Alex Abreham በነገራችን - ላይ @alexabreham Channel on Telegram

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

@alexabreham


በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር

1- አልተዘዋወረችም
2- ከዕለታት ግማሽ ቀን
3- ዙቤይዳ
4 - ዶክተር አሸብር
5 - እናት ሀገር ፍቅር
6 - አንፈርስም አንታደስም

💚💛❤️

Official Fan Channel !
አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው::
Contact me
@akexeth

Alex Abreham በነገራችን - ላይ (Amharic)

በአሌክስ አብረሃም በገበያ ላይ ማህበረሰብ መፅሐፍ ዝርዝር የሚለውን መነሻ አለመረጃነት ይችላሉ። ለአጠቃላይ ያላቹ ከዕለታት ግማሽ ቀን በነገሩ ይገኛሉ። ይህንን መፅሐፍ ዝርዝር በወቅታዊ፣ እናቶች ወሮች፣ ዶክተርዎች አሸብርዎች፣ እናቶች ሀገሮች ፍቅሮች የሚለውን መፅሐፍ በቃ ብሎ እንገናም። እናረጋለን። አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው፡፡ ምንድን አማራጭ ኖርናል? በቃ መሰል ቃል ጠይቀን? ከቀኑ ይመልከቱ፡፡ በአጭር አባል አቃቤ ከቴለጎም @akexeth እንደደውሉ።

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

31 Jan, 03:04


አለሁ ማለት ከንቱ!

መቸም አይነቱ ብዙ ቢሆንም በደፈናው "አልዛይመር" የመርሳት ችግር እንላለን አይደል? ይሄ በቃ መርሳት ነው። ደሞዝ በተጨመረ በሳምንቱ ባለስልጣኑ ለመመስገን በተገኙበት መስሪያ ቤት "እንዴት ነው ጭማሬው ?" "ቢሉ አንድ አዳራሽ ሙሉ ሰራተኛ "የቱ ጭማሬ" ያለውን የመርሳች ችግር እንዳትሉት😀 እሱ ኑሮ ነው። ሰሞኑን የሰማሁት ግን ትንሽ ይለያል። ቀድማችሁ ታውቁት ከነበረ እንጃ! ነገሩ መርሳት ሳይሆን የሰማችሁት ወይም ያያችሁት ነገር ዘግይቶ ነው አእምሯችሁ ጋ የሚደርሰው። ለምሳሌ አርብ የሆነ ኮሜዲ አይታችኋል አትስቁም እሁድ ቤተ ክርስቲያን ተቀምጣችሁ በአርቡ ቀልድ በሳቅ ትፈርሳላችሁ። ከዛ አዕምሯችሁ የእሁዱ ስብከት ሲጓዝ አድሮ ሰኞ ይደርሰዋል...የስራ ስብሰባ ላይ አሜን ትላላችሁ። ምሳሌ ልጨምር ይሆን? እሽ ልጅቱን ተንበርክከህ ታገቢኛለሽ? አልካት የተንበረከክበት ጥላህ ትሄድና በቀጣዮ ቀን ደውላ "Yes" ትልሃለ። በሳቅ እየተፍለቀለቀች። ችኩል ከሆንክ ቀለበቱ ተጠባባቂ የፍቅር ሂደት ሀላፊዋ ጣት ላይ ገብቷል። በሉ ደግሞ ለዚህ ፅሁፍ ከነገ ወዲያ ኮሜንት ስጡ አሏችሁ😀,

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

30 Jan, 10:39


በዚህ ሳምት ከወዳጀ የሰማሁት ተረት ነው!
ሰውየው በመንገድ ሲያልፍ አንድ ከሲታ ድመት ከፊቱ በእርጋታ ሲጓዝ ያይና "ውሮ ከመንገዴ ዞር በል እስቲ" ይለዋ። ድመቱ ሳይደነግጥ ዞር አለና " ኧረ ኑሮው ነው ድመት ያስመሰለኝ እንጅ እኔስ ነብር ነኝ😀

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

29 Jan, 11:03


ዘመኑ ለክፉወች ደግ ነው!

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Jan, 17:34


የጥንቃቄ መልዕክት!
******

• ስለ ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ምን ያህል ያውቃሉ ?

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ስልካችን ላይ ከማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች በምንጭናቸው መተግበሪያዎች አማካኝነት ወደ ስልካችን ሰርጎ የሚገባ ሲሆን እንደ ቴሌግራም፣ዋትስአፕ፣የመሳሰሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ጥቃትን የሚሰነዝር መተግበሪያ ነው፡፡
• ጉዳቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ክፍል ሰሞኑን ፋርማ ፕላስ (Pharma+) የተሰኘውን መተግበሪያ ጉዳት አምጪነቱን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ እንደገለጸው ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ከማህበራዊ ትስስር ገጾች አውርደን በምንጭናቸው ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር በመለጠፍ ወደ ስልካችን ሰርጎ በመግባት የስልካችንን ስክሪን ማየት፤ አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ማንበብ፣ ሀሰተኛ የመግቢያ ገጾቸን በማዘጋጀት የይለፍ ቃሎችን መመንተፍ እና የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን የሚሰርቅ መተግበሪያ ነው፡፡

የፋይናንሻል ግብይቶችን ከተጠቂው እውቅና ውጪመፈፅሙ እና ስልካችን ላይ ተጭነው ካሉት መተግበሪያዎች ውስጥ መደበቁ ማየት ስለማንችል ለመከላከል በጣም አዳጋች መሆኑ ነው።

• እንዴት ራሳችንን ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ይጠብቃሉ

• ካልታመኑ ምጮቾች ማንኛውንም መተግበሪያ ስልኮት ላይ አይጫኑ፤
• በማህበራው ገጽ አማካኝነት የሚላክሎትን ማንኛውንም ማስፈንጠሪያ ወይም መተግበሪያ ምንነቱን ሳያረጋግጡ አይክፈቱ፤
• ብቅ ባይ (Pop up) ማስታወቂያዎችን ወይም አጠራጣሪ ገጾችን በፍጹም አይክፈቱ፤
• እንደ ጎግል ፕሌይ፣ አማዞን፣ አፕስቶር ወይም ሳምሰንግጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ብቻ ይጠቀሙ።
ትክክለኛ የስልክ መተግበሪያዎችን በመጠቀም እራስዎትን ይጠብቁ!
#cbe #phishing #pharma+ #Ethiopia #alert #mobile_banking #banking

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Jan, 16:53


"በቀላሉ ተሰርቶ ሀብታም የሚያደርግ ስራ" የሚል ማስታወቂያ ያመናችሁ ቀን በስጋም በመንፈሰም በከባዱ ትወድቃላችሁ።

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Jan, 06:53


እኔና ቀበሌ
(አሌክስ አብርሃም)

እኔና ቀበሌ ያለን ግንኙነት በጣም ጥሩ አልነበረም። ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሆኘ ነበር መታወቂያ ላወጣ ቀበሌ የሚባል ነገር የሄድኩት። እና እንዲህ ሆነ... ሊቀመንበሩ የሆነ ግድንግድ ፋይል አስመጣና አቧራውን መታ መታ አድርጎ ካራገፈ በኋላ ፋይሉን ገለጠ! ....ፈልጎ ፈልጎ "ስምህ የለም...ምን እዚህ ለልማት አትመጡ...ለስብሰባ አትገኙ" አለኝና በመነጫነጭ ፋይሉን ወደጎን ገፋ አደረገው። ከላይ ያለውን ስም ሳየው የሌላ ቤተሰብ አባት ስም፣ የሌላ ፋይል ነው። "ኧረ ይሄ የአባቴ ስም አይደለም" ስለው አንዴ ገላመጠኝና ትክክለኛው ፋይል እንዲመጣ አዘዘ።

ቆይታ ቆይታ አንዲት የደከማት ፣ጆሮዋ ላይ ጤናዳም፣ አፍንጫዋ ላይ ነጭ ሽንኩርት የወተፈች ሴትዮ መጣችና ለቅሶ በሚመስል ድምፅ "ፋይሉ የለም" አለች። ሊቀመንበሩ ወደእኔ ዞሮ "የአንተም ስም የለም የአባትህም ስም የለም" አለኝ ሂድልኝ በሚል ፊት። በስጨት ብየ ስወጣ የቀበሌውን ስም ፊት ለፊት አየሁት፤ ቀበሌ 13 ይላል። የእኛ ቀበሌ ቀበሌ 5 ነበር😀 አባቴ ታዲያ ሲበሳጭ " ሰው ይሄን ሁሉ ክፍል ተምሮ ዮኒበርስቲ በመግቢያው የተሳሳተ ቀበሌ ይሄዳል?" ይላል። እናቴ በፊቸሪንግ ትገባለች
"ተምራ ተምራ ዳዊት ጨርሳለች
እንደገና ወርዳ ሀ ሁ ትቆጥራለች" አሉ 😀 እስካሁን ቀበሌ በተባለ ቁጥር ዘወር ብሎ በመነፅሩ አናት ያየኛል። ቀበሌው ራሱ ፈርሷልኮ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Jan, 06:10


አነቃቂ ንግግር ሰምታችሁ ጠላታችሁ ፊት ስትቆሙና...ደንገት ሆርሞኑ ቦታውን ለአእምሮ ሲለቅ😀

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Jan, 12:22


ምንም ጋር አይያያዝም! እንዲያው ዛሬ ሳነብ ገርሞኝ ነው። አንበሳ (የጫካው ንጉስ) ከአጠቃላይ ዕድሜው ከ65-75 በመቶ የሚሆነውን የሚያሳልፈው በእርሃብ ነው። በቃ ይርበዋል። ስንት ስምና ዝና የሸፈነው ርሃብ አለ እናንተ?!

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Jan, 10:42


‹‹ በቀኝ አሳድረኝ ››
(አሌክስ አብርሃም)

ቀጭ ….ቀጭቀጭ …ሲጥ ..ሲጥጥ
እህህህ ..‹‹ቀስ በል የኔ ጌ….ታ …››
በ ሹ ክ ሹ ክ ታ
ከግድግዳየ ወዲያ … ሁሉም ባረፈበት ማታ
ካዲስ ተጋቢዎቹ ቤት
አልፎ የሚመጣ ንዝረት
ጆሮ የሚያቆም ወላፈን
ደምፃቸውን ለቀቅ ….አፈን
‹‹ውይይይይ ….›› የሷ ድምፅ …... በሲቃ ሲተን
የዝምታ አለት …. በፍቅር ፈንጅ… አልጋቸው ላይ ሲበታተን
ደግሞ የሱ ከንፈር ዋይታ …….እ…..ሟ
የወንድ ልቡ ብረት ወኔው …በፍቅር እቶን ሲሟሟ
‹‹እፉፉፉፉፉ ››ድምፃቸውን እንደጅራፍ ባንድ ፈትለው ባንድ ገምደው
ድቅድቅ የጨለማን መንጋ በሲቃ ጩኸት አሳደው
ባንድ ላይ ሲቀላቀሉ የብቻን ግንብ ወዲያ ንደው
አውሎ እፎይታ
ከቀኝ ግድግዳየ ተጎራባች…. ሁሉ ባረፈበት ማታ
ዝምምምምምምታ !
ተኙ መሰል !!
*** **** ***
ሌላ ድምፅ ደግሞ ከግራ
በቆመ ጆሮየ ግርጌ ያልፋል ድሩን እያደራ
‹‹ እእእእእ ›› ይችኛይቱ ጎረቤቴ
እንዲህ በሙሉ ጨረቃ የሚያስቃዣት በሽተኛ
ሙሉ ሌሊት ስትዋትት ስትሰቃይ የማተኛ
ድፍን ሌሊት ስትዛብር ስታቃስት የሚነጋ
ሲጥ ሲጥጥ ወጉ እንዳይቀር የሷም አልጋ
ቀንም በመቀነቻ ነው … ወገቧን አስራ የምትቆመው
የበሽታ ክፉ አካናድ ስጋዋን እየጎሰመው
በሁለት ቅስቻ መሃል … ግራ ቀኙኝ እያደመጥኩ
ካንዱ <ጆሮየ አውጭኝ> እያልኩ… ሌላውን ባሳብ እያለምኩ
በመሃል የምኖር እኔ …
እንቅልፍ ሊጥለኝ ሲዳዳ በግዜር ላይ ቅኔ እቀኛለሁ
የወጉን ፀሎት ሰም አድርጌ ‹‹በቀኝ አሳድረኝ ››እላለሁ
**** **** ****
ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ኳ ኳ
አዲስ ተጋቢወች ማለዳ ተነስተው…. ለቁርስ ቲማቲም እየቀጠቀጡ
ሲጥጥጥጥጥጥጥጥጥ
ታመው ያደሩቱ ቤተስኪያን ሊስሙ …..ከቤት እየወጡ
በቀኝም በግራ እንዲህ የሚል ልሳን
‹‹ሰላም ያሳደርከን በሰላም አውለን ››
ይች ናት አገሬ … እኩል እግዚሃርን የሚዘይሩባት… እኩል ያላደሩ
እኩል ቀን ጀማሪ እኩል ባልሆነ ቁርስ ተስፋ እየቋጠሩ !
ከታች እስኪሾሙ ከላይ እስኪጠሩ !!
ከቀኝም ከግራም …መሃል ለሰፈሩ
ይች ናት አገሬ እንዲህ ነው አዳሩ !

@AlexAbreham @AlexAbreham
አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው !!
src Click Here

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Jan, 02:55


ከዕለታት የማምሻ ቀን
ከቢኒያም አቡራ

የማምሻ ፉንግና
የማምሻን እያንዳንዱን የሰውነት ክፍሏ ምን ያህል አስቀያሚ እንደ ኾነ ከመግለጽ ይልቅ፥ በማኅበረሰቡ የፉንግና መድሎት ላይ ያውላታል። ማኅበረሰቡ ባወጣው የቁንጅና መስፈርት ውስጥ ይገልጻታል። ዓይኗ፥ ጥርሷ፥ ከንፈሯ ከማለት ይልቅ በሰዎች አንደበት ውስጥ ያለውን አተያይ በመጠቀም ምስሏን ይከስታል። ለአብነትም፡- ዓይን የማይለምደው መልከ ጥፉነት … በቀለኛ አጋንንት በአጉሊ መነጽር እየተመለከተ፥ ትንሽ ሰውን ሊስበው ይችላል ብሎ የጠረጠረውን ሁሉ እየለቀመ ያፈራረሰ ነው የሚመስለው … እኔ ነኝ ያለ ደራሲ ቀርቶ ፎቶ አንሺ ራሱ በበቂ ሁኔታ ማሳየት የሚሳነው መልክ … ይሄ ቸብ ያደረገህ እጅ የማምሻ ቢኾን ኖሮ መፍለጫ እንዳረፈበት ጉቶ ወለል ላይ ትበታተን ነበር … እና መሰል አገላለጾችን በመጠቀም የማምሻን ፉንግና በእዝነ ልቦናችን እንዲከሰት ያደርጋል። ግሩም ዝየዳ ነው።

“ዓለም ፈውሷን እንድትቀበል የሎዛ ዓይነት እብዶች ሳያስፈልጓት አይቀርም!”
አንድ እጭ እንቁላል ውስጥ እያለ ከባድ ጊዜን ያሳልፋል። እንቁላሉን ሰብሮ ለመውጣት ይታገላል። እንቁላሉን ሰብሮ ለመውጣት በሚያደርገው ተጋድሎ ጡንቻዎቹ እየፈረጠሙ ይሄዳሉ። እንቁላሉን ራሱ ሰብሮ ሲወጣ የፈረጠመ ጡንቻ ስለሚኖረው ክንፎቹ ሳይዝሉ ለረዥም ጊዜ ይበራል። ነገር ግን እጩ በእንቁላል ውስጥ ኾኖ ከሚያደርገው መፍጨርጨር የተነሳ አንድ ሰው አዝኖለት እንቁላሉን ቢሰብረው እጩ ተጎጂ ነው። ከተሰበረለት እንቁላል የወጣ እጭ ጥቂት እንደ በረረ ይፈጠፈጣል። ምክንያቱም እንቁላሉን ለመስበር ጥረት በማድረግ ሂደት ውስጥ ያገኝ የነበረውን ጥንካሬን አይታደልምና። ከዚህም የተነሳ ከጥቂት ምዕራፍ በቀር መብረር ይሳነዋል። ይህ የገባት ሎዛ የማምሻን እንቁላል አትሰብራላትም፤ ለዚያም ነው ማምሻ በቀላሉ ክንፎቿ ያልዛሉት።

መኪና በሰዎች ኃይል ሲገፋ ጥቂት ሄዶ ይቆማል። ከራሱ ከሞተሩ ኃይል ከሆነ ግን አያሌ መንገድ ይጓዛል። የሰው ግፊት የሚያስፈልገው ሞተሩን መንጭቆ ለማስነሳት ነው። ሎዛ የማምሻ ሞተር እንዲነሳ ብቻ ነው የገፋችው። በዚህ ዐውድ ሴቶችን የማጎልበት (women empowerment) ተኮር የኾኑ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች ለሴቶች ሞተር መኾን እንደ ማይችሉ ጥቁምታ ሰጪ ነው። አነቃቂ ንግግርም (motivational speech) የመጨረሻ ግብራቸው መኪናውን መግፋት ብቻ መኾኑን ያሳያል።

ሎዛ የማምሻ ሞተር መንጭቆ እንዲነሳ ጥቂት ግፊት አድርጋለች ማለት የሎዛን ግብር ማሳነስ አይደለም። “አገሩ የበጎች ነው። ግን የበጎች ታሪክ ቦታ የለውም። በጎች ራሱ የሚተርኩት የአንበሶችን የጀግንነት ጀብዱ ነውግሩም ዝየዳ ነው። ምናልባት ታሪኩ የበጎችን ስም ካነሳ፤ በአንበሶች እንዴት እንደተበሉ ከመተረክ _ አያልፍም። የበግ ቆዳ የለበሱ አንበሶች ጠላታቸው የለበሱት ቆዳቸው ነው፤ ስለዚህ ይህን ቆዳ እንዲገፉትና ታሪካቸው እንዲጻፍ ትንሽ መርዳት አለብን። በሚል መነሻ ነው ማምሻን የምታግዛት። ሎዛ “ብዙ አይደለም…ትንሽ!” ብትልም ቅሉ ነገሩ ቀሊል አይደለም። ሲጀመር ሎዛ ለማምሻ ያደረገችላትን ነገር ለማድረግ ሎዛነትን ይጠይቃል። የሎዛን እብደት ይሻል።

ሎዛ ባዶ ቀረርቶ አይደለም ለማምሻ የለገሰችው። "ትችያለሽ!" የሚል ባዶ የማነቃቂያ የጅምናስቲክ ትርዒት አይደለም ያቀረበችላት። ማኅበረሰቡ በማምሻ የተጠለፉ ጥልፎችን ንቆ በዘመናዊ ማሽኖች የተፈበረኩ አልባሳትን ሲመርጥ፥ የማምሻን የእጅ ሥራ የለበሰችው ብቸኛ ሴት ሎዛ አይደለች? አብርሽ በእምቢታ የተወውን ትኩስ እንጀራ በመመገብ አይደል ሙያ እንዳላት በስውር የምትነግራት? ማምሻን “ለሰርግ ታዳሚነት ብቁ አይደለችም!” ብሎ በሚያምን ማኅበረሰብ ውስጥ፥ አንደኛ ሚዜ አድርጋ ለመሾም መሞከሯ ብቻውን ማምሻን እንደገና የመውለድ ያህል አይደለምን? … ሕጻናትን ለማስፈራራት “ማምሻን እንዳልጠራልህ”! የምትባለዋን ሴት፥ ለአንደኛ ሚዜነት እጩ ማድረግ ዕውን ቀላል ውለታ ነው? … በሰርጓ ቀን በጥበብና በወርቅ የተንቆጠቆጡ አክስቶቿን ረግጣ፥ ማምሻን ብቻ በማቀፍ የመፈለግ ስሜቷ ላይ ትንሳዔ አልዘራችባትም? ይሄ “አንቺ ተፈላጊ ሴት ነሽ” ከማለት የበለጠ መልዕክት አያስተላልፍም? ዱዱሻ የተባለች ሕጻን - አረንጓዴ እና ጥቁር ቀለም በመጠቀም በሳለችው ስዕል ላይ፣ “ማምሻ ሕጻኑን ልትበላ” በማለት የጻፈችው ስዕል - ከፒካሶ ስእል በላይ ቅርስ ሆኖ የሰፈሩ መሳቂያ የነበረችን እንስት፣ በሰርግ ቀን ሄዶ ማቀፍ ትርጉሙ ምንድነው? … “የምትናገሪበት አፍ አለሽ!” ከማለት ይልቅ ጆሮዋን በመስጠት አይደል የፈወሰቻት? ለዚያም አይደል ወደ ኋላ ላይ “አባትሽ ጋር ከሚሠሩ ሠራተኞች በምን አንሳለሁ ሎዛ?” የሚል አብርሆታዊ መጠይቅ ማምሻ ያቀረበችው? ሎዛ በጆሮዋ የማምሻን ዲዳነት ፈወሰችው ማለት ይህ አይደል? … ማኅበረሰቡ ሰገራ እንደ ነካ እንጨት ለወረወራት ሴት ማን ጆሮ ያውሳል? … ከወንዶች እኩል እንደምትሠራ እምነት እንዳላት ለአባቷ ነግራ ሥራ በማስቀጠር አይደለ “እምነት የሚጣልብሽ ሴት ነሽ” የሚል መልዕክት ያሰተላለፈችላት? ባዶ ሜዳ “አምንሻለሁ” ከማለት አይሻልምን? የማምሻ አባት “ወንድ ልጅ እስኪገኝ መቆያ ትሁን” ሲል “ማምሻ ቢኾነኝ” የሚል አሉታዊ ትርጓሜ ያዘለ ስያሜ በሰጣት ሴት የገዛ ልጅን መሰየም ትርጉሙ ምንድነው? ስም ውስጥ ንግርት አለ ብሎ በሚያምን ማኅበረሰብ ሎዛ የልጇን ስም ማምሻ ብላ በመሰየም አይደል የማኅበረሰቡን አስተሳሰብ የምትቃወምላት? የልጇን ስም ማምሻ ዳግም በማለት አይደል አሉታዊ ስያሜ፥ ከእርምጃ የሚገታ እግረ ሙቅ እንዳልኾነ የምትነግራት?

ሎዛ - የለውዝ ዛፍ ማለትስ አይደል? … እግዚአብሔር ነብዩ ኤርሚያስን “ምን ታያለህ?” ሲለው፣ “የለውዝ በትር አያለሁ!” በማለቱም አይደል “መልካም አይተሃል!” የተባለው? ማምሻንም ፈጣሪ “ምን ታያለሽ?” ቢላት፣ “ሎዛን አያለሁ!” የምትል ይመስለኛል። “መልካም አይተሻል!” እንደሚላት ጥርጥር የለኝም።

የዐምድነሽ ጀልባ፥ የማኅበረሰቡ ወጀብ፥ የሎዛ መቅዘፊያ እና የዳኒ ደሴት
የማምሻ ሞተር የተነሳው በትብብር ክንድ ነው። ወላጅ እናቷ ዐምድነሽ በየሰው ቤት ተንከራተው አሳደጓት። የሎዛ እብዳዊ መቅዘፊያ ለማምሻ የማኅበረሰቡን ወጀብ የምትጋፈጥበት መሣሪያ ሆነላት። ዳኒ ደግሞ ሙያን አስተምሯት፥ ትዳርን ያህል ጎጆ ቀልሶ ልጅን ያህል ስጦታ አስታቀፋት። የሕጻን ልጅ ውበት በልጅነቱ ውስጥ፥ የወጣት ውበት በአካሉ ላይ፥ የጎልማሳ ውበት በግርማ ሞገሱ እና የሽማግሌ ውበት በልምድና በእውቀቱ መኾኑ የገባው ዳኒ፥ ማምሻን ለማግባት አንዳች አላቅማም ነበር። ዳኒ ነው አናፂነት ያሰተማራት። እንጋባ ሲላት የቀልዱን ነበር የመሰላት። አንቺን የምትመስል ልጅ ነው የምፈልገው ሲል ግራ ገብቷት ነበር።

ቅሪት ስትኾን የጨነቃት እንደ ሴት የምጥ ጉዳይ ሳይኾን የልጇ መልክ ነበር። ገና ተወልዳ እንዳሳቀፏት የልጇን ጾታ ለማወቅ አልጓጓችም። የልጇ ቆዳ በመፍካቱ እና ራሷን ባለመድገሟ ነበር በሐሴት የተዋጠቸችው። ለዚያም ነው ልጇን አቅፋ በደስታ አለቀሰች። እውን ራስን አለመድገም ያስደስታል? … በማኅበረሰቡ ቅቡል የኾነ መልክ መውለድ ማኅበረሰቡን ከመውለድ ይተናነሳል? … ይሄ ተረክ በየቀዬያችን ያሉ ማምሻዎች ላይ ምን ያህል የወል ጥቃት (collective violence) እንዳደረስን ማሳያ አይደለምን? … የደስታዋ ምንጭ “ልጅሽ ቁርጥ አባቷን” ሲሉ መኾን ነበረበት?

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Jan, 02:55


ከሦስት እስከ አምስት ዓመቷ ድረስ በራስ ተነሳሽነት የመሥራት አልያም በተቃራኒው የጥፋተኝነት ስሜትን የምታዳብርበት ወቅት ነው። የብላቴና ዘመን ዕቅዶቿን ለማሳካት በምታደርገው መውተርተር የሚሰጣት ምላሽ ይሄንን ስሜት እንዲገነባ ያደርጋል። እዚህ ጋር ሎዛ የምትባለው ገጸባሕርይ ከልጅነቷ ጀምሮ መሥራት የምትፈልገውን ነገር ያለማንም ከልካይ ትከውን እንደ ነበር በታሪኳ መሐል ተሰንጎ እናገኛለን። ሎዛ ከጥፋተኝነት ስሜት የራቀ ማንነት የገነባችው በአባቷ ምክንያት ነው። በራስ ተነሳሽነት አንዳች ነገር ስትጀምር ከአባቷ ዘንድ ቅቡልነት ታገኝ ስለነበር ከአደገች በኋላም ይሄን የማኅበራዊ ልቦናዊ ጡብ የምናገኘው በአዎንታዊው ኩርባ ነው።

ከስድስት እስከ ዐሥራ አንድ ዓመቷ ደግሞ የተወዳዳሪነት ስሜትን ወይም የበታችነት ስሜትን በማንነቷ ላይ የሚገነባበት ወቅት ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መምህራን ወሳኝ ናቸው። ማምሻ የሞት ሞቷን እስከ ዘጠነኛ ክፍል ብትጓዝም ቀለም ግን ፈጽሞ ሊዘልቃት አልቻለም። በሠራችው ሥራ የበላይነት ስሜትን እንዳትጎናጸፍ ተደርጋ ይኾን? አብርሽ የተባለው ተራኪው ገጸባሕርይ ስለማምሻ ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዲህ ይላል፡- “በፌዝ - ከእኩዮቿ ጋር እኩል የማትቆም - በልጅነቷ የማኅበረሰቡ ግፍ ከብዷት የጎበጠች ወጣት ተፈጠረች።” የተወዳዳሪነት ስሜቷን በየቀኑ ማኅበረሰቡ እየቸረቸፈባት እንዴት ቀና ያለች ሴት ትፈጠር?

ከ12 - 18 ዓመቷ ደግሞ ጥንቅቅቀ ያለ ማንነት የምትገነባበት አልያም ግራ መጋባት የሚሠለጥንባት ወቅት ሲኾኑ ራስን ለመቻል፣ ከጥገኘነት ለመላቀቅ በሚሞክሩት ሙከራ በሚሰጣቸው ምላሽ ላይ ይመሠረታል። ትምህርት አልሆን ሲላት ከድር የተባለው ጫታም ደላላ ጋር ሄዳ፣ ሻይ ቤት እንዲስያስቀጥራት ስትነግረው፣ “ማምሻ … በዚህ ፊት አስተናጋጅነት…” ብሎ ተዘባበተባት። ቆየት ብላ የቦኖ ውኃ ቀጂነት ሥራ አገኘች። ግን እምብዛም አልቆየች። “ውኃ አታፍስሱ!” ብትላቸው እያሸሞሩባት ቁጡ አደረጓት። አንድ ቀን አንዷ ላይ ተከምራባት እልኋን ተወጣችባትና ከሥራ ተባረረች። ቤቷ ተከተተች። ጥንቅቅ ያለ ማንነት በሚገነባበት ዘመኗ የግራ መጋባት አስኬማ ደፍታ መነነች።

እስኪ ደግሞ ለንጽጽር ሎዛ ጋር እንሂድ። ሎዛ በአባቷ ምክንያት የተወዳዳሪነት ስሜቷ ላቅ ያለ ስለኾነ ባለጽኑ ማንነት ሆና እናገኛታለን። በዐሥራ-ቤቴ ዘመኗ ዩኒቨርስቲ ስትገባ የተፈጠረው ክስተት ለዚህ ትልቅ አስረጅ ነው። “እብደትን አትማሪያትም!” በሚል ንግግር እናቷን ጨምሮ ከሁሉም ሰው ዘንድ ተቃውሞ ገጠማት። “ሁሉም ተቃውመውኝ እኔ ብቻ ልክ ልኾን አልችልም” የሚል ግራ መጋባት ውስጥ ሳትገባ በጽኑ አቋም የመረጠችውን የፍልስፍና ትምህርት እንደተማረች ከታሪኩ ውስጥ እናገኛለን። የአባቷ ምላሽም እሷን የሚደግፍ ስለኾነ ከመደናበር (Role Confusion) ተሻግራ ወደ ሌላኛው እርከን ትሄዳለች። ወደ መወዳጀት መቻል። በአንጻሩ ግን ማምሻ ለዚህ አልታደለችም። ሎዛ በአባቷ ዘንድ ያላት ቅቡልነት ማምሻን ታህል በማኅበረሰቡ የተገፋችን ሴት ወደ መቀበል አሳደጋት። ግፋ ሲልም ሚዜዋ እስከማድረግ። ከዳግም ጋር ደግሞ ትዳር እስከ መመሥረት።

ከ19 -40 ባለው ዕድሜ ውስጥ የመቀራረብ ስሜት ወይም ራስን የመነጠል ስሜት የሚደረጅበት ነው። ከቅርብ ዘመድ ውጭ ከኾነ ሰዎች ጋር በሚደረግ ዘለቄታ ያለው መስተጋብር ውስጥ በሚኖረው የመሳካት ዕድል የሚወሰን ነገር ነው። ማምሻ የመቀራረብ ስሜት ለመገንባት ዕድሉን አላገኘችም። ከሁሉ ወጥታ፣ ራሷን ነጥላ ቤቷ ተከተተች። ወላጅ እናቷ የሰው ቤት ሠርታ በምታመጣው ፍራንክ የሰቀቀን ኑሮውን ተያያዘችው። ነገር ግን ባቀረቀረችበት ኪሮሽና ክር አንስታ ውብ ዳንቴሎችን፣ አልጋ ልብሶችን፣ የመጋረጃዎችን ጥልፍ ማምረት ጀመረች። ማኅበረሰቡ የማምሻን የእጅ ሥራ ውጤቶች ይሸምት ጀመር። የማምሻን አስቀያሚነት ውብ የእጅ ሥራዋ የዋጠው መሰለ። እናቷን በየሰው ቤት ከመንከራተት አዳነች። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ዘመናዊ የጥልፍ መኪናዎች መጡና የማምሻን እጅ ሰበሩ። ዳግም ወደ ማቀርቀሩ ተመለሰች። እናቷም ወደ ቀደመ ሥራዋ ተመለሰች። ማምሻ በቀቢጸ ተስፋ ዛጎል ተከተተች። እንግዲህ ሎዛ ከዚህ ሁሉ አሉታዊ የማኅበራዊ ልቦናዊ ማጥ ውስጥ ነው ማምሻን መንጭቃ እንድትወጣ የረዳቻት።

በዚህ ታሪክ ውስጥ የኤሪክሰንን ሰባተኛ እና ስምንተኛ ደረጃ እርከኖችን ለማተት ስለሚቸግር በዚህ እናበቃለን።

የመጽሐፉ ርዕስ - ከዕለታት ግማሽ ቀን
ዘውግ - የአጫጭር ልቦለድ መድብል
ደራሲ - Alex Abreham
የኅትመት ዘመን - 2013
የዳሰሳው አቅራቢ - ቢኒያም አቡራ ([email protected])

ጥር 14፣ 2017 ዓ.ም

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Jan, 02:55


ማምሻ በዐምድነሽ ጀልባ ላይ ተቆናጥጣ፣ ማኅበረሰብ የተባለ ማዕበል እያፍገመገማት፣ በሎዛ መቅዘፊያ ከዳኒ ደሴት የደረሰች ብርቱ ተጓዥ ናት። የተረጋጋ ሐይቅ ላይ መቅዘፍ የለመደ ሰው ጥሩ የጀልባ ቀዛፊ አይሆንም፤ በማዕበል የሚናወጥ ቀጠና ጋር ሲደርስ ይዋጣልና። ማምሻ ከልጅነት እስከ ዕውቀት በማኅበረሰብ ማሰሮ ተንጣ ከአናታቸው ላይ የወጣች ንጹሕ ቅቤ ናት። ማምሻ ኮብልሎ የሸሻት አባቷ አቶ ቢኾነኝን የምታስከነዳ ጽኑ ናት። ለሚዜነት አትመጥኚም ባዮቹን የሎዛ እናት፣ አባት፣ ፍኖትን፣ አብርሽን … መሳሳታቸውን የሚያሳይ ሕያው ዶሴ ናት። ውኃ እየደፉ ለውጥን፣ ሕይወትን፣ ንጽሕናን የገፉ ማኅበረሰብን ትምህርት የምትሰጥ የምትገለጥ መጽሐፍ ናት።

የሬሳ ሳጥን ሻጯ ማምሻ
የሬሳ ሳጥን ሻጭ በቀቢጸ-ተስፋ የተመላ፣ በሌሎች ጉዳት ውስጥ ትርፍ የሚያካብት፣ ሙያዊ የውዝግብ አጣብቂኝ (ethical dilemma) የሌለበት፥ ግብረገባዊ ውድቀት እንዳስከተለ ሰው ይታያል። በዚህ አጭር ልቦለድ መቋጫ ላይ ማምሻ የሬሳ ሣጥን ሻጭ ኾና ብቅ ትላለች። አብርሽ ለተሰኘው ገጸባሕርይ “ለምን እንደኾነ አላውቅም ግን የሬሳ ሣጥን ስሠራ ደስ ይለኛል” ትላለች። እሷ ተወልዳ ያደገችበት ሰፈር ላይ ያሉ ሰዎች ሲሞቱ የሚቀበሩት እሷ በሠራችው የሬሳ ሣጥን ውስጥ ነው። እውን ማምሻ በሌሎች መጎዳት ውስጥ ትርፍ ማጋበሷ ነው ያስደሰታት?

በኔ አተያይ ማምሻ በፌዝ ቢለዋ የተለተሏት ሐሳቦችን፣ የልጅ ማስፈራሪያ ያደረጋትን አመለካከት፣ የአትችይም መፈክር የያዘውን ሙት ሐሳባቸው የሚቀበርበትን የሬሳ ሣጥን የምታዘጋጅ አናፂ ናት። የማኅበረሰቡን የወል ጥቃት (collective violence) በሷ የእጅ ሥራ እየተቀበረ መኾኑንስ አይጠቁመንም? ታዲያ በዚህ ያልተደሰተች በምን ትደሰት? በሬሣ ሣጥኑ የሚቀበሩት የተቃወሟት፣ ያንኳሰሷት፣ አትችይም ያሏት ሰዎች ሳይኾኑ ሐሳቦቻቸው ናቸው። ሣጥኑን የምትሠራበት መዶሻ እጀታው ወርቃማ በቀል ቢመስልም ቅሉ፥ ቀጣዮቹ ማምሻዎች እንዳይጎዱ መንገዱ ላይ ያሉ ቁሙዱዎችን በጨፈቃ እንደ መጥረግ ያለ ትልም ይነበብበታል፤ ባይ ነኝ።

ማምሻ በገዛ እጆቿ በሠራችው የሬሳ ሣጥን የነገረ - ሴትን አተያይ ለመቅበር ታትራለች። አወዛጋቢው ብሪታኒያዊው ዲ ኤች ላውረንስ ስለ ሴቶች እንዲህ ይለናል፦ "የሴቶች ዋነኛ ችግር ወንዶች ስለሴቶች የሚኖራቸውን ጽንሰ ሐሳብ አሟልተው ለመገኘት መጣራቸው ነው" ብዙ ወንዶች የሚፈልጓትን አይነት ሴት መስለው። ኾነው። ማምሻ በወንዶች ዘንድ ያለውን የሴትነት መስፈርት አታሟላም። በማጌጫ እና በዱቄት ተለብጣ ከመስፈርቱ ልትገባ ስትሞክርም አናይም። መስፈርቱ ግን ምን ይኾን? … ሎዛ መረር ባለው አንደበቷ የምትጠቁመን ይኾን? … "እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ (ወዳሰበችበት) ከመራመድ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትስበከ ኑራለች። … እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መሥራት ነው። … ብዙ የፋሽን እና ዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ 'ዘመናዊ' ሴቶች፣እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽ እና እጃቸው እንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ። … ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠም የማይወደው። … በልስላሴ ሳይሆን በንጽሕናና ራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማንናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?! … ማምሻ ቆንጆ አይደለችም። ዕጣ ፋንታዋ ዓይንና ጥርሷ ላይ ሳይሆን፣ እጆቿ ላይ እንዳለ ግን ተገልጦላታል። ወንድ በእግሮቿ መሃል ካላለፈ የሚያልፍላት የማይመስላት ሴት አይደለችም።” ትለናለች። ማምሻ በገዛ እጆቿ በሠራችው የሬሳ ሣጥን የነገረ - ሴትን አተያይ ቀብረዋለች ለማለት ምን ይጎድለናል ታዲያ?

የሎዛ እናት ልክ አደፍርስ ላይ እንዳለችው ወ/ሮ አሰጋሽ ሰውን በመደባዊ አተያይ የመመልከት እርሾ አላቸው። ወይዘሮ አሰጋሽ ለአደፍርስ እንዲህ ይሉትም የለ? “ከሰውም ሰው አለው፤ “ከእንጨት መርጦ ለታቦት፤ ከሰው መርጦ ለሹመት” ሲባል አልሰማህም የኔ ልጅ? … አሁን ለምሳሌ አሽከሮቼን ገና ለገና በዝጌር አምሳል ተፈጥረዋል ብዬ ከኔ ጋር እኩል ናቸው ልል ነው? የለም የኔ ልጅ!” ይላሉ ወይዘሮ አሰጋሽ። አርስቶትልም "እኔ ቁጭ ብዬ እንዳስብ ምግብ የሚያበስልልኝ አካል ያስፈልጋል" የሚል መደባዊ አስተሳሰብ ያራምድም የለ? የሎዛም እናት “ታዲያ (ማምሻ) ሰው የኾነች እንደኾነስ? … እግዜር ሲፈጥረን መቸም ቦታ ቦታ አዘጋጅቶ ነው!” ይሉም የለ? ማምሻ እንዲህ ያለውንም አተያይ ሲቀበር እንደ ምታይ በማሰብ ነው የሬሳ ሣጥን ስትሠራ በሐሤት የምትሞላው፤ በኔ አመለካከት።

ማኅበረ-ልቦናዊ ዕድገት በማምሻ ታሪክ ውስጥ
ውልደቱ ጀርመን ቢኾንም በአሜሪካዊ ዜግነት የሚታወቀው ኤሪክ ኤች ኤሪክሰን Identity and the Life Cycle በተሰኘ መጽሐፉ፥ ማኅበረ-ልቦናዊ ዕድገትን በዕድሜ በዕድሜ ከፋፍሎ በስምንት አዎንታዊ እና አሉታዊ ስፍን ያስቀምጣል። "ማምሻ" የተሰኘው የአሌክስ አብርሃም ድርሰት ረዥም ልቦለድ ቢኾን ኖሮ፥ ማምሻን በኤሪክ ኤሪክሰን ትወራ ውስጥ ለስምንቱም ደረጃ የሚኾን ቅንጣት በየአንዳንድ የታሪኳ አንጓ ውስጥ እናገኝ ነበር። "ማምሻ" የአጭር ልቦለድ ዘውግ ስለሆነ ተረኩ እሚነጉደው በጥድፊያ ጎማ ነው። መኾንም አለበት። እኛም በጥድፊያ የሚመለከተንን ሰበዝ ብቻ በመምዘዝ በመጠኑ እንመልከት።

ከውልደት እስከ አንድ ዓመት ከመንፈቅ ባሉ ወራት ውስጥ እምነት ወይም ጥርጣሬ የሚሸመንበት ወቅት ነው። ይሄ በወላጆቿ እጅ ላይ ያለ ብዕር ነው። የተወለደችው ልጅ ተጠራጣሪ ወይም አማኝ እንድትኾን፥ ወላጆቿ የሚጽፉላት የአስተዳደግ ድርሰት ወሳኝነት አለው። የማምሻ ወላጆች እንክብካቤ ሰጥተዋታል ወይስ ነፍገዋታል? ወላጆቿ ማምሻ በተባለች ብራና ላይ እምነት ወይስ ጥርጣሬ ነው የከተቡት? አራስ ጥየቃ የሚመጡ ጎረቤቶች ማምሻን ላለመሳም የሚያደርጉት ሽሽት አባቷ እንዲሸሽ መዋጮ አላዋጣም? አራስ ሕጻኗን ማምሻን ለመሳም አንዳንዱ ሲገደድ፥ ዝግንን ብሏቸው ዓይናቸውን ሲጨፍኑ አባቷ አላየም ማለት እንችላለን? ባያይስ አይገባውም? ማምሻ አድጋ አግብታ ወልዳ ባለቤቷ የኾነው ዳኒ “አንድ ቀን እኔና ልጄን ጥሎን ይጠፋ ይኾን” የሚል ሥጋት እንዴት ተሰማት? ይህ የኾነው አባቷ ጋሽ ቢኾነኝ በልጅነቷ እሷንና እናቷን ጥሎ ጠፍቶ ሌላ ቆንጆ ሴት ስላገባ አይደለምን? በጨቅላነቷ የተዘራባት እምነት ሳይኾን ጥርጣሬ ነበር። ለዚህስ ማኅበረሰቡ የአቅሙን አላዋጣም? የወለዳቻት ልጅ ራሷን ባለመምሰሏ ታዲያ ለምን ማምሻ ተደሰተች? ሌላ ልጅ መውለድን የፈራችው ለምንድነው? ድንገት እሷን የምትመስል ልጅ ብትወልድ የእሷን እግር የተለተለው ቁሙዷዊ የማኅበረሰቡ ጉጠት ልጇንም መራመድ እንዳትችል እንዳያደርጋት አይደል? በማምሻ ሰውነት ውስጥ የሚመላለሰው ደም ሳይኾን ጥርጣሬ አይደል?

