➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺 @umureslan_aselefiya Channel on Telegram

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

@umureslan_aselefiya


👑👑👑👑👑👑
🎀ሰለፍያ እንስቶች፣
🎀የሀያዕ ንግስቶች፣
🎀እጅግ በጣም ውዶች
🎀በሂጃብ ጥብቆች።
ውዷ እህቴ ሆይ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ ።🎁
እርምት ካሎት
@talibetul3ilm
@umu_reslan_aselefiya

የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺 (Amharic)

ለምንለአንድ ቻናል እና ሜዳላዊ የሆነ እና የሚስጡ ሰለፍያ እንስቶች ቻናል ነው። ይህ ቻናል ስለ ሀያዕ ንግስቶችን እና እጅግ በጣም ውዶችን እንዴት መጨመረውን ታወከዋላችሁ። ለምሳሌ በእህቴ ሆይ ስለ ሂጃብ ጥብቆች በመረጃው እንገኝታለን። ለምሳሌ ስለ እርምት ካሎት የሚመለከቱ ጥቁር እና ሀኪሳ ሰውን መለሰኛው በበለጠ እንዴት በትንሽ እንሰልታለን። ስለዚህ ቻናልም እንደተለቀቀው ሌሎች ቻናሎች የተለያዩ አይደሉም። እኔም በተለይ እናሳት።

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

29 Oct, 22:37


Dinar Graphic Design ነፃ የትምህርት እድል ለማግኘት እየተወዳደርኩ ስለሆነ እባክዎ ይህን ሊንክ

➡️ https://t.me/+6cXAI_6MEIAzNGRk በመክፈት ቻናሉን ይቀላቀሉት።

ጀዛኩሙላህ ኸይር

~~~~

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

29 Oct, 22:35


➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺 pinned «📌«ደስ የሚል እንቅልፍ ለመተኛት በትንሹ ሞት ለመርካት አልጋንና ትራስህን እንደምታመቻቸው በትልቁ ሞትም እንድትረካና እንድትደሰት ከወንጀል ታቀብ ፣ ትእዛዞችን ተግብር  ከመተኛትህ በፊት ወደ አላህ ተመለስ 🌸 ለነገህ ያማረ ህልም አዘጋጅ! መልካም ህልም ወደ መልካም መንገድ ይመራል!!»...✍️ https://t.me/UmuReslan_Aselefiya»

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

26 Sep, 18:02


ማስታወቂያ ለአዳማ ሰለፊዮች በሙሉ



እሁድ ቀን 19/1/2017 በአዳማ በሁሉም መድረሳ የምትገኙ ሰለፊዮች አንገብጋቢ ለሆነ ጉዳይ ስለፈለግናቹህ ሁለቹሁም በቀጥርናቹህ ሰዓት እንድትገኙ።

አስር ቀበሌም ያላቹህ፣ቦሌም ያላቹህ፣ግንብ መናሀሪያ አካባቢም ያላቹህ፣ቁዱስ ቁርኣን አካባቢም ያላቹህ፣ኢብን ተይሚያ መድረሳም ያላቹህ፣ሌሎችም ቦታዎች ላይ ያላቹህ ሁላቹሁም ተጠርታቹሃል።
ሴቶችንም ይጨምራል።


የፈለግናቹህ ለአንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ በፍፁም እንዳትቀሩ።

ቀጠሮን ማክበር የሙእሚን ባህሪ ነው፣ቀጠሮን ማፍረስ የንፍቅና ባህሪ ነው።

ቦታው ኢብን ተይሚያ መድረሳ

ሰዓት 8 ሰዓት

አዳማና አካባቢዋ አህለሱና ወልጀማዕ ማህበር


t.me/ibnawolllll

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

06 May, 09:38


ወንድሜ ሆይ! አብሽር 3

በዙሪህ ያሉ ሰዎች በድለውሃል? አብሽር ትዕግስት አድርግ ምናልባት እነሱ ሊጎዱህ አስበው ላይሆን ይችላል። ሊጉዱህ ቢሆንም በነሱ ❴ሊጎዱህ ባሱበት ሰዎች❵ የሚጠቅም ሀያልና ጥበበኛ የሆነው ጌታህ አለ። አንተ የሚጠበቅብህ ከፈጣሪህ በኩል ያለውን መስመርህን ማስተካከል ነው።

አዎ እርግጥ ነው ያመንከው ወንድምህ፣ ሚስጥርህን ያካፈልከው አጋርህ፣ ተስፋ ያደረክበት ጓደኛህ ከምታስበው ተቃራኒ ስታገኘው ውስጥህ ይረበሻል። ሰዎችን ለማመን ይከብድሃል! ነገር ግን በዚህ አይነት ጉዳይ አትረበሽ!

