አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA @adise1111 Channel on Telegram

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

@adise1111


የተለያዮ አዝናኝና አስተማሪ ፁሁፎች እሚቀርብበት
የአንባቢያንኝ ፍላጎት ለማርካት እምንታትርበት ምርጥ ቻናላችን ነው!


ሀሳብ አስታየታቹሁን ከታች ባለው አድራሻ ፃፍልን
t.me/adise11

አዲስ ንስር ሚዲያ / ADDIS NISR MEDIA (Amharic)

አዲስ ንስር ሚዲያ / ADDIS NISR MEDIA በተለያዮ አዝናኝና አስተማሪ ፁሁፎች በተቀርብበት የአንባቢያንኝ ፍላጎት ለማርካት እምንታትርበት ምርጥ ቻናላችን ነው! እስከአሁን የዳግም አሰራርንን ከታች ባለው አድራሻ ፃፍልን በማስተማር መተዳመቂያዎችን እስከ t.me/adise11 ወደሚለው ላይ ይዘንብላችኋል።

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

19 Oct, 21:00


ሕይወት በትግል የታቀፈች አለም ናት። ሁሌ እንታገላለን። ያለ ትግል የምንውልበት ቀን የለም። ስለ ገንዘብ ፍላጎታችን ወዲህ ወዲያ ስንሮጥ እንውላለን; ስለ እውቀት ብለን ትምህርት ቤቶች ወይም አብያተ መጽሐትን እንጎበኛለን; ለቤተሰቦቻችን እና ለወዳጆቻችን ደስታ ከመገኛቸው አቅንተን እንጠይቃለን; በሥራ ስለተባለ አካላችን ረፍት ስንል ጥቂት ረፍት ወይም መዝናኛ ቢጤ እንቃርማለን። ሁሉንም ስንሰራ ታዲያ የፈጣሪ ፍላጎት መጠበቁን ስለመገምገም መዘንጋት የለብንም።


በኑሮ ትግላችን የምንመኘው ጫፍ ደስታ መሆኑ ግልፅ ነው። ሙሉ ቀን በስራ ተወጥሮ የሚውል ነጋዴ ወይም ሰራተኛ በሚያገኘው ገንዘብ ፍላጎቱን ያሟላል ወይም ደስታውን ይገዛል። የሀይማኖተኛ ደስታ በሞራል ስልት በተቃኙ ተግባራት ይደምቃል። ለዝህ ለዛው ደግሞ የፈጣሪውን ፍላጎት ይጠብቃል። ይህን በማድረጉ ደሞ ከሌሎች የተሻለ የትዕግስት ባለሟል ይሆናል።


               📚 :-ታጋሾችን አብስራቸው
                ✍️:-ሙሀመድ አሊ(ቡርሀን)

https://t.me/Yamanefas_Kafeta 💙

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

10 Oct, 21:07


https://youtu.be/JcW5ZUsVpMU?si=ipbsVyaVi8v-c5m2

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

09 Oct, 21:31


https://youtu.be/JcW5ZUsVpMU?si=EDOdrpOcg69SDw8K

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

06 Oct, 22:18


ስፖርት / ተቀናቃኞቹ ገንዘቤና ሲፋን  እሁድ ቺካጎ ላይ ቀጠሮ ይዘዋል!! / sport Ethiopia / ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ,
#አዲስ_ንስር_ሚዲያ #ስፖርት #ስፖርት365
ሉሲዎቹ አቻ ተለያዩ!
ጨዋታውን ለማየት የሄዱ ተመልካቾች በፓሊስ ተደበደቡ!!
#አዲስ_ንስር_ሚዲያ
#ስፖርት
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ
#ቤትኪንግ_ኢትዮጵያ
#sport

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

06 Oct, 22:18


https://youtu.be/VYU6Lzt_QPY?si=32Y7xTyQnyDd12md

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

04 Oct, 00:06


#እንዳትመለስ!

የምትፈልገውን ሳታገኝ…
እንዳትመለስ!!!

