Business Hub/ፈላጊ @bete1912 Channel on Telegram

Business Hub/ፈላጊ

@bete1912


Discover a variety of business idea tailored to all budgets from small investment to large-scale venture.

ፈላጊ

ፈላጊ (Amharic)

ፈላጊ ብንተርስ አና ማግኛ ቦታዎች ለገንዘብ መጠን በሚሰሩበት አነስተኛ እና ለመጠነኛ ግዜ በመግባት ለዚህ፣ ለከፍ ባለዊና እና ለሌሎች የቢዝንስ ሀሳቦች ማግኛ ቦታዎችን ተገኝቷል። ይህ ከፍ ማድረግ እና ለአዲስ መጠን እንዴት ማግኛት እንደሆነ የመዝግብ እቅዶችን መተግበር ካልቻለ ያስፈልጋል። ፈላጊ እንዲሁም ስለተጎናጎና በዚህ ጣቢያ ተጠቃሚ ይሆናል።

Business Hub/ፈላጊ

26 Nov, 18:38


https://t.me/thoughtsinmind

Business Hub/ፈላጊ

30 Oct, 16:00


Tutor Service (የማስጠናት አገልግሎት)

👨‍🏫 በስራቹ ብዛት ያላቸውን አስጠኚዎችን በመሰብሰብ አገልግሎቱን ከሚፈልጉ ወላጆች ጋር ማገናኘት ፤ በስራቹ ካሉት አስጠኚዎችም ከ15-25% ወይም በስምምነት ከሚከፈላቸው ክፍያ በየወሩ ድርሻ ይኖራቹሀል።

👨‍🏫 የእናንተ ትልቁ ስራ ሚሆነው ብቃት ያላቸውን አስጠኚዎች መሰብሰብ እና ፈላጊ ወላጆችን ማግኘት ነው።

👨‍🏫ስራው እጅጉን አትራፊ እና ኪስ የማይጎዳ መነሻ ገንዘብ ስለሚጠይቅ ብትሞክሩት ትጠቀማላቹ።

👨‍🏫 ይህን አገልግሎት ሚፈልጉ ወላጆች ጋር እንዴት ልድረስ ሚለው ? የስራው ዋና ፈተና ነው ፤ ፈተናውን ማለፍ የቻለ ጥሩ ገንዘብ ይሰራል።

👨‍🏫 ትምህርት ቤቶች አከባቢ Connection ያላቹ ሰዎች የተወሰነ ያህል ስራውን ያቀልላቿል።

      ሼር

Business Hub/ፈላጊ

28 Oct, 16:47


Crochet (የእጅ ስራ)
🪡 በ 3000 ብር መነሻ ገንዘብ[Maximum] ሊሰራ የሚችል ስራ ነው Crochet ወይም የእጅ ስራ።
🧶 ክሮችን በመጠቀም በተለያየ ዲዛይን እንደ ልብስ ፣ ኮፍያ ፣ እስካርብ ወ.ዘ.ተ በመስራት ለሱቆች ማስረከብ ወይም በራሳቹ መሸጥ ትችላላቹ። አሁን ለይ ልብስ ምን ያህል እንደ ተወደደ ሚታወቅ ነገር ነው ፤ ስለዚህ ገዢ በደምብ ይኖራል ጥርት ያለ ምርት እስከሆነ።
🧵 ሙያውን ለመልመድ ያለምንም ክፍያ YouTube መጠቀም ትችላላቹ።

🛠 ለስራው ሚስፈልጉ እቃዎች 🛠

🪡ኪሮሽ (Hook):ከ 70-100ብ💰

🧶ክር :እንደ ምሰሩት ምርት ይለያያል ለልብስ እና ለምንጣፎች ምትጠቀሙት የክር አይነት ይለያያል እናም ከ 100-350 ብር 💰[በሜትር 10ብር]

