☀️ኢስላም☀️ @mesud22 Channel on Telegram

☀️ኢስላም☀️

@mesud22


نفهم الكتاب والسنة بفهم سلفنا الصالح
Abu meryem

☀️ኢስላም☀️ (Amharic)

ኢስላም (የአማርኛ ጥሪ) በአዲስ ስም 'ኢስላም' የተጠቃሚ ችግር ተብዬ ገብተው ነው። ኢስላም በመተግበር ግንባታዎችን እና ምክንያቶችን በቴሌግራም በነበሩ ችግሮች ያሳያል። ኢስላም ያሉትን መንፈሳዊ ችግሮች ወደ እኛ ለመረዳት የሚፈፅሙልን አስተያየቶች ይታወቃሉ። ኢስላም መመልከት፣ ስህተት እና ስራው ስንትዮጵያዊ ነኝ ፡፡ በመሆን ኢስላም ወደ እርዳታ ማመልከት እና ሌሎች ትክክለኛ ነገሮች ተይዞ በአማርኛ እና ሰላም እንዲሁም አማርኛ ፡፡

☀️ኢስላም☀️

13 Jan, 13:13


ጊዜ አጠቃቀም

🎙 ሸይኽ ኤልያስ አህመድ

☀️ኢስላም☀️

13 Jan, 11:02


" መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " - ባለስልጣናት

በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አይታወቅም።

በሎስ አንጀለስ ዙሪያ 3 አካባቢዎች መቃጠላቸውን ቀጥለዋል።

በአሁኑ ላይ ትልቁ እሣት ሚገኘው በፓሊሳድስ ሲሆን 9307 ሔክታር መሬትን ሲያቃጥል 11 በመቶውን መቆጣጠር ተችሏል።

የኢቶን እሳት በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲይዝ ከ5665 ሔክታር በላይ አቃጥሏል። 27 በመቶው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከሞላ ጎደል በቁጥጥር ስር በዋለው በሃረስት እሳት 323 ሄክታር መሬት መቃጠሉ ታውቋል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች ትልቁን እሳት መቆጣጠር ቢጀምሩም ባለስልጣናት ግን ቀጣዮቹ ንፋሶች " አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

እሳቱ በአሜሪካ ታሪክ አውዳሚው ለመሆን መቃረቡ ተገልጿል።

የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።

ለሌላ በኩል ፥ የአደጋ ቀጠና ከሆኑ ቦታዎች ሰዎች እንዲወጡ የታዘዘ ሲሆን የወጡም አሉ።

ነዋሪዎች እንዲወጡ በታዘዙባቸው አካባቢዎች ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ 29 ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል።

ሰዎች ቤታቸው ለቀው ሲወጡ ሲዘርፉ የነበሩ በርካቶች ነበሩ።

ከዚህ ባለፈ ፥ በሰደድ እሳቱን ምክንያት አከራዮች በህገወጥ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭማሬ ማድረጋቸው ተነግሯል።

እሳቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ይጠየቅበት ከነበረው የቤት ኪራይ በሺዎች በመጨመር እንደተጠየቁ አንዳንዶች ገልጸዋል።

በሰደድ እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው አመድ ሆኗል። በርካታ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች " የማይቀምስ የቤት ኪራይ እና የሆቴል ክፍያ እየተጠየቅን ነው " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

☀️ኢስላም☀️

13 Jan, 05:22


እሳቷ ያገኘችውን እያነደደች ጉዞዋን ቀጥላለች። እየተምዘገዘገች ከካሊፎርኒያ ኒዮርክ ደርሳለች። አንቺ የአላህ ወታደር ሆይ ገስግሺ። አትጥፊ አትብረጂ። ወደነጩ ቤተ መንግስት ንጎጂ።


Mahi Mahisho

ቴሌግራም
👇👇

t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

☀️ኢስላም☀️

12 Jan, 18:41


#Update

እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ  ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።

እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወደሚሰሩበት " ሆሊዉድ " እየተቃረበ ነው ተብሏል።

በቀጣይ ቀናት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኛነት መተንበይ ባይቻልም ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

☀️ኢስላም☀️

12 Jan, 18:41


ትንሿ ወፍ የለኮሰችው እሳት ሰደድ ሆኖ አሜሪካን እያነደደ ሀገር ምድሩን ጉድ አሰኘ።

በእሳት ማጥፊያ ቴክኖሎጂ ቁጥር አንድ የሆነችው ሀገር ከ445 በላይ የእሳት አደጋ ሂልኮፍተሮቿን አሰማርታም እሳቱን መቆጣጠር አልተቻላትም። አለኝ ያለችውን ማክሸፊያ ሁሉ ተጠቅማ እስካሁን አላበረደችውም። ሌት ተቀን መንደድ ይዟል።

ክስተቱ አላህ በቁርአኑ ያወሳትን ወፍ ትዝ ያሰኛል ጠይረን አባቢልን!!

እንደሌሎች ወፎች እንደሌሎች አዕዋፋት በምድር ላይ ጎጆውን አይቀልስም። ከድንቢጥ ከፍ ከእርግብም አነስ ይላል። መልከ ጥቁር ነው። የገዘፉ ዓይኖቹ ጎላ ብለው ሰፋ ያለ አፉ ትኩረት ያሰጠዋል። እግሮቹ ላይ ያረፉት ትላልቅ ጥፍሮቹ ከትንሽነቱ ጋር አይመጣጠኑም። ግዙፍ ናቸው።

የአላህን ቤት ካዕባን ለማውደም ወደ መካ ያቀናውን የአብርሃ አል አሽረምን ሠራዊት ለማጥፋት ለታላቅ ተልእኮ ታጭተው የተሰጣቸውን ግዳጅ ሊወጡ የመካን ሰማይ እየሰነጣጠቁ ህዋውን አጥለቀለቁ። በቡድን ቡድን ከየአቅጣጫው እየጎረፉ ወደ ውስጥ ዘለቁ። አባቢል ተብለውም ተሰየሙ።

እያንዳንዳቸው በጀሃነም እሳት ውስጥ የተነከሩ ሦስት የሸክላ ድንጋዮችን ይዘው ዘመቱ። ሁለቱን በእግራቸው አንዱን በአፋቸው ታጥቀው በአብርሃ ሠራዊት አናት ላይ ለቀቁት። በአናታቸው ገብቶ በፊንጢጣቸው በኩል እየወጣ የውስጥ አካላቸውን አንድዶ አንፈራፍሮ ይገላቸው ያዘ። የሸሸም ወደ ኋላ ያፈገፈገም አልተረፈም።

ይህ ወፍ ከተልዕኮው በኋላ በቅፅበት እንደታየው ጠፋ። አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር እርሱን ማየት ብርቅ ሆነ። ካልያዙት በቀር መሬት አያርፍም። ካላደኑትም በቀላሉ አያገኙትም። የዚህን ወፍ እንግዳዊ አወቃቀር ለማጥናት የአሜሪካ ሳይንሳዊ ተመራማሪዎች እስካሁንም ያድኑታል።

የአብረሀ ቅሪቶች በዘመናቸው የአላህን ቤት አወደሙ። በትዕቢት የሙስሊሞችን ደም መጠጡ።  አላህም ምላሽ ሰጠ። ያውም በአንዲት ወፍ ከተማዋን እያነደደ አስጠነቀቀ። ይህ የቅጣቱ ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አለመሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ።

☀️ኢስላም☀️

11 Jan, 08:53


📌 የዱዓችን ተቀባይነት ማጣት ምክንያቱ ምን ይሆን?

ﻣﺮ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﺑﻦ ﺃﺩﻫﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍللّٰه تعالى ﺑﺴﻮﻕ ﺍﻟﺒﺼﺮﺓ ؛ ﻓﺎﺟﺘﻤﻊ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺇﺳﺤﺎﻕ: ﻣﺎ ﻟﻨﺎ ﻧﺪﻋﻮﺍ ﻓﻼ ﻳُﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻨﺎ؟

ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (رحمه الله) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦ ያ አባ ኢስሃቅ ዱዓእ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?

ﻗﺎﻝ: لإﻥ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻣﺎﺗﺖ ﺑﻌﺸﺮﺓ ﺃﺷﻴﺎﺀ!.

እሳቸውም፦ ቀልባችሁ (ልባችሁ) በአስር ነገሮች ሞታለች አሏቸው።

ﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻭﻣﺎ ﻫﻲ؟ ﻗﺎﻝ:

እነሱም፦ ምን ምንድ ናቸው? ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦

ﺃﻧﻜﻢ ﻋﺮﻓﺘﻢ ﺍللّٰه؛ ﻓﻠﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺣﻘّﻪ.
‏አንደኛ፡ አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።

‏ ‏ﺯﻋﻤﺘﻢ ﺃﻧﻜﻢ ﺗﺤﺒّﻮﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠّٰﻪ (ﷺ) ﺛﻢ ﺗﺮﻛﺘﻢ ﺳﻨّﺘﻪ.
‏ሁለተኛ፡ ነቢዩን (ﷺ) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፤ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።

‏ ‏ﻗﺮﺃﺗﻢ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﺑﻪ.
‏ሶስተኛ፡ ቁርኣንን አነበባችሁት አልሰራችበትም።

‏ ‏ﺃﻛﻠﺘﻢ ﻧﻌﻤﺔ الله، ﻭﻟﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺷﻜﺮﻫﺎ.
‏አራተኛ፡ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥّ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻋﺪﻭّﻛﻢ، ﻭﻭﺍﻓﻘﺘﻤﻮﻩ.
‏አምስተኛ፡ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።

‌‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺠﻨّﺔ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﻟﻬﺎ.
‏ስድስተኛ፡ ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ የሚሆን ስራ አልሰራችሁም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻨّﺎﺭ ﺣﻖ، ﻭﻟﻢ ﺗﻬﺮﺑﻮﺍ ﻣﻨﻬﺎ.
‏ሰባተኛ፡ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻤﻮﺕ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﺴﺘﻌﺪّﻭﺍ ﻟﻪ.
‏ስምንተኛ፡ ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።

‏ ‏ﺍﻧﺘﺒﻬﺘﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﻡ، ﻭﺍﺷﺘﻐﻠﺘﻢ ﺑﻌﻴﻮﺏ ﺍﻟﻨﺎﺱ، ﻭﺗﺮﻛﺘﻢ ﻋﻴﻮﺑﻜﻢ.
‏ዘጠነኛ፡ ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፤ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።

‏ ‏ﺩﻓﻨﺘﻢ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﺘﺒﺮﻭﺍ ﺑﻬﻢ
‏አስር፡ ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።

📙 ጃሚዑል በያን ዓልዒልም ወፈድሊህ፡ 2/12

☀️ኢስላም☀️

10 Jan, 06:05


በጋዛ  ወንድሞች እና እህቶቻችን መንገላታትና በቤቶቻቸው መቃጠል ሲሳለቁ የነበሩ የሆሊውድ ዱርየዎች የዘነጡ ቤቶቻቸው  ሲነድዱ እና እነሱም ሲነፋረቁ  ማየት ምንኛ ያስደስታል ?!!

አልሐምዱሊላህ  !!

አላሁ አክበር !! 

ገና አላህ ብዙ ያሳየናል - አንጠራጠርም !

አሜሪካን ያሉ ወንድሞች  እና እህቶችን አላህ ይጠብቃቸው

Muhammedsirage

☀️ኢስላም☀️

09 Jan, 13:59


የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄው 3 ነው። 1) ከወንጀል ተውበት ማድረግ 2) ዱአ ማድረግ 3) በሸሀዳ በውዱእ አዝካር ብሎ መተኛት
👉 ከዛ ውጭ መንግስትም በለው ማን መላሽ የለውም።

☀️ኢስላም☀️

09 Jan, 07:46


ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ተቋማት ማገዳቸው ሲገርመን ጭራሽ ህዝበ ሙስሊሙን ከአክሱም እናባርራለን እያሉ እየዛቱ ነው። የነዚህ ሰዎች ድን.ቁ ^ርና ደግሞ የተለየ ነው። ሙስሊሙ ምን በወጣውና ነው ለናንተ የእርስ በርስ ሽኩቻ ማወራረጃ የሚሆነው? ለምን በዚህ ዘመን የጅ.ል ፖለቲካ ትጫወታላችሁ?
IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

08 Jan, 11:27


🤲 በታላቁ አላህ ስሞችና መገለጫዎች ተማፅኖ ማድረግ ለዱዓእ ተቀባይነት ወሳኝ ነው!

ከቡረይዳ (📿) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦

ነቢዩ (📿) አንድ ሰው እንዲህ በማለት አላህን ሲማፀን ሰሙት፦

﴿اللهم إني أسألُك بأني أشهدُ أنك أنت اللهُ لا إلَه إلا أنتَ الأحدُ الصمدُ الذي لم يلدْ ولم يولدْ ولم يكن له كُفُوًا أحدٌ. قال فقال والذي نفسي بيدِه لقد سألَ اللهَ باسمِه الأعظمِ الذي إذا دُعيَ به أجابَ وإذا سُئِلَ به أعطى﴾

“‘አላህ ሆይ! (ጉዳዬን ትሞላልኝ ዘንድ) አንተ አላህና ከአንተ ውጪ ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን፣ አንድና ብቸኛ፣ የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ፣ ያልወለድክም ያልተወለድክም፣ አንድም ቢጤ የሌለህ አምላክ መሆንህን በመመስከሬ እማፀንሃለሁ።’ ይህን ግዜ ነቢዩ (📿) እንዲህ አሉ፦ ‘ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ! በርግጥም አላህን ትልቅ በሆነ ስሙ (መገለጫው) ተማፅንከው (ጠየከው)፤ የጠየከውን ዱዓእ መልስ በሚያሰጥና የጠየከውን የሚያሰጥ በሆነ።’”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 3475

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

06 Jan, 12:52


ወጣትነት እና የጊዜ አጠቃቀም
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
ዛሬ ምሽት 02፡30
በነሲሓ ቲቪ ይጠብቁን !!