#ራስን_መምራት መጽሐፍ በዴል ካርኒጌ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

📗📒📕

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

02 Oct, 22:37


ሳምንታዊ ስፖርት መረጃዎች / ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ / ቦክስ / አትሌቲክስ / ሴካፋ እና ሌሎችም ,,https://youtu.be/RQTV9fcIoVk?si=rkzDjS4ioLDloWuj

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

01 Oct, 20:38


🛑አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ🛑
 
🛑የታሪኩ ርዕስ🛑
🛑 #SCHOOL_LIFE🛑
(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ስድስት 6️⃣


ስገባም አልጋው ላይ እግሩን ወደ መሬት አንጠልጥሎ ተቀምጧል። ወይ የሰው መመሳሰል! አባዬ አልነበረም ግን በጣም ይመስላል።ቀድሞውኑ አይኔ ዋሽቶኝ ነው እንጂ አባቴ እንደዚህ አይነት ቅሌት እንደማይሰራ እና እንደዚህ አይነት ነውር እንደማያደርግ አውቃለው።


ቢሆንም አባዬ ስላልሆነ ንዴቴ አልቀነሰም ሊበርድልኝ አልቻለም ምክንያቱም ሰውዬው ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት የገባው ትልቅ ሰዉ ነዉ ። ቅሌታም ነህ ትልቅ ሰዉ አሰዳቢ እያልኩ ዘለፋዬን ቀጠልኩ
.......ሴተኛ አዳሪዋም ዞር በይ ገበያ አትዝጊብኝ ብላ እንደቆሻሻ አሽቀንጥራ ከቤትዋ አስወጣችኝ።

ቆሻሻውስ አንቺ ነሽ መገፍተር የሚገባሽ አንቺ ነሽ እያልኩ በልቤ የንዴት ስሜቴ ጥርሴን እያፈጫጨው ወደ ቤቴ ገባሁ።


ለከድር መናገር ያልቻልኩትንም ጭምር ንዴቴን አባብሶት እራስ ምታት እንደ መጋኛ አመመኝ።ቤትም እንደገባሁ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ። በማግስቱም እንደተለመደው ቦርሳዬን እና ምሳዬን ይዤ ወደ ትምህርት ቤት አመራሁ። መንገዱን እየተጓዝኩ የማስበው ስለ ከድር ነው። ስሜቴን ያወቀብኝ እየመሰለኝ በራሴ አፈርኩ። እሱን ማናገሩም ሞት መሰለኝ። ከዛን ቀን ጀምሮ ብዙ ጊዜ አሰላሙ አለይኩም ሲለኝ ባልሰማ አልፈው ጀምሬያለሁ
አስተማሪዎቼ ሁሉም ማለት ይቻላል በጣም ይወዱኛል። በተለይ ደግሞ ጥያቄ ለመጠየቅ እና የማስበውን ለመናገር ስለማልፈራ ያበረታቱኛል። ሀሳባቸውንም ቢሆን ለመቃረን ቅድሚያ የምነሳው እኔ ነኝ በዚህም ምክንያት ነው ለኔ ያላቸው ፍቅር ልዩ የሆነው.


ሰባተኛ ክፍል አጋማሽ ደረስን። የፋይናል(የመጀመርያ መንፈቅ አመት ማጠቃለያ ) ፈተናችንን ከተፈተንን በኋላ የ 15 ቀን እረፍት ተሰጠን። 15 ቀኑ 15 አመት ሆነብኝ ጊዜው አልቆ ትምህርት እስክንጀምር ጓጓሁ። የከድር ናፍቆት አላስቀምጥ አለኝ።መድረሳ ስሄድም ቆሜ ብጠብቀውም ላገኘው አልቻልኩም።አንዳንዴም እያለቀስኩ አላህዬ አንድ ጊዜ አይኑን ብታሳየኝ ምናለ እያልኩ አነባለሁ።

የእረፍት ጊዜያችን አብቅቶ የትምህርት ገበታችንን ጀመርን።እየሩስ ናፍቀሽኛል ብላ ተጠመጠመችብኝ።እኔም ናፍቀሽኛል ብዬ አንገትዋ ስር ተወሽቄ አለቀስኩ። ግን ያለቀስኩት በ ከድር ናፍቆት እንጂ በእሷ አልነበረም። ባለፉት 15 ቀን ውስጥ የተፈጠረውን አንድ አዳዲስ ነገር ማውራት ጀመርን።