ከሁለት ዓመቷ እስከ ሦስት ዓመቷ ደግሞ ራስን የመቻል ወይም የኅፍረት ጡብ የሚገነባበት ነው። ነገርን በራስ ለመከወን በምታደርገው መጣጣር የምታገኘው ቅቡልነት ነገርየውን ይበይናል። ማምሻ የአትችይም ጉጠት ከዚሁ ይሆን የጠቀጠቃት?

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Jan, 12:56


እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ
(አሌክስ አብርሃም)

ጋሽ አዳሙ የሰፈራችን ታዋቂ ሰካራም ከሰሞኑ ለአስራ አምስት ቀናት ጠፍቶ ሰንብቶ ንፍ…..ቅ ብሎን ነበር ….ድንገት ታዲያ ትላንት ማታ ልክ ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ እየፎከረ እየሸለለ ‹‹ እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ›› እያለ ሲመጣ በጨለማው ውስጥ ድምፁን ሰማንና ተሯሩጠን ቲቪ ነሽ ሬዲዮ ነሽ ዘጋግተን ጆሯችንን አቆምን ….. ጨለማው ውስጥ ቁሞ ብቻውን በስካር በተኮላተፈ ድምፁ ያወራል ……ጎርናና ድምፁ በነፍሳት ሲርሲርታና በመንደሩ ውሾች ጩኸት ታጅቦ ሲሰማ በሙሉ ባንድ የታጀበ ቆየት ያለ ሙዚቃ ነው የሚመስለው ….
‹‹ ወደን ነው እንዴ የምንሰክረው …… እዚህ ሰፈር ኳ ኳ ኳ ….አላችሁ ……? መልሱልኛ አላችሁ ወይ ? …… ሃሃሃሃሃሃ አሁንማ አለን ለማለትም ፈራችሁ ! ሃሃ ፍርሃታችን አስራ አንድ ነጥብ ምናምን በመቶ ጨመረች ……የራሳችሁ ጉዳይ! እኔ ደሆንኩ አለሁ ! ሃሃሃሃ … በደንብ አድርጌ አለሁ ! ገና እኖራለሁ ! በመኖሬ ደስተኛ ነኝ .....መኖሬ የሚያስከፋው ካለ ‹‹ በሊማሊሞ ገደል ›› ….ብለዋል የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ….. ገደል የሚጠቁም መሪ አያሳጣን …… ሃሃሃሃሃሃ ደሞ እሳቸው የጀመሩትን ብላችሁ ገደል እንዳታስገቡን …… !!
እና አላችሁ ወይ ስል ምነው ሰፈሩ ዝዝዝዝም አለ ? እኔኮ ግርም የሚለኝ ‹‹አላችሁ ወይ ›› ስትባሉ ጭጭ ትሉና ሌላ ሰው ‹‹አለሁ ›› ሲል ‹‹ከማናባቱ በልጦ ነው የሚኖረው ›› ብላችሁ እምቧ ከረዩ የምትሉት ነገር ሃሃሃሃ ኑር ሌሎች እንዲኖሩ አድርግ ይላል ሞፈክሩ … ሚስኪን መፎክር ፀሃፊ ልባችንን ባያውቃት !
እናተ የላችሁም መሰል ….. ቆይ ታዲያ እዚህ ሰፈር ያለው ምንድን ነው ……ይመስገነው … እዚህ ሰፈር ምንም የለ !! ሂሂ.... ኢቦላ የለ …. ውሃ የለ ….መብራት የለ …… ሰው የለ …. ተቀዋሚወች ደሞ ‹‹ፍትህ የለ›› …ይላሉ …መንግስት ደሞ ‹‹ተቀዋሚ የለ›› ይላል ….እሽ ማነው ያለው ? ምንግስት እኮ ግራ ቢገባው ነው ‹‹ አለ በጀምላ ›› ብሎ ሱቅ ያስከፈተው …..ሃሃሃሃሃ ….. አዳሙ ብቻ አንድ አገር ይዞ ብቻውን ይኑር ? ? ይችን በምታክል ‹‹የሶስት ትሪሊየን›› አመት ታሪክ ባላት አገር ብቻየን ልኑር አላሳዝናችሁም ? ››
ወደው አይደለምኮ አለቃ ገብረሃና የተናገሩት ……እንደኔ ግራ ቢገባቸው ነው …… አፈር ስሆን ስሙኝ ! አመት አላወራ …ስሙኝ ….ለነገሩ ደርግም <<አመት አላወራ>> ብሎ የመናገሪያ ሰገነቷ ላይ ከወጣ በኋላ ነው አስራ ሰባት አመት ያወራው ! አሁንም <<አመት አናዋራ እስከዚችኛዋ ምርጫ የማሪያም መንገድ>> … እያሉ ነው ሃያ ሶስት አመት ያወሩብን ….. ቢሆንም ግዴለም ስሙኝ ተረቱን ……..
እና …..አለቃ ገብረሃና ነበሩ (መቸም ‹ነበሩ› እንወዳለን እራሳችን አንኖርም እንጅ ) እና ሲኖሩ ሲኖሩ በአገሩ ረሃብ ገባና ህዝቡ ቅጠል መብላት ጀመረ አሉ ….ሰንሰል ነሽ …ጉሎ ነሽ …ግራዋ ነሽ ፅድ ነሽ ሙጃ ነሽ ሳር ነሽ … እንክት አድርጎ በላው ህዝቡ !! …የራበው ህዝብ አንበጣ ነው .... የማይበላው ነገር የለም ….መሪውን ሁሉ ይበላል ይላሉ ‹ተቀዋሚወች› ሃሃሃሃሃሃ ….ምናቸው ይበላል አንጆ ሁሉ,,,, ( አዳሜ ክትፎ ጥብስ የምትይው አባቶችሽ ቅጠል በልተው …መሪም በልተው ባቀኑት አገር ነው )
እና ….ያ የችጋር ቀን አለፈና የጥጋብ ቀን መጣ …አለቃና ጎረቤቶቻቸው ተሰብስበው እየተበላ እየተጠጣ ሲያወሩ ሁሉም ትላንትን ረስቶ ጉራውን ይቸረችረው ገባ
‹‹እኔ በዛ ችግር ወቅት ህዝብ ሲራብ ጎተራየ አበባ በመሰለ ጤፍ ሞልቶ ነበር ›› ይላል አንዱ ጉረኛ …ሃሃሃ
ሌላው ‹‹ ጎተራየ ገብስ በሽበሽ ነበር›› ይላል …
‹‹ እኔስ ብትል ባቄላ ሞልቶኝ መጣያ አጥቸ ›› እያለ ይወሸክተዋል ጉራውን …..አለቃ ታዲያ ግርርርርርርም ብሏቸው ጮክ ብለው ጓዳ ለምትንጎዳጎድ ሚስታቸውን እንዲህ አሉ አሉ ….
‹‹ እንች ማዘንጊያሽ ….በዛ ክፉ ቀን የድፍን አገሩን ቅጠል እና ሙጃ እኔና አንች ብቻ ነበርን ለካ በልተን የጨረስነው ›› ሃሃሃሃሃሃ
የሰፈሩ ሰዎች ሳቃችንን አፍነን በጉጉት ጋሽ አዳሙን እናዳምጣለን …..
‹‹እስቲ አሁን ማን ይሙት እግር እስኪቀጥን በአዲስ አበባ ቢዞሩ…. በክልል ቢዞሩ ….በአፍሪካ ቢዞሩ (አ…..ይ አፍሪካ እንኳን ራሷ ዙሮባት ምን ታዞራለች ሃሃሃሃሃ) እና በአለም ቢዞሩ ….በሌላ ፕላኔት ቢዞሩ እንደዚህ እንደኛ ሰፈር ውብ ሰፈር አለ ? በ………ጭራሽ !! ይሄ ሰፈር ማለት እኮ እትብቴ የተቀበረበት … አየሩ ብትሉ ….ውሃው ብትሉ …. ኔትዎርኩ ብትሉ …..የፈለጋችሁትን ብትሉ …. ሲያምያራችሁ የሚቀርበት ሰፈር እኮ ነው …… !
ምን ዋጋ አለው እነ አረጋሽ ለልማት ይፈርሳል እያሉ ያስፈራሩናል …..ለነገሩ ይፍረስ …ድሮስ መቸ ኖርን ! ይችን ሶስት ከተማ ወደሁለት እናምጣት ነው ያሉት ሰውየው … ባይሉትም ኑሮው ራሱ እንኳን መንደሩን ሰውን ራሱን ሁለት እያደረገው ነው .... እውነቴን ነው ሰው.... ሁለት ሁኗል እዚህ በጆሯችሁ ሌላ ነገር አውርቶ እዛንኛው ሰፈር ሌላ …አስር ጓደኛ ካላችሁ ሃያ ብላችሁ ያዙት ሰው ሁለት ሁኗላ !
ለነገሩ አይፈረድበትም አንዱን ሰው ብትሰሙት የሁለት ሰው ምሬት ነው የሚማረረው … ባንዴ ለሁለት ጉዳይ የሚሰለፍ ትውልድ ነውኮ ….…ይሄ ነገር በዚሁ ከቀጠለ ከጀርባው የገዥው ፓርቲ ምስል ከፊት የተቀዋሚ አርማ ያለበት ቲሸርት የለበሰ ሰላማዊ ሰልፈኛ መስቀል አደባባይ ማየታችን አይቀርም ! ‹‹ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች ›› ሀሃሀሃሀሃ ቀድሞ ሙችና ሰደቃሽ ይውጣ አሉ ….መጀመሪያ የሚተነተን ፖለቲካ ሲኖር አይደል ሃሃሃሃሃሃ አንዱ ሰውየ ….እዚህ ታክሲ ተሰልፎ እየጠበቀ እያያችሁት እዚሁ ኔትወርክ ተሰልፎ ይጠብቃል ….ይሄ እኮ ነው ሁለት መሆን …… ሃሃሃሃሃሃ
ቡፍ እያልን እንስቃለን ! በየቤታችን !
ሰልፉ በግል ነው ጎበዝ … ተበተን ብትባልም ወዴት ትበተናለህ …. ሰላማዊ ሰልፍ የለም ትላለህ እንጅ አዳሜ ግንባሩ ላይ የብሶት መፎክሩን በመከፋት ቀለም ፅፎ ብቻውን ሰልፍ ወጥቷል ! ስራፈላጊው በእጁ አንከርፍፎ የሚዞረው ፋይል መፎክር እኮ ነው ‹‹ስራ ለሰሪው ›› የሚል ….›› ጋሽ አዳሙ ዝምምም ብሎ ይቆያል በቃ ወደቤቱ ሄደ ብለን ወሬ ስንጀምር
‹‹እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ›› ብሎ በጩኸት ያንባርቃል! በሳቅ እናውካካለን …ጋሽ አዳሙ ሃሳቡም ንግግሩም እዚህና እዚያ እየረገጠ ይቀጥላል …..
‹‹ ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው ›› አለች አሉ አንዲት አርቲስት በቀደም የምታሳየው ፊልም ታግዶባት ሃሃሃሃ …የት ትሄዳለች … ኗሪውን እያሳቀቀች ታባርር እንጅ ! እውነቴን ነው … አንዳንዴ ኑሮን ለማሻሻል ሳይሆን ዜናም ለመስማት ስደት እስክንመኝ ድረስ ዜናው ስልችትትትትትትት ይለናል !

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Jan, 12:56


ባስራ አራት ኢንች ቴሌቪዥን አስራ አንድ ነጥብ ምናምን ፐርሰንት እድገት.. እድገቱ በዚሁ ከቀጠለ የቴሌቪዥናችን ኢንች ሳያድግ እድገቱ እስክሪኑን ሞልቶ ሊፈስ ነው …. ኧረ እድገታችን ቴሌቪዥናችን ጠበበው ..እስቲ ቴሌቪዥናችን ጋር የተመጣጠነ እድገት እንደግ.....ለነገሩ መንግስታችን ብልህ ነው …በየመንገዱ ዳር ባለትልልቅ ሶኒክስክሪን አስቀምጦልናል … ‹‹አለ በጅምላ በዜና መልክ›› መሆኑ ነው ሃሃሃ….
ችግር ነው በታዳጊ አገር መኖር ….አሁን ማን ይሙት አዳሙ አሜሪካ ሂዶ ‹‹ የአገሬ ዜና መረረኝ ዜናችሁን ልሰማ መጥቻለሁ የዜና ጥገኝነት ስጡኝ ›› ቢል ማን ይሰመዋል …..እና ይሄ ሁሉ በየጣራው ላይ የቆመ ዲሽ ምን መሰለሽ ህዝቡ የዜና ጥገኝነት ጠይቆ እየተሰደደ እኮ ነው ሃሃሃሃ.... ኦባማ እንደሆነ ማጣፊያው አጥሮታል ….ጥቁር ፕሬዝዳንት ብለው ያሞካሹት ሁሉ ፊታቸውን አጥቁረውበታል !
ዜናው ከማሰልቸት ሲመለስ አሳቃቂ ….የትውልዱን ቁልቁል እድገት አኮ ነው የሚያሳየን …ድሮሮሮ ንጉሱ ብቻቸውን ዙፋን ላይ ቁጭ አሉና ‹‹አንድየ አንድየውኑ ሹሞናል ›› ብለው … እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ሲሉን ….የትውልዱን የዘመን እሳቤ እግዜር ጋር አስተሳስረው አሳዩን …..ይሁና ብለን ሰገድን ! ጎንበስ ብለን ቀና ስንል ንጉሱ ዙፋናቸው ላይ የሉም …. ደርጉ ሰብሰብ ብሎ መከረና ንጉሱን በወታደራዊ ጫማ ከነዙፋናቸው በካልቾ ብሎ ሲያበቃ ተሰብሳቢውንም አንድ በአንድ ፈጅቶ እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ሲለን መድፍ ቀረሽ ሰላምታ ሰጥተን ተረግጠን ተገዛን … እምቢ ያሉትን እንደቢንቢ በጥይት ፊሊት አረገፋቸው …….
ኢሃዴግ መጣና ‹‹አምስት ሁነን ጫካ ገብተን ፋሽቱን የደርግን ጨካኝ አገዛዝ ገረሰስን በደማችን ነፃነትን ዋጀን እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ›› ሲለን ‹‹የማያልፉት የለም ›› እያልን ተቀበልን …….አረረም መረረም …ከፋም ለማም … ሁሉም አንድም ሁነው ነገሱ ደርግም ሁነው ተነካከሱ ወላ አምስትም ሁነው አገዛዝ ገረሰሱ ያው የትውልዱ ውጤቶች ናቸው….ነበሩ !!
ዛሬስ ……..ይሄ በጫት የነበዘ በመጠጥ የደነዘዘ አይኑን እያጉረጠረጠ የወሲብ ፊልም ላይ አፍጥጦ የሚውል አሸን ከትውልዱ መሃል እንደአረም እያቆጠቆጠ እራሱንም ለመሃበረሰብ ጠንቅ መሃበረሰቡንም ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና እንዲሰማ አደረገው … ከዩኒቨርስቲ ወጥተን አምስት ሁነን ጫካ ገብተን ጨካኙን አገዛዝ ገረሰስነው ….የሚል ታሪክ ለአንድ ሚሊየነኛ ጊዜ ልንሰማ ዜና ስንከፍት
‹‹ አምስት ሁነው ወደሽሻ ቤት የሸፈቱ ጎረምሶች አንዲት ፍሬ ልጅ ደፍረው ለሞት እንዳበቋት ነግሮን ቁጭ …. የዘመናችን ስፍር ነዋ ! ከትውልድ የሚመዘዙ በጎ ሰሪዎች ‹‹የኛው›› እንደሆኑ ሁሉ ትውልዱን ያሸማቀቀ ድርጊት አድራጊወቹም ‹‹ ከኛው ›› ናቸው ! ሴት ልጅ ሚስት ናት… እናት ላይ እያልሽ እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ቃል ለመቀመር ትሮጫለሽ …..ትላንት ‹‹ምናለበት›› እያልሽ ያናናቅሽው ሽሻ ይሄው እንዲህ አይነት ትውልድ ያመርታል …..ትላንት ምናለበት እያልሽ ‹የገባኝ አሪፍ › ነኝ ለማለት ያናናቅሽው አደንዛዥ እፅ ይሄው ዛሬ እንዲህ ራሳቸውን እንኳን መከላከል የማይችሉ ህፃናት ላይ ክንዱን ሲያሳርፍ !
ልጅቱን ማን ደፈራት ??
…አምስት ጎረምሶች ብቻ መሰሉሽ ? አሄሄ ግዴለሹ ህዝብ በሙሉ !! ቤቱን አከራይቶ ሽሻ ቤት ያደረገው …..ዩኒፎርም የለበሱ ታዳጊወች በየመጠጥና ጫት ቤቱ ሲኮለኮሉለት እየገለፈጠ ‹‹ምናገባኝ ያለው ›› በየአጥርሽ ስር እድሚያቸው ያልደረሰ እንቦቀቅሎች ዩኒፎርማቸውን ለብሰው አጉል ነገር ሲያደረጉ እያማተብሽ ያለፍሽ ሁሉ …… ትላንት ስለሱስ ሲወራ ‹‹አካበዳችሁ ›› ያለው በሙሉ ! ‹‹ አራዊቱ ›› ሚሊየን ነው …. ጫካው ፊቱ ሲመነጠር ተኝቶ ከርሞ ታዳጊዋ ችግኝ መቀጠፏን በዜና ሲሰማ ኡኡታውን ያቀልጠዋል …. አራዊቶቹ የሚወለዱት ያው ከአራዊት ነው ››
ጋሽ አዳሙ ምርር ያለ ድምፁ እየራቀ እየራቀ …ሄደና በመጨረሻ ከሩቅ በሚሰማ ድምፅ እንዲህ አለ ………
እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ እጅሽ ላይ ደም አለ !!

______________
የ2014 ፖስት

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Jan, 08:26


ለዛሬ ቅዳሜ የፃፍኩላችሁ በጣም እያሳቀ የሚያስተምር ቆንጆ ፅሁፍ በአንዳንድ የግል ችግር ምክንያት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ስላልቻለ እንዲሁ በእምነት እየሳቃችሁና እየተማራችሁ እንድትውሉ በአክብሮት እጠይቃለሁ! እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Jan, 16:43


የተማረ ይዝናና በእውነት🤔

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Jan, 15:46


ጓዶች የአሌክስ አብረሃምን Official የTelegram Channel ከታች ባለው ሊንክ Join አድርጉ።

https://t.me/officialalexabreham

አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው!!!

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Jan, 08:10


10:00 ሰዓት አራት ኪሎ ዋልያ ቡክስ!

ፌስቡክ ከሰጠን የጥንት የጧት ወዳጅ አንዱ አህመድ ሁስ(ሻድ) ዛሬ 10:00 ሰዓት አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ ቡክስ "የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" የሚል ረጅም ልብ ወለድ መፅሐፉን ያስመርቃል። ተመልከቱ የሚገኙትን እንግዶች!
እንኳን ደስ አለህ ጓድ🙏

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Jan, 05:28


የተጫረ ክብሪት !
(አሌክስ አብርሃም)

ሴቶች ግን አንድ ባለጌ በወረወረው ድንጋይ እንደመስተዋት ሞራላችሁ ከሽ የሚለው ለምንድን ነው? መልሱን እንኳ የማውቀው ይመስለኛል አጀማመሩ ቢቸግረኝ እንጅ! አንዲት ከብረት የጠነከረች ጓደኛ አለችኝ! በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተመርቃ ስራ አጣች። ጎበዝ ቆንጆ ቅን ! ጓደኞቿ እንሰደድ ሲሏት አገሬ ላይ ሰርቸ እቀየራለሁ ብላ ቀረች፤ ወንዶች ለጋብቻ ሲጠይቋት ፣ አግብተን ውጭ እንውሰድሽ ሲሏት ህልም አለኝ ብላ ክችች አለች። "ተኝተን አብረን ማለምኮ እንችላለን" ያላትም ነበር። ብቻ እንደምንም ሳንቲም ተበዳድራ ትንሽ የልብስ ሱቅ ከፈተች! የሚበዛው መደርደሪያ ባዶ ቢሆንም ቀስ ብሎ ይሞላል በሚል ተስፋ ጠበቀች። እንኳን መደርደሪያው ሊሞላ ገቢወች ያከናነቧት ግብር እሷንም አጎደላት ጭራሽ! ያኔም ሐዘን እንጅ ተስፋ መቁረጥ አልጎበኛትም!

ሱቁ የሴት ልብስ መሸጫ ቢሆንም ሲያደርቋት የሚውሉት ግን ወንዶች ነበሩ። የልብስ ዋጋ ሳይሆን የእርሷን ዋጋ የሚጠይቁ ጅል ወንዶች። ብዙ ወንዶች ሱቅ ውስጥ የቆመች ቆንጆ ሴት በድርድር የምትሸጥ ዕቃ ትመስላቸዋለች። እና አንድ ቀን አንድ ባለጌ መኪናውን ሱቋ በር ላይ አቆመና እየተጀነነ ገባ ። ለወጉ እንኳን ዕቃ አልጠየቀም። " ለምን ዘግተሽ ምሳ አንበላም ?" አላት በንቄት ሱቋን እያየ። አንድ አንድ ሲባባሉ ድርቅናዋ አበሳጨው "ሁለት ሱሪና አንድ ቀሚስ ሰቅለሽ የተቀመጥሽው የእውነት ልብስ ለመሸጥ ነው?" ዝም አለች። "አጥበሽ ያሰጣሻቸውን ልብሶች የሞትጠብቂኮነው የምትመስይው፣ ይሄን ውበት ካልሰራሽበት እዚህ ተቀምጠሽ ወንድ ከምታማልይ ለምን በሞያሌ በኩል አትሰደጅም?"

ደወለችልኝ ይሄን ሁሉ አወራን እና " እንደው ተሳክቶልኝ ብሰደድ ትቀበለኛለህ?" ጭራሽ ይህን ካለችኝ በወራቶች ውስጥ ሁለታችንም የምናውቀውን ባለጌ ሀብታም ልታገባ መሆኑን ሰማሁ። አልነገረችኝም ሰማሁ። የነገሩኝ ሰወች ምናሉ...አፈሰች! እሷ ድሮም ብልጥ ነበረች... የነዳጅ ጉድጓድ ቤቷ ፈለቀ! ሁሉም ወሪያቸው ቅናት እና መጎምጀት ነበረበት አንድም ሰው ስለሰውየው አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ባህሪ አላወራም! የነዳጅ ጉድጓድ ውስጥ የተጫረ ክብሪት ጋር በጋብቻ ለመኖር ፣ የራሷን የተስፋ ሻማ አጥፍታ መወሰኗ ለብዙሀኑ ((((ዕድል ነበር)))) በዛም በዚህም መስመሩ ቆንጆ ሴቶችን ወደአልጋ የሚያደርስ ነው? ምን አይነት ክፉ መሀንዲስ ነው ማህበረሰብ ይሉት ቀያሽ?!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Jan, 17:07


ደስ ዝብል እዩ! ናብ ካልእ ቋንቋታት ዝትርጉም ሰብ እውን ንጽበ ኣለና። ነዚ ቆልዓ ዝፈልጦ ኩሉ የቐንየልና።😀

"ለግዜር የተላከ ደብዳቤ" የሚለውን ግጥሜን እንዲህ በትግርኛ ተርጉሞ አቅርቦታል። በየቋንቋው እንለምነው እስኪ!

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Jan, 14:21


ብዙወቹ ሰነፍና ስራ ጠል መሆናችንን የሚነግሩን "ሐብታሞች፣ የስራ ፈጠራ አሰተማሪወች፣ ...አነቃቂወች፣ የሐይማኖት ሰወች " ሀብታም የሆኑበት አጋጣሚ፣ የተጣበቁበትን የዘር ፣የሐይማኖት፣ የፖለቲካ እንዲሁም የሙስና መንጠላጠያ ወደጎን አስቀምጠን በሉ እኩል እንደህዝቡ ያለምንም ልዮ ድጋፍና አድሎ በምክራችሁ መሰረት ሰርታችሁ አሳዮን ብንላቸው "ጥሩ ለማኝ" እንኳን መሆን የሚችሉ አይደሉም! ልክኮ ያለፉበትን መንገድ ሌላው እንዲያልፍበት ያመቻቹ ነው የሚመስሉት።
ምድረ ማሳለጫ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Jan, 08:26


!!

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Jan, 04:21


እናቶችን ማማታችንን እንቀጥላለን😀

ይታመማሉ(ሲሪየስ ህመም)! ከዛ ተጨንቃችሁ ተጠባችሁ አልሄድም ይሻለኛል ብለው፣ ለምናችሁ ምርጥ የሚባል ሆስፒታልና ዶክተር ጋር ትወስዷቸዋላችሁ። አሳክማችኋቸው፣ መድሀኒት ታዞላቸው ወደቤት ከተመለሱ በኋላ፣ ጎረቤት ጋር አጠር ያለ ስብሰባ ያደርጋሉ! ከዛስ?

"አይ ይሄ መድሃኒት ይቅርብኝ ፣አረጋሽ በባዶ ሆድ አቦል ቡና ከምንትስ ጋር ሰባት ቀን መጠጣት ንቅል ነው የሚያደርገው ብላኛለች" ሲሏችሁ " ማናት አረጋሽ? " ወይም እንደተበሳጨ ፈረንጅ Who the hell is አረጋሽ?" 😀
" ጎረቤቴ ናታ ! እሷም ባለፈው እንዲሁ አሟት ተሽሏታል፣ መዳኒት ይለምዳል፣ እዛ ታች ሰፈር ባለንቅሳቷ ሴትዮ የሞተችው እንዲህ ይሄን ኪኒና ቅማ ቅማ አንጀቷ ተደፍኖ ነው ብላለች" 😡😡

በቃ ለምን ራሳችሁ ዶክተር አትሆኑም ከአረጋሽ ቃል አትበልጡም! እና አረጋሽ መንገድ ላይ ምንም እንዳልተፈጠረ "አንተ ሰላም ሳትለኝ ልታልፍ ነው? ተጎረመሰና ተሞተ" ስትላችሁ "ወይኔ በላቸው!"😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

22 Jan, 18:45


አረጀሁ መሰል የዚህ ዘመን ነገር አልገባህ እያለኝ ነው "የእኔ ቆንጆ አደግሽልኝ" ከሚል ካፕሽን ጋር የልጁን ሰውነት (ጨዋ ልሁን ብየ ነው)  ከኋላ ፎቶ  አንስቶ የሚለጥፍ አባት እያየሁ እንዴት ነው የሚገባኝ? ነገሩኮ የልጅቱን የሚያምር ቅርፅ ማየት እኛም አንጠላም 😀 ግን...ብቻ አገራችንን ሰላም ያድርግልን😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

22 Jan, 14:39


ታፕ ታፕ ፌስቡክ ላይ ማን አይሰራም አላችሁ?!

እውነቱን ለመናገር አብሮ በመስራትና አብሮ በማደግ ረገድ የፌስቡክ ታዋቂ ሰዎች ከቲክቶከሮች እግር ስር ቁጭ ብለን መማር ነው ያለብን! «ታፕ ታፕ » እያልን የምንቀልድበት ነገር ለፌስቡክም አሳምሮ የሚሰራ፣ ተስፋ ቆርጦ በየጥጋጥጉ አካውንቱ አድርቶበት የተቀመጠውን ሁሉ የሚያነቃቃ አስገራሚ አብሮ የማደግ ኮንሴፕት ነው። ብዙዎች ልመና ነው፣ ምናምን እያሉ የፈጠሩት ማጣጣል የሁላችንንም አዕምሮ ዘግቶታል።

ለምሳሌ አንድ ጎበዝ ገጣሚ፣ወይም የተለያየ ጉዳይ የሚፅፍ ብሎገር ወይም ጋዜጠኛ  ውሰዱ፣ ፌስቡክ ላይ ለዓመታት ፅፏል ተከታዮቹ ቢበዛ ከሰላሳና አርባ ሽ አይበልጡም!(አጋንኘው) ከዚያ መሃል አክቲቭ የሆኑት ምናልባት 500 ከሆኑ በጣም እድለኛ ነው። ይሄ ሰው ፌስቡክ ላይ ያሉ ታዋቂ ሰዎች ፣ አንባቢዎቹ ጓደኞቹ በአንድ ላይ በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን አንድ ቀን ብቻ ወስደው (አንዲት ቀን) ሰዎች እንዲያውቁት በየራሳቸው ቢፅፉ ስራዎቹን ሸር እያደረጉ ቢያስተዋውቁ በቀን በሚሊየን የሚቆጠር ሰው እንዲያየው ማድረግ ይቻላል። ካዩት መሃል ብዙዎቹ ይከተሉታል። በሌላ ቀን ሌላውን እንዲሁ ተረባርቦ ከፍ ማድረግ! ታፕ ታፕ በቅንነት ስታዩት ይሄው ነው!

  ሶሻል ሚዲያው የአንተን ፍልስፍና አይሰማም፥ ግልፅ የሆነ አልጎሪዝም አለው። ብዙ ሰው ካየህ ለሌላ ብዙ ሰው እንድትታይ ያደርጋል! የማንም ሰው ፍላጎት ተሰጥኦውን ማውጣት በሌሎች እንዲታይለት ማድረግ መወደድ መደነቅ እንዲሁም ጠንካራ ከሆነ መተቸትም ነው! እንደው እውነቱን እናውራ እንደልፋታችን እንደምንሰዋው ጊዜና ኢነርጅ በዚህ ሁሉ ዓመት አንድ እንኳ ሚሊየን ቤት የገባ ፎሎወር ያለው ፀሐፊ አለመኖሩ አይገርምም? ኧረ ግማሽ ሚሊየን የለም! ጭራሽ አንዱ የሌላውን ስምና ዝና እንዴት እንደሚንደው ነው የሚያልመው! አጋጣሚ ጠብቆ አፈር ድሜ ማስበላት! ላይክ ላለማድረግ እራሱ ጋር እልህ ነው የሚጋባው! ለምን ብትለው መልስ የለውም! ወይም የሚያስመስልበት ምክንያት ይፈጥራል!የአስተዳደግ ይጉን፣ ድህነታችን ያመጣብን ጣጣ ራሳችንም አናውቀውም! በጣም መራርና ክፉዎች ነን! ከራሳችን በስተቀር ሌላው ተራ ቁም ነገር የሌለው ለክብራችን የማይመጥን ነው (ለየትኛው ክብር የሚለው እንዳለ ሁኖ)

እኔ በበኩሌ ምንም ሸም አይዘኝም! ፅሁፌን ከወደዳችሁ ደስ ካላችሁ ለተከታዮቻችሁ ለጓደኞቻችሁ «ፎሎው አድርጉት አንብቡት» ብላችሁ ብታስተዋውቁኝ ደስ ነው የሚለኝ!ሚሊየኖች ቢያነቡኝ ደስታየ ወደር የለውም!  እኔም ቁጥር ስፍር ለሌላቸው ገጣሚዎች፣ ደራሲያን የፌስቡክ ብሎገሮች ይህን ሁሉ ዓመት ሳደርገው የኖርኩት ይህንኑ ነው! ተመልከቱ ቲክቶክ ላይ ስራቸውን ማስተዋወቅ ብቻ አይደለም አብረው ስላወሩ ስለተሳሳቁ ብቻ በዶላር ጊፍት እስከመስጠት ይሄዳሉ! ምንድነው ያደነዘዘን? መፅሐፍ ስናሳትም፣ የፈረደበት ዩቲዩብ ስንከፍት፣ ወይም የሆነች ፊልም ስንሰራ ፖድካስት ስንከፍት  ለዓይናችን የጠላነውን ሰው ለዓመታት ሲደክም ያላገዝነውን ሰው እንደአንጀት የረዘመ ሊንክ ይዘን አስተዋውቅልኝ እንላለን! በነገራችን ላይ ስድብ ነው! አንተን እንደሰው አላይህም ተከታዮች ስላለህ እንጅ እንደማለት! መጀመሪያ ሰውን በስራው በማንነቱ አክብሩ! ሰዎች በሰሯት ትንሽ ስራ እውቅና አክብሮት ተሰጣጡ፣ ላጠፉም ባጠፉት ልክ ተቹ ምከሩ! ሀሜተኞች አትሁኑ! ስማቸውን ከኋላ አታጠልሹ! ሴረኞች አትሁኑ! ግሩፕና አድመኝነት የጅብ ዓይነት ባህሪ ነው!

ከዚህ የሞተ የመፅሐፍ ስራ እንኳን ግሩፕ እየፈጠራችሁ ስትጓተቱ ስታስጠሉ! እደግመዋለሁ ስታቅለሸልሹ! ለዚቹ ከሰርግ መጥሪያ ያነሰ ቁጥር ለምትታተም መፅሐፍ! በግሩፕ ማስተዋወቅ የሌሎችን ማጥላላት!  በተለይ  «ታዋቂዎች»  ምን አዚም ነው የወደቀብን? ምንድነው እንዲህ ግንችር ያደረገን! ኧረ እንቃ! ውስጣችን ያለውን ነገር አፍነነው አንለፍ! እርስ በእርስ ተኮራርፎ የማይነጋገረው ብዛቱ! ምን አደረገህ ሲባል መልስ የለም! መታወቁ ያበሳጨዋል! ስንቶቹ ከአጠገባችን ተለዩ! ይህን ማድረግ ሲያቅተን ቲክቶክ እንዲህ ሆኖ ፣አንባቢ የለም . . .ይች አገር ወደየት እየሄደች ነው?  ከመጎለት ተክትለሃት ሂድና ተመልከት! 

በሉ በዚህ ፅሁፍ የምትስማሙ በየገፃችሁ ሸር አሌክስን ተከተሉት አንብቡት በሉ. . . አዎ ብዙ ሽዎችን ጥሩ! አካውንታችሁ የሆነ የተቀደሰ መልዓኮች ብቻ የሚረግጡት አታስመስሉት ! ብዙ ተራ ወሬ እልቂት ፌዝ ስትለጥፉ ነው የምትውሉት! ሌሎች የሚጠቀሙ ሲመስላችሁ አይተናነቃችሁ!  በሳምንት አንዲት የምትወዱትን ደራሲ ወይም ሌላ የጥበብ ስራ የምታስተዋውቁባት ቀን ትኑራችሁ! ቲክቶክ ላይ ብትሄዱ ሰባቱንም ቀን እንደዛ ነው! አብረው ካላደጉ አብረው እንደሚወድቁ ተረድተውታል! ተሰዳድበውም ተዘላልፈውም ታፕ ታፕ ላይ አብረው ናቸው! ቢያንስ ሌላውን ተውትና ከመራር ድህነት እየቀለዱ ወጥተዋል! እኛ በቁም ነገር መውጣት አቅቶን ዛሬም እንደአሳማ በየራሳችን ጭቃ እንዳጎነበስን ነን!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

21 Jan, 17:02


ልጆች ለደሀ ቤተሰቦቻቸው ውድ ሶፉ ገዝተው እናቶች ግን የሆነች ኩርሲ ላይ ወይም ምንጣፍ ላይ ምናምን የሚቀመጡት ነገር😀 በቃ በቀላሉ አይዋሀዳቸውም! እና ሰበባቸው "እኔ እዛ ላይ አልንጠለጠልም ወገቤን እና እግሬን ራሴንና ዓይኔን ያመኛል 😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Jan, 15:40


አሁን ጀምር! ለምሳሌ ስልክህን ክፈትና ምናባቴ ልስራ ብለህ ቪዲዮ ቅረፅ! በቃ ስራው እሱ ነው! የሚሊየኖች ጥያቄ ነው የጠየከው ብሮሮሮሮሮሮ!😀

ወንድሜ! "በዚህ ዘመን ቆንጆ ሴት ካልሆንክ ማንም ዙሮ አያይህም" እያልክ ስለምን ትቆዝማለህ? ስለምንስ "አፈኞች፣ የተማሩ፣ ዘመድ ያላቸው ናቸው ደህና ቦታ የሚደርሱት ትላለህ? ይህ ሁሉ መላ ምት ስንፍናህና ፈሪነትህ የፈጠረው ሰበብ አይደለምን? ይገባኛል አንዳንዴ ከየት እንደምትጀምርም ግራ ይገባል። ስማኝ! ይሄ የሞታየውና የምታውቀው ሰው ካቢ ላሜ እንደአንተው ግራ የተጋባ ነበር። ሴኔጋል የምትባል ደሃ አገር ተወልዶ የአንድ አመት ልጅ እያለ ቤተሰቦቹ ጋር ወደጣሊያን ተሰደደ ። በትምህርት እምብዛም አልገፋም። እንደነገሩ ደረስ መለስ ብሎ አልሆነለትም መሰለኝ CNC ማሽን ላይ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ (ማሽኑ ድጅታል ከመሆኑ ውጭ በኢትዮጵያ ቶርኖ ቤት እንደሚባለው ነው)

በቀደም ኮቪድ ሲከሰት ፣ ከስራ ተቀነሰ! ደበረው እቤት ቁጭ አለ። ቲክቶክ ላይ ቆንጆወች ሲደንሱ ወይኔ ቆንጆ ብሆን እያለ፣ ወሬኞች ሲያወሩ ወይኔ እንግሊዝኛ ብችል እያለ፣ ዝነኞች ሲዘንኑ ታዋቂ ብሆን ...እያለ! ድንገት ..የሆኑ ሰወች ላይፍ ሃክ ምናምን ብለው ውሃ በብርጭቆ ለመጠጣት ሲሰቃዮ ተመለከተ ! የምን መንዛተት ነው አለና ስልኩን ፊቱ አስቀመጠ፣ ካሜራውን ከፍቶ በብርጭቆ ውሃ ቀድቶ ጠጣ ... ፖሰተው! ሳይባልግ ሳይሰዳደብ ድፍን አለም አወቀው! በቲክቶክ መቶ ሚሊየኖች ተከተሉት! ቀጠለ አንድ ቃል ሳይተነፍስ ስደተኛው፣ ያልተማረው፣ እንግሊዝኛ የማይናገር የማይሰማው፣ አማላይ ቆንጆ የማይባለው ካቢ ላሚ የእውቅና ማማ ላይ ቁጭ አለ። ዛሬ ሚሊየነር የአለም ታላላቅ ሰወች ፊቱን ሲያዮ ገና በፍቅር ፈገግ የሚሉለት ሰው ነው። አትፍሩ ሶሻል ሚዲያው ክስተት ሊያደርጋችሁ ሰዓታቶች ይበቁታል! ሞክሩ ታዮ ተሰሙ ....በጣም አነቃቃኋችሁ እንዴ?😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Jan, 10:32


ዛሬ በመንገዴ ብዙ ህፃናት ባለብዙ ከለር ቾክ ይዘው ሰፊ የኮንክሪት ሜዳ ላይ ሲፅፉ ስዕል ሲስሉ፣ አስተማሪወቻቸውም ሲያበረታቷቸው አየሁና የሆነ ነገር ታወሰኝ! ልጅ ሆኘ በጣም የምወደው ነገር ቾክ/ጠመኔ/ ነበር። ከትምህርት ቤት አስተማሪ አልቃበት የሚጥላት ቾክ ነፍሴ ነበረች። ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ቾክ ያገኘሁት አስተማሪያችን አበባ የምትባል ልጅ ለመምታት ሲወረውር ነበር። በዛ ርቀት አልሳታትም! እናተ የሰው ግንባር እንደዛ ይጮሀል! ቋአአአአ😀 እንኳን የዛን ቀን ዳስተሩን ያልወረወረው። አበባ አለቀሰች ቲቸር ትንሽ ተሳደቡና ሌላ ቾክ አንስተው ወደሰሌዳው ዞሩ! እኔ ግን ያችን ቾክ አንስቸ የሙሉ ጠመኔ ጌታ ሆንኩ። የአንዱ መርገምት ለሌላው ፀጋ ይሆናል አንዳንዴ!

