ማጄላንና ታላቁ ሙጃሂድ ላቡ ላቡ
╚═══════════════╝
ልጅ ሳለን ስለማጄላን ጥሩ ጥሩው ተነግሮናል። በየትምህርት ቤታችን አስተማሪዎቻችን ስለእርሱ መልካም መልካሙን አውግተውናል። ዓለምን የዞረ የጂኦግራፊ ሊቅ ተብሎ የሚወሳው ማጄላን ማን ነው? እውነተኛ ታሪኩን ላውጋችሁ።
ሙስሊሞች የፊሊፒንን ደሴቶች ማሃራጅ ብለው ይጠሯቸዋል። ከቻይና እና ከሱማትራ በመጡ ነጋዴዎችና ዳዒዎች እስልምና በአካባቢው ተስፋፍቷል። ለ“ማኒላ” ድንበር ነዋሪዎች በሙስሊም ነጋዴዎች አማካኝነት የኢስላም ጥሪ ደርሷቸዋል። የእስልምና ብርሃን ከ7000 በላይ ነዋሪዎች ዘንድም ፈንጥቋል። ይህ የእግር እሳት የሆነበት ማጄላን ሙስሊሞች እንዳይስፋፉ እስልምናን ማምከን ይቻለው ዘንድ ከፖርቹጋል ተነስቶ ምስራቅ አፍሪካን እስከ ህንድ አዳርሶ ሙስሊሞችን በገፍ ብትሩ ቀጥቷል።
ሙስሊሞችን በእጅጉ ይጠላል። በ1502 ለሐጅ ጉዞ 700 ሙስሊሞችን ጭኖ የሚጓዝ መርከብን አገተ። መንገደኞቹ ወዴት እንደሚሄዱም ጠየቀ። የአላህን ቤት ለመጎብኘት ወደ መካ እየተጓዙ መሆኑ ሲነገረው ለግብረ አበር ወታደሮቹ ትዕዛዝን አስተላለፈ። ንብረታቸውን ከተዘረፉ በኋላ በመርከቡ ላይ ሰብስበው ከነህይወታቸው አቃጠሏቸው። በዘመታቸው የመስቀል ጦርነቶች ከ300 በላይ መስጂዶችን አፍርሷል።
ሙስሊሞችን ማርኮ አፍንጫቸውንና ጆሮዎቻቸውን ቆራርጧል። ጥርሶቻቸውን እየሰበረ በድዳቸው አስቀርቷቸዋል። እጅና እግራቸው ተጠፍሮ በክፍል ውስጥ ታጭቀው ከነህይወታቸው በእሳት ነደዋል።
ማጄላን የምድር አሳሽ አለምን የዞረ ጆግራፊስት መሆኑን አስተምረውናል። ግና ለሙስሊሞች የነበረውን ጥላቻ ያደረሰባቸውን ግፍና መከራ አልነገሩንም።
እ.ኤ.አ. በ1521 በ“ፈርዲናንድ ማጂላን” የሚመራው የስፔን ጦር ፊሊፒን ደረሰ። የጎረቤት ደሴቶች በስፔን አክሊል ሥር እንዲተዳደሩና ክርስትናን የበላይ ለማድረግ በሚል ስምምነት ላይ ተደረሰ። አመጣጡም የእስልምናን መስፋፋት ለመግታትና ሙስሊሞችን አይቅጡ ቅጣት ለመቅጣት የታሰበበት ነበር።
በመስቀል ዘመቻው “ማክታን” የተሰኘች አንዲት ትንሽዬ ደሴትን ለመቆጣጠር ጉዞ ጀመረ። በወቅቱ ደሴቷ “ላቡ ላቡ” በሚባል ሙስሊም ሡልጣን ትተዳደር ነበር። በማጄላን የሚመሩት የስፔን ወታደሮች ከደሴቷ ጠረፍ መሽገው ከነዋሪዎቿ ምግብ እየነጠቁና ሐብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ሲያስቸግሩ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰማ። ላቡ ላቡ እጅግ ጠንካራ ሙጃሂድ ነበርና ለማጄላን ወረራ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማጄላን የአጎራባች ደሴት ነዋሪዎችን አነሳሳበት። ጥንካሬውን እና ዘመናዊ መሣሪያዎቹን ለማሳየት እድሉን ስላገኘ ደብዳቤ አስይዞ ወደ ላቡ ላቡ መልዕክተኛን ላከ።
