አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) @hakika1 Channel on Telegram

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

@hakika1


የሰው ልጅ ልብ ነው የገጣሚ ሀገር...!
@Run_Viva_Run

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (Amharic)

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) በገጣሚ ሀገር ማወቅ የሚችል አካባቢ ነው። የሰው ልጅ ልብ ለሁሉም በተያያዝ ለአምራች በተገኘ እንቅስቃሴዎችን መከተል ይችላሉ። ስለዚህ የገና እና የሚከማቸው ጥያቄዎችን በመከታተል ይቅርብናል። በተጨማሪም እናሸንፋ ጥሩ ሌላ ሀገር ነው የመቀነሱ እና የትንቢት ድርጊቶች ማግኘት። ይህን እና ሌሎች ተወዳጅ ጥሩ ሀገር ለመግከም እና ማድረስ የእውነት መረጃዎችን ይመልስ ይሆናል። እስቲ ከእርሱ ፣ @Run_Viva_Run የተገለጸ የትንቢት ድርጊት የሚሆነውን ይከሰት።

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

10 Jan, 16:49


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

09 Jan, 18:12


የውበት ምሳሌ

ከዋክብት ቀኑባትና፥ እሷ ላይ ሴራ ቀመሩ፤
ከነሱ እጅጉን በልጠው፥ ዓይኖቿ ስለሚያበሩ...
ትክ ብላ ከላይ አይታት፥ ንድድ'ድ አላት ጨረቃ፤
ጎዶሎ ሆኖባት ሳያውቅ፥ ማማሯ ስለተብቃቃ...
ፀሀይም ተከፍታ ዋለች፥ ፈዞባት ዋለ ውበቷ፤
አያል ነው ልጅት ድምቀቷ...
ውሀዎች ፏፏቴ ፈጥረው፥ ከሀገር እሩቅ ቢጓዙ፤
ይረዝማል ፀጉሯ ከወንዙ...

ታሳሳለች እንደ ህፃን
ለምዶበታል እጇ ማዳን
ከፍልቅልቅ ሳቋ ዳር ዳር
ብዙ ተስፋ ይወለዳል

ገፅታ ነች ገፀ ብዙ
ይማርካል መልኳ ወዙ
ካሳቀቀን ግፍ ጭቆና
አንድ ሰላም የእግዜር መና
ተስሎልን ከፊቷ ላይ
ግማሽ ምድር ግማሽ ሰማይ
ከህይወት ጋ አወዳጀን
ቁንጅናዋ...
ነፃነትን አቀናጀን።

እንቡር አልን ሄደን ሜዳ
ከጥርሳችን ሳቅ ተቀዳ
ጫፍ ቁጭ አልን ከተራራ
ተደመምን በእግዜር ስራ
አየን ለየን ድንቅ ውበትን
"ይሄ ነው አልን" መቆንጀትን

"መቆንጀት እንዲ ነው እንዴ?
ውበትስ ይሄ ነው እንዴ?"

ብለው ሲሉን ሰዎች ሁሌ፤
አንቺ ብቻ ተፈጥረሻል ለምሳሌ...

(አንቺ...አንቺ ብቻ)

Abrham F. Yekedas

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

28 Nov, 05:04


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

26 Nov, 17:50


ለሊት 7፡00 ግቢያችን ሌባ ገባ። ሌባው ከሄደ በኃላ የቤቴ አከራይ ጋሽ በላቸው ባደረጉት የቴክኒክና የታክቲክ ጥናት መሰረት መጀመሪያ ሌባው የግቢውን በር ለመውጫ እንዲያመቸው አድርጎ አዘጋጀ።...በመቀጠል የእያንዳንዱን የግቢ ተከራይ የቤት በር ከውጪ ቀረቀረ(ለምን? ቢጮህበት እንኳን ሰው ወዲያው ከቤቱ ወጥቶ እንዳይዘው በሚል)።...በመጨረሻ የእኔን የደሀውን በር ሰርስሮ ከፍቶ ገባ። ሰርስሮ ማለቴ እንኳን ለደንቡ ነው፤ የኔ በር ባይሰረስሩትም ከ 45ኪሎ በላይ የሆነ አንድ ሰው በአመልካች ጣቱ ገፋ ቢያደርገው እራሱ ብርግድ የሚል በር ነው። ብቻ ሌባው ቤቴ ገባ....

ኮሽታ ሰምቼ ብንን ስል ቤቴ በመጣበቡና የሚያነሳው ነገር በማጣቱ ምክንያት ሌባው እንደ ምድር በራሱ ዛቢያ ይሽከረከራል። ሳስበው ከቤቴ ምንም የሚዘርፈው ነገር እንደሌለኝ ገባኝ። በቃ ሲወጣ እጮሀለው ብዬ አይኔን ገርበብ አድርጌ አየው ጀመር። ጥቂት አማተረ አማተረ ፈታተሸና ጭንቅላቱን እየወዘወዘ "አይ ድህነት..." ብሎ ጠዋት ጠዋት ለቁርስ በዳቦ የምቀባትን የለውዝ ቅቤ ብልቃጥ ብድግ አድርጓት እግሩ ወጣ እንዳለ "ኡኡኡኡ...."ብዬ ያለ አንዳች ወንዳወንዳዊ እፍረት ጩኸቴን አቀለጥኩት።