ግን ችግር ገጠመኝ! ጠመኔው ቢኖረኝም መፃፊያ ቦታ አጣሁ! የት/ቤት ሰሌዳ ላይ አይሞከርም፣ወንበር ላይ ክልክል ነው፣ ግድግዳ ላይማ ያሰቅላል ሁሉ😀 የሆነ የሐብታም ቤት ግንብ ላይ የዘበኛው ማሳደድ እዳ ነው፣ ቤታችን በር ላይ ...ሁሉም ቦታ ክልክል! እና ሳድግ ትልቁ ምኞቴ ጥቁር ሰሌዳ መግዛት ነበር! ግን ምን ላይ ነበር እናንተ በቾክ መፃፍ የሚፈቀድላችሁ?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

10 Jan, 17:53


ህይወት አሰፋ ትባላለች። እንዲህ አንብበዋለች። ከአንባቢወቸ ጋር መተዋወቅ አለኝ እሞክራለሁ የምትሉትን ችሎታ ማሳየት የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በፊት እንዳልኩት አጭር ቪዲዮ በኢንቦክስ ብትልኩልኝ ፖስት አደርጋለሁ።

Comment

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

10 Jan, 10:01


መሬት ተንቀጠቀጠ አምላክ ተቆጥቶ፣ሰደድ እሳት ተነሳ አምላክ ተቆጥቶ፣ ጎርፍ እና ወረርሽኝ ተነሳ አምላክ ተቆጥቶ ...ቆይ እናንተን ሆድ በባሳችሁ ቁጥር አምላካችሁም ሆደ ባሻ የሚሆን ነው እንዴ የሚመስላችሁ? ወይንስ እዛ የሆነ ቦታ ያሉት ሰወች ያስቆጡትን ያህል እናንተ አላስቆጣችሁትም? አምላክ እናንተ በምታስቡት ልክ ቁጡና ግልፍተኛ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ይችን ምድር እንደበግ ቆ*ጥ ነበር እስክትፈነዳ የሚጠብሳት። በዚህ ሰዓት በቀን አራት ጊዜ የሚነዝረው ምድር ላይ ሆነን እስኪ አንታበይ! ያውም ኮሽ ባለ ቁጥር እህል ውሃቸውን ቋጥረው የሚደርሱልን በደረሰባቸው መከራ። አማኝ በሌሎች ስቃይ አይደሰትም!!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

10 Jan, 08:06


ጠባብ ዓለም!
(አሌክስ አብርሃም)

"አይደለምና ጓደኛህን አንድ ሰዓት አብሮህ የሚቆይን ሰው እንኳን የግል ንፅህናውን እንዲጠብቅ የመምከር ግዴታና ሀላፊነት አለብህ ! ...ምናገባኝ አይባልም። መምከር ብቻ ሳይሆን ማረጋገጥ መቆጣጠርም አለብህ።" አለኝ ኮስተር ብሎ።
"እንዴ..." ከማለቴ አቋረጠኝና "እንዴ አትበል ለምን በል! እኔ ብዙ የህይወት ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ! ይሄውልህ በሊቢያ በኩል ስንሰደድ ዘራፊወች እኔንና ጓደኛየን ያዙን፤ እግርና እጃችንን አስረው ፒካፕ መኪና ላይ ወረወሩንና ሸራ አለበሱን። ኬላ አካባቢ ሲደርሱ ጬኸን እንዳናስይዛቸው ስለፈሩ መጀመሪያ እኔ አፍ ውስጥ የሚወትፉት ካልስ ፈልገው ጫማየን አወለቁ፤ካልስ አላደረኩም ነበር። ከዛስ.... የጓደኛየን ካልስ አውልቀው አፌ ውስጥ ጠቀጠቁት። አየህ ጓደኛየ ከድሮ ጀምሮ ካልሱን ማጠብ አይወድም ነበር! ግን በውስጤ ታዝቤ ዝም ስል ነው የኖርኩት! ካሳለፍኩት የስደት ህይወት ይልቅ ያ ካልስ መራር ነበር። ንግግሬ ሳይቀር ለአመታት ጥሩ አልነበረም። አለና ተከዘ!😀 ምን ለማለት ነው? የሌሎች ድክመት ፣ የእናንተው ጣጣ የሚሆንበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላልና መምከር መቀየር ቢከብዳችሁ እንኳን በሰው ውድቀት መሳቅ ቀንሱ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Jan, 10:44


እንኳን ደስ አለን🙏

በ 'Facebook' አካውንት ለ13 ዓመታት ብዙ ጉዳዮችን ሳስነብባችሁ ቆይቻለሁ። መፅሐፍ ፅፎ ከማሳተም ውጭ በስራወቸ ከፌስቡክም ይሁን ከሌሎች ፕላት ፎርሞች ሰባራ ሳንቲም አይቸ አላውቅም። በተቃራኒው በእኔ ስራወች ሌሎች ተሻምተው ሲጠቀሙባቸው ነው የኖሩት። አሁን አካውንቴ ሞኒታይዝ ሆኗል። ይሄ ማለት  ፌስቡክ ያስቀመጠውን መስፈርት እስካሟላሁ ድረስ በኮንቴንት ሊከፈለኝ ይችላል እንደማለት ነው። ፌስቡክ ሞኒታይዜሽን ይባላል።

ከእናንተ ምን ይጠበቃል? ከኢትዮጵያ ውጭ ያላችሁ ከታች በፎቶ ባስቀመጥኩት መሰረት ከእያንዳንዱ ቪዲዮ ስር Show your support  የምትል ፅሁፍ አለች እርሷን በመጫን ኮከብ ጊፍት መስጠት ትችላላችሁ። ኮከቦቹ ከገንዘብ አንፃር ያን ያህል ዋጋ ኖሯቸው ሳይሆን  አሁን አካውንቱ ባለበት ደረጃ ፌስቡክ በራሱ ማስታወቂያወች እንዲከፍለኝ የአንባቢወቸን ድጋፍ ያሳያል። ሁለተኛው Follow ከሚለው በተን አጠገብ subscribe የምትለዋን በመጫን በቋሚነት በየወሩ ወይም ለአንድ ጊዜ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በመላክ ድጋፋችሁን ማሳየት ትችላላችሁ። ባጭሩ እንደዮቲዮብና ቲክቶክ ጊፍት መስጠት  ትችላላችሁ።  አገር ቤት ያላችሁ ደግሞ ፅሁፎቸ ደስ ካሏችሁ በመመረቅ በላይክና በኮሜንት ፣ ይች አገር ወደየት እየሄደች ነው በማለት አብራችሁኝ ቆዮ😀 በተረፈ አድርጉም አታድርጉም ወዳጅነታችንም የተሰማንን መካፈላችንም ይቀጥላል!!


ከምስጋና ጋር!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Jan, 09:25


ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ የሚረዳው ቀልድ!

ኑሮ ምን ያህል እንደተወደደ ፣ ብራች ምን ያህል እንደወደቀ ላሳይህ አለኝ አንድ በቅርቡ ኢትዮጵያ ደርሶ የተመለሰ ወዳጀ! ሰፈራችን ትንሽ ሱቅ አለች ከሰባት ዓመት በፊት ወደአሜሪካ ማታ ልበር ጧት ማስቲካ ገዛሁና ለሻጯ ድፍን 10 ብር ሰጠኋት። ተቻኩየ ስለነበር መልሴን ሳልቀበል ሮጥኩ። በዛው አሜሪካ መጣሁ። አሁን ስመለስ እርሷ አልረሳችውም፤ እና መልስ ብላ ሰባ አምስት ብር ሰጠችኝ😀

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Jan, 06:11


"ለግዜር የተላከ ደብዳቤ" ይህን ግጥም ከፃፍኩት 10 አመት አለፈ። ጊዜው እንዴት ይሮጣል። እስከአሁን መድረክ ላይ በተለያየ መንገድ ይተውኑታል። ቲክቶክ ላይ በርካታ ልጆች አንብበው አይቻለሁ። እነሆ አንዱ የደረሰኝ!

እስኪ ከ10 ስንት እንስጠው?

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

08 Jan, 21:29


በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1938 አንድ የከርሰ ምድር ውሃ የሚያወጣ የእርዳታ ድርጅት የሳውዲአረቢያ ደሀ የገጠር መንደር ውስጥ ቁፋሮ እያካሄደ ነበር። የመንደሩ ሰወች ለረዢም ጊዜ በጉጉት ኮዳቸውን ይዘው የውሃውን መውጣት ሲጠባበቁ ኖረዋል። ማሽኑ ሲቆፍር ከበው ይቆሙና ከንፈራቸው ደርቆ በጉጉትና በተስፋ ይመለከታሉ። አንድ ቀን መቆፈሪያ ማሽኑ ከቆፈረው መሬት ውስጥ ሽታው የሚሰነፍጥ ጥቁር ፈሳሽ ቡልቅ ብሎ እየተዝለገለገ ወጣ ። ከዚያ በፊት ታይቶ አይታወቅም። የነዳጅ ድፍድፍ ነበር። ቆፋሪወቹ በግርምት ሲራወጡ የመንደሩ ሰወች ግን እየየ ብለው አለቀሱ "አላህ ተቆጥቶብን ነው ውሃ ስንጠብቅ ይሄን የገማ ነገር የሰጠን" አሉ😀 ከዓመታት በኋላ የመንደሩ ነዋሪወች የሻወር ውሃ ከኒወርክ የሚያዙ ፣ መኪና ስጦታ የሚሰጣጡ፣ የመዋኛ ገንዳ ያላቸው ቪላወች በረሃ ላይ የገነቡ በባህር ላይ በግል ጀልባወቻቸው የሚንሳፈፉ ሞጃወች ሆኑ።

ይሄ ታሪክ በቤንዚን ዋጋ የተደበረ መንፈስህን አላነቃቃውም ብሮሮሮሮሮሮሮ?😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

08 Jan, 19:05


ጭምብላችን አፍኖ ሳይገድለን አውልቀን እንነጋገር!
(አሌክስ አብርሃም)

ፌስቡክ ላይ ያሉና የነበሩ ጋዜጠኛ፣ደራሲ፣ገጣሚ፣ዘፋኝ፣ አርቲስት፣ ተዋናይ፣ ሞዴል ፣ ተወዛዋዢ ወዘተ ያውም በትምህርት ዝግጅት፣ በስራ ልምድ፣ በችሎታ በሙያዊ ድስፕሊን ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ፕሮፌሽናሎች ለምን እንደቲክቶክና ዮቲዮብ ታዋቂወች በኑሮውም በአስተሳሰብም መቀየር አቃታቸው? ለምን ቁመው ቀሩ? ለምን እየፈለጉ መራመድ እልፍ ማለት አቃታቸው? ለምን ከጨዋታ ውጭ ሆኑ? ለምንስ ይሄን ህመም ይደብቁታል? ከዘመኑ በረከት ስለምን ጎደሉ?

ችግሩ የማነው ምንድነው? ፌስቡክ ስለማይከፍል ነው? ዮቲዮብና ቲክቶክ ላይ የሞካከሩት ለምን ተፅእኖ መፍጠር ጎልቶ መውጣት አቃታቸው? እንደውም የነበራቸውን ጣጥለው ከእነሱ ባነሱ ሰወች ተፅእኖ ስር ለምን ወደቁ? የእነዚህ ሰወች ከጨዋታው ውጭ መሆን በግላቸው ከገጠማቸው የኢኮኖሚ ፈተና በተጨማሪ ሶሻል ሚዲያውን በሚያሳዝንና ሀላፊነት በማይሰማውቸው ሰወች እንቶ ፈንቶ እንዲወረር አላደረገውም ወይ? ከገንዘብም፣ ከሚወዱትና ዋጋ ከከፈሉለት ሙያቸውም ከሁሉም አጥተው ተመልካችና አማራሪ የሆኑት ስንት ናቸው? አያሳዝንም? የሬዲዮ ቀን የጋዜጠኞች ምናምን ሲከበር ሄድ ፎኑን ገድግዶ ፎቶ የሚለጥፈውን ሰው ብዛት ቁጠሩት፤ የት ሄደ ያ ሁሉ?

ምንድነው ችግሩ? ለወራት የታዘብኩትን በሰፊው ፅፊያለሁ። በቅርቡ ከፋፍየ እለጥፈዋለሁ። የእውነት የማስመሰልና የመደባበቅ ጭምብላችንን አውልቀን መነጋገር መወያየት ዘመኑን መዋጀት ያለብን ይመስለኛል። ለማንም ስል አይደለም፤ እንደሰው ስነፅሁፍ አርት እንደሚወድ ሰው እነዚህ ሰወች የሚለምኑባት አገር የሚሳቀቁባት፣ ለማየት ለመስማት የሚቀፍ ዝቃጭ በጥበብ ስም የሚደፋባት አገር ማየት ያሳዝነኛል። ማንም በስራው ሌሎችን በሞራልም በእውቀትም ከፍ አድርጎ ዋጋ ባለው ስራ ከፍ ሲል ሲሳካለት ማየት እመኛለሁ።

በበኩሌ በወራት ውስጥ ሚዲያው ብቃት ባላቸው ባለሙያወች በበቂ መጠን እንዲያዝ ማድረግና ተፅእኖ መፍጠር ይቻላል የሚል ተፈትኖ ያለፈ ምክንያት አለኝ! ሜዳው ለሁሉም ክፍት ከሆነ እግራችንን አልያም ፈረሳችንን መመርመር አይሻልም? ምንድነው የሆነው? ምናልባት እርስ በእርስ ላትግባቡ ትችሉ ይሆናል ማንም ከጥሪው ጋር፣ ከህመሙ ጋር አለመሰማማት ግን አይችልም! ተገፍታችኋል ወይስ ጎታች እስኪጎትታችሁ ቆማችሁ ነው?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

08 Jan, 17:33


ስራ ቦታ አንዲት ህንዳዊት ጋር ተዋውቀን ነበር! መጀመሪያ ሳያት በጣም ወጣት ስለሆነች ሰራተኛ አልመሰለችኝም፤ የሆነች ለአባቷ ምሳ ልታደርስ የመጣች የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበር የመሰለችኝ። ስሟን ዶ/ር kjanishirtyasdfgeryytd ስትለኝ ኬጅ የጀመረችው ከዮኒቨርስቲ ነው እንዴ አልኩ። እሱን ተውትና ስሟን ማን አልኳችሁ? አያችሁ ለዛ ነው በተገናኘን ቁጥር "ዶክተር" ብቻ እያልኩ የምጠራት። ይሄ መላየ እስከትላንት ሰርቶልኝ ነበር። ትላንት ግን አንድ ስድስት የሚሆኑ ህንዳዊያን ባልደረባወቿ ጋር አገኘኋት። "ዶክተር" ስል ሁሉም ዞረው በፈገግታ አዮኝ! ሁሉም ዶክተሮች ነበሩ። ከመካከላቸው አንድም መላጣ፣ አንድም ከባድ መነፅር ያደረገ አንድም ከረቫት ያሰረ አልነበረም። እንደስማቸ እና ቀሚሳች ርዝመት በትምህርት ከፍ ያለ ደረጃ ለመድረስ የሚወስድባቸው አጭር ጊዜ ይገርመኛል። አሪፎቹን ሳንደምር የአገራችን አድቫይዘር በእድሜ እሱን እስከምታክል አይፋታህም😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

08 Jan, 14:04


መዝሙር በአንዲት ዘለላ ፀጉር
(አሌክስ አብርሃም)

አንዳንዱ ሰው እያንዳንዷን የህይወት ገጠመኝ እንዴት አጣጥሞ እንደሚጠቀምባት ሳስብ ይደንቀኛል። ጓደኛየ አብነት አርብ ማታ ደወለልኝና በተጋነነ ድምፅ "የሚገርም የሚደንቅ እፁብ ድንቅ ነገር ልነግርህ ነው " አለኝ። ሊያገባ ይሆን? ሎተሪ ደርሶት ይሆን? የሚገርም ግሬድ አምጥቶ ነው? ብዙ አሰብኩ ....

"ፂሜ ላይ አንድ ሽበት ወጣች" አለ ይቀጥላል ብየ ስጠብቅ
"አለህ አብርሽ ? ሰምተኸኛል?"
"ሽበት ነው ያልከኝ ...."
"አወወወወ! እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ እርሱ ዘመናትን ያቀናጃል፤ የእድሜ ፀጋ እርሱ ካልሰጠ...." ምንም ወሬው አልያያዝልህ አለኝ።

"ቆይ የሚደንቅ ነገር ብለኸኝ ነበር ...."
"ከዚህ በላይ ምን የሚደንቅ ነገር አለ? በሱዳን በርሃ ከእባብና ጊንጥ አትርፎ በምንትስ ጫካ ከአንበሳ መንጋጋ አውጥቶ ፣ በውቂያኖስ ከአሳ ነባሪ ጥርስ ታድጎ ለሽበት ያበቃኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? በምን ስራየ ?" ዝም አልኩ። የድምፁ ጥልቀትና ቃል አሰካኩ አንዷን ነጭ ፀጉር እንደበገና ክር ወጥሮ የምስጋና መዝሙር የሚዘምር እስኪመስለኝ መሳጭ ነበር። ያችን አንዲት ዘለላ ሽበት ፎት አንስቶ ላከልኝ ። አንዲት ፀጉር ናት፣ ገና በወጉ እንኳን አልነጣችም።

ታዲያ ዛሬ የበዓል ጥሪ ነበረን። ከጠሩን ቆይተዋል። ደውሎ "ተዘጋጅተሀል እየመጣሁ ነው" ሲለኝ
"ባክህ አንተ ሂድ እቤት መቆየት ነው የምፈልገው አልተመቸውም ምናምን በልልኝ " አልኩት።

"እንዴዴዴዴ አብርሽ ምን ነካህ? አብረን እንመጣለን ብለን ቃል ገብተን? ቃላችንን እንዴት እናጥፋለን? እኔማ እንዲህ ሁለት ፀጉር አውጥቸ አልዋሽም" አላለም!😀


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

06 Jan, 17:12


ከኛም ወዲያ ተኳሽ!
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ወዳጅ አለኝ... በየዓመቱ ጠመንጃ የሚገዛ! እውነቴንኮ ነው። ይሄ ወዳጀ ለፍቶ ግሮ ጥሮ ዶላሩ ጠርቀም ሲልለት ጠመንጃ ይገዛና እቤቱ ያውም ሳሎኑ ግድግዳ ላይ ባሰራው መደርደሪያ ላይ ይሰቅለዋል። ሰርቶ ለጠመንጃ! እንዲህ ያለ ሱስ ሰምቸ አላውቅም! የሰው አመሉ ብዛቱ እናንተ! ወደሰባት ጠመንጃ አራት የሚሆኑ ሽጉጦች ብዙ አይነት ጥይቶች የተደረደሩበት ባለመስተዋት መደርደሪያው ልክ የአገር ቤቱን የቁም ቡፌ ይመስላል። የግል ምሽግ!

ሚስት አላገባ ፣አልወለደ ፣ቤት አልሰራ፣ አይጠጣ ብሩን ለአልባሌ ነገር አያጠፋ በቃ Ak ck Jk እያለ ጠመንጃወቹን እንደልጅ በስስት ሲያያቸው ሲወለውላቸው ግራ ይገባኛል። ሆቢው ነው። በፈረንጆቹ የተለመደ ነገር ነው አሉ። እንግዲህ በየአመቱ ከከፈላችሁት የስራ ግብር መንግስት እንደቸርነቱ መጠን ቆንጥሮ ይመልስላችኋል። ለነገሩ አሰራር አለው። ሁልጊዜ በሚቀጥለው "ታክስ ሪተርን" ሊገዛ ስላሰበው ጠመንጃ በጉጉት እንዳወራልኝ ነው።

ታዲያ ባለፈው አዲስ ጠመንጃ ገዝቶ የፍንጥር ሊጋብዘን ቤቱ የወሰደን ጊዜ " ለመሆኑ መሳሪያወቹን ትተኩስባቸዋለህ?" አልኩት። ነገሩ ገርሞኝ! አልመለሰልኝም ይልቅ "በቀጣዮ ቅዳሜ ቀጠሮ እንዳትይዝ የሆነ ቦታ እንሄዳለን" አለኝ። ከከተማ ወጣ ብሎ በሰፊው የታጠረ ኮረብታ ነገር ነበር! ምድረ ፈረንጅ ክተት የተባለ ይመስል ጠመንጃውን ባጭር ታጥቆ ቡናውን በፍንጃል በርገሩን በፕላስቲክ አገልግል ቋጥሮ ተሰልፏል። አንድ ሻለቃ ፈረንጅ! ዶላር ሊተኩስ! በአንድ የተኩስ ልምምድ ያውም በሰዓት የሚከፍሉት ለደሀ ክረምት ያወጣል።

ጓደኛየም ጠመንጃውን እና አንድ እሽግ ካርቶን ጥይት ይዞ ወደሰልፉ ተቀላቀልን። መውዚር አማረኝ ያለ አሜሪካዊ እንግዲህ እዚህ መግቢያውን ከፍሎ አልያም የአባልነት ክፍያ ካለው ስሙን ነግሮ እስኪወጣለት ሲያኖጋው ይውላል። ከካርቶን የተሰሩ የሰው ምስሎች በተለያየ ርቀት ለኢላማ ተቀምጠዋል፣ አንዱ ተበሳስቶ ሲወድቅ ሌላ ከመሬት ተመዞ ይቆማል። (የካርቶን ትውልድ እላለሁ በውስጤ) የጆሮ መከለያ በገፍ አለ። ጓደኛየ ተራው ሲደርስ እንደሄድፎን የሚጠለቅ ነገር ለእኔ ሰጠኝና እያነጣጠረ ይለው ጀመር! እውነቱን ለመናገር ጎበዝ ተኳሽ ነበር። በጣም ሩቅ ያለ የካርቶን ኢላማ ልብ ልቡን እያለ ሲገነጣጥለው ነጮቹ በአድናቆት ያጨበጭቡለት ነበር።

"በል ያዝ" አለና ጠመንጃውን ደረቴ ላይ ቢለጥፈው እንደልጅ አቀፍኩት። አቤት አከባበዱ.... ይሄን ጉድ ነው እንደዛ አንጠልጥለው በሜዳ ተራራው የሚሮጡት? ራንቦ ይሄን ነው ባንዴ ሁለት ዮዞ ሆሊውድ ተኮስኩ ያለን? ደነቀኝ። የሰው ልጅ ፅናት! ያለዛን ቀን ጠመንጃ ነክቸም አላውቅ። ከአያያዝ እስካተኳኮስ ዘለግ ያለ ማብራሪያ ተሰጠኝና በል እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም ያው አለ ጓደኛየ ... እንደፎንቴን ውሃ ደሜ ወደአናቴ ሲረጭ ተሰማኝ። "ከእያንዳንዱ መከረኛ አፍሪካዊ ኋላ አንድ ጠመንጃ አለ" የሚል ጥቅስ እዛው ፈጠርኩ። ወደኢላማው ደረት ዓለምኩ...አነጣጠርኩ ...ትንፋሸን ዋጥኩ .....ቃታውን ባለ በሌለ ሀይሌ ሳብኩት 🚨🚀💣💱 የብዙ ነገር ድምፅና ምስል ነው የተሰማኝና የታየኝ።

መጀመሪያ የመሰለኝ ግን ሌላ ሰው ታንክ ተኩሶ ትከሻየን ያወላለቀው ነበር። አህያ ራሱ እንደዛ አይራገጥም! ሰደፉ የቀኝ ትከሻየን የረገጠኝ አረጋገጥ ሳልወድ እስክስታ ነው ያስወረደኝ። የሆነ አለምየ ሶራ! በረድ ሲልልኝ ጠመንጃው እጀ ላይ የለም ጓደኛየ ወስዶታል ....የጆሮ መከላካያውይ ዝቅ ሳደርግ "አንተ ወታደር ነበርክ እንዴ ? " አለኝ ወደኢላማው በአድናቆት እየጠቆመኝ! በግርምት ዞር ብየ ኢላማውን አየሁ፣ መሬው ተኳሹ መራዡ! ያንን የካርቶን ሰውየ አፍንጫው ላይ ቦድሸዋለሁ ... ህ! ድሮም እጀ ላይ ጠላት አይበረክትልኝም😎

ጠመንጃ መንፈስ ነው ነው ወገኖቸ! አሁን ይሄው አንዲት ቀለል ያለች ምንሽር ብሸምትና ሲደብረኝ ሄደት እያልኩ ያንን ካርቶን አሳሩን ባበላው... እያልኩ ማሰብ ከጀመርኩ ሰነበትኩ😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

06 Jan, 07:52


እድል ጀርባዋን ስላዞረችባችሁ አትዘኑ፣አስቀያሚ ፊቷን እንዳትዞርባችሁ ፍሩ!
(አሌክስ አብርሃም)

ዘጠኝ ጊዜ ሎተሪ ስለደረሳቸው ሰውየ ሰምታችሁ በእድለቢስነታችሁ ብትማረሩ ልክ ናችሁ! እናንተ ላይ ከልጅ ኢያሱ ዘመን ጀምሮ የጠመመባችሁ ዲቪ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሞላችሁላት ልጅ ቢመጣና ብትበሳጩም አልፈርድባችሁም፣ ግን እስኪ እድልን ገልብጡና ተመልከቷት ወገኖቸ!

ይህ ምስሉን የምትመለከቱት ጓድ ዋልተር ሳምፎርድ የእንግሊዝ ወታደራዊ ኦፊሰር ነበር̏። በ1918 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወደቤልጅየም ዘመተና ቆሰለ? የቆሰለው በጦርነቱ እንዳይመስላችሁ፣ ጦርነቱ ላይ የበታቹን እየመራ «በለው» ሲል የግዜር መብረቅ ወርዶ ወገብ ዛላውን አለው! (መብረቅ መታው) ይታያችሁ በጦርነት ላይ መብረቅ! ከፈረሱ ተወርውሮ ወደቀ፤ ፈረሱ ሞተ፣ እርሱ ግን ነፍሱ ቢተርፍም ከወገቡ በታች «ፓራላይዝ» ሆነ።

በተሽከርካሪ ወንበር እየተገፋ ኑሮውን ሲገፋ ቆየና "በቃ ካናዳ ልኑር" ብሎ ከነቤተሰቡ ወደካናዳ ሄደ። በሰላም አሣውን እያጠመደና እየተዝናና ሲኖር 1924 ዛፍ ስር አረፍ እንዳለ ምን ሆነ ? እንደገና መብረቅ አደባየው😀(አያስቅም) ደግነቱ ዛፉ ወደቀበት እንጅ እስከዚህም አልተጎዳም ነበር። ሁለት ቀን ያህል ታክሞ አገገመ። ቤልጅየም ያቆሰለው መብረቅ ካናዳ ተከትሎት በመሄዱ ግን ጉድ ተባለ።

1930 ጓዱ ከረዥም ጊዜ ህክምና በኋላ ፓራላይዝ የነበረ እግሩ በርትቶ መቆም ቻለ፣ መራመድም ቻለ ደስ አለው። እናም ደስታውን እያጣጠመ በእግሮቹ አቅራቢያው ወዳለ ፓርክ ሄዶ ሲንሸራሸር ድንገት አየሩ ተለዋወጠ. . . ሰማይ ጠቆረ. . . ጉርምርምታ. . . 😀 ከዛ ያው እንደምትገምቱት ይሄ እድለቢስ ሰውየ ለሶስተኛ ጊዜ በመብረቅ አደባየው! አሁንም ነፍሱ ተረፈ! በእርግጥ ገና ተራምዶ ያልጠገበባቸው እግሮቹ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልሰው ፓራላይዝ ሆኑ! በዚሁ ጠንቅ በደረሰበት አካላዊና ስነልቦናዊም ጉዳት ከሁለት ዓመት በኋላ ይችን ዓለም ተሰናበተ! «ተገላገለ በቃ» ትሉ ይሆናል፣ አላበቃም ወገኖቸ!

ቫንኮቨር ማውንቴን ቪው የሚባል መቃብር ወስደው ቀበሩት። ከተቀበረ ከአራት ዓመት በኋላ 1936 መቃብሩን ምን መታው ? መብረቅ😀😀 በእውነት! በቃ መብረቅ ወረደና «ደንበኛ ሰላም ነው?» ብሎ የመቃብር ሃውልቱን ሰነጣጥቆ ጣለው! የዓለማችን እድለቢስ ሰው የሚል መዓረጉን ተጎናፅፎ አሁንም በመቃብሩ ቀጣዩን መብረቅ እየጠበቀ ነው እላችኋለሁ! ከማትጋፈጡት ባላጋራ ይሰውራችሁ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

05 Jan, 09:27


ለጥንቃቄ ያህል
(አሌክስ አብርሃም)

በተለያዩ ህንፃወች ውስጥ የምትኖሩ ወይም የምትሰሩ ነዋሪዎች፣ባለቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኮሚቴዎች ወይም የሚመለከታችሁ ሁሉ። ሰሞኑን እየተከሰተ ባለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተሰማ ከባድ ጉዳት ባይኖርም ቀጥሎ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ይመከራል። ህንፃዎቻችሁን እያንዳንዱን ክፍልና ዙሪያውን በጥንቃቄ ተመልከቱ መርምሩ። ባለሙያዎቹ የህንፃ ዋና ቋሚ፣ ወይም ርብራብ? ወይም እነዚህ የሚሰሩበት የብረት ስትራክቸር፣ ህንፃው የሚያርፍበት አካባቢ /Slabs, Beams, columns, Footing / ወዘተ የሚሏቸው በዓይን ሊታዩ የሚችሉ የህንፃው ክፍሎች ላይ ቀጥሎ በፎቶ የተቀመጡት አይነት የመሰንጠቅ ፣የመፈራረስ፣ የመሸራረፍ ምልክቶች ካያችሁ ወይም በግድግዳ ላይ ርጥበት ፍሳሽ ካያችሁ በውስጥ የሚያልፉ የውሃ መስመሮች መሰበር ሊሆን ስለሚችል ማድረግ ስላለባችሁ ነገር ባለሙያዎችን በፍጥነት አማክሩ። ለበለጠ መረጃ መሐንዲሶችና የህንፃ ደህንነት ባለሙያዎችን ብታማክሩ ደግሞ ጥሩ ነው።

ሌሎቻችሁም ሸር በማድረግ የትኛውም ከተማ ለሚኖሩ ሁሉ አድሩሷቸው። አንዘናጋ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

31 Dec, 09:04


📸🏃‍♂️🏃‍♀️
(አሌክስ አብርሃም)

እውቅና መከራ ነው! በተለይ በአሁኑ ሰዓት እውቅና ያላቸው ሰዎች ከእውቅናቸው ጋር በማይገጥመው ኑሮ መጠለዛቸው ሳያንስ ስልክና ጣት ያለው ሁሉ ፓፓራዚ እየሆነ መኖሪያ አሳጥቷቸዋል። ባለፈው «ራበኝ» አለ አንድ ኪሊማንጃሮን የሚያክል ዕውቅናና የክብሪት እራስ የምታክል ገቢ ያለው ሚስኪን ታዋቂ ሰው። እና ግራ ቀኝ ገልመጥ ብየ ኪሴ ባለችው ብር እርጥብ የሚባለው ምግብ የሚሸጥባት የላስቲክ ቤት ገባሁ። የምታስተናግደው ልጅ በአንድ እጇ ያዘዝኩትን ርጥብ በሌላኛው እጇ አይፎን 15 ስልኳን ደግና እየገለፈጠች መጣችብኝ። አንገቴን እንዳቀረቀርኩ በልቸ ወጣሁ! ማታ ከአዲስ አበባ ህዝብ ግማሹ እና ዲያስፖራው የሊንክ መዓት ሲልክልኝ ደንግጨ ብከፍት ፎቶየ እርጥብ ከሞላ ጉንጨ ጋር ገጭ ብሎ « ጉድ ጉድ! ታዋቂው አርቲስት እከሌ ዛሬ በየሽመቤት ርጥብ ቤት ምን ገጠመው? » ይላል አንድ ሰዓት የሚፈጀው ዘገባ ርዕስ!

ሌላኛው በምግብ አለመስማማት ተቅማጥና ትውኪያ አጣድፎት ሆስፒታል ይሄዳል፤ ሁሉም ተራ የሚጠብቅ ታካሚ ማቃሰቱን አቁሞ ስልኩን ከየጋቢው ስር እየመዘዘ ደግኖ መቅረፅ ጀመረ! በቀጣዩ ቀን ወደሽንት ቤት ሲሮጥ ከሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ጋር « ተወዳጁ አርቲስት በእንትን ሆስፒታል ሲቀዝ* ዋለ» የሚል ዘገባ ቲክቶክ ላይ ተለቀቀ።

በቁም ነገር ግን ታዋቂ ሰወች ታመው ሆስፒታል፣ ወላጅ ሆነው ትምህርት ቤት ፣ ለአምልኮ ወደቤተእምነታቸው መሄድ በጣም ነው ከባድ የሆነባቸው! ደባሪው ነገር ደህሞ አንዳንድ ባለሙያዎች ጭምር በስራ ምክንያት የሚያገኝዋቸውን ታዋቂ ሰዎች ገመና አደባባይ ማስጣታቸው ነው። በሌላቸው አቅም ራይድ ለመጠቀም የተገደዱ በራሳቸው አገር እንደወንጀለኛ ተሳቀው ግራ ቀኝ እያዩ የሚኖሩ፣ ስልክ የያዘ ሰው ፊት ለፊታቸው በተቀመጠ ቁጥር ምቾት የሚያጡትን ቤት ይቁጠራቸው ! ታዋቂ ሰዎች ካለጥፋታቸው እንደታዋቂ ወንጀለኛ ከጥላቸው እየሸሹ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጊዜ ላይ ነን። በነገራችን ላይ ትልቅ መቀመጫ ያላቸውን ሴቶችም ካለእውቅናቸው የካሜራ ሲሳይ ማድረግ ፋሽን እየሆነ መጥቷል። እቤት ትተውት አይወጡ ነገር።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

30 Dec, 15:06


ይሄ ሶሻል ሚዲያማ አበላሽቶኛል😀  16 ወይም 17 ዓመት የሚሆናት ልጇ ጋር የምትኖር ሚስኪን ፈረንጅ ጎረቤት አለችኝ። ብቻዋን ነው ልጇን የምታሳድጋት። ትሁት ሰላምተኛየ ደግሞ። ሁሉ ነገሯ ፣ ህይወቷ ልጇ ናት ። የትም እናት ያው እናት ናት መቸስ! ልጅቱ ግን  ዕድሜዋ አጉል አይደል ትንሽ ጀብረር ያደርጋታል። እና ዛሬ ወደቤቴ እየሄድኩ የትራፊክ መብራት ላይ ቆሜ ዞር ስል ከጎኔ ሙዚቃው  እንደወፍጮ ቤት የሚጮህ መኪና ቆሟል።  መኪናው  ውስጥ ይችው ልጅና አንድ በንቅሳት ያበደ ጎረምሳ ምናምናቸውን ሲያጨሱ ዓይኔ ላይ ጣላቸው።  ....ጭራሽ ተንጠራርታ ያንን ታቱዋም  አትስመውም? አበሻነቴ ተነሳብኛ! ይሄው እስካሁን ድረስ  እቤት ገብቸ ሁሉ ለብቻየ በተለያየ ድምፅ "
ቤቲ ለናትሽ ....ለናትሽ ቤቲ ለናትሽ ...ታይተሻል " እያልኩ ነው😀😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

30 Dec, 05:56


የJawar Mohammed ን #አልፀፀትም

#Amharic Version

በSoftcopy /pdf ትፈልጋላችሁ ?

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

30 Dec, 03:48


እነዚህ በዮቲዮብ ፖድካስት የሚለቀቁ ቪዲዮወች ርዕስ ነገር ግን ወዴት እየሄደ ነው? እንዴ! መቸለታ አንዲት ቆንጆ ከአንድ ሰይጣን የሷን ተቃራኒ ለመስራት የተጋበት ከሚመስል ፖድካስተር ጋር ኢንተርቪው ያደረገችበትን ቪዲዮ አየሁ። ርዕሱ ዓለም በቃኝ ያሉ ወንዶችን እንኳን የሚፈትን ነበር።

" እየታገልኩ ሳስቸግረው ጓደኛውን ጠርቶ ለሁለት እግሮቸን ግራና ቀኝ ከፈቱና....ሲጨርሱ ግን በደስታ አለቀስኩ" ይላል። ይች አገር ወደየት እየሄደች ነው ብየ ተከዝኩ! ግን ጉዱን ልየው ብየ ቪዲዮውን ከፈትኩ ... ስታወራ ለጉድ ትስለመለመዋለች ! እያሳለፍኩና እየመለስኩ የእግሩ ጉዳይ ላይ ስደርስ የምታወራው ስላዋለዷት ሁለት ዶክተሮች ሆኖ አገኘሁት። ሜርድ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

29 Dec, 12:52


አስተዋውቀን አትበሉኝ ኑና ራሳችሁ ታወቁ!!
(አሌክስ አብርሃም) !

ለምንድነው ግን ሰብስክራይብ አስደርግልን "አስተዋውቀን" የሚል መልእክት መላክ የማይደክማችሁ? የት አውቂያችሁ ነው የማስተዋውቃችሁ? ስልችት ያለኝ ነገር! "የምንትስ ችሎታ አለኝ ግን እድሉን የሚሰጠኝ አጣሁ ፣ በቲፎዞ ነው፣ በዘመድ ነው ብዙ ሰው ላይክ አያደርገኝም ምናምን " እና ምን ይሁን? ማንም ስለእናተ ሰማይ ሰቅሏችሁ ስላወራ የሚቀየር ነገር የለም! አንድ ሰው ብቻ ነው ታሪካችሁን የሚቀይረው....ያ ሰው ደግሞ እናንተ ራሳችሁ ናችሁ!! በአንዲት አጋጣሚ ታይተው ሰማይ ጥግ የደረሱ ታዋቂወችን ተመልከቱ! እንዴትና ምን ይዠ በምን መንገድ ልታይ ነው ጥያቄው!

በአንድ ነገር ግን ልረዳችሁ ዝግጁ ነኝ! አሪፍ ነገር ሰርታችሁ ለህዝብ የምታቀርቡበት መንገድ የብዙወቻችሁ ችግር ነው። ራሳችሁን በራሳችሁ ለብዙ መቶ ሺወች ገፋ ሲልም ለሚሊየኖች እንድታስተዋውቁ እድሉን ላመቻችላችሁ እችላለሁ! ምንድነው ችሎታችሁ? ተሰጧችሁ? ጥሪያችሁ? ግጥም ማንበብ?፣ ፅሁፍ በአሪፍ ድምፅ መተረክ? መተወን፣ ወግ ? ኮሜዲ? ድምፅ ማስመሰል? መደነስ? መዝፈን? ፎቶ ማንሳት? ዶሮ ማርባት? ልብስ ዲዛየን ማድረግ፣ ሜካፕ መስራት? በየእምነታችሁ መስበክ? መነጫነጭ? ማልቀስ? መነገድ? መሳቅ? ልምዳችሁን ማካፈል? መምከር? መውደቅ ? መነሳት? ምን? ምንም ችሎታ የለኝም እንዲሁ አገር ይየኝ ቆንጆ ነኝ እወቁኝ በቃ ማለት ከፈለጋችሁም የራሳችሁ ፍላጎት ነው? ከመታየት ምን እንደሚፈጠር ምን አውቃለሁ?