ሲቀጥል ሊጎዱህ የሚፈልጉ ሰዎች በዙሪህ ካሉ የጓደኛ ምርጫህ ላይ ክፍተት አለ ማለት ነው። የውዱ ነብይህን ምሳሌያዊ ምክር አላስተዋልክምን? ቡኻሪና ሙስሊም የሚከተለውን ሐዲስ ዘግበዋል፡-
عَنْ أَبِي مُوسَى رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: ((مَثَلُ الْجَلِيسِ الصَّالِحِ وَالسَّوْءِ كَحَامِلِ الْمِسْكِ وَنَافِخِ الْكِيرِ، فَحَامِلُ الْمِسْكِ إِمَّا أَنْ يُحْذِيَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَبْتَاعَ مِنْهُ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ مِنْهُ رِيحًا طَيِّبَةً، وَنَافِخُ الْكِيرِ إِمَّا أَنْ يُحْرِقَ ثِيَابَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ رِيحًا خَبِيثَةً)

“የመልካም አቀማማጭና የመጥፎ አቀማማጭ ምሳሌው ልክ ሽቶ እንደያዘና ወናፍ እንደሚነፋ ሰው ቢጤ ናቸው፡፡ ሽቶ የያዘው ሰው ሊሰጥህ ይችላል ወይም ከእርሱ ልትገዛ ትችላለህ ወይም ጥሩ ሽታ ልታገኝ ትችላለህ፡፡ ወናፍ የሚነፋ ሰው ደግሞ አንድም ልብስህን ያቃጥላል፤ ወይም መጥፎ ሽታ ያጋጥምሃል፡፡”

ቡኻሪ ፡ 5534 ሙስሊም ፡ 2628

እናም ውድ ወንድሜ ወናፋ ነፊ መሳዮችን በዙሪያህ ሰብስበህ ልብስህ የተቃጠለ ያህል ቢጎዱህ፤ ወይም በመጥፎ ባህሪያቸው እና ስራቸው የሚሸት ❴የሚጎዳ❵ ድርጊት ቢፈፅሙብህ የውድ ነብይህን መልዕክት ዘንግተኛልና በጥፋትህ ስለሆነ ብዙ አትበሳጭ!!!

ተናካሾች ውድቀትህን ፈልገው ቢነክሱህ ምቀኞች ስኬትህን ጠልተው ቢመቀኙህ ቅናተኞች ብልፅግናህ አበሳጭቷቸው ቢያሰናክሉህ ከሙከራ ያለፈ ምንም ነጥብ አያመጡም። አዎ አንተን ለመጉዳት የአለም ህዝብ ቢንቀሳቀስ አይጎዳህም። ግን የአለምን ህዝብ የሚቆጣጠረውን ሀያል ጌታ ያዝ! ትክክለኛ ባሪያው ሁን ያኔ ማንም አይጎዳህም። አዛ ሊያደርጉህ ይችላሉ ትክክለኛ ጉዳትን ግን ማንም አያደርስብህም። አዛ ማድረጋቸው ደግሞ አጅርህን ከፍፍፍፍ የሚያደርግልህ ፀጋ ሊሆን ይችላል! አብሽር!

📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

ሀሳብ  ካለዎ 
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

23 Dec, 15:56


🟢ተጀምሯል

አሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሃዲይ አል_መድኸሊይ
አላህ ይጠብቃቸው።
 

🟢በቁርዓን እና በሱነህ(በሀዲስ) አንድ  ስለ መሇን
👇
https://t.me/almadkhalinet?livestream

ወይም
👇
https://t.me/almadkhaliweb?livestream

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

18 Dec, 16:40


እስከ 4 ማግባትን የሚከለክሉ ምዕራባዊያን ራሳቹዉ ግን በአማካኝ (በራሳቸው ምስክርነት) ከ4 እስከ 8 ከሚሆኑ ጋር ያማግጣሉ።

- «አንድ ሙስሊም የሆነ ሰዉ ከሁለት ሚስቶቹ ጋር እየሄደ የሆነ ቦታ ፖሊሶች ከአንድ ሚስት በላይ ይዞ መግባት አይፈቀድም ሲሉት፣ ሰዉዬዉም “ኣይ ሚስቶቼ ሳይሆኑ ሴት ፍቅረኞቼ ናቸዉ” ሲላቸዉ አሳለፉት» ተብሎና ፈረንጅ ሀገር የተከሰተ ነው ተብሎ የሚወራ ወሬ እንሰማለን። ታሪኩ በእውን የተከሰተ ባይሆን ራሱ ትርጉሙ ትክክለኛ ለመሆኑ ከላይ ያሰፈርኩት እዉነታ ያረጋግጣል።

- ሸይጧን አምላኪዎች የሰዉ ልጅ እንዲራባ አይፈልጉም። ከሃድያን ሙስሊሙ እንዲበዛ አይወዱም። ብዙዎቻችን በነሱ ወጥመድ ወድቀን ከአንድ በላይ ማግባት በዚህ ዘመን ጭራሽ የማይቻል ነዉ እያልን ነዉ። ሸሪዓዉ እኮ ከአንድ በላይ ማግባትን ሲፈቅድ ለእኛዉ ነዉ እንጂ መላእኮችን አይደለም።

- ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአንድ በላይ ማግባትን መላመድ አለበት። በተለይ የሱናው ማህበረሰብ እርስ በርሳችን መጋባት ነዉ እንጂ ለሌሎች አሳልፈን አንሰጣጥ!!!