ሌባው መለስ ብሎ "ኧረ ሳይኖርህ አታንባርቅ ..." ብሎ ተፈተለከ።

ከቆይታ በኃላ ከውጭ የቀረቀረባቸውን የጎረቤቶቼን በር እየከፈትኩ ሁሉም ዱላና ፍልጡን ይዞ ተሰበሰበልኝ። ጎረቤቶቼ "ወይ አብርሃም ም'ፅፅ! ዋናው ብቻ ነፍስህ መትረፉ ...ገለው እኮ ይሄዳሉ...ባለፈው እዚህ እታች መንደር አይደል እንዴ..." እያሉ ትንሽ የሌባ ታሪክ ዘገባዎችን እየመዘዙ ካወሩ በኃላ አከራዬ አቶ በላቸው አንሶላቸውን እንደተከናነቡ በሀል ላይ ቆመው "ግን ምን ወሰደብህ...?" ብለው ጠየቁኝ። ያኔ ነው ጥሩ ሰይጣናዊ ሀሳብ ብልጭ ያለልኝ

ዓይኔን እንባ እንዲጎበኘው ጭምቅ እያደረኩት..."ጠዋት እሰጦታለሁ ብዬ ያስቀመጥኩትን የቤት ኪራይ 5000 ብር ነው ይዞት የሄደው ጋሼ...ኧረ በያዘው ጩቤ ሊወጋኝ ሲል ሽል ባላልኩት... ኧረ ገሎኝ በሄደ ምነው....ምነው በያዘው ቆንጨራ በከተከተኝ ...ኧረ አሁንስ እኔ ይሄ አመት አልሆነልኝም። ብሄድ ይሻላል....ኧረ ዕድሌ...." እያልኩ ብክንክን አልኩ።

የአከራዬ ሚስት እማማ ዝናሽ "ተው እንደሱ አይደለም የኔ ልጅ ብር እኮ ይተካል...ዋናው ነፍስህ መትረፉ " ብለው ከተቀመጡበት ተነስተው ፀጉሬን እያሻሹ ባልተቤታቸው አቶ በላቸውን መመልከት ጀመሩ። ተከራዩ በሙሉ እሳቸው ላይ አፈጠጠ።

አከራዬ ጥቂት ዝም ካሉ በኃላ "ምን እንደው!....በቃ የዚህን ወር የቤት ኪራይ ምሬሀለው....ኪራይህን ማታ መስጠት ስትችል ልጅ አብርሃም አየኸው የተፈጠረውን? ...ሁሌ ሳምንታትን ካላዘገየህ መች ሰጥተኸኝ ታውቃለህ?....ከቀጣይ ወር ጀምሮ ይሄን ነገር አስተካክል..." ብለው ገሰፁ።

"እሺ ጋሼ ባይሞላልኝ ነው አስተካክላለሁ..." ብዬ የሌለኝን እንባ ጠረግኩ። ሁሉም "በል በርህን አጥብቅና ዝጋ" እያለ ቀስበቀስ ከቤቴ ተበትኖ እቤቱ ገባ።

በሬን ዘጋሁና 'አልያሼ ሹንቡራ' እያልኩ ድንስ 🕺...ከዛ ለጥጥጥጥ.....

"አሃሃ....ሌቦ ነይ" 😊🕺

Abrham F. Yekedas

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

22 Nov, 07:15


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

01 Nov, 13:42


ምን ያንሰኛል ግጥሞቼን ብለቅበትስ ብዬ Tiktok account ከፍቻለሁ።

እስካሁን ባለው 30 ተከታዮች አሉኝ😜። "ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ተቋማት ኽፓሏግርብድክክ..." ብዬ ልሰክስ አልፈልግም😊....ብቻ በቀና መንፈስ follow አድርጉኝማ።

https://vm.tiktok.com/ZMhQUwAfb/

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

29 Oct, 19:39


እየገዛችሁ...

ክንፋም ከዋክብት የግጥም መፅሀፍ የህትመት ሂደቷን እንደ ምጥ ቀን ቆጥራ ከተገላገለች እነሆ ሳምንትን አሳልፋለች.... ጥቅምት 16 2017 ዓ.ም በዋልያ መፅሀፍ መደብር አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቃለች።

ያሉ ቀሪ መፅሀፎችን እጃችሁ ማስገባት የምትፈልጉ @Run_Viva_Run ላይ አውሩኝ። እንቀባበላለን።

@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

27 Oct, 05:47


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

21 Oct, 17:14


ከ 50 ገጣሚያን ጋ የተሳተፍኩበት የግጥም መፅሀፍ ለገበያ በቅቷል... ምርቃቱ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ነው...እንዳትቀሩ😊

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

21 Oct, 13:55


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

29 Sep, 05:48


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

08 Sep, 18:29


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

04 Sep, 18:21


እዚህ መፅሀፍ ላይ ከሶስት የማይበልጡ ግጥሞቼ ከሌሎች ጎበዝ ገጣሚያን ስራዎች ጋር ለህትመት እንደሚበቁ ተነግሮኛል። ሙሉ በሙሉ ባላውቅም አብረውኝ ከሚሳተፉት 50 ገጣሚያን ውስጥ የአንዳንዱን ስም ስሰማ ደሞ የእዚህ መፅሀፍ ተሳታፊ መሆኔ ትልቅ ደስታን ፈጥሮልኛል። መጨረሻውን ደሞ ያሳምረው።