❗️ዋና ግብዓቶች እኚ ናቸው ፤ እንደ ምትሰሩት ዲዛይን ግን ምርቶቻቹን ለማስጌጥ ምትገዟቸው ነገሮች ይኖራሉ።

ሊገጥማቹ ሚችል ፈተና 🫨

🩻 ብዙ ሰዓት ተቀምታቹ መስራት የግድ ስለሆነ የጀርባ እና አንገት ህመሞች ይኖራሉ።
🌝 ከገበያ አንፃር ገዢ አለማግኘት ፣ የት መሸጥ እንዳለባቹ አለማወቅ ፣ ገበያቹን እንዴት መዘርጋት እንዳለባቹ አለማወቅ። Marketing & sales ጉዳይ ነው !።

🧶 በ Crochet ስራ ውጤታማ ይሆናል ብላቹ ለምታስብት ሰው ላኩለት።

ፈላጊ

27 Oct, 09:59


በ አነስተኛ ፣ በ መጠነኛ እና ከፍ ባለ የመነሻ ገንዘብ ሊሰሩ ሚችሉ የቢዚነስ ሀሳቦችን ከሙሉ መረጃ ጋር አዘጋጅተን ጨርሰናል ።

ከ 1000ሺ በላይ የቢዝነስ ሀሳቦች እናንተን ይጠብቃሉ። የመለወጥ ፍላጎት ያላቹ ሰዎች ብቻ ቤተሰብ ሁኑን!

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

05 May, 00:58


ተነስቷል !!❤️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓል!!

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

13 Apr, 05:15


📜የሰው ልጅ ሕልውና ምድር ላይ ሀ ብሎ ሲጀምር ጊዜ አሀዱ ብሎ መቁጠር እንደጀመረ ይገመታል። ምክንያቱም ሰው ከመፈጠሩ በፊትና ከሞተ በኋላ ስላለው አያውቅም፣ስለዚህ ህልውና ሲጀምር ጊዜ ጀመረ ፣ጊዜ ማለት በእጅ ውስጥ ያለ ነው። ትናንት አልፏል። ነገም ደግሞ አያስተማምንም። ስለዚህ ጊዜ ዛሬ ነው። በተለይ ደግሞ አሁን ።

📜ልማድ ብቻ ይዘን የትም ልንደርስ አንችልም፣ ባዶ ኩራት ይዘን እንቀራለን፣ ህልውናን መገመት ያለብን በስራ እንጂ በእድሜ: በሀሳብ እንጂ በትንፋሽ፡ በስሜት እንጅ በከንቱ የሚባክኑ ደቂቃዎች አይደለም ፣ ጊዜን የምናሰላው በልብ ትርታ መሆን አለበት።በስራ የማይገልጡትን ነገር በአፍ ብቻ መናገር ምላስን ማባለግ ነው።የባለገች ምላስ ህሊና ላይ ታምፃለች። እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሰሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል ወና ቤት መሆን ነው።

📜ከተማራችሁት ወጣቶች የሚጠበቀው'ኮ ያገሪቷን ችግር በጥሞና አስተውላችሁ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ነው፣ ለግልቢያውማ ማሀይምስ ብልጭ ካለበት ይጋልብ የለም እንዴ! ወደፊት ልንራመድ የምንችለው በወሬ በፍልስፍና በስራ በማይገለጥ የመፅሀፍ እውቀት አይደለም። ስርየታችን ስራ ነው፣ ስልጣን ይዞ በመኮፈስ ስልጣንን እንደ እውቀት በመቁጠር፣ ስልጣንን እንደ ሃላፊነት ሳይሆን እንደ መብት በማየት አይደለም በስራ እንደገና መወለድ ያስፈልጋል።

📜የኔ ጥሪ ስራ ነው። መናገር አላውቅም። ያ የጥሪ ሰዓት ሲደርስ በቆራጥነት መነሳቱ ሀጢያት አይደለም። ከማፍረስ መገንባት ፤ ከብዙ ምልልስ ትንሽ ስራን ፤ ከበቀል ይቅርታን ፤ከጥላቻ ፍቅርን ፤ ከማይምነት እውቀትን እመርጣለው።

በዓሉ ግርማ

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

11 Apr, 08:16


💔 ወርቃማው ጥገና!