☀️ኢስላም☀️

05 Jan, 05:09


ይህ በመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተ ክስተት ነው በትላንትናው እለት
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ
جَٰثِمِينَ
«ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡»  (አል አዕራፍ 7:78)

☀️ኢስላም☀️

04 Jan, 16:28


ፖለቲከኛ ሆደ ሰፊ ሲሆን ጥሩ ነው
~
በዚህ ባንዲራ ሰበብ ወንድሞች እየታሰሩ እንደሆነ ከአንድ ወንድም መረጃ ደረሰኝ። በዚህ ፖስት አንዱ ማስተላለፍ የፈለግኩት ነጥብ ይሄ ነው። ጥንቃቄ እንድታደርጉ።
በርግጥ ይህንን ባንዲራ እኔም አልወደውም። ይህን ብቻ ሳይሆን ቢጫውና ቀዩ ቀለማት የተጣመሩባቸው ባንዲራዎች ሁሉ የየትኛውም አካል ቢሆኑ አልወዳቸውም፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው።

ግን ፖሊቲከኞች (ፖሊሶች) በዚህ ሰበብ ሰዎችን ማሳደድ ለምን? መንግስትን በምትወክሉበት ስልጣን ላይ ሆናችሁ ግለሰባዊ የሚመስል እልህ ባታሳዩ መልካም ነው። በተለጠፈው ምስል በዋናነት ማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት "በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው በደል ይቁም። ፍትህ ይስፈን" የሚል ነው። በዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አይኑን የጨፈነ አካል ኮከብ አለ የለም እያለ ሰው ሲያሳድድ ማየት የሚገርም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

04 Jan, 11:11


🖋የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036

🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

04 Jan, 09:44


ትንሽ እንኳ አንደነግጥም አይደል⁉️

መሬት ደጋግማ እየተንቀጠቀጠች ነው። ይህ ከባዱ ማስጠንቀቂያ ነው። መሬት የተንቀጠቀጠችው ውስጧ እንዲህ እንዲያ ስለሆነ የሚለው የሞኝ ትንታኔ ወደ ጎን ትተን ሀሊቁ አላህን እንስማ ወደ እርሱም እንመለስ!

አላህ በቁርዓኑ አመፀኞቹ የነብዩላህ ሷሊህ (ዐሰ) ህዝቦች በመሬት መንቀጥቀጥ እንዴት እንደቀጣቸው ሲገልፅ:

فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
«ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡» (አል አዕራፍ 7:78)

ወደ አላህ ከመሸሽ ውጭ ምንም አማራጭ የለም። ወንጀላችን ሲበዛ፣ በደል ሲበዛ፣ የተበዳዮች እንባ ሲበዛ የአላህ ቁጣ መምጣቱ የማይቀር ነው። ተውበት በማድረግ ወደ አላህ እንመለስ፣ ሰደቃ በማድረግ የተቸገሩትን እንርዳ፣ የተበዳዮችን ይቅርታ እንጠይቅ፣ መበዳደል ይብቃን፣ ይቺ በሰከንዶች ለምትጠፋ አለም መስገብገብ ይብቃን

.....

☀️ኢስላም☀️

04 Jan, 03:57


ያ አላህ! ኸረ እንዳንጠፋ ኢስቲግፋር እናብዛ! ምንም ነገር ላይ ሆነን ኢስቲግፋር ማለት እንችላለን። አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይሂ!

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 16:10


እስቲ እንታረቅ❗️

🔅ምድር የሰው ልጆች ሆይ በቃኝ! ከዚህ በላይ አልታገሳችሁም!ከዚህ በላይ እኔ ላይ በሰላም መኖር አትችሉም!  ግፋችሁ በዛ!ከስሬ አድርጌ የዋጋችሁን እሰጣችኋለሁ! እያለች ይመስላልና እስቲ ወደ አላህ እንመለስ!

🔅እርሱ ይቅር እንዲለን እኛም ይቅር እንባባል/አውፍ እንባባል!

🔅አላህ እንዲታረቀን እስቲ እኛም እንታረቅ!

  🔅 መሪና ባለስልጣኖቻችንም
በየቦታው  እየፈሰሰ ያለውን ደምና የተበዳይ እምባን ለማስቆም ከመቼውም በላይ ጥረት ያድርጉ!

🔅ምድር እንደወትሮዋ ቀጥ ብላ እንድትቆምና ያለ ስጋት እንድንኖርባት ግፍና በደልን ከምድራችን ላይ እናስቁም።

🔅የዛሬ የጁሙዓ ልዩ ዱዓችን ላይም የሀገራችን የሰላምና ፍትህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ ያተኮረ ብናደርገው መልካም ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ጁሙዓ ረጀብ 3/1446 ዓ.ሂ

@ዛዱል መዓድ

🔹🔸🔹🔸🔹🔸

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 08:11


የአማን አሰፋ ጀናዛ ታጥቦ ተከፍኖ ከእናቱ ቤት ወደ አወሊያ በማቅናት ላይ ነን አወሊያ እንገናኝ

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 08:09


ከአማን አሰፋ(ረሂሙላህ)......ብዕሮቹ ካሰፈሯቸው መፅሀፎቹ ውስጥ
“አምላኬ ሆይ! በኃያልነትህና በልቅናህ እምላለሁ፡፡ በዚህ በማደርገው ጂሃዴ ይህቺን ጠፊ ዓለም አልሻበትም፡፡ ይልቁንም ከምንም በቀር ያንተን ውዴታና ውዴታ ብቻ እሻበታለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ! ባንተ መንገድ ወደሚደረገው ጂሃድ በመምራት አክብረኸኛል። ባንተ መንገድ በሚደረግ ጂሃድ ላይ የመሞትን ክብር ጨምርልኝ"
በሠይፎች ጥላ ሥር ............

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 04:23


የአማን አሰፋ ክቡር ገላ ሚኒሊክ ሆስፒታል ደርሷል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ጠዋት አወሊያ ታጥቦ እዚያው አወሊያ ተሰግዶበት ኮልፌ ክቡር ገላው ያርፋል ኢንሻ አላህ።

በአላህ መንነድ ሲታገል ከርሞ በፆመኛ አንጀቱ አላህን የተገናኘውን ሙጃሂድ ገጣሚና ፀሐፊውን አማን አሰፋን እንሸኘው


  

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 04:22


ያኔ በ"ድምፃችን ይሰማ" ጊዜ ጂهاዳዊ ሓረካት ፊልም ተሰርቶ ታስሮ የነበረውን ወንድማችን አማን አሰፋ ልንዘይር ሂደን አጊኝቸው ነበር። እርጋታው እና ለዲኑ ያለው ፍቅር top flight ነው። رحمة الله عليه

بإذن الله في زمرة الشهداء والمتقين

ነገ በአላህ ፈቃድ አወሊያ ተሰግዶበት ኮልፌ ይቀበራል

☀️ኢስላም☀️

03 Jan, 03:47


ጂሀዳዊ ሀረካት በሚል በ2004 በተሰራው ቪድዮ ላይ ሽብርተኛ ተብሎ Etv ላይ የቀረበው ወንድማችን አማን አሰፋ ዛሬ ወደ አኺራ መሄዱን ሰማን! አሏህ ቀብሩን የጀነት ጨፌ ያድርግለት!

እኛ የአሏህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን!

☀️ኢስላም☀️

02 Jan, 13:51


በትግራይ ክልል አንዳንድ ወረዳዎች ውስጥ ከአመታት በፊት ከሙስሊም እህቶቻችን ተቀምተው የተሰበሰቡ ሻሾች የሚቃጠሉበት የተለየ ቀን እንደነበር አሳምረን እናስታውሳለን ።

ክፋትና ጭቆናቸው እነሱን መልሶ ከመጉዳቱ ውጭ የትም እንዳላደረሳቸው የተመለከቱት አስተዳዳሪዎች ክፋታቸውን ሲያድሱት እንጂ ጥፋታቸው እየከለሱ ሲያርሙት ማየት ህልም ሆኗል ።
ክፋቱ የሚከረፋው ደግሞ ከወደ አክሱምና ዓድዋ አስተዳዳሪዎች የሚመነጨው ነው ።



https://t.me/Muhammedsirage

☀️ኢስላም☀️

02 Jan, 13:45


اللهم صل وسلم على نبينا محمد ..

☀️ኢስላም☀️

02 Jan, 11:57


የመጨረሻው ማረፊያችን
የነፍሳችንን ማረፍያ አዛኙ ጌታችን ጀነት ያርግልን

☀️ኢስላም☀️

27 Dec, 12:12


ዑመር (ረዐ) በንግድ ጉዳይ ላይ ሸሪዓዊ እውቀት የሌለው ሰው መነገድ የለበትም ይሉ ነበር። ስለዚሁ ሲናገሩም ❝ኢስላምን ያልተረዳ ሰው በገበያ ውስጥ ሊሸጥ አይገባውም። ካልሆነ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሪባ ሊበላ ይችላል።❞ ይላሉ።
(ሸሂድ አል-ሚህራብ 209)
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ደግሞ ነጋዴ ነው። ስለዚህ ከሁሉም አስቀድሞ ስለ ንግድ ማወቅ አለበት። ካልሆነ አውቆም ይሁን ሳያውቅ የአላህን ሃቅ ያጠፋና የዱንያንም በረካ ሊያጣ በአኼራም ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል።
ሰሞኑን ሸይኽ ኤልያስ ❝ገንዘብና ወለድ❞ የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። ይሄን መጽሐፍ ፈልጋችሁ አንብቡት። ይሄን የምለው ለማስታወቂያ ሳይሆን አንዴ በምታነቡት የዘላለም እውቀት ልታገኙ ስለምትችሉ ትጠቀሙበታላችሁ በሚል ነው።
በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
➤ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
➤ አት-ተውባ መጽሐፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
➤ አት-ተቅዋ መጽሐፍት መደብር (ቤተል)
➤ ዛዱል መዓድ መጽሐፍት መደብር (ፋሪ)
ዋጋ= 400 ብር

☀️ኢስላም☀️

26 Dec, 18:27


#ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

☀️ኢስላም☀️

26 Dec, 17:01


እንደ ሙስሊም መጠቀሙ ሐራም በሆነ ነገር መነገድ አይቻልም። ሙስሊም ነጋዴዎች በሐራም ነገር አትነግዱ። አላህን ፍሩ። በሐላል ተብቃቁ። በወንጀል መተባበር ወንጀል ነው።

እንዲህ አይነት የእምነታችንን አስተምህሮት ስናስተምር እንደ ፅንፈኝነት የምትቆጥሩ አካላት እረፉ። በናንተ ጓዳ ውስጥ ገብተን "ይሄ ይፈቃድላችኋል። ይሄ ደግሞ አይፈቀድላችሁም" አላልንም። ያወራነው ስለራሳችን እምነት ነው። ማንም ጋር አልደረስንም። በሰው እምነት ውስጥ ገብቶ ሐላልና ሐራምን ልወስንላችሁ ማለት ነውር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Dec, 12:32


ፍልስጤማውያን ያለቁት አልቀው የተረፉት ደግሞ በፈራረሰ መንደራቸው እንኳን የመኖር መብት ተነፍጓቸው በዚህ መልኩ ይንከራተታሉ። "የሰለጠነው" ዓለም አይኑንም፣ ጆሮውንም ደፍኖ እልቂት ወስኖባቸዋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ይመጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Dec, 04:38


ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች

ሙስሊም መሆን ወንጀል አይደለም

☀️ኢስላም☀️

25 Dec, 09:57


"ሒጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም" በሚል በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ናቸው። የክልሉ መጅሊስ የቻለውን ያክል ቢጥርም የሚሰማው እንዳጣ በደብዳቤ ገልጿል። እምነቱን ተንተርሶ የራስን ወገን የመጨቆን የከረመ በሽታ መቸ ይሆን የሚለቀን?ተማሪዎቹ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ 3 ሳምንት አልፏቸዋል፣ ለማትሪክ ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን መሙላት አልቻሉም። በዚህ አዳፋ ተግባራችሁ መጻፍ የምትፈልጉት ታሪክ ምንድን ነው?

☀️ኢስላም☀️

24 Dec, 13:32


አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ...

ገንዘብና ወለድ - እውነታ እና ብዥታ

በሸይኽ ኢልያስ አህመድ የተዘጋጀ በአይነቱ ልዩ ጥናታዊና ወቅታዊ መፅሐፍ

ዋጋ = 400 ብር

በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
1) ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
2) አት'ተውባ የመጻሕፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
3) አት'ተቅዋ የመጻሕፍት መደብር (ቤተል)
4) ዛዱል መዓድ የመጻሕፍት መደብር (ፋሪ)

الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!

☀️ኢስላም☀️

23 Dec, 08:54


🚫 ያጠፋችሁ ነበር!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ، وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ، فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ﴾

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ!  እናንተ ሀጢያት የማትፈፅሙ ቢሆን ኖሮ አላህ ያጠፋችሁ ነበር። ከዛ ሀጢያት የሚፈፅሙ ህዝቦችን ያመጣና በሀጢያታቸው ምክንያት አላህን ምህረት ይጠይቁታል እሱም ይምራቸዋል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2749

☹️☹️😭🙁😭🙁☹️🙁

🤖በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

22 Dec, 18:17


ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

22 Dec, 18:15


ትራንስፖርት ላይ ሆኖ የሶላት ወቅት እንዳያልፈው የሰጋ ሰው ምን ያድርግ?
~
1- በመጀመሪያ በወቅቱ ለመስገድ መጣር አለበት። ለምሳሌ ከመሳፈሩ በፊት መስገድ ከቻለ ይሰግዳል። ወይም ጉዞውን ቀደም ብሎ በመፈፀም ከዚያ ሶላቱን በወቅቱ ይሰግዳል። ባጭሩ እስከቻለ ድረስ ጉዞውን ከሶላቱ ወቅት ጋር በማይጋጭ መልኩ ያመቻች። ሾፌሩን አናግሮ ወርዶ የሚሰግድበት እድል ካለ የአፈፃፀም ስርአቶቹ ያልተጠበቀ ሶላት መኪና ውስጥ ሊሰግድ አይገባም። ስለዚህ ለሶላቱ ትኩረት ይስጥ።

2- በወቅቱ ለመስገድ ካልቻለስ? ጀምዕ ማድረግ የሚቻል ሶላት ከሆነ ለምሳሌ ዙህር እና ዐስር ወይም መግሪብ እና ዒሻእ ከሆኑ በማስቀደም ወይም በማዘግየት ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ወቅት በስርአት መስገድ ይችላል። ሙሳፊር ቢሆንም ባይሆንም። ወይ ወደ መጓጓዣው ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ ወይ ደግሞ ከመጓጓዣው ሲወርድ አዘግይቶ በስርአቱ ይሰግዳል። በስርአቱ ስል በወቅቱ ለመስገድ ብሎ መኪና ውስጥ አርካኖችን ሳያሟላ እንዳይሰግድ ነው።