ብቻ ስለእናተ ምንም አስተያየት አልሰጥም፣ ራሳችሁ ችሎታችሁን የሚያሳይ ፣ ወይም ለሌሎች ማስተላለፍ መንገር የምትፈልጉትን ነገር ካለ አጭር ቪዲዮ ቀርፃችሁ በኢንቦክስ ላኩልኝ ... እዚህ በሶሻል ሚዲያው በርካታ ሰወች ከሚጎበኟቸው አካውንቶች አንዱ የሆነው የፌስቡክ አካውንቴ ላይ ተከታይ የለውም ከምትሉት የፌስቡክ ወይም ከቲክቶክ አድራሻችሁ ጋር ፖስት አደርግላችኋለሁ፣ ከዚያ ስራችሁ ያውጣችሁ! አሁን እኔ ጋር እኩል ተመልካች፣ አንባቢ አላችሁ ማለት ነው። ይሄው ነው።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Dec, 17:50


ፌስቡክ ላይ በመልክም በፀባይም የምታምረኝ ልጅ!
(አሌክስ አብርሃም)

እንደምን አደራችሁ? ማክሰኞ ጧት እንዴት ነው?

Dementia ስለተባለ ህመም ሰምታችኋል መቸም። በልምድ አጠጋግተን አልዛይመር (የማስታወስ ችሎታን የሚጎዳ/ የሚያሳጣ በሽታ) የምንለው ማለት ነው! አልሰማችሁም? መርሳት ጀምራችኋል😀 እና ዳይሜንሽያ አንጎላችን የሚከውናቸውን ወሳኝ ስራወች እንደማሰብ፣ ማስታወስና ምክንያታዊ መሆን ወዘተን የመሳሰሉትን በማወክ — የየዕለት ስራችንን በአግባቡ እንዳንሰራ ያደርጋል። እስከአሁን ይሄ ነው የሚባል ህክምና የለውም ይላሉ። የብዙ አገር መንግስታት ለህዝባቸው ስለበሽታው ግንዛቤ ለመፍጠር የተለያየ ነገር ሲያደርጉ አንዳንድ አገሮች ግን መሪወቹ እንደጃፓኖቹ አስተናጋጆች በሽታው ቀድሟቸዋል መሰል ህዝባቸውን ይረሳሉ! (የቱ ህዝብ?😀)

ጃፓን ውስጥ ያለ አንድ ሬስቶራንት ታዲያ ትንሽ ፈገግ እያደረገ ስለህመሙ ግንዛቤ የሚፈጥር አሰራር ዘርግቷል። መጀመሪያ በሬስቶራንቱ የሚሰሩት አስተናጋጆች በሙሉ ይህ የመርሳት ህመም ያለባቸው ናቸው። ሲቀጠሩ ራሱ የመርሳት ብቃታቸው ታይቶ ነው። እና ደንበኞች ገብተው "እስኪ አንድ ሳንድዊች" ብለው ቢያዙ አስተናጋጆቹ ቀልጠፍ ብለው ሄደው ቢራ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። ቢራ አላዘዝኩምኮ ካለ ኦ ይቅርታ ብለው ይመለሱና ጨው ይዘው ከተፍ! እንዲሁ እንደተደበላለቀ፣ ባቢሎን እንሆነ የሚውል ቤት ነው።

ታዲያ ከመላው ዓለም ቱሪስቶች እየጎረፉ ቤቱን እያጨናነቁት ነው ። ካዘዙ በኋላ ምን ይመጣልኝ ይሆን ብለው የሚያስቡበት የዓለማችን ብቸኛ ሬስቶራንት! ያላዘዝኩት ቀረበልኝ ተሳሳተብኝ ብሎ እንቧከረዮ የለም! በቃ የሬስቶራንቱን ስም አይተህ ገብተሀላ! Restaurant of Mistaken Orders ይባላል። ትዛዝወትን የሚያሳስት ሬስቶራንት! ማስታወቂያው"እኛ ጋር ይምጡ የፈለጉትን ይዘዙ የእርስወን ትዛዝ ማን ያስታውሳል ..."😀

የተሳሳተ ማቅረቡ አንድ ነገር ነው...ምግብ አዘው እጃቸውን ታጥበው ሲጠብቁ ላልቀረበላቸው ምግብ ሒሳብ ተሰርቶ ከነተታክሱ የሚመጣላቸው አሉ ፣ቲፕ ሁሉ ይጠበቃል😀 ተበሳጭተው "ምን አይነት ሬስቶራንት ነው?" ቢሉ አስተናጋጁ "የቱ ሬስቶራንት" ሊል ይችላል! ምን ለማለት ነው?...ህዝቡ በራሱ ግብር ደመወዝ ጭማሬ ሲጠይቅ መዋጮ የሚጠየቅ ፣ ኧረ ዘይትና ጤፍ ሲል ፣ ቅጠልና ጨው የሚያቀርብ፣ ቤት ቸገረን ሲል መናፈሻ እነሆ የሚል መንግስት ያለባት የሆነች አገር አውቅ ነበር....ስሟኮ አፌ ላይ ልቤ ላይም አለ ... መርሳት አብዝቻለሁ 🤔

መልካም ቅዳሜ ይሁንላችሁ🙏

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

27 Dec, 18:26


በእናቶች ብርጌድ የሚጠበቅ ችግር!
(አሌክስ አብርሃም)

እውነት እላችኋላሁ እናቶች ለዘመናት ያጠራቀሙትን አሮጌ የቤት ዕቃ ከመቀየር መንግስትን መቀየር ይቀላል። ምንግስት ምናለው! የደበራችሁ መንግስት ቢበዛ ኢስራኤል ራሽያ ምናምን ባሰለጠነቻቸው ኮማንዶወች ቢጠበቅ ነው። እናተም ሰልጥናችሁ  ገድላችሁም ይሁን ሙታችሁ ታስወግዱታላችሁ። በቃ!  እናቶች የሚከዝኑት አሮጌ ዕቃ ግን ...በስመአብ!  ብትጠሉትም የሚጠበቀው በጣም በምትወዷት እናት በምትባል፣ ፍቅር ያሰለጠናት ኮማንዶ ነው።ለተነደለ ብረት ድስት ሁሉ እስከደም ጠብታ የምትዋጋችሁ እናት ክፍለጦር😀

በበኩሌ ተስፋ የቆረጥኩት መቸ መሰላችሁ ? ማዘር ከመቆየቱ ብዛት ቅድም አያቴ የሚመስለኝ  የተነደለ ማንቆርቆሪያ አላት....አንበሳ አርማ ከመሆኑ በፊት ስለተመረተ አርማው ሁሉ ዳይኖሰር ነው! እና አንድ ቀን "አሁን ይሄ አሮጌ ማንቆርቆሪያ ምን ያደርግልሻል? " አልኳት ...ካለችበት በፓራሹት ወርዳ ማንቆርቆሪያው አጠገብ ቆመችና በአይነ ቁራኛ እያየችኝ " አሁን ይሄ ምኑ ነው አሮጌ? አንተ ስትወለድ ወድቆ ትንሽ ጫር ብሎ እንጅ ገና ጥሬኮነው" 😀እንግዲህ ወገኖቸ እኔ ማለት እንደምታውቁት  በሰገሌ ጦርነት ጊዜ ስንት ጀብዱ የሰራሁ ወንድማችሁ ነኝ። አንዳንዴ ታዲያ ከዚህ ቀልድ ባለፈ ስለነገሩ  አስባለሁ፣ እናቶች ቤታቸው ሲፈርስ በውስጣቸው የሚፈጠረው ሀዘን...በውስጣቸው የሚፈራርሰው የሆነ የማናውቀው በጓዳቸው  ለዓመታት የገነቡት መንግስት....

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Dec, 13:22


ኒቆ ያች መፅሐፍ ቅዱሰ ላይ ያለ የምስጋና ጥቅስ ሁሉ ፖስት አድርጋ የጨረሰች የፌስቡክ ወዳጀ፣ ሰሞኑን መነጫነጭ ማማረር ጀምራለች። የዛሬ ሳምንት "ሰውን ማመን ቀብሮ ነው" ብላ ለጠፈች፤ ከዘፍጥረት እስከራዕይ አስሸ ጥቅሱ ከመፅሐፍ ቅዱስ እንዳልተወሰደ ገባኝ። ከትላንት ወዲያ "ለፍቅረኛው በዓመት አንድ ቸኮሌት ገዝቶ የማያውቅ አስሯን ሴት ይመኛል🤣🤣 ብላ ከሳቅ ኢሞጅ ጋር ፖስት አደረገች፤ ስለማን እንዳወራች አላውቅም ግን የስምንት ዓመት የፌስቡክ ጓደኛየ ነበረችና ላይክ አደረኩ።/የጉርብትና ላይክ የምለው አለኝ/ ከሰላሳ ደይቃ በኋላ ያ ሄኖክ የሚባል የፌስቡክ ጓደኛየ የቁጣ ኢሞጅ ለብሶ ኢሞጅ ጎርሶ "አንድ ጥናት ላይ እንዳየሁት ውሻ ቸኮሌት ከበላ ይሞታል" 😡😡ብሎ ለጠፈ ። እኔም ይሄን ነገር ሰምቸ ስለነበር ለመደገፍ ላይክ አደረኩ። አሁን ሁለቱም ብሎክ አድርገውኛል! የሳት ራት የሆንኩ ሰውየ! የዛሬ ዓመት ሁለቱም "የሰው ፅሁፍ ላይክ አታደርግም ታዋቂ ሆነህ ልብህ ውልቅ ብሏል" ብለው ወቅሰውኝ ነበርኮ! በእውነቱ ፍቅረኛ እንደነበሩም ባለፈው ሳምንት እንደተለያዮም ገና መስማቴ ነው። እንዲህኮ ነው በሁሉም ነገር ሳይገባን እየጠነቆልን የእሳት ራት የምንሆነው!

ወይኔ በላቸው!!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Dec, 10:34


ቁማችሁ የምትቀሩት ቁጭ ስለማትሉ ነው¡¡
(አሌክስ አብርሃም)

ሴቶች በተደጋጋሚ ግልፅ ወንድ እንወዳለን ትላላችሁ፤ አይመስለኝም እህቶቸ። ምንድነው ግን ችግራችሁ? እንደው አሁን ማን ይሙት ከጓደኛየ ብሩክ የበለጠ ጥሩ፣ ግልፅ ልጅ እዚህ ፌስቡክ ላይ ይቅርና በድፍን ኢትዮጵያ ይገኛል? መልሱልኛ ምን ትቅለሰለሳላችሁ?!

ግን ባለፈው ሳምንት የለጠፈውን ትሁትና ግልፅነት የተሞላው መልዕክቱን ብዙወቻችሁ እንዳላየ አልፋችሁታል። አትረጋጉማ! ቁጭ ብላችሁ አታነቡማ! ስልካችሁ ላይ ጭምር በጣታችሁ እየሮጣችሁ በየት በኩል ቁም ነገር ይድረሳችሁ? ጣታችሁን ላየውኮ በቆሎ የምትፈለፍሉ ነው የምትመስሉት...ስክሮላም ትውልድ¡ (በዚህ አያያዛችሁ እስከምፅዓት ቁማችሁ ብትቀሩ ይገርማል? ሩጣችሁ ሩጣችሁ ትንፋሽ ሲያጥራችሁ አንዱ ክንድ ላይ ተዝለፍልፋችሁ ትወድቃላችሁ፣ የመጀመሪያ እርዳታ ምናምን ብሎ ለራሱም የሌለውን አየር ልስጣችሁ ይልና ከንፈሩን ያሞጠሙጣል ... የፍቅር ኪስ ምናምን ትላላችሁ! ለበለጠ የህክምና እርዳታ "ተኝቶ መታከም" ይባላል...ኧረ ወዲያ እናንተን በመምከር ሸበትኩ) እና ጓደኛየ ብሩክ ምን ነበር መልዕክቱ ?

"ስሜ ብሩክ ፍስሀ እባላለሁ፣ ዕድሜየ 35 ሲሆን በሙያየ ሀኪም ነኝ። ትዳር መመስረት እፈልጋለሁ። ፎቶየ ከታች የምትመለከቱት ሲሆን ምንም አይነት ሱስ የለብኝም። የእውነት ለትዳር ዓላማ ያላት ፣ዕድሜዋ ከ25 -30 የሆነች፣ቢያንስ እስከ12ኛ ከፍልና ከዚያ በላይ የተማረች ሴት በውስጥ ብትፅፍልኝ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኔን በትህትና አሳውቃለሁ" ይላል።

በሳምንቱ የኮሜንት ቦክሱ ተጨናንቆ እንደሚያገኘው በመገመት በማንበብና በመምረጥ እንድረዳው ቤቴ መጣ። እጁ እየተንቀጠቀጠ ከፈተው። ያሳዝናል ወገኖቸ። ሁለት ሰወች ብቻ ነበሩ የፃፉለት። 28.63 ሚሊየን ያላገቡ ሴቶች ባሉባት አገር ሁለት! የመጀመሪያዋ ሴት የፕሮፋይል ፒክቸሯ ላይ እንደምትታየው ጠይም እና ውብ ልጅ ነች "ሰላም ብሩክ። ሳራ እባላለሁ የ29 ዓመት ወጣት ስሆን ባለፈው ዓመት በሲቪል ምህንድስና በጥሩ ውጤት ተመርቂያለሁ። መልእክትህን ሳይ በግልፅነትህ ልቤ ተነክቷል። በአሁኑ ሰዓት ሳሪ ላቭ የተባለ የወላጆቻቸውን ፍቅር በቲክቶክ ሱስ የተነጠቁ ህፃናትን አሰባስቦ ፍቅር የሚሰጥ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርቸ በመንቀሳቀስ ላይ ነኝ። ይህንን መልዕክት የፃፍኩልህ የፈለካትን ሴት ካገኘህ በኋላ በሰርግ የምታገባ ከሆነ ከሰርግ ወጭህ ላይ በመቀነስ የተወሰነውን ለድርጅታችን በጎ አላማ እንድትለግስ ለመጠየቅ ነው " ይላል።

ሁለተኛውን መልእክት ከፈተው ... "ወንድሜ ብሩክ የጌታ ሰላም ይብዛልህ ....ትዳር መፈለግህ የተቀደሰ ሐሳብ ነው ግን ከማግባትህ በፊት እነዚህን አስር ነጥቦች ታስተውላቸው ዘንድ በጌታ ፍቅር ልኬልሀለሁ ....

1. ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም ባይሆንም መልካም ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት ....
2. ልባምን ሴት ማን ያገኛታል ...
3... .....
10. በሚመችህ ሰዓት ቢሮየ ብቅ ብለህ ስለዚህ መልካምና የተወደደ ህብረት ብንነጋገር ...

ወንድምህ ፓስተር ቸሬ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Dec, 12:35


~እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ~

ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው ። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው።

ትምህርት አያስፈልግም ብለው የሚናገሩ ሰዎች በኩራት የሚያነሷት ነጥብ "የተማሩ ሰዎች የት ደረሱ" የምትለዋ ቀሽም የማሸማቀቂያ ምክንያት ስትሆን፤ የተማሩት የት እንደደረሱ አብረን እንመልከት።

ከመሰረታዊ ጥናቶች እንጀምር።

1. ወንጀል

በ2021 Institute for Securities Studies (ISS) ባሳተመው ጥናት መሰረት 92.7% ገደማ ከባድ ወንጀሎች የሚፈፀሙት ዩንቨርስቲ ባልቀመሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ 6.5% ወንጀሎች ዲግሪ ባላቸው እና ቀሪው 0.8% ብቻ ደግሞ ማስተርስ እና ከዛ በላይ ባላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ ናቸው ይላል።

ይሄ ጥናት ኢቶጲስ ውስጥም የሚሰራ መሆኑን ለማወቅ፤ ስልክ ለመስረቅ ብሎ አንገት በጩቤ የሚወጉትን እና ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብለው ሚስታቸውን በዘነዘና ከሚገሉት ሰዎች ጀምሮ መመልከት በቂ ነው።

እዚህ ጋር የተማረ ሰው ምን አተረፈ ካልክ? "ህሊና" የሚባል ነገር እልሀለሁ።

2. ገንዘብ

ሌላኛው የተማሩ ልጆች ላይ የመዘባበቻ ነጥብ፤ ስራ እና ገንዘብ የማጣታቸው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ የነሱ ድክመት ሳይሆን የሀገሪቱ ድክመት ነው፤ እሱን ትተን ወደ ንግድ እንኳ ብንመለስ፤ ንግድ ላይም የተማረ እና ያልተማረ ሰው ቢሳተፍ የተማረው ሰው የተሻለ successful የመሆን እድል እንዳለው የሚያሳዩ ብዙ ዳታዎች አሉ።

ለምሳሌ አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መሀል 71 ፐርሰንቱ ከዩንቨርስቲ ዲግሪ እስከ PhD የጨረሱ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው። Bill Gates ወይም ማርቆስ Zuckerበርግ አይነት በጣም ጥቂት ባለሀብቶች በእርግጥ ከኮሌጅ ት/ት አቁመዋል፤ ነገርግን እነዚህ ግለሰቦች ት/ት ያቆሙት ከ Harvard እና Yale እንጂ ማትሪክ ወድቀው አይደለም።

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ሀብታሞቹ ደንቆሮ ሆኑ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፤ አግባብም ነው። ለዚህ ቀላሉ መልስ "ቁጥር 1ን" ተመልከት ነው፤ የኛ ሀገር ሀብታም በአመዛኙ ደፋር፣ ወንበዴ፣ አጭቤ፣ አምታች ነው። ይሄንን ውንብድና ደፍሮ እንዲሰራ የሚያደርገው ደግሞ አለመማሩ ነው።

ኢትዮጲስ ውስጥ ለምን generational wealth እንደሌለ ታውቃለህ? አባት ሀብታም ሲሆን ልጆቹን ጥሩ ቦታ ያስተምራል፤ ከዛ ልጆች ህሊና ይኖራቸዋል፤ ከዛ የአባታቸውን የወንበዴ ቢዝነስ ማስቀጠል ይከብዳቸዋል፤ አለቀ።

የተማረ ሰው ቁጥር ማነስ ከPolitical Stability፣ ከPoverty Alleviation፣ ከInnovation & ከEntrepreneurship እና አጅግ ብዙ አሁን ላለንበት አዘቅት ምክንያቶች ጋር በብዙ ጥናቶች አስደግፎ ማስረዳት ይቻላል።

በአጭሩ ት/ት ምን ያደርጋል የሚልህ ነጋዴ ሂሳቡን የሚያሰራው በተማረ Accountant ነው፣ ሲከሰስ ተከራክሮ ንብረቱን የሚያስመልስለት የተማረ ጠበቃ ነው፣ ህንፆውን የሚያስገነባው በተማረ ኢንጂነር ነው፣ ሲያመው የሚሄደው የተማረው ዶክተር ጋር ነው፤ ከዛ አልፎ ልጁን አጥና እያለ የሚጨቀጭቀው እና ፅድት ያለ international school ልኮ የሚያስተምረው ይሄው ራሱ ሰውዬ ነው።

እና ምን ልልህ ነው፤
አለመማር አያኮራም።
እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ አይባልም፤ ነውር ነው።

Natnael Afework

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Dec, 08:31


አርፈሽ ምላስ ሰንበር በይ!

የእኔ እህት! ስሜት ስሜት ነው... ዘመናዊ ስሜት ኋላ ቀር ስሜት የሚባል ነገር የለም! ስሜትን መቆጣጠር እንጅ በሌለ ስሜት ቀይሮ ማስመሰል ጨዋም ስማርትም አያስብልም! በምሳሌ ላስደግፈው ወይንስ ገብቶሻል? ይሄ ሳይገባሽ ነው ዝም ብለሽ ፍቅር ውስጥ የተዘፈቅሽው? ምናይነት ጣጣ ነው!

እሽ በቃ ስሚ ! አፈቀርሽ እንበል...ያፈቀርሽው ሰው ከልቡ አፍቅሮሻል። እና ምን ላምጣልሽ፣ ወይም ምን ልግዛልሽ የኔ ቆንጆ አለሽ (ይገባኛል ቆንጆም ላትሆኝ፣ ለገንዘብም ብለሽ ላትቀርቢው ትችያለሽ፤ ግን በቃ ምን ልታዘዝ አለሽ...ደግሞ ከልቡ ነው) እና ውስጥሽ በትክክል የፈለገው፣ ያማረሽ፣ ያሰኘሽ (((ማንትስ ኮንስፓኛ ወስዶ "ምላስ ሰንበር" የተባለውን፣ እንደድሮ ደመወዝ አንዴ ከበሉት ለወር የሚያጠግብ ፣ ከተለያዮ ጥቃቅንና አነስተኛ የከብት አካላት የተሰራ የስጋ ዘር ጥብስቅ አድርጎ እየተጎራረሱ መብላት ነው))) ግን አጉል ዘመናዊ ለመሆኖ ብለሽ "ቸኮሌት ግዛልኝ" ወይም "አበባ አምጣልኝ ፍቅር" አትበይ!! እንዴት ያለ ነገር ነው በመድሀኒያለም! ምላስ ሰንበር በይ አርፈሽ!

እውነተኛ ፍቅር ጌጃ ነው አይሳቀቅም፣ ያማረውን አይደብቅም! ምላስ ሰምበር እና ቸኮሌት መካከል ያለው ርቀት ዘመናዊነትሽን አያሳይም! በትክክለኛ ማንነትሽና በ"ፌክ ፐርሰናሊትሽ" መካከል ያለው ልዪነት ነው። እመኝኝ እህቴ ከተወለድኩ ጀምሮ ወንድ ሁኘ ነው የኖርኩት፣ እና የወንድ ፀባይ ይገባኛል ...ግስጥ ያለ እውነት የምትናገር ሴት ነፍሳችንን ነው የምትቆጣጠረው። ካላመንሽ "ኤክስሽ" ወይም "ኤክሶችሽ " ያገቧትን ሴት ተመልከች! ወንዶች የሆነ እንደአሳ ጊልስ ከጆሯችን በታች የተገጠመ ነገር አለን... የማንኛዋም ሴት ፌክ ንግግር በማይክሮ ሰከንድ ይገባናል! ወንድ ስሜቱ እንጅ ጆሮው ደንቆሮ አይደለም! ግን ሳያገባ በፊት ስሜቱንና እ.... ሲያገባ ደግሞ ጆሮና አእምሮውን የሚጠቀም ፍጡር ነው። እና ምላስ ሰንበር በይ! አበባ ትላለች እንዴ?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Dec, 19:31


ህይወት ክሽን ያለች ድራማኮ ነች። አላመናችሁኝም? ያዙ ይችን ወግ ...

ጓደኛየ በድሉ ፍቅረኛ ነበረችው! በጣም ነበር የሚወዳት። ቶሎ የኮሌጅ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ ነገር ይዞ እሷን ማግባት ነበር ዓላማው። ልጅቱ ስታስበው ስታስበው ራቀባት! ገና ስራ ፈልጎ ለዛውም በደመወዝ ኑሮ ምናምን አለችና አማራጭ ነገር አየት አደረገች። የሆነ ክፉኛ የሚፈልጋት ልጅ ጋር ተግባባችና በሱዳን በኩል ተያይዘው ተሰደዱ። ልጁ አሜሪካ ቤተሰቦች አሉኝ ሱዳን ከደረስን በኋላ ያስወጡናል ተጋብተን ምናምን ብሏታል። ምን ዋጋ አለው ለሁለት ዓመት ከተዝናናባት በኋላ አውላላ አሸዋ ላይ ትቷት ሄደ። ወደስድስት ዓመት በረሀ ለበረሀ ስትንከራተት ያች ቆንጅየ ልጅ መልኳ ሁሉ ወደግመልነት ተቀየረ። በመጨረሻ የሆነ እርዳታ ድርጅት የሚቀበልሽ ሰው ካለ የአሜሪካ ቪዛ እናመቻችልሻለን ይላታል። ወደቤተሰቦቿ ደውላ አሜሪካ የሚቀበለኝ ሰው የነፍስ ፈልጉልኝ ስትል ምን ቢሏት ጥሩ ነው? እንዴ በድሉኮ አሜሪካ ነው በዲቪ ከሄደ አራት ዓመቱ! 🤔

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Dec, 07:11


ጆሮ እንኳን የማትሰጡ መናጢወች አትሁኑ!
(አሌክስ አብርሃም)

ማንም ሰው፣ የፈለገ ጠንካራ ቢሆን  የሆነ ጊዜ ችግሩን የሚሰማው ሰው ይፈልጋል፤ የገንዘብም ይሁን ሌላ እርዳታ ምናምን ከእናንተ ባይፈልግ እንኳ በቃ የሆነ የሚሰማው ጆሮ የሚሰጠው ሰው። እና አንዳንድ "ብሽቅ" ሰወች አሉ፤ የገጠማችሁን፣ያዘናችሁበትን፣ ወይም የተበሳጫችሁበትን፣ ከአቅማችሁ በላይ ሆኖ ሊያሳብዳችሁ የደረሰን ከባድ ጉዳይ ስታወሯቸው ተሽቀዳድመው "እኔምኮ" ብለው የራሳቸውን እንቶ ፈንቶ ችግር ለአንድ ሰዓት የሚዘበዝቡ! ከችግራችሁ ጎን ችግራቸውን እያስሮጡ ሰዓት አሻሽለው ለመቅደም የሚጣጣሩ። ሰው በችግር ይወዳደራል? ቢያንስ ምንም ማድረግ ማፅናናት ባትችሉ እንኳን አይዞህ/አይዞሽ፣ ፈጣሪ ይርዳህ ፣ ያልፋል፣ ምንድነው ታዲያ እኔ በዓቅሜ ላደርግልህ የምችለው? ምናምን በሉ እስኪ! በየጓዳቸው በችግር እያለቀሱ በደስታ በሀዘን አብረው ሲደሰቱና ሲያፅናኑ የኖሩ አባትና እናቶች ነበሩኮ ያሳደጉን!  ወይስ ጎዳና ነው ያደጋችሁት? ቢያንስ ችግሩን ያወራችሁን ሰው ድካም ፣ህመም እንደተረዳችሁት ማሳየት ትልቅ ነገር ነው። በዓለም ላይ ችግር የሌለበት  አንድም ሰው የለም። ቢያንስ በየተራ መሰማማት ማንን ገደለ?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

22 Dec, 15:30


"ተፀፅቻለሁ"
(አሌክስ አብርሃም)

ትላንት ስለአንድ ውሻ ባጋራሁት ፅሁፍ ስር የሰጣችሁትን አስተያየት ስመለከት፣ በውሻ ዙሪያ ያላችሁ ዓለም አቀፍ እውቀት አናሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አይዟችሁ እኔም ከሶስት እና አራት ዓመት በፊት እንደእናተው ነበርኩ። ባደረኩት " ያላሰለሰ ጥረት" ዛሬ ላይ ያለሁበት ደረጃ ደርሻለሁ። (የት ደረስክ?) ጥያቄውን መጨረሻ ላይ እመልሳለሁ። ከዛ በፊት እነሆ ግርምቴ ....

ኮቪድ የገባ ሰሞን ሁሉ ነገር ሲዘጋጋ ቀድሞም በቁሙ የሞተው የአሜሪካዊያን ማህበራዊ ህይወት አፈር ድሜ በላ። ሰወች ይሄ ቀን ይመጣል ብለው አላሰቡምና ብቸኝነት ባዶ ቤት ሊያሳብዳቸው ሆነ። ከ1900 ጀምሮ የተሰሩ ፊልሞችን አይተው ጨረሱ ¡ ሪሞታቸው እንደጭልፋ እስኪጎደጉድ ጠቀጠቁ፣ ቲቪያቸው እንደምጣድ እስኪግል አንቦገቦጉት፣ ምንም አልረዳቼውም። "ኦን ላይን" ተጋቡ ፣ተፋቱ ፤ ምንም! በጭንቀት ማበድ፣ራሳቸውን ማጥፋት የማይታመኑ ነገሮችን ማድረግ ጀመሩ። ለዘመናት የገነቡት ግላዊነት መዘዙን ይመዘው ጀመር።

እውነት ለመናገር ብዙሀኑ የአበሻ ዲያስፖራ ግን ተስማማው! አማረበት ወፈረ ወዛ! ሳይሰራ እየተከፈለው ከዓመታት ድካሙ ትንሽ አረፈ፣ ልጆቹ ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ አገኘ። ምን እበላለሁ የት እኖራለሁ የሚል ሀሳብ አልነበረም። በየቦታው ምግብ ውሰዱ አትራቡብኝ አለች እናት አገር አሜሪካ። እትብታቸውም ወረቀታቸውም ለተቀበረባት ነዋሪወቿ ሁሉ በዘር በቀለም ሳታዳላ መቀነቷን እየፈታች ረብጣውን ከፈለች። የቤትና የመኪና እዳ ያለባችሁ አትጨነቁ ነገሮች እስኪስተካከሉ ክፍያው ይቆይ ብላ እደኛውን ሁሉ አረጋጋችው። ደበረኝ ብሎ ሚስቱን የሚደበድብ ካለ በዚህ ቁጥር ደውሉ ተባለ! ከታመማችሁ ህክምናውን በእኔ ጣሉት፣ ልጆቻችሁ ከቤታቸው ይማሩ ዘንድ አይፓድ ፣ላፕቶፕ ውሰዱ አለች። የሆነ ሆኖ ግን በዚህ ሁሉ ድጋፍና እርዳታም አሳዛኝና ዘግናኝ ጊዜ ነበር(ነበር እንዲህ ቅርብ ነው?)

የዛን ሰሞን ህዝቡ ብቼኝነቱን ለማስታገስ የቤት እንስሳትን ገዝቼ ልሙት አለ። የቤት እንስሳ ያልኩት "pet" የሚለውን ቃል ነው። United States Pet Market በዘመኑ ገጥሞት የማያውቀውን ርዝቅ አፈሰ። ውሻ ወርቅ ሆነ! ድመት፣ ለማዳ ጢንቸል ፣ ወፍ፣ ምን ያልተሸጠ አለ። ሰው ቢገዛ ቢገዛ እባብ ይገዛል ወገኖቸ? ከምር እባብ ገዝተው እንደድመትና ውሻ እቤታቸው የሚያሳድጉ ሰወች ብዙ ናቸው። "ፒተር ሻየን እንዳትደፋ" ይሉታል ጠረጴዛቸው ላይ የሚጥመለመለውን እባብ። (ለፃፍኩትም እንዴት እንደሚቀፈኝ) እና ሳይካትሪስቶች ደግሞ ይሄን የእንስሳ አብሮነት የተቀደሰ ሀሳብ ነው አሉና "ቡች ትሪትመንት" ለጭንቀት መፍትሄ ይሆን ጀመረ።

በዛ ሰሞን ምን ሰይጣን ሹክ እንዳለኝ እንጃ እኔም ውሻ መግዛት አማረኝ። ስለውሻ እንደጉድ አነበብኩ፣ ያላየሁትን የዮቲዮብ ቪዲዮ ጠይቁኝ። እውቀቴ ውሻን በማየት ብቻ ዘሩን እስከመለየት ፣ድምፁን በመስማት ብቻ ውሻው ምን እንደፈለገ ምን እንደተሰማው እስከማወቅ ደረሰ። አንዳንዴ ሰወች ጅራት ሲቆሉ ሁሉ የየትኛው ውሻ ባህሪ እንደተጠናወታቸው እገምት ነበር። ብዙ ግራ የገባቸው አዲስ የውሻ ባለቤቶችን ሳይቀር የሚያስደምም ገለፃ በማድረግ በእርሃብ የሚያውቋትን አገሬን በበጎ እስከማስጠራት ደርሻለሁ። ቀላል እንዳይመስላችሁ ወገኖቸ! እርስ በእርሳችን መገዳደል ብቻ ሳይሆን ለእንስሳ ያለንን ደግ ልብ ያሳየሁበት መድረክ ነበር። ጉራ እንዳይመስልብኝ አንድ ጎረቤቴ የነበረ ፈረንጅ የሰጠውን ምስክርነት እዚህ ላይ እዘለዋለሁ😀

እና ውሻ ለመግዛት ገበያ ወረድኩ። የሚያሳሱ ቡችላወች በመስተዋትና በአጥር ተደርድረው፣ ህዝብ እየመረጠ የሚገዛበት የውሻ ገበያ ተገኘሁ። ጎግል የእንስሳት ማቆያወች ውስጥ ከ$100- $250 ብር ብቻ በመክፈል ውሻ መውሰድ ይቻላል ስላለኝ ደረቴን ነፍቸ ነበር የሄድኩት። የገባሁት ግን የግል የውሻ መሸጫ ስቶር ውስጥ ነበር። የመጀመሪያዋን ቡችላ ሳያት "ነፍስ አልቀረልኝም " እንደሚሉት ዓይነት ሆንኩ። በረዶ የመሰለች ነጭ ውሻ ፣ፀጉሯ የሚርመሰመስ ፣አይኖቿ ሰማያዊ! ደግሞ ስታየኝ አባቷ ከትምህርት ቤት ሊወስዳት ዘግይቶ የመጣላት ህፃን ነበር የምትመስለው። ተፍነከነከች፣ እንደምወስዳት እርግጠኛ ሆንኩ። አንገቷ ላይ ስሟ እና ዕድሜዋ ተፅፏል። መስተዋቱ ስር ዋጋ ተለጥፎበታል። ዋጋውን ጎንበስ ብየ እንዳየሁት ባለማመን እጀን ወደኪሴ ልኬ መነፅሬን መፈለግ ጀመርኩ...ትዝ ሲለኝ መነፀር አልጠቀምም ለካ😀

ባጭሩ $9,500 ይላል። (ዘጠኝ ሽ አምስት መቶ ዶላር ልድገመው ዳላር) እንደማንኛውም አበሻ በብላክ ማርኬት አሰላሁት! በወቅቱ ምንዛሬ ወደሰባት መቶ ምናምን ሽ ብር ነበር። ዓይኔን ባለማመን ጉሮሮየን ጠራርጌ ከሚያስተናግዱት አንዷን በምልክት ጠራኋት። ዝርዝሩን ስጠይቅ የውሻዋ ታሪክ የተፃፈበት ወረቀት ሰጥታኝ በሰፊው አብራራችልኝ። የጤና ኢንሹራንስ ፣ ታክስ፣ ምናምን ተደማምሮ ወደ $10,700 ደረሰ። ብቻ ምን አለፋችሁ በብላክ ማርኬት ለማስላትም እራሴ ጨላለመብኝ። እድሜዋ ሁለት ወር ለሆነ ቡችላ ሚሊየን ፈሪ ብር ከፈልኩ አይደለምና ሲጠራ ሰማሁ ብል አገሬ መግቢያ አለኝ? በሽብርተኝነት፣ በሙስና፣ የመንግስትና ህዝብን ገንዘብ ሳይወስዱ በማባከን ፣ የእንግጭላ ወረዳን ድልድይ ፣ የህዳሴ ግድብን ተርባይን ተሸክሞ በመጥፋት፣ እንደውም አስገድዶ በመድፈር ሁሉ አትከሰኝም? ወገኖቸ ሲጀመር ውሻ ገባያ ወርጀ ዋጋ በመጠየቄ ሁሉ "ተፀፅቻለሁ"

ከዛን ቀን ጀምሮ ውሻ እየጎተተ የሚያልፍ ፈረንጅ ሲያጋጥመኝ የሚጮህና የሚራመድ ካዝና በቀበቶ አስሮ የሚጎትት ንክ ስለሚመስለኝ መንፈሱን ወግቸው አልፋለሁ። ግን የአገሬ ሰው እዚች ላይ ስማኝ! (((ይሄ ሁሉ ዋጋ የሚከፈለው ለውሻ እንዳይመስልህ፤ የነፍስን ብቸኝነት ፍራቻ ነው! አሁን እኛ ውሃ ቀጠነ ብለን እያፈራረስነው ያለው ማህበራዊ ህይወት ነገ በምንም የማይተመን የሩቅ ትዝታ የእግር እሳት እንደማይሆንብን ምን ማረጋገጫ አለን? አይቀፍም ሰው አጥቶ ውሻ የሙጥኝ ማለት?)))

በመጨረሻ ከላይ የት ደረስክ ላላችሁኝ ጥያቄ .... ውሻ የማይደርስበት ቦታ ደርሻለሁ። አሁን ላይ የቡችላ ውሻ ዋጋ ወርዷል ይላሉ ውሻ አድናቂወች! እስኪ ከታች ያሉትን ውሾች ፎቷቸውን እየጠነቆላችሁ ከነዋጋቸው ተመልከቱና ቀጥሎ ያለውን መፈክር በማሰማት የቅዳሜ ወጋችንን እናሳርግ

"እኔ ግን በዋጋ የማልተመን ውድ ፍጡር ነኝ ነኝ 😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

20 Dec, 10:31


ይህን ያውቁ ኑሯል? 😀

በዓለማችን ላይ እስካሁን የታወቁ 339 የውሻ ዝርያወች አሉ። መቸስ ስለውሻ እህ ብላችሁ ከሰማችሁ ዝርዝሩ ለጉድ ነው። እናላችሁ ይሄ ፎቶውን ከታች የምታዮት የውሻ ዘር ባሳንጂ ይባላል። ሲያድን ንስር በሉት፣ ቤት ጠብቅ ካላችሁት ወፍ ዝር አይልም፣ ታማኝነቱ ወደር የለውም፣ በውበትም በጣም ነው የሚያምረው በዛ ላይ ጎበዝ ዋናተኛ ነው። ፀጉሩ ስለማይበን አለርጅ አያስጨንቅም። ይሄን አስገራሚ ውሻ ከሌሎቹ 338 ዝርያወች ልዮ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? አይጮህም! በቃ በውሻ ታሪክ መጮህ የማይችል ብቸኛ ዝርያ ነው!! ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ የአፍሪካ አገራት ይህን የማይጮህ የውሻ ዝርያ "ባለቤት አልባ" እያሉ በመርዝ ይገድሉታል። አሜሪካ እና አውሮፓ ላይ እነዛ የሚጮሁት ተንደላቀው አይጥ ሲያዮ እየተደበቁ ሶፋ ላይ ይንደላቀቃሉ!! ከንቱ ዓለም!


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

20 Dec, 03:35


ሚስት የለህም እንጅ አግብተሀል!!
(አሌክስ አብርሃም)

ይሄ ፅሁፍ ገና ስታየው ረዘመብህ? ሳታገባ በፊት ግን ባንዴ ነበር ፉት የምትላት...አየህ ሚስት ባይኖርህም አግብትሃል!

"አግብትሃል?" ብላችሁ ስትጠይቋቸው "አወ...ማለቴ አላገባሁም" የሚሉ ወንዶች አልበዙባችሁም? የሆነ "ችት" ማድረግ የፈለጉ ምናምን ሊመስላችሁ ይችላል ...እኔም ይመስለኝ ነበር! ግን እውነታቸውን ነው አግብተዋ ...ማለቴ አላገቡም!  ነገሩን በትኩረት ስከታተለው ይሄ ነገር በብዛት የሚታየው ሶሻል ሚዲያ ፣በተለይ ቲክቶክ አብዝተው የሚጠቀሙ ወንዶች ላይ መሆኑን ደረስኩበት። ያገባ ሰው ከሚያገኛቸው ልዮ ጥቅሞች እና ከሚጠብቁት  ሐላፊነቶች መካከል የተወሰኑትን ንገሩኝ እስኪ? ...እና በዚህ ዘመን ሳትፈልግ ሁሉንም እንደተሸከምክ ላሳይህ?  አቆልቁል....

1ኛ. በጭራሽ ለማግባት ሀሳብ የሌለህን ሰውየ እጮኛ እንኳን ሳይኖርህ ፓስተር ቸሬ ይመጣና ለእጮኞች ብቻ የሚሰጥ የቅድመ ትዳር  ትምህርት ሳትወድ በግድህ  በየቀኑ ያስተምርሃል ፣ ዶ/ር እከሌ  ደግሞ ወደፍች ስለሚወስድ ስነልቦናና ማህበራዊ ኑሮ ቤተሰብ ያለውን መስተጋብርና መስተናግርት ሚስትን ስለመታገስ ይተነትንልሃል።

2ኛ. ያገባ ወንድ ሚስቱን በጡት ማስያዣ ወይም ካለማስያዣ፣ በስስ ፒጃማ ወይም ያለፒጃማ 360° የማየት መብት ይኖረዋል ! ቢራራቁም የመተያየት መብት አላቸው! ዌል እንግዲህ ቲክቶክ ባታገቧቸውም በርካታ ሴቶችን ሚስቶቻችሁ እስኪመስሏችሁ  በጌም ስም በኮንቴንት ክርኤቲቭ ምናምን ስም ላይቭ እንድታዮዋቸው  መኝታ ቤታቸው ድረስ እንድትዘልቁ ያመቻችላችኋል... የምታያት ባለትዳር ሴትም ልትሆን ትችላለች! አንዲት ሴት ከባሏ ጋር በአይንህ በመንፈስህ ተጋርተሃል ...አንድ በስጋ ሳታገባ በመንፈስ የሺ ባል ሁነሀል ። ካገባህ ደግሞ በስጋ አግብተህ በመንፈስ ተፋተሃል!

