Islamic Post✨🕋 @solualenebiiy Channel on Telegram

Islamic Post🕋

@solualenebiiy


ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ ;"እኔ ከሙስሊም ነኝ" ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? (41:33)

"For any Comment and cross
@Solualenebi

Islamic Post✨🕋 (Amharic)

የአሁኑ ግል የመኖሪያ እና የትክክለኛ መረጃ የሚያገኝ አዝናኝ ድራማ ነገር ከእንግሊዝ ጋር ይባላል። 'Islamic Post' በተለያዩ አካባቢ መታሰቢያዎቹን ለማፍቀግ እና ልማት እንደሚፈልግ ይገልጻል። የትነግርህ ምንድን ነው? 'Islamic Post' አምላክን በሙስሊሙ እና አላህን ለመበልጠው ባለሙያዎችን መሰረት የመጽናናት መልኩት ለማድረስ እና እንዲሁም ለአብዛኞች የሚሰራበት አገልግሎት። የ'አላህ ይመልከቱ' በመንገድ ቢስ በላይ የሚጠቀመውን እና ተስፋውን ማንበብ በማድረግ በብቃት። ከተጠቃሚው መካከል ስናባል አላህ ቅሪህን አሠቃ። ተጨማሪ እና ማስተማር እንችላለን።

Islamic Post🕋

23 Nov, 19:33


📍ከፍቶሀል ሀቢቢ?🥺💔🙇‍♂

         አንቺስ ከፍቶሻል ኡህቲ?🙇‍♀🥺💔

👌 ቀናቹን ፍክት የሚያረጉ 😍😍😍

💖ስሜታቹን የሚቀይሩ ምርጥ ቻናሎችን ተቀላቀሉ ስሜታቹ ይቀየራል ❣️❣️❣️❣️

🔰 ሊያመልጥ የማይገባ ቻናሎች ናቸዉ❗️

Islamic Post🕋

23 Nov, 18:40


👌ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ የኢትዮጲያ  ቻናሎች ❤️❤️

⚠️ ከ 10 ደቂ ቡሃላ ስለማታገኙት ፈጥነዉ ይቀላቀሉ!👇👇👇

Islamic Post🕋

23 Nov, 18:08


👒የልጅነት ጊዜ ጨዋታ
እስከምን ጊዜም የማይጠፋ❤️

ጨርሱት አላቹ ቤተሰብ ዛሬ አንድ ለየት ያለ ቻናል ይዘን መተናል ቻናሉ ልጅነታችንን የሚያስታውሱ ማንኛውም ነገሮች የሚለቀቁበት ነው እና ቶሎ ተቀላቀሉ❤️‍🔥