የዚህ ቻናል ቤተሰቦች... ለስራዎቼ ትልቅ ብርታት ናችሁና ምስጋናዬ የበዛ ነው።🙏

@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

04 Sep, 18:07


ክንፋም ከዋክበት
እነሆ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቀቀ።

አዲሱ ትውልድ እና የግጥም ጣዕም የገባቸው፤ 100 የሚሆኑ ወጣቶች ሥራዎቻቸውን በጋራ ለማሳተም ቅድመ ምልከታ ስናደርግ ቆይተናል።ለአዲሱ ዓመት መቀበያ ፤ የ50 ገጣሚያን ሥራዎችን መርጠናል።
  በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች ተሰጥኦ፣ ንባብ እና ምናብ ያላቸው  ያልታዩ ወጣቶች ገና ብዙ አሉ።በዚህም መሠረት ጥዑም፣  ለዛ ያላቸው  እና ሸጋ ግጥሞች በቅጽ ሁለት ለንባብ ይበቃሉ።
የመጀመሪያው ምዕራፍ ገጣሚያን እንኳን ደስ አላችሁ።  መጽሐፋን የመመረቅ፣ አንጋፋዎቹን ለበዓል የመጠየቅ መሰናዶ ከፊት ይጠብቀናል።
እርስዎ ደግሞ የዚህ ደስታ እና ባለ ታሪክ እንዲሆኑ በክብር ጋብዘናል።

እነሆ ቅድመ ሽያጭ ጀምረናል።
የመጽሐፉ ዋጋ 300:ብር ሲሆን
እነዚህን ከዋክብትን እና መጪዎቹን ለማበርታት አብረውን ይጓዙ። እናመሰግናለን።

1000420583528 ሰይፉ ወርቁ
1000143312244 ጌታቸው ዓለሙ  ደረሰኙን ይላኩልን። መጽሐፋን ባሉበት እንልካለን።

+251 924 913036
+251 911 125788

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

27 Aug, 11:06


"ሲኦል በር ላይ ቀዝቃዛ ውሀ መሸጥ እፈልጋለሁ?"

"ምነው አልክ?" ድምፁ በእርጋታ የተሞላ ነው

"ታውቃለህ እኔ በምድር ላይ የተሳካልኝ የቢዝነስ ሰው ነኝ...ግን ሳስበው ያ ብቻ በቂ አልመሰለኝም ....ሌሎች ብዙ የቢዝነስ እቅዶችን እያሰብኩ አወጣሁ አወረድኩ...ግን የሲኦል በር ጋ ቀዝቀዝ ያለ ውሀ እንደመሸጥ አዋጭ ነገር ያለ አይመስለኝም"

"እምምም....የሆነስ ሆነና እንዴት ልትመጣ አሰብክ?"

"የት?"

"ሲኦል....ያልከውንስ ቀዝቃዛ ውሀ ከምድር ነው የምታመላልሰው?"

"እእእ....እሱን ሞትን አናግርልኝ ጌታ ሆይ .....ውሀውን ከምድር እንኳን ማመላለስ አይሆንም ......ጌታ ሆይ ፈቃድህ ቢሆን ከገነት አንድ ምንጭ ብትሰጠኝ?"

"ይሁን..." በሀሳቤ ይደሰት አይደሰት ለማወቅ አልቻልኩም....የፈጣሪ ፊት ዝም ያለ ነበር።....ይህን ሁሉ ዓመት በንግድ ስሰራ አንዱ የስኬቴ ምንጭ ደንበኞቼ በምሰጣቸው ነገር ተደስተዋል ወይ ብዬ የፊታቸውን ገፅታ አይቶ መረዳት ነበር። የፈጣሪ ይሁንታ ግን ግራ አጋባኝ፤ ግን ይሁን ብሏል።

########

ጠዋት በሬን ስከፍት አንዳች ነገር  በሬጋ ቆሟል "ማነህ አንተ?" አልኩት

"ሞት.."

"እንዴ...አንተ እንዴት ነህ ባክህ....?"

"ይመስገን ..ከፈጣሪ ጋ አውርተን ነበር...ጊዜ ሳናጠፋ ብንሄድ ይሻላል"

"ልብስ ልያ'ዛ ቆይ...."

"አንድ ካኔተራ ይበቃሀል"

"ለምን?"