3ኛ. ትዳር ለወለዳችሁት ልጅ አስፈላጊውን የገንዘብና የሞራል ድጋፍ የማድረግ ሀላፊነት ይሰጣችኋል። ለሚስታችሁ የፍቅር ስጦታ መስጠትንም ይጨምራል ቲክቶክና ሌሎች ሶሻል ሚዲያወች ላይ ያልወለዳችሁት ልጅ ወይም ልጆች ይዘው "መቸም አንተ እያለህ ልጆቸ በእርሃብ አይሞቱም ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ አያልፍባቸውም ብየ እንጅ ልመና ምናምን አይመቸኝም  የሚሉ እህቶች  እንደጉድ የሚንጋጉበት መድረክ ሁኗል። በተለይ የሆነች ትንሽ ስኬት ነገርህን ደስ ብሎህ ለወዳጆችህ ካካፈልክ ፣ በንፋስም ይሁን በጎርፍ አገር ለቀህ ከወጣህ ወዘተ "እና ብቻህን ልትበላው ነው?" በሚመስል ፈጣጣነት ያልተፈራረምከውን ሰማንያ ይዘው ከች ይሉልሃል። አሳዛኙ ነገር ያንኑ ቴክስት ከዓመት ዓመት ለብዙ ሰወች ስለሚልኩ ነገሩ የአንድ ሰሞን ችግር ሳይሆን የተደራጀ የልመና ቢዝነስ መሆኑ ይገበሀል። ልጅን የማሳደግና ገቢህን የማካፈል በጎ ስራ ፍላጎት ሳይሆን ግዴታ ከተደረገብህ ባታገባም አግብተሀል።

4ኛ. ሚስትህ ጋር ብቻ ልታወራቸውና ከእርሷ ብቻ ልትሰማቸው  የሚገቡ "የግል ወሬወችን" 24 ሰዓት ሙሉ የሚያወሩልህ ሴቶች ስልክህን በከፈትክ ቁጥር ከመጡብህ በመንፈስ የጋብቻን ሀላፊነት ተሸክምሃል። ማውራት ብቻ አይደለም ላይክ አድርገኝም ትባላለህ። ቃል በነፃም ብትሰማው ተራ ነገር እንዳይመስልህ? ጆሮ አይሞላም እያልክ  የሰማኸው ነገር አንተን ያጎድልሃል።

5ኛ. በእናተ እንዳይደርስ ለመምከር ነው የምትል ባሏ ጋር የተፋታች ሴትዮ ለአንድ ሰዓት በትዳሯ ውስጥ ስለነበረ ገመና ከነተረከችህ ፣ ባልየው በተራው መጥቶ "እመነኝ ወንድሜ የዲኤን ኤ ምርመራ ካላሰራህ ልጅ አለኝ እንዳትል" ካለህ....በሌለህ ትዳር ተመክረህ በሌለህ ልጅ ስጋት ውስጥ ከገባህ ብታገባስ ከዚህ በላይ ምን ትሆናለህ?

6ኛ. ከቤትህ ስትወጣ የሪል ስቴት ኤጀንቶች፣ የባንክ ሰራተኞች "ለአዲስ ጎጆ ወጭ ብርና ቤት ወሳኝ ነው" እያሉ ሁለት ሁነው መገናኛ ያለህ እስኪመስልህ ቀንህን ግርግር ሲያደርጉብህ ፣ ድፍን የሴት ዘር ተጠራርቶ ስንት ሽማግሌ መላክ እንዳለብህ፣ እንዴት መንበርከክ እንዳለብህ ፣ምናይነት ቬሎ እንደሚፈልጉ ሳትጠይቃቸው ሲያወሩህ አልጋ ላይ ሁሉ ስለሚሰራው ጉዳይ ጥልቅና ዝርዝር መመሪያ፣ ማስጠንቀቂያና ማረሚያ ሲሰጡህ ....አግብቻለሁ ነው የምትለው አላገባሁም?

7ኛ. ሳትፈልግ የማታውቃት ልጅ ቤተሰብ ጋር ትውውቅ፣ ቅልቅል ታደርጋለህ  እናቷ ሁሉ በኦን ላይን ይመርቁሃል፣ አባቷ ስለልጃቸው ጨዋነት ይነግሩሃል ....የኦን ላይን አማቾች!

8ኛ.መጥፎ ትዳር ኑሮህ አልያም ባለጌ ሁነህ ሚስትህን መስደብና መደብደበ የትዳርህ አካል ከሆነ ፣ እርሱም ቲክቶክ ላይ በሽበሽ ነው። በቃል ቢሆንም ስትገባ ስትወጣ ትጠዛጠዛለህ!

9ኛ. ትዳር ሀላፊነቱ እንደበፊትህ እንድትሆን አይፈቅድልህም። ማንበብ ትቀንሳለህ ፣ ማህበራዊ ኑሮህ ውስን ይሆናል በጊዜ ትገባለህ ! ቲክቶክ ከጀመርክ ጀምሮ እንደበፊትህ ታነባለህ?ሰዎች ጋር ትገናኛለህ ታወራለህ? አግብትሀል የምልህ ምልክቱን አይቸ ነው!

10ኛ . ምን ቀረህ ጓድ ? እእእእእእእእ? እሱንም ቢሆን ጋብቻህ የመንፈስ ነውና ህልመ ሌሊቱ ፣ ምኞተ ጡዘቱ ስልክህ ላይ የምታየው እንትን  ወዘተው  ያው ያንተው ጣጣ ነው!  እስኪ ከእናንተ ያላገባ ቀድሞ ይውገረኝ ...ወገኖቸ አግብታችኋል ወይስ አላገባችሁም?


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

18 Dec, 15:51


በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1911፣ ታዋቂው የሞናሊዛ ሰዕል ፣ከተሰቀለበት ሙዚየም ተሰርቆ ነበር ! እና በዛ ዓመት ስዕሉ ተሰቅሎበት የነበረውን ባዶ ግድግዳ የጎበኘው ሰው ቁጥር ሳትሰረቅ በፊት የሞናሊዛን ስዕል ከጎበኘው ሰው ቁጥር በጣም ይበልጥ ነበር። እዚህ ጋ ነበረች እየተባባለ። ምንም ቅኔ ዘወርዋራ ነገር የለውም በቃ ይበልጥ ነበር ነው😀 ግን የምንጎበኘው ባዶ ነገር አልበዛባችሁም? እዚህ ጋ ነበርንኮ ምናምን እያልን ?


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

18 Dec, 02:35


"ሽቶ ነስንሱ ህንፃ ቀልሱ"

በአንዳንድ "መንፈሳዊ" መምህራን ክፉኛ እየተስፋፋ የመጣው "ሽቶ ነስንሱ ህንፃ ቀልሱ" አይነት ስብከትና እንጨት የሆነ ኢ ሰብአዊ አስተሳሰብ መረን እየለቀቀ ነው። ልማትን ማድነቅ ጤናማ ነው፣ ግን ህንፃና መንገድ የወንጌል ነፀብራቅ ከሆነ ይህ ሰው ያለው ወንጌል ንክች ያላደረጋቸው እነቻይና፣ የግንባታ ብር የሚመፀውቱን የአረብ አገራት የገነቡት ውብ ከተማ የምን ውጤት ሊሆን ነው? የዋናው መልእክት መዛነፍ ይቆየንና የሰውየውን ቃል አጠቃቀም ተመልከቱት "እብድ" "እብድ ቆሻሻ ነው የሚፈልገው" ... ወዘተ! ወንጌል ኢየሱስ የአእምሮ ህመምተኞች በየመቃብሩና በየቆሻሻው ሄዶ ሲፈውሳቸው እንጅ መገኛቸውን አውሮፓ አስመስሎ እንዳጠፋቸው አይነግረንም። ይሄ ሰው እነዛ "ቆሻሻ የሚፈልጉ" ሚስኪኖች ከአይኑ ዘወር መደረጋቸው በደስታ አምነሽንሾታል...ጓድ የት ሄዱ የት ወደቁ በል ...ተጠርተህ ከሆነ የተጠራሃው ህንፃ እንድትቆጥር አይደለም፣ እነዛን የወደቁ ሰወች የት ወደቁ እንድትል ነው! ብቻ የእግዚአብሔር ሰወች እግዚአብሔር ይሁናችሁ ፣ይሄ ዘመን ካለልኩ አዲስ ልብስ እንደተገዛለት የድሀ ልጅ ሰፋፍቶባችኋል! መንፈሳዊ ክሳት!


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

17 Dec, 17:05


ኦቲዝም፣ ዕምነት፣ መርፌ፣ ጠንቋይ፣ባህል፣እርግማን፣አየር ወዘተ. . .
(አሌክስ አብርሃም)

ይህን ፅሁፍ የምፅፈው (((በተለይ))) ኦቲስቲክ(የአእምሮ እድገት ውሱንነት ችግር) ጋር የተወለዱ ልጆች ላሏቸው ወላጆች ነው። የምፅፍበትም ምክንያት በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭ አገራት የሚኖሩ አንዳንድ ኢትጵያዊያንና ኤርትራዊያን ወላጆች ችግሩ ላለባቸው ልጆቻው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚያደርጉትን አሳዛኝ ነገር በተደጋጋሚ በማየቴ ምናልባት ትንሽ የሚጠቅማችሁ ከሆነ ሐሳቤን ለማካፈል ነው።

1ኛ. ኦቲስቲክ ልጆች ማለት «አዕምሯቸው የማይሰራ ልጆች» ማለት ሳይሆን «በገጠማቸው የአዕምሮ እድገት ውስንነት ምክንያት አዕምሯቸው በተለየ መንገድ የሚሰራ፣ነገሮችን በተለየ መንገድ የሚረዱ፣ስሜታቸውንም በተለየ መንገድ የሚገልፁ፣ በዚህም ምክንያት ያለው የተለመደው እየኖርንበት ያለው የአረዳድ ስርዓት ጋር በእኩል ፍጥነት ለመናበብ የሚቸገሩ ፣ አዕምሯቸው መደበኛውን የአረዳድ መንገድ እንዲያዳብር ፣ አጠቃላይ ሰርዓቱ ጋር እንዲግባባ ስልጠና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ልጆች ማለት ናቸው!

2ኛ. የኦትስቲክ ልጆች ወላጅ መሆን ማለት ምንም የሚያሳፍርም ሆነ የሚያሳቅቅ ነገር አይደለም። የልጆቹም የወላጆችም ጥፋት አይደለም፣ የእግዚአብሔርም ይሁን የአላህ ቁጣ አይደለም፣ ወላጆች በልጆቹ ባህሪ ምክንያት የምትከፍሉት እጅግ ከባድ ዋጋ ባለፈ ሕይወታችሁ ለሰራችሁት ሐጢያት ቅጣት ይሆን እንዴ ብላችሁ አታስቡ. . . አይደለም! ሰዎች ለሰሩት ሐጢያት እንደቅጣት ኦትስቲክ ልጅ እንዲወልዱ ፈጣሪ ቢወስን ኑሮ በምድር ላይ አንድም ወላጅ «ኖርማል» ህፃን አይወልድም ነበር። አንዴ ስለተወለዱ ወደፊት ማድረግ ስላለባችሁ ነገር እንጅ ለምን እንዴት አምላኬን ምን በድየው ወደሚል ምንም የማይጠቅምና በስሜትም በአካልም መልሶ እናተን ወደሚጎዳ ጥያቄ አትመለሱ!

3ኛ. ኦቲስቲክ ልጆች ምንም ጥያቄ የለውም ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ፣ በየደይቃው፣ በየቀኑ ፣ ከልጆች ጋር፣ ከመህበረሰቡ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት (በተለይም እንደኛ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ዝቅ ያለና የተሳሳተ አመለካከት ካለው ማህበረሰብ ጋር ) ብዙ የወላጅን ልብ የሚነካና መቸም የማይለመድ ማግለል፣ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ወዘተ ይኖራል። የሆነ ሁኖ ግን በትዕግስት እና በፅናት ለእነዚህ ልጆች ተገቢውን ሙያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ በመርዳት የኋላ ኋላ ራሳቸውን ችለው ትልቅ ቦታ እንዲደርሱ ማድረግ ይቻላል! በእርግጥ ይቻላል መፎክር አይደለም በሚሊየን የሚቆጠሩ ተመሳሳይ ችግር ጋር የተወለዱ ልጆች ስለቻሉ ነው። እንደውም ብዙዎቹ በሳይንስ ፣ኪነጥበብ ወዘተ ታላላቅ የፈጠራ ስራ አስመዝግበው ታይተዋል።

4ኛ. ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስ ኦርደር ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ፤ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ ሰማያዊ ቀለም ውሰዱ ሰማያዊም ሆኖ ብዙ አይነት ሰማያዊ ነው ያለው። ፈዘዝ ካለ ሰማያዊ ጀምራችሁ በደረጃ እስደማቅ ሰማያዊ ልታዩ ትችላላችሁ ልጆች ላይ የምታዩት የኦቲዝም ደረጃም እንደዛው የተለያየ ደረጃ ሊኖረው ስለሚችል ለሌላ ልጅ የሚደረግ ትሪትመንት ለእናተም ልጅ ይሰራል በሚል ከባለሙያ ድጋፍ ውጭ በወሬ ፣ በሶሻል ሚዲያ በሚሰጡ ሙያዊ ባልሆኑ አስተያየቶች ወዘተ በመነሳሳት ልጆቻችሁ ላይ ሙያዊ ያልሆነ ነገር አትሞክሩ። ችግሩ በአነስተኛ መጠን ኑሮባቸው ግን እናንተ የምታውቁት አይነት ስላልሆነ ልጆቻችሁ የሚያሳዩትን ወጣ ያለ ባህሪ «የባህሪ ችግር» አድርጋችሁ የምታዩም ልትኖሩ ስለምትችሉ ትኩረት ሰጥታችሁ ልጆቻችሁን ተከታተሉ።

5. እምነት ጥሩ ነው! ለልጆቹ ብቻ ሳይሆን ወላጆች መንፈስ ላይ የሚፈጥረው ጥንካሬና ፅናት ቀላል የሚባል አይደለም። ፀልዩ፣ በየእምነታችሁ አስፀልዩ ግን «የፈውስ ፆሎት» በሚል ሰበብ ልጆቹን በሚረብሽ መንገድ ህዝብ ፊትና ካሜራ ፊት እያቆማችሁ ለባሰ ጭንቀትና መረበሽ መዳረግ፣ አዲስ ፀበል ፈለቀ ወይም የሆነ ተመሳሳይ ችግር ያለበት ሰው ተፈወሰ በሚል መረጃ ልጆቹን ለአካላዊ እንግልት በሚያጋልጥ ሁኔታ አስቸጋሪና ላለባቸው ችግር የማይመቹ ሩቅ ቦታዎች በመውሰድ፣የሚያሳዩዋቸውን ባህሪያት ከእርኩስ መንፈስ ጋር በማያያዝ ውጣ አትውጣ ትግል እንዲዳረጉ ማድረግ ተገቢ አይደለም። በተለይ በውጭ አገራት የምትኖሩ ወላጆች፣ ልጆቹን ወደባለሙያ መውሰድ «ጅል የሚያደርግ፣የሚያፈዝ፣የሚያደነዝዝ መድሃኒት ይሰጧቸዋል መርፌ ይወጓቸዋል» በሚል አሉባልታ ልጆቹ ማግኘት ከሚገባቸው ተገቢ እርዳታ ማስተጓጎል ፈፅሞ ልክ አይደለም። በጣም የሚያሳዝን ነገር ሁሉ የሚያደርጉ ወላጆች አሉ (ጭንቀታቸው ይገባኛል) አገር ቤት ጭው ያለ ገጠር ያለ ጠንቋይ በማያውቀው ታሪክ ልጆቻቸው ላይ ወሳኝ እንዲሆን እስከመገበር የሚደርሱ ወላጆች ። ይሄን በቡና ይጠጡ ፣ይሄን ግራ እጃቸው ላይ ይሰሩ እያለ የወላጆቹን ጭንቀት ተጠቅሞ በሰለጠነ አለም ኋላ ቀር ዝባዝንኬውን የሚተበትብና የሚልክ ገንዘባቸውን የሚበዘብዝ ብዙ ነው!

መደምደሚያ!
ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ አየር መቀየር ጥሩ ነው በሚል አልተገናኝቶ ወሬ ልጆቹን ወደአገር ቤት የምትወስዱ፤ በተሟላ ተቋም ደህና እንክብካቤና ለዘመናት የዳበረ ትሪትመንት ከሚያገኙበት የሰለጠነ ዓለም፣ ገና ኦቲዝም ርግማን ነው ብሎ ወደሚያምን ማህበረሰብ ወስዳችሁ አታጎሳቁሏቸው። እውነቱን ለመነጋገር ኢትዯጵያ ለኦቲስቲክ ህፃናት የሚሆን ይሄ ነው የሚባል ቁሳዊም ስነልቦናዊም ዝግጅት የለም። ግንዛቤው ራሱ ሬዲዮም ቴሌቪዥንም ያለበት አገር እስከማይመስል ያስገርማል። እዚህና እዛ የተጀማመሩ ትናንሽ ትምህርት ቤቶች ሙከራቸው ቢበረታታም በብዙ ችግር የተተበተቡ እንዳሉም የማይቆጠሩ ናቸው። ለእረፍት እና ቤተሰብ ጥየቃ ካልሆነ በዚህ ጉዳይ የተሻለ ነገር ፍላጋ ብዙ ባትደክሙ ነው የሚሻለው።

እንደወላጅ የምታሳልፉትን ከባድ ፈተና ማንም ክብደቱን ያልሞከረው ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችል አይደለም፣ማውራት ቀላል ነው። መኖሩ ሌላ ታሪክ ነው! ግን ከንቱ ልፋት አይደለም! ከቻላችሁ በተመሳሳይ መንገድ የምታልፉ ወላጆች ሶሻል ሚዲያው ላይ ፕራይቬት ግሩፕ ከፍታችሁ በጋራ ችግሮቻችሁ ላይ ብታወሩ፣ መረጀ ብትለዋወጡ በተለይም በትምህርት የገፉና በዚሁ ጉዳይ የሚሰሩ ወላጆች ግራ በሚገባችሁ ጉዳይ ብዙ መንገድ ሊጠቁሟችሁ ይችላሉ ፣ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ ስራ ከሚሰሩ ድርጅቶች የተለያዩ የሐሳብም ይሁን ቁሳዊ ድጋፎችን ለማግኘትም በዛ መንገድ በአንድ ላይ መቆም የተሻለው መንገድ ይመስለኛል።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

17 Dec, 16:58


የ 13 ወር ግር ግር. . .

ሁሉም ድርጊት ውጤት አለው ...ለምሳሌ በታሪክ የታህሳሱ ግርግር ሲባል ሰምታችኋል! 1953 በወንድማማቾቹ ገርማሜ ነዋይና መንግስቱ ነዋይ ጠንሳሽነት ንጉሱ ላይ የተሞከረ መፈንቅለ መንግስት ነበር። ለኢትዮጵያ ልክ አዳምና ሂዋን ያችን ፍሬ የበሉባት አይነት ቅፅበት ነበር። ንጉስንም "መሳፈጥ" ይቻላል ለካ የተባለበት፣ ጅኒው ከጠርሙዙ የወጣበት! ከዛ በፊትም ግር ግር ባያጣንም ከዛን ጊዜ በኋላ ግን ነገረ ስራችን ሁሉ የባሰ ግር ግር ሆኗል! ነገሩን "ግርግር" ብሎ የሰየመው ሰው እስከአሁን ይገርመኛል። በአገራችን ጥር ግርግር ነው፣ የካቲት ግርግር ነው፣ መጋቢት ግርግር ነው፣ ሚያዚያ ግርግር ነው፣ ግንቦትማ በጣም ግርርርርርር ግርርርርርር ነው፣ ሰኔ ግር ግር ነው፣ ሐምሌ ግርግር ነው፣ ነሐሴ ግር ግር ነው፣ ጷግሜ እንኳን በአቅሟ ግር ግር ናት። የ13 ወር ግርግር !! ፖለቲካው ግርግር ነው ሲጨንቀን ግር ብለን የምንሄድበት የሐይማኖት ተቋም ግርግር ሀኗል፣ ዲፕሎማሲው ግርግር ነው፣ ዲያስፖራው ግርግር ነው፣ ትምህርቱ ግር ግርነው.... የምትጨምሩት ግርግር አለ? ቃላት እንዲህ ሲደረደሩ የሆነ የኑሮ ፎቶኮ ነው የሚመስሉት እስኪ ተመልከቱ ...?

ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግርግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር ግርግር

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

17 Dec, 10:12


ተረት ተረት ...
(አሌክስ አብርሃም)

ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ዛፍ ቆራጮች መጥረቢያና ገመዳቸውን ይዘው ዛፍ ለመቁረጥ ወደጫካ ይሄዳሉ! ጫካው አጋማሽ ላይ ሲደርሱ አንዳች የሚያክል አንበሳ መንገዱን ዘግቶ ጋደም እንዳለ ተገጣጠሙ። ደንገጥ ብለው ...
"እንደምን አደርክ የጫካው ንጉስ" አሉ በአክብሮት
"የጫካ ንጉስ? ከተማውንስ ማን ከልክሎኝ ..."አለ ቆጣ ብሎ አንበሳው። ምግብ ከቀመሰ ሶስት ቀኑ ስለነበር ... ሰወቹ ሰው ሳይሆኑ የሚራመዱና የሚናገሩ ቁርሶች መስለው ነበር የሚታዮት ...
"አይይይይ...ማለት የፈለግነው ....እ...." ሲሉ አቋረጣቸው

"አሁን እሱን ተውት ዛፍ ቆራጭ ናችሁ አይደለም?
"አወ ጌታየ "
"እናንተ ናችኋ ጫካውን ጨፍጭፋችሁ መኖሪያ ያሳጣችሁን"
"ኧረ ጌታየ ጋሬጣ እንዳይሆንብወት የደረቀውን እንጨት ነው የምንቆርጠው ...ደግሞኮ ጫካው ለእርሶ ይቅርና ለልጅ ልጆችወ ይበቃል....ዋናው ተቻችሎና ተሳስቦ መኗኗሩ ነው"

"ጥሩ እንግዲህ ጫካው ለመኖር ይበቃል ካላችሁ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ ...ለመሆኑ ለአንድ አንበሳ መኖሪያ የሚሆን ጫካ በውስጡ ስንት ዛፎች ሊኖሩት ይገባል? ነግሪያለሁ "ብዙ" እንዳትሉኝ ቁጥር ንገሩኝ?"

ሰወቹ ተጨነቁ ሺ ብንል ናቃችሁኝ ይላል ሺ ዛፍ ለአንበሳ የከተማ ሰወች ስቱዲዮ እንደሚሉትኮነው ...ሚሊዮን ብንል አጓጉል ግነት ነው ....በቃ አስር ሺ እንበል " ተባባሉና "ለእንደርሰወ ያለ ጌታ ለጊዜው አስር ሺ ዛፍ ይበቃል ጌታየ "አሉ።

አንበሳ ቀና አለና ወደኋላቸው እያየ "ማነህ በል የጫካውን ዛፍ ቁጠርና አሳውቀን " ብሎ አዘዘ። ዞር ቢሉ አንድ የተራበ ጅብ ከኋላቸው መንገድ ዘግቶ መቆሙን ተመለከቱ። ጅቡ ጫካውን ለግማሽ ደይቃ ቃኘት አደረገና ቶሎ ተመልሶ
"ዛፎቹ 9999 ናቸው አያ አንበሳ " አለና በሰፊው አዛጋ ።
አንበሳ ወደሰወቹ እያየ "አያችሁ በገለልተኛ ወገን በተደረገው ሳይንሳዊ ቆጠራ አንድ ዛፍ ጎድሏል... እንግዲህ እንኗኗር ካላችሁ አንድ ችግኝ በጋራ እንትከል ፣ግን እስከሚበቅል እዚሁ እኔ ጋር ትቆያላችሁ"
በቀጣዮ ቀን በደም የተጨማለቀ መጥረቢያና ገመድ በመንገደኞች ወድቆ ተገኘ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

15 Dec, 07:43


ለማያውቅሽ ታጠኝ እየተባባሉ ነው...

አስመራና አዲስ አበባ ከንፈራቸውን እየጠረጉ መጠዛጠዙን ጀምረውታል። ሬዲዮ ፋና ኢሳያስ አፈወርቄ የሰጠውን ረዢምና ጠብ ያለሽ በዳቦ ኢንተርቪው ተከትሎ ወገቡን ይዞ እያጥረገረገው ነው😀 ከአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ በ"ክርስማስ ጎርፍ" የተጫረ ሰነፍ ተማሪ እንደነበረ ሁሉ እንደገና እየነገሩን ነው😀 ደሞ አፉን ሲያላቅቅ አለማፈሩ ሲሉማ አልቻልኩም😂😂😂 ለኢትዮጵያ አንድም ጊዜ ሰላምና መረጋጋት አስቦ አያውቅም ሲሉም አእምሮየ "ማን ኢሱ?" ይልብኛል😀 ጋዜጠኞቹስ እሽ ...ይሄ ማሰራጫ አንቴናው ምናምን ተሳቆ ይሄንማ አላስተላልፍም አለማለቱ ይገርመኛል። ጋዜጠኞቹኮ "ኢሱ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር ማንም ጋር የለም" የሚለውን ዜና ሲሰሩ የለበሱትን ልብስ እንኳን ገና አልቀየሩም!

የሆነ ሆኖ ነፋሱ ሲታይ ትራምፕ ከሜክሲኮ አጥር የተረፈ አሸዋና ሲሚንቶ ከረዱን ድንበር እንጠር የሚያባብል አይነት "ሙድ" ላይ ነን😀 ካረዱንም የኢትዮጵያ እናት በድባብ ትሂድ የልጇን አጥንንት ለአጥር ታዋጣለች። ምንድነው ግን ? እርግማን ነው ? ድግምት ነው? ፍቅር ሰላም በየሁለት እርምጃው እየተደናቀፈ የሚደፋው ልባችን ውስጥ ምን አይነት እንቅፋት ቢቀመጥ ነው? የሆነ ሆኖ መታረቅ አለና በተለይ ሚዲያወች በየወንዙ ለሚማማል ፖለቲካ እባካችሁ ካለፈው ተማሩ፤ በለስላሳው ተሰዳደቡ! ፕሮፖጋንዳም ከሆነ ፕሮፌሽናል በሆነ ፣በህዝቦች መካከል ጥላቻና ቂም በማይዘራ መንገድ ብታደርጉት🙏


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

15 Dec, 06:35


እስኪ ትንሽ ቦታ...

ሴትና ወንድ "የቸርች ልጆች " በጣም ተጠጋግተው ተቀምጠው በሰበብ አስባቡ ሲነካኩ የተመለከቱ አገልጋይ ነገሩ ጨነቃቸው፣ በቅኔ ቢናገሩ በጥቅስ ልጆቹ አልፋታ አሉ። እና ሰውየው በትህትና " ሁለትም ሶስትም ሁናችሁ በስሜ በተሰባሰባችሁበት በመካከላችሁ እገኛለሁ ይላል ጌታ...ወጣቶች እስኪ በመካከላችሁ ለኢየሱስ ትንሽ ቦታ ክፈቱለት" ያሉት ነገር ነው የገጠመን😀 ነገሩን ለየት የሚያደርገው የዘመናችን መጣበቅ ጡጦ ባልጣለው ምዕመንና በንዋዮ ፍቅር በወደቁ አገልጋዮች መካከል መሆኑ ነው። እስኪ ትንሽ ቦታ ከፈት አድርጉ...

ለባለቤቱ ትንሽ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

14 Dec, 17:20


ወገኖቸ ቅዳሜም ትሰራላችሁ እንዴ?
(አሌክስ አብርሃም)

ይሁን ግዴለም! ብቻ ይችን ነገር ስሙ! አሜሪካዊው ሰውየና ሚስቱ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ፍርድ ቤት ሄዱና ከአፍሪካ መጥቶ ከጎናቸው የሚኖር ጎረቤታቸውን ከሰሱ! በቃ ችሎት ገተሩት! ምን አገናኛቸው? በዶሮ ነው? በልጅ ነው? በሚስት ወይንስ በድንበር? በሁሉም አይደለም ! ነገሩ በጣም ወዲህ ነው። እንደውም እኛን ጭቁኖችን ሳይመለከተን አይቀርም!

ከሳሽ ባል የ65 ዓመት ሰው ሲሆን ሚስቱም እዛው ዕድሜ ክልል አካባቢ ናት። በቂ ገንዘብ ስላልቆጠቡ ጡረታቸውን አራዝመው ትንሽ ለመስራት ያሰቡ፣ ግረው ጥረው የሚያድሩ ፈረንጆች ናቸው። እድሜ ልካቸውን ሰርተው ይሄን የሚኖሩበትን ቆንጆ ቤት ገዝተዋል፤ እዳውን በሰላሳ ዓመት ገና ሰሞኑን ከፍለው መጨረሳቸው ነው። ሁለት ልጆቻቸውን እንዲሁ በስንት ዓመት ብድር አስተምረው ራሳቸውን ችለው ሄደውላቸዋል። አርባ አመት ሙሉ ረዢም ረፍት ምን እንደሆነ አያውቁም፤ ወፍ ሲንጫጫ ወጥተው ጅብ ሲንጫጫ የሚመለሱ ላብ አደር ታታሪወች። ስራ ስራ ስራ ነው! አሁን ደግሞ መጦሪያ ለማጠራቀም ይሰራሉ። በአሜሪካ የተለመደ ስለሆነ ምንም ቅር ብሏቸው አያውቁም።

እንግዲህ ከአንድ አመት በፊት አንድ ናይጀሪያዊ ሰባት ልጆቹና ሚስቱ ጋር ሆኖ ከጎናቸው ያለውን ባለመዋኛ ገንዳ ቅንጡ የተንጣለለ ቪላ ገዝቶ ገባ። መልካም ጎረቤት ናቸውና አዲስ ገቢወቹን እንኳን ደስ ያላችሁ ሊሏቸው ሲሄዱ በጨዋታ መሀል ቤቱን በካሽ ከፍለው መግዛታቸውን ሰሙ። ብዙወች ቢያደርጉትም አሜሪካ በጣም ሀብታም ካልሆኑ እንዲህ ያለው ግዢ የተለመደ አይደለም። "What do you do for a living?" ቢሉ ናይጀሪያ ውስጥ ትንሽ የመንግስት ስልጣን የነበረው ሰው መሆኑንና መንግስት ጋር ባለመስማማቱ ከነቤተሰቡ አገሩን ትቶ መምጣቱን በትካዜ ነገራቸው። አዘኑ።

እያደር ግን የዚህ ናይጀሪያዊ ቤተሰብ አኗኗር ባልና ሚስትን ለከባድ ድብርት ዳረጋቸው። በእርግጥ ምንም የደረሰባቸው ነገር የለም፣ ስርዓት ያለው ጨዋ ቤተሰብ ነው። ግ...ን መዋኘት ነው...ጥግብ እስኪሉ መተኛት ነው...ደግሰው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ዘና ማለት ነው...ውድ መኪና ፣ ልብስ መቀያየር ነው፣ ደስታ ነው። በቃ ድፍን ቤተሰቡ እንዲች ብሎ ስራ አይሰራ አይማር... እነዛ ሚስኪን ባልና ሚስቶች ምናምን የተቀባች ዳቦና ቡናቸውን ይዘው ጧት ሱክ ሱክ እያሉ ወደስራ ሲሄዱ የአጅሬው ቤተሰብ በጧት እነደፀሐይ ወጥቶ በረንዳው ላይ ቡናና ጠረጴዛ ሙሉ ምግብ አቅርቦ ቁርስ ደግሶ ቀኑን በከባዱ ሲጀምር ያያሉ...ማታ በስራ ጨርቅ ሁነው ሲገቡ... ጎረቤት ዋይኑ ተደርድሮ ግሪል ጥብሱ እየጠረነ ሙዚቃው በስሱ ተከፍቶ ሳቁ ጨዋታው ደርቶ ያገኙታል ... ቅዳሜና እሁድማ ሰርግ ነው። ባልና ሚስት የመስኮት መጋረጃቸውን ገለጥ ያደርጉና ተቃቅፈው መጎምጀት ሆነ ስራቸው።እና መረራቸው! ከባድ የስነልቦና ጥቃትና ዋጋ ቢስነት እንዲሰማን ከመሆናችንም በላይ የስራ ሞራላችን ሙቷል ...በየቀኑ በምናየው ቅንጡ ኑሮና ያላሰለሰ ረፍት፣ ቀኑ ሁሉ እሁድ እየመሰለን ነው...በቃ እሁድ ስራ የገባን እየመሰለን ነው አሉ። ከሰኞ እስከአርባችንን እሁድ አድርገውብናል!

የአሜሪካ መንግስት ህግ ላይ ቀልድ አያውቅም፣ ነገሩን በከፍተኛ ጥሞና ሰምቶ ሲያበቃ ምናላቸው ?
አይዟችሁ ቻሉት! 😀ኤዲያ አሜሪካ ምን ህግ አለ! እና ቅዳሜ በቁርጥ ቤት በር ስታልፉ ምናምን በምታዮት ሁሉ አይዞን! ከሰኞ እስከአርባችሁን እሁድ ጋር ያምታቱባችሁ ጎረቤቶች የፌስቡክ ሰለብሪቲወች ወዘተወች ቢኖሩ ....
በቃ አይዞን!


@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

13 Dec, 18:34


አለሁ ማለት ከንቱ!
(አሌክስ አብርሃም)

ታላላቅ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ በየሐይማኖቱ ያሉ ሰባኪወች ዘማሪወች፣ሀብታሞች ፣ በጎ አድራጊወች ወዘተ...በማህበራዊ ሚዲያ ያላቸውን የተከታይ ቁጥር የተወዳጅነታቸው መለኪያ ሲያደርጉት እና ሲታበዮ ይታያሉ። ይችን ነገር ስሙ.....ራሻያዊዋ ሱፐር ሞዴል አይሪና ሸይክ የታዋቂው ኳስ ተጨዋች ክርስቲያን ሮናልዶ ፍቅረኛ ነበረች፤ ብዙ ሚሊየኖች ኢንስታግራም ላይ ይከተሏታል ያንቆለጳጵሷታል። ያው በቁንጅናዋ እንደሚከተሏት ነበር ሚዲያው ሁሉ የሚያራግበው። እና አንድ ቀን ክርስቲያን ሮናልዶ ጋር ፍቅራቸው አልቆለት ተለያዮ... አጅሪት በብስጭት "ከአሁን ጀምሮ ከራሴ ማንነት ይልቅ የክርስቲያኖ ፍቅረኛ ስለሆንኩ ብቻ ፎሎው ያደረጋችሁኝ አንፎሎው አድርጉኝ" ብላ ለጠፈች። በ24 ሰዓት ውስጥ 11 ሚሊየን ህዝብ አንፎሎው አድርጓት ጭር። በዘራችሁ አይድረስ! በሶሻል ሚዲያ ታሪክ እንዲህ አይነት የአንፎሎው ጎርፍ ታይቶ አይታወቅም! በእርግጥ አሁን የራሷን ተከታይ አፍርታለች።

ምን ለማለት ነው ....የአገራችን ታዋቂወች ....የሚከተላችሁ ህዝብ ከስራችሁ የተኮለኮለው ለምትመሯት አገሩ፣ ለምትሰብኩለት ዕምነቱ፣ ለምትነግሩት መረጃ ፣ ለምትረዷቸው ሚስኪኖች ሲል እንጅ እናንተን በግላችሁ ወዶ ላይሆን ይችላል የት አውቋችሁ? አንድ ቀን ከስልጣን ወይም ከተደገፋችሁት መድረክ ስትወርዱ ጥላችሁ ራሱ የማይከተላችሁ ጥላ ቢስ ልትሆኑ ትችላላችሁ።
አለሁ ማለት ከንቱ😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

12 Dec, 16:56


የተስፋየ ካሳ የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ.... ልጁ ቤት ሊከራይ ሄዶ አከራይ እያሳዮት ነው።
"ይሄው እንግዲህ ቤቱ...በዚህ በር አለው...በዚህም በር አለው...ከፈለክ ይሄንኛውን ወደጓሮ የሚወስደውን ትዘጋና  ...ዋናውን  በር ደግሞ ትከፍታለህ ያው የገባንበት ማለት  ነው...." ሲሉት

"እንዴ ማዘር ይሄ ሁሉ በር ምን ያደርግልኛል?"

"አሄሄ እሱንኳ ተወው ፣ ሌባ መሆንህን ደላላው ነግሮኛል ባንዱ ፖሊስ መጥቶ ሲቆም በሌላው...." 😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Nov, 17:01


What is value judgement?

የማህበረሰብ እሴቶች መቼና እንዴት ይሠራሉ? እንዴት ይሸረሸራሉ? መቼ ይፈርሳሉ?

ከ30 ዓመታት በፊት ያሉት Values አሁን ይሠራሉ ወይ? በእኛ ሀገር ከተሞች ያለው ሞራል ቫልዩ ከዐረብ ሀገራት ጋር አንድ ነው ወይ?

