Alif media @alif_media_1 Channel on Telegram

Alif media

@alif_media_1


Alif media (English)

Alif media is a Telegram channel dedicated to providing the latest news and updates on the entertainment industry. With a focus on movies, music, and TV shows, this channel is your go-to source for all things entertainment. Whether you're looking for movie reviews, celebrity gossip, or behind-the-scenes insights, Alif media has got you covered. The channel is updated regularly with fresh content, so you'll never miss out on the latest trends. Join the community of entertainment enthusiasts and stay connected with Alif media for all your entertainment needs. Who is it? Alif media is a channel for anyone who loves keeping up with the latest news and updates from the world of entertainment. What is it? Alif media is a source of entertainment news, including updates on movies, music, and TV shows. Don't miss out on the latest trends - join Alif media today!

Alif media

06 Feb, 19:44


መልካም ሪዝቅ
መልካም አዳር
መልካም እንቅልፍ

ተወፍቃችሁ እደሩ ወዳጆቼ።

Alif media

06 Feb, 14:34


ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል፡- “ሸዕባን እንደ ረመዷን መግቢያ ስለሆነ በረመዷን የተደነገገው እንደ መፆም እና ቁርኣን ማንበብን የመሳሰሉ በውስጡ የተደነገገው ለረመዷን መምጣት ለመዘጋጀት እና በዚህም ነፍስን በጣም ለማለማመድ በውስጡ ተደንግጓል።
ሀቢብ ኢብኑ አቢ ሳቢት
የሻዕባን ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር።

"ይህ(ሸዕባን) ወር የቁርዓን አንባቢዎች(ቁራዖች) ወር ነው።

Alif media

04 Feb, 06:20


የሐረሩ_ጀግና

                   ኢማም_አህመድ

                         ክፍል
5



የሽምብራ ኮሬው ጦርነት እንደለመደው ዐፄው ሙስሊሙ ላይ ጥቃት ሰነዘረ። በዚህ ጊዜ ጦርነቱ ተጀመረ። ሁለቱ ሠራዊቶች ተገናኙ። የቀስተኞች ፍላፃ አየሩን ሞላው። ሰይፍ ከሰይፍ ተጋጨ። የፈረሶች ኮቴ ያስነሣው አቧራ ወደ ሰማይ ተበትኖ እንደደመና ፀሐይን ጋረዳት። የዐፄ ልብነ ድንግል ጦር ጥቃቱን አፋፋመ። ወደ ማሸነፍ ተቃረበ። በግራ በኩል የሶማሌያውያን ጦር ነበር የተሰለፈው። በዚህ ብርጌድ የጊሪ ጎሣ፣ መራይሃን፣ ይቤሪ፣ ሃርቲ፣ ጀራን፣ መዛር፣ እና ባርሱብ ጎሳዎች ሁሉም በጎሣው አለቃ መሪነት ተሰልፈዋል። ጦርነቱ ሲያይል ከግራው ሱማሌ ብርጌድ ሦስት ሺህ ሙስሊሞች ተሰዉ። የተቀሩት መሸሽ ጀመሩ። ሆኖም ዋና ታላላቅ የጎሣ መሪዎቹ እነ መታን ቢን ዑስማን፣ አሕመድ ጊሪና ዐሊ ገራድ (የመታን ወንድሞች)፣ የበሻራ ወንድም፣ ዐሊ ማድ ጂራ፣ ሑሴን ሙሳ ቢን ዐብደላህ ማኪዳ እና ዩሱፍ ለተሂያ ንቅንቅ ሳይሉ በአስደናቂ ሁኔታ ተጋደሉ ።

በተለያየ አቅጣጫ ሙጃሒዶች መሰዋታቸው እየበዛ ሄደ። ማፈግፈግም ሆነ መሸሽ ብሎ ነገር የለም። ጦርነቱ በረታ። አቧራ አየሩን ሞላው። ጦሩ የራሱን ወገን መለየት ሁሉ አቃተው። ‹‹አላሁ አክበር!››… ‹‹የሙሐመድ ጦር ጽኑ!››… ‹‹ላ ኢላሃ ኢለላህ!››… ‹‹ድል የኢስላም ነው!›› እና መሰል መፈክሮች በተደጋጋሚ በሙጃሒዶቹ መካከል እዚያም እዚህም ይሰማሉ። ሙጃሒዶች ንቅንቅ ሳይሉ መጋደል ቀጠሉ። የዐፄውንና የኢማሙን ጦር ብዛት ስናነጻጽር ልዩነቱ ሰፊ ነበር። 216,000 ለ 12,560 !!! እያንዳንዱ የኢማሙ ወታደር 17 ክርስቲያን ወታደሮችን ነበር የገጠመው። ከቀኑ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ ሙስሊሞች የበላይነቱን ተቆጣጠሩ። የኢማሙ ጦር ማሳደድና መማረክ ቀጠለ። ከዐፄ ልብነ ድንግል ጦር ታላላቅ መሪዎች ተገደሉ። የተረፈው መሸሹን ቀጠለ። 10 ሺህ ወታደሮች ተገደሉ። ታሪኩን በጦርነቱ ላይ በመገኘት ዐረብ ፈቂህ ‹‹ፉቱህ አል ሐበሻ›› በተሰኘው መጽሐፉ እንደተረከው 5 ሺህ ሙስሊሞች ተሰውተዋል። ይልማ ደሬሳ የሟቾቹን ቁጥር ከተጠቀሰው ከፍ ያደርጉታል። እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-

በዚህች ቀን ሽምብራ ኩሬ ላይ የሞቱት የኢትዮጵያ ሰዎች ከክርስቲያኑ ሠራዊት 12 ሺህ፣ ከእስላሞች ከ 6 ሺህ
የሚበልጡ ወታደሮችና የጦር መኮንኖች ናቸው ሲል ታሪክ መዝግቧል።… #ኢማምአህመድ ሽምብራ ኩሬ የኢትዮጵያ ታሪክ መንገድ የለወጠችበት ቀንና ቦታ ነች። (የኢትዮጵያ ታሪክ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን፣ ገጽ 66) የሽምብራ ኩሬው ጦርነት የክርስቲያኑን ሠራዊት ወኔ አንኮታኩቶታል። በጦርነቱ የተገደሉት ከ 10 -12 ሺህ ቢሆኑም የተቀረው 204 ሺህ 206 ወታደር እግሬ አውጪኝሲል መሸሽን መርጧል። ይህ የኢማሙ ሠራዊት የጂሐድ......

ምንጭ (የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ከ615–1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ በአህመድን ጀበል በ2003 ከታተመው መፅሀፉ የተወሰደ ።


ክፍል 6
                                 

                 ይቀጥላል ......

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

03 Feb, 19:25


-የፕሮግራም ጥቆማ

መቀመጫውን በደሴ ከተማ ያደረገው መርከዘል አቅሷ የሴቶች እና የወንዶች የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ከ2008 ዓ.ል ጀምሮ ላለፉት ስምንት አመታት በርካታ ታዳጊዎችን ቁርአንን በተጅዊድ በማስሐፈዝ እንዲሁም የተለያዩ የተርቢያ ትምህርቶችን በማስተማር ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።

አሁን ደግሞ መርከዙ ባለፉት ጊዜያት ያስተማራቸውን ተማሪዎች የካቲት 2/2017 ዓ.ል ሁለተኛ ዙር ምርቃቱን በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ታላላቅ ኡለማኦችና ኡስታዞች በተገኙበት ያካሂዳል።በመሆኑም እርሶም በዚህ ዝግጅት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

© ሀሩን ሚዲያ

Alif media

03 Feb, 06:45


የጫት መዘዙ

Alif media

03 Feb, 06:32


የትምህርት ሚኒስቴር Exit Examን በጁምዓ ሰዓት አድርጓል!

ጁምዓ ቀን በመንግስት መስሪያ ቤቶች ደረጃ ከ5:30 - 7:30 ለስግደት በሚል ዝግ እንደሆነ ይታወቃል:: የፌደራል መጅሊስ በቅርቡ በሰጠው ፈታዋም የጁምዓ ሶላት የደረሰበት ማንኛውም ሙስሊም ወደ መስጂድ ሄዶ መስገድ ግዴታው እንደሆነ አሳውቋል:: ሆኖም የትምህርት ሚኒስቴር የመውጪያ ፈተናን በመጪው ጁምዓ ከ5:30 - 8:00 ለመስጠት ፕሮግራም አውጥቶ ሙስሊም ተማሪዎችን ከጁምዓ ሶላትና ከፈተናቸው እንዲመርጡ የሚያስገድድ ሁኔታ ፈጥሯል:: ይህ ሀገራችንን የምትመራበትን መመሪያ መጣስ ብሎም የሙስሊም ተማሪዎችን መብት መዳፈር ነው::

በትምህርትም ሆነ በፈተና ፕሮግራም ከትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ከዩኒቨርሲቲዎች ወይንም ከበታች ትምህርት ቤቶች በተደጋጋሚ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶች በዘላቂነት ሊፈቱ ይገባል:: ካላንደር ከሌላቸው ወይንም ስለሙስሊሙ መሠረታዊ መብቶች እውቀቱ ከሌላቸው እንዲያውቁ ይደረጉ:: እየረሱ ወይንም ሆን ብለው እያበላሹ ከሆነ ደግሞ መንግስት ብዙም የማይረሳና የማያበላሽ ሰው በቦታው ላይ ያስቀምጥ::

Alif media

01 Feb, 15:10


የቁርዓን ውድድሩ ነገ ከጧቱ 12:30 ጀምሮ ይካሄዳል:: ትኬቱ በመደበኛ 800 ብር ሲሆን ለተማሪ ደግሞ 400 ብር ነው:: በአዋሽ: ሒጅራ: ዘምዘም ባንክ እና በቴሌብር ማግኘት ይችላሉ::

የቻላችሁ መቁረጥ አትዘንጉ:: በጣም የምትችሉ መጋበዝ አትዘንጉ:: especially የመድረሳ እና የግቢ ተማሪዎችን ጋብዙ:: ከዚያ አልፎ የሚተርፍ ትኬት ካለ አዘጋጆች ለሚቸግራቸው ሰዎች በነፃ ስጡ::

ፕሮግራሙ ታሪካዊ ነው ••• የሚችለውም የማይችለውም የሚሳተፍበት መንገድ ቢመቻች ጥሩ ነው!

