ሰናይ ግጥም @gitimochi Channel on Telegram

ሰናይ ግጥም

@gitimochi


ሰው ማለት ሰው ያጣለት ለሰው የቆመ ሰው ማለት ነው 😍

✍️ Creater @Amele_Senai

ተቀላቀሉን @gitimochi

ሰናይ ግጥም (Amharic)

ሰናይ ግጥም በአማርኛ የተለየ ደምበኛ ውጤት እና ተቀላቀሉን በገጠማ የግጥም እና መረጃዎች እንዴት በተመለከተ እንደከፈለት ጥሩ ነው። ሰው ማለት ለሰው የቆመ ሰው ማለት ነው በዚህ እግር እና ልብ ምንድነው? ሰናይ ግጥም የሰው ማለት ማሻሻያ አለን። በተቀላቀሉን ድረ-ገጽ @gitimochi በበባህር በቀለን እንደክፈለት በአጭር ቀላል ተጨማሪ ሰውየውን በግጥም ወንጌል ይኖርበን።

ሰናይ ግጥም

23 Feb, 21:17


ወርቃማ አባባሎች

* ፍቅር የስሜቶች ሁሉ መዝሙር ነው።/አርስቶትል/

* ፍቅር የተፈጥሮ ሁለተኛ ብርሃን ናት።/ማርቲን ሉተር/

* ፍቅር የአንድ ሰው ከሁሉም በላይ የላቀ ስጦታ ነው።
/ጆአንአኒሲን/

* ከፍቅር ሁሉ የጀማሪ ፍቅር ንፁህ ነው።/ ከቃል መፅሀፍ/

* የምግብ ፍላጎት የሚዘጉ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው፥ትካዜ እና ፍቅር
   
               
@giximochi

ሰናይ ግጥም

16 Feb, 19:50


🌜በጨረቃ ፍቅር የወደቀ ለኮኮቦች ዴንታ የለዉም😎

@gitimochi

ሰናይ ግጥም

11 Feb, 12:53


✅️ሁላችንም ሁለት ኪሶች ሊኖሩን ይገባል !!

****

እንዴት ታደርጋለህ መሰለህ?🤔

✅️ሁሌም ሁለት ኪሶች ይኑሩህ:: ሁለቱም ኪሶች ውስጥ እጅህን ስትሰድ የተለያዩ ወረቀቶችን ታገኛለህ : ሁለቱም ወረቀቶች የተለያየ ጽሁፍ እንዲኖር አድርግ

ስትጨነቅ: ብቸኝነት ሲሰማህ: ሲከፋህ እና አቅም ሲያንስህ  እጅህን ወደ ቀኝ ኪስህ ትሰድና ወረቀቱን አውጥተህ ታነባለህ

እንዲህ ይላል:

👇🏾

"አለም የተፈጠረችው ለእኔ ነው : የማያልፍ የለምና ይህም ያልፋል:: ብርቱ እሆናለሁ: በፈተናም እፀናለሁ"

*

በሌላ ጊዜ ደግሞ አለም በእጅህ የገባች ሲመስልህ: ኪስህ ሲሞላ እና ሰው ሁሉ ሲያሸበሽብልህ እጅህን ወደ ግራ እጅህ ኪስህን ትሰድና ወረቀቱን አውጥተህ ታነባለህ

እንዲህ ይላል:

👇🏾

“ከአፈር ነው የመጣሁት : ወደ አፈርም እመለሳለሁኝ:: ሸክላ ነኝና በማንኛውም ጊዜ ተሰባሪ ነኝ”

🙌🏼❤️

ሰናይ ግጥም

29 Jan, 18:36


የማርያም ንግስ ለት

@giximochi
@giximochi

ሰናይ ግጥም

15 Jan, 10:04


የእኔ አባት የእኔ ደግ የኔ የዎህ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን በጣም ነው የምወደህ ጎበዝ ሰራተኛ ነህ ከኑሮ በአሜሪካ እስከ እስከ እሁድን በኤቤስ 😭😭😭😭😭

ሰናይ ግጥም

09 Jan, 14:06


ለፈገግታ

በአንድ ሰፈር የሚኖሩ አንድ ብልጥ እና አንድ ሞኝ ልጅ ነበሩ፤
ከእለታት አንድ ቀን ብልጡ ልጅ ሞኙን በመጣራት ና..... እንጫወት ሲል ጠየቀው።ሞኙ ልጅም "እኔ ጨዎታ አልችልም" ሲል መለሰለት። በመቀጠልም ብልጡ ልጅ፤ "እሺ እንቆቅልሽ እንጫዎት"
በማለት ሲጠይቀው፤አሁንም በድጋሚ አልችልም ይለዋል።" እንቆቅልሽ የምንጫወተው እኮ እኔ አንድ ብር፤አንተ ደግሞ 50 ሳንቲም አስይዘህ የጠፈው/ያላወቀ/ ይባላል" ይላል ብልጡ ልጅ።ሞኙ ልጅ በዚህ ሀሳብ ይስማማል፤ጨዋታውን ሞኙ ልጅ ይጀምራል
እንቆቅልህ
ምን አውቅልህ
አስራ ሁለት እግር ያለው በሰማይ ላይ የሚሄድ ሲል ይጠይቀዋል
ብልጡም ይግባኝ አላውቀውም
መልሱን ንገረኝ ሲል ብልጡ ልጅ ይጠይቀዋል።ሞኙም መልሱን
አላውቀውም ሃምሳ ሳንቲምክን እንካ አለው 🤣🤣

@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

07 Jan, 06:51


ሁለት ልደት አሉት
እንዴት ማለት
አንድ በአባቱ አለም ሳይፈጠር
ሁለት በእናቱ በድንቅ ምስጢር
.........
የኢያቄብ የሀናን ልጅ ማርያም
እንዴት ቢወዳት ነው እንዴት ቢያከብራት
የአለሙን ጌታ በእቅፎ ያስታቀፋት
አንቺ ቤተልሄም የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ታደለሽ አንቺን ሲመርጥሽ
ቤተ መንግስቱ ለእሱ ሆኖል ቆሻሻ
በረት ውስጥ ተወልዶል ትህትናን ሲሻ
የተወለድከው ለእኛ ደስታ ለራስህ መከራ
ለእኛ የወርቅ አክሊል ለራስህ የእሾህ አሜኬላ
ለይስሀቅ ወርዶል ነጭ በግ ሊታረድ
አንተ ግን አንተ ነህ ኢየሱስ የመስዋቱ በግ
አለምን የሚፈውስ የሚያድነው
የአንተ ደም ብቻ ነው
እንኳን ተወለድክ የአለሙ ጌታ
የአዳምን እንባ ለውጠህ አደረከው ደስታ
የመወለድህ ረቂቅነት ቢያስደንቅም
ዓለምን ከአዳንክብት ምስጢር ግን አይበልጥም።

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን። እመቤቴ ማርያም ሆይ የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው እና ደስ ይበለሽ🙏
ደስታ የተባለውን ንጉስ ክርስቶስን ወልደሽልናልና ምስጋና ይገባሻል?።

ሀገራችንን ሰላም አርግልን

መልካም የልደት በዓል

#ገና ታህሳስ 28 እለት ሰንበት

ሰናይት ሲሻው

@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

31 Dec, 19:56


ለፍቅር መስፈርትሽ ምን ይሆን?

አለ አይኖን እያየ

መልሶን ሲጠብቅ ዝም ብላ አይን አይኑን አየችው

ከብዙ ዝምታ በኋላ,,,,,,,,, በእርግጠኝነት ቤት ይሆን መኪና ሲል በግንባሩ ተለማመጣት

አሁን ዝም ማለት አልቻለችም,,,,,,ቤት ያረጃል ይሰለቻል እድል ከለለህ መንግስት ለስራ ብሎ ይወስደዋል ፡መኪናም ጋራጅ ትገባለች ስትል ንግግሮን ዘጋች።

ታፈቅሪኛለሽ?,,,,,,, አለ

ዙሪያ ቀኞን አይታ አላውቅም እያለች ቦርሳዋን ይዛ ሄደች ።

ከዚያ ቀን በኃላ አይቶት አያውቅም ከዓመታት በኋላ እሱ ልጆቹን እና ሚስቱን ይዞ አንድ ሬስቶራንት ተገናኙ በጣም ደስ አላት ከሚስቱ እና ከልጆቹ ጋር አስተዋወቃት እና ጣቶን ሲያይ ምንም ቀለበት የለም ግራ በመጋባት ስትነሳ እየሸኛት ፤የፍቅር መስፈርትሽን አላገኘሽውም እስካሁን አዳም እንዴት እነዚ የሚያምሩ ጣቶችሽ ላይ ቀለበት አላረግም ሲል ጠየቃታ

እንዲውም በአርምሞ የምትታወቀው ሄዋን የምወደው የማፈቅረው ሰው ከፊት ለፊት ቆሟል ግን ለዚ ሰው አባ የሚለው ጩጬ ልሰጠው አልታደልኩም አለች እምባ እያነቃት ስታለቅስ ለመጀመሪያ ጊዜ አያት አሳዘነችው ቀጠለችለት መስፈርቴ ለሚያፋቅሩት ሰው መስዋትነት መክፈል መሆን ነው ደስታህን ካየው በቂዬ ነው አለች እና እንደመሄድ ስትል ቆይ ከዚህ በኃላስ ምን አሰብሽ አላት ያኔ እንደሚወዳት አስተያየት እያያት


አለውቅም እኔጃ አለች እና አይበሉባውን ሳማችው አይኖቾ ደመና እንዳዘሉ ልዝነብ አልዝነብ እንደሚሉ ዝናብ ያዘቻቸው እና በቃ ደህና ሁን አለችው።😢

ሰናይት ሲሻው

@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

20 Dec, 19:00


ብር ፍቅርን ሰውሮት ጎጆ ቢያጣፍጥም
እኔ ግን ምስኪኑ
ያንችን ልብ ትርታ ለማንም አልሰጥም
ይሔው በደረቴ ሀቅ አንሾካሾከኝ
የልቤን ጥግጋት
በምቱ ሊያጠምደው ቀርቦ እየታከከኝ

ኣኣ...
ፍቅር ዘመተብኝ
እንጃልኝ
አንችን ከነኩብኝ😂

@gitimochi
Senai poem

ሰናይ ግጥም

15 Dec, 04:11


መልካም ልደት እህት ዓለሜ😘🥰😍🍰🥳🥳🥳 እስኪሰለችሽ ኑሪልኝ።

ታህሳስ 5

ሰናይ ግጥም

04 Dec, 20:25


ከግጥም አታልፊም

🌓
🌓1

መጣሽም :አልመጣሽ
ኮራሽም: አልኮራሽ
ደመቅሽም ፡አልደመቅሽ
አወቅሽም ፡አላወቅሽ
ብትሽኮረመሚ፡ ብትኮሳተሪ
ዝም ፡ጭጭ ፡ብትይ ፡ደሞም፡ ብታወሪ
ብትገላመጪ ፡ብትንቀባረሪ
መፅሐፍ ፡ብትደግሚ፡ ቁርአን ፡ብትቀሪ
መሐይም፡ ብቶኚ፡ አልያ ፡ብትማሪ
ያሻሽን፡ ቢያረግሽ፡ ያሻሽን ፡ብቶኚ
,ልብሽ ፡ቢርገበገብ፡ አልቅሰሽ፡ ብታዝኚ
ብትንከራተቺም እኔን አታገኚ!
ምናልባት!
አንጀቴ፡ እንኳን ፡ሳስቶ፡ ልቤ ፡ቢወድሽም
አድናቆት፡ ካለው፡ ቃል፡ ከግጥም፡ አታልፊም

poet :🔆 ዳዊት ጥዑማይ

Join and share
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@gitimochi
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥

ሰናይ ግጥም

03 Dec, 08:08


ነግሬሽ ነበረ💔💔💔


@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

28 Nov, 15:54


አንዱ ወንበዴ ሰው በጩቤ ወግቶ ይገልና ይታሰራል፤ ፍርድ ቤት ይቀርባል ከዛ ዳኛው ይሄን ጩቤ ታውቀዋለህ ብሎ ጠየቀው? ተከሳሽም በፍፁም አይቼው አላውቅም አለ። በሌላ ቀጠሮ አሁንም አታምንም ይሄን ጩቤ ከዚህ በፊት አይተኸው አታውቅም ብሎ ዳኛው ተናዶ ጠየቀው፤ ተከሳሽም እዎ ይሄንንማ አይቼው አውቃለው አለ። ዳኛውም ደስ ብሎት በዚ ጩቤ እከሌን ስለመግደልህስ ታምናለህ አለው፤ እዎ ክቡር ፍርዱ ቤት ይሄን ጩቤ የማውቀው እኮ ባለፈው እርሷው አሳይተውኝ ነበር እርሱ እንዴ🤪

@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

22 Nov, 13:18


በውሸት ታሪክ ላይ ያልተመሰረተ


ገጠርም የሚባል አደል ከተማም ማለት ያዳግታል ብቻ መካከለኛ ከተማ ይባል ብዙ እህት እና ወንድም አለኝ ለቤቱ ሁለተኛ ልጅ ነኝ ስሜ ውዴ ይባላል ታለቅ ወንድም እና ከእኔ በታች ሶስት እህቶች እና መንታ ወንድሞች አሉኝ በጠቃላይ ሰባት ነን ከእናት እና ከአባቴ ጋር ዘጠኝ ሆን ማለት አይደል። ፐ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዘዎለው ያለው ለአብርሃም ሳይሆን ለእኔ አባት ነው የሚመስለው ስለ ኑሮችን ሳወራ ደሃ ነን ነጭ ደሃ ነው የሚሉት ሲያጋንኑት። እናቴ መንታ ወንድሞቼን በቅርቡ ነው የወለደቻቸው መውለድ ፈልጋ አይደለም ማስወረጃ ብር አጥታ ነው የሰፈሩ ሰው የእንቁላል መፈልፈያው ምንድነበረ? እኩልቤተር ናት በዚ ኑሮ ልጆችን ለምን ታሰቃያቸዎለች ይላሉ ለእኛ አዝነው አይመስለኝም በወለደች ቁጥር ይዘው መጠየቅ ስለማረራቸው ይመስለኛል እኔ ስምንተኛ ክፍል ነኝ እህቶቼ ታች ክፍል ናቸው ውጤታቸው ከመጨረሻ አንደኛ ነው ድህነት የገባቸው አይመስሉም ኃላፊነቱን በሙሉ ራሴ ላይ የምጠለው አዳሪ ትምህርት ቤት ብገባ ሚኒስትሪን በደንብ ሰርቼ ይሄ ስቃይ ይቆማል በማለት ማታ ሳነብ ነው የማድረው እንደማረገው ደግሞ በደንብ አውቃለው የራሳችን ዬኒፎርም የለንም ጫማም እንደዛው በፈረቃ ስለምንማር አንደኛዎ እህቴ ልብሱን ጫማውን አውልቃ ለዛችኛው ትሰጣለች እኔም እንደዛው በዚ መሀል ይረፍዳል አንድ ክፍል ጊዜ ያመልጠናል ስለለመድነው ምንም ማለት አይደለም በግዜ የሄድን እንደሆነ የክላስ ጓደኞቻችን በሰላም ነው ብለው ያፌዙብናል ቦታ ሰጥቻቸው አላውቅም። ወንድሜ በሶስት ዓመት ይበልጠኛል ትምህርቱን አቁሞ ጋራጅ ይሰራል ለእኛ ሲል ያገዝኩት እየመሰለኝ በዘይት የተጨማለቀውን ልብሱን አጥብለታለው ባይለቅም እንዳይከፋን ፈገግ ይላል ውዷ እህቴ ሳይል አይውልም ፍቅራችን ልዩ ነው ሀብታም ስሆን መጀመሪያ ላንተ ነው መኪና የምገዛለህ እለዋለው።ስለ አባቴ ሳወራ ልጆቹን በጣም ይወዳል ስራውንም አለው አለው አልሆነለትም ሄደ የት? ሄዶል በቃ። ሚንስትሪ የምፈተንበት ቀን ደረሰ እንዳሰብኩት ቀላል አይደለም ተፈትኜ ጨረስኩ እናቴም ስራ መስራት ጀምራለች ልብስ እናጥባለን እህቶቼ መንታዎቹን ይጠብቃሉ ግን ጠግበን ማደር አልቻልንም። ወንድሜን አናገርኩት ውጪ ላከኝ አልኩት ትምህርትሽስ ብሎ ሲጠይቀኝ የምማረው ለገንዘብ እንደሆነ በዚህ ሁኔታ እንደማንቀጠል ፆማችንን ማደር እንዳንፈገፈን ስቃያችንን አብዝቼ ነገርኩት። በሀሳቤ ተስማማና ፕሮሰስ ጀመርን መታወቂያ ፖስፖርት ሁሉንም ጨራረስኩ መሄጃ ገንዘብ ወንድሜ ተበደረ ከባለ ጋራጁ ባለቤት ሁላችንም ተላቀስን እና ጉዞ ወደ ቤሩት ከደረስኩ በኋላ አሰሪዎቼ ተቀበሉኝ የምፈልገውን ማንኛውም ነገር እንድጠይቃቸው ነገሩኝ። በጣም ሀይማኖተኛ ፈጣሪያችውን ፈሪሃ ነበሩ የሀብት መጠናቸው የሚጋነን አይደለም ግን ጥሩ ኑሮ ሀሪፍ ይከፍሉኛል። የመጀመሪያውን ደሞዝ ለ ወንድሜ ላኩለት እዳውን እንዲከፍል በየወሩ እልካለው እንዲጠቀሙበት እና እንዲያስቀምጡ ስልክ አስርዬ የአመት በዓል ጊዜ ስጦታ ሰጠችኝ ስለ ሀገሬም ሆነ ስለቤተሰቤ ለማወቅ ቀላል ሆነልኝ እንደ fb imo ያሉትን መጠቀም ከአንዲት አረብ ሰራተኛ መፅናኛ ነው እና በfb ከአንዱ ጋር ተዋወቅን ርቄ ስላለው ይሆን አላውቅም ኢትዮጵያ ስመለስ ወንዱ ሁሉ አግብቶ ይጠብቀኝ ይመስል እሱ ጋር ሙጭጭ አልኩኝ ብር ሲለኝ መላክ ነው ማስቀመጥም እሱ ጋር ሆኖል ስራዬ በፍቅር እፍፍፍ አልን እኔ ብቻ ሳልሆን ይሄ የብዙዎቻችን የአረብ ሰራተኞች ችግር ይመስለኛል ወንድ ብርቃችን ነው ምን አስዋሸን። ሁለት ዓመት ሊሞላኝ ሲል ግን ብዙዎችን ያስደነገጠ ቤሩትን እንዳልነበረች ያደረገ ፍንዳታ ተፈጠረ። ፍንዳታው ከተፋጠረበት ቦታ የእኛ ይርቃል ግን መስተዋቱ አይኔ እያየ ተሰነጣጠቀ የኢትዮጵያ አምላክ ነው የደረሰለኝ እንጂ ዛሬ ይሄን ታሪክ ባላወራውት ተረስቼ ነበር። በዚህም እኔ እና ቤሩት ደንግጠናል ሀገሬን አልኩኝ አሰሪዎቼም ኑሮቸው ተናጋ ማለት ይቻላል እንደ ሀገር ነው እና የሚከፍሉኝ እራሱ እየተጭናነቁ ሆነ እኔም የሰበሰብኩትን ሰልባጅ ይጄ ወደ እምዬ ሀገሬ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቼ ደነገጡ ምክንያት ገና ብዙ እንደምቆይ ነበር የሚያውቁት ምንም ለውጥ የላቸውም ጥያቼው እንደሄድኩ ነበር በጣም አዘንኩኝ ተቀማጭ ብርም የለም እናቴም ጉስቅል ብላለች ፍቅረኛ የተባለውም ስልኩ አይሰራም የለም አእምሮዬ ተረበሸ ፈጣሪን ለምን አልኩት እጄ ላይ ባለው ብር ዱባይ የመሄድ እና ለመጨረሻ ጊዜ ስቃዩን ማብቃት እንዳለበኝ ወሰንኩ። ዱባይ ከገበው ጊዜ አንስቶ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ ይዞል እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ አሁንም በስደት ላይ ነኝ ምን አልባት በቅርቡ ወደ ሀገሬ እመጣለው።
ጨረስኩ

ባለታሪክ????

ሰናይት ሲሻው


@gitimochi
@gitimochi

ሰናይ ግጥም

20 Nov, 19:12


በተቀደሠው ተራራ

ቅዱስ እግዚአብሔር
ተገለጠ ከሙሴ ጋር
የኮሬብ ተራራ
የአምላክን ክንድ ሲፈራ
ተንቀጠቀጠ ቅዱሱ ተራራ
እግዚአብሔር አምላክ ሆኖ
በደመና ለሙሴም ትእዛዝ ተሰጠው      አለው ወደኔና
        ሙሴም ወጣ ወደ ሲና
እግዚአብሔርም በደመና ሆኖ
    ትእዛዛትን ሰጠ
ተራራውም ከአምላኩ ክብር የተነሳ
     ቀለጠ እንደ ሻማ
እንደጧፍ ነደደ አረረ በሰለ
ክብሩንም መሸከም ስላልቻለ
         ዘ ሲና  ያተራራ
ክብር የተገለጠበት ከሙሴ ጋራ
የእስራኤል ሕዝቦች ተሳሳቱ
መሪያቸው ሙሴ ባለመታዬቱ
አሮንን አማልክት ስራልን አሉት
በአሮን ላይ ሸመቁበት
ከሚስቶቻቹህና ከልጆቻቹህ
ወርቅን ስጡኝ አላቸው
እነሱም ሰጡት ታውሮ ልቦናቸው
የኀይላቸው ትእቢት
የዐይናቸው አምሮት
የነፍሳቸውም ምኞት
የልባቸው ክፋት
ከፈርኦን ባርነት ያወጣቸውን
መቼ አሰቡት እግዚአብሔርን
እየዘፈኑ ሲያመጡ ጣጣ
ሙሴም ፈጥኖ ሲመጣ
ለሞተ መሥዋዕት አገኛቸው
እየተበላ እየተጠጣ
ተንበርክከው እየሰገዱ
በጣኦታትም ስህተት ሄዱ
ከግብጽ ባርነት ያወጣቸውን ትተው
አምላክ ይላሉ አምላክ ላልሆነው
መልስም ለማይሰጠው
የሰው እጅ ሥራ ለሆነው
እግዚአብሔር አምላክን ትተው
ዛሬም አሉ ከእነሡ ተምረው
ጠንቋይ ያውቃል ብለው
ከመንገድ የወጡ በሀሠት አብለው
ጠንቋዮች በምትሃት አስተዋቸው
እውነት ፈሪጁን ትተው
ሄዱ ጠንቋይ በሆነው
ጠንቆይም አስጠንቆይም ልብ ብለህ ስማ
በጥንቆላ አይደለም ሀገር የምትለማ
በንስሐ ተመለሱ
መዳንም እንዳለ እንዳትረሱ
ኀጢአትም እንዳለ
መዳንም አለ
       በንስሐ መታደስ
       ወደ ቀልብ መመለስ
ወደ እግዚአብሔር መቅረብ
በንስሐ ታጥቦ ተመልሶ ማበብ
የእግዚአብሔር ቸርነቱ
ጠፍተን እንዳንቀር ነው ፍላጎቱ
እግዚአብሔር ልጆቼ ሲለን
አቤት እንበለው አባታችን
ዐይናችንን ያብራልን
የፍቅር ጣዕሙን ይስጠን
Senait Sishaw

ሰናይ ግጥም

16 Nov, 08:26


"ያቺን ልጅ ንገሯት"

@giximochi

ሰናይ ግጥም

15 Nov, 13:49


ስልኩ ይጠራል ግን አያንሳም😢