https://t.me/Khedir_M_Abomsa/3102

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

11 Dec, 18:28


የአላህ ባሮች ሙስሊም ሰለፍዮች ሆይ ሚዲያ ላይ ዑለሞቻችሁን በጋጠ-ወጦች አታሳድቡ!!

እንደሚታወቀው ከአሁን በፊት የተምይዕ በሽታ የወረራቸው ሚዲያ ያገነናቸው ሰዎች ዘደ እያፈላለጉ የቢድዓ ባለቤቶችን እያጠናከሩ በእድሜ የበሰሉ ናቸው እያሉና ቀን ከሌት በስውር ዘደ ለነሱ እየደከሙ .  .  .
.  .  .
ለዲን ለሱና በመልፋት እድሜያቸውን የጨረሱ የሱና ዑለሞችን ደግሞ የእንጨት ሸበት በእድሜያቸው ልክ የማያስቡ እብድ ውሻ እያሉ ሲሳደቡ የታዘብነው ነው። በመሆኑም ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ እስከ አሁንም ድረስ በዚያ መጥፎ ስምሪት የተመረዙ አላዋቂ ጭፍን ተከታይ ከንቱዎች የሱና መሻይኾችን በእድሜያቸውና በሽበታቸው ሲጽዳዱ እየተመለከትን ነው።

ሰለሆነም እናንተ እነዚህ ባሉበት ሰፈር እየሄዳችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጋቸው ትልልቅ የሱና መሻይኾችንም ከማሰደብ የሙመይዓ አካሄድ ምን እንደሆነ በእነዚሁ በሱና ዑለሞች የተብራራውን ሼር ማድረግ ነው የሚጠበቅባችሁ!!

ኢስላምን እየገደሉ ስለ ኢስላም ቢያወሩ፤ የነብያችንን ሱና እያደበዘዙ የሳቸውን ሀዲስ እናስተላልፋል ቢሉ፤ የደጋግ ቀደምቶችን የነ ኢብኑ ተይምያህን ያን ሁሉ የደከሙለትን በእጅ አዙር እያስመቱ ስለነ ሸይኽ ኢስላም ኢብኑ ተይምያህን የሚደግፉና ለነሱ የሚቆረቆሩ መስለው ቢጽፉ፤ አላዋቂ ሞኛ ሞኝን ብቻ ነው የሚሸውዱት።
ሥለዚህ አሁንም የምንላቸው የሚያዋጣው ነገር ከሁሉም በፊት ሰው የሚሰበሰብበትን ዘደ እያጠኑ ያን ማድረግ ሳይሆን፤ አላህ በሚወደው ያቀዘቀዙትን ያበላሹትን ያደበዘዙትን ማስተካከል ያሳሳቱትን ያጃጃሉትን ህዝብ መጀመሪያ ራሳቸው ተፀጽተው መመለስ ነው።

እኔ በበኩሌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ እያየሁ የግድ እየቻልኩ የማልፋቸው አሳዛኝ ነገሮች በርካቶች ናቸው። ሆኖም ግን እንደ አስፈላጊነቱ ሀቅ ፈላጊ የሆነን ሙስሊም ማህበረሰብ መታደግ ስለሚያስፈልግ ዝቅ ከፍ እያደረግን ሀቅ ለህዝብ ማድረሰ ይጠበቅብናል ብለን ስለምናስብ በተሻለ መልኩ እንቀጥላል።

በመሆኑም ከስር መሰረቱ ሱናን እንዲንገነዘብና የፈለገ በንግግራቸው ቢንቀለቀሉ እንዲሁም አበጃጅተው ቢፆፉምኳ የዲን የሱና ገዳዮች እነማን እንደሆኑ በእውቀት በመረጃ ላይ ሆነን እንዲናውቀውና እንዲንረጋገጥ በአላህ ፈቃድ እንደሚከተለው የሀገራችን ትልልቅ መሻይኾችን በቂና ጠቃሚ ትምህሮቶች የማያያይዝላችሁ ይሆናል ቻናሉን ተቀላቀሉ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6298
.

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

11 Dec, 02:28


°°

صلاة الفجر كانت يومًا
على المنافقين دليلاً

إنها عبادة الصادقين ،
وسبيل المؤمنين ،

وطريق المخلِصين .

🌿 #صلاة_الفجر

°°

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

09 Dec, 15:49


🚫   የሺዓዎች ሐሰንን ትተው ሑሰይንን የመውደድ ሚስጢር

    ሺዓዎች ( ኢራኖች )  ለምንድነው ከዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ልጆች ውስጥ ሑሴንን ብቻ ለይተው በመውደድ ስም የሚያመልኩት ?
ይህ ብቻ አይደለም 12 የሺዓ መሪዎች የሑሰይን ዘሮች መሆናቸውንስ ያውቃሉን ?
    የዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ልጆችስ 11 መሆናቸውንስ ያውቃሉን ? እንግዲያውስ መጀመሪያ የሑሰይን የእናትና የአባት ወንድሞቹን እንወቅ ።
    ➡️   እነርሱም የሚከተሉት ናቸው : –

1– ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ
2 – ሐሰን         "  "            "  "
3 – ሙሕሲን    "   "            "  "
4 – አል ዐባስ    "   "            "  "
5 – ሂላል           "   "            "  "
6 – ዐብዱላህ     "   "            "   "
7 – ጀዕፈር          "   "           "    "
8 – ዑስማን         "   "           "    "
9 – ዑበይዱላህ    "   "           "     "
10 – አቡ በከር      "   "          "     "
11 –ዑመር            "   "          "     "
    እነዚህ ሁሉ የዐልይና የፋጢማ ልጆች ናቸው ። የነብዩ ቤተሰብ ( አህሉል በይት) ናቸው ። እሺ በሺዓዎች ባንዲራ ላይ ያ ሐሰን ፣ ያ ሙሕሲን ፣ ያ ዐባስ የሚል ተፅፎ አይታችሇልን ?
መልሱ አላየንም ነው ። ታዲያ ለምንድነው ያ ሑሰይን የሚል የተፃፈበት ? 
   🔹 አስገራሚው መልስ : –
  በዑመር ዘመነመንግስት ከፋርስ ጋር በተደረገው ጦርነት ሙስሊሞች አሸንፈው የኪስራን ንጉስ ገለው የተሸነፉትን ይማርካሉ ። ከሙርከኞቹ ውስጥ የዝደጅረድ የተባለው ንጉሳቸው ሴት ልጅ ሸህርባኑ የተባለች ልጅ ነበረች ።
    እቺን ልጅ ዑመር ለሑሰይን ይሰጡትና ያገባታል ። ከሷም ልጆች ይወልዳል ። እንግዲህ ሺዓዎች ( ኢራኖች) ሑሰይን አማቻቸው ነው ። የንጉሳቸውን ልጅ ያገባ በመሆኑ ነው በመውደድ ስም የሚያመልኩት ።
   እንግዲህ ሺዓዎች የነብዩን ቤተሰብ ሳይሆን የሚወዱት የንጉሳቸውን ቤተሰብ ፋርሳዊያንን ነው ። ነገር ግን ሙስሊሞችን ለመሸንገል የነብዩ ቤተሰቦችን እንወዳለን ይላሉ ።
በጣም የሚገርመው የሑሰይን ከርበላእ ላይ መገደል ዋናው ተጠያቂ ሺዐዎች ናቸው ። ራሳቸው ገለው ራሳቸው ያለቅሳሉ አላህ ይግደላቸውና ። ታዲያ ሺዓዎች ስለሚወዱት ነው እንዴ ጠርተው ያስገደሉት አይደለም ነገር ግን የፋርሳዊያን ዘር ካስገኘላቸው በኋላ የነብዩ ዘር ስለማይፈልጉ ነው ያስገደሉት ። ይህ ነው የሺዓዎች እውነታ ልብ ያለው ልብ ይበል ።

ፅንሰ ሐሳቡ ከሸይኽ ሙሐመድ ባዝሞል የዐረቢኛ ፅሑፍ የተወሰደ ነው ።

https://t.me/bahruteka

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

09 Dec, 06:47


   የሙኻሊፎችን ትምህርት አትስሙ የሚባለው ለምንድነው ? 

     እንደሚታወቀው የቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶች ( ሰለፎች ) በሙኻሊፎች ላይ የነበራቸው አቋም ጤነኛ ልብ ላላቸው የሱና ሰዎች ግልፅ ነው ።
   የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጥቅሉ ከቢዳዓ በየሳምንቱ ጁሙዓ ፊታቸው ተቀያይሮ ፣ አይናቸው ቀልቶ ፣ ድምፃቸው ጠላት ሊወረው የመጣን ሰራዊት እንደሚያስጠነቅቅ መሪ ከፍ ብሎ ያስጠነቅቁ ነበር ። ከአንጃ ከኸዋሪጆች አስጠንቅቀዋል ። እንዲሁም ከዙል ኹወይስራ በነጠላ ደረጃ አስጠንቅቀዋል ።
ሶሓቦች የሳቸውን ፈለግ ተከትለው ከአንጃ ከቀደሪዮች ፣ ከራፊዳዎች ፣ ከሐሩርዮችና ከሌሎችም እንዲሁም በነጠላ ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አስጠንቅቀዋል ።
    የነብዩንና የባልደረቦቻቸውን ፈለግ የተከተሉት የሰለፍ ዑለሞች በአንጃ ደረጃ ከሙዕተዚላዎች ፣ ከሱፍዮች ፣ ከጀህምዮች ፣ ከሙርጂኣዎች ፣ ከአሻዒራዎችና ከመሳሰሉት ሲያስጠነቅቁ በነጠላ ደግሞ ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ግለሰቦች አስጠንቅቀዋል ።