ጋባዥ ከተገኘ ና

Alif media

01 Feb, 07:38


      የሐረሩ_ጀግና

                   ኢማም_አህመድ

                         ክፍል
4



70 00 ሺ እግረኛ ነቅድያ አብዱል ከሪም ቢን ኡስማን (ደዋሮ) ➾ኡመር ቢን አብደሏህ፣ኡስማን ቢን አብደሏህ እና ሙሀመድ በተባሉ5ት ሰለምቴወች አሚርነት ስር አዋቀረ።


የክርስቲያኑ ጦር #ሙስሊሙን ለማጥቃት ሲመጣ መመከቱ እንደሚያስጠቃ የተረዳው ኢማም ከመከላከል ይልቅ የማጥቃት ስተራቴጅን ተከተለ ትግሉ በሙስሊሙ ክልሎች ሳይሆን በአፄው ይዞታ ውስጥ መሆን እንዳለበትም ወሰነ ደዋሮን በማጥቃት ከክረስቲያኑ መንግሰት አገዛዝ ነፀ አወጣ ወደ ክርስቲያኑ አገር ጦሩ ሄዶ እንድያጠቃም አዘዘ ባሌቤቱ ባቲ ድል ወንበሯ አብራ ለመዝመት ተዘጋጀች ጦሩ በሷ መዝመት ደስተኛ አልነበረም።ቅሬታውን እንድህ ሲል አስቀመጠ: – ባለቤትህ ባቲ ድል ወንበሯ ወደ ሙስሊሞች አገር ካልተመለሰች በቀር ወደ #ሀበሻ ( ሰሜን) አብረንህ አንሄድም። እርሷ ወደ ከሀድወች ሀገር ከኛ ጋር አትሄድም። ከአንተ በፊት ከነበሩት አሚሮች መካከል አንዱም ወደዘመቻ ሲሄድ ሚስቱን አላስከተለም።አንተ ብቻ ነህ። ባቲ ድል ወንበሯ ግን ከባሏ ጋር ጅሀድ ካልሄድኩ ብላ ለመመለስ ፍቃደኛ ሳትሆን ቀረች።በዚህ በመጀመሪያው ዘመቻ እስከ ኢፋት ድረስ ሸኘቻቸው።በሇላ ላይ ግን በሌሎች ዘመቻወች አብራቸው ዘምታለች።
    
የኢማሙን አይ በገሬነት ያሳየው ታላቁ ጦርነት የሽምብራ ኮሬው ጦርነት ነበር። ኢማሙ ከዚህ ጦርነት በፊት የተለያዩ ድሎችን
ቢያስመዘግብም➣የሽምብራ  ኮሬው ግን ወሳኙና የአፄውን ጦር ያላሸቀ ነበር። ሽምብራ ኮሬ በአዳማና ቢሾፍቱ መካከል በሞጆ ወንዝ አቅራቢያ
ነበር የተካሄደው።

ኢማም አህመድ ጦሩን አደራጅቶ ከጨረሰ በሇላ ከዝቋላ ወደ ሞጆ ወንዝ አቅራቢያ ተጓዘ። በማርች 7—1529 ኢማሙ ስትራቲጅያዊ በሆነው የሽምብራ ኮሬ መንደር ጦሩን አሰፈረ።
    
    
የአፄ ልብነ ድንግል ጦር ኢማሙ ዝቋላን ለቆ   መሄዱን ተመለከተ።ወደ ሞጆ ተከተለው። የሽምብራ ኩሬ ጦርነት ሊጀምር ነው– ማርች11 – 1529። ልብነ ድንግል 16 ሺህ ፈረሰኞችና 200ሺህ እግረኛ ጦር አሰልፏል። ኢማም አህመድ በበኩሉ 56

       ኢማም አህመድ በበኩሉ 560 ፈረሰኞችና 12ሺህ እግረኞች ሰራዊት አሰልፏል ።ይልማ ደሬሳ ስለ ክርስቲያኑ ጦር ብዛት

እንድህ ሲሉ ፅፈዋል: —

የሰራዊቱ ብዛትና የመሪወቹ ጀግንነት የኢስላምን ሰራዊት ልብ ትር ትር ማሰኘቱ አልቀረም።አህመድ ኢብራሂም ግን በልቡ ቆራጥነትና በነፍጦቹ ተመክቶ ይህ መአት የሆነ ሰራዊት ሳያወላውል ለመግጠም ተዘጋጅቶ ቆየ።


ሙስሊሙን ሲጨፈጭፍ የነበረው የአፄው ጦርና ኢማሙ ሊገጥሙ ተፋጠዋል።ጂሀዱ ሊጀምር ነው።የኢማሙ ጦር የዳእዋ
ክፍለ ሙስሊሙን ማነሳሳት ጀመረ።የቁርአን አስተማሪው ሸኽ
አቡበክር ቢን ነስረድ ቢን ሙሀመድ(አርሹናእ)ለሙስሊሙ ጦር ስለ ጅሀድ ዳእዋ አደረገ ። ስለ ጀነት ታላቅነት ለኢስላም ሲሉ በፅናት መዋጋት እንዳለባቸው መከረ።ሸሂድ(መስዋእትነት) ስለመሆን በማስታወስ ሙጃሂዱን
አስለቀሰ።ብዙ መከራቸው የጅሀድ ስሜታቸውን
አነሳሳ።በመጨረሻም ከቁርአን ምእራፍ 9 ቁጥር 111 እንድህ ሲል አነበበላቸው። <<አላህ ከአማኞች ነፍሶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገዛ ። በለውጡም ጀነት(ገነትን) አዘጋጅቶላቸዋል።በአላህ መንገድ ይፋለማሉ።
ይገድላሉ፣ይገደላሉም።(ይህ)በእርግጥም ተፈፃሚ የሚያደርገው የተስፋ ቃሉ ነው።ከተውራትም፣ከኢንጅልም፣
ከቁርአንም ውስጥ አስፍሮታል።ከአላህ ይበልጥ ቃል ኪዳኑን የሚሞላ ማን ነው? በፈፀማችሁት ሽያጭ ተደሰቱ።ይህ ታላቅ ስኬታማነት ነው።>> ጦሩ የጂሀድ ስሜቱ ተቀጣጠለ ። ለኢስላም ሲል ለመሞት ቆረጠ።ኢማሙን <<እናጥቃቸው>> ሲል ጠየቀ።

ኢማሙ ግን <<ቦታችሁን ያዙ።እነርሱ መጋደል እስኪጀምሩ ድረስ ጥቃት አትጀምሩ።ጦራችሁን በተጠንቀቅ ያዙ።ከቆዳ የተሰራውን
የጦር መከላከያ ልብስም ልበሱ።አላህን እያስታወሳችሁ ቢሆንጅ
ለአንድት እርምጃ እንኳን እግራችሁን አታንቀሳቅሱ>>ሲል አዘዘ። << አላህ ሆይ!ሁላችንንም ታጋሽና ለሀይማኖት አሸናፊወች
አድርገን>> ሲል አላህን ለመነ። እንደለመደው አፄው ሙስሊሙ ላይ ጥቃት ሰነዘረ። በዚህ ጊዜ ጠርነቱ ተጀመረ.......

ምንጭ (የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ከ615–1700 የጭቆናናየትግል ታሪክ በአህመድን ጀበል በ2003 ከታተመው መፅሀፉ
የተወሰደ)


ክፍል 5
                                 

                 ይቀጥላል .....