join የሚለውን በመንካት ተቀላቀሉ
👇👇👇👇

Islamic Post🕋

21 Nov, 05:10


❤️ ቀይስ አል መጅኑን❤️

ይህ ለፍቅር ሲሉ ልባቸውን ከሰጡ ልብ ገባሪዎች ውስጥ እውቅ ሆኖ እንደተምሳሌት የሚወሰድ የ"መጅኑን" እና የ"ለይላ" የፍቅር ታሪክ ነው። ይህ ልብ ሰቃይ የሆነ የመጅኑን እና የለይላ ታሪክ በሚተረክ ጊዜ በብዙዎች ልብ ውስጥ ስቃያቸው ተስምቷል፡፡ በዚህም የራስ ህመም ተደምጧል። ዘመኑ እንደ ሂጅራ አቆጣጠር ከ645 ዓ.ሂ ጀምሮ እስከ 688 የዘለቀ ነው።
ፍቅር ከልበ ልቦና የሚመነጭ ሰብዓዊ ስሜት ሲሆን እዚያው ልብ ውስጥ ጎጆ ቀልሶ እዚያው ህያው ሆኖ ዝንተ ዓለም የሚንቀሳቀስ ተፈጥሯዊ ስሜት ነው። ፍቅር መንፈስ እና አካል የተጋመዱበት ሚስጢር ነው ይባላል። የአካል አስፈልጎት እና የመንፈስ ቀለብ የሚጣመሩበት የተለየ የግንኙነት ነጥብ ነው። ፍፃሜ መቋጫ የሌለው የጸና ክቡር ቃል ኪዳን ነው። በዚህም ራሳቸውን ገዝተው በበለጸገ የፍቅር ስሜት የአላህን ታላቅነትና ኃያልነት እያደነቁ የሚኖሩበት የህይወት መንገድ ነው።
እንደተምሳሌት ለፍቅር ሲሉ ልባቸውን ከሰጡ ልብ ገባሪዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን "መጅኑን እና ለይላ"ን ላስተዋውቃችሁ ወደድኩና እንካችሁ አልኩ።
የውልደት ሥሙ "ቀይስ" ነው። ጧትም ሆነ ማታ የሚያውጠነጥነው "ለይላ"ን መሆኑን የተመለከቱ ሰዎች "መጅኑን ለይላ" የሚል ስያሜን ቸሩት። በእርግጥም በፍቅር የከነፈው ወጣት እስትንፈሱ "ለይላ" ነበረችና ነው።
በ"ለይላ" ፍቅር የከነፈው የእብዶች ሊቅ "ቀይስ" ነው። "መጅኑን" የሚለው የዐረበኛ ቃል "እብድ" ማለት ሲሆን እርሱ ግን በፍጹሞ እብድ አይደለም ይላሉ።
ከፍቅሩ ውጪ ለዚች ዓለም ቁብ የሌለው ሆኖ የፍቅር ጥም አልቆረጥለት ስላለው እና፣ ኗሪ በሌለበት ኦና በሆነ ዓለም የጧት ማታ መመሰጫው እሷን ብቻ በማድረጉ ነው የእብደት ስያሜ የተሰጠው። ለርሱ ሕይወት ማለት ለይላን ማፍቀር ነው። ፍቅር በቅርበትና ርቀት ሳይለካ በመስፈርያ ሳይሰፈር፣ በማግኘትና በማጣት ሳይመዘን ማፍቀር መሆኑን ስላስተማረ ነበር። በማጣት ውስጥ ማግኘትን ሰንቆ ሳይደክም እስከ መቃብር ስለዘለቀ "መጅኑን ለይላ" የተባለው።
"ለይላ" ከሀብታም ቤተሰብ የተወለደች ቆንጅዬ ልጅ ነበረች፡፡ በቁንጅናዋም ልዕልት ነች። "ቀይስ" ደግሞ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነው። ሆኖም በዓረቦች ባህል መሰረት ልጅን ወደ ገጠራማ ስፍራ ልከው ያሳድጉ ነበርና ሁለቱም በአፍላ ዕድሜያቸው አብረው ጫካ ለጫካ፣ በየ ጋራና ሸንተረሩ ፍየል ጠብቀው፣ አፈር ፈጭተው አደጉ። ጭቃ አብኩተው ጠፍጥፈዋል። ውኃም ተራጭተዋል።
ይህን ተከትሎ በመንደሩም ውስጥ አንዳንድ ሰዎች፦
"ለይላ ከድሃው ልጅ መጅኑን ጋር በፍቅር ወደቀች" ብለው ማውራታቸው የሚያጠራጥር አልነበረም፡፡ እርስ በእርስ የነበራቸው ጥልቅ ፍቅር ገደብ አልነበረውምና፡፡
በዕድሜያቸው ከፍ እያሉ ሲመጡ "መጅኑን" እና "ለይላ" የሚገናኙበት መንገድ እየጠበበ መጣ። በቁንጅናዋም ከልዕልት ያልተናነሰች በመሆኗ ሀብታም ሰው አግብታ ስኬታማ ሕይወት እንድትኖር በቤተሰቦቿ የምትጠበቅ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ እጣ ፈንታቸው ሆኖ ሁለቱ ፍቅረኛሞች እርስ በእርስ ከመተያየት ታገዱ፡፡ ከዚያም አልፎ የ"ለይላ" ቤተሰቦች ካለ ፈቃዷ ለሀብታም ባል ለኢብን ሰላም ዳሯት። በትልቅ እልፍኝ ውስጥም መኖር ጀመረች፡፡
አፍቃሪዋ "ቀይስ" መመለሻዋን ቀን ይጠባበቃል። ያንን የልጅነት አፍላ ዘመን እንደዚያው እንደ ልጃገረድነቷና ያለለውጥ እንደምትመለስ በተስፋ ተሞልቷል። ያንን ቀን ይጠባበቃል።
ከዕለታት አንድ ቀን የ"ለይላ" ውሻ እያለከለከ በመንገድ ላይ ሲሄድ ቀይስ ይመለከተዋል። በለይላ ናፍቆት ልቡ ተሰልቧል። ውሻውን ከኋላ እየተከተለ ለይላ ያለችበት ቦታ ለመድረስ ጉዞ ጀመረ። መንገድ ላይ ሰላት የሚሰግዱ ሰዎችን አሳብሮ አለፈ።
በዚያው መንገድ ተመልሶ ሲያልፍ ሰላት ይሰግዱ የነበሩት ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦
"ለምንድን ነው … ሶላት እየሰገድን በፊት ለፊታችን ቆርጠክ ያለፍከው?" አሉት። እርሱም፦
ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺇِﻧِّﻲ ﻟَﻢ ﺃﺭَﺍﻛُﻢ ﻛﻨﺖ ﻣﺸﻐﻮﻝ ﺑﺄﻣﺮ ﻟﻴﻠﻰ ﻭﺷﻐﻠﻨﻲ ﺣﺒﻬﺎ ﻋﻦ ﺭﺅﻳﺘﻜﻢ … ﻭﺍﻟﻠﻪ ﻟﻮ ﻛﻨﺘﻢ ﺗﺤﺒﻮﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻛﻤﺎ ﺃﺣﺐ ﻟﻴﻠﻰ ﻟﻤﺎ ﺭﺃﻳﺘﻤﻮﻧﻲ ﻭﻷﻧﺸﻐﻠﺘﻢ ﺑﻪ ﻭﺑﻤﻨﺎﺟﺎﺗﻪ ﻋﻦ ﺭﺅﻳﺘﻲ
"ወላሂ በለይላ ፍቅር ላይ ባተሌ ሆኜ ስትሰግዱ አላየኋችሁም። …እኔ "ለይላን" የምወዳትን ያህል እናንተ "አላህን" ብትወዱ ኖሮ እኔን ባልተመለከታችሁኝ ነበር። እናንተ አላህ ፊት ሆናችሁ እኔን ተመለከታችሁ እኔ ግን ከለይላ ውሻ
ኋላ ሆኜ እንኳ አልተመለከትኳችሁም" ሲል መለሰ።
ታላላቅ ዐሊሞች አላህን እና መልዕክተኛውን በተመለከተ የሰው ልጅ ሁሉ ሊኖረው ስሊሚገባው ፍጹማዊ ትስስር ሲመክሩ ይህንን መሰል ታሪኮች እያነሱ ምክራቸውን ያዋዛሉ። "እንኳን ፍጡር ለፈጣሪ፣ ሰው ለሰው እንዲህ ተሳስሯል" ይላሉ።
ለይላ በትዳር ውስጥ ሆና ዓመታት ነጎዱ። በአንድ ወቅት ለባሏ እንዲህ ስትል ጠየቀች፦
"መጅኑን በዚህ በኛ መንደር ግዛት ዙርያ በአንዱ ጫካ ሰፍሯል አሉ። ካለበት ቦታ ፈልጌ እንዳገኘውና ከአጠገቡ ቀርቤ እንዳዋራው ትፋቀድልኝ ዘንድ እባክህ ልለምንህ" በማለት ተማፀነችው። ባለቤቷም ፈቀደላት። ይፈልጉት ጀምር። ከአንድ ኮረብታ ቦታ ላይ ተቆናጦ አገኘቺው።
ቀረብ ብላ "ቀይስ" አለች። መልስ አልሰጣትም።
"እኔ ለይላ ኮ ነኝ" ስትለው … ከታች እስከ ላይ ቃኛትና፦
ﺇﻟﻴﻚ ﻋﻨﻲ ﺃﻧﺎ ﻣﺸﻐﻮﻝ ﺑﻚ ﻋﻨﻚ
"…እስኪ ተይኝ ሂጂ እኔ ካንቺ ባንቺ (ፍቅር) ላይ ባተሌ ነኝና" አላት። (እኔ ያፈቀርኩት ሰውን ሳይሆን ፍቅርን ነበርና፣ አሁንም ፍቅርን በማፍቀሬ ማፍቀርን ወድጄ ይኸው በምቾት እዚያው ለይላ ፍቅር ላይ እገኛለሁ) እንደ ማለት ነው ሲሉ አፍቃሪያን ያብራራሉ።
ሁለቱ አፍላ ጣምራዊያን በትልቅ እልፍኝ ህመም ውስጥ መኖር ጀምረዋል። ለይላ ከፍቅረኛዋ ጋር መለያየቷን መቋቋም ባለመቻሏ ወደ ዘላለማዊው ሕይወት ተሻገረች፡፡ መጅኑንም በፍቅረኛው ሞት ልቡ በመሰበሩ እና በሀዘን በመዋጡ ለእብደት ተዳረገ በመጨረሻም የለይላን መቃብር ተደግፎ እዚያው ሞተ። እነዚህ አስገራሚ ፍቅረኛሞች እርስ በእርስ ለነበራቸው ፍቅር ሕይወታቸውን እስከማጣት በመድረሳቸው ለፍቅራቸው የነበራቸው ስሜት ህያው ሆኖ እንዲኖር አደረገው

_
ምንጭ:
كتاب: روضة المحبين لابن القيم
أسرار المحبين
كأنك الله
الإعتبار بحب المخلوق
_
https://t.me/solualenebiiy

Islamic Post🕋

14 Nov, 18:35


Islamic Post🕋 pinned «#ዑዝላ_ጤንነት_ነው ዑዝላ ማለት መነጠል፣ መገለል ማለት ነው። በርካታ ፍቺዎች ያሉትን ይህን ባሕርይ ታላላቆች ነፍስን ለማዳኛ፣ መንፈሳዊነትን ለማጎልበቻ የተጠቀሙበት መንገድ ነው። የመጨረሻ መጨረሻ ደረጃ የሚባለው ትርጓሜው ከሰዎችና ከክፉ ሐሳቦቻቸው፣ ለዱንያም ለአኺራም ከማይጠቀመው ሐሳባቸው የምንገለልበት መንገድ ነው። ልክ የካህፍ (ዋሻው) ሰዎች ከአምባገነኑ አገዛዝ ራሳቸውን እንዳሸሹት፣ ልክ የአላህ…»

Islamic Post🕋

14 Nov, 17:28


#ዑዝላ_ጤንነት_ነው

ዑዝላ ማለት መነጠል፣ መገለል ማለት ነው። በርካታ ፍቺዎች ያሉትን ይህን ባሕርይ ታላላቆች ነፍስን ለማዳኛ፣ መንፈሳዊነትን ለማጎልበቻ የተጠቀሙበት መንገድ ነው። የመጨረሻ መጨረሻ ደረጃ የሚባለው ትርጓሜው ከሰዎችና ከክፉ ሐሳቦቻቸው፣ ለዱንያም ለአኺራም ከማይጠቀመው ሐሳባቸው የምንገለልበት መንገድ ነው። ልክ የካህፍ (ዋሻው) ሰዎች ከአምባገነኑ አገዛዝ ራሳቸውን እንዳሸሹት፣ ልክ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሒራ ዋሻ ውስጥ እንደተገለሉት እንደማለት ነው።

በዛሬ ዘመን ሚድያዎች በተለያየ ቅርጽ የሰዎች ውስጥ እንዳይረጋጋ ይቆምራሉ። ሆነ ብለው ይህን የሚሰሩ የሚድያ ቅርጾች እንዳሉ ኹሉ የሌሎችን መንፈስ የሚያራግፉም አልሉ።

ትዳር ከብዶ ዝሙት ከቀለለ፣ ሕይወት አሰልቺ ኾኖ ሞትን ካስመኘ፣ ሓይማኖታዊ ሰበካዎች ሞልተው ኢማን (እምነት) ከጠፋ፣ አስተማሪዎች ከተማሪዎች ጋር ከተመሳሰሉ የሕግ አስከባሪዎችና ጠባቂዎች ዘራፊ ሲኾን ስታይ ከቀውሱና ንትርኩ ራስህን በማግለል፣ ከማይመለከተን ቦታ በመራቅ ነፍስን መታደግ ያስፈልጋል።

ስታያቸው አላህን ከማያስታውሱህ፣ አብረኻቸው ስትቀማመጥ የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከማያስናፍቁህ ሰዎች፣ ክህሎትን ከማታሳድግባቸው፣ ከማትማርባቸውና ከማትዝናናባቸው ሰዎች መራቅን መለማመድ አስፈላጊ መንፈሳዊ ልምምድ ነው። የምትፈጥርባቸው አዎንታዊ ለውጥ ወይም ትክክለኛ የዐላማ ግንኙነት ከሌለህ አብሮ መዛለቁ ጥቅም የለውም። ይህ ክፋት አይደለም ይህ እውነተኛው መረዳዳት ነው።

ከተለመዱ ስብስቦችህ ውስጥ የኢማን እድገት ከሌለ፣ የአስተሳሰብ ልሕቀት ካልተፈጠረ ምንም አታደርግም መንገድ ለመቀየር ደፋር ኹን። ምንም ዓላማ ከሌለህ አከባቢ ብዙ ሰአት በማባከን ጊዜህን አታጥፋ። ከስበህ (ሰርተህ) ለቤትህ የምታመጣውና ምንዳ የምታገኝበት ቦታ ላይ ኒያን በማስተካከል ከአላስፈላጊ ነገሮች ራስህን ማቀብ ከቻልክ ይህ በራሱ ዑዝላ ነው።

ከማይጠቅሙ የሚድያ አጠቃቀሞች መሸሽ፣ ከአላስፈላጊ ስብስቦች ራስን ማቀብ (ሃይማኖታዊ ቢኾኑም እንኳን) ቅርብ ለኾነው ሞት እንድንዘጋጅ ያግዛል።

ዑዝላ ኒያ ይፈልጋል። ዑዝላ ከሐቅ መሸሽ አይደለም፣ ከመታገል መታቀብ አይደለም፣ አለመጋፈጥም አይደለም። ሀይል ማሰባሰቢያ ነው፣ ዐዲስ መንገዶችን የምንፈልግበት መንገድ ነው፣ የተበላሹ ነገሮችን ከትክክለኛው ነገር የምንለይበት መንገድ ነው። በተለይ ወጣቶች (ተማሪዎች) ስብስቦች የሚያድናቸውን ያህል እራሳቸውን እንዳይመለከቱም ስለሚያደርጋቸው ከበርካታ ጥፋቶች እንዲታደጉ ሲባል የወላጆች ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ያሻቸዋል። በመገለልና በመሰባሰብ መካከል ያለውንም ልዩነት እንዲረዱ በማስቻል መገለላቸውን ለጥፋት አለማዋላቸውን ማጣራት ያሻዋል።

በመገለል ውስጥ ሊሰሩ ከሚችሉ በርካታ ነገሮች መካከል ዋነኛውም አምልኮኣዊ ተግባራት ናቸው። አካላዊ ጤንነትን ለመጠበቅ፣ አዕምሮኣዊ ደህንነትንም ለመንከባከብ አስፈላጊው መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ከሰዎች በምንነጠልበት ጊዜ ከአላህ ጋር ብዙ ለማውጋት ስለሚረዱ ከለመድናቸው ቦታዎች ስንሸሽ ሌሎች ዐዳዲስ ቦታዎች ላይ በዐዲስ ባሕርይ መገኘትም እንችላለን ማለት ነው።

አላህ ያስረዳና

በመቀላቀል ውስጥ ከሚመጣ በላእ ይጠብቀን

©️Best kerim

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

08 Nov, 04:00


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

በሶለዋት የደመቀ ውብ ጁምዐ ይሁንልን💚

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

07 Nov, 03:40


በጣም ብዙ ነገርን ደብቀህ
ከሰዎች እኩል ለመቆም እንደምትጥር ስታስበው ምናልባት የምታያቸው ሰዎች ግልፅ ሆኖ ስለታየ ነው እንጂ እኛም የራሳችን ብዙ ወንጀሎች ይኖሩብናል
የራሳችን ድክመቶች ይኖሩብናል
የራሳችን ስንፍና ይኖሩብናል

ስለዚህ mature እያደረግን ስኔድ ሰዎችን መገመት እናቆማለን ።
የወደቁ ሰዎች እንደሚነሱ ይገባናል
የተነሱ ሰዎች ደሞ ሊወድቁ እንደሚችሉ ይገባናል

ወንጀል የሚሰሩ ሰዎች ተውበት ሊያደርጉ እንደሚችሉና ወደአላህ እንደሚመለሱ ይገባናል

ህይወት ያስተምረናል
ዛሬ ጥሩ የሆኑ ሰዎችም ነገ መንገድ ሊስቱ እንደሚችሉ ይገናባል

ስለዚህ ሰዎችን መመዘን judge ማድረግ በመጥፎ ማየት እያቆምን እንሄዳለን ።😊

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

06 Nov, 18:09


በፀጋዎችህ ታግዘን ፣እዝነትህን ተማምነን ስለተዳፈርናቸው ወንጀሎች ሁሉ ይቅር በለን
ያረብ

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

06 Nov, 18:06


ለችግሮቻችን side effect የሌለው መድሀኒት ዱዓ ነው። አላህዬ የሁላችንንም ልብ ለዱዓ ይክፈትልን ።

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

06 Nov, 04:40


📍በቀን ክፈለ ጊዜ ላይ የሚተኙ ሶስት የእንቅልፍ አይነቶች አሉ እነሱም
(ሀይሉላ ፣ ቀይሉላ እና ዐይሉላ) ይባላሉ።

1 ሀይሉላ / حيلولة
ጠዋት ከፈጅር ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ ።
الحيلولة : هي النوم بعد صلاة الفجر وهي تحول بينك وبين رزقك.
📌 በሰዉዬዉ እና በርዝቁ መሀል መጋረጃ/ግርዶሽ ትሆናለች ፣ ዱኒያዊም ሆነ አኺራዊ ብዙ ማግኘት እና ማትረፍ የሚችል ነገር ታስመልጠዋለች ።
📌ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂወሰለም) አላህ ለህዝባቸዉ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ዉስጥ በረካ እንዲያደርግላቸዉ ዱዓ አድርገዋል ፣ ሁሌ በዚህ ሰዓት የሚተኛ ሰዉ ይሄ ዱዓም እንዳመለጠዉ ነዉ።

2 ቀይሉላ / قيلولة
ከዱሃ ሶላት ቦሃላ ወይም ከ ዙህር ሶላት ቦሃላ ለተወሰነ ደቂቃ ጋደም የምትባል እንቅልፍ ናት።

القيلولة : هي النوم بعد صلاة الضحى او بعد صلاة الظهر لمدة 30 دقيقه وهي مفيدة للصحة الجسم للتقوية على العبادة.
📌ለአካል ጤና እጅግ በጣም ጣቃሚ ነዉ።
📌ኢባዳ ላይ ኢንዲያጠናክረዉ ነይቶ የተኛ ሰዉ አጅር ያገኝበታል ።
📌ሶሃባዎች እና በርካታ አኢማዎች ይተኟት ነበረ።

3 ዐይሉላ /عيلولة
ከ አሱር ሶላት ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ።
العيلولة: هي النوم بعد صلاة العصر وهي تسبب علة للجسم والنفس وضيق لصدر.
📌በዚህ ጊዜ መተኛት የተከለከለ መሆኑ እና እጅግ በጣም የጠላ መሆኑን በሰሂህ ሀዲስ ተዘግበዋል ፣ የሚያስተኛዉ በቂ የሆነ ምክንያት/ዑዝር ከሌለዉ በቀር ።
📌በጤናችንም ላይ ለበሽታ ሰዉን ያጋልጣል
📌ለጭንቀት እና የሀሳብ ጥበት ላይ ሰዉን ይጥላል።

እኔ ከ10 አመት በላይ ቀይሉላ የመተኛት ልምድ አለኝ 😁ብዙ ነገርም አትርፌበታለሁኝ።

እናንተስ በዬትኛዉ ሰዐት ላይ የመተኛት ልምድ ነዉ ያላችሁ? ምን ምንስ ታዝባቹሃል?

©Muaz shamsu

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

01 Nov, 03:30


አላህ ሆይ!
በጁመዓ ቀን...


ለታመመ ሁሉ አፊያን
ለሞተ ሁሉ እዝነትን
ልባችንን ምራልን
ጉዳያችንን ሙላልን
ይህንንም ጁመዓ ለታገሰ ሁሉ ደስታን

ለሁሉም ዱዓ ተቀባይነትን ያረበል ዓለሚን

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

31 Oct, 16:16


#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

የቀጋውን ጢሻ ሁቡ መነጠረው!

ለእስልምና የነበረው ጥላቻ የገነገነ ነው። ነቢን ለመግደልም ይቋምጥ ነበር። አንድ ጊዜ ምንም ሳያመነታ አንገታቸውን ለመቅላት ሰይፉን ሞርዶ የመካን ቁልቁለት ይንደረደር ጀመር። መካ ውስጥ በድብቅ ሰልሞ የነበረ አንድ ወጣት ሁኔታውን ይከታተል ነበርና ነገሩ አላምር ቢለው ተከተለው። ተወዳጁ ነብይ አደጋ ውስጥ መሆናቸው ተሰማው። ለነፍሱ ሳይሳሳ ወደ አይደፈሬው ሰው ጋለበ። ደርሶ እሳት የሚተፉትን ዓይኖቹን ቢያይ ተሸበረ። ደፈር ብሎ ግስጋሴው ወዴት እንደሆነ ጠየቀው። "የሕዝባችንን አንድነት የበተነውን፣ አማልክቶቻችንን ያጠለሸውንና እኛን ያሞኘንን ሰው ልገድል ነው የምሄደው።" አለው። ወጣቱ ይህን ሲሰማ የፈራው ሊደርስ መሆኑ ገባው። ጭንቀቱ አየለ። በወሬ ሊይዘው ቢሞክርም አልተሳካለትም። ያ ሃይለኛ ሰው መላ አካሉ በንዴት እየተንቀለቀለ ነበር። በመጨረሻም ወጣቱ አፉ ያመጣለትን አንድ ቃል በደመነፍስ ወረወረ። እየተርበተበተ "ለምን ከራስህ ቤት አትጀመርም?" አለው። ሰውዬው ለአፍታ ቆም አለና "ከቤትህ ጀምር ስትል ምን ማለትህ ነው?" ብሎ ጠየቀው። ለካስ የዚህ ሰው ተወዳጅ እህትና ባለቤቷ በሚስጥር እስልምናን ተቀብለው ኖሯል። ወጣቱ የውዱን ነብይ ህይወት ለማትረፍ ሲል የጥንዶቹን ሚስጥር ይፋ አወጣው።
ጋላቢው ከመቅፅበት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ እህቱ ቤት እንደ አቦሸማኔ ተፈተለከ። ወደ ቤታቸው ሲቃረብ የቁርአን ድምፅ ይሰማ ነበር። በሩን በሃይል አንኳኳ። ውስጥ የነበሩት ሰዎች በድንጋጤ ቁርአኑን ለመደበቅ ተራወጡ። ግና እስኪከፈትለትም አልታገሰም። ቀድሞ ገብቶ የሰማውን ድምፅ ምንነት ጠየቀ። እህቱ ፈጠን ብላ "ኧረ ምንም አይደለም ስናወራ ሰምተህ ነው!" አለች። እሱ ግን ድምፁ የቁርአን መሆኑን አውቋል። "ሙስሊም ሆናችሁን?" አለ። ባለቤቷ ወደፊት ራመድ አለና "አዎን እስልምናን ተቀብለናል!" ብሎ በድፍረት አረጋገጠለት። ይሄኔ በቡጢ ነርቶ መሬት ላይ ዘረረው። ባለቤቱ ልትከላከልለት ስትሞክር እሷንም ደሟ እስኪፈስ በጥፊ አላጋት።

እህቱ የወንድሟ ቢጤ ናት። እሱ ይታወቅበት የነበረው ሃይለኝነትና ጥንካሬ ተችሯታል። ተነሳችና የተቆጣ ወንድሟ ፊት ለፊት ቆማ "አንተ የአላህ ጠላት! በአላህ ስላመንኩኝ ብቻ ልትመታኝ ትችላለህ። ግን ወደድክም ጠላህም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም መልእክተኛው እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ያሻህን አድርግ።" አለች ፈርጠም ባለ አንደበት። ይሄኔ ከእህቱ ፊት ደም እየፈሰሰ መሆኑን አስተዋለ። ንግግሯም በጆሮው ውስጥ አቃጨለበት። ቀስ ብሎ ቆመ። ወደ ቤታቸው ሲቃረብ የሰማውን የቁርአን ድምፅ ዳግም መስማት ፈለገና እንዲያነቡለት ጠየቀ። "ጧሃ ማአንዘልና ዓለይከል ቁርአነ ሊተሽቃ ኢልላ ተዝኪረተን ሊመን የኽሻ…ቁርአንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ ይሆን ዘንድ እንጂ!" ይላል። እሳት ያመነጩ የነበሩ ዓይኖቹ እንባ አዘሉ። "ይሄንን ነው ልናጠፋ ስናሳድድ የነበርነው? የዚህ ንግግር ባለቤት ሊመለክ ይገባዋል።" እያለ ብቻውን አወራ። ያ ሰው ጀብደኛው፣ ሞገሱ የሚያስፈራው፣ ግርማው ሰውን ቀርቶ ሰይጣንን የሚያርበደብደው፣ ቁረይሽ የሚመካበት፣ የወንዶቹ መስፈሪያ፣ የጀግኖቹ ቁና ዑመር ኢብኑልኸጧብ ረ.ዓ ነበር። ወዲያው ከእህቱ ቤት ወጥቶ ወደ ረሱሉሏህ አቀና። እዛ ሲደርስ ባልደረቦቻቸው ነቢን ሊተናኮል መስሏቸው ፈሩ። እርሳቸው ተቀበሉትና "የኸጧብ ልጅ ሆይ ምን አመጣህ?" አሉት። በትህትናና በደስታ ዓይን ዓይናቸውን እያዬ "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እዚህ የመጣሁት በአላህና በመልዕክተኛው ማመኔን ላሳውቅ ነው።" አለ። የኔ ነቢ እጅግ ተደሰቱ። "አላህ ታላቅ ነው!" እያሉም ያለቅሱ ጀመር። ከሁለቱ ዑመሮች በአንዱ እስልምናን እንዲያበረታ የለመኑትን ልመና ጌታቸው ሰማ።

ሁለቱ ዑመሮች…!

የሚታወቀው ዑመር በሚለው ስሙ ባይሆንም ከዑመር ኢብኑልኸጧብ ሌላ አንድ አስፈሪ ሰው ነበር። ይህ ሰው በመሰረቱ አቡልሐኪም ወይም የጥበብ አባት እየተባለ ይጠራ የነበረ ታሪክ ግን አቡጀህል ወይም የድንቁርና አባት ብሎ የሚያወሳውና ቀንደኛው የኢስላም ጠላት አምር ኢብን ሂሻም ነው። ታድያ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በአንድ ወቅት ነቢ አላህ ከሁለቱ ዑመሮች እርሱ ዘንድ ተወዳጅ በሆነው ኢስላምን እንዲያበረታ ተማፅነዋል። ለኢስላም ጠላቶችም ሆነ ለነቢ ባልደረቦች የዑመር ኢብኑልኸጧብ እስልምናን መቀበል ፈፅሞ የማይታሰብ ነበር። ለነቢ መሻት ሲባል ግን አይሆንም የተባለው ሆነ።
ሰይዱና ዑመር እስልምናን በተቀበሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ የቁረይሾችን በትር ፈርተው ጌታቸውን በድብቅ ይገዙ የነበሩትን ሙስሊሞች በግልፅ ወደ ካዕባ ወሰዷቸው። ጭቁኖቹ አንገታቸውን ቀና አደረጉ። ማን ወንድ ነኝ ያለ ሊነካቸው?! በዚህ ጊዜ ነው ሰይዳችን ኢብኑልኸጧብን "ዑመሩል ፋሩቅ" ብለው የሰየሟቸው። የውሸትን ጭለማ በእውነት ወጋገን የገፈፈ ጀግና።
ከብረት የጠነከረው ጥላቻ በነቢ ፍቅር ቀለጠ፣ ነቢን እገድላለሁ ሲል እንዳልነበር ህይወትና ሞቱ ለአላህና ለነቢ ሆነ። ይኸው ነው በቃ የወለላው ነቢ ኸበር የቀልብን ጉንጉን ይፈታል፣ ዳገቱን ሜዳ፣ ነጅሱን ጡሃራ፣ መርዙን ፈውስ፣ ዑመርን እንዳደረገው ጀግናውን አልቃሻ፣ ሴቱን ሪጃል ያደርጋል።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

29 Oct, 05:29


ሁላችንም በልጅነታችን የሆነ ማንነት አለን አደል ነበር ሆኖ የቀረ።
ለአላህ ቅርብ የነበረ
ለመስጂድ አገልግሎት ቅርብ የነበረ እኮ የሆነ ማንነት ነበረን።

በቃ እንመለስ
ሁሌም ሚፈልገንን አላህ እኛም እንፈልገው

ያ ልጅነታችንን እንመልሰው
በጣም እንደሚከብድ አቃለው
ማታ የማይሆን ወንጀል እየሰራን ጠዋት ለዱዓ እጅን መዘርጋት እኮ በጣም ከባድ ነው።
ሼም የሚያሲዝ ነገር ነው። አይናችንን በጨው አጥበን ምንም እንዳላደረገ ሰው አላህ ፊት መቅረብ በጣም ከባድ ነው።

ግን ወደ ተውበት ሊመራን ሊመልሰን የሚችለውን ነገር ዱዓና ዱዓ ነው።
ወደ አላህ መቅረብ ብቻ ነው።
ስለዚህ የአላህ ማህርታነት ማመን መቻል አለብን።
በአላህ መሀሪነት
በአላህ ይቅር ባይነት እርግጠኛ መሆን አለብን ከልባችን ።
አላህ አለማድረግ የሚችለው እኛን አለመማር ነው ይቅር ባይ ጌታ ነው ያለን።

እንመለስ ወደ አላህ 😊

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

27 Oct, 05:31


በአንድ ጊዜ አራት የጣት ቀለበት አጠለቀላትና አንች አራቱም ነሽ አላት።😁

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

25 Oct, 16:51


#ፍቅር ምንድነው ብለው ጠየቁኝ ?
#መልስ :-የምትወደውን ነገር ለምትወደው ሰው መመኘት።

       
#ጀነትን ወድጄ ተመኘሁላችሁ..
🥰 ከወደዳችሁኝ የምትወዱትን ተመኙልኝ
😊

መልካም ውሎ 😍
@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

24 Oct, 17:59


" እወቅ .. በሠይደልዉጁድ ﷺ ነብይነት ማመንን  ሙሉ ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አሏህ የተከበረው ሰውነታቸውን  ከሳቸው በፊትም ይሁን ከሳቸው ቡኃላ እንደሳቸው አይነት አካል በሌለ መልኩ እንደፈጠራቸው ማመን ነው .."

🦋ኢማም አልቁስጡላኒይ🩵

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

24 Oct, 17:14


Islamic Post🕋 pinned «ምሽቱ ኸሚስ ለሊቱ ጁምዓ 🥰 ......... እስቲ በሰለዋት እናድምቀው😍😍 ....... 🍁ሰሉ ዓለ ነብይ ❤️🥰 .......... ﺍﻟﻠَّﻬﻢَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى سَيِّدَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻮْلَانَا مُحَمَّد ، وَ عَلَى آلِ سَيِّدَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻮْلَانَا مُحَمَّد ، بِعَدَدِ كُلِّ زَرَّةٍ أَلْفَ أَلْف مرَّ❤️❤️ @Solualenebiiy…»

Islamic Post🕋

24 Oct, 17:00


ምሽቱ ኸሚስ ለሊቱ ጁምዓ 🥰
.........
እስቲ በሰለዋት እናድምቀው😍😍
.......
🍁ሰሉ ዓለ ነብይ ❤️🥰
..........
ﺍﻟﻠَّﻬﻢَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى سَيِّدَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻮْلَانَا مُحَمَّد ، وَ عَلَى آلِ سَيِّدَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻮْلَانَا مُحَمَّد ، بِعَدَدِ كُلِّ زَرَّةٍ أَلْفَ أَلْف مرَّ❤️❤️

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

Islamic Post🕋

24 Oct, 02:20


ለፈጅር ሶላት ይቀሰቅሳት ነበር
አንዳንዴ ስትሳነፍ እየቀለደ
በጀነት በደረጃ እበልጥሻለሁ ከዛ አብረን አንሆንም!
#ሰላተል_ፈጅርአህባቢ

@Solualenebiiy || ★Islamic Post★

7,659

subscribers

192

photos

45

videos