3- ሶላቱ ጀምዕ ለማድረግ የማይመች ከሆነስ? ለምሳሌ የሱብሕ ሶላት ወቅት ሳይገባ ተሳፈረ። ወይም ከዙህር በኋላ ቀድሞ ያልታሰበ ጉዞ ጀምሮ ትራንስፖርት ላይ እያለ የዐስር ወቅት ሊወጣበት ሆነ። መኪናው ወቅት ሳይወጣ የማይቆም ከሆነበት ምን ያድርግ? ወቅቱ ሳይወጣ መኪናው ላይ ይሰግዳል። መኪናው ላይ መቆም ከቻለ ይቆማል። ካልቻለ በተቀመጠበት ሆኖ ይሰግዳል። ሩኩዕ እና ሱጁድ ለማድረግ ካልተመቸ ጎንበስ እያለ ይፈፅማል። ለሱጁዱ ከሩኩዑ ይበልጥ ዝቅ ይላል። ውዱእ ከሌለው ተየሙም ያደርጋል።

4- ቂብላን በተመለከተ በሙሉ ሶላቱ ወደ ቂብላ መዞር ከቻለ ለግዴታ ሶላት ቂብላን መቅጣጨት ግዴታ ነው። ካልቻለ ሶላቱ ሲጀምር ወደ ቂብላ ዙሮ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ መኪናው ቂብላውን ቢለቅም ባለበት ይሰግዳል።

(ሼር ብታደርጉት ባረከላሁ ፊኩም።)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

22 Dec, 18:12


ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሌሎችም ባጠቃላይ እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ለመስገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ከገጠማቸው ዙህርን እና ዐስርን በአንዱ ወቅት፤ መግሪብን እና ዒሻእንም እንዲሁ በአንደኛው በሚመቻቸው ወቅት መስገድ ይችላሉ። መንገደኞች ባይሆኑ እንኳ ማለቴ ነው። ስለዚህ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመግሪብ ሶላት ቀደም ብሎ 12:00 ላይ ለፈተና እንዲቀመጥ ቢገደድና የፈተናው ጊዜ እስከ ዒሻእ ወቅት የሚረዝም ከሆነ ፈተናውን ካጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ እንደገና ዒሻእን ይሰግዳል። ይሄ ሶሒሕ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ለተጨማሪ የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ድምፅ አያይዣለሁ።

ተጨባጭ ምክንያት ካልገጠመው ግን ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው መስገድ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِینَ كِتَـٰبࣰا مَّوۡقُوتࣰا }
''ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።" [አኒሳእ፡ 103]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

20 Dec, 07:49


አለም ችላ ብሎህ አንዲት የጌታህ አንቀፅ ታፅናናሀለች
😍 "አትዘን አላህ ከኛ ጋር ነው"😍
አላህ ከሱ ጋር የሆነው ከቶ ምን ሊያጣ

☀️ኢስላም☀️

20 Dec, 07:34


ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:-
من أحبَّ أن يلحق بدرجة الأبرار ، فلينو في كل يوم نفع الخلق فيما يسر الله من مصالحهم على يديه.
"የደጋጎች ደረጃ ላይ መድረስ የሚወድ በያንዳንዷ ቀን አላህ በሱ ሰበብ ባገራለት መጠን ፍጡራንን ለመጥቀም ያስብ።" [አልኢማኑል አውሰጥ: 1/609]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

19 Dec, 04:00


▪️ገንዘቤ!

🔻ከዐብደሏህ ኢብኒሽሺኪኪር - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ ነብያችንን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - { ألهاكم التكاثر } እየቀሩ ወደነሱ መጣው እናም እንዲህ አሉ ፦ " የአደም ልጅ ንብረቴ ንብረቴ ይላል ፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ከንብረትህ በልተሀው ያጠፋሀው ወይም ለብሰህ ያበሰበስከው ወይም ደግሞ ሰደቃ አውጥተህ ለአኺራህ ያሳለፍከው ካልሆነ በስተቀር ምን ንብረት አለህ? " (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

☀️ኢስላም☀️

18 Dec, 12:48


ዛሬ ዛሬ የብዙዎቻችን መነጋገሪያ ጭንቀት የሆነው የዋጋ ግሽበት
የኑሮ መክበድ ||
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ይበሉ
https://t.me/yeilyaswedaj

☀️ኢስላም☀️

18 Dec, 11:20


የሹዐይብ ጥሪ!
~
((وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ * بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُمْ بِحَفِيظٍ)
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡ አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡» [ሁድ: 85–86]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

17 Dec, 06:51


አሰላሙዋለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ እህት ወንድሞች እንደምን አላቹ ይህ ከላይ የምትመለከቱት ወንድማችን በህመም ምክንያት እየተሰቃየ ይገኛል ከጎኑ ማንም የለው የሚረዳው አድራሻውም ሁሉም ነገር በቪዲዬው ላይ ተቀምጧል የተቻላቹሁን እርዱት ሼርም አድርጉት ለወዳጅ ዘመዶች

☀️ኢስላም☀️

04 Dec, 08:28


የሸሪዓ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን እሴት የጠበቀ ተቋም አይደለም።

- የአመቱ ገብሬል የሚከበርበት
- መዝሙር የሚከፈትበት
-ለበአላት ቄጤማ የሚጎዘጎዝበት

ሙስሊሞች ለሸሪዓ ፍርድ ሲመጡ የሙስሊም ተቋም እንደገቡ የሚጠራጠሩበት ተቋም ሆኗል።

#ተሀድሶ
#Reformation

በኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተነሳ ሃሳብ

☀️ኢስላም☀️

04 Dec, 06:24


ጥያቄ፦ ለአጫሾች የሚሆን ምክር እንፈልጋለን።

መልስ፦ "አጫሾችን የሲጋራ ፋብሪካ ባለቤቶች መክረዋቸዋል።"

ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አልቡረዒይ
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

03 Dec, 12:27


የካሀዲያን የቴክኖሎጅና የፈጠራ ምጥቀታቸው ኩፍራቸውን ከማየት እንዳያግድህ ተጠንቀቅ ። በእምነታዊ እይታው ሁድሁድ የበለጠው ሰው ኸይር የለውምና።

አላህ ሁድሁድ ስለተባለው የሱለይማን ወፍ ሲተርክ እንዲህ ማለቱን አትዘንጋ፦

«እኔ የምትገዛቸው የኾነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡»
(አን ነምል 23)

ሁደሁድ የቢልቂስ ዙፋን ፣ የአገልጋዮቿ ብዛት የወታደራዊ አደረጃጀት ብቃቷና የፖለቲካዊ ስርአቷ  አወቃቀር አስደምሞታል። ዙፋኗ ርዝመቱ 40ሜ ፣ ስፋቱ 20ሜ ከፍታው 15ሜ ነበር። ለዚያውም ከንፁህ ወርቅ የተገነባና እግሮቹ ከአልማዝ የተሰሩለት።

600 ሴት አገልጋዮች፣ 100ሺ ምክትል አስተዳዳሪዎች አሏት ፤  በእያንዳንዱ መሪ ስር 1መቶ ሺ ተዋጊ ወታደር ያለበት፣ 312 አማካሪዎች ነበሯት እያንዳንዱ 12ሺ ሰው ይወክላሉ። ነገረ ጉዳዩዋ ቢያስደንቀው ታድያ «ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ፡፡» አለ ሁድሁድ።

ኢብኑ ከሲር ይህን ሲተረጉሙ እንዲህ አሉ ፦
« አንድ የተመቻቸ ንጉስ የሚያስፈልገው የዱንያ መጠቃቀሚያ ሁሉ የተሰጣት ማለት ነው» 

ትልቁ ሚስጥር ግን ከዚህ በኃላ ያለው ነው፦

«እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ሰይጣንም ለእነሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡» (አን ነምል 24)  አለ ።

ሁድሁድ በቢልቂስና በህዝቦቿ «ስልጣኔ» መገረሙ ኩፍርና ሽርካቸውን ከማየት አላገደውም!ተውሒድህ ሲፀዳና ወላእና በራእ ላይ አቋማዊ ስትሆን አእምሮህ ውስጥ ቀድሞ የሚታይህ ተውሒድና ተፃራሪው ሺርክ ነው።

ብሶትና ቁጭት ይዞትም እንዲህ አለ፦

«ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገ ልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል፡፡» (አል ነምል 25)

አሁን የተፈተንነው በዚህ እይታ ነው።

ሙስሊሙ የምእራባውያንን የቴክኖሎጅና የዱንያዊ እውቀት ምጥቀታቸውን ተመልክቶ ሺርክና ኢልሓዳቸውን መመልከት ስላልቻለ ህልሙ ሁሉ በዲቪም ሆነ በሲቪ ወደነርሱ መሰደድ ሆኗል።

ስለ ስልጣኔያቸው አውርቶ አይጠግብም ፣ ፊልማቸውን ሊኖረው ይመኛል፤ ቁርጣቸውን፣  አለባበሳቸውን ይኮርጃል።

እነርሱ ያሉበትን ቅንጡ ህይወት ባየበት ማስተዋሉ ግን በአላህ የካዱና በስነምግባር የዘቀጡ መሆናቸውን ማየት አልቻለም።

ከምትኖርበት አፓርታማ 75%ቱ  ሰዶማዊና ሰዶማዊት መሆናቸውን እያወቅክ ተመሳሳይ ፆታዎች በአንድ ቤት እየኖሩ እያየህ ምን አይነት ህይወት ልትኖር ትችላለህ?? ይህ ህይወት ነው እነርሱ ጋር ያለው።

ታድያ ሁድሁድ ለዚህ የዳረጋቸውን ትልቁን የስነምግባር ብልሸት ማየት ቻለ –በአላህ መካድ! 

ዑለማእ «ከኩፍር በኋላ ወንጀል የለም»  አሉ።

እያየን ወገኖቼ! አላህ ይምራን!
ismaiilnuru

☀️ኢስላም☀️

02 Dec, 06:19


የሶሪያ ነገር
~
የሶሪያ ተቃዋሚዎች ሰሞኑን በበሻር አልአሰድ መንግስት እና ተባባሪዎቹ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት እያደረሱ ነው። እየተዋጉ ስላሉት አካላት ጠለቅ ያለ መረጃ የለኝም። ሆኖም ግን ቢሆንላቸው ከበሻር የማይሻል የለም።
እስከዛሬ በነበረው ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሶሪያውያን አልቀዋል። በዚህ እልቂት ላይ የኢራንና የሩሲያ መንግስት ጦሮች፣ የሒዝበላት ጦር ሚና ከበሻር ጦር ብዙም የተለየ አይደለም። ሁሉም እጃቸው በንፁሃን ደም የተጨማለቀ ነው። አሁንም ሽንፈት ከገጠመ ከባድ እንደሚሆን ይገመታል። አላህ ያብጀው።

በርግጥ የተቃዋሚዎቹ አቅምና ዝግጅት ባይታወቅም የበሻርና የአጋሮቹ ተጨባጭ ከትናንቱ በብዙ መልኩ ይለያል። ከፊሎቹ የራሳቸው ጉዳይ በቂ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል። ከፊሎቹ ጡንቻቸው ዝሏል። ትናንት በሻርን ከውድቀት ያተረፉት ሩሲያ፣ ኢራንና ሒዝበላት በቀድሞው አቅማቸውና ትኩረታቸው መጠን አይደሉም። ቢሆንም በሻርን እንደ ዋዛ ችላ ይሉታል ተብሎ አይታሰብም። የጋራ ትብብራቸው ደግሞ ትርጉም ይኖረዋል። ራሺያ የአየር ድብደባዋን አጠናክራ ቀጥላለች። ከዒራቅ ጀምሮ የሺ0 ቡድኖችም እየተጠራሩ ነው። የበሻር መውደቅ እንደ ሀገር ለኢራን ትርጉሙ ከባድ ነው። ምናልባትም የመጨረሻዋ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል። በሊባኖስ፣ በዒራቅ፣ በየመን ያላትን ተፅእኖ ከማዳከም አልፎ ሊያጠፋው ይችላል። እንዲያውም አንድምታው ከዚህም ሊያልፍ ይችላል። ስለዚህ የሞት ሞቷን ትታገላለች እንጂ ለአፍታ ችላ አትልም።

ሒዝበላት ሙሉ ለሙሉ ተፍረክርኳል ባይባልም ክፉኛ ቆስሏል። ትናንት ሶሪያውያንን የጨፈጨፈበት አቅሙ በነበረበት መጠን የለም። ይሄ ጦርነት ግን ለሱ የህልውና ጉዳይ ነው። ከእስ ራኤል ጋር ካለው ጦርነት የበለጠ እንጂ ያነሰ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ አይጠበቅም።
ስለዚህ የኢራን መንግስት እና በተለያዩ ሃገራት ያሉ የሺ0 ቡድኖች በሻርን ለማትረፍ እስከ ደም ጠብታ ሊታገሉ ይችላሉ።
ስጋቴ ምናልባት ተቃዋሚዎቹ የረባ አቅምና መደራጀት ከሌላቸው አፀፋው ይበልጥ እንዳይከፋ ነው። አላህ የሶሪያን ህዝብ ከበሻር ይገላግለው። ኸይሩንም ይምረጥለት።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

29 Nov, 03:42


ረሱል በልጅነታቸው  አያታቸው ዐብዱልሙጠሊብ በህይወት ሳሉ መካ ላይ ድርቅ ተከሰተ። ዐብዱልሙጠሊብም አላህን ዝናብ ለመለመን ሰዎች ተሰብስበው  ወደ ሜዳ እንዲወጡ አደረገ። ከህፃናት መሃል ሙሐመድ ፊት ላይ ደመና የሚመስል ነገር ይታይ ነበር።ይህም ደመና መሰል ነገር ከፊታቸው ላይ ተገለጠና ዝናብ መዝነብ ጀመረ ተብሎ ተተርኳል።

አጎታቸውም አቡጣሊብ ይችን ክስተት በሚያስታውስ መልክ እርሳቸውን በማወደስ  ገጠመላቸው።

ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይህ!

☀️ኢስላም☀️

28 Nov, 09:14


በመጨረሻም የሸይኻ ፋጡማ ሙስሊም አይነ ስውራን ተማሪዎች ሶላታቸውን እንዲሰግዱ ተፈቅዶላቸዋል። ጉዳያቸው አስጨንቋችሁ በየፊናችሁ ለለፋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈላችሁ፤ አልሐምዱሊላህ

☀️ኢስላም☀️

27 Nov, 10:28


🤲ከአራት ነገሮች በአላህ ተጠበቅ!