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

01 Feb, 06:07


ዕለተ ቅዳሜ ጥር 24፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂዳል።

በሌላ በኩል የምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከሙስሊም የህግ ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ መረጃዎቹን እየተከታተለ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ።

Alif media

31 Jan, 13:56


የሐረሩ_ጀግና

ኢማም_አህመድ

         ክፍል 3


  ......... ሱልጣን አቡበክር ኢማም አህመድን ለመግደል ማሴር ጀመረ። ስምምነቱ በሱልጣኑ ተጣሰ።የኢማሙ ወዳጆችን ገደለ። በመሆኑም ኢማሙ ከ3 ፈረሰኞች ጋር በሌሊት ወደ ትውልድ መንደሩ ዘእካ ከተማ ሸሸ።

ሱልጣኑ ኢማሙን ሊገድል በመፈለግ ያለበትን ለማወቅ በየስፍራው ሰላዮችን ላከ ። ዘእካ መኖሩን ሰምቶ ጦርላከበት።የኢማሙን ቤት አቃጠሉ፣ንብረቱን ዘረፉ፣ሆኖም ኢማሙን ሊያገኙት አልቻሉም።ኢማሙ ከቦታ ቦታ ይሸሽ ጀመር ።

በኡለሞች ጫና ዳግም በመካከላቸው ስምምነት ተደረሰ።ሱልጣኑ ሸሪአን እንድጠብቅ ፣ይህ የሚሆን ከሆነ ኢማሙ ለሱልጣኑ ሊታዘዝ ተስማሙ።ከጥቂት ቀናት በሇላ ሱልጣኑ ወደነበረበት ተመለሰ።ፈሳድ ተስፋፋ።አሁንም ኡለሞች ለሶስተኛ ጊዜ ለማስማማት ጣሩ። አሁን ግን ሱልጠኑ ስምምነቱን ተቃወመ።ኢማሙን ለመግደልም ዛተ። ጦር አዘመተ ። ኢማሙ ለፈሳድ መስፋፋት ምክኒያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክርን ማስወገድ ብቸኛው መፍትሄ ሆኖ አገኘው እናም ጦር ገጠመው ሱልጣን አቡበክር ተገደለ።

ኢማሙ የሱልጣኑን ወንድም ኡመረዲንን በሱልጣንነት ሾመው። ደገልሀን የተሰኘው የአፄ ልብነ ድንግል አማች በኦክቶበር 18ቀን 1525 አዳልን አጠቃ። ኢማም አህመድ ከሀረር በስደቡብምእረብ በሚገኘው አማሬሳ ወንዝ አቅራቢያ ጦሩን አደራጀ። ደገልሀንን <ድር>በተሰኘ ስፍራ ( የዛሬዋ ድሬዳዋ አቅራቢያ) ገጠመው።ኢማሙ ድል አደረገ በርካታ ሰራዊትማረከ። ቀሪውን ደመሰሰ። ቀጥሎ ወደ ሱማሌ ክልል በመሄድ ማረጋጋትን አሰፈነ። ተበታትኖ የነበረው ህዝበ ሙስሊም አደራጀ። አሰለጠናቸው በስነ ምግባር አንፆ ለጂሀድ አዘጋጃቸው የ21 አመቱ ኢማም ሰራዊቱን ይዞ በ527 (በ934 አመተ ሂጅራ) በድል አድራጊነት ሀረር ገባ ። ሰራዊቱን በክፍለ ጦር አዋቀረ።

በአሚረ ሁሴን አል ተጉሪ የሚመራውን መቶ ፈረሰኞች እና እግረኞች ያሉበትን ክፍለ ጦር ቀይ ባንድራ አስይዞ አዘመተ። መቶ ፈረሰኞችና እግረኞች ያሉበትን ሌላ ክፍለ ጦር በወዚር ኑር መሪነት ነጭ ባንድራ አስይዞ ለጂሀድ አሰማራ 200 ፈረሰኛና እግረኞች ያሉበትን ሰራዊት ኢማሙ በራሱ መሪነት በቢጫ ባንድራ ስር አዋቀረ ።
እንድሁም 7000 ሺ እግረኛ ነቅድያ አብዱል ከሪም ቢን ኡስማን (ደዋሮ) ኡመር ቢን አብደሏህ፣ኡስማን ቢን አብደሏህ እና ሙሀመድ በተባሉ 5ት ሰለምቴወች አሚርነት ስር አዋቀረ።

     
ክፍል 4
                                 

                 ይቀጥላል ......

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

31 Jan, 07:49


ሳላይህ አመንኩብህ፣
ሳላይህ ሰገድኩልህ፣
ሳላይህ ለመንኩህ፣
ሳላይህ ተመካሁብህ፣
ያየኸኝ እና ያየሁህ ቀን እዘንልኝ፣
ካንተ መገናኘቴን አሳምርልኝ።

ያ ረብ ።


https://t.me/Alif_media_1

Alif media

30 Jan, 18:47


Alif media pinned «"  ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አልጋዚ "                              ክፍል 2 ........ ወዳጁ ገራድ አቡኑ የተገደለበት ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም የሱልጣን #አቡበክር ጦር ከቁርአንና ሱና መንገድ መውጣት አበሳጨው። ሸሪአን ባለመጠበቁ ተናደደ።ወደ ትውልድ መንደሩ ሁበት ተጓዘ። ጦር ያደራጅም ጀመር።ከመቶ በላይ ፈረሰኛ ጦር አሰባሰበ። ለሙስሊሞች ነፃነት ሲታገሉ የተሰውትን…»

Alif media

30 Jan, 18:36


ደይፍ ይሉታል እንግዳ እንደማለት ነው። በእርግጥም እርሱ በወራሪዋ ደህንነቶች ታድኖ ሊገደል፣ ተጠፍሮም ሊያዝ ያልቻለ አሳዳጆቹ እጅ ሳይገባ ሀያ ዘጠኝ አመታቶችን ያስቆጠረ ሁሌም እንግዳ ሰው ነበር።

በማለዳ ተነስተው ከስክስ ጫማቸውን አጥልቀው ሮጠው ያላገኙት፣ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ያልደረሱበት የጥይት አሩር እየተኮሱ ቦንብ ከአውሮፕላን ቢያዘንቡ ፍፁም ሊገሉት ያልቻሉት የፍልስጤማዊያን ቁልፍ ሰው።

ለበይኪ ያ አቅሳ ብሎ በለጋ ዕድሜው የተነሳ ወጣትነቱን በትግል ያሳለፈ ትንታግ። ወንድሞቹ ሲሞሻለቁ፣ እህቶቹ በድምፅ አልባ መሳሪያ ሲወቁ ትከሻም ልቡም ለመሸከም አልፈቀዱለትም፡፡ ድንቡሽቡሽ ፊት ያላቸው እንቦቃቅላ ልጆቹን ትቶ፣ የእናቱን የእጅ ደበሳ ርቆ በጂሃድ ሜዳ ላይ ተሰየመ፡፡

የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የመሐፈዝ አቅሙ ከፍተኛ የሰማውን ቀብ፣ ያየውን ልቅም አድርጎ የሚይዝ ፈጣን ነው። በየትኛውም ቴሌቪዥን ታይቶ አይታወቅም። ምንም አይነት ቴክኖሎጂ የማይጠቀም ባለ ዊልቸሩ የጦር መሪ።

አባቱ ልብስ እየሰፉ በአነስተኛ የዶሮ እርባታ እንቁላል እየሸጡ ያሳደጉት ልጅ ዛሬ ስሙን እንጂ ማንነቱን ለማወቅ የከበደው ሰው ሙሐመድ ደይፍ ነፍሱ ከምትወደው አላህ ጋር መገናኘቱን አቡ ዑበይዳ ተናግሯል። ሸሂድ ሆኗል ሲል እንባ እየተናነቀው አውስቷል። ኢላ ረህመቲላህ ያ አቡ ኻሊድ


              Mahi Mahisho

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

30 Jan, 18:07


ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የቀሳሞች ጦር መሪ ሙሐመድ ደይፍ ወደማይቀረው አለም መሸጋገሩን አቡ ዑበይዳ በይፋ አስታውቋል።

አላህ ቀብሩን ኑር ያድርግለት

Alif media

30 Jan, 17:57


"  ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አልጋዚ "
 
                           ክፍል 2


........ ወዳጁ ገራድ አቡኑ የተገደለበት ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም
የሱልጣን #አቡበክር ጦር ከቁርአንና ሱና መንገድ መውጣት አበሳጨው። ሸሪአን ባለመጠበቁ ተናደደ።ወደ ትውልድ መንደሩ ሁበት ተጓዘ።
ጦር ያደራጅም ጀመር።ከመቶ በላይ ፈረሰኛ ጦር አሰባሰበ። ለሙስሊሞች ነፃነት ሲታገሉ የተሰውትን የኢማም መህፉዝ ልጅ ባቲ ድል ወንበሯን አገባ። ዝነኛ ሆነ።ከሱልጣን አቡበክር ጋር ትግሉን ቀጠለ።"#ኢማም#" የሚል የማእረግ ስያሜ ተሰጠው። ይህ በእንድህ እንዳለ ፋኑኤል የተሰኘ የክርስቲያን የጦር መሪ ከደዋሮ አቅጣጫ ወደ ሁበት ዘመተ።ወታደሮቹ ሙስሊሙን አጠቁ፣ገደሉ፣ንብረትን ዘረፉ<<ከሙስሊሙ የሚቋቋመው ማን አለ? > በሚል ስሜት እንደለመዱት የሙስሊሙ ህፃነትንና ሴቶችን ማርከው ይዘው ሄዱ። በአቅራቢያው ለነበረው ኢማም አህመድወሬው ደረሰ።የራሱን ሰራዊት ይዞ የፋኑኤልን ጦርተከተለ።<አቂም>(አማሬሳ)ወንዝ ተገናኙ። በመካከላቸው ከፍተኛ ውጊያ ተካሄደ ። ኢማሙ ከጠላት ጦር መሀል ገብቶ አጠቃ ።ሌሎች በግራ አቅጣጫ የፋኑኤልን ጦር አጠቁ።ከራሱ ላይ የብረት መከላከያ ባጠለቀው ፋኑኤል የተመራው ጦር የቀኝ ክንፍ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈተ። በመጨረሻም #ኢማም #አህመድ የመጀመሪያው የሆነውን ጂሀድ በድል አድራጊነት ተወጣ ። ከ ጠላት ወገን 60 #ፈረሰኞችና እግረኞች ተማረኩ በርካቶችምተገደሉ።