    የሰለፎችን ፋና የተከተሉት የሱና ዑለሞችም ከቀደምትና በኋላ ከመጡት እንደ ተብሊጝ ፣ ኢኽዋንና ሙመዪዓዎች አስጠንቅቀዋል ።
    ከዚህ መሰረት በመነሳት የሱና ሰዎች የሰለፎችን መንገድ የተቃረኑ አንጃዎች ውስጥ የተካተቱ ግለሰቦችን ኪታብ ( መፅሐፍ )ን ማንበብም ይሁን ትምህርታቸውን መከታተል ይከለክላሉ ።
    🔹 ለምንድነው የሚከለከለው ሰው ሰምቶ ወይንም አንብቦ መጥፎዉን ትቶ ጥሩዉን አይዝም እንዴ ለምን እንደፈረስ ጋሪ ግራና ቀኝ አትይ አንድ አቅጣጫ ብቻ እይ ይባላል የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ  ። ይህ ጥያቄ በተለይ ከኢኽዋኖች በኩል በሰፊው የሚሰራጭ ሲሆን አላማው በአመክንዮ ሰዎችን ለማሳመን እንዲመቻቸው ነው ። 

    ➡️  የዚህ ጥያቄ መልስ ብዙ ቢሆንም ዋነኛው ግን እነዚህ አካላት ሙስሊሞችን ከትክክለኛው የእስልምና አስተምሮ አስወጥተው ወደ ፍልስፍና በማስገባት ከነብዩና ከሶሓቦች መንገድ እንዲያፈነግጡ ስለሚያደርጉ ነው ።
    ይህን የሚያደርጉት የሙስሊሙን ልብ በሲራና በፈዳኢለል አዕማል በመያዝ ነው ። የዚህን ጊዜ ሰሚው ልብ ውስጥ ስለሚገቡና ከዛ በኋላ ያ ሰው ተው አትስማ ሲባል ስለወደደው አልቀበልህም ስለሚል ነው ።
ለዚህ ምሳሌ : –

    ሀገራችን ውስጥ የኢኽዋን መሪዎች በተለያየ ረቃኢቅ ህዝቡን ከያዙት በኋላና እንደወደዳቸው ሲያውቁ ዒሳ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው አሉ ተከታዩ ምንም አልመሰለውም ።
ኢትዮዽያ ውስጥ ሁሉም አህሉሱና ነው አሉ
ቀጠለ : – እኛ ሱፍዮች ነን አሉ
አሁንም በዚህ አላቆመም የኢስላም ዋናው ክፍል ፖለቲካ ነው አሉ
አልሰማሁም አላየሁም ሆነ ። አሁንም ቀጠለ አሽዓሪያን አህሉሱና እንበል !!! ሱፍያን ነፍስን ማጥራት ነው እንበል ወጣቱ የሚቀበለው እንዲ ስንል ነው አሉ
   በዚህ ጊዜ ሁሉ ምላሽ እየተሰጠ ወጣቱ  ከእነዚህ የጥፋት አንጃዎች አልላቀቅም ያለው የሰዎቹን የመጀመሪያ የማጥመቂያ ትምህርት በመስማቱና እነርሱን በመውደዱ ነው ።
    የድሮዎቹ ሙመዪዓዎችና የአሁኖቹ ኢኽዋን የመርከዙ ሰዎችንም ሆነ የእነርሱ እንባ ጠባቂ አዲሶቹ ሙመዪዓዎችም ወጣቱ አለቅም ያለበት ምክንያትም ተመሳሳይ ነው ።
     ይህ ከመሆኑ ጋር ብዙ ሰለፍዮች አሁንም የኢኽዋንና ሙመዪዓዎች ቻናሎችን ለቀው መውጣት ከብዷቸው እያነበቡና እየሰሙ ይገኛሉ አብዛኛዎች ከመረባቸው መግባታቸው አይቀርም ። የሰለፎችን መርህ ያልተከተለ መፈተኑ አይቀርምና ።
    
https://t.me/bahruteka

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

04 Dec, 08:36


👉 የጡት ካንሰር ወረርሽኝ

➪ ውድ እህቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በገጠርም በከተማም በአሁኑ ጊዜ የጡት ካንሰር በሚገርም መልኩ እየበዛ ነው። አንዳንድ እህቶች ዝም ብሎ ማሳከክ ነበር ይላሉ። ሌሎች አልፎ አልፎ ይወጋኝ ነበር ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ይላሉ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞች እያመመኝም ሐኪም ቤት መሄጃ ስላልነበረኝ ዝም ብዬው ነው ይላሉ። በዚህ መልኩ ቀላል ነው እያሉ ይቆዩና መጨረሻ ላይ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄዱ ካንሰር ሆኗል ይባላሉ።