💔በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡

💔ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡ “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና!

💔ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡

💔በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡

❤️ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡
 
Beauty can be found in imperfection.

              ዶ/ር እዮብ ማሞ
@bete1912
@bete1912

       

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

09 Apr, 06:00


🪽በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።

  🪽መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።

 🪽ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።

🪽ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም።

ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።

📖አርምሞ
@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

07 Apr, 06:29


🫧አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤  እጅ እና እግር እንደተጠፈረ  አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ።

🫧አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ።  መባተልን የምትመስልበት፤   የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ።

🫧አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤   የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤   ሰው ሁሉ  የጠላኽ የሚመስልህ ፤  ኃላ  የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ።

🫧አንዳንድ ወቅት አለ  ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ  የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት  ።

🫧እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ

እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ

🫧በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል  ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል።

                አድሃኖም ምትኩ
መልካም ሰንበት❤️

@bete1912
@bete1912
     

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

05 Apr, 04:41


💡ከዜሮ መጀመር ትችላለህ

📍ያለንን ነገር ሁሉ ብናጣ ፡ የተመካንባቸው ሰዎች ቢርቁን ፡ በሽታ ቢያሰቃየን ፡ የባንክ አካወንታችን ባዶ ቢሆን ፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢከሰቱብን ፡ ሁሌ ከዜሮ መጀመር ይቻላል።

እድሜያችን ቢገፋ እንኳን በልጅነታችን የተመኘነውን ማንነት በየትኛውም ጊዜ መገንባት እንችላለን ። ከኛ የሚጠበቀው ለመለወጥ ያለን ቁርጠኝነታችን ፡ ፅናታችን ፡ እምነታችንና ትዕግስታችን ነው። ማትኮር ያለብን ችግሩ ላይ ሳይሆን ወይም ስለችግሩ ማልጎምጎም ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት የሚረዱንን መሰረታዊ ጽንስ ሀሳቦች ቁርጠኝነት ፡ ጽናትና ፡ ትዕግስት ላይ ነው።

💡 የሕይዎትህ መለወጫ መሪ ያለው በራስህ እጅ ላይ ነው። ሌሎችንና ሌላ ጊዜን አትጠብቅ። ጊዜው አልፏል ብለህም አትቁም ፡ ያንተ ጊዜ አሁን ነው። ጉዳይህ ያለቀና ያበቃለት ቢመስልም አንተ ከጠነከርክ እንዲሁም ከልብህ ፡ እኔ አሁንም ተስፋ አለኝ ብለህ ከባዶ የመነሳቱ ድፍረቱ ካለህ ያኔ አንተ አንፀባራቂ ብርሀንን ታያለህ። ራስህንም ድሮ ከነበርክበት ባዶነት አውጥተህ እንደገና ሕይዎትን የመኖር ፅንሱን ውስጥህ ትፀንሳለህ።

ያኔ አንተ ተቆርጠህ ከተጣልክበት ትቢያ እንደገና አገግመህና ፡ አቆጥቁጠህ ትታያለህ። ልምላሜህም ከበፊቱ የበለጠ ይሆናል። ቅርንጫፎችህ ፡ ተቆረጡ እንጂ ዋናውን የሕይዎት ምስጢር የያዘችው አንተን ከአፈሩና ፡ ከውሃው የምታገናኝህ ስራህ አልተቋረጠችምና እንደገና ትለመልማለህ። እንደገና እራስህን በእድገት ምናብ ከዋጀኽው በድጋሚ ታብባለህ።

📍በድጋሚ ቀንበጥ ፡ ቀንበጥ የሆኑ የሚያስጎመጁ ፡ አረንጓዴ ቅጠሎችንና ፡ ቅርንጫፎችን ፡ ታቆጠቁጣለህ። ግመል በበረሓ ስትጓዝ በረሓው ላይ ውሃ እንደሌሌ ታውቃለች። ግን ወደ በረሓው እንድትገባና ፡ እንድትጓዝ ስናደርጋት ፡ ወደ ኋላ አታፈገፍግም ወይም አትፈራም። ምክንያቱም ፡ የሻኛው ጮማ ውስጥ በቂ የሆነ ምግብና ፡ ውሃ እንዳለ እርግጠኛ ስለሆነች እሷ የምትዘጋጀው ከበረሓው ፡ ከመግባቷ በፊት ውስጧ ምግብ በማጠራቀም ነው።