"ሲኦል በርጋ አይደል የምትቆመው...ሙቀቱን አትችለውም" ኮስተር አለ ፊቱ .....አታከትኩት መሰለኝ

"እሺ እንሂድ..." እንዳልኩት ፊቴን አንዳች ሀይል መትቶኝ ሞት እፍስፍስ ሲያደርገኝ ይታወቀኛል....ከዛ ግን እራሴን አላውቅም ነበር።

####

ከውስጥ ሰፊውን  በር አልፎ የሚሰማው ጩኸት ከባድ ነው። ያስፈራል!!! የበሩ ጠባቂዎች ፊት ላይ የሚታየው ቁጣ ብቻ ነው። ከበራፉ ጠጋ ብሎ ከገነት የተዘረጋች አንድ ቧንቧ እና በሀይላንድ መሳይ  ቅርፅ የተሰሩ ብዙ የብረት መጠጫዎችን አየሁ።መጠጫው በፕላስቲክ ቢሆን ሙቀቱን አይቋቋምም ልክ ናቸው አልኩ በውስጤ... ከዛ እንድቀመጥ  በተወሰነልኝ ቦታ ቁጭ እንዳልኩ የሲኦል በር ተከፈተ ለመቁጠር የሚያዳግቱ ሰልፈኞች ዥውው ብለው ተሰልፈው ወደእኔ መጡ።

ሁሉም ጠምቶታል ሰልፉ እስኪደርሰው ይቁነጠነጣል።
"ቅድሚያ ሂሳብ ነው...ስትከፍሉ ውሀውን እሰጣለሁ " ስል ወርቅ...የእጅ ሰዓት....ሀብል....አልማዝ ለጉድ እየሰጡኝ እያስቀዱ መሄድ ጀመሩ። እውነትም የተሳካ የቢዝነስ ዕቅድ ነው(አልኩ በውስጤ)።እየቆየ የምቀበለው ሂሳብ ከጀርባዬ ክምር ሰራ....."አሁን ይሄን ወስጄ ምድር ላይ የሆነ ፋብሪካ ማቋቋም አለብኝ ደሞ" ብዬ አሰብኩ። በሳምንቱ ፈጣሪ ጋ ሄድኩ።

"እሺ.... እንዴት እየሄደልህ ነው?" አለ። ፊቱ ያኔ መጨረሻ ላይ እንዳየሁት ነው።

"ጌታ ሆይ በጣም በጣም በጣም ስኬታማ ነበር ....አሁን ግን ወደ ምድር ልመለስ አንዳንድ ነገሮችንም እዛ ለመስራት አስቤያለሁ"

"እምምም.....እስቲ ሞትን አናግረው...." አለኝና ቸኩሎ ከፊቴ ሽው አለ

ወደ ሲኦል በር ልመለስ ስል....ሞት ነፍሶችን ከምድር ተሸክሞ ሲመጣ ተገጣጠምን

"እንዴ ሞት ...ስፈልግህ ስፈልግህ" አልኩት ቶሎ መገናኘታችን ደስ ብሎኝ

"ምነው?"

"የሸጥኩበትን ሂሳብ ይዤ ወደ ምድር መመለስ ፈልጌ ነበር ባክህ...ምድር ናፈቀችኝ...በሳምንት ነው ሀብቴ እጥፍ የሆነው"

"ህም...መመለስ አትችልም....ሞተሀል"

"እእእእ..."

"ሞተሀል...። አርፈህ እዚሁ ነግድ"

"እንዴ...እንዲ ነው እንዴ የተስማማነው...ይውሰደኝ ብዬ አ እንዴ ያመጣከኝ?"

"አዎ....ግን ትመልሱኛላችሁ አላልክም ነበር።እኔም መውሰድ እንጂ መመለስ አላውቅም።" አለ ኮስተር ብሎ

"እንዴ እና ገነት ነው የምገባው ወይስ ሲኦል..."

"እሱን እንግዲህ ፈጣሪን አዋየው.." ተቻኮለ ለመሄድ

"እህህህ..."

"እህህህ አትበል እስከዛ ዝም ብለህ ነግድ..." ከጎኔ እልም አለ።


" ጉድ ነው የጉድ ሀገር
ጉድ ነው የጉድ ሀገር
ቋሚው ይናዘዛል ሟቹ ሳይናገር።"

Abrham F. Yekedas

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

27 Aug, 04:48


Dogs በትላንትናው እለት ለሰሩት ሰዎች ክፍያውን ሰጥቷል።

እስካሁን እኔ በሰማሁት በኢትዮጵያ እስከ 960$ የሰራ ሰው አለ(ከዛ በላይም ሊኖር ይችላል)።

960×120= 115,200 ብር በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሊያውም ታብ ታብ ሳይደረግ ለሀያ ቀናት በቀን አንዴ ወጣ ገባ ስላሉና ጥቂይ Task ስለሰሩ ብቻ... የሰራ ሰው በሰራው ልክ አግኝቷል፤ ግን ከአምስት ሺ ብር በታች ያገኘ ሰው ያለ አይመስለኝም።

አሁንም አልረፈደባችሁም Dogs ካልሰራችሁ cats ተጀምሯል። በመስከረም ላይ እየተጠበቀ ነው....link ከስር አለ ጀምሩ ጀምሩ...🫡

t.me/catsgang_bot/join?startapp=oFOjrtLyE2gX4LX32xLZP

ቡችዬን የቀመሰ ውርዬን ችላ አይልም😋😊

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

11 Aug, 19:08


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

04 Aug, 17:13


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

01 Aug, 04:14


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

25 Jul, 16:43


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

19 Jul, 13:38


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

16 Jul, 04:53


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

15 Jul, 08:59


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

10 Jul, 04:09


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

30 Jun, 16:35


ሰዓት ደቂቃውን፥ ሰከንዱን ታቅፎ፤
በሽክርክር ዙረት፥ ዕድሜን አንከርፍፎ..
ምቱን ሳይቀላቅል፥ ሳይሸራርፍ ዜማ፤
በሰከንድ አጭር ዘንግ፥ ቃሉን እያሰማ..