"ከማጄላን ለማክታን ደሴት ገዢ ላቡ ላቡ በእየሱስ ስም እጀምራለሁ እኛ የነጭ ዘሮች የስልጣኔ ቀዳሚዎች ይህንን ሀገር የመግዛት ስልጣን ከእናንተ የበለጠ ይገባናልና ስልጣንህን አስረክብ"
ላቡ ላቡ ደብዳቤውን አንብቦ እንዳበቃ በግልባጩ አጭር ምላሽን ፅፎ ሰደደ "ኃይማኖት የአላህ ነው። የምናመልከው አምላክ ቀለማቸው ምንም ይሁን ምን የሰው ልጆች ሁሉ አምላክ ነው" ሲል መለሰ።
በዕለቱ ፀሐይ በሰማይ መሃል አናት ላይ ነበረች። የማጄላን መርከቦች በፊሊፒን ከሚገኙት የሙስሊም ደሴቶች በአንዱ ላቡ ላቡ በሚያስተዳድረው የማክታን ደሴት ዳርቻ እየተቃረቡ ነው። ዓመቱ 1521 ነው። ፊሊፒናዊያን በወጣት መሪያቸው “ላቡ ላቡ” መሪነት ተሰብስበው ለጂሃድ ተዘጋጅተዋል። ትናንሽ ጀልባዎች ላይ አድፍጠው የወቅቱን ዘመናዊ መሳርያ ታጥቀዋል። የራስ ቁር በአናታቸው አጥልቀው ሰይፍና ጋሻን ይዘዋል። በተንጣለለው ደሴት ላይ ከቀርከሃ በተሠሩ ቀስቶችንና አጫጭር ሰይፎችን ሸክፈዋል። የማጄላን ወታደሮች ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲጠጉ ካደፈጡት ሙጃሂዶች ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ሁለቱ ጭፍሮች ተገናኙ። የማጄላን ወታደሮች እንደለመዱት የሙስሊሞች አንገት ከራሳቸው ሊያበሩ ተዘጋጁ። በሹል ሰይፎቻቸው ሰውነቶችን ሊቀዳድዱ ቋመጡ። ግና ስላደፈጡት ሙጃሂዶችና ስለቀርከሃ ቀስቶች መረጃው አልነበራቸውም። የራስ ቁር እና ጋሻ ይዘው ያፌዙባቸው ጀመር። ጎራዴ ከጎራዴ ጋር ተፋጨ። በ“ላቡ ላቡ” እና “ማጄላን” መካከል እጅግ ጠንካራ ፍልሚያ ተደረገ።
የብረት ጡሩር ደረቱ ላይ ያጠለቀው ማጄላን በባዶ ራቁቱ በሚዋጋው ሙጃሂድ በላቡ ላቡ ሠይፍ ተመቶ ወደቀ። ጉዳቱ ለሞት የሚዳርግ አልነበረም። ወጣት መሪ ላቡ ላቡ ለሁለተኛ ጊዜ የማጄላን አንገት ላይ ሰነዘረ። የማጄላን ጭንቅላት በደም ተጨማለቀ። የመሪያቸውን መገደል ያዩት ወታደሮች ከመሸሽ በቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውምና አስክሬኑን ጥለው ወደ መርከባቸው መፈርጠጥ ጀመሩ።
ፊሊፒናዉ ሙስሊም ጀግና የተዋጣለት ተዋጊ ሙጃሂድ ‹ላቡ ላቡ› ማጄላን በሙስሊሞች ላይ የሰራውን ግፍና እየፈፀመ የነበረውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሰምቶ በእጅጉ ተቆጥቶ ነበርና እነሆ ዛሬ እስከወዲያኛውም ወደ ቀብር ሸኘው።
ፊሊፒናውያን አሁንም ላቡ-ላቡን ብሔራዊ ጀግናቸው አድርገው ይመለከቱታል።
እንደ አለመታደል ሆኖ የእስልምና ጠላቶች የማጄላንን የሐሰት ታሪክ አስውበው ፃፉልን። እኛም በምዕራባውያን መስቀለኞች ዓይን እንድናነበው ተደረግን። በልባችን ውስጥ እንደጀግናና ተአምረኛም ይዘከር ይዟል።
ማስታወሻ:- ምስሉ ማጄላንን የገደለው ሙጃሂድ የጀግናው “ላቡ ላቡ” ነው።
═════════════════
ምንጭ:-
كتاب قبسات من نور
╔═══════════════╗
http://t.me/sehkaliderashid
╚═══════════════╝