♻️ የዚህን ጊዜ ቀኑ ይጨልምባቸዋል። አብዛኞቹ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ሞታቸውን መጣባበቅ ይጀምራሉ። በጣም ጥቂቶቹ በሕክምና ሰበብ ይድናሉ። ይህ በሽታ ካንሰር በሚሆን ጊዜ የብዙ ቤተሰብ ሰቀቀን ሆኖ ህፃናት እንዲበተኑ የሚያደርግ ስለሆነ እህቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ለእናቶች ግንዛቤ በመስጠት የጡት ህመም በሚኖር ጊዜ ወዲያው እንዲታዩና በጊዜው በሕክምና መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲያረጉ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለያየ የኑሮ ደረጃ ላይ ያላችሁ እህቶች በሽታው መፍትሄ የሌለው ደረጃ ላይ ደርሶ የትኛውም ዘመድ ምንም ቢያደርግ ሰበብ መሆን አቅቶት ሰቀቀን ውስጥ ከመግባቱ በፊት በጊዜ ሐኪም ቤት መታየት እንዳለባችሁ ለጓደኛም ለዘመድም ነግራችሁ መታየት ይኖርባችኋል።

ይህ በሽታ ካንሰር ሆኖባችሁ በጭንቅ ውስጥያላችሁ እህትና እናቶች የአላህን ውሳኔ በሶብር በመቀበል በሶላት፣ በዚክርና ኢስቲጝፋር መታገዝ አለባችሁ። ይህን ጭንቅ በሞት ትገላገሉታላችሁ በጣም አሳሳቢው የአኼራው ጭንቅ ነውና ከዛ ጭንቅ ለመውጣት ዛሬ ወደ አላህ ተመልሶ ራስን ማዘጋጀት ነው የሚያስፈልገው

አላህ ከዱንያውም ከአኼራውም ጭንቅ ይጠብቀን።

https://t.me/bahruteka

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

03 Dec, 12:00


የሀላባ ሰለፍዮች እንኳን ደስ አላችሁ!!!
➴➘➷➴➘➷
https://t.me/AbuImranAselefy/7600

ይህ የድሉ መጀመሪያ ነው። ፅኑ ታገሉ ወደ ተውሒድ መጣራት መብታችሁ ነው። ላሰሩዋችሁም ለተባበሩም ዱዓእ አድርጉላቸው አላህ ሂዳያ ሰጥቷቸው በተውሒን እንድንገናኝ ያድርገን። መስጂድ ቢወሰድ ሜዳ ላይ፣ መንገድ ላይ ፣ ዛፍ ስር ወደ ተውሒድ ተጣሩ። ወንድሞቻችን የሰለፎቻቸውን ፈለግ በተግባር አሳይተዋል። ወደኋላ ማለት የለም ወደፊት ነው። መቶ ጊዜ መታሰር ለተውሒድ ያንሰዋል።
   
🎞 እነዚያ ብርቅዬ የኢስላም የበኩር ልጆች አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ደረታቸውን ለቀስትና ለጦር ሰጥተዋል። ይህ ለተውሒድ የተከፈለ ዋጋ ነው። በደማቸው ተውሒድ እንዲለመልም እንዲፈካ እንዲያብብ አድርገዋል። የኛ ከእነርሱ አንፃር ኢምንት ነው
   
🍭↪️ ሞዴሎቻችን
🌴አቡበከር ሲዲቅ፣
🌴ዑመር ኢብኑል ኸጧብ፣
🌴ኢማሙ ማሊክ፣
🌴ኢማሙ አሕመድ፣
🌴ኢብኑ ተይሚያ፣
🌴ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሀብ ናቸው። አሁንም ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለም። አብሽሩ ለተውሒድ መነሰር ሰበብ አላህ ያድርጋችሁ አላህ ሁላችንንም ሰባት ይስጠን።

📝 ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ

https://t.me/bahruteka


🏝 ሀላባ ሰለፊዮች 🔰
🔎🔎🔎🔍🔍🔍

🔦 የሀላባ ሰለፊ ወንድሞችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ኣግኝቻቸኃለሁ። ከሀዋሳ በቅርብ በመገኘቷ፣ ለፕራክቲስ ወደከምባታ ዱራሜ በሄድን ጊዜ ሀላባን ስለምንቋርጣት፣ እንዲሁም ለሀዋሳ ሪፈራል መስጂድ ለማስተባበር ወደሀላባ መመላለስና በዚሁ ምክንያቶችም የሀላባ ሰለፊ ወንድሞች ጋር መተዋወቅና መቀራረብ እድሉ ነበረኝ።

💻 ከዚህ ሁሉ በላጩ ደግሞ
📷 በሼይኽ አብዱልሀሚድ ለተሚ (ሀፊዘሁሏህ) መሪነት ከኢኽዋን ጋር የተካሄደዉ የሙናዘራ (የክርክር) መድረክ ልዩ ትውስታዬ ነች።

🌄 በዛ መድረክ በሀላባ የሀሰን አል በና ፍልፋዮች ምን ያህል መርዝን እንደቋጠሩና የሰለፊያን ደዕዋ ለመንቀፍ ያለባቸዉን አካሄድ፣ በዛ በበለጠ ልክ ደግሞ ሰለፊ ወንድሞች ያላቸዉ ፅኑ አቋምና ጀግንነት አይቼባቸዋለሁ። ልክ እንደጠበኩትም ከዛህን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ኢኽዋንም ሱናን እየነቀፈ፣ ሰለፊዉም እየታገለ ነዉ።

🔭 ሰሞኑን የእስርና የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲደረግባችሁ የነበራችሁ ሰለፍይ ወንድሞች እንኳን ከእስር ተፋታችሁልን፣ አልሀምዱልሏህ!!!