"ጣ"...

"ጣ"...

"ጣ"...

"ጣ"...

'መንበር' ነው ለዓለም፥ የጊዜ ሰሌዳ..

Abrham F. Yekedas

ለ መንበረ ማርያም ኃይሉ

ሐምሌ 1 ከቀኑ 11፡00 ወደ ብሄራዊ ብቅ በሉ እንግዲህ

@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

24 Jun, 16:32


@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

23 Jun, 18:47


"ትምህርት ቤት አትሄድም እንዴ?" አለች እናቴ ከተኛሁበት አልጋ ፊት ቆማ....

"አልሄድም..." ፊቴን በብርድ ልብስ ሸፈንኩ

"ለምን ሲባል..." ቆጣ አለች

"የአስተማሪዎች ስብሰባ ነው..."

"እንዴ... አራት ቀን ሙሉ....የባዩሽ ልጅ እየሄደ አሁን አየሁት አይደል እንዴ?.....ወይስ እሱ አብሯቸው ይሰበሰባል?.....ትሰማኛለህ ማታ አባትህ ሲመጣ ከምነግረውና ከሚዘቀዝቅህ ቀጥ ብለህ ቁርስህን በልተህ ውጣ..."

"እህህህህ...እማ ደሞ"

"የምን እህህህ......ተነስ ውጣ በዚህ እንዳልቀነድልህ....ትንኝ... ዘጠነኛ ክፍል ገባህና አደኩኝ ነው?" በር መቀርቀሪያውን ይዛ መጣች

"እሺ በቃ...እሄዳለሁ" እያጉተመተምኩ...ተነሳሁ

####

"ይድረስ ለምወድሽ"...አይይ አይባልም

"የሠማይ መሬቱ የባህር ጥልቀቱ".....ጥልቀቱ ነው ስፋቱ🤔 ...ኧረ እንደዛም አይባልም አታካብድ አብርሃም.... ወይ ጉድ

"አፈቅርሻለሁ ማህሌት አፍቃሪሽ አብርሃም"ብዬ ፅፌ ዳርዳሩ በሰማያዊና ቀይ በጌጠ ፖስታ ማሸጊያ አሽጌ የዝናሽ ቦርሳ ውስጥ ከተትኩት....

እዚጋ ነው ትልቁ ስህተት የተፈጠረብኝ... ማህሌት ወድጄ ደብዳቤ ፅፌ የዝናሽ ቦርሳ ውስጥ መክተቴ(ቦርሳቸው ተመሳሳይ መሆኑን ልብ አላልኩም).... ከእረፍት ስንመለስ ማህሌት ቦርሳዋን ስከፍት ተመለከትኩ ደብተሯን አወጣች ሌላ አዲስ ለውጥ አላየሁባትም...ለካ ለውጡ የተፈጠረው ዝናሽ ጋ ነው።

ዝናሽ ደብዳቤውን አነበበችና "ዊቂቂቂቂ..." ብላ ተሽኮርምማ ለዮርዳኖስ ሰጠቻት....ዮርዳኖስ ለበለጡ....በለጡ ለትህትና.....ትህትና ለአብርሃም (ሞክሼ ነው ከኔ ጋ).....አብርሃም "እኔ አልፃፍኩም ያኛው አብርሃም ነው ፅሁፉ ያስታውቃል" ብሎ እያጉረመረመ ለኤርሚያስ.....ኤርሚያስ ለማስረሻ.....ማስረሻ.....አይ ማስረሻ።! እኔ መቼም አልረሳለትም(መቼም አሁን ላይ የአንድ ዕድር ጥሩንባ ነፊ ሆኗል😒) ተማሪው ፊት ሰሌዳው ጋ ደብዳቤውን ይዞት ቆመ። እንደ ድንገት ደብዳቤውን እጁ ላይ ሳየው ወባ እንደያዘው ሰው ሰውነቴን ላብ ዘፈቀውና አንቀጠቀጠኝ።መድሀኒያለም ድረስ😔

ማስረሻ ዓይኔን እያየ "አንዴ ፀጥታ ፀጥታ.... እዚህ አንድ የክፍላችን ልጅ በፍቅር ምክንያት በጣም ጉዳት ላይ ነው። በደብዳቤ ለአንድ ሰው ይህን ፅፏል 'አፈቅርሻለሁ ማህሌት አፍቃሪሽ አብርሃም'...ሀሀሀ" እየሳቀ ወረቀቱን በእጁ ከፍ አደረገው.... ተማሪው በሙሉ በአንዴ ዝም አለና ዞር ብሎ አፈጠጠብኝ.... ማህሌትም ዞር ብላ አይታኝ እንደ አንቡላንስ እየጮኸች ለቅሶዋን ስታቀልጠው ተማሪው እንዳለ በሳቀ አውካካ(በሳቁ መሀል የጮኸም አለ መሰለኝ) እየሮጥኩ ከክፍል ወጣሁ። ይሄ የሆነው አርብ ከሰዓት ነው....ከዛ እስከ ሳምንት ሀሙስ አስተማሪዎች ስብሰባ ናቸው እያልኩ ትምህርት ቤት አልገባሁም። በሳምንቱ አርብ ትምህርት ቤት ስገባ የሁሉ መጠቋቆሚያ ሆኛለሁ። ብቻ የተማሪው አፍ እስኪለቀኝ በሰቀቀን ትንሽ ተሰቃየሁ "አብርሃም አፍቃሪው" ስያሜዬ ሆነ....ማህሌት በዓመቱ ትምህርት ቤት ቀየረች።

