በ Comprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ዙርያ ከአባል ተቋማት ብቻ መረጃ ለመሰብስብ ባስተላለፍነው መልዕክት ዙሪያ ግልፅነት ስለመፍጠር፡-
1. ማህበሩ መረጃ ብቻ ነው እያሰባሰበ ያለው። ቅሬታ የመቀበልም የመወሰንም ምንም ስልጣን የለውም፡፡ የማህበሩ ዋና ሚና ከአባል ተቋማት ያሰባሰበውን መረጃ አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብና ተፈፃሚነቱ እና ግብረ-መልሱ ላይ ክትትል ማድግ ብቻ ዓላማ ያደረገ ነው።
2. መረጃውን ለመሰብሰብ የተፈለገው ከአባል ተቋማት(ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች እና ኮሌጆች) እንጂ ከተማሪዎች አይደለም። ስለዚህ ተማሪዎች ያጋጠማቸውን ችግር እየተማሩበት ባለው ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወይም ኮሌጅ እንዲያቀርቡ ያሳስባል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች የተናጠል (የግል) ጥያቄዎቻቸው ወደ ማህበሩ ማቅረብ የለባቸውም።
3. ማህበራችን አባል ያደረገው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቅሬታዎችና መሰል ጉዳዮችን አይቀበልም፤ አያስተናግድም።
ከአክብሮት ጋር!
የኢት/የግ/ከ/ት/ቴ/ሙ/ተቋማት ማህበር
ወቅታዊ መረጃዎችን👉
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/profile.php?id=61558414384952&mibextid=ZbWKwL
በቴሌግራም - https://t.me/ephetveta
በሊንክድኢን- www.linkedin.com/company/ephetvetia
በዌብሳይት www.ephetveta.com ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ!