ደስታን የምትፈልግ ከኾነ
ከባለጸግነት፣ ከሥጋ ጤንነት፣ ከ[ምድራዊ] ክብር፣ ከሹመት፣ ከቅምጥልነት፣ ከተትረፈረፈ ማዕድ፣ ከጌጠኛ ልብስ፣ ከውድ መሬት፣ ከተጌጠና ለእይታ ከሚማርክ ቤት ወይም ይህን ከመሰለ ሌላ ነገር አትፈልገው፡፡
✅ ከዚህ ይልቅ
[ደስታን] እንደ እግዚአብሔር በኾነው መንፈሳዊ ጥበብ፣ ምግባር ትሩፋትንም በመያዝ ፈልገው፡፡ እንዲህ የምታደርግ ከኾነም አሁን ያሉ ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉ ነገሮች አንተን ማሳዘን አይቻላቸውም፡፡
✅ አይቻላቸውም የምለውስ ለምንድን ነው?
በእውነት ሌሎች ሰዎችን የሚያሳዝነአቸው ነገሮች [እንኳን ሳይቀሩ] ለአንተ የደስታ ምንጭ ይኾኑልሃል፡፡
እንግልቶች፤ ግድያዎች፣ ማጣቶች፤ ሐሜቶች፤ ክፉ አቀባበሎች፣ እነዚህንም የመሳሰሉ ኹሉም ነገሮች በእኛ ላይ ሲደርሱ ስለ እግዚአብሔር ብለን የምንቀበላቸው ከኾነና ምንጫቸው ይኸው ከኾነ ወደ ነፍሳችን ብዙ ሐሴትን ያመጡልናል፡፡
እኛው ራሳችን እንደዚያ እንድንኾን ካልፈቀድን በቀር ጎስቋሎች እንድንኾን ማድረግ የሚቻለው ማንም የለምና፤ ወይም ደግሞ በሌላ መልኩ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን እኛው ራሳችን ንዑዳን ክቡራን ካላደረግን በቀር ማንም ይኹን ማን ብፁዓን ሊያደርገን የሚቻለው የለምና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️