###

ትምህርቴን ካጠናቀኩ በኃላ ሴት መቅረብ ፍራቻ ሆነብኝ። ሰው ሁሉ ደግሞ "አግባ እንጂ ምን ቀረ?" እያለ ጎትጓች ሲሆንብኝ አንድ ወዳጄን ሳማክር "ከሬድዮ ፕሮግራሞች ትዳር የሚያገናኙ አሉ" ሲለኝ እዛ ላይ አዳምጥ ገባሁ። ከዛ ትሆነኝ ይሆናል ያልኳትን መርጬ ስልክ ቁጥር ወሰድኩ። ደወልኩላት... እንገናኝ አለችኝ። በቻልኩት ፏ ብዬ ሄድኩ....የተቀጣጠርንበት ሆቴል ገባሁና እንደ ቆምኩ ደወልኩላት።....ቀድማኝ ደርሳ ኖሮ የእጅ ምልክት አሳየችኝ....ተራመድኩ ተራመድኩ ስደርስ "እንዴ....አብርሽሽሽ!" አለች በትልቅ መደነቅ

"ማህሌት...!" እጥፍ ተደነቅኩኝ። ብድግ ብላ ተቃቀፍን....ከድሮ ጀምሮ ትምህርት ቤት ያሳለፍነውን ህይወት አወራን...አብረውን ስለተማሩ ተማሪ አወሳን አወራን...አወራን...አወራን አላለቀብንም። ወደ ቤቷም ሸኘሁዋት እያወራን ወክ አደረግን ወሬያችን አሁንም አላልቅ አለ (ኮከባችን ገጥሟል መሰለኝ) .... በጣም ተጫዋች ሆናለች።

"ማሂ..." አልኳት የግቢዋ በር ጋ ስንደርስ

"ወዬ...አብርሽ"

"እስካሁን ለምን አላገባሽም?"

"ባክህ የፍቅር ጥያቄ ፍራቻ ውስጤ ነበረብኝ....ያኔ class ስንማር እንደዛ ከተፈጠረ በኃላ ለእንደዚ ነገር አይምሮዬ ልክ አልነበረም....የስነ ልቡና ሀኪም ጋ ሄጄ ነው አሁን እንድሻሻልም የሆንኩት አብርሽ"

"አንተስ?"

"እኔ....ያንቺ ፍቅር አልወጣ ብሎኝ ነዋ...ትዝ ይልሻል አ...'አፈቅርሻለሁ ማህሌት አፍቃሪሽ አብርሃም'😊"

ከት ብላ ከሳቀች በኃላ "ያኔማ አዋረድከኝ...ትምህርት ቤት እስክቀይር ድረስ እንዴት እንደቸኮልኩ እኮ....በቃ ሽማግሌ ላካ እኔን ለማግኘት😊"

"መላኬማ አይቀርም...." እንደበፊቱ እንደ አንቡላንስ እየጮኸች አላለቀሰችም(አልተነፋረቀችም) እንደውም ሳቀች።ያኔ በደብዳቤው ምክንያት ያ ሁሉ ከተፈጠረብኝ ወዲህ ሴቶችን ሁሉ የፍቅር ጥያቄ ብጠይቃቸው እሪሪ ብለው የሚያለቅሱብኝና ሰው ተጠቋቁሞ የሚስቅብኝ ይመስለኝ ነበር።ለሌላ ቀን ተቀጣጥረን ተሰነባብተን.... በዓይኔ እየሸኘሁዋት ግቢዋ ገባች።

አሸኙትም ወይ...አሀሀ
አሸኙትም ወይ መሄዱ አይደለም ወይ👏👏👏

ወደ ቤት ተመለስኩ...
"እማዬ"

"ምንድነው?"

"ወገብሽን ጠበቅ!"

Abrham F. Yekedas

@HAKiKA1

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

15 Jun, 12:45


"በሰባት ዓመት 8 ቤት"