ከአቡ ሁረይራ (▫️) ተይዞ፡ ረሱል (▫️) ከነዚህ ነገሮች ጥበቃ ይጠይቁ ነበር፦

﴿مِنْ جَهْدِ البلاءِ، ودَرَكِ الشقاءِ، وسوءِ القضاءِ، وشماتةِ الأعداءِ،﴾

“ከመከራ ብርታት፣ ከዘቀጠ ክፉ ዕድል፣ ከመጥፎ ፍርድ፣ በጠላት ከመሳለቅ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2707

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

27 Nov, 08:02


ቁርኣን ማዳመጥ
~
ኢብኑ ባዝ ረሒሙላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ቁርኣን የሚያዳምጥ ሰው የሚቀራውን ሰው በእያንዳንዱ ፊደል በመልካም ምንዳ ይጋራዋል። መልካም ምንዳ በአስር አምሳያዋ ትባዛለች።"
[ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ፡ 26/350]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Nov, 16:29


የሸይኻ ፋጢማ የአይነ ስውራን ት/ቤት ጉዳይን በተመለከተ መጅሊሱ አንድ እርምጃ መሄዱ መልካም ነገር ነው። ከንቲባዋ ይስተካከላል ብላ ቃል መግባቷን መጅሊሱ አሳውቋል። ጉዳዩን እንደሚከታተሉና እስከ ፍጻሜው እንደሚያደርሱት ተስፋ እናደርጋለን። የሁሉም ሙስሊም ጭንቀት የልጆቹ እንባ መታበሱ ነው። አላህ ሲስቁ እንዲያሳየን ዱዓችን ነው።

☀️ኢስላም☀️

25 Nov, 04:00


በቅርቡ…
ኢን ሻአ'ላህ
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ (hafizehullah)

☀️ኢስላም☀️

24 Nov, 16:01


ጫማህ እንኳን ዋስትና ያጣው ኢስላማዊ አስተዳደር ስለሌለ ነው

600ብር የገዛሀውን ጫማ በትንሹ በቀን 2,3 መስጅድ ከሰገድክ 5ብር ለጠባቂ ትከፍላላህ። በወር 150 ። በአመት 1,800። ጫማህ በአመቱ የሁለት ጫማ ዋጋ ይጨምራል። 

ልብ በል!  የገዛሃውን ጫማ ዳግም የተከራየኸው ዘራፊን ፈርተህ ነው። ዘራፊ የተበራከተበት ብቸኛ ምክንያቱ ደግሞ  እጁን እንዲሰበስብ የሚያደርግ አስተማሪ ቅጣት ስለሌለ ነው። ያ ቅጣት ደግሞ ያለው ኢስላም ውስጥ ብቻ ነው  ።

ርካሽ  ነገር እንዲህ ዋጋ ካስከፈለህ ነፍስና ንብረት ደግሞ ውድ ሀብቶች ናቸው። ዛሬ ላይ የሰው ደም እንዲህ ከጫማ በታች ዋጋ ያጣበትና  ስርአት አልበኝነት የነገሰበት  ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው። ይህም  የሆነው ዓለም  ከሸሪዐ ህግ ስላፈነገጠና ሸሪዐን አልቀበል ስላለ  ነው።

የቤተሰብና  የልጆችን ጉሮሮ ለመሙላት ሐላል ለመከሰብ የወጡ ነፍሶች ጭራሽ ቀለል ተደርገው እንደ ትንኝ ህይወት በአጭር ይቀነጠሳሉ። ዘራፊዎች በ“እስር”  ይቀጣሉ። ያልተፈቀደ የሰው ደም  እንዲሁ ሜዳ ላይ ይቀራል። ቤተሰብ ሌላ ችግር ውስጥ ይወድቃል።ልጆች የቲም ይሆናሉ፤ ሚስት ሌላ ሃላፊነት ሌላ ድካም ይከተላታል።

የሚገርም ነው ወላሂ ! ሰውን የገደለ ሰው በእስር ይቀጣል። ለሚገባው ሰውኮ ትልቅ ስላቅ ነው ። ጭራሽ አሁን ላይማ ዓለም ለገዳይ በ"ሰብአዊነት” የሚከራከርበት ተጨባጭ ላይ ደርሰናል። ሟች አንድ ጊዜ ሞቷልና ለገዳይ ይቅርታ ይደረግለት አይነት "እዝነት" ። እስር ማለትም ይሄው ነው። የሰውን ነፍስ የሚያክል ነገር አጥፍቶ እስር ማለት ሟችን ሁለት ጊዜ መግደል ነው  ። ለዚህም ነው ጥበበኛው የገደለን መግደል ህይወት ነው ያለው።

«ለእናንተም ባለ አእምሮዎች ሆይ! በማመሳሰል (ሕግ) ውስጥ ሕይወት አላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ (ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ)፡፡» (አልበቀራህ 179)

የሰው ልጅ የአላህን ህግ አልቀበልም አለ። የርሱ አምሳያ ሰዎች የደነገጉለትን  ህግ ተከተለ። አላህም ይህን ህግ ጃሂሊያ ሲል ሰየመው።

«أَفَحُكمَ الجاهِلِيَّةِ يَبغونَ ۚ وَمَن أَحسَنُ مِنَ اللَّهِ حُكمًا لِقَومٍ يوقِنونَ»

«የማይምንነትን ፍርድ ይፈልጋሉን ለሚያረጋግጡም ሰዎች ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው? »

አላህ ወንድማችንን ይዘንለት ።

የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru

☀️ኢስላም☀️

24 Nov, 04:06


ድሮ ላይ አንድ ሳምንት
7 ቀን ነበር ...
አላህ ሆይ እድሜያችንን ባርክልን! ከኛ የወደድክ ሆነህ እንጅ አትውሰደን!copy

☀️ኢስላም☀️

23 Nov, 06:33


🎈በሰላም ጀነት ትገባላችሁ!

የሰላም ሀዋሪያው ሰላም ወዳዱ ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላም (📿) ከሰላሙ አርበኛ ከውዱ ነቢያችን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላህ (📿) እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት አስተላልፏል፦

﴿يا أيُّها الناسُ ! أفْشُوا السلامَ، و أطْعِمُوا الطعامَ، وصِلُوا الأرحامَ، وصَلُّوا بالليلِ والناسُ نِيامٌ، تَدْخُلوا الجنةَ بسَلامٍ.﴾

“እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አብዙ፣ የተራበን አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች ሲተኙ በሌሊት ስገዱ፣ ጀነትን በሰላም ትገባላችሁ፡፡”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 2648

▪️▪️▪️▪️🔸🔸▪️▪️▪️▪️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

💬፦ https://bit.ly/41zEZkk

📷፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

📺፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

22 Nov, 12:33


ድካምህንም ስኬትህንም ዝምብለህ ላገኘኀው ሰው አትናገር
ለሁሉም ስሜትህ አጥር አድርግለት!!

☀️ኢስላም☀️

20 Nov, 09:30


🚫 የሞት አደጋ ለገጠመው!

“ኡሙ ሰለማ (📿) ረሱል (📿) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ትላለች፦ አንድ ባሪያ አንድ ሙሲባ (መከራ) ችግር በሚገጥመው ግዜ፦

﴿إنا للهِ وإنا إليه راجعونَ، اللهمَّ أجرْنِي في مصيبتِي واخلفْ لي خيرًا منها﴾

‘እኛ የአላህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን። አላህ ሆይ! ባገኘኝ መከራ ምንዳን ለግሰኝ። ከርሱ የተሻለንም ተካልኝ’ ካለ አላህ ለደረሰበት መከራ ይመነደዋል። ከርሱ የተሻለንም ምትክም ይለግሰዋል። ከዛ እንዲህ ትላለች፦ ባለቤቴ አቡ ሰለማ በሞተብኝ ግዜ ረሱል (📿) ይህን ዱዓ እንድል አዘዙኝ። አልኩኝ። አላህ በዚህ መከራ የተሻለን ረሱልን (📿) ተካልኝ (በትዳር አጣመረኝ)።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 918

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

18 Nov, 10:27


🎁 በተሰጠህ ፀጋ እገዛ ያድርግ…

ከአቡ ሰይድ አልሁድሪ (📿) ተይዞ፡ ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن كان معه فضلُ ظَهْرٍ، فَلْيَعُدْ به على مَن لا ظَهْرَ له، ﴾

“በግልፅ የሚታይ ፀጋ የተዋለለት ሰው። በግልፅ ላልተዋለለት ሰው እገዛ ያድርግ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1728

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

17 Nov, 12:31


መርካቶ ዛሬም ቃጠሎ ደረሰ እየተባለ ነው። ግራ የገባ ነገር። ለማንኛውም ነጋዴዎች አደጋውን በመከላከልም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ ላይ ማድረግ የምትችሉት ጥንቃቄ ካለ አስቡበት። እቃ መቀናነስ፣ በተለየ ትኩረት የሚፈልጉ በጣም ውድ እቃዎችን ወይም ዶክመንቶችን ማራቅ ሊሆን ይችላል። ብቻ የሚቻላችሁ ካለ አስቡበት። መርካቶ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያላችሁ ትኩረት አድርጉ።
የተጎዳችሁን አላህ ይተካችሁ። ሌሎቻችሁን አላህ ይጠብቅላችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

16 Nov, 18:09


ከአረቦቹ መንደር..........
እንዲህ ይላሉ

አንድ ሰው ከቤቱ የነበረው አህያ ሚስቱን ረግጦ ገደላት ፤ በርካታ ሰዎች ሊያፅናኑት ይመጡና ሴቶቹ የሆነ ነገር ሲጠይቁት ጭንቅላቱን እያነቃነቀ አዎ ይላቸዋል። ወንዶች መጥተው ደግሞ የሆነ ነገር ሲጠይቁት ጭንቅላቱን እየነቀነቀ አይ ይላቸዋል። ብዙም ሳይቆይ ሌላ ሚስት አግብቶ መኖር እንደ ጀመረ አህያው አዲሷን ሚስቱንም ይረግጣትና ትሞታለች። እንደ መጀመርያው በርካታ ሰዎች እየመጡ ሲያፅናኑት ለሴቶቹ ጭንቅላቱን እየነቀነው አዎ ይላቸዋል ለወንዶቹ ደግሞ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ አይ እያለ መልስ ይሰጣል።
ይህንን ክስተት ይታዘብ የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ጠጋ ይልና ሴቶችን አዎ ወንዶችን ደግሞ አይ እያልክ በጭንቀላትህ ምልክት በመስጠት መልስ የምትሰጣቸው ምን ቢጠይቁህ ነው ይለዋል።

ሰውየውም ሴቶቹ መጥተው ሌላ ሚስት ታገባለህ ወይ ሲሉኝ አዎ አገባለሁ እያልኩ እመልስላቸዋለሁ ፤ ወንዶች ደግሞ እየመጡ አህያውን ትሸጠዋለህ ወይ ብለው ሲጠይቁኝ አይ አልሸጥም እያልኩ ስመልስላቸው ነበር አለው ይባላል።

☀️ኢስላም☀️

15 Nov, 11:18


አንዳንዱ ነገር በኛ ልፋት ብቻ አይወሰንምና ጀሊሉን መለመን ቀደሩን መቀበል ግድ ነው።
ልጅህ ጠማማ ቢሆን ያሳዝናል። እስከለፋህ ድረስ በልጁ ሁኔታ ራስህን አትውቀስ። ነብይ አሳድጎት የሚከፍ*"ርም ልጅ አለ።
ልጆችህ ባይስማሙ ቀልብ ይሰብራል። አንዱ ባንዱ ሲነሳ ያሳዝናል። ሆኖም ራስህን አዛ አታድርግ። ነቢላህ የእቁብ (አሰ) ያሳደጋቸው ልጆች በዩሱፍ ላይ ያደረጉትን አትርሳ።
ሚስቴ ጥሩ ባህሪ ለምን የላትም ብለህ አትገረም። የጠናው ቀደር የገጠመ እለት እንደ ሉጥ (አሰ) ሚስትህ በአመጸኞች ባህሪ ስር አድራ አላህ ካጠፋቸው ሰዎች ትሆናለች።
ባሌ ሀይለኛ ነው አመጸኛ ሆነ ብለሽ ራስሽን አትጉጂ። እስከሆነ ትኖሪያለሽ። ጀሊሉ በሂክማው አስያን በፊርአውን ስር ያሳቀፈ ጌታ ነው። እንደው በደፈናው አግራው እያሉ መኖር ነው።
ሰርቼ ለፍቼ ለምን ሀብታም አልሆንኩም ተብሎ ማማረር አያስፈልግም። መስራቱ እንጂ ሀብታም መሆን እጣህ ላይሆን ይችላል። እንደው የተሳሳተ ትርጓሜ እንጂ ለፍቶ ከሚኖር በላይ ሀብታም ማን አለ?
አላህ በቸርነቱ ዚክርን ተውባን ሰለዋትን ሀምድን ለሁሉም አድሏል። ያለከልካይ የፈለገ ከገኒማው እንዲዝቅ እና በሰኪና ባህር በዚህች አለም እንዲነግስባት ለሁሉም አድሏል። የኖሩት እንደነገሩን በዚህ ባብ ሲኖር ታዲያ ከ physical dimension ወጣ ብለው በሌላ ደረጃ ይኖራሉ። ከዛም ኢማን ይጣፍጣቸዋል።
ኢማን ስኳር ስኳር ወይም ማርማር አይልም። የራሱ ኢማን ኢማን የሚል ጣእም አለው። ረሱል እንዳሉት " 3 ነገሮችን በውስጡ የተገኘበት ሰው የኢማንን ሀላዋ ጣእም ቀምሷል አሉ 1) አላህና መልክተኛው ከነሱ ውጭ ካለ ሁሉ ይበልጥ የወደደ 2) ሰውን ሲወድ ምክንያቱ ለአላህ ብቻ ከሆነ 3) ወደ ኩፍ*ር መመለስን እሳት ላይ ከመጣል እኩል የሚጠላ ከሆነ።
መልካም ጁምአ

☀️ኢስላም☀️

15 Nov, 11:11


💡ሚስጥር መጠበቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِذَا حَدَّثَ الرَّجُلُ الْحَدِيثَ، ثُمَّ الْتَفَتَ فَهِيَ أَمَانَةٌ﴾

“አንድ ሰው ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሆነ ወሬ
ከነገረህ አማና (ሚስጥር) ነው ማለት ነው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 1959

🙁☹️😭🙁😭🙁☹️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

15 Nov, 03:42


የድብቅ  ወንጀሎች ...❗️❗️❗️❗️

ኡስታዝ  ሙሐመድ  ሲራጅ

☀️ኢስላም☀️

14 Nov, 17:25


ይህ ያለ ቅጣት ያልፋል ብሎ ያሰበ በእርግጥም የአላህን ፍትሀዊነት ዘንግቷል
ለአድራጊውም ለተሳታፊውም ለዝም ባዩም ወየውለት!