ለእየሩስም ከድርን አፍቅሬዋለሁ ብየ ነገርኳት። በዚህ መሀል ይክፍላችን ልጅ የሆነው ሮቤል ንግግሬን ሰምቶ በፌዝ ዘቢባ ፍቅር ያዛት እያለ አወራ። ሙሉ የክላሱ ተማሪዎችም ማፍቀሬን እና ማንን እንዳፈቀርኩ አወቁ።


ከድር መኖሪያ ቤቱ ከትምህርት ቤታችን አጠገብ ስለሆነ ማንነቱን ለማወቅ አልተቸገሩም። እኔና እዩ ወንዶችን የፍቅር ጥያቄ መጠየቃችንን አላቆምንም
የ ስድስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን ናትናኤልን ለመጠየቅ ወሰንን እና ይሄንን ድርጊት እኔ እንዳደርገው ወስነን ደብዳቤውን ሰጠሁት።

በማግስቱም ጠዋት የመጀመርያ ክፍለጊዜ ላይ እየተማርን እንዳለ የክፍል ሀላፊዬ የክፍልን በር አንኳኳ እናም ስሜን ጠርቶ ቢሮ እንደምፈለግ ነገረኝ።
....... እኔም ምክንያቱን ባላቅም ወደ መምህራን ቢሮ አመራሁ። ሁሉም ክፍለጊዜ የሌለው አስተማሪ ተደርድሮ ቁመዋል። በተጨማሪም ናትናኤል እና አባቱም አሉ። ጉዳዩ ግራ ገባኝ የጠረጠርኩት ነገር አልነበረም።


ዳይሬክተራችን ነገ ወላጅ ይዘሽ እንድትመጪ አሁን ቦርሳሽን ይዘሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ አለኝ። ምክንያቱ ሊገባኝ አልቻለም።
....... እንዴ ለምን?? ምን አጠፍሁ ቲቸር??? እባክህ እያልኩ ለመንኩት
.......ዳይሬክተሩም እንዳንቺ አይነት ባለጌ ተማሪ አንፈልግም ብሎ እየገፈታተረ ከቢሮ አስወጣኝ....

Part 7️⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

👇👇👇Join👇👇👇
t.me/adise11

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

01 Oct, 20:33


👉በህይወታችን ብዙ ፈተናዎችን እናስተናግዳለን ብዙ ፈተናዎችን እናልፋለን እኖድቃለንም ግን እኛ ፈተናዎቻችንን የምንወድቀው ለምን ይመስላችኋል? ከህይወት የሚሰነዘርብንን ጠንካራ ዱላ እላያችን ላይ ካረፈ እኛ እንደምንጎዳ እና ዳግመኛ ማንሰራራት እንደማንችል ስለምናምን ነው በአጭሩ ቶሎ ተስፋ እንቆርጣለን እስከ መጨረሻው መሄድን እንፈራለን ግን እኮ እኛ የፈራነው መጨረሻ አሁን ካለንበት ህይወት ይልቅ ውብ ነው ምክንያቱም ሁሌም ቢሆን ከሀዘን በኋላ ደስታ ስላለ ስለዚህ ህይወት እኛ ላይ የምትሰነዝረው ዱላ ማቆሚያ የለውም እኛም ደግሞ ተስፋችን ከህይወታችን መጥፊያ መንገድ እንዳይኖረው ማድረግ አለብን ሁሌም ከአሁኑ አስከፊ ቀን በኋላ ደማቅ ቀን እንደሚጠብቀን እንመን ከዛም ጠንካራ እንሆናለን ተስፋችንንም በቀላሉ አናጣውም።

https://t.me/adise1111

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

01 Oct, 20:33


ይህ ሰው❗️

"የፅናት ውጤት ነው"