ከክፍለ ሀገር አዲስ አበባ ከትሜ እየሰራሁ ግማሽ መጠን የደረሰ የወር ደሞዜን ለቤት ኪራይ የምገብር አንድ ወጣት ነኝ። አዲስ አበባ ከመጣሁ ጊዜውን ሳላውቀው ድፍን 12 ዓመት ቢሞላኝም የከተማውን ሰው ባህሪ ለመላመድ ግን እስካሁን አልቻልኩ። ከክፍለሀገር ወደ ከተማው ስመጣ ለዩንቨርስቲ ትምህርት ነው። ከተወለድኩበት ከተማ ወደ አዲስ አበባ ልከትም ስል "ማንንም እንዳታምን የከተማው ሰው ጩልሌ ብቻ ነው!" የሚል ምክር ከተማ እየተመላለሰ ማር እያዞረ የሚሸጠው አጎቴ በደምብ አስምሮበት ቃሉን ጠበቅ አድርጎ ስለመከረኝ እስካሁንም የሚታየኝ ጩልሌ ብቻ  ነው። ዩንቨርስቲ ትምህርቴን ጨርሼ ወደ ተወለድኩባት ከተማ መመለስ አልፈለኩም እዚሁ አዲስ አበባ ቀረሁ። ታድያ ዩንቨርስቲዬን ለቅቄ ቤት ተከራይቼ በኖርኩበት ሰባት ዓመት 7 ቤት መቀያየሬ እንደ ድንቅ ሪከርድ ቢያዝልኝ ባይ ነኝ።የቤት ኪራይና ካልሲ አይበረክቱልኝም አገኘሁ ብዬ ጥልቅ ስል ከጫፋቸው ለመውጫ ተቀደው ነው የማገኛቸው። አከራዮቼ ፀባያቸው ድንገት ደርሶ ልውጥ ይላል። አንዳንዶቹ "ቤቱን ልሸጠው ነው ውጣ" ይሉኛል ....አንዳንዶቹ "ልጄ ከውጭ ልትመጣ ነው 1 ወር ሰጥቼሀለው" ይሉኛል .... አንዳንዶቹ አዲስ አበባ ባላፈራሁት ወዳጅ "ሰው አበዛህ" ብለው በውሸት ምክንያት ያባሩኛል ብቻ ጉዱ ብዙ ነው።

መጨረሻ ከቤታቸው የለቀኩት አከራዬ ዕድሜያቸው ከእታተይ (ወላጅ እናቴ) ጋር የሚስተካከል ሆኖ ሳለ ሁኔታቸው 29 ዓመቷን ጨርሳ 30ኛ ዓመቷ ፊቷ ደቀን እንዳለ ወይዘሪት ነው። ደላላዬ እቃ ያስገባሁ ቀን ...በል እንግዲህ ይቅናህ....ፀባይህን ካሳመርክ እየተከፈለህ የምትኖርበት ቤት ነው...." ብሎኝ ሳቅ አለ። ነገሮች ቶሎ ስለማይገቡኝ " ኧረ እንዳፍህ ያርግልኝ...ወንድሜ" አልኩት

አከራዬ ባላቸው ሞቶ ልጆቻቸውን ውጪ ሀገር ልከው ብቻቸውን ስለሚኖሩ ሁሌ ማታ ከስራ ስገባ ቡና ጠጣ ተብዬ እጠራለሁ።ቡና መጠጣቱ ሌሊት እንቅልፍ ቢከለክለኝም ተከራያዊ ይሉኝታዬ አሻፈረኝ ማለትን ስለከለከለኝ ሄጄ እጋታለሁ....ተከራይ ነኛ

ታድያ ቡና ልጠጣ ስሄድ እንደ ባህላችን ሰው አይታማልኝም...እታች ሰፈር ስላሉት ሰዎች ዝርዝር ጥንቅር አይቀርብልኝም ጨዋታው ሁሉ "ደምብዛቴ ዛሬ ተሰቅሎ ደም ግፊቴ ደሞ ወርደ.....ደምብዛቴ ዛሬ ወርዶ ደምግፊቴ ዛሬይይ ተሰቀለልህ...አብርሃዬ" ይሉኛል።ውጪ ሀገር ሄዳ ልጃቸው በላከችላቸው DVD ማጫወቻ  ቲቪያቸው ላይ ሁሌ  የሚከፍቷትን የቢዮንሴን "I am single leady" የሚለውን ዘፈን ከነ videoው እየተመለከትኩ "አይዞት እማማ" እላለሁ።

"ሟ....ያርግህ ይሄን አንቱታህን ተው አላልኩም ብለው ቆጣ ሲሉ....ከቤቴ ልቀቅ ይሉኝ ይሆን ብዬ ድንግጥ ስል.... "ሁሁሁይ  አይዞህ እንጂ አይ አብርሃዬ....ወንድ ሁን.....አይ እኛ የዘመኑ ወጣቶች ስንባል" ይላሉ እራሳቸውን አጠቃለው....ከዛ ስስቅ አብረው እየተሽኮረመሙ ይስቃሉ። በእውነት ይሰቀጥጠኛል። ኃላ ላይ እኔም እንዳልገባው ሰው ልግም ስል " አብርሃዬ የደምብዛቴም ግፊቴም መድሀኒት አንተ ነህ።" ብለው ሲያፈጡ ቤቴ የዘረጋሁዋትን ፍርናሽና መፅሀፍ መደርደሪያዬን ጠቅልዬ ከቤታቸው ወጣሁ። አሁን ያለሁበት ቤት በዛው ደላላ ተፈላልጎ ገባሁ። ደላላው "እናት ልጅ ትሆናላችሁ ብዬ ጠብቄ ..." አለኝ...."ተወኝ እስቲ..."አልኩት....ሳቀ