አንተም እንደ ግመሏ ውስጥህ ላይ አትኩር። ሌሎችን የበረሓው ግለት ፡ የበረሓው ንዳድ ፡ የበረሓው አሸዋና ፡ የበረሓው መጨረሻ መራቅ ተስፋ ቢስ ሲያደርጋቸው ፡ አንተ ግን ለድል አነሳሳቸው ፡ ውስጣቸው ያለውን የአሸናፊነት  ጮማ ፡ የተስፋ ጮማ ፡ የፍቅር ጮማ ሻኛ እንዳለ ንገራቸው። አንተ ከፊት ሆነህ ባለህ የዕውቀት ፡ የፅናት ፡ የትዕግስት ፡ ብረሀንህ ጉዟቸውን አቅልጥላቸው።

💡አንተ ራስህን ከምንምና ፡ ከባዶ አንስቶ ለትልቅ ደረጃ ፡ የሚያበቃ አቅም በውስጥህ አለ። አንድ ልታውቀው የሚገባህ ትልቅ ቁምነገር ፡ ዜሮ ፡ የቁጥሮች መጨረሻ ሳይሆን ፡ የቁጥሮች መጀመሪያ መሆኑን ነው። ያለህ ነገር ሁሉ ዜሮ የሆነ ከመሰለህ ፡ እንግዲያው አንተ ደስ ሊልህ ይገባል። ምክንያቱም ፡ በህይዎትህ ያለህ ደስታ ሁሉ ፡ ያለህ ሀብት ሁሉ ፡ ያለህ ዝና ሁሉ ፡ ያለብህ ገንዘብ ሁሉ ፡ ያለህ ተቀባይነት ሁሉ ፡ እንደገና ከዜሮ ፡ መጨረሻ ፡ ወደሌለው ቁጥር "ሀ" ብሎ ሊንደረደር ነውና !!!

        📓የኔ ስጦታ
ብሩክ የሺጥላ
@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

03 Apr, 04:26


🐶 ቅብጥብጡ ውሻ

🐶የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡

🐶በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡

የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡

🐶የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡

🐶ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡

ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .

🐶ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡

ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
   
ዶ/ር እዮብ ማሞ

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

01 Apr, 15:11


📚የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ መፅሀፍትን ለማግኘት: @book1912
🔎ፈልጋችሁ ያጣቹት መጽሀፍ ካለ ደሞ: @yabuka1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

01 Apr, 15:08


#ዝምታ🤫

የስኬትን ሀይል የተረዱ በዝምታ ውስጥ ሆነው አንገታቸውን አቀርቅረው ለህልማቸው እውን መሆን ይፈጋሉ ። የዝምታን ሀይል ያልተረዱ ደግሞ ሕልማቸውን ላገኙት ሰው ይናገራሉ ። በአከባቢህ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ ለአንተ ከፍታ መሰላል የሚሆኑ በተቃራኒው ደግሞ መሰላልህን የሚነቀንቁ። የዝምታ ሀይል እጅጉን ግዙፍ ነው ። ፀሀይ ምታበራው በዝምታ ውስጥ ነው ፤ የመሬት ዙረት ሚከናወነው በከባድ ድምፅ ታጅቦ አደለም ፤ ሰውነታችን ውስጥ የሚካሄደው የ ሕዋሳት ዝውውር በዝምታ ውስጥ ። በዝምታ ውስጥ ትላልቅ ተዐምራት ይፈጠራል ። ወዳጄ !! ከነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ማነስ የለብህም በዝምታ ስራ ስኬትህ እንደ ፀሀይ ማብራቱ እርግጥ ይሆናል!።