  

☀️ኢስላም☀️

14 Nov, 12:31


አላህ ሆይ! የስሜታችን ተከታይ (ባሪያ) አታድርገን!

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لَيْسَ فِي الأَرْضِ شَيْءٌ أَشَدُّ مِنْ تَرْكِ الشَّهْوَةِ﴾

“በዚህ ዓለም ውስጥ ስሜትን (የግል ዝንባሌን) አንደመተው የበረታ (የከበደ) የሆነ አንድም ነገር የለም።”

📚 [አል‐ሂሊያ (98/8)]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM

☀️ኢስላም☀️

14 Nov, 04:48


የነቢዩ ባልደረቦች የሰውነታቸው ጠረን እስኪቀየር ድረስ ይሰሩ ነበር ! ለዱንያ መስራቻቸውና ሰርተው ማግኘታቸው ግን ለአኺራ ከመልፋት አያግዳቸውም ነበር

☀️ኢስላም☀️

13 Nov, 05:02



  ይመጣል በድንገት  የለውም ቀጠሮ
   አይጎስም ነጋሪት  አይመታም ከበሮ፤

አላህ ወስኖታል  በሁሉም ባለ ነፍስ
ዘገየም ፈጠነ  የሞት ፅዋ መቅመስ

☀️ኢስላም☀️

12 Nov, 14:13


አንድ ሰው ሶላት ውስጥ ሆኖ የተነጀሰ ልብስ እንደለበሰ ካስታወሰ
* በቀላሉ የተነጀሰውን ጥሎ መቀጠል የሚችል ከሆነ (ለምሳሌ ጃኬቱ፣ ጥምጣሙ ሊሆን ይችላል) የተነጀሰውን ከጣለ በኋላ ሶላቱን ባለበት ይቀጥላል።
* የተነጀሰውን ልብስ ጥሎ ለመቀጠል የማይመች ከሆነ ከነነጃሳው ሶላቱን ሊቀጥል አይገባም። ስለዚህ ከሶላቱ በመውጣት እንደገና አስተካክሎ ከለበሰ በኋላ ሶላቱን እንደ አዲስ ይጀምራል።
* የልብሱን ነጃሳ መሆን ያወቀው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ወይም ቀድሞ ቢያውቅም ረስቶት ኖሮ ሶላቱን ከጨረሰ በኋላ ካስታወሰ ሶላቱ ምንም ችግር የለበትም። ስለሆነም እንደገና አይሰግድም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

11 Nov, 07:39


🤎ለፍጡራን ማዘን!

ከአብደላህ ቢን ዐምሩ (📿) ተይዞ፡ ነቢዩ (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿الراحمون يرحمُهم الرحمنُ. ارحموا من في الأرضِ يرحمْكم من في السماءِ﴾

“አዛኞችን አዛኙ ያዝንላቸዋል። በምድር ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል።”

📚 አቡ ዳውድ፡ (4941) ቲርሚዚ፡ (1924) አህመድ፡ (6494) ዘግበውታል

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

✔️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

11 Nov, 04:52


ትንሽ ስለ ንቦች

ንቦች 3 ዓይነት ናቸው። እነሱም፦
♦️ ንግስት ንብ (Queen Bee)
♦️ ድንጉላ ንብ (Drone Bee)
♦️ ሰራተኛ ንብ (Worker Bee) ናቸው።

👉 ንግስት ንብ እና ሰራተኛ ንብ ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ ድንጉላ ንብ ደግሞ ወንድ ነው።

♦️ ንግስት ንብ
👉 የመንጋው አለቃ ናት
👉 በመጠኗ ከሁሉም ትበልጣለች
👉 ስራዋ እንቁላል መጣል ሲሆን በቀን እስከ 2000 እንቁላል ትጥላለች
👉 ዕድሜዋ ከ5-7 ዓመት ነው
👉 ንግስት ንብ ስትሞት ወይም ስትታመም ሰራተኛ ንቦች በ14 ቀናት ውስጥ ከእንቁላሎቹ የተወሰኑትን በመምረጥ የተለየ ምግብ ይመግቧቸውና የንግስና ተፈጥሮ ያላት ስትወለድ ንግስት ያደርጓታል። ተመሳሳይ ወቅት ሌላ ንግስት ከተፈለፈለች ደግሞ ሁለቱ ንግስቶች እስከ ሞት ይፋለሙና ያሸነፈችው ትነግሳለች።

♦️ ድንጉላ ንብ
👉 በመጠኑ ከንግስት ንብ ያንሳል
👉 ትልልቅ ዓይኖች ያሉት ሲሆን ይህም ንግስቷን ለመለየት ነው።
👉 አይናደፍም
👉 ስራው ከንግስት ንብ ጋር ግንኙነት ማድረግ ብቻ ነው
👉 ግንኙነት የሚያደርገውም አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ግንኙነት ካደረገ በኋላ መራቢያ አካሉ ከአንጀቱ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ከንግስቷ ለመላቀቅ ሲሞክር አንጀቱ ተበጥሶ ይሞታል።
👉 በክረምት ጊዜ በቂ ምግብ ስለማይኖር ከቀፎው ይባረራል። በበጋ ወቅት ደግሞ ምግብ ስለሚኖር ቁጥሩ ይጨምራል።
👉 ዕድሜው ከ1-2 ወር ነው

♦️ ሰራተኛ ንብ
👉 በመጠኗ ከሁሉም ታንሳለች
👉 ስራዋ ማር መስራት፣ ቤት ማፅዳት፣ የሚፈለፈል እንቁላሉን መመገብና ንግስቷን መንከባከብ ነው።
👉 በየቦታው አበባ ሲቀስሙ የምናያቸው ንቦች ሁሉ ሰራተኛ ንቦች ናቸው።
👉 ከወንዱ ድንጉላ ንብ ጋር ግንኙነት አታደርግም
👉 ጠላት ሲመጣ ትናደፋለች። በዚህም መንደፊያ አካሏ ከአንጀቷ ጋር የተጣበቀ በመሆኑ ከነደፈች በኋላ በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለች። የማር ንብ ካልሆነች ግን በአንድ ንድፊያ ላትሞት ትችላለች።
👉 ዕድሜዋ በክረምት ስራ ስለማይበዛ እስከ 9 ወራት ስትኖር በበጋ ደግሞ ስራ ስለሚበዛባት 2 ወር ሳይሞላት በድካም ትሞታለች።

«ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ። ❝ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ። ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ። የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።❞ ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል። በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት።»
(አን-ነህል 68-69)

☀️ኢስላም☀️

10 Nov, 05:41


ሰሓቦች በእርቃን ምስሎች አልተፈተኑም!
ሰሓቦች በእርቃን– ለባሽ ሴቶች አልተፈተኑም!
ሰሓቦች በወረቀት ገንዘብ ግሽበት አልተፈተኑም!
ሰሓቦች በልቅ ድራማና ፊልም አልተፈተኑም!
ሰሓቦች ተቀንድበው በሚወጡ ሴቶች አልተፈተኑም!
                በኢኽቲላጥ አልተፈተኑም!
                በሙዚቃ አልተፈተኑም! 
ሰሓቦች ዐቂዳና መንሀጅ የሚያስተምራቸው አጥተው አልተፈተኑም!
ሰሓቦች ጂሃድ ሲሉ በሚያጣጥልና  ከካሀዲያን ጋር አብሮ በግልፅ በሚወጋ ሙስሊም ነኝ ባይ አልተፈተኑም!
ሰሓቦች መህር በሚሰቅሉ ሴቶች  አልተፈተኑም!
ሰሓቦች በዲሞክራሲና ሴኩላሪዝም በላእ አልተፈተኑም!
                      ሰሓቦች ወንድና ሴትን አቀላቅሎ                                              በሚያስተምር ስርአት                                                   አልተፈተኑም!
ሰሓቢያት ደረታቸውን በተራቆቱ ወንዶች ፎቶ  አልተፈተኑም!
እርግጥ ነው በርሃብ ተፈትነዋል!
በድርቅ ተሞክረዋል!
በአላህ መንገድ ፈግተዋል!

በዚህ ዘመን ያለ ሙስሊም ወጣት ከነዚህ ፈተናዎች ጋር ግብግብ ይዟል። በዚህ በሴት ይፈተናል ፤ ሐራም ላይ እንዳልወድቅ ብሎ ለማግባት ተፍ ተፍ ሲል መህር ይቆለልበታል! በዚህ ጎን አጠገቡ እርቃን አለች አይኑን ሰብሮ ወደዚያ ሲዞር ሌላኛዋ እዛ ጋር።

በዚህ ጋር የአላዋቂዎች ትችት፣ መሀይም ተድርጎ መታየቱ .... እዚህ ጋር ሒጃቧን ትጠብቃለች በአላህ ጠላቶች በሒጃቧ ይመጣባታል፤  እዚያ ጋር የስነ ልቦና ጦርነት አለባት እዚህ ጋር ሌላ ግፊያ ...

ሙስሊምና ሙስሊማት ወጣቶች –በተለይም ዲኔን ያሉት –እነዚህ የፈተና ማእበሎች አንዱ ወዳንዱ እያላተመ ያሽመደምዷቸዋል።
በሰሓቦች ጊዜ በነበሩትም ይሁን አሁን ላይ ባሉ ፈተናዎች ሁሉ እየተሞከሩ ነው!

አላህም ፈተናቸው ከሰሃቦች በላይ ነውና የሰሃቦችን እጥፍ አጅር ሊሰጣቸው ደነገገ!

ለመሆኑ ሰሃቦች የተገረሙበትን ሐዲስ ሰምታችኋል?

ውዱ ሙስጠፋ ﷺ አንድ ቀን ለሰሃቦች  እንዲህ አሉ፦

« ከናንተ በኋላ የትእግስት ዘመን ይመጣል፤ በርሱ ውስጥ (ዲኑን) ጨብጦ የያዘ ከናንተ የአምሳ ሸሂዶችን አጅር አለው»
(ሰሒሑል ጃሚዕ 2234)

ሰሃቦችም ግርም አላቸውና ፤የአጅሩ ልቅና አስደነቃቸውና ፦
«(ያረሱለላህ)  ከኛ የአምሳ ሰው ወይስ ከነርሱ የአምሳ ሰው አጅር?» ብለው በመገረም ጠየቁ!

እርሳቸውም ﷺ መለሱ ፦
«ይልቁንም ከናንተ የአምሳ ሰው አጅር! »
(ሰሒሑት ተርጚብ 3172)

አዎ! የአላህ መልእክተኛ ﷺ የትእግስት ዘመን ይመጣል ማለታቸው በዲን ላይ መታገስና መፅናት ከምን ጊዜም በላይ አስፈላጊ የሚሆንበት  የፊትና ዘመን ማለታቸው ነው! ይህ የፈተና ዘመን አሁን ነው! አንድ ሙእሚን ጧት ወጥቶ ማታ እስኪገባ ስንት ጊዜ በዲኑ እንደሚፈተን አላህ ይወቅ! በዲኑ ላይ የታገሰና የፀና በዚህ የረሱልﷺ ብስራት ደስ ይበለው! !

እናንተ በዲናችሁ የሶበራችሁና የፀናችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ከዚህ በላይ ምን ብስራት አለ? ለናንተ በፅናታችሁ የ50 ሸሂድ ሰሃባ አጅር አለላችሁ!!

ለኛም ዱዐ አድርጉልን! አላህ ይመልሰን! አላህ ከሙእሚኖች ያድርገን!!

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru

☀️ኢስላም☀️

09 Nov, 14:56


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ስራ ነው! ከሀረር የተፈናቀሉ ወንድሞቻችን እህቶቻችን  ከባዶ ተነስተው በመንግስት እርዳታ ውስጥ ሆኖ ለሚበሉት ለሚጠጡት ይህንን የምትመለከቱትን መስጅድ እዚህ ለማድረስና ለመጨረስ የሚችሉትን እያደረጉ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱል ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለአኼራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል አቡበክር ሲዲቅ  በለገጣፎ ከተማ  140 መናኸሪያው ወደ ውስጥ ገባ ብሎ  መሪሳ የሀረሪ ተፈናቃዬች ካምፕ ውስጥ  ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለአካባቢው  ድምቀትም አካባቢው ላይ ከነሱ ውጪም ላለው ሙስሊም መሀበረሰብ ያለ ብቸኛ መስጅድ  ነው። በተጨማሪም ብዙ ደረሶች የሚቀሩበት እና  ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
❗️❗️ማሳሰቢያ በግል አሰራለሁ ለማመንም ይቸግራል መጥተን በአካል  ማየት አለብን ለምትሉ አህለል ኸይሮች ካላቹ  ጥርጣሬ  ለሚፈጥርባቹ
በዚህ ስልክ ቁጥር ማናገርና በቀጠሮ ማየትም ማሰራትም ትችላላችሁ ስቁ 0988504999 ወይም 0934492187
የአቅማቹን ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ - 1000388791369
Oromia bank:-1017500029076

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/mesud22

☀️ኢስላም☀️

09 Nov, 11:54


ያ........ኔ………
በኹሹዕ ስትሰግድ ፣ ቁርዓን በተደቡር ስትቀራ ፣ ከጌታህ ጋር የነበረህ ሁኔታ እጅግ ያማረ በነበረ ጊዜ ፣ ልብህ በኢማን ተሞልታ ፍንድቅ ስትል በሚታወቅህ ወቅት ፣ ፊትህ ኑር በተላበሰች እና ከጌታህ ጋር በየትኛውም ወቅት ለመገናኘት ዝግጁ የሆንክበትን ጊዜያቶችን………
አስታወስክ !?
ታድያ አሁን የት አለህ!?
ምን ሆንክ !?
ወደነዚያ ጣፋጭና ውብ ጊዜያት መመለስን አላሰብክምን!?

