፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ያሳተመው የቱሪዝም ማውጫ እንደሚያትተው ግሸን ማርያም የተቆረቆረችው በ517ዓ.ም በአጼ ካሌብ የክርስትና አባት የሆኑት አባ ፈቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ናቸው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሔር አብን ጽላቶች ከሃገረ ናግራን /ከዛሬዋ የመን/ ይዘው ረጅም ጉዞ ተጉዘው አቀበቱን መንገድ አጥተው ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተንጣሎ በማየታቸው ቦታውን ሲያደንቁ ይህስ ‹‹አምባ ሰል›› ነው ያሉ ሲሆን ስል ማለት በአረበኛ ማር ሲሆን ትርጉሙ የማር አምባ ማለት ነው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ ሁለት ጎጆዎች አሰርተው ያመጡትን የአብና የድንግል ማሪያምን ጽላቶች በማስገባት እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይነገራል፡፡

አምባው በተፈጥሮው ቀራጺ ባለሙያ የሰራው መስቀል የሚመስልና ወደ አምባው ለመውጣት ከአንዲት በር በስተቀር እንደ ምሰሶ የተቀረጸ ገደል ያለበት ነው፡፡

ይህችም በር በአጼ ኃይለ ስላሴ በጠፍጣፋ ድንጋይ ደረጃ ከመስራቱ በፊት አምባውን ለመውጣትና ለመውረድ በገመድ ወይም በመጫኛ ወገብ ታስሮ ነበር፡፡

ግማደ መስቀሉ ተቀብሮበታል ተብሎ የሚታመነው የእግዚዓብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን በአጼ ዘርዓያዕቆብ እንደገና የተሰራ ሲሆን በዳግማዊ ሚኒሊክም ታድሷል፡፡ በውስጡ በርካታ ኃይማኖታዊ ታሪክ ያላቸው ስዕሎችና ቅርሶች አሉት፡፡

መልካም በዓል የድግል ማሪያም ምልጃና ጸሎት አይለየን...,🙏


......Join.....

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 14:28


††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ግሼን ደብረ ከርቤ †††

††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"

ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::

በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::

የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል::

አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል::

††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::

በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው::

††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ †
††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::

††† ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና †††

††† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::

በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::

በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::

አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::

ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::

††† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::

††† መስከረም 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
2.ብዙኃን ማርያም
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 14:28


እንኳን አደረሳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን

" ንግስቲቱ#ግሸን_ደብረ_ከርቤ "

ከደሴ ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ 82 ኪሎ ሜትር በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው ዳግማዊት እየሩሳሌም በመባል የምትታወቀው ግሸን ደብረ ከርቤ ከእምነትና ከአስተዳደር ጋር የተቆራኙ ታሪኮችን ይዛለች፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ያሳተመው የቱሪዝም ማውጫ እንደሚያትተው ግሸን ማርያም የተቆረቆረችው በ517ዓ.ም በአጼ ካሌብ የክርስትና አባት የሆኑት አባ ፈቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ናቸው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሔር አብን ጽላቶች ከሃገረ ናግራን /ከዛሬዋ የመን/ ይዘው ረጅም ጉዞ ተጉዘው አቀበቱን መንገድ አጥተው ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተንጣሎ በማየታቸው ቦታውን ሲያደንቁ ይህስ ‹‹አምባ ሰል›› ነው ያሉ ሲሆን ስል ማለት በአረበኛ ማር ሲሆን ትርጉሙ የማር አምባ ማለት ነው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ ሁለት ጎጆዎች አሰርተው ያመጡትን የአብና የድንግል ማሪያምን ጽላቶች በማስገባት እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይነገራል፡፡

አምባው በተፈጥሮው ቀራጺ ባለሙያ የሰራው መስቀል የሚመስልና ወደ አምባው ለመውጣት ከአንዲት በር በስተቀር እንደ ምሰሶ የተቀረጸ ገደል ያለበት ነው፡፡

ይህችም በር በአጼ ኃይለ ስላሴ በጠፍጣፋ ድንጋይ ደረጃ ከመስራቱ በፊት አምባውን ለመውጣትና ለመውረድ በገመድ ወይም በመጫኛ ወገብ ታስሮ ነበር፡፡

ግማደ መስቀሉ ተቀብሮበታል ተብሎ የሚታመነው የእግዚዓብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን በአጼ ዘርዓያዕቆብ እንደገና የተሰራ ሲሆን በዳግማዊ ሚኒሊክም ታድሷል፡፡ በውስጡ በርካታ ኃይማኖታዊ ታሪክ ያላቸው ስዕሎችና ቅርሶች አሉት፡፡