እስኪ የሞራል ሰባኪ መጽሓፍቶችን ጥቆማ አድርጉ።

እኔ አንድ ሁለቱን ልጠቁም።

#Antigone

#The_Teachings_of_Don_Juan

ሌሎቹን ደግሞ የእናንተን ዓይቼ ጨምራለሁ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Nov, 11:13


ንጉሱ ብር ቸገረው። በጣም ብር አስፈለገው። ማስታወሻ ላይ ያነበብኩት እውነተኛ ታሪክ ነው። ገንዘቡን ከሕዝቡ ለመሰብሰብ ሞከረ ! ሕዝቡ ግን በመዋጮ፣በግብር፣ በቅጣትና በጉቦ ተማሮ ነበርና ለዚህ ቢሰጡት ቢሰጡት በቃኝ ለማያውቅ ንጉስ መስጠት አልፈለገም። በመጨረሻ ንጉሱ መላ ዘየደ። በህዝቡ ልክ የሽንት መሽኛ ፖፖ አስመረተ፣ ፖፖው ላይ የንጉሱ ምስል ከነዘውዱ እንዲታተም አዘዘ። እና. . ."ፖፖውን ያልገዛ ይቀጣል" የሚል ህግ አወጣ፣ሁሉም ገዛ።

ፖፖውውን ከገዛ በኋላ የሸናበት የንጉሱ ምስል ላይ ስለሸና ይቀጣል!!
ፖፖውን ገዝቶ ሳይሸናበት ያስቀመጠ ደግሞ ያው ይቀጣል! ላይሸናበት ለምን ገዛው? ይሄ ጥጋበኛ ብር ቢተርፈው ነው የማይጠቀምበትን ፖፖ የገዛው! ለማንኛውም ሰሞኑን የትራፊክ ቅጣት አማረረን የምትሉ ሹፌሮችም ሆናችሁ ሌሎች ተቀጭወች ያው ህግ አክብሩ ነው የምለው😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Nov, 14:49


የፀጋን ወንድሞች እየጠበኩ ነው!
(አሌክስ አብርሃም)

አብደላ የሚባል ሚስኪን የአዕምሮ ህመምተኛ ነበር ። ጫቱን ይዞ የሆነች ሙዚቃ ቤት በር ቁጭ ይላል፣ በቃ በምድር ላይ ሌላ ስራ የለውም። ሁሉም ሰው ግን ይወደዋል። አስባችሁታል ለመወደድ የምትደክሙት ድካም? የምትናከሱት ንክሻ፣ የምታልፉበት ጦርነት፣ የምትበሉት ፍዳ? አብደላ ግን በዝምታ ሙዚቃውን እየኮመኮመ ጫቱን እየቃመ ቃል ሳይተነፍስ በሁሉም ይወደዳድ ነበር።

አንድ የክረምት ቀን ፣ክረምት አግቢ የሚባሉት በረሮዎች እንዳለ ሰፈሩን ሞልተውት ይርመሰመሳሉ! አብደላ እዛቹ ቦታው ላይ ብቻውን በሳቅ ፍርስ ሲል አገኘሁትና "አብደላ ምን ያስቅሃል ?" አልኩት
እየሳቀ በጫት እንጨት ወደአንድ ድመት ጠቆመኝና « አንዲት አንበጣ በረሮዎቹን እያሳደደች ስትለቅም ስትለቅም ስትለቅም . . . እዛ አበባው ጋ ስትደርስ እንቁራሪት ከድንጋዩ ስር ወጥታ አንበጣዋን ቀጨም አድርጋ ዋጠቻት ህህህህህህህ . . .ከዛ የሆነች ወፍ ከላይ ከጣራው ተወርውራ እንቁራሪቷን ቀጨም ህህህህህ . . .ከዛ ድመቷ. . .ያች ድመት ወፏን ቀጨም ! ህህህህህህህህህህህ አሁን ፀጋን እየጠበኩ ነው» አለኝ ድንገት ወደፀጋ ሱቅ በጉጉት ዞር ብሎ እየተመለከተ።
" ፀጋ ደግሞ እዚህ ውስጥ ምን አገባት?" አልኩት አብሬው እየሳኩ! ፀጋ አለፍ ብሎ ወተት መሸጫ ቤት የነበራት ቆንጆ ሴት ነበረች።
«ጧት ይች ድመት የፀጋን አንድ ባልዲ ወተት ደፍታባታለች እንዳለ ደፋችው! ብዙ ወተት፣ መሬቱ ነጭ ሆነ ህህህህህ. . . ዘነዘና ይዛ ዛሬ ካልገደልኳት ፀጋ አይደለሁም ስትል ነበር ህህህህህ» ዞር ብየ ድመቷን ተመለከትኩ፣ እውነትም የወፍ ላባ ዙሪያዋን ተበታትኖ ደም የተለቀለቀ አፏን በምላሷ ትጠራርጋለች። ይሄ ከሆነ ከስንት ዓመት በኋላ ፀጋ ወታደር ባሏ በሌላ ወንድ ጠረጠርኳት ብሎ እንደገደላት ሰማሁ። እኔ ራሱ ራሴን በአብደላ ቦታ ተክቸ የፀጋ ወንድሞች ባሏ እስሩን ጨርሶ ሲወጣ ይምሩት ይሆን? እያልኩ ማሰቤን አስታውሳለሁ . . . ሲዝቱ ነበርና። አብደላም ዛሬ የለም ሰፈሩ ሲፈርስ የት እንደሄደ እንጃ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Nov, 18:52


የማንን ጅራፍ ነው የምንገረፈው?
(አሌክስ አብርሃም)

በቀደሙት ዘመናት ወንጀል የሰሩ ሰወችን በግርፋት መቅጣት /Flagellation/ የተለመደ ነበር። ከጅራፉ በላይ ሰወችን የሚያዋርድ፣ በህዝብ ፊት የሰውነት ክብራቸውን የሚያስጥል ከዚያም በላይ እስከእለተ ሞት አካልም አዕምሮም ላይ ጠባሳውን የሚተው ኢ ሰብአዊ የቅጣት አይነት ነው። ለጥፋታቸው የተፈረደ ነውና ቢያስቀይምም ሁሉ እንደየስራው ሒሳቡን ያወራርዳል ይባል ይሆናል።

እኔ የገረመኝ በ17ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የነበረ አንድ አስገራሚ የግርፋት አፈፃፀም ነው ። ወንጀል የሰራው ሰው የ"ደህና ቤተሰብ" አባል ከሆነ ወይም ገንዘብ ካለው። በእርሱ ፈንታ የሚገረፉለት ሰወችን በገንዘብ ይገዛል። እነዚህ ሰወች መገረፍ መተዳደሪያቸው ነው። ብር ይከፈላቸዋል፣ እርቃናቸውን ቁመው የጥፋተኛውን ጅራፍ ይቀበላሉ። ባገኙት ብር ቤተሰብ ያስተዳድራሉ። በዘመኑ ይህን ነገር የሚቃወሙ ቢኖርም "ያስገደዳቸው የለም በፍላጎታቸው ነው" ይባላል። በተዘዋዋሪ ግን የሚያስገርፋቸው ድህነት ነበር። ድህነቱ ደግሞ የገራፊው ስጦታ ነበር።
#
በዚህም ዘመን ጅራፉ ይለያይ እንጂ ግርፋቱ ብዙ አይነት ነው። ቲክቶክ ላይ እያየሁ ነበር። በደጉ ቀን ተገለመጥኩ ብላ የምታለቅስ ቆንጆ የሰው ልጅ ይቋቋመዋል የማይባል ዘለፋና ማንቋሸ እንደቆሻሻ ገንዳ ሲደፋባት እየሳቀች አበባና ምናምን ስትጠብቅ ታዘብኩ። ለነዛ ሳንቲሞች ጅራፉን መቻል! የትኛውንም ውርደት መቀበል። ስቃይን ስራ ማድረግ። እየከፈሉ የሚገርፉን እነማን ናቸው? እላለሁ በውስጤ። የሆነን ሰው ቅጣትማ ካለሀጢያታችን እየተቀበልን ነው። ሰው በስርዓት ከተማረ ከሰራ አገሩንና ህዝቡን ካገለገለ ስቃዮን ምን አመጣው? እንደው ተሸፋፍኖ እንጅ ብዙሀኑ የህሊናው ጀርባ ላይ የዘመኑ ጅራፍ የተወው ጠባሳ አይጠፋም። ጅራፉ ባይታያችሁም ህመሙ ከተሰማችሁ ፣ ህመሙ ቢያስጠላችሁና ከአቅማችሁ በላይ ቢሆንም ለመኖር ስትሉ ከቻላችሁት ያ ነው ያልኳችሁ ጅራፍ!!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

23 Nov, 10:05


በነገራችን ላይ የኑሮ ደረጃህን ሁልጊዜ  የአለም ባንክ እስኪነግርህ አትጠብቅ። የድህነት ወለል ጣራ እያልክ አትድከም።  ድህነትህን ቤት ባፈራው ነገር ለካ።  ለምሳሌ ለይሄ ፎቶው ላይ የሚታየው ምንድነው?  አየህ! መልስህና አጠቃቀምህ ደረጃህን ይነግርሃል ....ሐብታሞች በብዛት ገዝተው በብዛት ለብር ማስያዣነት ይጠቀሙበታል። ደሀ ሴቶች ለፀጉር ማስያዣ ፣ ደሀና ከይሲ ፈላወች ወስፈንጠር ሰርተው አላፊ አግዳሚ ለመነጀስ ይጠቀሙበታል። አንድ የሀብታም ልጅ በወስፈንጠር ሲጫወት አታገኝም። ይሄን ላስቲክ "ለቁርጥማት ጥሩ ነው" ብሎ እንደብራዝሌት እጁ ላይ የሚያስር ቁርጥማታምም አለ። ምን ላይ ነን ?😀 በነገራችን ላይ ይሄንንም ከቻይና ነው የምናስመጣው አይደል? ቁርጥማቱ እንደአገር ነውኮ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

21 Nov, 03:56


ቄሱም ዝም መፅሐፉም ዝም

በስመ ጥሩው የአገራችን የስነመለኮት ትምህርት ቤት "EGST" እና በ"Church of Sweden" መካከል ተደረገ ስለተባለው በትብብር የመስራት "አጋርነት" Getahun Heramo በተደጋጋሚ ያውም በማስረጃ እየፃፈ፣ ስለጉዳዮም ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጥ እየጠየቀ ነው። ይህ የስዊዲን ቤተክርስቲያን ለይቶለት ግብረሰዶማዊነትን የተቀበለ፣ ይህንኑ የሚሰብክ፣ የሚያስተምር ፣እንደውም ይህ ልምምድመፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወደሚል ፀያፍ አስተምሮ የገባ ተቋም ነው። እንግዲህ የኛው የስነመለኮት ትምህርት ቤት እዚህ ተቋም እግር ስር ሲርመጠመጥ ምንድነው ችግርህ? ቢባል መልስ ለመስጠት አሻፈረኝ ብሏል። የሚገርመው የተቋሙ ዝምታ ብቻ አይደለም። አጥር ፈረሰ ፣ሞንታርቦ አጮሀችሁ ተባልን፣ባልና ሚስት ተጣላ፣ ባለስልጣን አስነጠሰ እያሉ በመግለጫ አገር ይያዝ የሚሉት የክርስቲያን ህብረ መሪወች ፣ "መንፈሳዊ ሰለብሪቲወች" እንዲሁም ይህን ፀያፍ ልምምድ ወጋነው ነቀልነው እያሉ በየጉባኤው ሲጮኹ የሚውሉ ሁሉ ዝም ጭጭ ብለዋል?

ማድበስበስ መፍትሄ አይሆንም። ይሄ የአንድ እምነት ተከታዮች ጉዳይ ብቻ አይደለም። በእርግጥም የእምነቱን ተከታዮች በማያውቁት ፈፅሞም በማይቀበሉት ነገር ስማቸውን ማስነሳትና ተቋማዊ ማስመሰል ነው። እንደአገር ወደምድራችን ለሚገባ "የጥፋት ውሃ" የመግቢያ ሽንቁር መሆን ነው። በተቋሙ የተማራችሁ፣ የምታስተምሩ የተከበራችሁ መምህራን እባካችሁ ለምን በሉ! ዝምታችሁ በዚሁ ከቀጠለና ተቋሙ መልስ መስጠት ካልቻለ፣ ፍላጎቱ የተቋሙ ሳይሆን የግለሰቦች ነው ወደሚል መደምደሚያ ይወስዳልና ተቋሙ ውስጥ በሀላፊነት የምትሰሩና ጉዳዮ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላችሁን ግለሰቦች በስም በፎቶ እየለጠፍን መልስ መጠየቃችንን እንቀጥላለን። እንደአገር ይመለከተናል። ግብረሰዶም በኢትዮጵያ ወንጀል ተብሎ የተበየነ ልምምድ ነው። ጥያቄው በእምነት ስም ወንጀል ከሚሰብክ ተቋም ጋር ያደረጋችሁት አብሮ የመስራት ስምምነት ምንድነው? ልክ ነን ካላችሁ ለምንድን የምትሸፋፍኑት? ንገሩንና አብረን ልክ እንሁን! መልስ መልስ መልስ። እናንተ ታልፋላችሁ የዘራችሁት ዘር ግቢያችሁ ውስጥ አይቆምም እየተሳበ አገር ይሸፍናል። መልስ እንሻለን!!ያለን ችግር የተሸከምነው ቀንበር የበቃናል።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

19 Nov, 06:38


አንድ የዱር አጋዘን ኮለራዶ የሚባለው የአሜሪካ ግዛት ወደሚገኝ የምግብ መሸጫ ሱቅ ድንገት ገብቶ ይቆማል። እንግዲህ አጋዘን እንኳን በዚህ ልክ ሰወችን ሊቀርብ የቅጠል ኮሽታ እስከጠረፍ የሚያስሮጠው እንስሳ ነው። በአቅራቢያው ካለ ጫካ ወጥቶ ነው እንግዲህ። እና የሱቁ ባለቤት ይሄ አጋዘን እንደተራበ ስለገባው የታሸገ ለውዝ ይከፍትና ይሰጠዋል። ያችን አጣጥሞ ወጥቶ ወደጫካው ሄደ። ከሰላሳ ደይቃ በኋላ ግን አጋዘኑ ቤተሰቡን ( ሚስቱንና ሁለት ልጆቹን) ይዞ ወደሱቁ ተመለሰና ቁልጭ ቁልጭ። እንግዲህ በአጋዘንኛ "እኔና ደጀኔ ቸግሮናል" ነው😀 ርሀብ የሞራልም የተፈጥሮም ባህሪያችሁ የማይፈቅድበት ቦታ የሚያቆም አሳዛኝ ነገር ነው። በተለይ ቤተሰብ መቸም አይራብ!! እንደአገር እንደህዝብ ራሳችንን ነው ያሳየኝ። ለቤተሰብ ሲሉ ከከብር አጥራቸው ወጥተው ሰው ፊት ለቆሙ ሁሉ እስኪ መልካም ዘመን ይምጣ🙏

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

18 Nov, 19:38


የተወጋ ትዳር!
(አሌክስ አብርሃም)

በነገራችን ላይ ቆንጆ ሴት ስላገቡ ቆንጆ ልጆች መውለድ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወንዶች አሉ። ስለዚህ ለትዳር ቆንጆ ሴት ያሳድዳሉ። በሰው ምርጫ መግባት አልፈልግም። ግን የአንድ ጓደኛየን ተሞክሮ ማካፈል እፈልጋለሁ። ለነገሩ የሱም ተሞክሮ ለህይወታችን ምንም አይጨምርም እንተወው። ዋናው ነገር ግን ልጆች ሲወለዱ ሜካፕ፣ሂውማን ሄር ፣የተወጋ ከንፈር፣ በሰርጀሪም ይሁን በኤክሰርሳይስ የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅና የተጠና አማላይነት ከእናታቸው አይወርሱም። በኋላ የኔ አይደሉም እንዳትሉ!

በዘር የሚተላለፉ የጤና ችግሮች፣ ደከም ያለ አዕምሮ፣ ባህሪ ወዘተ ግን ሊወርሱ ይችላሉ። እና ስትጋቡ ከፍቅር አልፋችሁ "ስለምርጥ ዘር" እስከማሰብ የደረሰ የከብት እርባታ መንፈስ ካደረባችሁ ቢያንስ ለትውልዱ ስትሉ ጤናና ባህሪ ላይ ላይ አተኩሩ።

ሴቶችም እንደዛው "ከሚያምር ረዢም ወንድ የሚያምር ልጅ " የሚል መፎክር ውስጣችሁ ካደረ ፣ የምትመርጡት ለምርጥ ዘር የሚሆን ኮርማ እንጅ ባል አይደለም። መለሎው ኮርማ የቅድም አያቱን ስንዝሮ ቁመትና መጋፊያ እግር ለልጃችሁ ሊያወርስ ይችላል። ሆስፒታል አቀያይረውብኝ መሆን አለበት እስክትሉ የጀነቲክስ አልጎሪዝም እብድ ነው። የሆነ ሁኖ መሠረቱ ከተወጋ ትዳር ቆንጆ የምትሉትም ይወለድ መልከ ጥፉ ዋጋው ውድ ነው። ከምታፈቅሯቸው ውለዱ ፣ ከፍቅር የተወለዱ መልአክ ናቸው። ልጆች ምንጊዜም ውብ ናቸው። አስቀያሚ የሚያደርጓቸው አስቀያሚ ሒሳብ የሚሰሩ ወላጆች ፣ የእነዚህ ወላጆች ስብስብ የፈጠረው ማህበረሰብ ነው። የተወጋ ትዳር የተወጋ ማህበረሰብ ይፈጥራል።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

16 Nov, 17:18


ፊትአውራሪ መሸሻና ማይክ ታይሰን!

አቤት የነገር መገጣጠም እናንተ! ለካ የዛሬውን የቦክስ ግጥሚያ ከሃምሳ ዓመት በፊት በተፃፈው በፍቅር እስከመቃብር አንብበነው ነበር! ፊታውራሪ መሸሻ በ70 ዓመታቸው በእድሜ በእጥፍ የሚበልጡትን ዘመን ያነሳው ባላባት ካልተፋለምኩ ሙቸ እገኛለሁ አሉ። ሰውየው በጨዋነት ያሳደጓት ልጃቸው ሰብለወንጌልን ለጋብቻ ጠይቆ ሲፈቀድለት «ዕድሜዋ ስለተላለፋት በድንግል ወግ በሰርግ አላገባም፣ በፈትነት ልብሷን ይዛ ቤቴ ትግባ» በማለቱ ነበር። አበዱ ፊታውራሪ! "እንደማንም ውሃ ስትቀዳና ከብት ስትጠብቅ? ጫካ ለጫካ እረኛ ጋር ስትማግጥ ክብሯን እንዳስወሰደች ባላገር? ልጀን እንዴት እንዲህ ይላል? ዳይ ፈረሴን ጫኑ ፣ጋሻና ጦሬን ወልውሉ" አሉ።
«ምነው ፊታውራሪ በዚህ እድሜወት ጎረምሳ ጋር?» ቢባሉ

«እፋለመዋለሁ! ይሄን የመሰለ የክብር ሞት ደጀ ድረስ መጥቶልኝ አታስመልጡኝ! ቢገለኝም የሞተ ሽማግሌ ገደለ እንጅ ጀግና አይባል፣ ብገለውም መሸሻ ሬሳው እንኳን ጀግና ገደለ ነው የሚባል በዛም አለ በዚህ ክብሩ የኔው ነው»😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

16 Nov, 09:56


አንዳንዱ አባት ፀልዮ ነው የሚሳሳተው?!
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ አብሮን የተማረ ጓደኛችን ወደአውሮፖ በሊቢያ በኩል ልወጣ ሞክሬ ለአንድ አመት ከዳከርኩ በኋላ ነገሮች ተበላሹብኝ፣አሁን ወደኢትዮጵያ መመለሻ የተወሰነ ብር ፈልጌ ነበር ፣ይልና ለአንዱ ጓደኛችን ይነግረዋል። ልጁ የተረጋጋ ከተመረቅን በኋላም አሪፍ ስራ የነበረው ልጅ ስለነበር በነገሩ አዘንን። በቃ ሁላችንም የቻልነውን እናድርግ ተባለና የተወሰነ ብር ተዋጣላት፣ በሰላም ኢትዮጵያ ገባ። ከስድስት ወር በኋላ አንድ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ።

እንዳለ የተዋጣለትን ብር አመስግኖ ላሰባሰበው ልጅ ይመልሳል። ነገሩ ብድር ስላልነበር ሁላችንም ተገረምን። እና ምን እንደገጠመው ስንጠይቅ ከነመኖራቸው የማያውቃቸው ሁለት የአባቱ ልጆች አፈላልገው አግኝተውት እህቶችህ ነን ለዓመታት ስናፈላልግህ ነው የኖርነው። አባታችን አባትህ ነበር። የኑሮ ችግር የለብንም ምናምን ይሉታል። በአጭሩ የሞላ የተረፋቸው ሃብታም እህቶች በአንድ ጀምበር ያውም ከሆነ አውሮፓ አገር ሄደው ያንን ከርታታ ኑሮውን ቀያየሩት። እሱም ሰበብ ነበር የሚፈልገው መስመሩን ይዞ "ስትመጡ ወጭ በኔ ነው " ብሏል አለኝ። አንዳንድ አባቶች ፀልየው ነው መሰል የሚሳሳቱት ብሎ ቀለደ አንዱ ወዳጃችን።



ገንዘብ ያሰባሰበው ወዳጃችን በነገሩ ውስጡ ተነካ፤ እኔምኮ ላገኛቸው ፈርቸ እንጅ አባቴ ከመሞቱ በፊት ከሌላ የተወለዱ ሁለት እህቶችና አንድ ወንድም እንደነበሩኝ ነግሮኛል ይለኛል። እንዴ ምን አስፈራህ ዘመድ ጥሩ ነው፣ አግኛቸው በማለት አበረታታሁት። መከርኩት። በሞራል የሶስት ወር ረፍት ወስዶ ሄድና አፈላልጎ አገኛቸው። ታሪኩን ሳሳጥረው ወደአሜሪካ ሲመለስ በቦሌ ሄዶ በሊቢያ በኩል በእግሩ የተመለሰ እስኪመስለኝ ከስቶ በአንዴ ሽበት ሁሉ ወሮት ሳገኘው ደነገጥኩ።

ምን እንደገጠመው በሰፊው አጫወተኝ። እህቶቹን አገኛቸው። አንዷ ባሏን በሊጥ መዳመጫ ገድላ እስር ቤት ነበር ያገኛት፣ ወንድሟ እንደሆነና ከአሜሪካ እንደመጣ ሲነግራት «እስከዛሬ አሜሪካ በርገርህን እየገመጥክ ነው እንዲህ ስንቸገር ዝም ያልከው? ብላ ካፈጠጠችበት በኋላ ፣ከእስር ቤት እስከምትፈታ አምስት የቲም ልጆቿን እንዲንከባከብ አስጠንቅቀዋለች። ዘጠኝ አመት ነው የተፈረደባት ሁለቱን ጨርሳለች። "ሰባት ዓመት እሩቅ እንዳይመስልህ፣ አትወጣም ብለህ በዛው ትጠፋና እንደገና ወደኢትዮጵያ ዙረህ አታይም" ብላ ሁሉ ዝታበታለች።

ሌላኛዋ እህቱ ጫት ቤቷ በልማት ፈርሶባት ያገኛታል። ከሚከስር ብላ የተረፈውን ጫት እዛው ፍርስራሹ ላይ ፈርሻ እየቃመች ፣ሁለት ጉንጯ ተወጥሮ የየመን ወታደር መስላ ነበር። እንኳን የአባቷን ልጅ ከአባት መወለዷን ሁሉ በብዙ ማብራሪያ ነው ያስታወሰችው! ለዚያውም «ኦ አስታወስኩ አባቴ በሱማሊያ ወረራ ጊዜ ነው የሞተው፣ ተረግዠ ነበር ወደጦርነት የሄደው » ትለዋለች። የተወለደችው ግን 19 89 ነበር። ይሄ ማለት እንደሰው ዘጠኝ ወር ሳይሆን በ1969 ተረግዛ ከ20 ዓመት በኋላ የተወለደች ልዮ ፍጥረት። አይ ጫት...እዚህ ኑሮ ላይ ሲደመር ይሰራዋል ስራ! የሆነ ሁኖ የስድስት ወር የቤት ኪራይ ከፍሎ፣ ወረት ሰጥቶ ነበር የተመለሰው። ገና ከመመለሱ ደወለች። ሰላም መግባቱን ለማረጋገጥ መስሎት ነበር፣ ግን የተከራየችው ቤት እንደገና ለልማት መፍረሱን ነገረችው።

ሶስተኛው ወንድሙ እንኳን ደህና ነበር። ዝንጥ ያለ ፈገግታ የማይለየው አካውንታት። መላጣ። እና ምን አለው «ዋናው ወንድምነቱ ነው! ፈልገኸን ስለመጣህ አመሠግናለሁ። ትልቅ ሰው ነህ። እንኳን ተገናኘን! ብዙ ላስቸግርህ አልፈልግም፣ አሜሪካም ቢሆን ገንዘብ ከመሬት አይታፈስም ወንድም አለም ! ብቻ ይችን ፀጉሬን ቱርክ ሄጀ ማስተከል የዘወትር ህልሜ ነበር። እንዲሁ ትንሽ ዶላር ከላክልኝ ይበቃኛል። ስትመለስ ይደርሳል ብዙ አያስቸኩልም😀

አንዳንድ አባት ስህተቱ መራር ነው። ስህተትም እነደሎተሪ ዕድል ይጠይቃል መሰለኝ። እና በመጨረሻ ደሜ መራር ነው መቸም ምናለኝ ? «ባትመክረኝ ኑሮስ አብርሽ . . .ተው ብትለኝስ...»

አሁን ደግሞ ለእርሱ እያዋጣን ነው።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

16 Nov, 09:53


ማይክ ታይሰን ለእኔ ቦክሰኛ አይደለም!
(አሌክስ አብርሃም)

ከህይወት ቡጢ ለማምለጥ ሲሮጥ ያቀረቡለት የቦክስ ጓንት ውስጥ የወደቀ ሚስኪን ወፍ ነው። እንደብዙ ጥቁር አሜሪካዊያን ገና በልጅነቱ ብዙ መከራ ተቀብሏል። አባቱን በእርግኝነት አያውቅም ነበር። አንድ ጀማይካዊ የታክሲ ሹፌር ነው ይባላል።ይሁንና እሱ አባቴ ብሎ የሚያስበው /የተነገረው/ ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት የሚያቀርብ ሰካራምና ዱርየ ሰው ነበር። ያም ሆነ ይህ ከንቱ ነበሩ። የሆነ ሁኖ የአባት ፍቅርም ይሁን ከለላ ሳይኖረው እናቱ ጋር መጠጥ አደንዛዥ እፅ ፣ወሲብና ወንጀል በተሞላ በዘግናኝ ሰፈር ውስጥ ለመኖር የተገደደ ሚስኪን ህፃን ነበር። የባሰው አሳዛኝ ነገር እናቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ሴት መሆኗሲሆን የምታሳድጋቸው በዚሁ ስራ ነበር። ማይክ እናቱ በመጠጥና ድራግ በናወዙ ሰካራሞች እናቱ ላይ ብዙ ግፍ ሲፈፀም አይቷል።

በቤተሰቤ እንደተሳቀኩ ነው የኖርኩት ይላል በሀዘን።ብዙዎቹ የተገፉ ህፃናት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፣ ከሰው ያጡትን ፍቅር ከአሻንጉሊት፣ ከቤት እንስሳት ወይም በሃሳባቸው ከሚፈጥሩት ታሪክ ለማግኘት ይጥራሉ. . .ማይክ ታይሰን ርግብ ነበረችው የሚወዳት ! አንድ የሰፈር ጉልበተኛ እርግቡን ገደለበት . . .የማይክ ታይሰን የታፈነ ብሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ሁኖ የተገለጠው እዚህ እድለቢስ ወጣት ላይ ነበር ይላሉ ታሪኩን የፃፉ! ከዛማ ምኑ ቅጡ ማይክ ከአንደበቱ ቡጢው የሚፈጥን የለየለት ተደባዳቢ የጎዳና ልጅ ሆነ። እስርቤትና ፖሊስ፣ ክስና መታሰር. . .!

በመሰረቱ ይሄ ባህሪው በዛ መንደር መሞቻው ነበር! ግን አንድ ጣሊያናዊ የቡጢ አሰልጣኝ ዓይን አረፈበት! የማይክን የጎዳና ቡጢ ከሞት ወደህይዎት፣ ከእስር ቤት ወደቦክስ ሪንግ አመጣው! እነዛን ቁጡና በብሶት የተሞረዱ የማይክን ሰንጢ ጥፍሮች በጓንት ሸፍኖ ስፖርት አደረጋቸው። ደም ሳይሆን ዝናና ገንዘብ አፈሰሱ። የምታዩት ማይክ ታይሰን ተፈጠረ። ስሙ በዓለም ናኘ። ግን ምን ዋጋ አለው ገና በ20 ዓመቱ የአለምን የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻንፒየን የተቆጣጠረው ማይክ የገንዘብ ጎርፍ አጥለቀለቀው፣ የልጅነቱን ስነልቦናዊ ህመም ፣ብቸኝነትና የውስጡን ረብሻ የማያክም ገንዘብ። በ16 አመቱ በካንሰር ለሞተች እናቱ ያልደረሰ ገንዘብ ። እንደጉድ ብሩን ረጨው፣ ባለፈ ባገደመበት ሴት ነው፣ መጠጥ ነው፣ ድራግ ነው። ውድ መኪና ቅንጡ ቤት ... ከተራ ሰው እስከፖሊስ በውሃ ቀጠነ እየደበደበ ቅጣት ነው። ባዶውን ቀረ።

ይታያችሁ ፎርብስ አንድ ጊዜ የማይክን ሃብት 685 ሚሊየን ዶላር ገምቶት ነበር። ዛሬስ? ከየኪሱ የቀሩትን ሳንቲሞች ጭምር ቆጣጥሮ የቀረው ሀብት 10 ሚሊየን ብር ቢሆን ነው። ተራ በሚባሉ ፊልሞች ሳይቀር ተራ ገፀ ባህሪ ወክሎ አሰሩኝ እያለ እስከመለመን ደርሶ ነበር። ማይክ ታይሰን ብዙዎች እንደሚያስቡት የሚንጎማለል አንበሳ ፣ ከአለት የጠነከረ የቡጢ ንጉስ አይደለም። ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዲሁም ዘረኝነት የፈጠረው ጠባሳ ለዚህ ያበቃው የቦክስ ጓንት ውስጥ ጎጆውን የሰራ ሚስኪን ወፍ ነው። የልጅነት አዕምሮ ላይ የቆመ ጠባሳ በተጠቂው ቡጢ አይጣልም። ልጆች ላይ የሚሰነዘርን የህይወትን ቡጢ፣ የስነልቦና ፍላፃ ይከላከል ዘንድ የተፈጠረ ጋሻ ወላጅ ይባላል። ወላጅ ናችሁ? እንግዲያውስ ለልጆቻችሁ ህያው አጥር ሁኑ!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

15 Nov, 11:51


"የከሸፉ ሐይማኖተኞች" ከሚድኑ ዳይኖሰር  በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀለዋል!
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ፈጣሪን በጥልቀት ወይም ከነጭራሹ የማያውቅ ፣ ባለማወቁም የማይፈራ ነፍሰ ገዳይ አምላኩን ያወቀ ቀን ፍፁም ከቀደመ ክፋቱ የመመለስ እድሉ ከፍተኛ ነው። ከነክፋቱ ወደፈጣሪ ሲቀርብ ነገሮች ይቀየራሉ። ይሄን ለማረጋገጥ  ታላላቅ የሚባሉ የሀይማኖት አባቶችን ታሪክ ተመልሳችሁ ፈትሹ።

በክርስትናው ከብሉይ ኪዳን ጀምራችሁ  የኢየሱስ 12 ደቀመዛሙርትን ይዛችሁ  እስከአሁን ያሉትን፣ በሌሎቹም እምነቶች በየዘመኑ የተነሱትን ተመልከቱ። አንዳንዶቹ አመንዝራ፣ሌሎቹ ቀራጭ ፣ ሌባ ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ ለማህበረሰብ መከራ ወዘተ የነበሩ... ከዛስ? የገባቸው ቀን  የእውነት የተቀየሩ የፈጣሪ ባሪያወች ፣የማህበረሰቡም ምሳሌወች ይሆናሉ።  ሩቅ ሳንሄድ በዚህ ክፍለ ዘመን ራሱ ዘር ማጥፋትን ጨምሮ ብዙ ዘግናኝ ወንጀል የሰሩ ባለስልጣናት፣ አሸባሪወች ፣ አደንዛዢ እፅ አዘዋዋሪወች ፣ ሴተኛ አዳሪወች ወዘተ እስር ቤት ውስጥ  ፈጣሪን አውቀው ተለውጠው ሲወጡ ማየት የተለመደ ነው። ብዙ መዘርዘር ይቻላል። እነሱም አይደብቁም እንዲህ ነበርኩ ፈጣሪ ቀየረኝ ይላሉ በአደባባይ።

አሁን ተመለሱና ከይሁዳ ኧረ ከዛም በፊት  ጀምሩ...የተመረጡ የፈጣሪን ታላቅነት፣ ክብር ፣ ያወቁ ተዓምራቱን ያዮ  ፣የተመረጡ የተቀደሱ ለአመታት የሰበኩ፣ ያስተማሩ "ሐይማኖተኞች"  ሸርተት ብለው ገንዘብና ጥቅማጥቅም  ውስጥ ከገቡ፣ ወሲብ ፣ስልጣን፣ የታመመ ፖለቲካ ፣ ዘረኝነት ውስጥ ከተዘፈቁ ከሞት በስተቀር ምንም ከክፋታቸው አይመልሳቸውም። ምንም! የመጨረሻውን ሀያል አምላክ ክደውት ተመልሰዋል ማን ይዳኛቸዋል? ኢየሱስን ራሱን አሰቅለውታልኮ!  ችግሩ ደግ ሰወች ፣ ትሁትና ፈጣሪን የሚወዱ ሰወችን ከነፍሳቸው ይጠላሉ። ምክንያቱም ክህደታቸውን፣ ያፈረሱትን መለኮታዊ ቃል ኪዳን ያስታውሷቸዋል። ተቅበዝባዢ ናቸው። የጎደለው ከፍሳቸው ስለሆነ ምንም ምድራዊ ሀብት ስልጣን አይሞላቸውም። እና እንዲህ መሆናቸውን አያምኑም። አሁንም ሊሰብኩ ሊያስተምሩ  ይችላሉ። የሚሰብኩት ግን ራሳቸውን ነው። የወደቁለትን ሐብት ፣ዝና ፣ስልጣን ነው።

ንሰሐ መጨረሻ ባይኖረውም  በገሀድ እንደምናየው፣ እንዲህ አይነት "ሐይማኖተኞች" ግን በታሪክም በአሁኑ የኑሮ እማኝነታችንም  ስጋና  ደም የለበሱ የአጥፍቶ ጠፊ ፈንጅወች ናቸው። የጭካኔም የብልግናም መጨረሻወች። አገር ሳይቀር ያፈራርሳሉ። በነገራችን ላይ ሰይጣን ራሱ መለዓክ ነበር ዘጭ ሲል ነው አሁን የሆነውን የሆነው! አሰራሩ አንድ አይነት ነው።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

14 Nov, 02:33


መፅሐፍ ከማሳተማችሁ በፊት🚫
ለማሳተም ሐሳብ ላላችሁ
(አሌክስ አብርሃም)

ብዙ ወዳጆቸ መፅሐፍ ለማሳተም  እንደምትፈልጉና  ከህትመት ጋር በተያያዘ አስተያየት እንድሰጣችሁ በየጊዜው ትጠይቁኛላችሁ። ምክንያቱ ባይገባኝም በተለይ ሰሞኑን ደግሞ
ጥያቄው በዛ ብሏል። አንዳንዶቻችሁ መልስ አለመስጠቴ ትንሽ እንዳሳዘናችሁ ፅፋችሁልኛል። ኩራት አልያም ንቄት ነው ያላችሁኝም አላችሁ። እውነታው በዚህ ጉዳይ ምክርም አስተያየትም መስጠት አስቸጋሪ ሆኖብኝ ነው። የግድ አስተያየቴን መስጠት ካለብኝ ግን ቀጣዮቹን 10 ነጥቦች ላካፍል። የተለየ ሐሳብ ካለም በደስታ እቀበላለሁ።

1ኛ. እንኳን ፃፋችሁ፣ መፃፋችሁን ቀጥሉ! ከእናንተ የሚጠበቀው ከባዱ ሀላፊነት ይሄው ነው። የፀሐፊ ስራው ሳይታክት መፃፍ፣መፃፍ አሁንም መፃፍ  ነው። ይህ ፅሁፍ ግን ስለመፃፍ ብቻ ሳይሆን ((ስለማሳተም)) ነው።

2.መፅሐፍ ስታሳትሙ ለህትመት ያወጣችሁትን ገንዘብ እንደጠፋ፣ እንደተሰረቀ ወይም ፈፅሞ ከዚህ በኋላ እንደማታገኙት ሐብት ቁጠሩት። ከተመለሰ እሰየው! ካልተመለሰም በሞራልም በገንዘብም ህይወታችሁን እንዳያመሳቅል ብዙ ተስፋ አታድርጉ።

3.🚫በጣም እንዳትሞክሩት የምመክረው ...ንብረት በመሸጥ፣ በማስያዝ፣ ወይም በብዙ ድካም ለሌላ ጉዳይ ያጠራቀማችሁትን ገንዘብ በማውጣት መፅሐፍ አታሳትሙ። እባካችሁ አታሳትሙ። ስፖንሰር ከተገኘ፣ ለማሳተም ብዙም የገንዘብ ችግር ከሌለባችሁና ለስሜታችሁ ስትሉ ማሳተም ከቻላችሁ ችግር የለውም።

4. የግጥም መፅሐፍ ማሳተም  አሁን ባለው የመፅሐፍ ገበያ የሚመከር አይደለም።

5. ጥሩ ፅፋችሁ በአመታት ድካምና መስዋዕትነት  ያሳተማችሁት መፅሐፍ በቀናት ውስጥ በዮ ቲዮብ፣ በሬዲዮ ጣቢያዎች ፣ በቲክቶክና በቴሌግራም አየር ላይ ተበትኖ የሽያጩ ነገር ከአፈር ሲደባለቅ ማየት የዚህ ዘመን የደራሲያን የልብ ስብራት ነው።

6. እነእንትና እንኳ ፅፈው ተነቦላቸው የለ የሚል ሞኝ ንፅፅር ውስጥ ራሳችሁን አታስገቡ። ሰወች ምንጊዜም እንደባህር አለት ጫፋቸው ብቻ የሚታይ ፍጥረቶች ናቸው ውሀው ውስጥ ያላቸውን መሠረት አናውቅም።

7. ሁልጊዜም ሽፋን ላይ የምታዮት ዋጋ ለደራሲው በቀጥታ የሚደርስ አይደለም። እውነታው ግማሹ እንኳን አይደርሰውም። ስለዚህ ማሳተም ስታስቡ ይሄን ያህል ኮፒ በዚህ ዋጋ ቢሸጥ ከሚል የዋህ "ቀቢፀ ሒሳብ" ውጡ።

8. እንዲህም ሆኖ ብዙ መፅሐፍት ይታተማሉ የሚል ግርታ ውስጥ ከሆናችሁ ከብዙወቹ እንደአንዱ ከመሆናችሁ በፊት በእነዚህ ነጥቦች ላይ የራሳችሁን ጥናት ደግሞ አድርጉ። በማይገባኝ ምክንያት ደራሲያን ትክክለኛውን መረጃ እርስ በእርስ አይለዋወጡም።

9. መሠረታዊ ችግሩ በሁሉም ዘርፍ ያለው የዋጋ መናር ካለን ደካማ የንባብ ባህል ጋር መዳመሩ ሲሆን በተጨማሪም አንባቢው  በተደጋጋሚ በሚታተሙ መፅሐፍት ያሰበውን ያህል እርካታ ማግኘት አለመቻሉ ያሳደረው ተፅዕኖም ቀላል የሚባል አይደለም።

10. መፅሐፋችሁ መሸጡ ወይም አለመሸጡ የእናተን ደካማ ደራሲነት ወይም ጥሩ ፀሐፊነት ማረጋገጫ ላይሆን ይችላል። ሊሆን የሚችልበትም አጋጣሚም ይኖራል።  የመፅሐፍ ገበያ እብድ ነው። ታዋቂ ሁናችሁ ያጨበጨበው ሁሉ ድራሹ ሊጠፋ በተቃራኒው  ድንገት ብቅ ብላችሁ ህዝብ ሊሻማ ጥሩ ሊሸጥና ሊነበብም ይችላል። ግን ከመቶ ሁለትና ሶስት  እንኳን ይሄ እድል አይገጥመውም። በበኩሌ ህይወትን ለዕድል መተው ለማንም የምመክረው ነገር አይደለም። ዕድልን በህይወት ውስጥ መጠቀምን እመርጣለሁ። ምክንያቱ ብዙና ውስብስብ ነው። የሆነ ሆኖ የተሻለ ተስፋ ብሰጣችሁ ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን እውነታው ቢታደጋችሁ ይሻላል። አውቃችሁ ተጋፈጡት!!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

13 Nov, 11:23


አሜሪካ ማለትኮ ከአለም አንደኛ ሀብታም የሆነውን ሰውየ ካድሬ አድርጋ የምትሾም ብቸኛ አገር ናት😀

ጓድ ኤለን መስክ
በዮኤስ ኤ /አስ/ የዶ/ት/አስተ/ቢ/ወ/ሙ/የስራ ሒደት ዋና ሀላፊ😀

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

13 Nov, 06:30


📌 ተሽጧል Sold out
#Advertising
#AddisAbeba
በ16,000 ብር ብቻ ብሩ ተፈልጎ ነው።
4GB Graphics Card ያለው ቆንጆ ላፕቶፕ

Toshiba c55
Core i5
8GB RAM
500 HDD
4GB nivdia graphics card
Price 16,000 birr

0910030123 / 0955555561

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

13 Nov, 02:46


በቃ እንዲሁ ልንቀጥል ነው?
(አሌክስ አብርሃም)

"የዛሬ አምስት ዓመት የምሰራበት የህክምና ተቋም ህንፃ ላይ የተፃፈውን ስምና፣ ዋንጫ ላይ የተጠመጠመ እባብ ከነምላሱ ከዚህ ጋ ሆኘ ቁልጭ አድርጌ ማየት እችል ነበር...አሁን ግን በጣም ካልተጠጋሁ በስተቀር ቀለሙ እንጅ ፊደሎቹም እባቡም አይታየኝም። ብዢዢዢ ይልብኛል። ይህን የታዘብኩት ከወር በፊት ነው በአጋጣሚ" አለኝ። ከሩቅ የሚታየውን ህንፃ እያሳየኝ። እናም " አይኔን ያደከመው ቀን ሌሊት ሳልል የምጎረጉረው ስልክ ነው። መነፀር ያስፈልገሀል ተብያለሁ። ፀሐይ ላይ ስሆን እንባየ ያስቸግረኛል። ካየሁት ሁሉ ምን ተጠቀምኩ? ተዝናናሁ እንበል ለመዝናናት የዓይን ጤናን መክፈል ያዋጣል? እንቅልፍ ያጣሁባቸው ምሽቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፤ ምን አገኘሁ? ምንም። መረጃ እንበል ፣ እንቅልፍ የሚከፈልለት መረጃ የትኛው ነበር ? የት እንዳይሄድ? የቱ ህይወት የሚቀይር መረጃ? " አለም አንድ ሆነች ብለው ከራሳችን ለዮን።

እያወራኝ አሰብኩ ...በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የማይመለከቷችሁን ቪዲዮዎች አያችሁ፣ እንቅልፍ እንደበፊቱ እየተኛችሁ አይደለም በጣም እየተጎዳችሁ ነው፣ ከምትወዷቸው ጋር የምታሳልፉት ጊዜ ተወስዷል፣ ( ልጆቻችሁ ጭምር) ብዙወቻችሁ አይናችሁን ቸክ ተደረጉ እስኪ ወይም ራሳችሁ አድርጉት እይታችሁ እንደበፊቱ ነው? ... ሌላም ውሎ አድሮ የሚከሰት አካላዊም ይሁን አዕምሯዊ ችግር አይቀሬ ነው። ያውም የኢንተርኔት ክፍያው፣ የስነልቦና ጫናው፣ ጥላቻው፣ ስጋቱ፣ ባልተገባ ውድድር የሚፈጠርባችሁ የበታችነት ስሜት፣ ከእምነትና ማንነታችሁ ጋር የሚጋጭ ትእይንትና ነውር ወዘተ ሳይቆጠር። ምንድነው ሳናቋርጥ ስልካችን ላይ የምንፈልገው? ምን? የሆነስ ሆነና ሶሻል ሚዲያው ላይ "ዘና ለማለት" በሚል ይሄን ሁሉ መክፈላችን ያዋጣል? እንደቀልድ ቁጭ ብለን ሰዓቱ እንዴት እንደሚፈተለክ አስባችሁታል? ዕድሜ የሚከፈልለት ምን? በቃ እንደዚህ እየኖርን ልናረጅ ነው? በቃ ህይወታችን ይሄ ሊሆን ነው ?እስከመቸ?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Nov, 16:29


የቁም ተስካራችሁን አውጡ!
(አሌክስ አብርሃም)

ዕድሜ ልካቸውን ስለታላላቅ ሰወች ፣ ስለታላላቅ ስራወች  በማውራት ትልቅነታቸውን ለማሳየት ፍዳቸውን የሚበሉ ሰወች አሉ። በተለይ በጥበቡ ውስጥ ስለነበሩና ስላሉ ታላላቆች። ዘፋኞች፣ ተዋናዮች፣ ደራሲያን ወዘተ።  እንዲህ አይነት ሰወች  መቸም ታላቅ አይሆኑም። ወደራሳችሁ ተመለሱ፣ ሰው የተፈጠረው ዕድሜ ልኩን ሌሎችን ሲዘክር ለመኖር አይደለም። ሰው የራሱን የቁም ተስካር እንዲያወጣ እድል የተሰጠው ፍጡር ነው። የራሳችሁ ትንሽነት ዘክሩ። ማድነቅና ማክበር እንደእርሾ ነው። ለራሳችን ስኬት የሚረዳ ቅመም ነገር።

ታላላቆች ምን ሰሩ ብለን እንጠይቅ? ታናናሾችን በጥበባቸው አጎሉ። መንገድ ጠረጉ፣ ድምፅ ሆኑ ። አንብቡ የአለምን ሊትሬቸር...ስለጭቁኖች ማንም ዙሮ ስለማያቸው ጥቃቅኖች የተፃፈው ይበዛል። አንድ ዘፋኝ ታዋቂና ታላቅ ሰው  አፈቀርኩ ብሎ ሲዘፍን ሰምታችኋል? ስለተቀደደ ጫማችሁ ፃፉ፣ ባል ስለማጣታችሁ ፃፉ፣ ስለነተበ ሸሚዛችሁ ፃፉ፣ ዘይት ስላነሰው ሹሮ ወጣችሁ ፃፉ ፣ ጠይቃችኋት እምቢ ስላለቻችሁ የቤት ሰራተኛ ፃፉ፣ ስለተንጨባረረ ትዳራችሁ ፃፉ፣ ስለህመማችሁ፣ ስለረሀባችሁ፣ ስለብስጭትና ተስፋችሁ ፣ስላንገሸገሻችሁ ኑሮ ፃፉ። በህመማችሁ ልክ አቃስቱ፣ በሀዘናችሁ ልክ አልቅሱ፣ በደስታችሁም ልክ ሳቁ። ጫማችሁ ሸቷቸው ስላስነጠሳቸው ሰወች ስለተሰማችሁ ሀፍረት ፃፉ!  በተለይ ነፍሴ ለጥበብ ተጠርታለች ብላችሁ የምታስቡ ጊዚያችሁን በማጨብጨብ አታባክኑ! የሚያጨበጭቡ እጆች ብእር መጨበጥ አይችሉም። ሚሊየኖች እንደምታጨበጭቡላቸው ሰወች ሳይሆን እንደእናተ ነው የሚኖሩት። እናተ ሚሊየኖች ናችሁ። ታላቅነት በሰው ተስካር አደጋገስን ማሳመር አይደለም፣ የቁም ተስካርን ማውጣት ነው። ወደትንሽነታችሁ ተመለሱ። ከአንቆላባሽነት ውጡ። ጥሩ ነው ታላቆችን ማክበር ግን የእድሜ ልክ ስራ አይደለም። ቢያንስ መሰላሎቹ ላይ ለመውጣት ሞክሩ። መሰላል ተሸክሞ መዞር ከፍ አያደርግም።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Nov, 10:04


ቸርቿ ልትሸልመኝ ይገባል!