•═•••🍃🌺🍃•••═•

✍️ በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ

✍️ በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ

✍️ በ17 ዓመቱ 4 የተለያዩ ስራዎቹን አጥቶ ነበር

✍️ ከ18 እስከ 22 ዓመቱ የባቡር ትኬት ቆራጭ ሆኖ ሰራ ነገር ግን አልተሳካለትም

✍️ የሀገሩን መከላከያ ቢቀላቀልም ተባረረ

✍️ ህግ ለመማር አመለከተ አልተሣካለትም

✍️ ለአንድ ኢንሹራንስ ድርጂት ግብይት ሰራተኛ ሆነ ይህም አልተሣካለትም

✍️ በ19 ዓመቱ ደግሞ ልጅ ወልዶ ነበር 2ዐ ዓመቱ ላይ ሚስቱ ልጃቸዉን ይዛ ጥላዉ ሄደች

✍️ በአንዲት ትንሽየ ካፌ ምግብ አብሳይና ሰሃን አጣቢነት መስራት ጀመረ

✍️ የራሱን ልጅ አግቶ ሚስቱን ወደ ቤት እንድትመለስ ለማግባባት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀረ
.
.
.
✍️ 65 ዓመት ሲሞላዉ ጡረታ ወጣ

✍️ ጡረታ በወጣ በመጀመሪያዉ ቀን የ$105 ቼክ ከመንግስት ደረሠው። እሱ ግን የተረዳዉ መንግስት "ራስህን መመገብ አትችልም" እንዳለዉ ነበርና ከዚህ በኋላ መኖሩ ጥቅም እንደሌለዉ ራሱን አሣምኖ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረግ፤ ይህም ሳይሆን ቀረ

✍️ አንድ እለት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ምኞቶቹን ወረቀት ላይ ማስፈር ፈለገ የፃፈዉ ግን በህይወቱ ሊያደርጋቸዉ እየቻለ ሳያደርጋቸዉ ስለቀሩ ነገሮች ነበር። ከዝያም በእርግጠኝነት ማድረግ እንደሚችለዉ የሚያዉቀዉን አንድ ነገር አሰበ፤ ምግብ ማብሰል፡፡

✍️ ወዲያዉም የመንግስትን የዉለታ ቸክ መልሶ $87 ተበደረ

✍️ በዚያች ብድርም ቅመሞቹን ሸምቶ ፍራይድ ችክን አዘጋጀ። እናም በኬንታኬይ ለሚኖሩ ጎረቤቶቹ በራቸዉ ድረስ እየሄደ መሸጥ ጀመረ

✍️ አስታዉሱ ይህ ሰዉ በ65 ዓመቱ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አድርጎ ነበር

✍️ ግን በ68 ዓመቱ ኮሎኔል ሳንደርስ የኬንታኬይ ፍራይድ ችክን KFC ኢምፓየር መስራች ቢሊየነር ሆነ!

«ስለዚህ ወገን ከዚህ ሰው ብዙ መማር ይቻላል ተስፋ መቁረጥ የሰነፎች መፈክር መሆኑን ተገንዝበህ ሁሉንም ሞክር አንድ ቀን መክሊትህ የት እንዳለች ታውቃለህ፣ እሷም ስትቀርባት ትጠራሃለች።

https://t.me/adise1111

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

30 Sep, 17:10


አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA pinned «https://youtu.be/F3bxzO6U6qc?si=v7jND2Y-VSZNGJM9»