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

29 Mar, 22:44


samsung S 20 ⚡️
256GB
12GB RAM
Price : 42,000💰
Inbox: @yabuka1912 & @alicaso

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

28 Mar, 13:13


#share ለምታቋቸው ሰዎች

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

28 Mar, 08:44


#Notcoin

ብዙዎቻችን በነጻ ገንዘብ ስለሚገኝበት መንገድ ሲነገረን "መስሚያችን ጥጥ" ነው። ትክክል ነው፤ በነጻ የሚባል ነገር የለም።

በቴሌግራም #Notcoin የሚባል ዲጂታል ገንዘብ "በነጻ" ሰብስቡ ሲባል ጥቂት የማይባሉት ግድ ያልሰጣቸውም ለዛ ነው። ነገር ግን #Notcoin ነጻ አይደለም።

#Earn የሚለውን ስትነኩት 100 ሺህ እና ከዛም በላይ Notcoin የሚያስገኙ ተግባራት አሉ። ማስታወቂያዎች ናቸው። በእነዚህ ማስታወቂያዎች ቴሌግራም ከመቶ ሚሊዮኖች የሚበልጥ ዶላር ይሰበስባል። እናንተ ማስታወቂያ ያሰራው ድርጅት የማህበራዊ ሚዲያ ገዖችን  #Follow ስታደርጉ በ #Notcoin ክፍያ ትቋደሳላችሁ።

ቴሌግራም ደግሞ ለማስታወቂያ ገቢው ምክንያት በመሆናችሁ #Tab በማድረግ ተጨማሪ ዳረጎት ይለግሳችኋል።

በቅድመ ግብይት ከ 2.1 ትሪልየን በላይ ለሽያጭ ቀርቧል። ወደዚህ ሽያጭ ለመግባት ቢያንስ 10 ሚሊየን #Notcoin ያስፈልጋል።

አሁን አሁን ብዙ ኢትዮጵያውያን በቲክቶክ #ስለNotcoin እየተወያዩና እየሰበሰቡ ነው። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። ነገር ግን መሰብሰቡ ቆሞ በመደበኛ ዲጂታል ገበያ ለሽያጭና ለግዢ ለመቅረብ ከ #10 ያነሱ ቀናት ብቻ ናቸው የሚቀሩት። በእነዚህ ቀናት የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ኮይን ሰብስቡ።

ከታች ባለው ሊንክ ወደጨዋታው ስትገቡ premium ቴሌግራም ከሆናችሁ 50,000 በመደበኛው ደግሞ 2,500 ተጨማሪ #Notcoin ታገኛላችሁ።

https://t.me/notcoin_bot?start=rp_34346347

ጨዋታውን ስትጀምሩ በምስሉ እንደሚታየው ነው የሚመጣላችሁ። ከዛ የcoin ምልክቱን ደጋግማችሁ በመጫን ኮይን መሰብሰብ ትችላላችሁ።

TAP ከማድረግ በተጨማሪ በቀስት የጠቆምኩት ውስጥ በመግባት Taskኮችን በመፈፀም ኮይን መሰብሰብ ትችላላላችሁ።

ግድ የላችሁም ፤ ችላ አትበሉት !!!
https://t.me/notcoin_bot?start=rp_34346347

አሁን ለይ የ አንድ Bit coin ዋጋ 70,000 $ ደርሷል አጀማመሩም እንዲው እንደ Notcoin ነበር ። ለዛ ሞክሩት coin ሰብስቡ!!