አንዱ የቤተክርስቲያን ኪቦርድ ተጨዋች  ትልቅ ስህተት ይሳሳታል።  እሱ እንኳን ጥሩ ልጅ ነበር ፣ያ የተረገመ ሰይጣን የሆነ ቀን ኪቦርድ ከሚያስተምራት የፓስተሩ ሚስት ጋር አሳስቶት እንጅ። እሷም ጥሩ ልጅ ነበረች ዕድሜዋ ከባሏ በ22 ዓመት ከማነሱና ጌታ ጭው ካለ ገጠር ካወጣው ፓስተር ጋር የተጋባች የከተማ ልጅ ከመሆኗ  ውጭ! እና ከማንኛውም አገልግሎት ይታገዱ  በሚሉና ለዛሬ በምክር ይታለፉ በሚል ምእመኑ ለሁለት ተከፈለ። መከፈል ብቻ አይደለም  በዓለም እንኳን ተሰምቶ በማይታወቅ ፣ማንም ከዚህ በፊት ባልተሳደበበት ፣ ገና በዛ ዓመት ከጥልቁ ተመርቶ ለገበያ በቀረበ ዜሮ ዜሮ ስድብ ጉባኤው ይሞላለጭ ጀመር። ከቃል አልፎ በጣት ምልክት ሁሉ እንካ እንች ምናምን እየተባባሉ። እና ልጁ በግርምት ስድድቡን ዛቻውን ሲኮመኩም ቆየ። የሱ ድርጊት ከሚያየው ጉድ አነሰበት። ሲወጣላቸው ሲረጋጉ "እሽ አስተያየትህ ምንድነው ይሉታል ንስሀ ትገባለህ ወይስ?"

ወገኖቸ ! የገረመኝ የእኔ መባለግ አይደለም። እኔኮ ስትቅለሰለሱ ስትፀልዩና ስትሰብኩ በትእግስት የጌታን መምጣት  የምትጠባበቁ ነበር የመሰለኝ። ለካ እዚህ ተሰብስባችሁ ብልግናችሁን የምትተነፍሱበት አንድ ባለጌ ስትጠብቁ ነው የቆያችሁት። ሰበብ ሆንኳችሁ፣ ለዓመታት በፆሎት ያልተገለጠ አጋንንታችሁ በብልግናየ  እየጮኸ ወጣ....ቸርቿ ልትሸልመኝ ይገባል😀

ምን ለማለት ነው? የማንም መባለግ እናንተ  ባለጌ እንድትሆኑ ልዮ ፈቃድ ሊሆናችሁ አይችልም። የጨዋነታችሁ መሰረቱና ሚዛኑ የሌላው መቅለል አይደለም። ሰሞኑን አንዱ የጊኒ ባለስልጣን የባለገበትን የወሲብ ቪዲዮ ለማየት የተለየ ፈቃድ የተሰጣችሁ ይመስል ስትራኮቱና ስትኮመኩሙ ፣ ልገስፅ ላስተምር  ስትሉ ለከረማችሁ "ሸም ኦን ዩ" 😀 በቀጣይ ብትፆሙ ብትፀልዮ እድሜ ልካችሁን ከአእምሯችሁ ትእይንቱ የማይጠፋ የወሲብ ፊልም ነው ስትጋቱ የከረማችሁት።

🚫 የወሲብ ቪዲዮ /pornography/ ለአንድ ደቂቃ ብትመለከቱ ትዕይንቱ በትንሹ ለ20 ዓመታት ከአእምሯችሁ አይጠፋም። ያውም እንደዕድሜ ደረጃችሁ።  ይሄ በጥናት የተረጋገጠ እውነት ነው። ጆሮ ያለው ይስማ።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Nov, 03:16


ጉተታው
(አሌክስ አብርሃም)

ኤለመንታሪ ተማሪወች እንደነበርን  አስማተኛ ነኝ የሚል ሰው በጆሮየ መኪና እጎትታለሁ  ሃምሳ ሳንቲም ትኬት ቁረጡ እያለ ወደትምህርት ቤታችን መጣ..ማንም አልቆረጠለትም፤ እንደውም መፈንከት አምሮን ነበር። ከዛ በፊት ተታለን ነበራ!  ጅል መሰልነው እንዴ?! ይህን የሰሙ ወላጆች ሁሉ ሳይቀር  ተቆጡ። በኋላ  እኛ ፈላወቹ የባነንበት ሰውየ ሀይስኩል ሄዶ መኪና በጆሮው እንደሚጎትት እና ትኬቱም አንድ ብር እንደሆነ ሲነግራቸው እንኳን ተማሪ አስተማሪና ወላጆች ሳይቀሩ ትኬት ለመቁረጥ ግድያ ሆነ።  የተቆጡ ወላጆች ሁሉ ሐሳባቸውን ቀይረው ይጋፉ ጀመር። ግራ ገባን። እንደውም ቦታ ጠቦ ብዙ ትርኢቱን ሊመለከቱ የሄዱ ሴቶች እያዘኑ ተመለሱ። "በአጥርም ቢሆን ይሄን ጉድ  እናያለን" ያሉም ነበሩ። 

የገረመን ለመመልከት ከሚጋፉት ሴቶች ይበዙ ነበር። ሰውየው  እውነትም አስማተኛ  ነው ...ከኋላ ከፍሎ ባሰማራቸው ሰወቹ  መኪናውን የሚጎትተው በጆሮው አይደለም ልጅ ፊት እንደዛ ስለማይባል ነው እንጅ በእንትኑ ...ነው የሚጎትተው" ብለው አውርተው ነበር። ህዝቡ ነቅሎ ገባ። ብለው ብለው መኪና ሊጎትቱበት? እየተባባለ። ልጆች እዛች ግድም እንዳንደርስ ተከለከልን።  በኋላ ሰውየው አንዲት ታክሲ እንደምንም በጆሮው ትንሽ ጎተተ ። ህዝቡ አልተደነቀም፣ ልቡ የተሰቀለው ሌላው ጉዳይ ላይ ነበር።  ቀጣዮን ለማየት አዳሜና ሂዋኔ እንደጓጓ "ትርኢቱ አለቀ" ብሎ ኩም አደረጋቸው አስማተኛው።

እንዴ እንትኑሳ?
ምኑ?
መኪናውን የምትጎትተው  በእንትንህ...ነው አልተባለም እንዴ? አሉ ወደእንትኑ እየጠቆሙ።
ፈገግ ብሎ የሱሪውን ዚፕ እየነካ "በዚህማ ይሄን ሁሉ አንድ ከተማ  ህዝብ ጎተትኩበት!!"😀

ይሄው እስከዛሬ እንትን ጋር የተያያዘ ወሬ እንደጉድ እየጎተተ ይሰበስበናል። እንዳለ ህዝቡ አስማት ሊያይ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅልሎ ገባኮ ጓዶች።😀 ያ የተረገመ ሰውየ  በእንትኑ  ጎትቶ ጊኒ አጎረን።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Nov, 03:10


የእለት ‹‹ነገራችንን›› አትንሳን!
(አሌክስ አብርሃም)

እያንዳንዱ ብሔርና ብሔረሰብ  "ኢትዮጵያ አገሬ ባህሌን፣ ወጌን ፣ትውፊቴን  ታክብር አለበለዚያ ...." ቢልስ? ለምሳሌ ብዙ ጊዜ የሰወችን "አክሰንት" ወይም ሌላ አካላዊ ገፅታ፣ ባህልና አምልኮ  በመስማትና በመመልከት ? በጨዋነት ብሔራቸውን ትገምታላችሁ። እና አክሰንታቸው እንደፈለገ ይወለጋገድ ፣ ገፅታቸውም ይሁን አለባበስና ባህላቸው ምንም ይሁን እምነታቸውን አትመኑበት ቢያንስ ፊት ለፊት መጥፎ ነገር አትናገሩም። ብሔር ናታ! እሳት ናታ! ኡፉ ናታ! እንደውም "ኢትስ ኦኬ" ልትኮራበት ነው የሚገባው  ብላችሁ ለመመሳሰል ዘጭ እንቦጭ ምናምንን ነው የምትሉት። ኋላ ቀር ጎጅ ምናምን ማለትማ አይታሰብም።

ቦርጫም ወንድ ስታዮ ግን፣ ስፖርት ስሩ፣ ኮሌስትሮል .... ምናምን የምትሉት ለምንድነው? ለቅፅበት እንኳን ፊታችሁ የቆመው ጓድ የቦዲ ማህበረሰብ ያፈራው ኢትዮጵያዊ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ለምን አታስቡም? ከተማ ብገባም ወግና ባህሌን ማንነቴን አልጥልም እምቢኝ  ያለ ቦዲያዊ የለም ያለው ማነው?! በቅድም አያቴ በምንጅላቴ  ቦዲ ነኝ ቢልስ?  እንደውም "ቦርጭን ለማጥፋት" የሚል ንግግር የአንድን ብሔር ወግና ባህል ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ በህግ ሊታገድ ይገባል ቢልስ? በብሔራዊ ቴሌቪዢናችን ሳይቀር  ባለሙያ  ጋብዛችሁ "እንዴት ቦርጭ ማጥፋት እንደሚቻል" ትሰብካላችሁ።  ምንዓይነት ሕዝብን መናቅ ነው ይሔ ወገኖቸ?! የጥላቻ ንግግር ልንለው እንችላለንኮ።

የሆነ ሆኖ የቦዲ ማህበረሰብ ግን በሞጋሳ / ጉዲፈቻ ወዘተ የብሔራቸው አባል የሚያደርጉበት ስርዓት ይኖራቸው ይሆን? ባንዴ በኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ነበር የሚሆኑት። ወይ ደህና መካሪ ማጣት!ከተሜው በሙሉ ቦርጭ የታደለው ነውኮ የሚመስለው። ደግሞ ጅም ሂዱ ማለት ምንድነው የአንድ ብሔረሰብን መገለጫ ለማጥፋት ይሄ ሁሉ ርብርብ ለምን?  እንደውም ከለጠጥነው ዘር ማጥፋት ጭምር ነው!  ቦርጭ ከሌለ ሚስት የለም! ሚስት ከሌለ ዘር ከየት ይተካል? ዘር ማጥፋት ወይ የተወለደውን መጨፍጨፍ አልያም እንዳይወለድ ማድረግ አይደለምን? ይችንም ብሔር ጋር ካላያያዝናት  ማንም እየተነሳ ሊዘልፈን አይደል? በዚህ አጋጣሚ የሐመር ሴቶች ኢቲቪ ፣ፋና ተቀጥረው በባህላዊ አልባሳታቸው ተውበው ዜና ያንብቡ ፕሮግራም ይምሩ ፣ ፖርላማ ይሰየሙ  ብየ የጠየኩት ነገር ከምን ደረሰ? ኧረ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ እየሰጣችሁ ጓዶች!

እስኪ ሰላም ያውለን!

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

10 Nov, 00:51


የእውነት ግን ትንሽም ቢሆን ስፖርት ስሩ፣ ኧረ ዱብ ዱብ በሉ ጓዶች። አሁን አጠገቤ ተቀምጦ ስልኩን ሲጎረጉር የነበረው ዘናጭ  ወጣት ፣ ድንገት ተነስቶ ሲቆም ጉልበቱ እንዴት እንደተንቋቋ! ቋቋቋቋቋቋ ቅጭጭጭጭ! ከስጋና አጥንት የተሰራ ሰው እንዴት እንዲህ ይንቋቋል? ዲሞፍተር ያቀባበለኮ ነው የሚመስለው😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Nov, 10:38


በቃ እንዲሁ ልንቀጥል ነው?
(አሌክስ አብርሃም)

"የዛሬ አምስት ዓመት የምሰራበት የህክምና ተቋም  ህንፃ ላይ የተፃፈውን ስምና፣ ዋንጫ ላይ የተጠመጠመ እባብ ከነምላሱ ከዚህ ጋ ሆኘ ቁልጭ አድርጌ ማየት እችል ነበር...አሁን ግን በጣም ካልተጠጋሁ በስተቀር ቀለሙ እንጅ ፊደሎቹም እባቡም አይታየኝም። ብዢዢዢ ይልብኛል። ይህን የታዘብኩት ከወር በፊት ነው በአጋጣሚ" አለኝ። ከሩቅ የሚታየውን ህንፃ እያሳየኝ። እናም " አይኔን ያደከመው ቀን ሌሊት ሳልል የምጎረጉረው ስልክ ነው። መነፀር ያስፈልገሀል ተብያለሁ። ፀሐይ ላይ ስሆን እንባየ ያስቸግረኛል። ካየሁት ሁሉ ምን ተጠቀምኩ? ተዝናናሁ እንበል ለመዝናናት የዓይን ጤናን  መክፈል ያዋጣል?  እንቅልፍ ያጣሁባቸው ምሽቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፤ ምን አገኘሁ? ምንም። መረጃ እንበል ፣ እንቅልፍ የሚከፈልለት መረጃ የትኛው ነበር ?  የት እንዳይሄድ? የቱ ህይወት የሚቀይር መረጃ? "  አለም አንድ ሆነች ብለው ከራሳችን ለዮን።

እያወራኝ አሰብኩ ...በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የማይመለከቷችሁን ቪዲዮዎች አያችሁ፣ እንቅልፍ እንደበፊቱ እየተኛችሁ አይደለም  በጣም እየተጎዳችሁ ነው፣ ከምትወዷቸው ጋር የምታሳልፉት ጊዜ ተወስዷል፣ ( ልጆቻችሁ ጭምር) ብዙወቻችሁ አይናችሁን ቸክ ተደረጉ እስኪ ወይም ራሳችሁ አድርጉት እይታችሁ እንደበፊቱ ነው?  ... ሌላም ውሎ አድሮ የሚከሰት አካላዊም ይሁን አዕምሯዊ ችግር አይቀሬ ነው። ያውም የኢንተርኔት ክፍያው፣ የስነልቦና ጫናው፣ ጥላቻው፣ ስጋቱ፣ ባልተገባ ውድድር  የሚፈጠርባችሁ የበታችነት ስሜት፣ ከእምነትና ማንነታችሁ ጋር የሚጋጭ ትእይንትና ነውር ወዘተ ሳይቆጠር። ምንድነው ሳናቋርጥ ስልካችን ላይ የምንፈልገው? ምን? የሆነስ ሆነና ሶሻል ሚዲያው ላይ "ዘና ለማለት" በሚል ይሄን ሁሉ መክፈላችን ያዋጣል? እንደቀልድ ቁጭ ብለን ሰዓቱ እንዴት እንደሚፈተለክ አስባችሁታል? ዕድሜ የሚከፈልለት ምን?  በቃ እንደዚህ እየኖርን ልናረጅ ነው? በቃ ህይወታችን ይሄ ሊሆን ነው ?እስከመቸ?

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

07 Nov, 16:00


ሰሞኑን አንድ ስለሳይንስና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች በፍቅር የሚያወራ ልጅ ቲክቶክ ላይ ተመለከተኩ። (የዮኒቨርስቲ መምህር ነው አሉኝ) ልጁ ለቴክኖሎጅ ያለው ፍቅር ደስ ይላል ፤ በሚያወራውም ነገር በእርግጥ በጉዳዮ ላይ ደህና መረዳት እንዳለው ያስታውቃል። ብዙሀኑ ግን ልጁ ላይ ሙድ ከመያዝ ባለፈ የሳይንሱ ነገር አልተዋጠለትም። ለምን? የልጁ ድምፅ ቀጭንና አክሰንቱም ወደገጠር ወሰድ የሚያደርገው ነው በሚል። የአይዶል ተፅእኖ ሕዝቤ ላይ አርፏል። አብዝቶ ስለዘፋኞች ከማውራቱና ዘፋኞችን ከመተቸቱ የተነሳ ሳይንስ የሚያወራን ሰው ሳይቀር "ድምፅህ ቀጥኗል እንደገና ሞክር" እያለ ነው😀

ልጁ አንድ ቪዲዮው ላይ "ምን ይሻላል? ብናለቅስ ይሻል ይሆን?" እንዳለው ነው ነገሩ😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

07 Nov, 15:53


እየገረመኝ ያለው ነገር በአገራችን ጉዳይ ላይ ሚዲያወች መዋሸት አለመዋሸታቸው አይደለም አሱኔማ አደግንበት አረጀንበት። የሚገርመኝ አድማጭ ተመልካቹ ውሸት መምረጡ ነው። አለ አይደል "በፍላጎቴ ልክ የተወራ ውሸት እውነት ነው" ብሎ መገገም። ለምሳሌ ስለሆነ ጉዳይ መስማት የምትፈልገው ውድቀቱን ነው እንበል፤ ውድቀቱን የሚያወራልህን ሚዲያ ከፍተህ ትሰማለህ። ያንኑ ዜና በተቃራኒው ስኬቱን መስማት ብትፈልግ ስኬቱን የሚያወራልህን ሚዲያ ትከፍታለህ። ሁሉም ዜና እንደቻይና እቃ በመግዛት አቅምህ ፣ በሙድህ ልክ ይሰራል። ምሳሌ ልጥቀስ ወይስ አልገብቷችኋል? 😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

05 Nov, 09:11


እንደምን አመሻችሁ በመላው አሜሪካ የምትኖሩ አበሻ አሜሪካንስ መራጮች? እንዲሁ ለሰላምታ ነው😀

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

05 Nov, 06:56


ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ከላይ ከተለጠፈው ፅሁፍ ጋር በተገናኘ ደስተኛ እንዳልሆናችሁ ተረድተናል። የአንባቢዎቻችንን ፍላጎት ያማከል ባለመሆኑ ይቅርታ እንጠይቃለን🙏

አስተያየቶቻቸሁን ተቀብለናል እናመሰግናለን
ፅሁፉን አንስተናል።

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

02 Nov, 18:30


ተከራይ ኪራይ ለመክፈል፣ አከራይ ሌላ የምትከራይ ሰርቪስ ለመቀለስ ሁሉም ቲክቶክ ላይ ይጨፍራሉ😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

02 Nov, 08:44


እንደምን አደራችሁ? መልካም ቅዳሜ።  ድሮ ድሮኮ ቅዳሜ ቅዳሜ  ጠረጴዛውን በጠርሙዝ ሞልታችሁ መጠጥ ትጠጡ  ፎቶም ትለጥፉ ነበር አይደል? እንደውም ሰው ትጋብዙ ሁሉ ነበር!  እኔም አትጠጡ፣ እናተም አታብዙ እንጅ አትጠጡ አይባልም ምናምን እንባባል ነበር እ? ነበር እንዲህ ቅርብ ነው? አሁን ግን ጠጡ ብላችሁ እንደውም ወንድ ከሆናችሁ አብዝታችሁ ጠጡ ብላችሁ ድሮ ጠጥታችሁ ባልመለሳችሁት ጠርሙዝ ነው የምትፈነክቱኝ😀 በዚህ ኑሮ ጠጡ ይላል እንዴ "ምኑ ጀዝባ ነው" አሉ ያ ሰውየ....😀

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

28 Oct, 17:12


ያከሸፈቻቸው ያከሸፏት አገር!
   (አሌክስ አብርሃም)

የ8ኛ ክፍል ተማሪወች እንደነበርን ነው።  አንድ ቀን የሆነ አስተማሪ ቀረ። በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሰራ (አብዛሀኞቻችን ወሬና መንጫጫት) አንድ ምስጋናው? የሚባል ስዕል መሳል የሚችል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ። ስዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ስዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ  የፊታቸው መስመር፣  ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ፣ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን እና ጌጣጌጥ  ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች። ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም። እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም  ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከነንጉሳዊ ልብሳቸው ወደጎን ዞር ብለው። ሁላችንም ተገረምን ተደነቅን። የስእሎቹ መጠን የእውነት ሰው ያካክሉ ነበር።

ቀጣዮ ክላስ  ጅኦግራፊ ። ኮስታራው አስተማሪያችን  ገባና ስዕሎቹን አየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ። በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር። ራሱ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ ለአንድ ክፍል ልጅ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ቀጠቀጠው። ምስጋናው በህመም ተንሰፈሰፈ።  እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚሸናበት አይደለም፤ ደደብ!" ብሎ ደነፋ። ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ሀይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው። አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።

ብዙ ዓመታት አለፉ። አንድ ቀን  አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ አየሁ ምስጋናው ነበር። ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም። ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ  ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ  የሳለው ስእል በአስተማሪዎቹና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ። ስዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን  ብላለች ርዕሰ መምህርቷ። አገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች። ይህ ሒሳብ የገባቸው ብፁአን ናቸው።  ለትውልድ ፍቅር ያወርሳሉና።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Oct, 16:01


ልስን ድሃ
(አሌክስ አብርሃም)

የዛሬን አያድርገውና  "ያጣ የነጣ" የሚለው አባባል ድሃና ድህነትን የሚገልፅ አባባል ነበር። አሁን ላይ በተለይ የከተማ ድሃ ያጣል ግን አይነጣም። ከምግብ ሳይሆን ከሜካፕ እና ከፊልተር በሚፍለቀለቅ ወዝና ውበት በአካልም በሚዲያም እያማረ ይራባል። ድሃ ነው ግን አይነጣም ፣አይገረጣም። ሜካፑ እንዳይበላሽ የሚያለቅሰው ወደውስጡ ነው።  ይህ ውበት የነጣና ያገጠጠ ድህነትን ከላይ በሚያብረቀርቅ ነገር በመለሰን የሚሸፋፍን ሲበዛ አሳሳች ውበት ነው።

ልክ እንደመቃብር ሃውልት የውጩ ውበት የውስጡን አፅም ይሸፍንብናል። በዛ ላይ ሀውልቱ ላይ የሚፃፈው የተጋነነ  ታሪክና የሚለጠፈው ፎቶ ለሟች ከማዘን ይልቅ በሀውልቱ እንድንደመም ያደርገናል። የሟች ቤተሰቦች ከሟቹም በላይ አንጀታቸውን አስረው ለሀውልት ባወጡት ወጭ ያለቅሳሉ። መፅሐፉ "እናተ በኖራ የተለሰናችሁ መቃብሮች ናችሁ" ያለውኮ እንዲህ ያለው የውስጥና የውጭ ባህሪ አልገጥም ቢለው ነው።  ነገሩ ግለሰባዊ ብቻ አይደለም ከተሞችም ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። ለምሳሌ አዲስ አበባን ተመልከቱ። በመብራት፣ በቀለም፣ በህንፃ ተለስና ስትታይ ከምድራችን የድሃ ድሃ  አገራት የአስከፊዋ ድሃ አገራችን ዋና ከተማ ትመስላለች?  የደሀ ደሀ ፣ ልዝብ ደሃ፣ መራር ደሃ ከሚሉት ማዕረጎቻችን በተጨማሪ " ልስን ድሃ" የሚል የድህነት ደረጃ ጨምረናል።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Oct, 17:44


ይሄ ሞት የሚባል ነገር ከመካከላችን አንድኛችንን ሲያነሳ የሚተወው ሰፊና ጨለማ ቦታ ጥልቀቱ ይጨንቃል። ድንገተኝነቱ የሆነ የሚያፍን ግራ የሚያጋባ ነገር አለው። የኢዮብ ነገር ያሳዝናል። አንዳንድ ሰው አለ ወደውስጣችሁ የሚያስለቅስ። ያሳዝናል። ነፍስህ በሰላም ትረፍ።

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

20 Oct, 06:40


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ  አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።  "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት) "እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው።

@AlexAbreham @AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

20 Oct, 06:36


መዘበራረቅ

ዝብረቃ 1. 

ተኝታችሁ ከተስማማችሁ በኋላ ተንበርክካችሁ "ታገቢኛለሽ?" ማለታችሁ ትንሽ የቅደም ተከተል ችግር አለበት ልበል? ለፆለት የሚንበረከከው ወንድ ከዚህኛው መንበርከክ በቁጥር እያነሰ መምጣቱ እንዳያስቀስፈን ጓዶች።

ዝብረቃ 2.

ፊልሙን ለመስራት  1.5 ሚሊየን ብር አወጣን ካላችሁን በኋላ የዋናዋ  ገፀ ባህሪ ሰራተኛ እህት ልጅ  ሁና የተወነችው እንስት  የሽልማት መድረኮች ላይ 2.9999 ሚሊየን ብር የፈጀ ቀሚስ(አውትፊት ይሉታል)  ለብሳ የምትታይበት ሳይንስ ትንሽ ግራ ያጋባል። አንዳንዴ በውበትም በዋጋም ከፊልሙ የሚበልጥ ቀሚስ ስናይ የልብስ ሰፊወች አዋርድ እየመሰለን ተቸግረናል። ለነገሩ የትም አለም የተለመደ ነው።

የውጭ ዝብረቃ 3.

ኤለን መስክ የሚባል በቴክኖሎጅ ፍቅር ልብሱን ጥሎ ያበደ ሰውየ፣ የሆነ መሪ የሌለው መኪና እያስተዋወቀ ነው። በዓለም የመጀመሪያው ካለመሪ የሚንቀሳቀስ ነው አለ። እንኳን መኪና እእእእእ 😀 እሽ ይሁን።  የሆነ ሆኖ መኪናው እናንተ ቤታችሁ ተቀምጣችሁ ብቻውን ሄዶ ኡበር /ታክሲ/ ይሰራል ይሸቅላል ሲል ነበር። እና ሮቦቶች የሰወችን ስራ አይነጥቁም? ሲባል ምናለ? ይንጠቋ! ሮቦቶች ይሰራሉ ሰወች ዘና ብላችሁ የኪስ ገንዘብ እየተሰጣችሁ ትኖራላችሁ። ከመጠግረር ምን አላችሁ?

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

17 Oct, 18:38


ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ!
ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ!
(አሌክስ አብርሃም)

ፍቅር ብቻውን መልስ የሚሆንበት ጊዜ  ላይ አይደለንም።
በማንም ላይ መፍረድ ከባድ ነው። ሲቸገሩ መርዳት አለመቻል ከሚፈጥረው ህመም ለመራቅ ከምንወዳቸው  ወዳጆቻችን እንርቃለን። ዓይናቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ ላለማየት ዓይናችንን እንሰብራለን።የአቅማችንን መደገፍ እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል። የተወለድንበት እና ያደግንበት ስር የሰደደ አብሮነት፣ መረዳዳት አሁን እግር ከወርች ካሰረን ኑሮ ጋር አብሮ አልሄድ ብሎ አስጨንቆናል። ረስተነው ወደወዳጆቻችን መንገድ ከጀመርን ፣ልንደውል ስልክ ካነሳን በኋላ ባዶ አይናቸው እጃችሁ ከምን ቢለንስ ብለን ተመልሰናል። ከመሄዳችን በላይ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን አንደበታቸው ሳይሆን ኑሯቸው ሁኗል። የተጨነቀ መንፈስ፣ የተጨነቀ አየር። የማንንም እርዳታ የማይፈልጉ መንፈሰ ፅኑ ወዳጆቻችን ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነውባቸው በዓይናቸው ባዶ ኪሳችንን ሲቃኙ ብናይ መርዳቱ ቢቀር አንታዘባቸውም። "እንትናም ተቸገረ?" ብለን አናሾካሹክም። ይገባናል ሰው ወደገደል ቢወድቅ አዳነውም አላዳነውም አጠገቡ ያገኘውን ሳርም ይሁን ቅጠል በደመነፍስ ጨምድዶ እንደሚይዝ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።ልብሳችንን አንቀው የሚማፀኑን እኛም የሌሎችን ልብስ አንቀን መንጠልጠላችንን ያውቃሉ። የመያያዙ መጨረሻ፣ የገደሉ ጫፍ የት እንደሆነ ማን ያውቃል?! እጃችን እየዛለ ነው። ደመነፍስ ላይ ነን። ማንንም ለመዳን እንይዛለን በማንም እንያዛለን።  ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ። ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።

Alex Abreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

16 Oct, 14:18


‹‹አላውቅሽም››
------

ከቅርብ ጓደኛዬ ሳሮን ጋር ፊሊ ካፌ የተለመደው ቦታችን ተሰይመን እያወራን እያለ ስልኳን አሁንም አሁንም እያነሳች ሰዐት ስታይ፣
‹‹ምን ሆነሽ አስሬ ሰዐት የምታይው?›› አልኳት::
‹‹ብዙ መቆየት አልችልም፡፡ ከአስራ አንድ ተኩል በፊት ሆስፒታል መድረስ አለብኝ›› ብላ ስትመልስልኝ፣
ደንገጥ ብዬ ግማሽ የደረሰ የማኪያቶ ስኒዬን አስቀመጥኩና፤

‹‹ሆስፒታል? ምን ሆንሽ?›› አልኳት
‹‹ምንም አልሆንኩም›› አለች ቀኝ እጇን ወደ ታች አወናጭፋ፡፡ ‹‹ነገ በጠዋት ሰርጀሪ እደረጋለሁ፤ ሆድሽ ውስጥ የሆነ እጢ አለ፤ ቶሎ መውጣት አለበት ብለውኝ ነው፡፡ የአራት ሰዐት ፕሮሲጀር ነው፡፡ እዚያ ማደር አለብሽ ስላሉኝ እንዳልዘገይ ብዬ ነው…››

የምትለውን ማመን አቅቶኝ በግርምት እያየኋት፤

‹‹ነገ ጠዋት ሲሪየስ ሰርጀሪ እንዳለብሽ የምትነግሪኝ አሁን ነው?…ለዚያውም እንዲህ ቀለል አድርገሽ?›› አልኩ፡፡

የቀዘቀዘ ሻይዋን በዝግታ ማማሰሏን ሳታቋርጥ፤

‹‹ያው እኔን ታውቂኛለሽ፡፡ ደሞ ከባድ ነገር አይደለም እኮ…ያው ግድ ሆኖብኝ ነው እንጂ፡፡ ይልቅ ማታ የላኩልሽን መቅዲዬ የሰራችውን ቲክቶክ አየሽው?›› አለችኝ፡፡

-----
ከሶስት ወራት በኋላ ለምሳ ተቀጣጥረን ስደርስ ጠረጴዛው ተበታትነው የተቀመጡ መአት ወረቀቶች ታተራምሳለች፡፡ አንዱን በትኩረት አየሁት፤

‹‹ሉንዲን ዩኒቨርስቲ- ስዊድን›› የሚል ነገር አይኔ ገባ፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ ሁሉ?›› አልኳት ስሜያት እንደተቀመጥኩ፡፡
‹‹እ…ወረቀቱ…? ሉንዲን ዩኒቨርስቲ ማስተርሴን ለመማር ሙሉ ስኮላርሺፕ አገኘሁ፡፡ ሚዲያና ፖለቲክስ ለሁለት አመት ልማር ነው፡፡ ከሃያ ቀን በኋላ እሄዳለሁ››
‹‹ምን….? ከሃያ ቀን በኋላ ስዊዲን ልትሄጂ መሆኑን ዛሬ ነው የምትነግሪኝ? ›› አልኳት በድንጋጤ፡፡
‹‹ያው እኔን ታውቂኛለሽ፡፡ ነገር ማካበድ አልወድም…በዛ ላይ ወሬን ወሬ ካላነሳው እንዴት አስታውሼ እነግርሻለሁ…? ገና እኮ ሃያ ቀን አለን…››

----
ከስዊዲን በተመለሰች በሳምንቱ ውጪ በመቅጠር ፋንታ የእናቷ ቤት ሄጄ እንዳገኛት ስትጠይቀኝ ግር ቢለኝም ሄድኩ፡፡

ወደ ሳሎኑ እንደገባሁ ባለ ሶስት መቀመጫው ሶፋ ላይ ጋቢ ተደርቦለት የተኛ ቆንጅዬ ብስል ቀይ ህጻን ልጅ አየሁ፡፡

ስድስት ወር ይሆነዋል፡፡

ሁለት ታላቅ እህቶቿ እዚያው ቤት ከእናታቸው ጋር ስለሚኖሩ ‹‹የማን ልጅ ይሆን?›› ብዬ አስቤ ሳልጨርስ ፣
ቡናዋን አቀራርባ ከተቀመጠችበት መጥታ ተቃቅፈን ከተሳሳምን በኋላ፤

‹‹የማነው ቆንጅዬ ልጅ?›› አልኳት ልጁን እያየሁ፡፡
‹‹የእኔ›› አለችኝ ፍርጥም ብላ፡፡
‹‹ምን?››
‹‹ምን ምን አለው? የእኔ ልጅ ነው››
‹‹ወልደሽው?››
‹‹አይ…እንደ እንቁላል ፈልፍዬው…
‹‹ሳሮን..ሲሪየስሊ…ምንድነው የምታወሪው?››
‹‹ልጄ ነው አልኩሽ…ከማስተርሴ ጋር አብሬ የሰራሁት…ይልቅ ፀሃይ መቶሻል መሰለኝ…ፊትሽ ከስሏል…ውሃ ላምጣልሽ? ››

ሳሮን በየጊዜው የምትጥላቸው ትልልቅ የዜና ቦምቦች እንዳስደነገጡኝ፣ በእርግጥ ጓደኞች ነን እንዳስባሉኝ ነው፡፡
ይሄኛው ግን ከሁሉ ከረረብኝ፡፡

ውሃ በብርጭቆ ይዛልኝ ስትመለስ፣
‹‹ልጅን የሚያህል ነገር አርግዘሽ ስትወልጂ…ይሄን ሁሉ ጊዜ ስናወራ ለጓደኛሽ እንዴት አንዴ እንኳን አትናገሪም?›› አልኩ ንዴቴን በሚያሳብቅ ድምፅ፡፡
‹‹ያው እኔን ታውቂኛለሽ፡፡ ነገር ማካበድ አልወድም…..›› የተለመደ መልሷን ቀጠለች፡፡

አሁን ግን ፣ ‹‹የለም አላውቅሽም›› ብለሻት ውጪ ውጪ አለኝ፡፡

By Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

11 Oct, 06:35


‹‹አስቴር አወቀ፣ ኤች አይ ቪ እና ሽምግልናዬ››
_________

(እንደእኔ) ካገቡ የቆዩ ሰዎች ስለ ዘንድሮ ልጆች የሽምግልና ዝግጅት በብዛት ሲያጉረመርሙ እሰማለሁ፡፡

የዘንድሮ የሽምግልና ድግስ የጥንቱን ባህል መሰረት ያደረገ ነው?
አይደለም::

ወጪው ከባድ ነው?
በጣም::

የድግሱ መጋነን በወጣቶች መሃከል ከባድ የፉክክር ስሜት ፈጥሮ ሊያገቡ ያኮበኮቡ ጥንዶችን ጋብቻ በወጪ ፍራቻ ሳቢያ ወደኋላ እያስባላቸው ነው?
ምናልባት::

ግን ይሄ ሁሉ እኛን ያገባናል?
አያገባንም፡፡

እኛ የዘመናችንን ኖርን፡፡

እኛም (እኛ ስል ባለፉት 20-15 አመታት ውስጥ ጎጆ የወጣን ሰዎችን ማለቴ ነው) ብንሆን ወላጆቻችን ባህሉን የጠበቀ ሽምግልና ነው ከሚሉት የሽምግልና ስርአት እንደዛሬዎቹ ልጆች እጅግ ባንርቅም ማፈንገጣችን ግን በጊዜው በሰፊው ተተችቷል፡፡

ለምሳሌ የእኔ ሽማግሌዎች አንድ ጊዜ ብቻ መጥተው እሺ እንዲባሉ መደረጉ ያናደዳቸው አክስቶቼ ዛሬም ድረስ ባሌን ሲያዩ፣

‹‹እሱማ አንዴ አራት ሰው ልኮ አፈፍ አደረጋት›› እያሉ ይሸነቁጡታል፡፡
ልክ እኔ ተስማምቼ አፈፍ እንዳልተደረግኩ ሁሉ፡፡
ሽምግልናው እናትና አባቴን ለማክበር ተከናወነ እንጂ እምቢ ቢሉም አመታት ቀድሞ ልቤን ከወሰደው ሰው አልለይ ነገር፡፡ ለዚያ ነው አይመላለሱ ተባብለን ባጭር የቀጨነው፡፡

ያሁኖቹ ወጣቶችም የራሳቸውን ነገር እያደረጉ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ ሃምሳ ሽማግሌም ተላከ አራት፣ አምስት ሺህ ብር ወጣበትም አምስት ሚሊዮን ከሽምግልናውና ከከበረቻቻው፣ ከሆያሆዬውና ከድግሱ በላይ ትልቁ ነገር ሰላማዊ ትዳር ነው፡፡ በአሸወይና የቆመ ፣ በሽምግልናው ድግስ ስፋት የሚፀና ሶስት ጉልቻ የለምና፡፡

“ዛሬ በምን ትዝ ብሎሽ ነው በጥቅምት መባቻ ስለ ሽምግልና የምታወሪው?” ልትሉ ትችላላችሁ፡፡

ቅድም የአስቴር አወቀን ‹‹መዘዝ አለው›› ዘፈን ስለሰማሁ ነው፡፡

የአስቴር መዘዝ አለው (በእኔ እድሜ ያላችሁ ሰዎች እንደምታውቁት) ዩኤስኤይድ ሙዚቃን በመጠቀም ኢትዮጵያዊያንን ስለ ኤች አይቪ ለማስተማር ያሰራው አስደማሚ የሙዚቃ አልበም ላይ ያለ ድንቅ ዘፈን ነው፡፡

(ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ይሄም ዘፈን ሆነ ሌሎቹ (የፍቅርአዲስ በድንገት…የቴዎድሮስ ፍቅሬ ሆይ… እና ሌሎቹም በዚህ አልበም የተካተቱ ዘፈኖች በግጥምና ዜማ ለዛቸውና የደረቀ የማስተማሪያ ዘፈኖች ባለመሆናቸው እስከዛሬ ድረስ ስለ ኤች አይ ቪ እንደተሰሩ ተረስቶ እንደ ጥኡም የፍቅር ዜማ የሚሰሙት ነገር ነው) ፡፡

ለማንኛውም እኔ እና ባሌ አስቴርን ከፍተን፣
‹‹አንድ ሰው ለአንድ ነው-
ትርፉ መዘዝ አለው›› ስንል ነው የዛሬ 17 ዓመት የነበረው ሽምግልናችን ትዝ ያለን፡፡

አሁን ደግሞ “እሱስ ይሁን ግን ኤች አይቪና ሽምግልና ምን አገናኘው?” ሳትሉ አትቀሩም፡፡

ባሌ ለቤቶቼ ሽምግልና ሲልክ ኤች አይ ቪ በሃገሩ ላይ እንደ ልቡ የሚፈነጭበት፣ ወጣቱን የሚያጭድበት፣ ጎልማሳውን አፈር የሚያለብስበትና ጨቅላዎችን ያለ አሳዳጊ ባዶ ቤት የሚያስቀርበት አስከፊ ጊዜ ነበር፡፡

ስለዚህ የዚያን ጊዜ ሽማግሌዎች ልጃችሁን ስጡን ብለው አባትና እናት፣ዘመድ አዝማድ ፊት ሲቀርቡ፣
ለመሆኑ ምን አለው?
ስራው ምንድነው?
በምን ያስተዳድራታል?
ቤትና መኪና አለው?
ከዚህ በፊት ትዳር ነበረው?