የጦር መሳሪያም ማረኩ።የተማረኩትን ሙስሊሞችአስለቅቀው በድል አድራጊነት ወደ ዚፋህ ከተማ ገቡ። የኢማሙ ገድልና ዝና ናኘ።በአቅራቢያው የነበረው ሱልጣን አቡበክር ከአካባቢው ሸሸ። ኢማሙ ባገኘው ድልና ምርኮ ተናደደ። ኢማሙ የሱልጣኑን ሁኔታ ሰማ።ሁለቱም ጢርነት ገጠሙ። ሱልጣኑ ተሸንፎ ሸሸ። ኢማሙም ወደ ሀረር ከተማ ገባ።ሱልጣኑ በርካታ ሰራ ዊት መልምሎ ኢማሙን ለማጥቃት ተመመ።

ኢማሙ ደግሞ ሀረርን ለቆ ወደ ሁበት ሸሸ።የሱልጣኑ ጦር ተከተለው።ኢማሙ በሁበት ተራራ (ጋረ ሙለታ)ላይ ወጣ የሱልጣኑ ጦር ተራራውን ከበበ።ለ2 ሳምንታት አላንቀሳቅስ አለ። በዚህ የተሰላቸው የኢማሙ ጦር በምሽት ከተራራው ወር ጦርነት ገጠሙ። ከኢማሙ ጦር ውስጥ አሚር የነበረውኡመረድን ተገደለ።ኢማሙና ተከታዮችም ወደ ቀያቸው አቀኑ።በኢማም አህመድና በሱልጣን አቡበከር መካከል በኡለሞችአማካኝነት ስምምነት እንድፈጠር ተደረገ።በስምምነቱ መሰረትኢማሙና ሰራዊቱ የሱልጣኑን ጦር እንድቀላቀሉ ተደረገ።

ሱልጣኑም ሸሪአን ሊጠብቅ ተስማሙ።ሇኖም ስምምነቱ ከጥቂትቀናት በላይ አልዘለቀም።ሱልጣን አቡበክር ኢማም አህመድንለመግደል ማሴር ጀመረ።ስምምነቱ በሱልጣኑ ተጣሰ።የኢማሙወዳጆችን ገደለ። በመሆኑም ኢማሙ ከ3 ፈረሰኞች ጋር በሌሊትወደ ትውልድ መንደሩ ዘእካ ከተማ ሸሸ ..........

#ክፍል3
ይቀጥላል..................

ምንጭ (የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ከ615–1700 የጭቆናና
የትግል ታሪክ በአህመድን ጀበል በ2003 ከታተመው መፅሀፉ
የተወሰደ)


{አቅራቢ  ➫➫ Alif media }

{ፖስቱን  ሸር በማድረግ ለሌሎችም ያስተላልፉ።}

ቴሌግራም   ግሩፕ ሊንክ
 
https://t.me/Alif_media_1

Alif media

30 Jan, 13:20


"  ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አልጋዚ "

ክፍል 1

ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አልጋዚ በ1506 ተወለዱ። የተወለዱት በሀረር አቅራቢያ ‘ ሁበት’ በተባለ ስፍራ ልዩ ስሙ ‘ዘእካ ’ በተባለ መንደር ነበር⁴³³። እንደ ብሮካምበር ገለፃ ሁበት በደቡብ ምእራብ ሀረር ከሚገኘው ‘ጋረ ሙለታ‘ ተራራ አካባቢ ነበር ።⁴³⁴ ሁበት ከሀረር ከተማ 32 ኪሎ ሜትር (20ማይል) ይርቃል።⁴³⁵ የልጅነት ጊዜውን በዚያው በሁበት አሳለፈ።አባቱን ኢብራሂምን ከባርነት ቀንበር ነፃ ባወጡት አድሊ(አዶሊ) ጥበቃና ቁጥጥር ስር አደረገ።⁴³⁶

አዶሊ በአህመድ ስብእና ላይ ተፅእኖ ፈጣሪ ነበሩ።
አህመድ በወጣትነቱ በተደጋጋሚ ጥቃት የተዳከመችውን አዳልን በማረጋጋትና ወንጀልን በመዋጋት ከገራድ አቡን ጋር ተሰለፈ። በገራድ አቡን ጦር ውስጥ ፈረሰኛ ሁኖ ትግሉን ጀመረ። በአህመድ አርቆ አሳቢነት እና ቆራጥነት የተደመመው ገራድ አቡን እጅግ አቀረበው።
 
የሱልጣን አቡበክር አስተዳደር የሙስሊሙን ባህል በመጠበቁ ረገድ ተዳከመ።ኢስላማዊ ያልሆኑ ባእድ ባህሎች  ወደ ሙስሊሙ በስፋት በስፋት መቀላቀል ያዙ ። ገራድ አቡን ቢን አዳሽ ለ3 አመታት ሰላም በማውረድና በማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት አደረገ። በአካባቢው የተከሰተው መጥፎ ገፅታ ለመለወጥም በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ጀመረ። ቁማርን አገደ፣ሽፍቶችን በቁጥጥር ስር አዋለ፣የሙዚቃ መሳሪያወችን ከለከለ ፣ኡለሞችን ወደ ራሱ አስጠጋ።
      ሱልጣኑ የአያቶቹን ዝና በመጠቀም የአዳልን ዋና ከተማ ከደካር ወደ ሀረር አዞረ።
ሱልጣን አቡበክር ከነገራድ አቡን ጋር ግጭት ውስጥ ገባ። ሱልጠኑ የገራድን አካሄድ ፈፅሞ አልወደደም።ሱልጣኑ ገራድ አቡንን በሽፍቶች አስገደለው።የተገደለው በፈረንጆቸ አቆጣጠር በሜይ 30—1525 ( ማክሰኞ 7—ሸእባን  መግሪብ ላይ በ931) ነበር።ገራድ አቡን ይቆጣጠር የነበረውን አካባቢ ሱልጣን አቡበክር በግዛቱ ጨመረ። ሽፍቶች ዳግም ተመለሱ፣ አሰካሪ መጠጥ ተንሰራፋ፣ፍትህ ጠፋ፣ቀማኛ በዛ ሱልጣን አቡበክር ታላላቅ ሰወች የቁርአን መምህራንና ኡለሞች በተግባሩ ገሰፁት።

  ወዳጁ ገራድ አቡን የተገደሉበት አህመድ አብኑ ኢብራሂም የሱልጣን አቡበክር ጦር ከቁርአንና ሱና መውጣት አበሳጨው። ሸሪአን ባለመጠበቁ ተናደደ።ወደ ትውልድ መንደሩ ሁበት ተጓዘ። ጦር .....

     ክፍል 2  ይቀጥላል ....................

ምንጭ (የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ከ615–1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ በአህመድን ጀበል በ2003 ከታተመው መፅሀፉ የተወሰደ)


https://t.me/Alif_media_1

Alif media

30 Jan, 12:24


የ Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council በህግ ሙያ ላይ ለተሰማሩ ሙስሊም ባለሙያዎች ጥር 24 ቀን 2017 ቅዳሜ 2:30 ላይ ጦር ሀይሎች በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት እንዲገኙ ጥሪ አቀረበ።

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

30 Jan, 08:19


ትናንት አክሱም ዛሬ ኮምቦልቻ

Alif media

30 Jan, 08:15


የሒጃብ ክልከላዉ ወሎ ኮምቦልቻ ደርሷል

ኒቃብ ለብሳችሁ የምትመጡ ከሆነ   ለፈተና እናስገባችሁም መባላቸውን ሙስሊም ተማሪዎች ሰሞኑን መረጃ እየተናገሩ ነበር ።

ኮምቦልቻ የሀይስኩል ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ትናንት ከልክለዋቸዉ ወንዶቹም እነሱ ካልገቡ አንገባም በማለት የትናንቱን ፈተና ለመፈተን ችለዋል። ዛሬ ግን ካላወለቃችሁ አትገቡም ብለዉናል ዱዓ አርጊልኛ ብላኝ ነዉ ልጄ ወደ ትምህርት የሄደችዉ  ስትል አንዲት እናት ተናግራለች ።

የአክሱም ሲገርመን ወሎ ላይ ተጀምሮል

Alif media

29 Jan, 18:46


بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ


ምስጋና በሙሉ  ለአላህ ብቻ ይሁን ያ በብቸኝነት መገዛት ያለበት አምላክ፣የተውሂድን ፀጋ የሰጠኝ ለጋስ -ከዚህ የበለጠ ፀጋ የለም ና- ያ ኢስላምን ሙሉ ሃይማኖት ያደረገ ደንጋጊ ፈጣሪ፣አድስ መጤን ጥመት፣ጥመትን የእሳት መሆኑን ያረጋገጠ ንጉስ፣የእርሱ ሰላም እና ሶላት በብያችን ላይ ይሁን የታላቁ ሃውድ ባለቤት፣አዛኙ ነብይ ፣በኢስላም ላይ የጨመሩትን ያስጠነቀቁ፣የሺርክን በር በሙሉ የዘጉ፣የቢድዓን መምጫ ጥቅል በሆነ ንግግራቸው ከርችመው ይቀበሩ ለአላህ ሲሉ የሚወዱ ለእርሱ ሲሉ የሚጠሉ ነብይ፣የአላህ ኸሊል  ፣በመልካም ተከታዮቻቸው ላይም ይሁን።
ከዚህ በመቀጠል ለመስጅድ ኢማሞች፣ለዱዓቶች፣ለዐሊሞች፣በእጃችህ ላይ ማይክ ያላችሁ በሙሉ ማለት የምፈልገው ነገር።