አዲሶቹ አከራዮቼ ካየሁዋቸው ሁሉ ይሻላሉ.....አንድ አራት ወር ከቆየሁ በኃላ በተሻለ ተላመድኳቸው። አንድ ከስምንት ወደ ዘጠኝ ክፍል የተሸጋገረ የ 14 ዓመት ልጅ አላቸው። ልጅ ስለምወድም እሱን በደንብ አቀረብኩት።ቤት ይመጣል። ያጫውተኝና ይሄዳል።

አንድ ቀን ከስራ ገብቼ አልጋዬ ላይ ጋለል እንዳልኩ ተከትሎኝ ገብቶ ከመፅሀፍ መደርደሪያዬ ላይ መፅሀፍ እንዳውሰው ጠየቀኝ። በደስታ መርጠህ ውሰድ አልኩት። ከስራ ደክሞኝ ስለነበር ከአልጋዬ ትከሻዬን ቀናም አላደረኩት።

"አብርሽ አንድ መፅሀፍ ጨምሬ ልውሰድ?"አለኝ

ሊወስደኝ ከጀመረው የእንቅልፍ ሰመመን ስላባነነኝ በስጨት እያልኩ"ቤቢ ከፈለክ መደርደሪውንም አብረህ ተሸክመህ ውሰደው" አልኩት

"ሁለት ይበቃኛል...ደህና እደር" ብሎ ከቤቴ ወጣ.....ከዛ በኃላ ለሶስት ቀናት ያህል  ስራ ስለተደራረበብኝ እያመሸው ስለምገባ አግንቼው አላውቅም ነበር።

በአራተኛው ቀን ጠዋት ወደስራ ልወጣ ፊቴን እየታጠብኩ ልጁ የቤታቸው በረንዳ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ንጋቱን እየታዘበ ወደ ሰማይ አፍጧል"ባቢ ደህና አደርክ?"ስለው ሰላምታዬን ችላ አለና አይኑን ጠበብ አድርጎ በአንክሮ አይኔን እያየ "አብርሃም" አለኝ

ነገረ ስራው ሁሉ ለወጥ አለብኝ "አቤት አልኩ" ፊት መታጠቢያ የያዝኩትን ጆክ ከርፈፍ አድርጌ ይዤ

አይኑን እንዳጠበበ "ከጨለመ ነጋ ወይስ ከነጋ ጨለመ?" ብሎ ጠየቀኝ .....ግራ ገባኝ ምንድነው የሚዘላብደው ብዬ....."ከስራ   ስመጣ እመልስልሀለው" ብዬው ወደቤት ገባሁ። ተመልሼ ወደስራ ስወጣ እዛው ቁጭ ባለበት በትዝብት እያየኝ ነበር..

ማታ ከስራ  ተመልሼ የቤቴን በር እንኳን  ሳልከፍት እናቱ እየታውረገረገች አባቱ ከጀርባዋ ፊቱን ከስክሶ እየገላመጠኝ እንደ አክተር ድቅን ድቅን አሉብኝ...ግራ ገባኝ

"ስማ አንተ...?" አለችኝ በቁጣ

"አቤት" አልኩ.... በጣም ስለተጠጋችኝ እጇን ከሰነዘረች ብዬ እጇን መልከት ስል የኦሾን መፅሀፍ ይዛለች። የአባትየውን እጅ ስመለከት የቀኝ እጁን መዳፍ እንደ ቡጢ መምቻ ጨምቆ ....በግራ እጁ የስብሀትን "ሌቱም አይነጋልኝን" መፅሀፍ ይዟል።

"ብለህ ብለህ ልጄን አባልገህ ልታሳብደው ነው?" አለች ውርግርግ እያለች.....መውረግረጓ በፊት እማማ ቲቪ ላይ የማያትን ቢዮንሴን አስታወሰኝ.....

"ማለት...." አልኩ

"በቃ በቃ ንግግር አያስፈልግም...." አለ አባትየው ከኃላ ሆኖ

ለካ ልጅየው ከመደርደሪያዬ የኦሾንና የስብሀትን መፅሀፍ ወስዶ እምሽክ አድርጎ ነው በጠዋት ሲቀባጥርብኝ የነበረው።
እናቱን"እውን አንቺ ነሽ የወለድሽኝ በምንስ ላውቅ እችላለሁ...ለምንስ ወለድሽኝ?" ብሎ ሳይፈላሰፍባት አይቀርም... ለአባቱም ስለ ውቤ በርሀ ከበርቻቻ ትንሽ ወግ ብጤ ሳይጠርቅለት አልቀረም ...

በኃላ እንዳሰባችሁት አይደለም እያልኩ ለማስረዳት ብሞክርም አሻፈረኝ ብልም መፅሀፌን ደረቴ ላይ አስታቅፈውኝ " በል በል ቤትህን  ፈልግ" ብለው በቆምኩበት ጥለውኝ ገቡ። ቤቴን ከፍቼ ገባሁ አይ ቤቢ ጉድ ሰራኝ.....አይ ኦሾ ጕድ ሰራኝ....አይ ስብሀት ጉድ ሰራኝ።መፅሀፎቹን ወደሼልፍ መለስኩዋቸው። ሪከርድ ተሻሽሏል በሰባት ዓመት 8 ቤት....

     Abrham F. Yekedas

@HAKiKA1