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

29 Sep, 22:52


https://youtu.be/F3bxzO6U6qc?si=v7jND2Y-VSZNGJM9

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

25 Sep, 23:33


https://youtu.be/0TU7mOo-rJw

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

24 Sep, 22:03


#ሀብታም__ለመሆን የሚተገበሩ 4 ነጥቦች🔥

#1_ወጪህ_ከገቢህ_አይብለጥ

ለፍላጎትሽ ገደብ አበጂለት።
ከአቅምሽ በላይ ውድ አልባሳት፣ ጌጣጌጦች፣ እና ውድ ስልኮች ላይ ገንዘብ ማውጣ ብልሀት አይደለም።

ተበድረህ አትጠጣ፣ ብልህና አላማ ያለህ ሁን።

የፋይናንስ ነጻነት እስከሌለህ ድረስ ፍላጎትህን ለማሙዋላት ከገቢህ በላይ ማውጣትህ ይበልጥ ያደኸይሀል እንጂ አይጠቅምህም።

#2_አላስፈላጊ_ወጪዎች_ቀንሰህ_የተወሰነ_ገንዘብ_ቆጥብ።

የምታገኘውን ገንዘብ በሙሉ አታጥፋ።
ለአደጋ ጊዜ እና የቢዝነስ እድል ሲመጣ መጀመሪያ ጥቂት ገንዘብ መቆጠብን ልማድ አድርግ።

#3_ተጨማሪ_የገቢ_ምንጭ_ፈልግ

አንድ የገቢ ምንጭ ብቻ አይኑርህ።
ተጨማሪ የገቢ ምንጮችንም ፍጠር።
ገቢህን ሁሌ ከፍ አድርግ፤ ጨምረው።

#4_ገንዘብህ_ገንዘብ_እንዲሰራልህ_አድርግ

ኢንቨስት ማድረግ ጀምር።

ጥቂት ገንዘብም ትሁን፣ ተጨማሪ ገንዘብን እንድትሰራ ማድረግ ተማር።

የፋይናንስ ነጻነት እንዲኖርህ ከፈለግክ ስለ ገንዘብ እና ኢንቨስትመንት በቂ ግንዛቤ ሊኖርህ ይገባል።
👇👇👇
VîrãVîrãl Mïd
Vîrãl Mïd🔥
ከደራሲያን አለም ፔጅከደራሲያን አለም ፔጅከደራሲያን አለም ፔጅ

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

24 Sep, 22:02


በአንድ ወቅት ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተናገረው:

“አሁን ላለሁበት ትልቅ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረገው ጏደኛዬ Albert Fantrau ማመስገን እፈልጋለሁ:: በወጣት ክለብ ውስጥ አብረን ተጫውተናል::

ሰዎች ከስፖርቲንግ ሊዝበን ክለብ ወጣቶችን ለመምረጥ መጡ:: እናም ብዙ ጎል ያስቆጠረውን አንዱን ተጨዋች እንደሚመርጡ ነግረውን ጨዋታው ተጀመረ:: ጨዋታውን 3 ለ0 አሸነፍን:: የመጀመሪያውን ጎል እኔ አስቆጠርኩ:: ሁለተኛውን ጎል ጏደኛዬ አልበርት በጭንቅላቱ ገጭቶ አስቆጠረ:: ብዙዎችን ያስገረመው ግን ሶስተኛው ጎል ነው:: አልበርት ከበረኛው ጋር አንድ ለ አንድ ተገናኜ: እኔ ከጎኑ ሮጣለሁ: በረኛውን ሸውዶ አለፈ: ባዶ ጎል ጋር ተገናኜ: ነገር ግን ባዶ ጎል ከማስቆጠር ይልቅ ኳሱን ለእኔ አቀበለኝ:: ባዶ ጎል አገባሁ:: እናም እኔ ተመርጬ ስፖርቲንግ ሊዝበን አካዳሚ ገባሁ::

ጨዋታው እንዳለቀ: ‘ለምን ባዶ ጎል ማግባት እየቻልክ ለእኔ ሰጠኸኝ ኳሱን?’ ብዬ ጠየኩት:: እሱም “አንተ ከእኔ ትሻላለህ:: አንተ ይህን እድል ማግኜት አለብህ” አለኝ::”

ከብዙ ዓመታት በሗላ ጋዜጠኞች አልበርት ቤት ሄደው ታሪኩ ትክክለኛነቱን አረጋገጡ:: የአልበርትም የኳስ ህይወት ከዚያ ጨዋታ በሗላ አከተመ:: አሁንም ስራ የለውም:: ነገር ግን የሚኖረው በጣም ትልቅ ቬላ ውስጥ: የሚያሽከረክረው መኪናዎች ውድ ናቸው:: የሚኖረው ልክ እንደ አንድ ባለሃብት ነው:: ጋዜጠኞችም “ስራ የለህም የምትኖረው እንደ ሃብታም ነው:: ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ብሩ ከዬት መጣ?” ብለው ጠየቁት:: እሱም በኩራት “ብሩ ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ ነው የመጣው!” አላቸው::

Moral of the story: ታች እያለህ የረዱህን ሰዎች ትልቅ ስኬት ላይ ስትደርስ አትርሳ!