ሶፍትዌር ኢንጂነር ሶፎንያስ አስቻለው

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

20 Mar, 14:39


🔺“ሰው - ራሱን እንኳ የሚያስደምመውን ተቃርኖ በውስጡ ተሸክሞ የማይፈራ።

“ሰው” -ጨክኖ መግደልን ከአፍቅሮ መግደል ጋር አስማምቶ ሲኖር እንቅልፍ የማያጣ።

ሰው' -ሰፍሮ ያልጨረሰው መሬት ቢጠበኝ ብሎ የሚሰፋ።

“ሰው -የስጋ ደካማነቱን ማካካሻ ከምናቡ ቆርጦ፥ በስራው፣ በሰራው እና በሚሰራው፤ ደካማነቱን የረታ፣ የሚረታ።

“ሰው -የማያቋርጥ የተቃርኖ ጅረት፣ የማይጠግ ጥበብ ምንጭ፤ የፍርሀት ልጅ፣ የድፍረት ወላጅ።

“ሰው - ምንነቱ ከማንነቱ የተምታታ፤ ምንነቱ ማለቂያ ቢስ፣ በማንነት የሚታሰር።

ሰው ፥ ይህ ሰው! እንዴትና በምን ?” ምንስ ሆኖ ?” ራሱን፣ ማንነቱን፣ ሰው-እነቱን ረሳ ?! ከዚህ በላይስ ምን ይገርማል !

📍ለማንኛውም ካላስታወሳችሁ አይፈረድባችሁም፡፡ ራሱን የረሳ ሰው፥ ሌላ ነገር አስታውስ ተብሎ ሊጠየቅ አይገባም፡፡ ግን ለምን አይገባም ?” ባይገባም፣ ባይገባም ግን ይጠየቃል፤ ይጠይቃል፣ ይመልሳል። የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን፣ የኖረውን ሳይሆን የተነገረውን፣ እውነቱን ሳይሆን የተባለውን ይመልሳል።

ሰው መሆን በጣም ይደንቃል። ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ወንድ መሆኑን ግን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ነጭ ወይም ጥቁር መሆኑን ሲያስታውስ አይደንቅም ?”

መሬት ላይ የተፈጠረ ሰው፥ መሬትን ረስቶ ሀገሩን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ከሌላው ጋር መግባቢያ ቋንቋ እንዳለውና ይህም ደግሞ ከየትኛውም ፍጡር እንደሚለየው ረስቶ፥ መናገሪያውን ማስታወሱ አይደንቅም ?”

ብትረሱም አልፈርድባችሁም። ዞሮ ዞሮ ምንም ነገር እንዳለኝ ወይም እንደነበረኝ ያወቅሁት፥ ሳይኖረኝ ሲቀር ነው። እናትም፣ ቋንቋም፣ ሀገርም፣ አያትም፣ አባትም፣ ሃይማኖትም ሁሉም፡፡

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

22 Feb, 07:10


ራስን በማየት ሰው ያድጋል፤ ሌላውን በመውቀስ መኖር ሰው መሆንን ይቀማል። ሰውነቱን ያጣ የሚያወራበት ቋንቋ ጩኸት ይበዘዋል፤ እንደወይፈን ያተራምሳል።

ሰው መሆንን የሚያስብ ትርምሱ ወደ ራስነቱ ስለሚሆን ሌላውን አይወጋም። ራሱ ላይ ይፀናል። ራሱን ያላየ ሌላን እንዴት ያያል? አየን ብለን ስለማናይ ሰርክ ከበጎ ይልቅ ክፉ እንጋግራለን።

ከመማር ይልቅ ማስተማር እንመርጣለን። ከራስ ገመና በላይ የሌላውን እንጮሃለን። ራሱን አይቶ ያልጨረሰ ሌላን እንዴት አየሁ ይላል? ሰው ራሱን ማየት የሚደርሰው (የሚቋጨው) በሞት ከፈን ሲታቀፍ ነው።

ስለዚህ፦ ሌላውን ከመቁጠር ራስን ማበጠር ቢቀድምስ? ያልተጋገረ አይበላም። በርሚል ሊጥ ያው ሊጥ እንጂ የእንጀራ ዋጋ የለውም። ሊጡን በእንጀራ ሰፍረን አንተርጉም። ዝምድና ቢኖራቸውም ልዩነታቸው ግን ይሰፋል።

ቡርሐን  አዲስ ✏️

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

02 Feb, 06:51


🟨ሕይወት ሁላችንም ላይ ጫናዋን ማሳረፏን
አታቋርጥም፡፡
ከፊሉ ተስፋ ይቆርጣል.፤ከፊሉ
ይታገላል፤ከፊሉ ከዚያ መማር ያለበትን ነገር
ይቀስማል፡፡
ሕይወት ያዘጋጀችልንን ትምህርት
በአግባቡ በተማርን ቁጥር በአግባቡ
እንሰራለን፣ካልሆነ ግን የሕይወት ጫና
ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፣