☀️ኢስላም☀️

08 Nov, 04:44


ስታነውር ትፈተናለህ
~
ኢብኑ ሲሪን ሃብታም ነበሩ። ሃብታቸው ከሰረና በድህነት ውስጥ መኖር ያዙ። በዚህን ጊዜ ሰዎች፡ "እንዲህ የሆንክበት ምክንያቱ ምንድነው?" ብለው ጠየቋቸው።
"ይሄ አንድን ሰው፡ 'አንተ ድሃ!' በማለቴ የተነሳ ለአርባ ዓመት ቅጣቱን ስጠብቀው የነበረ ወንጀል ነው" አሉ።

በዚህ ላይ ዳራኒይ እንዲህ ይላሉ፦ "ወንጀሎቻቸው በመቅለላቸው የተነሳ ቅጣት ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣባቸው ያውቃሉ። የኔና ያንተ ወንጀል ግን በመብዛቱ የተነሳ ቅጣት ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣብን አናውቅም።"

[ሒልየቱል አውሊያእ፡ 2/271]

በዚህ ዘመን መከራ የበዛብን ያለ ምክንያት አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

07 Nov, 04:24


ሁላችን ጉዞ ላይ ነን፣ ወደ ኣኺራ!
ሟቾች እንደሆንን ሁላችንም በርግጠኝነት እናውቃለን። የማናውቀው የቀጠሮውን ቀን ነው።

ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"ሁሉም ይጓዛታል - ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን - ያለው ስንቁን ይዞ።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

07 Nov, 04:22


ሴት ልጅ ለሶላት ፀጉሯን መሸፈን አለባት። ብቻዋን እንኳ ብትሆን። ካጠገቧ ማንም ባይኖር እንኳ።
እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا يقبل الله صلاة حائض إلا بخمار
"አላህ ለአቅመ ሄዋን የደረሰችን ሴት ያለ ጉፍታ ሶላቷን አይቀበላትም።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 596]
ፀጉሯን የምትሸፍንበት ልብስ ስስ ሆኖ ፀጉርን አሳልፎ የሚያሳይ መሆን የለበትም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

06 Nov, 04:55


እህቱን ወይም ልጁን ሊድር የሚሻ ሰው ቀድሞ ከቁሳዊ እሳቤ ጭንቅላቱን ማፅዳት አለበት። ገና ለገና ደህና ኢኮኖሚ ካለው ጋር ስለመዛመድ ብቻ እያሰበ የሴቲቷን ህይወት የፅልመት አረንቋ ውስጥ መጨመር ትልቅ በደል ነው። «ዲኑንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው ከመጣ ዳሩት» ያሉት መልዕክተኛው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ። አንድ ቤት ቤት ሆኖ እንዲቆም የባል ምግባር ትልቅ ሚና አለው። ለዚያም ነው ረሱለላህ "አኽላቅን" ዲን ውስጥ የሚካተት ነገር ሆኖ ሳለ ከዲን ነጥለው ለብቻው የጠቀሱት።

☀️ኢስላም☀️

05 Nov, 15:46


አንድ የማውቀው ዘበኛ አለ። እና በትርፍ ሰዓቱ ጥንቆላ ይሰራል። ታዲያ ብዙ ሃብታሞች ጨለማን ተገን አድርገው መኪኖቻቸውን ከሚጠብቅበት አጥር አጠገብ እያቆሙ ሲጠያይቁት አያለሁ።

እሱ ጥንቆላ የጀመረው ገቢ አጥሮት ኑሮውን ለመደጎም ነው። እነሱ ደግሞ ከእኛ የተሻለ እውቀት አለው ብለው ያማክሩታል። የአቅል መነጠቅ እንጅ ከእነሱ የተሻለ አንድ ሃብታም ጋር ሄደው ቢጠይቁት እኮ የተሻለ መንገድ ያመላክታቸው ነበር። መቼም ጠንቋይ ጋር ሄደው ስለ ዱንያ እንጅ ስለ አኼራ አይጠይቁም ብዬ ነው። ግን አላህ ልብን ከሸፈነ ገላጭ የለውም።

ብዙዎቹ ኢትዮጵያ ሃብታሞች ጧት ምፅዋትና ሰደቃ አብልተው ተስያት ጠንቋይ ቤት ናቸው ይባላል። ይሄ እንግዲህ አንተም አትርሳኝ አንተም አስታውሰኝ መሆኑ ነው።

አላህ እውነት ተናገረ፦

«አብዛኞቻቸው እነሱ አጋሪዎች ሆነው እንጅ በአላህ
አያምኑም።»
(ዩሱፍ 106)

☀️ኢስላም☀️

04 Nov, 14:19


ኒካሕና ቃዲ
~
እንደሚታወቀው በኢስላም የትኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ወሊይ ከሌለስ? በዚህን ጊዜ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ስለዚህ ኒካሕ ለማሰር ቃዲ የሚያስፈልገው ወሊይ ለሌላት ሴት ነው ማለት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له)
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል]

በተጨማሪም ወሊዮች ያለ ተጨባጭ ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ከዚህ ውጭ አባት ወይም ሌላ ወሊይ ወይም ወኪል ካለ ኒካሑን የሚያስሩት እነሱ እንጂ ቃዲዎች አይደሉም። ወሊይ ወይም ወኪሉ "ሰጥቻለሁ" ካለ፣ አግቢው ወይም ተወካዩ "ተቀብያለሁ" ካለ ኒካሕ ታስሯል። ኹጥባውን (ሸርጥ ካለመሆኑም ጋር) ወሊይ ወይም ሌላ ቦታው ላይ የተገኘ ሰው ሊያደርገው ይችላል።

ኒካሕ ለማሰር የተለየ ውስብስብ መስፈርት የለም። የዐረብኛ ቃላት መጠቀምም አይጠበቅም። መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን መስጠትና መቀበል ከተገኘ ኒካሕ ታስሯል። ስለዚህ በሃገራችን በሰፊው እንደሚደረገው ወሊይ እያለ ቃዲ መጥራት አይጠበቅም። ቃዲዎች ወሊይ ባለበት ሁኔታ ኒካሕ ለማሰር አትቀደሙ። ያለ ስልጣናችሁ ጣልቃ አትግቡ።

ወሊይ የሆናችሁ ሰዎች ደግሞ ቃዲዎችን ለሰርግ ከጠራችሁ እንደማንኛውም እድምተኛ ተስተናግደው ይመለሱ እንጂ እዚያው ተቀምጣችሁ ለነሱ ውክልና አትስጡ። "ልጄን እከሊትን ድሬሃለሁ" ማለት ያቅታችኋል? ምንም የተለየ የተቀመጠ ቃል የለምኮ። እሱም "ተቀብያለሁ" ካለ፣ ቦታው ላይ ሁለት ታማኝ ምስክሮች ከኖሩ ኒካሑ ታስሯል አለቀ። ባገር እያለህ፣ ዐቅልህ ጤነኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ከፊትህ ለሚፈፀም ጉዳይ ውክልና ትሰጣለህ? ምንም የሚያስፈራ ነገር የለምና እራስህ ፈፅመው። ሁሉም ነገር በቃዲ በኩል እንዲያልፍ መደረጉ አንዳንድ መረን የለቀቁ ባለስልጣናት በማያገባቸው የእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር እየከፈተ ነው። አንዳንድ ቃዲዎችም ጉዳዩን ያላግባብ የሚጠቀሙበት ሁኔታ አለ።
=
ኢብኑ ሙነወር

☀️ኢስላም☀️

04 Nov, 12:28


😂😂😂😂

☀️ኢስላም☀️

04 Nov, 12:28


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።
* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።
- "አዎ" አለ ሰውየው።
* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።
- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

04 Nov, 05:21


⚠️⚠️ አንተስ ሲበዛ ለታመመው ቀልብህ ምን ያህል ግዜ እስቲግፋር ታደርጋለህ?

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّه لَيُغانُ على قَلْبِي، وإنِّي لَأَسْتَغْفِرُ اللَّهَ في اليَومِ مِائَةَ مَرَّةٍ﴾

“ልቤ ይጋረድብኛል በዚህ የተነሳ በቀን ውስጥ መቶ ግዜ እስቲግፋር አደርጋለሁ (ጌታዬን ምህረት እጠይቃለሁ)።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2702

🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

03 Nov, 14:23


ተናፋቂው ወር 116 ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል 🌙
ያ ረብ ደርሰው ከሚፆሙት አድርገን 🤲

☀️ኢስላም☀️

03 Nov, 14:12


አንዱ ደግ ሰው እንዲህ ይላል፦
* "በስራ ከተማ ስገባ ገበያዎቹ ተዘግተዋል። መንገዶቹ ባዶ ናቸው። 'የበስራ ሰዎች ሆይ! እኔ የማላውቀው ዒድ አላችሁ እንዴ?' አልኩኝ።
- ' እንደሱ አይደለም። ነገር ግን ሐሰኑል በስሪይ መስጂድ ውስጥ ሰዎችን እያስተማረ ስለሆነ ነው' አሉኝ።"
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

01 Nov, 18:40


ሴትን የሚንቁ ወንዶች 👂👂
በሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ሀፊዘሁላህ
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/mesud22

☀️ኢስላም☀️

01 Nov, 13:43


በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ አካባቢ ታግተው የነበሩት የመስጅድ ኢማም ከነ 12 ቤተሰቦቻቸው መገደላቸው ተሰማ!
- ሀሩን ሚዲያ፣ ጥቅምት 22/2017
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጣራው አካባቢ ከሀጂ አህመድ መስጅድ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 ቤተሰቦቻቸው ጋር በዛሬው ዕለት መገደላቸው ተሰምቷል።
ሼይኽ ሙሀመድ ከሳምንታት በፊት የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው የተገለፀው። ከቀናት በኋላ በተደረገ የገንዘብ ድርድር የኢማሙን እናት እና ባለቤት ጨምሮ ጥቂት ሰዎች መለቀቃቸው ተጠቁሟል።
ኢማሙን ጨምሮ 12 ቤተሰቦቻቸው ግን በዛሬው እለት መገደላቸው ተሰምቷል። ግድያው የተፈፀመው መንግስት "አሸባሪ" ብሎ በፈረጀው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አማካኝነት መሆኑን ከስፍራው ለሀሩን ሚዲያ የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ሼይኽ ሙሀመድ መኪን የታላቁ አሊም ሼይኽ አህመድ ደራ የልጅ ልጅ ሲሆኑ የሃጂ ሙሀመድ ወሌ የወንድም ልጅ መሆናቸው ተገልጿል። ሼይኽ ሙሀመድ መኪን የሃጂ አህመድ መስጅድ እና ኻሪማ ኸሊፋ በመሆኑ በርካታ ደረሶችን እያስተማሩ እንደነበር ተሰምቷል።
- ሀሩን ሚዲያ አላህ ለእሳቸው ጀነትን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሰብርን እንዲለግሳቸው ይመኛል።
© ሀሩን ሚዲያ

☀️ኢስላም☀️

01 Nov, 07:53


💭 የጁምዓ ቀን ትሩፋት!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنِ اغْتَسَلَ ثُمَّ أتى الجُمُعَةَ، فَصَلّى ما قُدِّرَ له، ثُمَّ أنْصَتَ حتّى يَفْرُغَ مِن خُطْبَتِهِ، ثُمَّ يُصَلِّي معهُ، غُفِرَ له ما بيْنَهُ وبيْنَ الجُمُعَةِ الأُخْرى، وفَضْلُ ثَلاثَةِ أيّامٍ﴾

“ገላውን ታጥቦ፣ ወደ ጁምዓ የሄደ፣ በቻለው ልክ ሱና ሰላቶችን የሰገደ፣ የኢማሙን ኹጥባ እስከ መጨረሻው ያዳመጠ፣ ኢማሙን ተክትሎ የሰገደ፣ ካለፈው ጁምዓ እስከሚቀጥለው ጁምዓ ድረስ ባለው ሶስት ቀናትን ጨምሮ የሰራቸውን ኃጢያቶች አላህ ይምረዋል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 857

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

⬇️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

01 Nov, 04:55


ጁሙዐ ይለያል!
~
ጁሙዐ ከሳምንቱ ቀናት የተለየ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ነጥቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል:-

1- ጁሙዐ የሳምንቱ ቀናት አይነታ ነው። ከሁሉም በላጭ የሆነ ቀን ነው፣ ሳምንታዊ ዒድ።
2- ጁሙዐ አደም የተፈጠሩበት እና የሞቱበት የዓለም ፍፃሜ የሚሆንበትም ቀን ነው።
3- አላህ ዘንድ ከሶላት ሁሉ በላጩ የጁሙዐ እለት በጀማዐ የተሰገደ የሱብሕ ሶላት ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1119]
4- ጁሙዐ የጠነከረ ትእዛዝና ማሳሰቢያ የመጣበት ልዩ የሆነችዋ የጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ቀን ነው።
5- ሳምንታዊ ኹጥባ የሚገኝበት ቀን ነው። ኹጥባውን በፀጥታ ማዳመጥም ግዴታ ነው።
6- ገላን በመታጠብ ትእዛዝ የመጣበት ቀን ነው።
7- ሽቶ መቀባት፣  መፋቂያ መጠቀም ይወደዳል።
8- ያማረ ልብስ መልበሱ ይወደዳል።
9- ጁሙዐ ግዴታ ለሆነበት ሰው የሶላት ወቅት ከገባ በኋላ ጁሙዐን ሳይሰግዱ መንገድ መውጣት አይፈቀድም።
10- ጀሀነም በየ እለቱ ትቀጣጠላለች፣ ጁሙዐ ቀን ሲቀር።
11- ጁሙዐ ቀን አላህ ዱዓእን ከሌሎች ጊዜያት በተለየ የሚቀበልባትን ሰዓት የያዘ ቀን ነው።
12- ጁሙዐ ቀን ሱረቱል ከህፍ መቅራት የሚወደድበት ቀን ነው።
13- ጁሙዐ ቀን በነብዩ ﷺ ላይ ሶላት ማብዛት የሚወደድበት ቀን ነው።
14- ጁሙዐ ቀን ሱብሕ ሶላት ላይ ነብያችን ﷺ ሱረቱ ሰጅደህ እና ሱረቱል ኢንሳንን ይቀሩ ነበር።
15- የጁሙዐ ቀን ወይም ሌሊት የሞተ ሰው አላህ ከቀብር ፈተና ይጠብቀዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1074]
16- ጁሙዐ ለወንጀሎች ምህረት የሚገኝበት ቀን ነው።
17- የጁሙዐ ቀን በፆም፣ ሌሊቱን በሶላት መለየት የተከለከለ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