🖼 ሸይጧናዊ ሴራ ነቢያዊ ተልዕኮን ያሸነፈበት ታሪክ የለምና፣ ታሸንፉ ዘንድ ተዉሂድና ሱናን ይዛችሁ ወደፊት!!!

© ወንድማችሁ ዶ/ር ኸድር ሙሀመድ (አቦምሳ) ነኝ!

https://t.me/Khedir_M_Abomsa/3071

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

29 Nov, 02:01


በ2016 ምድባችሁ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-

    በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን ::

   በመቀጠል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ በታላቅ ደስታ ልነግራችሁ እወዳለሁ ::

   ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::
    

👌ፈድሉ ከድር ........0937240724(main campus )

👌መካሪም ሁሴን.........0936503106(main campus )

👌ነስረዲን ሙሐመድ ....ዐ961203437(main campus )

👌ሚስባህ  ናስር              .....ዐ931838227(main campus )

👌ቃሲም ሸሪፍ......0961860535(main campus )


የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (ጀምዓ)


https://t.me/WCUMSJ1

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

28 Nov, 15:38


حال السلف مع الطعام والشراب :

عن أبي جعفر رحمه الله قال:

إذا امتلأ البطن،

طغى الجسد.

📚موسوعة ابن أبي الدنيا 4/83

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

26 Nov, 10:41


📌«ደስ የሚል እንቅልፍ ለመተኛት በትንሹ ሞት ለመርካት አልጋንና ትራስህን እንደምታመቻቸው በትልቁ ሞትም እንድትረካና እንድትደሰት ከወንጀል ታቀብ ፣ ትእዛዞችን ተግብር  ከመተኛትህ በፊት ወደ አላህ ተመለስ 🌸 ለነገህ ያማረ ህልም አዘጋጅ! መልካም ህልም ወደ መልካም መንገድ ይመራል!!»...✍️

https://t.me/UmuReslan_Aselefiya

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

21 Nov, 15:04


የደላው  መች  ቀረ ......
ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ

ሁሉም  ይጓዛታል ያቺን  የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ


ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ
ይቸግራል  እንጂ  አላህ  ፊት ሲቆሙ

ዛሬማ  ምን  አለ  ቢጠጡ  ቢሰክሩ
ይቸግራል  እንጂ  ሙተው  ሲቀበሩ

ዛሬማ  ማን  አለ   የሚያጋልጥሽ
ከቀብር  ስትገቢ  ይታያል  ጉድሽን


🏝 ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (አላህ ይዘንላቸው)

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

21 Nov, 08:55


ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም
===========>


♻️ በእነሞር ወረዳ የፊታችን እሁድ 16/03/216 E.C ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅ ይጠብቃችኋል።

🪑 ተጋባዥ እንግዶች፦
🎙 ዶክተር ሑሴን ሙሐመድ
🎙 ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን
🎙 ኡስታዝ ባህሩ ተካ

🏝 አላህ ካለ ወደፊት የሰለፍያን ዳዕዋ ከሚረከቡ ተተኪዎች የተውሂድና የሱና ጮራ ሲፈነጥቅ ታያላችሁ!!!

https://t.me/bahruteka/4241

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

21 Nov, 08:55


የተፈጠርከለትን የአላህን ዲን ላለመማርህ አላህ ዘንድ ምክንያትህ ምንድነው...???
———
ታላቁ ዓሊም ዐብዱረህማን ቢን ናሲረሰዕዲ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
«እናንተ እውቀትን ከመፈለግ የራቃችሁ ሆይ! አላህ ዘንድ ምክንያታችሁ ምንድነው? አላህ ጤናን ሰጥቷችሁ እየተጠቃቀማችሁ እያለ። ከእውቀት ምንድነው የሚከለክላችሁ? እናንተ የጌታችሁን ሪዝቅ የምትመገቡ ሆናችሁ እያለ።
እናንተ እንደምትጓዝ እንስሳ መሆን ትፈልጋላችሁን? ልባችሁ ከናንተ ዝንጉና የዋለለች ሆነ ከቀናው መንገድ ስሜትን ትመርጣላችሁን?።
የመሀይማንን መንገድ ትመርጣላችሁን እሷ የዋላዮች መንገድ ሆነ ሳለ? ቀናውን መንገድ ትተዋላችሁ እሷ ግልፅና ጠቃሚ መንገድ ሆነ ሳለ?