የመጀመሪያዎቹ ሕይወት ጫና
ስትፈጥርባቸው ዝም ብለው የሚመለከቱ
ሲሆኑ ሁለተኞቹ ግን ለጫናው በብስጭት
ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡

እኛስ ከየትኞቹ ነን ብለን ራሳችንን እንጠይቅ

@bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

26 Jan, 07:27


samsung s21  ultra  ⚡️
128 GB
12 GB RAM
1 SIM

Unpacked
Price : 43K

Inbox : @alicaso / @Yabuka1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

16 Jan, 09:26


ለፊልም አፍቃሪ ወዳጆቻቹ አጋሩ

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

16 Jan, 09:24


ሶስት የህይወት ታሪክ ፊልሞችን ልጋብዛችሁ።ነጮች ጀግኖቻቸውን መፅሀፍ በመፃፍ፣ፊልም በመስራት ፍቅራቸውን ይገልጻሉ።ዘለአለማዊ ያደርጓቸዋል።

ስቴፈን ሀውኪንግ-ሙሉ ለሙሉ ሽባ ያደረገው፣መናገርም እንዲሳነው ያስገደደው ህመም ታይቶ ”በቃ አንተ ከአሁን በኋላ አትጠቅምም“ አልተባለም።ይልቁንም ምርጥ ጭንቅላቱን ከቀረው አለም ጋር የሚያገናኝ ዘመናዊ እና ልዩ ኮምፒውተር ተሰርቶለት በquantum physics በተለይ ደግሞ ስለ black holes ጠቃሚ ጽንሰ ሐሳቦችን አበርክቷል።(The Theory of Everything)

ፍራንክ አበግኔል ጁኒየር—በ16 አመቱ ማጭበርበር ጀመረ።ከአምስት አመት በኋላም በ26 የተለያዩ ሀገራት 2.5 ሚሊዮን ዋጋ ያላቸውን የሀሰት ቼኮች ሳይታወቅበት መመንዘር ችሏል።በዚህም ግዜ ስምንት የተለያዩ ማንነቶች ነበሩት።ዶክተር፣ፓይለት፣ጠበቃ እንዲሁም የመንግስ ኤጀንት መስሎም ብዙዎችን አሞኝቷል።አሜሪካ ግን ይህ ሰው”ካሁን በኋላ አይጠቅመንም፤ረብ-ቢስ ነው ዋጋ የለውም“ ብለው ከእስር ቤት አላበሰበሱትም።ይልቁንም የተፈረደበትን ጥቂት የእስር ግዜ ሲጨርስ የFBI አማካሪ ሆኖ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች በየአመቱ የሚከፈለው የናጠጠ ሀብታም ሆነ እንጂ።እነሱ ምርጥ ጀግኖቻቸውን ማክበር ብቻ ሳይሆን አጥፊውን እንኳን አልሚ የማድረግ ብቃት አላቸው።ጥገኛ እና ኪራይ ሰብሳቢ ጀግናን ወደ ልማታዊ ጀግና የመቀየር ኃይል አላቸው።(Catch Me If You Can)

ጆን ፎርበስ ናሽ—ካደረበት የስኪዞፍሬና ህመም ጋር እየታገለ ለምጣኔ ሀብት የእውቀት ዘርፍ የሚጠቅም አስተዋጾ ያበረከተው ይህ የሒሳብ ሊቅ“እብድ ነው”ተብሎ አልተተወም።ይልቁንስ ከሌሎች ሁለት ሳይንቲስቶች ጋር የኖቤል ሽልማት ተበርክቶለታል(A Beautiful Mind)
ቴዎድሮስ ሽዋንግዛው እንዳሰ @bete1912
@bete1912

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

06 Jan, 21:24


ንጉስ ተወልዷል !!!

መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ

ፈላጊ

21 Apr, 11:00


Channel created