Qal Mes

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

24 Sep, 22:02


💚💛#Good__Moring💚💛
* ስኬታማ ሰወች ከንፈር ላይ #ሁለት ነገር ይስተዋላል !
1ኛው «#ዝምታ» ሲሆን
2ኛው «#ፈገግታ» ነው።

ስኳርና ጨው አንድ ላይ አደባልቀህ መሬቱ ላይ ብታስቀምጥ ጕንዳኖች ጨውን ትተው ስኳሩን ልሰውት ይሄዳሉ።
ወደጆቼ ሆይ እናንተም ህይወታችሁን የሚያጣፍጥላችሁን ሰው ምረጡና ጣፋጭ ኑሮን ኑሩ።
ግብህ ጋ መድረስ ከተሳነህ ግብህ እንጅ ተስፋህ አይቀየርም።
ዛፎች ቅጠሎቻቸውን እንጅ ስሮቻቸውን አይቀይሩም።
ክብር መስጠት ላለብህ ጉዳዮች ላይ ክብር ስጥ።
ቀለል ማድረግና አንዳንዴም ማለፍ ላለብህ ጉዳዮች ላይ ጊዜህን አታባክን።

#ከተመቸወ ሼር፣ላይክ
አስተያየት ?????
#ከደራሲያን__አለም_ፔጅ
ከደራሲከደራሲያን አለም ፔጅ ከደራሲያን አለም ፔጅ
ከደራሲያን አለም ፔጅ

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

24 Sep, 22:01


👉ውሸታሟ እናቴ።

እናቴን አላምናትም ዋሾ ናት ቀጣፊ
ህያው መስላ ኖራ ድንገት ታይታ ጠፊ።

ኑሮ እያሳቀቃት ከፍቷትም ተጨንቃ
ትቀርባለች ፊቴ,,,,,
በጥርሶቿ መሀል ሀዘኗን ደብቃ።

ታማ እንኳን ተኝታ ሆና በሽተኛ
"ተመስገን!!" ትላለች,,,,,
የደላው ሰው መስላ ልክ እንደ ጤነኛ።

##########

እናቴን አላምናትም ዋሾ ናት ቀጣፊ
ህያው መስላ ኖራ ድንገት ታይታ ጠፊ።

ወጥቼ እስክመለስ እስክገባ ቤቴ
አታምነኝምኮ ውሸታሟ እናቴ።
ደርሶ አልችል እያላት እንስፍስፉ አንጀቷ
"ልጄን ጠብቅልኝ!" የዘወትር ፀሎቷ።

መምጣቴን ስታውቀው ድምፄንም ስትሰማ
ለአምላኳ ምስጋናን ውዳሴ አስቀድማ
አትረካም ደባብሳኝ አትጠግበኝም ስማ።

##########

እናቴን አላምናትም ዋሾ ናት ቀጣፊ
ህያው መስላ ኖራ ድንገት ታይታ ጠፊ።

እህል እያሰኛት በርሀብ ዕዳ ወድቃ
"አሁን በላሁ" ብላ አንጀቷን ደብቃ
ትላለች ለልጄ ከጉሮሮዋ ነጥቃ።

##########

ቀጣፊዋ እናቴ,,,,,
ህያው ዘመን ፍጡር የኖረችው መስላ
ስትዋሸኝ ነው እንጂ,,,,
ለካ እሷም አፈር ናት ተሰባሪ ሸክላ።

የዓለም ጌጥ ሆናልኝ እስትንፋስ ህይወቴ
የእግዜር ስጦታዬ ፀጋ በረከቴ
ዛሬ ብደሰትም አጠገቤ እያለች
ነገር ግን እውነታው,,,,
ቀን የጠራት ለታ
ሳትሰናበተኝ ድንገት ትሄዳለች።

👌ገጣሚ ዘሪሁን ከ አሰላ።👌
ህዳር 03/03/2014 ዓ,ም።

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

24 Sep, 22:01


ሌላ ሪከርድ በማራቶን ትዕግሥት አሰፋ...ማንም ሊደፍር በማይችል መልኩ አሻሽላለች

https://vm.tiktok.com/ZMjUTDr7T/

አዲስ ንስር ሚዲያ /ADDIS NISR MEDIA

23 Sep, 15:44


https://youtu.be/-Gwt1RFVT58?si=Vw8JJ0AQgDvvpdxa