ጌታህ ማነው? ሀይማኖትህ ምንድነው? ነቢይህ ማነው? ተብለህ ስትጠየቅ መልስ የማትሰጥ መሆንን ትፈልጋለህ?።
እንዴት ነው የምትሰግደው አላህን በምን መልኩ ነው የምታመልከው ስትባል ትክክለኛ ያልሆነን መልስ መመለስ ትፈልጋለህ??
አንተ ከሀራሙ ሀላሉን ለይተህ ያላወቅከ ሆነህ እንዴት ነው የምትሸጠው የምትገዛው የምትገባየው??
ወላሂ ይህቺን ሁኔታ የእንስሳ ብጤ የሆነ እንጂ አይወዳትም!!። አላህ ይዘንላችሁና የምትማሩ ሁኑ!። ባትማሩ እንኳን ትምህርት በሚሰጥበት ቦታ ሆናችሁ አድምጣችሁ የምትጠቀሙ ሁኑ!። መቃናትን ማወቅን የምትፈልጉ ስትሆኑ አዋቂዎችን ጠይቁ፣ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ከእውቀት ሙሉ በሙሉ ርቃችሁ ጠፍታችኋል ከከሳሪዎችም ሆናችኋል።
በእውቀት መጨናነቅ ከታላላቅ የአምልኮ አይነቶች መሆኑን፣ወደ አላህ ከሚቃረቡባቸው መልካም ስራዎች ሁሉ የላቀ እንደሆነ፣የምድርና የሰማይ ጌታ የሆነው አላህ ዘንድ መወደድን ግድ የሚያሰኝ እንደሆነ አላወቃችሁምን??
እውቀትን ፍለጋ የምትቀመጠው መቀመጥ በዱኒያና በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ ይበልጥልሃል፣ በእውቀት ቦታ ቁጭ ብለህ የምትጠቀመውን የሚመዝንና የሚወዳደረው ነገር ምንም የለም!።

እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! አላህን ፍሩ! የተፈጠራችሁለት በሆነው ነገር አላህን በማወቅና እሱንም በማምለክ ላይ ተጨናነቁ!፣ አላህን በእዝነቱ በእገዛው እንዲገጥማችሁ ጠይቁት!።
 
﴿أَمَّن هُوَ قانِتٌ آناءَ اللَّيلِ ساجِدًا وَقائِمًا يَحذَرُ الآخِرَةَ وَيَرجو رَحمَةَ رَبِّهِ قُل هَل يَستَوِي الَّذينَ يَعلَمونَ وَالَّذينَ لا يَعلَمونَ إِنَّما يَتَذَكَّرُ أُولُو الأَلباب} الزمر ٩

“እርሱ የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት የሚፈራ የጌታውን ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶች ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው  እንደ ተስፋ ቢሱ ከሀዲ ነውን? እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን? በላቸው። የሚገነዘቡት ባለ አዕምሮዎቹ ብቻ ናቸው።” አዝዙመር 9»
[ምንጭ:- አልፈዋኪህ አሽሸሒየህ ፊል ኹጠቢል ሚንበሪያ 66]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

18 Nov, 09:12


ሸይኽ ሙሳ አል ቀጧን በፊት
በፊት በሱሩሪዮች እንዳጠቃላይ በዶክተር ጀይላን ላይ በተለይ በሙመዪዓዎች ላይ ባጠቃላይ በመርከዙ ሰዎች ላይ በተለይ የተናገረውን ስሙ
በሐበሻ ምድር የሰለፍያ ዳዕዋ ጠላቶች ዶክተር ጀይላንና የመርከዙ ሰዎች ናቸው ይላል ። !!!!!
ይህን ሁሉ ሲል አቡ ሒዛም ( ዐ/ራሕማን) ከሚባለው ሰምቶ ነበር ። አሁን እሱ ሙመዪዓ ሆኖ ይዞት መጥቶ በተቃራኒው የገነባውን አፈረሰ
አላህ ፅናቱን ይስጠን ።

https://t.me/bahruteka

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

18 Nov, 09:12


"القُرآن الكَرِيم إن زِدتَ منهُ، زاد نصيبك من الأُجور".
أرح سمعك وقلبك 📜

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

17 Nov, 05:13


↩️ قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين

የአላህ መልዕክተኛ ነብያችን ﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ  መካከል ብርሃንን ያበራለታል።))

صحيح الجامع - رقم : (6470)

የጁመዕ ቀን ሱናዎች

↩️ ‏سنن يوم الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة

↪️ የጁምዓ ቀን ሱንናዎች
➊ መታጠብ
➋ ሽቶ መቀባት
➌ ሲዋክ መጠቀም
➍ ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ ሱረቱል ከህፍን መቅራት
➏ ለጁመዓ ሶላት መጣድ

https://t.me/AbuImranAselefy

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

17 Nov, 05:12


🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸



قَالَ رَسُولُ اللَّه ﷺ :- (أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ ، فمَن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى اللهُ عليهِ عَشرًا )
صحيح الجامع - رقم: (1209)


                              ˓٭˛✿🌹🍃

2,014

subscribers

322

photos

37

videos