31 Oct, 04:58


ጥላቻቸውን በሴኩላሪዝም ስም ያቀርቡታል
~
በሴኩላሪዝም ስም የሙስሊሞችን መብት እየተጋፉ ከትምህርት ገበታ ያርቃሉ። በሴኩላሪዝም በሚታወቁት የምእራቡ ዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ግን ሙስሊም ሴቶች ከነ ኒቃባቸው ተምረው ሲመረቁ እያየን ነው። እኛጋ ሴኩላሪዝም ሽፋን እንጂ መንስኤው ጥላቻና ክፋት ብቻ ነው። ምስሉ ላይ እንደሚታየው መንግስታዊ አካላት ፍጥጥ ባለ መልኩ ከነ ዩኒፎርማቸው ሃይማኖታዊ አጀብ ይፈፅማሉ። በየ ቢሮው ስትገቡ መዝሙር ተከፍቶ ታገኛላችሁ። ሃይማኖታዊ ስእሎችንም ይለጥፋሉ። ሙስሊሙ ጋር ሲደርስ ግን በሲኩላሪዝም እያመሀኙ የመማር መብታቸውን ይነፍጋሉ። ማስመሰል በቃ! ጥላቻችሁን በስሙ ጥሩት! በአፄው ዘመን የነበረው ሙስሊሞችን ከትምህርት የማራቅ ሴራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

30 Oct, 13:35


እንቁ መልክት
ተማሪዎችን ሂጃብ መከልከል???
በሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/mesud22

☀️ኢስላም☀️

29 Oct, 09:29


ሀቅ ይውጣልህ ወንድማችን

☀️ኢስላም☀️

29 Oct, 08:46


💡ለብቻህ ስትሆን የምትፈፅማቸው አምልኮዎች በዲን ላይ ለመፅናት ወሳኝ ናቸው!!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿صلاةُ الرجلِ تطوُّعًا حيثُ لا يراهُ الناسُ تَعدِلُ صلاتَهُ على أعينِ الناسِ خمسًا وعشرينَ.﴾

“ሰውዬው ሰዎች ሳያዩት የሚሰግደው ትርፍ (የሱና ሰላት) ሰዎች አይተውት ከሚሰግደው ሰላት በሃያ አምስት ደረጃ ትስተካከላለች (ብልጫ አለው)።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 3821

▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

💬፦ https://bit.ly/41zEZkk

📷፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

📺፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

29 Oct, 05:15


ብሶት ደም ያስነባል
ፈርተን አይደለም የምናለቅሰው !!!
ፍትህ ለኒቃብ ለባሽ ተማሪ እህቶቻችን

☀️ኢስላም☀️

29 Oct, 05:07


ሙዘኒይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፦

ሻፊዒይ ዘንድ ገባሁ። በሞቱበት ህመማቸው ላይ ሳሉ ነው። "እንዴት አደርክ የ0ብደላህ አባት?" አልኩኝ።
እራሳቸውን ቀና አደረጉ። ከዚያም:
"ዱንያን እየለቀቅኩ፣ ወንድሞቼን እየተለየሁ፣ ክፉ ስራዬን ለመገናኘት፣ ወደ አላህ ለመጓዝ የቀረብኩ ሆኜ አድሬያለሁ። ሩሔ ወደ ጀነት ሆና የምስራች የምላት ትሁን፣ ወደ እሳት ሆና የማረዳት ትሁን አላውቅም" አሉና አለቀሱ።

📚 [አሲየር : 10/75]
IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

29 Oct, 05:06


ሙሳኮ አላህ ለርሱ ብሎ ባህሩን እንደሚከፍልለት አያውቅም። ባህሩ ጋር የደረሰውም አስቦበት አልነበረም። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነበር “ጌታው መቼም በዚያ አጣብቂኝ ውስጥ እንደማይተወው”። አቤት… የቂን፤ ዐጀብ ተወኩል ፤ “ተው(አትስጉ) ጌታዬ ከኔ ጋር ነው” የሚል ተራራ ኢማን!! ኧረ እንዲህ አይነት የቂን ሸልመን ያ ወዱድ!!

☀️ኢስላም☀️

27 Oct, 05:21


#ጥያቄና_መልስ

የምንቀሰቀሰው በነፍሶቻችን ነው በአካላችን አይደለም ብሎ የሚያምን ሰው እንደ ካፊር ይቆጥራልን?

🔖 በኦዲዮ (MP3)

🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://www.facebook.com/share/v/oZiDG5x15v5uYWjX/

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

t.me/ustazilyas

☀️ኢስላም☀️

26 Oct, 13:16


የእስራኤል ወታደሮች ናቸው፣ ንጹሀን ላይ የለመዱት መሳርያ ወንዶቹ ጋ ሲሆን እንዳሰቡት አልሆነላቸውም።

https://t.me/Yahyanuhe

☀️ኢስላም☀️

26 Oct, 10:26


ተጠንቀቅ! ደካማ አያልቅስብህ
~
በጉልበትህ፣ በስልጣንህ፣ በወገንህ፣ በሃብትህ፣ ... ተማምነህ ሰዎችን አትግፋ። "ጌታዬ! እኔ አቅም የለኝም፣ አንተ ፍረደኝ!" ብሎ ሰው ካለቀሰብህ ወላሂ ወዮልህ! ያኔ እርቃንህን ብቻህን ከአላህ ፊት ለምርመራ ስትቀርብ ምን ይውጥሀል?! ያኔ ዛሬ የተመካህበት ጉልበት ይከዳሀል። ያኔ ዛሬ የጠገብክበት ስልጣን ያዋርድሃል። "ምነው በቀረብኝ?!" ትላለህ። ያኔ ዛሬ የተመካህበት ዘመድና ወገን ጥሎህ ይሸሻል።
{ فَإِذَا جَاۤءَتِ ٱلصَّاۤخَّةُ (33) یَوۡمَ یَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِیهِ (34) وَأُمِّهِۦ وَأَبِیهِ (35) وَصَـٰحِبَتِهِۦ وَبَنِیهِ (36) لِكُلِّ ٱمۡرِئࣲ مِّنۡهُمۡ یَوۡمَىِٕذࣲ شَأۡنࣱ یُغۡنِیهِ (37) }
"አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ ከእናቱም ከአባቱም፤ ከሚስቱም ከልጁም እንዲሁ። ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁነታ አልለው።" [0በሰ፡ 33-37]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Oct, 04:36


የልብ ድርቀትን ለመከላከል
~
በዚህ ዘመን በልብ ድርቀት ያልተጠቃ ይኖር ይሆን? ሃሳብ ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ሆነ። ዒባዳችን ለዛ አጣ። መተዛዘን ጠፋ። ስግብግብነት ነገሰ። ስስት ከደም ከስጋችን ጋር ተዋህደ። የዱንያ ምኞታችን ከመርዘም አልፎ ተንዘላዘለ።
ወንድሞች እህቶች ወላሂ! የልብ ድርቀት በጣም ሊያስጨንቀን የሚገባ ህመም ነው። የልብ ድርቀት አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የአላህ ቅጣት ነው። ከዚህ ህመም ልባችንን እንዴት እናክም? ከዚህ የአላህ ቅጣት እንዴት እንውጣ? ጥቂት ሰበቦችን ልጠቁም። ራሴም ጤነኛ ሆኜ አይደለም። ከማጨስ እንደሚያጠነቅቅ አጫሽ፣ ከህመም እንደሚያስጠነቅቅ ህመምተኛ ቁጠሩኝ።
1- አላህን በማሰብ ራስን አጠቃላይ ከወንጀል መጠበቅ፣ የቅርብም ይሁን የሩቅን ሰው ከመበደል መጠንቀቅ፣ ግብይታችንን፣ ገቢያችንን ሐላል ማድረግ፣ የሰው ሐቅ እንዳይመጣብን መጠንቀቅ
2- ምላስን ከውሸት፣ ከመጥፎ ንግግር፣ ከሃሜትና መሰል ክፍቶች መቆጣጠር፣ ጆሮዎቻችንን ሐራም ነገሮችን ከማዳመጥ፣ አይኖቻችንን ሐራም ነገሮችን ከመመልከት፣ እጆቻችንን ለሐራም ነገሮች ከመጠቀም፣ ልባችን በክፋት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ... ላይ ከመጥመድ መቆጣጠር
3- ዚክር ማዘውተር፣ በቋሚነት የቁርኣን ዊርድ መያዝ፣ ደጋግሞ ከልብ ዱዓእ ማድረግ፣ ተደቡር፣ ተፈኩር ማድረግ፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን ማልቀስ
4- ከሰላት፣ ከፆም፣ ከሶደቃው፣ ... ከግዴታው ባለፈ ነፍል ዒባዳዎችን ማዘውተር
5- ሞትን፣ ቀብርን፣ ሂሳብን፣ ሲራጥን፣ ... ኣኺራን ማሰብ
6- ደግሞ ደጋግሞ ኢስቲግፋርና ተውበት ማድረግ
7- ቁርኣን በእርጋታ መቅራት፣ ኹሹዕ የሚያጋባ አቀራር ያላቸውን ቃሪኦች ማዳመጥ፣
8- ቀብር መዘየር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤትን አቅም በፈቀደ መጠየቅ
9- ችግረኛን በገንዘብም፣ በሃሳብም፣ በጉልበትም፣ በእውቀትም መርዳት፣ ሶደቃ ማድረግ
10- የዙህድና የረቃኢቅ ኪታቦችን ማንበብ፣ ውስጥን ሰርስረው የሚገቡ ሙሓደራዎችን እየፈለጉ ማዳመጥ፣ የነብዩን ﷺ ስራዎች፣ ራስን ለመታዘብ የሚያግዙ የሰለፎችን አስገራሚ ታሪኮች፣ የዑለማኦችን ጣፋጭ ወጎች በትኩረት መከታተል
11- በየትኛውም የዒባዳ መስክ ላይ ኢኽላስን አጥብቆ መፈተሽና ማቃናት።
12- ከራስ ጋር መተሳሰብ። ጊዜ አልፎ ጊዜ በተተካ ቁጥር ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ከአምና ዘንድሮ፣ ከባለፈው በዚህኛው፣ ሳምንታችን፣ እለታዊ ውሏችን መሻሻል አለው? ወይስ ያው ነው? ወይስ ጭራሽ እየባሰበት ነው? ከዱንያችን በላይ ኣኺራችን ያሳስበናል? ድንገት ብንሞት ያለንበት ሁኔታ በፀፀት ጣት የሚያስነክስ አይደለም? ራሳችንን ለመለወጥ የምር እንታገል።

እኔ የራሴን ድክመቶች በመመልከት ድንገት የመጣልኝን ነው የፃፍኩት። ሁሉም ነገን አስቦ ዛሬ ራሱን ይመልከት።
﴿بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَى نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ﴾
"በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡" [አልቂያመህ ፡ 14]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Oct, 04:34


በጊዜ ተንፍስ
~
አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ።
የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው።
ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

26 Oct, 04:33


ከዚህ ስሜት ያለን ርቀት ምን ያህል ነው?
~
ሰዒድ ብኑ ጁበይር - ረሒመሁላህ - "ከማንም በላይ ይበልጥ አላህን ተገዢ /አምላኪ ማነው?" ተብለው ተጠየቁ። ምላሻቸው ምን ሆነ?
"ወንጀል ፈፅሞ ያን ወንጀሉን ባስታወሰ ቁጥር ስራውን ዝቅ አድርጎ በመመልከት ለጌታው የተሰበረ ነው" አሉ።
[አልቢዳያህ ወኒሃያህ 9/99]

ያ ረብ ወዳንተ መቅረብን ወፍቀን።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

25 Oct, 16:50


የእነርሱን ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም ልብስ ገፈው እርቃነ ገላ አድርገውናል።
ሩህማከ ያ አላህ

Mahi Mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

☀️ኢስላም☀️

25 Oct, 11:40


ሁሉም ከእንቅልፋቸው አልነቁም። አስራ አራቱም። በአልፋራህ መጠለያ ውስጥ እንደተኙ አላህን ተገናኙ። በወራሪዋ ድሮን ላይመለሱ ይህንን ዓለም ለቀው ወደማይቀረው ዓለም ተሸጋገሩ።

ጌታዬ ሆይ! ከነቢያት ከሸሂዶችና ከሲዲቆች ተርታ አሰልፋቸው።

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

☀️ኢስላም☀️

25 Oct, 11:40


"ጎዳናው በጀናዛ ቅሪቶች ተሞልቷል። ፊታቸውን መለየት ገፅታቸውን ማወቅ በማይቻል ወንድሞች ተጥለቅልቋል።

በሞትና በባሩድ ሽታ አየር ምድሩቢሞላም የጀነቱ ንፋስ ግን ይበልጥ ያውዳል።

በታንክ በሚሳኤል ጆሯችን ቢናጥም መላእክቶች አይዟችሁ የሚሉን ይመስላል በጣም ተረጋግተናል" ይላል ስቃዩን በአካል የሚኖረው ሐምዛ ሙስጠፋ።

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

☀️ኢስላም☀️

25 Oct, 05:15


በጁሙዐ ቀን ከሚወደዱ ተግባሮች ውስጥ አንዱ በነብዩ ﷺ ላይ ሰላት ማውረድ ነው። ምን ያህሎቻችን ይሄ ልማድ አለን?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

24 Oct, 17:30


የኢትዮጵያ ነገር እዚህ ደርሷል
~
መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል

በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።

"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።

መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።

ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።

ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።

ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።

አሳፋሪ ነው!
(ኤልያስ መሰረት)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

24 Oct, 08:22


⚠️⚠️ የሚስትህን ድብቅ ሚስጥሮች ጠብቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ مِن أَشَرِّ النّاسِ عِنْدَ اللهِ مَنْزِلَةً يَومَ القِيامَةِ، الرَّجُلَ يُفْضِي إلى امْرَأَتِهِ، وَتُفْضِي إِلَيْهِ، ثُمَّ يَنْشُرُ سِرَّها﴾

“በትንሳዔ ዕለት ከሰዎች ሁሉ መጥፎ ሆኖ አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ ሰውዬው ከሚስቱ ይጣቀምና (ግብረ ስጋ ግንኙነት ያደርግና) እሷም ትጣቀምና ከዛ ሚስጥሯን (ገመናዋን) የሚዘራ ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1437