ደብረ ነጎድጓድና ደብረ እግዚዓብሔር በመባል ትጠራ የነበረቸው የግሸን ማሪያም በአጼ ዘርዓያዕቆብ እህት እማሆይ እሌኒ በኋላም በአጼ ኃይለ ስላሴ ባለቤት እቴጌ መነን ታድሳለች፡፡ ከዚህ ኃይማኖታዊ እምነት በተጨማሪ የግሸን አምባ ከመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ካቋቋሟቸው የፖለቲካ ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛው ነበር፡፡ የግሸን አምባ እንደ ቤተ-መንግስት ወህኒ ቤትነትና በተቋምነት ተቋቁሞ የነበረው ከአጼ ይኩኖ አምላክ በኋላ ነው፡፡

ግሸን በየዓመቱ መስከረም 21ና ጥር 21 ቀን እጅግ በጣም በርካታ ምዕመናን በተገኘበት ትከበራለች፡፡ 

እንኳን አደረሳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ
የአመት ሰው ይበለን
የግሸኗ እናቴ ናፍቀሽኛል
ፈቃድሽ ሁኖ አንዴ ደጅሽን ረግጨ ነበር
ድጋሜ ሀገራችን ሰላም አርገሽ ለደጅሽ አብቂኝ እናቴ

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 14:27


Channel photo updated

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 14:24


ማዕዛሽ ናፈቀኝ የግሸኗ ንግስት
እንደ ምግብ እራብሺኝ
እንደ ውሃ ጠማሺኝ
የግሸኗ ማርያም ሐገራችንን ሰላም አድርጊ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ጠብቂ
ደጇን ለመርገጥ ያብቃን
🙏🙏🙏

መላኩ@-Halemikae

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

30 Sep, 14:23


የመስቀል ቅርፅ አለው የተራራው እራስ
ሁሉም ይናፍቃል እዛ እስኪደርስ

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

28 Sep, 19:52


​​☦️ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

☦️ ቅዱስ ዕፀ መስቀል፦ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት: ከሰይጣን ባርነት: ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል።

☦️ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ "እንዳለ ሊቁ። ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት።
➡️ እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6): ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12): ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ. 48:14): ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር (ዘጸ. 14:15): የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል።

ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል። (መዝ. 59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል።

ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
➡️ አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል። የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና።

➡️ ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል።

➡️ በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል። ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም።

☦️ በዓለ መስቀል መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም።
➡️ መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ270 ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት ተራራ ሆነ።

➡️ ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ (ሔለና) በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች።

➡️ መስከረም 17 ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት 10 ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል። ከ10 ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም 17 ቀን ተቀድሷል።
☦️ ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ (ግሸን ማርያም) ተለብጦ ተቀምጧል።


☦️ አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን።
            ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
            Join
            ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

26 Sep, 01:39


"  መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው ፤ የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው ፤ መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው ፤ የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው፡፡

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደ እርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው፡፡
መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው፡፡ መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው ፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው፡፡

መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው፡፡
መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው፡፡
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም
ነው፡፡ "
🌸ውዳሴ መስቀል 🌸



join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

26 Sep, 01:38


"እስኪ ርእሱን ከዕፁ ወደ ሌላኛው ዕፅ እንቀይር፤ (ዘፍ. 2፡17)፤ ከዕፀ በለስ ወደ ዕፀ መስቀል።(ገላ. 6፡14)። አስታውሱ ያኛው ዕፅ ሞትን አመጣብን፤ ይኽኛው ግን ሕያውነትን አደለን። ያኛው ከገነት አስባረረን፣ ይኽኛው ወደ ገነት መራን። ስለዚህ ኹላችንም በዚኽ ሕይወትን በሚሰጠው ዕፅ (ቅዱስ መስቀል) ጋሻ ራሳችንን እናስታጥቅ!"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳች ✝️✝️✝️

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Tewahdotisfafa  
@Tewahdotisfafa

☝️ይቀላቀሉን☝️

ተዋህዶ_ቤተ_ሚዲያ

26 Sep, 01:29


🎵Argamee fanoon

🔊Faruu Masqalaa

Afaan oromo Haaraa

👇👇Join godhaa 👇👇👇
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@Guge21ko
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

React 👍🥰🥰

1,089

subscribers

1,643

photos

98

videos