1ኛ.መጪውን የረመዳንን ወር ተከትሎ በእርሱ ውስጥ ስለሚደረግ የጎዳና ላይ ኢፍጣር- መጤ- እንድታስጠነቅቁ።  ቢላህ

2ኛ.የረመዳን የመጨረሻዎቹን አስር ቀናት የኮሚቴ መጫወቻ ስለሆኑ፣የመስጂድ በጀት መዝጊያ በሚል ሰበብ ገንዘብ ማካበቻ እንጅ የኢባዳ ቀናቶች መሆናቸውን ስለተቀማን የት ሄደን እንስገድ፣የትኛው መስጅድ ከዚህ የጠራ ነው  የት አለ?
ለመስጅድ ቦታ መግዣ ይላሉ፣ሲገዛ ለግንባታ ይላሉ፣ሲገነባ ለመድረሳ ይላሉ፣እርሱንም ሲገነባ ለውሃ፣ለመብራት፣ለአመት ወጪ መዝጋት መቼ  ያልቃል የኮሚቴ ጣጣ
አደራ አስጠንቅቁ ለሚመለከተው አድርሱ ሁሉም ሰው ነገ አላህ ፊት ይጠየቃል በተለይ ለእዚህ ቅርብ የሆናችሁ መጠየቅ፣መልስ ምስጠት የምትችሉ በሙሉ። ልታብራሩ በአላህ ጠይቂያለሁ።

ابو أميويه محمد بن بشير

https://t.me/HanbeliyaMazhabGroup

Alif media

11 Jan, 10:50


የረመዳን አስቤዛ   በሚያስፈልገውት ጊዜ እኛ አለንሎት በፈለጉት ማህበራዊ ሚድያ ያገኙናል  098266748

☑️  ሱካር
  ☑️ቡና
☑️በርበሬ
☑️ሽሮ
☑️ዘይት በፈሳሽ ዘይት  የሚረጋው
☑️ድፍን ምስር
☑️ምስር ክክክ
☑️አተር ክክ
☑️ቴምር.
☑️ነጭ ዱቄት
☑️ኒዶ ወተት
☑️ጤፍ
☑️የሾርባ እህል በአጅል ፣በገብስ
☑️የአጥቢት እህል



ማንኛውንም የሚያስፈልገዎትን ከኛ ያገኛሉ።


ማዘዝ የፈለገ በውስጥ የሚፈልገውን ዝርዝር በማስቀመጥ ዋጋውን የምንነግረዎት ይሆናል።

ወደ ገበያው ማእከል ዋትሳአፕና ቴሌግራም ግሩፕ


https://chat.whatsapp.com/KXlgP9QgbrB5rnKQgl5w7r

https://t.me/+oHsJkCP5k7QzMzc8


ቴሌግራም በዚህ ያገኙናል @wollo_nagaa1

Alif media

22 Dec, 18:20


ስለ ሰው ጉዳዬ ብለህ ስለማትከታተል፤ ተረጋግተህ የራስህን ሕይወት ስለምትኖር ብቻ ስንት የሚበሳጭ ሰው አለ መሰለህ፡፡

መሳአል ኸይር!


https://t.me/MuhammedSeidAbx

Alif media

19 Dec, 18:55


ከመሬቱ ተንጋለለ። ብቻውን በደም ጨቅይቶ ግርግዳውን ተደገፈ። ፍርሀት ውስጡን አርበደበደው። ህመሙ እርሱነቱን አናወጠው። ዓለም እያየ እንዳላየ በዝምታው ተዋጠ።
አድጎ ሊበቀል መሳሪያውን ሲያነሳ ጠመንጃውን ሰብቆ ሲነሳ አሸባሪ ይሉታል።
አጀብ ይህቺ አለም


   Mahi Mahisho

ቴሌግራም‌‌

Translation: am-en
He fell off the ground. Alone, covered in blood, he leaned against the wall. Fear gripped him. The pain shook him. He was engulfed in silence as if the world was watching.
They call him a terrorist when he picks up his weapon to take revenge.
Accompany this world


   Mahi Mahisho

Telegram‌‌


https://t.me/Alif_media_1

Alif media

16 Dec, 15:50


ያን ሁሉ አቀበት ወጥተን፣ ውጣውረዱን ሁላ አልፈን፣ ተራራ ወንዙን ተሻግረን፣ መሰናክሉን ጥለን...እዚህ ድረስ መጥተንማ መድከም የለብንም ። እጅ መስጠት የለብንም። ዱንያን በርትተን እንጨርሳት።

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

13 Dec, 18:16


በአላህ ካዝና ውስጥ ብዙ ኸይሮች፣ ብዙ በረከቶች ፣ ብዙ ሰርፕራይዞች አሉ።
ቀጣዩ ሰርፕራይዝህ/ሽ

ዑምራ ሊሆን ይችላል፣
ኒካሕ ሊሆን ይችላል፣
እርግዝና ሊሆን ይችላል ፣
ልጅ ሊሆን ይችላል ፣
ሀብት ሊሆን ይችላል ፣
ሐጅ ሊሆን ይችላል ፣
መኪና/ ቤት ሊሆን ይችላል ፣

ማን ያውቃል ። እስቲ ተመኙ። በአላህ ላይ መልካም አስቡ። ዱዓ አድርጉ፣ ኢስቲግፋር አብዙ።
አላህ ብዙ አለው።

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

08 Dec, 16:43


ሻምም ነፃ ወጣች!

ጀግና አዛኝ ጠቢብ ተብሎ ምሳሌ ሲሰጥ ስማቸው ደጋግሞ የሚነሳላቸው ሶሪያውያን ከ61 አመታት የግፍ አገዛዝ ቡሃላ ድል አደረጉ::

የአላህ ቃል በ11 ቀናት ውስጥ በጀግኖቹ ተፈፀመ:: አላህ አይረሳም:: ምስጋና በሀያልነቱ ልክ ይገባው::

Alif media

07 Dec, 06:41


እኛስ ቁርኣን ስንቀራ ምን ይሰማናል?
~
"የነብዩ ﷺ ሶሐቦች ቁርኣንን ሲሰሙ እንዴት ነበረ?" ተብላ የተጠየቀችው አስማእ ቢንት አቡበክር መልሷ እንዲህ የሚል ነበር:–
"تدمع أعينهم وتقشعر جلودهم، كما نعتهم الله".
"አይኖቻቸው ያነባሉ። ቆዳዎቻቸው ይኮማተራሉ። ልክ አላህ እንደገለፃቸው!" 📚أخرجه البيهقي ٢/٣٦٥.
እኛስ በምንድን ነው የምናለቅሰው? ለመሆኑ ቁርኣንን ስንቀራ በዛቻው እንርዳለን? በተስፋ ቃሉ እንቋምጣለን? ታሪኩን እናጣጥማለን?

ሲጀመር ቁርኣን እንቀራለን ወይ? መልሱ "አዎ" የሆነ ሰው ምንኛ የታደለ ነው? ግን መቼ ነው የምንቀራው?
★ በየቀኑ?
★ በሳምንት ጁሙዐ?
★ በአመት ረመዳን ወር? መቼ?
አላህ ይድረስልን።

ነገ አዋጅ አለ! እንዲህ የሚል ነብያዊ አዋጅ!
(وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا)
[ الفرقان 30]

"መልክተኛውም ‘ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት’ አለ፡፡" [አልፉርቃን: 30]
ያኔ ምን ይሆን መልሳችን?

©Ibnu Munewor

Alif media

29 Nov, 18:37


አላህ ሆይ! ኢስላምን ሳንጠይቅህ እንደሰጠኸን ሁሉ፤ ጀነትን ጠይቀንህ አትከልክለን።


قيل لإعرابي : أتحسن أن تدعو ربك ؟
فقال : نعم ، قيل : فادع

فقال : اللهم إنك أعطيتنا الإسلام من غير أن نسألك، فلا تحرمنا الجنة ونحن نسألك.

Alif media

22 Nov, 18:34


የአላህ ሲትር ባይኖርልን እኮ የሚወደንና የሚያከብረን ሰው ሁሉ እንዴት ይሸሸን እንደነበር።

ጌታዬ ሆይ ሲትርህን አታንሳብን።

Alif media

21 Nov, 16:42


ሀ- ዑለማኦቹ ያደነቁት በሚያዩዋቸው መልካም ስራዎች እንጂ በጥፋቶቹ አይደለም። ነው ጥፋት ያለበት አካል መልካም ቢሰራም አይደነቅም፣ እንዲያውም ይወገዛል ነው መርሃችሁ?
ለ- እንደዚያ ከሆነ ለምንድነው ኢራንን የምታደንቁት? ኢራን በሺርክ የተወረረች፣ ዑለማኦቿ ሶሐባ የሚሳደቡ፣ ብልግና የተንሰራፋባት፣ ሱኒዮችን የምትጨፈጭፍ ሃገር ናት።
ለምንድነው ኤርዶጋንን የምታወድሱት? ኤርዶጋን ከማል አታቱርክን የሚያወድስ፣ ቀብሩ ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጥ፣ የአታቱርክ ልጆች ነን ብሎ የሚኮራ፣ የኢስላምን ህግጋት ማደስ ይገባል የሚል፣ የአንግሎ ሳክሰን ሴኩላሪዝም ነው የምንከተለው የሚል፣ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብን ደዕዋ እንደሚጠላ በግልፅ የሚናገር፣ "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚል፣ የራሱ ባለ ስልጣን በነብያችን ክብር ላይ የተሳለቀ፣ ዝሙት በመንግስት ደረጃ ተፈቅዶ ግብር የሚሰበሰብበት፣ የእርቃንኖች ሆቴል ፈቃድ ያገኘበት፣ ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ኢኽዋን ሰፈር ኤርዶጋን በተለየ ይወደሳል። ቀርዷዊ "አላህና መላእክቱ ከኤርዶጋን ጋር ናቸው" ይላል። እስኪ ከናንተ ውስጥ በሱና ዑለማእ ላይ እንደምታደርጉት ቀርዷዊንና መሰሎቹን አጥፊዎችን አወደሱ ብሎ የሚተች አለ? የለም። ለምን? አስቡት የሐሰን ነስረላህ፣ የዐብዱልመሊክ አልሑሢ፣ የቀርዷዊ፣ የዑመር ገነቴ አድናቂ በፈውዛን ላይ አፉን ሲከፍት። አስቡት እሱ ከነዚህ አፈንጋጮች እየተከላከለ እኛ ከነፈውዛን ለመከላከል ስንሸማቀቅ።

ምክንያት ሁለት፦ "ዑለማኦቹ እነዚህን ጥፋቶች እያዩ ለምን ዝም አሉ" የሚል ነው።                                                                                                                                                    100 % copy

Alif media

21 Nov, 16:41


100 % copy ((ግድ ስለሆነብኝ እንጂ አንዲንም የሙሊም መሪ ጥፋቱን ለህዝብ ያጋለጠ ሰውን ሃሳብ አላስተላልፍም ነበር)) የሪያዱ ፀያፍ ድግስ እና የቢድዐ ኃይሎች ጥምር ዘመቻ
~
ሰሞኑን በሰፊው እየተራገቡ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ ምናልባትም ቀዳሚው እጅግ ሰቅጣጭና አሳፋሪ የሆነው የሪያዱ የጭፈራ ድግስ ነው። ድግሱ ካልተሳሳትኩ በያመቱ እየተፈፀመ ያለ የሸር ድግስ ነው። ሃገሪቱ ቀድሞም ቢሆን ተጨባጭ የሆኑ ችግሮች እንዳሉባት ይታወቃል። እንደ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን ያሉ ሃገሪቱን የሚወዱም የሚያደንቁም ዑለማኦች ራሳቸው ችግሮች እንዳሉ በግልፅ ተናግረዋል። ከቅርብ ዓመታት በኋላ ደግሞ እነዚህ ክፍተቶች በአይነትም፣ በብዛትም እየጨመሩ መጥተዋል። "ሀይአቱ ተርፊህ" የተሰኘው መስሪያ ቤት ትውልድ እያወደመ፣ ሃገር እየጎተተ፣ ወዳጅ እያሳፈረ፣ ጠላት እያስቦረቀ ያለ መስሪያ ቤት ነው።

በቅድሚያ ክስተቱን በተመለከተ መጥራት ያለባቸው ነገሮች አሉ።

1- የከዕባን ምስል የሚያራክስ ክስተት ተፈፅሟል? መደምደም አይቻልም። ይሁን እንጂ ከአራት ስክሪኖች በህብር የተላለፈው የብርሃን ቅንብር በቪዲዮው መሀል ላይ ከዕባን የሚመስል ነገር ያሳያል። ከዕባ ታስቦበት ከሆነ በዲን ሸዒራ ላይ መሳለቅ ነው። በርግጥ ክስተቱ የዘንድሮ አይደለም። ባለፈው አመት በተካሄደ የቦክስ ውድድር ላይ የተፈፀመ ነው። ለምን አመት ቆይቶ የአሁን አስመስሎ ማሰራጨት እንደተፈለገ አላውቅም።
2- በከዕባ ቅርፅ በተሰራው ምስል ላይ ዘፋኝ ወጥታ ስትጨፍር ብለው ያሰራጩም አሉ። ይሄ ውሸት ነው። በ2023 አርጀንቲና ላይ የተከሰተን ክስተት ነው አቀናብረው ያመጡት።
3- የከዕባን ምስል ዙሪያውን ጣዖቶች አድርጎ የተሰራጨውስ? ይሄ የተቀናበረ ሃሰተኛ ምስል ነው። ለምን አስፈለገ? ሳያጣራ የሚያራግበውን መንጋ ለመጋለብ።
4- በሪያዱ ድግስ ላይ የዐሊይን ዙልፊቃር ሰይፍ ታጥቃ የወጣች ዘፋኝ መታየቷስ? ይህም ሃሰት ነው። አንደኛ ዘፋኟ ፍልስጤማዊት ናት። ሁለተኛ ሪያድ ሳይሆን አሜሪካ ኒዮርክ ውስጥ የተከሰተ ነው። ሶስተኛ ዙልፊቃር በሌለበት የዙልፊቃር ምስል ነው ማለትም አይቻልም።

ከዚህ ውጭ ፀያፍነቱ የማያከራክር እርቃን ቀረሽ ጭፈራ ነበር የተካሄደው። ይሄ ግልፅና ሰቅጣጭ ጥፋት ነው። ይሄ አልበቃ ብሎ:-

1ኛ፦ ምስል ማቀናበር፣ የሌላን ሃገር ክስተት አጭበርብሮ ማቅረብ ራሱን የቻለ ወንጀል ነው። ከኢስላም ለመከላከል ወይም ጥፋትን ለማውገዝ መዋሸት አያስፈልግም። ለሳዑዲ ያለህ ጥላቻ በከዕባ ዙሪያ ጣኦት እስከ መስራት ካደረሰህ ራስህ በከዕባ ላይ እየተሳለቅክ ነው። ኢስላም በግልፅ ከሃ .ዲዎች ላይ እንኳ በደል እንዳይፈፀም ይከለክላል። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ⁠مِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ }
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ። አስተካክሉ። እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።" [አልማኢዳህ፡ 8]

2ኛ፦ የተከሰተውን እርቃን ቀረሽ ምስል ማሰራጨቱም ራሱን የቻለ ጥፋት ነው። ብልግናን ለማውገዝ ብልግናውን ማሰራጨት ተቀባይነት የሌለው ምክንያት ነው።

ይህንን ጥፋት ተከትሎ እንደተለመደው በሱና ዑለማኦች እና በሰለፊያ ደዕዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ የማጠልሸት ዘመቻ ተከፍቷል። በሳዑዲ ሙንከራት በተከሰተ ቁጥር ሁሌ ጥፍራቸውን ስለው፣ ጥርሳቸውን አግጥጠው በሱና ዑለማኦች ላይ የሚዘምቱ አሉ። እነማን ናቸው? ሺርክን 0ቂዳው ያደረገው አሕባሽ፣ የዲሞክራሲን የኩ. ፍር ስርአት ቅዱስ የኢስላም አካል ያደረገው ኢኽዋን፣ እጁ በሙስሊሞች ደም፣ ልቡ በሶሐቦችና ጥላቻና በሺርኪያት የጨቀየው ሺ0 እና አድናቂዎቻቸው፣ በሱና ዑለማኦች ቂም ያረገዙ ኸዋ -ሪጆች ናቸው። ሌላው በቀደዱለት የሚፈስ የነፈሰው ሁሉ የሚወዘውዘው መንጋ ነው። እንዲህ አይነቱን ክፍል ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ "ሰፊው ህዝብ ማለት አንዳንዴ ሰፊሁ ህዝብ ማለት ነው" ይላሉ። በፎቶሾፕ እያቀናበሩ የሚያቀርቡለትን ሳይቀር ሳያላምጥ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በዑለማእ ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ይሆናል።

አሁን የሱና ዑለማኦችን ለማብጠልጠል ሰበብ ከሆናቸው የከፋ፣ የባሰ እና የበዛ ጥፋት ሺ0 ላይ፣ ሱፊያ ላይ፣ ኢኽዋን ላይ አለ። እንደ ሃገርም እነዚህ ዘማቾች የሚያወድሷቸው ኢራን እና ቱርክ ውስጥ ከዚህ የከፋ ብዙ ጥፋት አለ። እንደ ታዋቂ ሰዎች እነ ቀርዷዊ፣ ሰይድ ቁጥብ፣ በሃገር ውስጥም እነ "ሙፍቲ" ዑመር ላይ አለ። ከመሆኑም ጋር እንዲህ አይነት የተቀናጀ ዘመቻ አድርገውባቸው አያውቁም። የኢኽዋን ቡድን እንዲያውም ከሺ0 ጋር ያለው ልዩነት እንደ አራቱ መዝሀቦች የፊቅህ ልዩነት ነው የሚልበት አለው። ከኢስላም የሚያስወጡ ግን ደግሞ በኢስላም ስም የሚፈፀሙ ጥፋቶች ላይ አይናቸውን ጨፍነው እያለፉ የሱና ዑለማኦችን ፈፅሞ በማይደግፉትና እጃቸው በሌለበት ነገር ተጠያቂ ያደርጓቸዋል። ለምን? የመንሀጅ ልዩነት ስላለ ለማጠልሸት እስከ ጠቀመ ድረስ በሌሉበትም ከመክሰስ አይመለሱም። የተከሰተ ብቻ ሳይሆን የሌለውን አቀናብሮ ከማቅረብም አይታጠፉም፡፡

ዑለማኦቹ ላይ ለሚያነሱት ክስ ሁለት ማመሀኛዎችን ሲያነሱ ማየት የተለመደ ነው። አንዱ ዑለማኦቹ የሳዑዲን መንግስት ያደንቃሉ የሚል ሲሆን ሌላኛው እነዚህን ጥፋቶች ለምን አልተቹም የሚል ነው። ሁለቱም ምክንያቶች የቀደመ ጥላቻን ለማራገፍ የሚነሱ ሰበቦች እንጂ ዑለማኦቹ ላይ ለመዝመት የሚያበቁ አይደሉም። በየተራ እንመልከት፦

ምክንያት አንድ፦ "ዑለማኦቹ የሳዑዲን መንግስት ያደንቃሉ"

Alif media

29 Oct, 20:09


«በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።

ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው።
ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ ለአስፈላጊ ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት  እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።

በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣  አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች።
«ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ራሱ የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።»

#ሒጃብ #ኒቃብ #ትምህርት
#ሀገራዊ_ምክክር

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

Alif media

29 Oct, 20:02


የ ስልክ መሰረቅ ን ስሜት የሚረዳው የተሰረቀበት ብቻ ነው !!!

Alif media

29 Oct, 19:57


እብሪትና እልህ አይወጥራችሁ። ካፈርኩ አይመልሰኝ አትበሉ። "ልክ ነህ ግፋበት" ብሎ የሚደልላችሁንና የውሸት ጉልበት የሚሠጣችሁን ስሜት ወዲያ ግፉ።

  አንዳንድ ጊዜ መለስ በሉና ምን ያህል ትልቅ ሰው እንዳጣችሁ እመኑ። በገዛ እጄ ለዱንያ አኺራዬ የሚጠቅመኝን ማጣት ያልነበረብኝን ሰው እኮ ነው ያጣሁት በሉ።

ለናንተው ለእልኸኞች

Alif media

21 Oct, 17:27


የክህደት ዓይነቱ ብዙ ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ እሱን መቅረጽ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ ድምፁን ላውድ ላይ በማድረግ ሌላውን ማስደመጥ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ የሱን ፎቶ አንስቶ መፖሰትም ክህደት ነው።

* እያዳመጡ ባለመምሰል የሰውን ሚስጢር ማዳመጥ ክህደት ነው።

* ምንም የማያውቁ ልጆችን ስለቤተሰባቸው ሁኔታ በማውራት ለማውጣጣት መጣርም ክህደት ነው።

*በሠራተኞች አማካይነት ጎረቤትን መሰለልም ክህደት ነው።

* የሰውን ነውር መከታተልም ክህደት ነው ።

* የሰው ሚስጢር መበተንም ክህደት ነው።

* የሠሩትን ለማጋለጥ በመዛት ሙስሊምን ማጨናነቅም ክህደት ነው።

* መርዳት በሚገባ ቦታ ላይ ሙስሊም ወንድም/እህትን አሳልፎ መስጠት ክህደት ነው።

ሙስሊም በሙስለም ወንድሙ ይተማመናል።
ይጠብቀኛል ብሎ ወንድሙ ላይ ራሱን ይጥላል ።

አንድ ሙስሊም ሚስጢር ሲያወራህ ይነግርብኝ ይሆን ብሎ ከተጠራጠረ ይከዳኛል ብሎ እየፈራ ነው ማለት ነው።

ወንድም እህቶቻችሁ አምነው የሚደገፉባችሁ አስተማማኝ ግድግዳ ሁኑ።

መሳአል ኸይር

Alif media

09 Oct, 08:05


ይህ ውብ መስጂድ የት ይገኛል ?

@alif_media_1

Alif media

09 Oct, 06:24


«"ሄሎ ያ ሸይኽ! አሰላሙ አሌይኩም!"

"ወአለይኩሙ ሰላም ወሯህመቱላህ ቀጥዪ ቀጥዪ!"

«"ያ ሸኽ! ኢትዮጵያ እያለሁ ባል አገባሁ፣ አልተስማማኝ ተፋታሁ። ጅቡቲ ስሔድ ባል አገባሁ ከእሱ ጋር ተፋታሁ … ሳዑዲ መጥቼ አገባሁና ፈታሁ … አሁን አራተኛ ላገባ ነው… "

ሸይኽ፦  "በቃሽ በቃሽ! አንቺ ዝም ከተባልሽ እኛን ሁላ ማዳረስሽ አይቀርም …"»

ከፌስቡክ መንደር

@alif_media_1

Alif media

09 Oct, 06:18


የ ባሏን ሀቅከማጠብቅ ሴት አላህ ይጠብቀን!!

የ ሚስቱን ሀቅ ከ ማይጠብቅ ወንድ አላህ ይጠብቃችሁ!!


@alif_media_1

Alif media

09 Oct, 05:27


" ጦለሀ ጃፈር ፣ አፄ ሚኒሊክ ና ጣልያን "


https://t.me/Alif_media_1

Alif media

09 Oct, 04:45


ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ! የእነ ጀሚላ ትውልድ!

መጋቢት 16/2001 ዓ.ል የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ባልታወቀ ምክንያት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ጋቢ፣ ነጠላና ጅልባብ ለብሶ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ገለፀ:: ይህንንም ተከትሎ ጅልባብ ትለብስ የነበረችው የአፕላይድ ኬሚስትሪ ተማሪዋ ጀሚላ ሙስጠፋ፤  የአፕላይድ ሒሳብ ተማሪዋ ሹክሪያ አወል፤ የሒሳብ ት/ት ክፍል ተማሪዋ ሰሚራ ደምስ እንዲሁም የአፕላይድ ባዮሎጂ ተማሪዋ ገነት ሆሻ የዚህ ኢ-ፍትሐዊ የሆነ መመሪያ ሰለባ ሆኑ። እነሱም ጅልባብ ከጋቢና ነጠላ እንደሚለይ ብሎም ሃይማኖታቸው እንዲለብሱ ግዳጅ ያደረገባቸው ልብስ ስለሆነ ነፃነታቸው ተከብሮ ይማሩ ዘንድ ጠየቁ። ሆኖም በማግስቱ መጋቢት 17 ካፌ ውስጥ ጅልባብ ለብሰው መግባትና መመገብ እንደማይችሉ ተገለፀላቸው::

እነርሱም ምግብ ውጪ ገዝተው እየተመገቡ ጥያቄያቸውን ከበላይ ላሉት የተማሪዎች ዲንና የፋካሊቲ ዲን ያቀርቡ ጀመር:: እነርሱም ጥያቄያቸውን በቀናነት ከመቀበልና ከመወያየት ይልቅ የሚባሉትን ሳይቀበሉ ተማሪዎችን "ይህ የአክራሪነት መገለጫ ነው። ሕገ- ወጥ ናችሁ።" በማለት ይዝቱባቸውና ያስፈራሯቸው ጀመሩ::

ይህ ሲሆን ተማሪዎች ለማጠቃለያ ፈተና 3 ቀናት ብቻ የቀራቸው ቢሆንም የሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ከተማሪዎች ፊርማ በማሰባሰብ ከተማሪዎች መማክርት ጀምሮ አቤቱታቸውን ያቀርቡ ጀመር:: ሆኖም ግን የዩኒቨርሲቲው አመራር እነዚህን ተማሪዎች ለማወያየት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ገለፀ:: ተማሪዎችም አንድ ደረጃ ከፍ በማለት ድምፃቸው ይሰማ ዘንድ ለ3 ተከታታይ ቀናት ካፌ ላይ ምግብ ያለመመገብ አድማ መቱ:: ሆኖም ይህንን አይቶ ቀና ውይይት ሊያካሂድ የፈለገ አንድም የዩኒቨርሲቲው አመራር አልነበረም::

ይህ ሲሆን ጊዜ ሙስሊም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው በመውጣት ማረፊያቸውን መስጅድ አደረጉ። ለ15 ቀናትም የአካባቢው ማህበረሰብ አባት እናት ሆኖ እየተንከባከበ፤ እያፅናና አስቀመጣቸው። ሆኖም ግቢ ውስጥ የነበሩ አመራሮች ከመንግስት ደህንነቶች እና አመራሮች ጋር በመሆን መስጂድ ድረስ በመምጣት ያስቸግሩ ጀመር። በሰዓቱ የነበረው መጅሊስም ከመንግስት ጋር ተዳብሎ "ወደ ግቢ ተመለሱና ችግሩ ይቀረፋል!" በሚል ማሳበቢያ በተማሪዎች ላይ ጫና በማድረግ ወደግቢ እንዲገቡ አደረገ።

ሆኖም ወደግቢ እንደገቡ በእነዚህ አራት ተማሪዎች ላይ ከዶርም እና ካፌ ጀምሮ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው ጀመር:: ይህንን አይችሉ ሲሉም ከግቢ ውጭ ተከራይተው መማር በጀመሩ 7 ቀናት ውስጥ ከተከራዩበት ቤት ፖሊስ እንዲባረሩ ካደረገ ቡሃላ ወደ ግቢ ተመለሱ:: ግቢ ደርሰው ምሽት ላይ ከዶርም እንደገቡ የዶርም አገልግሎት ፕሮክተሯ መታወቂያቸውን ቀምታ ማደር ስለማይችሉ በቶሎ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ እንደመጣ አስተላለፈች። ብትለመን ብትለመን አልሰማችም። ተማሪዎችም ውጭ ከወጡ ጧት ገብተው እቃቸውን ማውጣት ስለማይችሉና ከዶርምም ማደር ስለማይችሉ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚገኘው የኬሚስትሪ ላቦራቶሪ ፊትለፊት በረንዳ ላይ አደሩ። ሲነጋም ማንነታችሁን ጠብቄ ለመማር ፈቃደኛ አይደለሁም ያለችውን ግቢ ጀርባ ሰጥተው ከሐዘን ጋር ተለያዩ::

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

09 Oct, 04:33


ሲራ_ክፍል_5_በኡስታዝ_በድሩ_ሑሴን_የነብዩ_ሙሐመድ_ሰ_ዐ_ወ_የህይወት_ታሪክ_

#ሲራ_#አፍሪካ_ቲቪ

Alif media

08 Oct, 19:21


"ሙስሊሞች አጥንት ሲግጡ ተፈናጥሮ የክርስቲያኑን ስጋ ያረክሰዋል!"-  አቶ ገብረክርስቶስ

የደርግ መንግስት ሊወድቅ ጫፍ በደረሰበት 1983 ዓ.ል ነበር:: ከዚያ በፊት ግቢ ካፌ ላይ ይቀርብላቸው የነበረው ስጋ ለክርስቲያኖች ከታረደው እንደሆነ ያስተዋሉ ሙስሊም ተማሪዎች "ለምን ሙስሊም የሙስሊምን አያርድም?" የሚል ጥያቄ አንስተው በተወካዮቻቸው በኩል ወደዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ላኩ:: ተማሪዎችም መጀመሪያ ላይ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ "እኛ ለሙስሊም ለክርስቲያን ብለን አናርድም:: ቢስሚላህም ሆነ በስመአብ ሳይባል በማሽን ነው የሚታረደው" የሚል ጭፍን ምላሽ ሰጡ:: ይህ ደግሞ በክት ነው የምንበላው ማለት ነው የሚል አዲስ ትኩሳትን ፈጠረ::

ሆኖም ተማሪዎቹ እዚያው ከሚሰሩ ሰዎች ሲያጣሩ "ቄራ የሚታረደው ለሙስሊም እና ለክርስቲያን ተለይያቶ ነው:: ሆኖም የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች የሚያዙን ለሁለቱም ከክርስቲያኖች እንድናቀርብ ነው።" የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። ይህንን የሰሙት የሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው እሳት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ዘንድ ሄዱ።

በውይይቱም የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳነት ዶክተር መኮነን ዲልጌሳ፣ የተማሪዎች ዲን አቶ ገብረክርስቶስ እና ሌሎች አመራሮች ነበሩ። ተማሪዎቹ በቁርጠኝነት ጥያቄዎቻቸውን ከሙሉ ምክንያት ጋር ሲያቀርቡ ቁርጠኝነታቸውን የተረዱት አመራሮች "ሐገሪቱ ጦርነት ላይ ነች። እናንተም ዘመቻ ልትሄዱ ነው:: ተረጋጉ።" የሚል መልዕክት አስተላለፉ:: ተማሪዎችም "እንዘምታለን። ግን ዘመቻውና የመብታችን ጉዳይ አይገናኙም። እስክንዘምት መብታችን ይከበር።" አሉ::

በመጨረሻም የጥያቄውን አግባብነት የተረዳው ም/ፕሬዚዳንቱ "ጥሩ! የጠየቃችሁት ነገር ትክክል ነው:: ተመቻችቶ መብታችሁ ይከበራል።" ሲል ያልተዋጠለት የተማሪዎች ዲን "ክቡር ፕሬዚዳነት! ይህማ እንዴት ይሆናል? ሙስሊምና ክርስቲያን ተማሪዎች ተቀላቅለው በሚመገቡበት ሰዓት፤ ሙስሊሞች አጥንት ሲግጡ ተፈናጥሮ የክርስቲያኑን ስጋ ያረክሰዋል።" በማለት ጥላቻውን ዘረገፈ:: በዚህን ጊዜ ሁሉም ደንግጠው አቀረቀሩ:: ከተማሪዎቹም በመበሳጨት "ይህንን ወራዳ ጨምላቃ ሽማግሌ ትመለከቱታላችሁ?" የሚል የቁጣ ድምፅ ተስተጋባ:: ዶ/ር መኮንንም በአቶ ገ/ክርስቶስ ንግግር እያፈሩ "ግዴለም! ሁሉንም አሟልተን እናስተናግዳችሗለን!" ሲሉ መለሱ:

Alif media

08 Oct, 17:23


እነርሱም 365 ቀናት ነበሩ። እነርሱም የአላህ ሲትር፣ ዓፊያና ሪዝቅ የተሞላባቸው ቀናት ነበሩ ። ጌታዬ ሆይ በያመቱ ምስጋና ላንተ ይሁን። ምንም ብታደርግ የምትመሰገን አንተ ብቻ ነህ።

Alif media

08 Oct, 16:58


ሲራ_ክፍል_4_በኡስታዝ_በድሩ_ሑሴን_የነብዩ_ሙሐመድ_ሰ_ዐ_ወ_የህይወት_ታሪክ_

#ሲራ_#አፍሪካ_ቲቪ

Alif media

08 Oct, 08:13


እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ!
~
እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው። ለማን ነው ይህን ያደረግሽው? አላህ ምን ይለኛል ብለሽስ አስበሻል? ተይው አላህ ዘንድ ሰው ዘንድ ራሱ ያስንቅሻል። ከጌታሽ ተጣልተሽ፣ ሰዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ወድቀሽ ምን ትርፍ ታገኛለሽ?

ለማንኛውም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا ؛ قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُءُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا "
"ሁለት አይነት ሰዎች ከእሳት ጓዶች ውስጥ ናቸው። እኔ አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ።)
* እንደ ከብት ጅራት ያለ መግረፊያ ይዘው ሰዎችን በነሱ የሚደብድቡ ሰዎች እና
* ለብሰው የተራቆቱ፣ ለሌሎች ጥፋታቸውን የሚያስተምሩ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ፣ ፀጉሮቻቸው እንዳዘነበሉ የተከመሩ የግመል ሻኛዎች የሆኑ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነትን አይገቡም። ሽታዋንም አያገኙም። ሽታዋ ከብዙ ርቀት የሚገኝ ነው።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦

https://t.me/Alif_media_1

Copy -  IbnuMunewor

Alif media

08 Oct, 04:05


Sira be ustaz bedru Hussen kifl_3
አፍሪካ_ቲቪ1

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

07 Oct, 17:36


ሲራ_ክፍል_1_በኡስታዝ_በድሩ_ሑሴን_የነብዩ_ሙሐመድ_ሰ_ዐ_ወ_የህይወት_ታሪክ_

#ሲራ_#አፍሪካ_ቲቪ

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

06 Oct, 19:36


ልክ በዛሬዋ ለሊት የቀሳም ሙጃሂዶች ለኦክቶበር 7 ጥቃት እየተዘጋጁ ነበር። ድልን ወይም ሸሂድነትን አላህ እንዲወፍቃቸው አልቅሰው እየለመኑ ለሊቱን በዱዐና አነጉ።

Mahi mahisho

Alif media

06 Oct, 17:52


ወደ ስልጠናው መግቢያ ሊንክ


👇👇👇👇👇👇

https://t.me/AfricaAcad?livestream

Alif media

06 Oct, 17:34


ስልጠናው ሊጀምር 2 ሰአታት ብቻ ይቀሩታል

🎙አቅራቢ= ኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ

ሰአት = 3:00 በኢትዮ አቆጣጠር

ስልጠናው በቴሌግራም ቻናል ቀጥታ


#አፍሪካ _አካዳሚ

Alif media

05 Oct, 17:54


ሙጃሂድ ዑመር አል-ሙኽታር በተፋፋመው ውጊያ መሐል ጦራቸውን ሰብቀው ወደ ፊት ይገሰግሱ ይዘዋል። ከግንባራቸው ላቦተ ይንጠባጠባል። በድንገት ፈረሳቸው ወለም ብሎት ወደ መሬት አንከባሎ ጣላቸው። ከፊት ለፊታቸው መውደቃቸውን ያየ የጠላት ጦር በሕይወት ሊማርካቸው እየተንደረደረ ወደሳቸው ገሰገሰ።

በምስሉ ላይ የሚታየው ሙጃሂድ ኢስማኢል ሲዋጋበት ከነበረው ፈረስ ላይ ወርዶ ለዑመር ሙኽታር ሰጥቶ እርሱ ተማረከ። በዚህ ጀግንነቱ የተገረመው የጣሊያን ጦር መሪ ግራዚያን ለወታደሮቹ እንዲህ በማለት አዘዘ፡-
"የፈለገውን ያህል ማር እስኪጠግብ ይብላ ከወተትም አቅርባችሁ ያሻውን ይጠጣ እንደነጋ በጠዋት ስቀሉት" አለ።

  አላህ ይቀበለው ከሸሂዶችም ጋር ይቀስቅሰው ሙጃሂድ ኢስማኢል አል አርጃህ

ምንጭ
مجاهدون في الصحراء

mahi mahisho

https://t.me/Alif_media_1

Alif media

05 Oct, 13:16


ኤምሬትስ ከዱባይ እሰከ ሻርጃይ አቡደቢ እና ረእስ አልኸይማ ያላችሁ እነኚህንና ሌሎችንም በርካታ ኢስላማዊ መፃሕፍት መግዛት የምትፈልጉ @wollo_nagaa ዘንድ ታገኛላችሁ።

አትጨነቁ ፣
ከአላህ ጋር፣
ፍቅርና ደስታ ፣
ቢስሚከ ነሕያ፣
የፍቅር በረከት፣
ህልም አለኝ፣
ልብ ላላሉ ልቦች፣
ደስ የሚል ጉዞ

1,212

subscribers

69

photos

12

videos