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

⬇️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

💬፦ https://bit.ly/41zEZkk

📷፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

📺፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

23 Oct, 17:48


የሰዎች ትንኮሳ መቼ ነው የሚጎዳህ?
~
ሰዎች በንግግር፣ በፅሁፍ፣ በሃሜት፣ በየትኛውም አይነት ክፉ ቃል ሲፈትኑህ እየተብከነከኑ ጤናንም፣ ሰላምንም፣ እንቅልፍንም ማጣት አይገባም። ቢቻል አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ነው። ካልሆነ ግን የሚፈትሉትን ክፋት እዚያው እነሱው እንዲጠመዱበት መተው ነው። በመርሳት ሰላምህን ጠብቅ። ካልሆነ ግን ክፋታቸው ሳይሆን ማብሰልሰልህ ይጎዳሀል። ሰዕዲይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦

"የሰዎች ትንኮሳ አይጎዳህም። ይልቁንም እነሱኑ ነው የሚጎዳቸው። ትኩረት በመስጠት ራስህን ካልጠመድክ በስተቀር። ያኔ እንደሚጎዳቸው አንተንም ይጎዳሀል። ቦታ ካልሰጠኸው ግን ምንም አይጎዳህም።"
[አልወሳኢሉል ሙፈደህ ሊልሐያቲ ሰዒደህ፡ 30]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

23 Oct, 04:10


"ዱዓ ለተከሰተም ገና ለሚከሰትም መከራ
እጅግ ጠቃሚ ነው።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! ከዱዓ እንዳትዘናጉ አደራ!!"
ረሱል (ﷺ)
(ሰሂህ አልጃሚዕ: 3409)

☀️ኢስላም☀️

22 Oct, 17:11


ለእኔ ይህ የ ኢማን ከፍታን ማሳያ ነው ።ወንድሜ ሰብርህ የምር ያስቀናል ።ደሞ ሁሉን ቻይ እና አዋቂ የሆነው አላህ ጥሎ አይጥልህም ።ወላሂ በትግስትህ ልክ እረ ከዚያም በላይ ሰጥቶህ ደሞ ያስደስትሃል ።

አላህ ጭንቀትህን በብስራት ሃዘንህን በደስታ ኪሳራህን በትርፍ ትእግስት ና ኢማንህን በጀነት ይተካልህ አብሽር ወንድሜ አብሽር !!!!

ምንአለ ከዚህ በላይ ማለት በቻልኩ ???
ምናለ ኖሮኝ ባስደሰትኩህ ???

ግን እመነኝ ብዙዎቻችን ያጣነውን የሌለን ኢማን ሰብር እና ወንድምን ማስቀደም አንተ አለህ ።አላህ ይጨምርልህ አኺ!!!!

☀️ኢስላም☀️

22 Oct, 05:47


🔻በመጀመርያ መርካቶ በነበረው የእሳት አደጋ ንብረታችሁን ላጣችሁ ወንድሞቻችን አሏህ በተሻለ ይተካችሁ። ሶብሩንም ይስጣችሁ።

🔻በመቀጠል መርካቶም ሆነ ሌላም የንግድ ቦታዎች ላይ ያለን ሰዎች የትናንቱ እሳት ካለንበት የማጭበርበር ወንጀል ወደአሏህ እንድንመለስ ማንቅያ ደውል ነው። ሰዎችን ሸውደን ያልሆነ እቃ ሽጠን ምናካብተው ሀብት በደቂቃ እንደሚጠፋ ማሳያ ነው። ወደአሏህ እንመለስ!

@ibnyahya777

☀️ኢስላም☀️

22 Oct, 04:38


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

20 Oct, 13:36


ዋጋህን ባያውቁልህ ልታዝን አይገባም ፤ ሙሉ የአንድ መንደር ህዝብ ዋጋቸውን ባለማወቁ ለሙሳና ለኸድር (ዐለይሂመሰላም) በሩን መክፈት አልፈቀደም ነበር ... አላህ ዘንድ ለሚኖርህ ዋጋ ትጋ! ሰዎችን እርሳቸው! የድብቅ ዒባዳዎችን አብዛ!
(ከዚሁ ሰፈር የዐረብኛ ፖስት የተተረጎመ)
የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru

☀️ኢስላም☀️

20 Oct, 05:44


ሁላችንም የወደፊት ጀናዛዎች ነን ፣ እኛ የዱንያ አይደለንም ዱንያም የኛ አይደለችም።

☀️ኢስላም☀️

19 Oct, 11:19


👆🏻👆🏻👆🏻
📚የቴሌ እና ሌሎች አክሲዮኖችን ስለመግዛት


🔗 ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ustazilyas/1279

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

☀️ኢስላም☀️

15 Oct, 11:28


ከሶላት በኋላ የተስቢሕ አፈፃፀም
~
1- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ። 100ኛ "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለት። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
2- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 34 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [ሙስሊም]
3- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ ማለት። ድምሩ 99 ይሆናል። [ሙስሊም]
4. ሱብሓነላህ 10 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 10 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 10 ጊዜ ማለት። ድምሩ 30 ይሆናል። [ቡኻሪይ]
5. ሱብሓነላህ 11 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 11 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 11 ጊዜ ማለት። ድምሩ 33 ይሆናል። [ሙስሊም]
6. ሱብሓነላህ 25 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 25 ጊዜ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ 25 ጊዜ እና አሏሁ አክበር 25 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]

☀️ኢስላም☀️

14 Oct, 12:42


⚠️ያለፍቃዳቸው የሰዎችን ወሬ ከማድመጥ ተጠንቀቅ❗️

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنِ اسْتَمع إلى حَديثِ قَوْمٍ وهُمْ له كارِهُونَ، أوْ يَفِرُّونَ منه؛ صُبَّ في أُذُنِهِ الآنُكُ يَومَ القِيامَةِ﴾

“ሰዎች ሳይፈልጉ የነሱን ንግግር ያዳመጠ ሰው በዕለተ ትንሳዔ ጆሮው ዉስጥ የቀለጠ እርሳስ ይፈሰስበታል (ይደፋበታል)።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 7042

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

10 Oct, 08:40


በቂያማ እለት የአላህ ጎረቤቶች እነማን ናቸው?

ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿اللهَ لَيُنادِي يومَ القيامةِ: أين جِيرانِي، أين جِيرانِي؟ قال: فَتقولُ الملائكةُ: رَبَّنا ! ومَنْ يَنبغي أنْ يُجاوِرَكَ؟ فيقولُ: أين عُمّارُ المَساجِدِ؟﴾

“አላህ በትንሳዔ ዕለት ጎረቤቶቼ የታሉ፣ ጎረቤቶቼ የታሉ? በማለት ይጣራል። መላእክቶች ይላሉ፦ ጌታችን ሆይ! ላንተ ጎረቤት ሊኖርህ የተገባ አይደለም። አላህም መስጂድ አሳማሪዎች የታሉ? ይላል።”

ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 2728

☀️ኢስላም☀️

10 Oct, 07:55


አቡበክር አል አስመዒይ የተባሉ ሰው እንዲህ ይላሉ፦
በስራ በተባለችው ከተማ ጎዳና ላይ አንዲት አሮጊት "ሩማን" የተባለውን ፍራፍሬ በጭንቅላቷ ተሸክማ እየሄደች ሳለ አንድ ሰው ቀስ ብሎ ሳታውቅበት አንዲት ሩማን ወሰደባት (ሰረቃት) ። እኔም ይህንን ሰው ተከትዬ የሚሆነውን መታዘብ ጀመርኩ ፤ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ አንድ ሚስኪን ሰው አገኘና ከሰትየዋ የሰረቀውን ሩማን ለዚህ ሚስኪን ሰጠው።
አል አስመዒይ ወደዚህ ሰው ጠጋ አሉና "እጅግ የምትገርም ሰው ነህ እኔ ከሰትየዋ የሰረቅከው እርቦህ መስሎኝ ነበር ነገር ግን ሰርቀህ ለሚስኪን መስጠትህ በእውነቱ ገርሞኛል" አሉት።
ሰውየውም ፦ "ኸረ እኔ እርቦኝ አይደለም ይልቁንስ ከአላህ ጋር ንግድ እያጧጧፍኩ ስለሆነ ነው " አላቸው።
አል አስመዒይ እጅግ ተገርመው ፦ "ደግሞ እንዴት ነው ከአላህ ጋር የምትነግደው !?" ሲሉ ጠየቁት።
ሰውየው እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጣቸው ፦ "በእርግጥም ከሰትየዋ ሰረቅኳት አንዲት ወንጀል (ሰይዓህ) ተፃፈችብኝ ፤ ነገር ግን የሰረቅኩትን ሩማን ሰደቃ በመስጠቴ አስር ሀሳናት ተፃፈልኝ ፤ ጌታዬ ዘንድ ዘጠኝ ሀሰናቶች ቀሩልኝ ማለት ነው ታዲያ ከዚህ በላይ ምን የተሻለ ንግድ አለ!?" አላቸው።
አል አስመዒይ እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡት፦ " አዎን ሰትየዋን ሰረቅካቸው አላህ ዘንድ አንድ ወንጀል ፈፅመሃል ተብሎ ተፃፈብህ ፤ ግና የሰረቅከውን ሰደቃ ብትሰጥም አላህ አይቀበልህም ፤ ምክንያቱም አላህ ጥሩ ነው ጥሩ ስራን እንጂ አይቀበልም ፤ አንተ እኮ ልብሱ ተነጅሶበት በሽንት እንዳጠበ አይነት ሰው ነህ" አሉት።
ዛሬ በዘመናችን ስንት እንዲህ አይነት ሰዎች አለን!?
ለራሱም ይሁን ለሌላው እንደመሰለው ፈትዋ የሚሰጥና በስሜት የሚጓዘው ስንቱ ነው!? ስንቱስ ነው ሀራሙን ሀላል ፤ ቢድዐውን ሱና የሚያደርግና ነፍስያውን ሀቅ ላይ ነሽ እያለ ራሱን የሚያታልለው !?
አጀበን!

☀️ኢስላም☀️

10 Oct, 07:47


ውዱእ ያለው ሰው ነጃሳ ቢነካው ውዱኡ አይጠፋም። ነጃሳው እርጥብ ከሆነ ነጃሳውን ማጠብ ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ነጃሳው ደረቅ ከሆነ ቢነካውም ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም፡፡ ውዱኡም ላይ ይሁን የነካውም ቦታ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ የለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

☀️ኢስላም☀️

09 Oct, 05:39


የመካ  ሙሽሪኮች በአላህ ፈጣሪነት  ያምኑ ነበርን  ?  ...የ ኡሉሁያ ጉዳይ እና ተያያዥነት ያላቸው መስአላዎች


https://t.me/Muhammedsirage

☀️ኢስላም☀️

07 Oct, 07:57


በዑመር ኢብኑ ኸጣብ ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሞ ነበር

ዑመር እንዲህ አሉ ! ወይ እኔ ወይ እናንተ አላህን አምፀናል ወንጀል ተዳፍረናል አዲስ ነገርን ፈጥረናል .....

☀️ኢስላም☀️

07 Oct, 07:27


በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው።
በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች። ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል።
ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው።
በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር። ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል። ወደ አላህ እንመለስ። ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን። አላህ እንዲታረቀን፣ በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል። አላህ ምህረቱን ይለግሰን!!

☀️ኢስላም☀️

04 Oct, 06:05


የጀግኖች ህይወት ምን እንደሚመስል ከጋዛ ሴቶች ተማር

ጀነት በራፍ ላይ ቆመህ "በሰላም ግቧት" የሚለውን የመላኢኮች ጥሪ ስትሰማ የዱንያ መሪር ቀናት ችግር ጉስቁልናው እርግፍ ብሎ ይወገድልሀል አዎ ጀነት በር ላይ ብቻ! ረቢ አደራ ጀነትህን!

☀️ኢስላም☀️

02 Oct, 11:38


መረጋጋት ምንጩ ይች አለም ጠፊ መሆኗን እኛም ከአፍታ በኋላ የማንገኝ መሆኑን ማመኑ ላይ ነው (ኢልመል የቂን)። የሞቱ ሰዎች ሁሉ የሄዱት ብልጠት ጎድሏቸው አይደለም። አትጨናነቅ ህይወት ሂደት ነው።

☀️ኢስላም☀️

02 Oct, 11:23


🌹 ጡባ ‘ጀነት’ አለው!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿طُوبى لِمَنْ ملك لسانَهُ، ووسِعَهُ بيتُهُ، وبَكى على خطيئتِهِ﴾

“ምላሱን ለተቆጣጠረ፣ ቤቱም ለሰፋው፣ ለሀጢያቱም የሚያለቅስ ጡባ (ጀነት) አለው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 3929

▫️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

01 Oct, 12:00


ስኬታማና ደስተኛ በሆንክበት ወቅት ቆመው ከሚያጨበጭቡልህ ሺህ ሰዎች ይልቅ ስትወድቅ ወይም መንገድ ስትስት አብሸር ብሎ ከወደቅክበት የሚያነሳህና የሚያፅናናህ አንድ ሰው የተሻለ ነው።

☀️ኢስላም☀️

30 Sep, 07:51


⚠️⚠️ ስራህ ብቻውን ከጀነት አያደርስህም…

ከአቡ ሁረይራ (▫️) ተይዞ፡ ረሱል (🤲) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لن يُدخلَ أحدًا منكُم عملُه الجنةَ قالوا ولا أنت يا رسولَ اللهِ قال ولا أنا إلا أن يَتَغَمَّدَنِيَ اللهُ منه بفضلٍ ورحمةٍ﴾

“አንዳችሁም በሚሰራው መልካም ስራ ብቻ ጀነትን አይገባም። ሶሃበቹም አሉ፦ አንተም ብትሆን የአላህ መልዕክተኛ? እኔም ብሆን! አላህ በእዝነቱና በትሩፋቱ ሸፍኖኝ ቢሆን እንጂ።”

📚 ቡኻሪ (5673) ሙስሊም(2818) ዘግበውታል

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

☀️ኢስላም☀️

23 Sep, 06:20


ካንተ የባሱ መጥፎ ለነበሩ ሰዎች፤ አንተ ከሰራሃቸው በላይ የከበዱ ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ጌታዬ ይቅር ብሏልና አንተም ተስፋ አትቁረጥ ወደርሱ ተመለስ። إنه ربى

1,256

subscribers

1,129

photos

321

videos