ከሚሉት ጥያቄዎች አስቀድሞ የሚጠየቀው፣

‹‹ ህጋዊ ማህተም ያለበት ከኤ ች አይ ቪ ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ይዛችኋል ወይ?›› ተብሎ ነበር፡፡

ታዲያ ብዙ ወንዶች የሃሰት ማስረጃ እያስያዙ ሽማግሌዎች ስለሚልኩ ሃኪም ቤቶች ሰርተፊኬቱን በመላክ ፈንታ ‹‹የሚመለከተው ሰው›› መጥቶ እንዲያይ አዝዘው ነበር፡፡

‹‹ሮማንቲክ›› አይደለም ግን አስፈላጊ ነበር፡፡ ሰው ጊዜውን ነው የሚመስለው፡፡

እናም ይህንን የማይቀር መሰናክል ለማለፍ ሲል የዚያን ጊዜ ቦይፍሬንዴ ለኤች አይ ቪ ምርመራ ሲሄድ አብሬው ሄጄ ነበር፡፡
ቤተሰቤን ወክዬ (የአይጥ ምስክር ድምቢጥ ! ሃሃሃ)

ለክፉ የሚዳርግ የሰራው/የሰራነው ስራ ባይኖርም፣ በሽታው ‹‹በዚያ ነገር›› ብቻ ሳይሆን መምጫው ብዙ ነውና መፍራታችን አልቀረም፡፡

የ”ነጻ ነው” ሰርተፍኬታችንን ስናገኝ ግን…
አባቴ ከመፍቀዱ በፊት፣
ከሰርጉ በፊት፣
ከጫጉላው ሽርሽር በፊት የተጋባን መስሎን ደስ አለን፡፡

አሁን ስለ ምንከራየው ቤት ማሰብ ፣ አሁን የሶፋችንን ቀለም መምረጥ፣ አሁን ቤት ሳናስፈቅድና ሳንዋሽ ሁልጊዜ አብረን ማደር እንችላለን ተባባልን፡፡

ያ ነው የአስቴር ዘፈን- የኤች አይቪው ሰርተፍኬትና የሽምግልናዬ ግንኙነት፡፡

ለማንኛውም በጥቅምትና በመጪው የበልግ ወራት በሽምግልናም ሆነ ያለ ሽምግልና፣ ደግሳችሁም ሆነ ሳትደግሱ ጎጆ ለምትወጡ እዚሁ የአስቴር ዘፈን ላይ ባሉ ውብ ስንኞች መልካም ጋብቻ ልበላችሁ!

‹‹ከለመዱት ጠረን- ከወደዱት ጋራ
እምነት ፍቅር ካለ- ይገፋል ተራራ››

By Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Oct, 15:35


እንውጣ
(በእውቀቱ ስዩም)

ወንድ ልጅ አይጣ! ምን አይጣ? ሚስት አይጣ! መልስ አይጣ! መውጫ አይጣ! ይልቁንም ገንዘብ አይጣ!

በቀደም እሁድ ለታ፥ ኤቲኤም ማሸኑ ላይ ሄጄ ተገተርኩ ፤ ዞር ብየ ታዛቢ መኖር አለመኖሩን ካረጋገጥኩ በሁዋላ” ሁለት መቶ ብር” የሚለውን አማራጭ ጨቆንኩት ፤ ማሽኑ ካርዴን መለሰልኝና “ ውድ ደንበኛችን፤ ለሁለት መቶ ብር ብለንማ በሰንበት መጋዘናችንን አንከፍትም! እባክዎ ባቅርቢያዎ ከሚገኝ የባንክ ዘበኛ ይበደሩ “ የሚል ጽህፈት ሰደደልኝ ፤

ከላይ ያለው ቀደዳ ሲሆን፥ ከታች ያለውን ግን የገሀዱ አለሜ ነጸብራቅ ነው!

ማርያምን ወንድ ልጅ አይጣ! ወንድ ልጅ በጣምም አያግኝ ! ሲያገኝ እንደኔ ጽጋበኛ ያለ አይመስለኝም! ከበቀደም ሁለት ቀን አስቀድሞ ልዝብ ሀብታም የሚያሰኘኝ ገንዘብ ሸቅየ ነበር፤ ሼክ አላሙዲን መክሰስ በሚበላበት ባርና ሬስቶራንት ገብቼ የምግብ ናዳ አዘዝሁ፤

ለማሳረጊያ ያዘዝኩት፥ ብርቱካን አናናስ እና ፓፓየ ጠረጴዛየ ላይ ተከማችቶ ያየ ሰው የሆነ የፍራፍሬ እርሻ የሚያስመርቅ የዞን ባለስልጣን ነው ምመስለው፤

ፈንጠር ብሎ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሰውየ ተቀምጦ ያየኛል( ስሙን በሌላ ቦታ የገለጽሁት ሲሆን እዚህ ላይ አጅሬ እያልሁ እቀጥላለሁ)

አጅሬ ፈገግ ብሎ ሲያየኝ ከቆየ በሁዋላ “ ይሄን ያህል በምግብ ተጎድተሀል እንዴ ?” ብሎ ለከፈኝ ፤

እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ፤ አዝመራው የተባለ ዘመዴ ትዝ ይለኛል፤ ድሮ ከትምርት ቤት ስንመለስ የሰፈር ጎረምሶች አስቁመው ነገር ሲፈልጉን እኔ ከድብድብ ለማምለጥ ያሉ የሌሉ ዘዴዎችን ሁሉ አሟጥጬ እጠቀማለሁ፤ ጎረምሶቹ በለስላሳ ምላሴ ተማርከው በሰላም ሊያሰናብቱን ከጨረሱ በሁዋላ አዝመራው እመር ይልና ክምር እንዳየ ዝንጀሮ አንዱ ላይ ይወጣበታል ፤ ከቴስታ አቅም እንኳ ሶሰት አይነት ቴስታ ያውቅ ነበር፤ ሸራፊ ቴስታ- ማይግሪን የሚያስይዝ ቴስታ እና ለኮማ እሚዳርግ መርዘኛ ቴስታ-

ጎረምሶችን አሸንፎ ሲያበቃ የሚሸልላት አትረሳኝም፤

“ዘራፍ አዝመራ ! ( ከስሙ መጨረሻ ያለችውን “ው” ለቤት ምታት እንቅፋት ስለምትሆን ያስወግዳታል)
ቁመቱ አጣራ
ልቡ ተራራ”

ለወትሮው ሰላማዊ የነበርኩት ሰውየ ድንገት የአዝመራው መንፈስ ተጋባብኝ ፤ ብልጭ አለብኝ! በዚያ ላይ ለሁለት ወር የkick boxing ስልጠና መውሰዴ ተራራም ባይሆን የሰፈር ዳገት የምታክል ልብ አጎናጽፎኛል፤

ከለካፊየ ጋር ትንሽ የስድብ ልውውጥ ካደረግን በሁዋላ “ልብ ካለህ እንውጣ ! “ አልሁት፤ እሱ ግን ቸል ብሎኝ ድራፍቱን መቀንደሉን ቀጠለ፤ እኔ በዛቻየ ቀጠልኩ፤ አጅሬው ሰማኝ ሰማኝና በመጨረሻ በረጅሙ ተንፍሶ እንዲህ አለ፥

“ እንዲያው አሁን፥ አስሬ እንውጣ የምትለኝ ፤ ልትመታኝ ነው ብርድ ልታስመታኝ?”

By Bewuketu Siyoum

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Oct, 06:45


‹‹ ነገር ይገንብኛል››

---=======------

‹‹ለትንሹም ለትልቁም ነገር አቃቂር ማውጣት ትወጃለሽ›› የሚሉኝ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
‹‹ሊያውም ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ ሁሉን ነገር መተቸት…ሁሉ ነገር እንከን የለሽ እንዲሆን መጠበቅ አይከብድም?›› ይሉኛል፡፡

አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በመኖሩ ብቻ የተርመጠመጠ ነገር በቂው ነው ያለው ማነው?

…በቃ ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ይህችን ታህል ነው?
…ለዚህ ይሆን አንድ ስፍራ ፀድቶና አምሮ ሲታይ፣
‹‹…ዋው ኢትዮጵያ አይመስልም›› የምንለው…?

እቅጩን ንገሪን ካላችሁ፤ “እኔን አቃቂር ታበዣለሽ” እያሉ የሚከሱኝ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለን ደህና ነገር አይገባንም በሚል የበታችነት ስሜት የሚሰቃዩ ሰዎች ናቸው፡፡

…እነሱ ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት ከደረጃ በታች ስለሆነ፣ ያገኙትን ሁሉ ተስገብግበው ስለሚያነሱ፤ እንኩ የተባሉትን ሁሉ አጎንብሰውና በጀ ብለው ስለሚቀበሉ፣ የከፈሉበትን ነገር እንኳን ተሸቆጥቁጠው ተጠቃሚ ስለሆኑ፣ መራጭ ሳይሆን አግበሽባሾች ስለሆኑ….

እኔ ‹‹አረ ይሄ ነገር ከልክ በታች ነው›› ስል አፋቸውን ለትችት ያሞጠሙጣሉ፡፡
ለሽሙጥ የተሞረደ ምላሳቸውን ዘርግተው, ‹‹እስቲ ክፉ ክፉን ብቻ ማየት ትተሸ አይንሽ ለበጎውም ነገር ይከፈት›› ይላሉ፡፡

ደግሞ እኮ ነገር ይገንብኛል እነጂ ፣ ያን ያህል እንከን ፈላጊ ሰው ሆኜ አይደለም፡፡

ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡

ባለፈው አንድ ቄንጠኛ ካፍቴሪያ (ስቀብጥ) ገብቼ ለአንድ ማኪያቶ 140 ብር እንደሚጠይቁ ሚኑውን ሳይ ብረዳም “አንዴ ገብቻለሁ” በሚል (የሃበሻ) ይሉኝታ አዘዝኩ፡፡

ማኪያቶው (ሶስቴ ፉት ብልለት በሚያልቅ መጠን እንስ ባለች ስኒ) ሲመጣ ባሬስታው በማኪያቶው አናት ላይ በአረፋ የሰራው የልብ ቅርፅ ወደ አንድ ጎን መንሻፈፉን ሳይ ተበሳጨሁ፡፡

አንዳንድ ሰው፣ ‹‹አሁን ይሄ ምኑ ያበሳጫል…አርፈሽ አትጠጪውም›› ሊል ይችላል…ግን እስቲ ትንሽ ረጋ ብላችሁ አስቡት፤ 140 ብር የተከፈለበትን ማኪያቶ ላይ ልብ የሚስል ባሬስታ የስእል ችሎታው ከአፈወርቅ ተክሌ ጋር ሊስተካከል አይገባም…?

አለበለዚያ ለዚህች ፉት ሲሏት ጭልጥ ለምትል ተራ ማኪያቶ ይሄ ሁሉ ክፍያ ለምንድነው…ለጠማማ ልብ?

በማኪያቶው ጉዳይ የሆንኩትን ለጓደኛዬ ስነግራት፣
‹‹እዛ ቤት እኮ ማኪያቷቸው ምርጥ ነው፡፡ ዋናው መጣፈጡ ነው፡፡ ልቡን አትበይው›› ብላ ነገሩን አጣጣለችብኝ፡፡

‹‹ ሴትዮ…ያለነው 2017 ላይ ነው…ማኪያቶ መጣፈጥም ማማርም አለበት..በተለይ በዚህ ዋጋ›› ብያት ተነስቼ ሄድኩ፡፡

በዚህ ጠባዬ ሳቢያ የአዲሳባ ምግብ ቤቶች የእኔን ጨጓራ በመላጥ የሚደርስባቸው የለም፡፡

ባለፈው አንዱ ጋር ለቁርስ ገብቼ ፍርፍር አዘዝኩ፡፡ ሲመጣ ምን ሆኖ መጣ…?

ግማሾቹ እንጀራዎች በብረት ዘነዘና የተቀጠቀጡ ያህል ደቀው ቁሌቱ ውስጥ ቦክተዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ በረጅሙ እንደተጠቀለሉ ሳይቆራረጡ ከቁሌቱ ሳይደርሳቸው ደረቅ ግንድ መስለው ተጋድመዋል፡፡

‹‹ ይሄንማ ፍርፍር ብዬ አልበላም›› ብዬ የነገርኩት አስተናጋጅ እንዳበድኩ ዓይነት ሲያየኝ መልሼ አፈጠጥኩበት፡፡

ማምረሬ ሲገባው ፍርፍር ብሎ ያመጣውን ነገር በሃፍረት ይዞ ተመለሰ፡፡

አንዴ ደግሞ ስለቸኮልኩ ራይድ ጠራሁ፡፡

ሲደርስ በጣም ፈዛዛ ወይን ጠጅ ቪትዝ ነው፡፡
አፕሊኬሽኑ ላይ ቀለሙ ‹‹ወይን ጠጅ›› ተብሎ ስለተመዘገበ ስጋት ሽው አለኝና ሳልገባ በፊት ጎንበስ ብዬ ለሹፌሩ ይሄንኑ ነገርኩት፡፡

ሳቁ እያፈነው፣ ‹‹ፀሃይ መቷት ነው›› ብሎ አቃለለው፡፡

የታርጋ ቁጥሩን አመሳክሬ ካየሁ በኋላ ስለቸኮልኩ ከነቅሬታዬ ገባሁ፡፡

መኪናዋ ውስጥ እንደገባሁ ከባድ እፍነትና ሙቀት ተቀበለኝ፡፡

ወቅቱ በጋ ነው፣ ሰአቱ ቀትር፡፡

ከስር የሚንቀለቀል እሳት፣ ከላይ የተቃጠለ ኩበት ተደርጎ አክንባሎ እንደተደፋበት ድፎ ዳቦ ሰራኝ፡፡

ዋናው መንገድ ላይ ስንወጣማ ባሰብኝ፡፡

‹‹በጣም ይሞቃል- ኤሲውን ታበራው?›› አልኩኝ ለታሪክ በሚቀመጥ ትህትና፡፡

በታላቅ መገረም፤ ‹‹ኤሲ ነው ያልሽው…እንዴ! ..ኤሲማ አላበራም ነዳጅ ይበላብኛል…ከፈለግሽ መስኮቱን ክፈቺው›› አለኝ፡፡

ሁኔታው ኤሲ እንዲከፍት ሳይሆን የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር እንዲፈታ የጠየቅኩት ነው የሚመስለው፡፡

እኔ የምለው…የምከፍለው ለነዳጁም አይደለም እንዴ…?.ደግሞስ መገናኛ መሃል መስኮቴን ከፍቼ “ስልኬን ብሉኝ “ የምል ጅል እመስለዋለሁ?

ሆ! ሰው ማፈር አቆመ እኮ እናንተ፡፡

ለዚህ ለዚህማ ባይመቸኝ እንኳን አንከውክዎ የሚያደርሰኝ ሚኒባሴ ምናለኝ፡፡

ከብሬም ከምቾቴም ሳልሆን ስልኬን ከድሮን ጥቃት እንደምጠብቅ ሁሉ ከልዬ መስኮቱን ከፈትኩና ሄድኩ እላችኋለሁ፡፡

እዚህ ሃገር ከፍለውም፣ መሰረታዊም ቢሆን ደህና ነገር መጠየቅ አበሳ ነው መቼስ፡፡

ብቻ አያችሁ አይደል…እኔ የአመክንዮ ሰው ነኝ..ቀበጥ አይደለሁ፣ ብዙ ነገር አልጠይቅም ግን ትንሽዋን ነገር እንኳን ስጠይቅ ቀይ ባህርን ለሁለት ክፈሉልኝ ብዬ የጠየቅኩ ያህል ይገንብኛል፡፡

ነገሬን ለማሳመን አንድ ሌላ ነገር ልጨምርላችሁና ልልቀቃችሁማ፡፡

ሰሞኑን ሰርግ ተጠርቼ ነበር፡፡ በሰርግ ወረቀት፡፡
ግን ቀረሁ፡፡ የቀረሁት ደግሞ እንዲሁ በትንሽ ጉዳይ አይደለም፡፡

የጥሪውን ወረቀት ከፍቼ ሳነበው የሚዘገንን ነገር አየሁ፡፡

ከሙሽሪት ስም በፊት በ‹‹ወይዘሪት›› ፈንታ ‹‹ወይዘሮ›› ብለው ፅፈዋል፡፡

ይቅርታ ግን…ሙሽራዋ በጋብቻ ላይ ጋብቻ እየፈፀመች ነው ወይስ ነገሩ እንዴት ነው…? በእኔ እይታ፣ ይሄ ትልቅና ይቅር የማይባል በአማርኛችን ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው…

‹‹ይሄንን ስህተት እንደ ዋዛ የሰሩ ሰዎችን ሰርግ ታድሜ ተጋቡ አልልም›› ስል ጓደኞቼ እንደ ንክ ሰው እያዩኝ ነበር፡፡

አልፈርድባቸውም፤ እንዲህ ያለው ስህተት በተጋቢዎቹ ላይ እያደር የሚያመጣውን መዘዝ ስላልተረዱት ነው፡፡

ለማንኛውም ከወረደው ሰው ጋር ሁሉ አልውረድ እንጂ ራሴን ማሻሻል የምጠላ ሰው ስላልሆንኩ ከትላንት በስቲያ ወደ አንዱ (ደህና የምለው) ምግብ ቤት ሄጄ ነበር፡፡

‹‹እስቲ ለ24 ሰአት ምንም እንከን ሳላይ፣ አቃቂር ሳላወጣ እንደ ሌላው ሃበሻ ልዋልና ልደር›› ብዬ ራሴን ልፈትን፡፡

ገባሁ፡፡ ተቀመጥኩ፡፡ የምፈልገውን ምግብ አዘዝኩ፡፡

ከአስር ደቂቃ በላይ ለማይፈጅ ምግብ 11 ደቂቃ አስጠበቁኝ (ቻልኩት)

የምጠጣው ነገር ቀድሞ ይምጣልኝ ብልም አስተናጋጇን ማስታወስ ነበረብኝ (እሱንም ቻልኩት)

ያመጣችልን የሚጠጣ ነገር ካዘዝኩት በተቃራኒ ቀዝቀዛ ነበር፡፡ እኔ የጠየቅኩት " ቀዝቀዝ" እንዲል ነበር። ሎሚ ረስታለች (ይህንንም ቻልኩት)

በመጨረሻ ምግቡ መጣ፡፡

የቀረበውን ነገር ሳየው ግን መቻል አቃተኝ፡፡

ከሩዝ በአትክልት ጋር እንጀራ አጃቢ ሆኖ መጥቶልኛል፡፡

ይሄን ጊዜ ያችኑ ቀልብ የሌላትን አስተናጋጅ ጠራሁና፣
በትህትና- በጣም በትህትና- ሩዜ ከእንጀራ ጋር የመጣበትን ምክንያት ጠየቅኳት፡፡

‹‹አንዳንድ ሰው እንጀራ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በዚያ ላይ ዳቦም አምጥተንልሻል እኮ…በዳቦ መብላት ከፈለግሽ›› አለችኝ ዳቦና እንጀራው አጠገብ ለአጠገብ ተሰትሮ የተቀመጠበትን የእንጨት ትሪ እያሳየችኝ፡፡

ልክ እስካሁን ዳቦ መኖሩን እንዳላየሁት ሁሉ፡፡

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

09 Oct, 06:45


‹‹ዐይኔ ያያል ዳቦ እንዳመጣሽ አውቃለሁ…ጥያቄዬ እሱ አይደለም›› አልኩ ትንሽ ገንፈል እያልኩ፡፡
‹‹እና ታዲያ ችግሩ ምንድነው?››
‹‹ችግር አላልኩም…ጥያቄ ነው ያልኩት››
‹እሺ ምንድነው ጥያቄሽ?››
‹‹በየት ሃገር ነው እንጀራ ከሩዝ ጋር የሚቀርበው?››

ልጅቱ ድምጽዋን ዝቅ አድርጋ ጥላኝ ለመሄድ እየተዘጋጀች..

‹‹ሆ…ስንት ዘመድ ያጣ እብድ አለ ባካችሁ›› ስትል ነገሩ ለየለት፡፡

ያበጠው ፈነዳ፡፡

ከዚያ የተፈጠረው ብዙ ነው ግን ለማሳጠር ያህል ልጅቱን ካልደበደብኩ አልኩ፤ ማኔጀሩ መጣ፤ ውጪ አለኝ፤ አልወጣም አልኩ፤ ከባድ ግርግር ሆነ፡፡ ፖሊስ መጣ፡፡

እና ምን ለማለት ነው…? ነገር ይገንብኛል፡፡

By Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

06 Oct, 06:46


‹‹ዋለለ››
-----
(ክፍል ሁለት)

-------------------

ለብቻችን ሆነን ለማውራት ስንፈልግ ስንፈልግ የምናዘወትረውና ሰው የማይበዛበት ካፌ ቀጠርኩት፡፡

ቦታውን የመረጥኩት በነገርኩት ነገር ቢናደድ እንኳን ቤት ውስጥ ስላልሆንን እንደ አባትና እናቴ ወይ እንደልቡ እንዳያንባርቅብኝ ያግደዋል፣ ግን ደግሞ ሰው ስለማይበዛበት በማናውቃቸው ሰዎች ፊት ገመናችንን ለማስጣት እንገደድም ብዬ ነው፡፡

ብዬ ነበር፡፡

ግን ያላሰብኩት ሆነ፡፡

ቀድሜው ደርሼ ትንሽ እንደጠበቅኩት ሰማያዊ ሱፍ ግጥም አድርጎ ለብሶ መጣ፡፡
ግራ ተጋባሁ፡፡
አማን ሰርግ ወይ የስራ ኢንተርቪው ከሌለበት ሱፍ መልበስ ሞቱ ነው፡፡
ምን ተገኘ?
በእሱ አለባበስ ተገርሜ ሳላበቃ ገና ከመቀመጡ ለወትሮው ትእዛዛችንን ተቀብለው ለብቻችን የሚተዉን አስተናጋጆች ባልተለመደ ሁኔታ ወዲህ ወዲያ ውር ውር እያሉ ሲመለከቱን ይበልጥ ግራ ተጋባሁ፡፡

ምንድነው?

ግራ መጋባቱ ሳይለቀኝ ሰላም ካልኩት በኋላ ራሴን ወንበሩ ላይ አመቻችቼ እንዲህ አልኩት፤

‹‹አማንዬ ስማኝማ…የማናግርህ ትልቅ ጉዳይ አለ ግን ሳልጨርስ እንዳታቋርጠኝ እ?››

በቃኝ ስልህ እንዳትጮህ፣ እንዳትናደድ ማለቴ ነበር፡፡

ገና የምለውን ነገር ሳይሰማ ፊቱ በደስታ እያበራ፣ ‹‹ሄዋንዬ እሺ ወዳንቺ እንሄዳለን ግን መጀመሪያ ልነግርሽ የጓጓሁለት ነገር ስላለ ሳልፈነዳ በፊት እኔ ልቅደም?›› አለኝ፡፡

ምንድነው?

‹‹ምን…ምንድነው ምታናግረኝ?›› አልኩ፡፡
አዲስ መጫወቻ እንደተገዛለት ህጻን ልጅ እየቦረቀ፣
‹‹የማወራሽ ትልቅ ነገር አለ›› አለኝ፡፡

ጌታ ሆይ!

‹‹ቪዛውን ሰጡህ?›› አልኩት አዎ ካለኝ እንዴት አድርጌ በቶሎ ማርሽ እንደምቀይር እያሰብኩ፡፡
‹‹አዎ ግን ስለ እሱ አይደለም የማናግርሽ!›› አሁንም ጥርሶቹ በሙሉ እስኪታዩኝ እየሳቀ፡፡

ስለ እሱ አይደለም?

እኔ የሚለኝን ነገር ለመረዳት ስባዝን የሚከተሉት ነገሮች በቅደም ተከተል ሆኑ፡፡

1ኛ- ቅድም ሲተራመሱ የነበሩት አራት አስተናጋጆች 40 ኢንች ቲቪ የሚያህል ፍቅር ስንጀምር የተነሳነው ሰልፊ ፎቶ ያለበት ኬክ እየተንገዳገዱ ተሸክመው መጡ፡፡
2ኛ- ቤስት ፍሬንዱ በትልቅ ስልኩ የሚሆነውን ሁሉ እየቀረጸና በጫት አረንጓዴ የሆኑ ጥርሶቹን ፈልቅቆ እያሳየ አጠገቤ መጥቶ ከነስልኩ መሽከርከር ጀመረ፡፡
3ኛ- ዛሬ እንለያይ ልለው የቀጠርኩት ቦይፍሬንዴ መሬት ላይ በግራ እግሩ ተንበርክኳል፡፡ በቀኝ እጁ ቀይ፣ ከፋይና ተከፍታ ቀለበት የያዘች ሚጢጢ ሳጥን ወደ ፊት አንከርፍፎ፡፡

ቀለበት! ባለ ፈርጥ የቃልኪዳን ቀለበት፡፡
እኔ ወንበሩ ላይ እንደተለሰነ ሰው በተቀመጥኩበት ‹‹ታገቢኛለሽ?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡

ያን ጊዜ ነው የወንዲ ማክ
“ታገቢኛለሽ ወይ” ሙዚቃ በካፌው ስፒከሮች ያለቅጥ ያንባረቀው፡፡

ዘፈኑ፣
‹‹ውዴ…እኔና አንቺ ለዚህ ቀን እንደርሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ?›› ብሎ በንግግር ሲጀምር፣
ክው አልኩ፡፡ ህእ! አስቤ አላውቅማ!
ዝም ብዬ በተቀመጥኩበት ጓደኛው መቅረጹን ሳያቆም መጥቶ በግድ ጎትቶ አስነሳኝና የተንበረከከው አማን ፊት አቆመኝ፡፡

ቁልቁል ሳየው እንዲህ ብሎ ቀጠለ፡፡
‹‹ሄዋንዬ፣ ካናዳ ሄደን አዲስ ሕይወት እንድንጀምር እፈልጋለሁ፡፡ ቀለበት እንሰር፤ እንጋባና አብረን እንሂድ፡፡ እንውለድ፤ እንክበድ፡፡ ታገቢኛለሽ?››
ጌታ ሆይ!

ከባድ ወጥመድ ውስጥ ገባሁ፡፡ ለዚያውም በቪዲዮ የሚቀረፅ ወጥመድ ውስጥ፡፡

ዘፈኑ ሲሟሟቅ፣ ካፌው ውስጥ የነበረው ጥቂት ሰው ሁሉ ወደ እኛ ሲመለከት፣ የከበቡን አስተናጋጆች (ታሪካችንን ያውቁት ይመስል) እያሽቃበጡ ሲያጨበጭቡ፣ ጓደኛው ብዙ እንደተከፈለው የቪዲዮ ባለሙያ እየዞረን ሲቀርጽ፣ አማን አይን አይኔን ሲያየኝ እንደ መንቃት ይባስ ደነዘዝኩ፡፡

ልቤና መንፈሴ ዋለለ፡፡
ምን ባደርግ ይሻለኛል?
እምቢ ብዬ እዚህ ሁሉ ሰው ፊት ላዋርደው…ቅስሙን ልስበረው?
ቲክቶክ ላይ ሊለቀቅ የሚችል ቪዲዮ ላይ ‹‹እምቢ አላገባህም!›› ልበለው?
ወይስ በይሉኝታ እሺ ብዬው ራሴን የባሰ ማጥ ውስጥ ልክተት?

‹‹እ….ታገቢኛለሽ?›› አለ ደግሞ በልምምጥ፡፡

በተበታተነ ሃሳቤ መሃል አማንን አተኩሬ አየሁት፡፡

በድንገት ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ ‹‹አግቢኝና ካናዳ ልውሰድሽ›› የሚለው ልለየው ያቀድኩት ቦይፍሬንዴ ብቻ እንዳልሆነ ተከሰተልኝ፡፡

ፊት ለፊቴ የተንበረከከው የማይደገምና ብዙዎች የሚመኙት፣ ብዙዎች መስዋእትነት የሚከፍሉለት፣ ንብረት ሸጠው የሚገዙት ታላቅ ከዚች ሃገር የማምለጥ እድል ነው፡፡
ስራ ለመሄድ የታክሲ ወጪዬን እንኳን የማይሸፈን አስር ሺህ ብር ደሞዝ እየተቀበልኩ እየኖርኩ እንዲህ ያለውን ታላቅ እድል እምቢ ብዬ ብገፋ የእግዜርን ዐይን መውጋት አይሆንም?

እምቢ ብለው፣ እማዬ ቆዳዬን ነው የምትገፈው፡፡
ጓደኖቼ እብድ ነሽ ይሉኛል፡፡ የአማን ዐይኖች ያረፉባት የልብ ጓደኛዬ ደግሞ ይሄንን እድል ብታገኝ ከመቀበል አልፋ ለማንኛውም ብላ (ለቀብድ እንዲሆን ) መንታ ታረግዝለት ነበር፡፡

ስለዚህ እሺ ልለው ወሰንኩ፡፡

ነገር ግን አማንን አግብቼ ካናዳ ብሄድ መንገድ የለመዱ አይኖቹ ሌሎች ሴቶችን ሲቃኙ፣ ጓደኞችና ኳስ ጨዋታን ደጋግሞ ከእኔ ሲያስቀድም፣ ከእሱ በስተቀር ሌላ ሰው በማላውቅበት ሃገር በብቸኝነት ሲያቆራምደኝ ታየኝና ‹‹እሺ›› የምትለዋ ቃል ከንፈሬን አልፋ መውጣት አቃታት፡፡

ቢሆንም እሺ አልኩት፡፡

የከበበን ሰው ሁሉ በሆታ ሲያጅበን፣ ካናዳን ከመርገጤ ታናሽ እህቴን ቶሎ ወስጄ እንደምፈታው እያሰብኩ ነበር፡፡

Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

05 Oct, 15:08


‹‹ዋለለ››
(ክፍል አንድ)
----------------

ከቦይፍሬንዴ ጋር መለያየት የነበረብኝ ከስድስት ወራት በፊት ነበር፡፡ ግን ይሄው ደህና ከጀመረ በኋላ አለ ቅጥ እንደተንዛዛውና ለዛውን እንዳጣው ሰው ለሰው ድራማ ነገሮችን ስጎትት ስጎትት እዚህ ደረስን፡፡

ለምን በጊዜ መቁረጥና መለያየትን ፈራሁ?

ምነው እንደ ትዕግስት ዋልተንጉስ ሰራሽ አትበሉኝና፤ ይሄ ጠባዬ ከልጅነት ጊዜ ጠባሳዬ ጋር ይገናኝ ይመስለኛል፡፡

ሰውን ፊት ለፊት ገጥሞ በግልጽ ማውራትና ያበጠን ማፈንዳት ክፉኛ እፈራለሁ፡፡ ሰዎች ከጣራ በላይ እየጮሁ ሲያወሩ ሁለመናዬ ይረበሻል፤ ጠብ ያርደኛል፡፡

እናቴ አባቴ ላይ በሆነው ባልሆነ ትጮህበት ነበር፡፡

አለ አይደል…ለምን ማታ የተቃጠለውን የመኝታ ቤት አንዱን አምፖል ወዲያው አልቀየርከውም ብላ ድምፅዋ አድዋ ተራሮች ድረስ እስኪሰማ ታምባርቅበታለች፡፡ እሱም የዋዛ አይደለም- መልሶ ያምባርቅባታል፡፡ ያን ጊዜ ሽንቴ ሊያመልጠኝ ይዳዳል፡፡

በእንዲህ ሁኔታ ሲጯጯሁ በነበረ ጊዜ ሁሉ እንደኔ በፍርሃት የምትርደውን ታናሽ እህቴን ይዤ ወደ መኝታ ክፍላችን እሸሽና በሩን ዘግቼ ክፍላችን ራስጌ ጠረጴዛ ላይ ያለችው ቴፕ ውስጥ ያኘሁትን ሲዲ አለ ቅጥ ከፍ አድርጌ እከፍትና ከጩኸትና ስድባቸው ልከልላት እሞክራለሁ፡፡

እኔን የሚከላከልልኝ ሰው ግን አልነበረልኝም፡፡ ያን ጊዜ ጭንቅላቴን እግሮቼ መሃል ድፍት አድርጌ ጆሮዎቼን በሁለት እጆቼ ለመሸፈን እየሞከርኩ ፣

ለምን ቀስ ብለው አያወሩም?
ለምን እንዲህ ከሚጮሁ ነገሮችን በውስጣቸው ችለው በዝምታ አያሳልፉም? እል ነበር፡፡

ለዚህ ይመስለኛል ሁለት አመት ተኩል አብሬው ከቆየሁት ቦይፍሬንዴ ጋር ሲሆን ከዐመት፣ ቢያንስ ከስድስት ወራት በፊት መለያየት ሲኖርብኝ እስከዛሬ ነገሮችን ችዬ የከረምኩት፡፡

ያለ ነገር አይደለም ልለየው የምፈልገው፡፡ ምክንያቶች አሉኝ፡፡ ሁለቱ አንኳር ችግሮቼ እነዚሁና!

አንደኛ- ለእኔ የሚሆን ጊዜ የለውም፡፡ የማስበውን ያህል፣ የማስብለትን ያህል አያስበኝም፣ አያስብልኝም፡፡ ከሥራ እና ከእንቅልፍ የተረፈውን ሰዐቱን በተቀዳሚነት የሚሰጠው ለሁለት ነገሮች ነው፡፡ ለእግር ኳስና ለጓደኞቹ፡፡ እኔ የትርፍ ጊዜ ሥራው፣ ትዝ ስለው ጊዜ የሚሠጠኝ ነገር ነኝ፡፡

ወንድሙ ጅራ፣
‹‹የእኔ ጉዳይ የኔ ኑሮ ካሁን በኋላ፣
ያንቺ ሆኗል የኔ ፍቅር የኔ ወለላ፣
ቅድሚያ የምሰጥሽ ከምንም፣
ለእኔ በምድር ላይ ያለሽ ጉዳዬ ነሽ›› ብሎ ሲዘፍን ደሜ የሚንተከተከው ለዚህ ነው፡፡

ሁለተኛ- ዐይኖቹ ቅብዝብዝ ናቸው፡፡

እዚህም እዚያም ሌላ ያያሉ፡፡

ቆንጆ ሴትን በመስገብገብ ሰርቀው ይቃኛሉ፡፡ ሌላ ሴት ያያል ስላችሁ ዝም ብሎ መንገድ ላይ፣ በየካፌው ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ እነዚሁ ቀበጥባጣ ዐይኖቹ ስንቱ ሴት ላይ ነጥረው ሲያበቁ የልጅነትና የልብ ጓደኛዬ ላይም አርፈዋል፡፡

እርግጥ ነው እሱ በለመደው ምኞቱ ይመልከታት እንጂ በሁለቱ መሃከል ምንም የተፈጠረ አይመስለኝም፡፡ ቆይቶ ግን፣ ‹‹እኔ ግን አስተያየቱ ስለሚደብረኝ አብሬያችሁ ባልሆን›› ስትለኝ ሃፍረት አንገቴን አስደፋኝ፡፡ ያኔ ነበር ልለየው የሚገባኝ ግን እንዳልኳችሁ ሁኔታን ተጋፍጦ ማለፍ ስለማይሆንልኝ ታስሬ ቆየሁ፡፡

ለዚህ ነው ነፃነት መኮንን የምትባል የዘጠናዎቹ ዘፋኝ፣
‹‹ከእኔ ምን አጥተህ ነው- ከእኔ ምን ጎድሎህ ነው፣
ዐይንህ ታዲያ ሌላ የሚያየው -መንገድ መንገድ ያሰኘው›› የሚል በልጅነቴ የሰማሁት ዘፈን ዛሬ ደርሶብኝ ሲገባኝ የተብሰለሰልኩት፡፡

ይህንን ጉዳይ ይበልጥ ያወሳሰበውን ነገር ደግሞ ልንገራችሁ፤ ቦይፍሬንዴ እንዲህ በብዙ ነገር ስሜቴን ይጉዳው፣ ጨጓራዬን ይላጠው እንጂ ደህና ጎን የለውም ለማለት አልችልም፡፡

ይንከባከበኛል፡፡ ጊዜውን እንጂ ገንዘቡን አይሰስትም፡፡ ሁልጊዜ በአበባና በተለያዩ ስጦታዎች እንዳንበሸበሸኝ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ያለ ምክንያት፣ ሳይጠየቅ፣ ሳይጠበቅበት የሚገርም ነገር ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ቤት ደብሮኝ ቁጭ ብያለሁ ምናምን ስለው ቻኖሊ ሄዶ የምወደውን ኑድልስ አሰርቶልኝ ቤት ድረስ ያመጣልኝና ስሞኝ ይሄዳል፡፡

ደስ አይልም?

የዛሬ ዘጠኝ ወር አባቴ ሲሞትም ካጠገቤ አልተለየም፡፡ ቀን በሉት ሌሊት በሉት እጄን ይዞ ትከሻዬን እየደባበሰ ሲያፅናናኝ፣ ነገሮችን ሲያስተካክልና ስርአት ሲያሲዝ፣ እኔንም፣ እናቴንም፣ እህቴንም አንደኛ ዘመድ የተባለ ሰው ካደረገው በላይ ሲንከባከብና ሲያፅናናን ከረመ፡፡

ይሄን ሁሉ ሲያይ የሰነበተው እድርተኛ፣ ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ፣ ‹‹ይሄማ ብረት መዝጊያ ነው›› ብሎ የምስክር ወረቀት ሰጠው፡፡
በዚያች ሰሞን ለነበረው ቦይፍሬንድነቱ ያ የምስክር ወረቀት ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም ግን…..እንዳልኳችሁ ሁልጊዜ እንደዚህ አይደለም፡፡ ያ ነው ናላዬን የሚያዞረው፡፡ አንዱን ይዞ ወጥ ሰው ቢሆንማ ምንኛ በቀለለኝ፡፡

አባቴን አፈር ባቀመስን በሶስተኛው ወር፣
‹‹የካናዳ ቪዛ ፕሮሰስ ከጀመርኩ ሶስት ወር ሆነኝ፡፡ እያለቀልኝ ነው፡፡ ከተሳካልኝ የምመለስ አይመስለኝም›› አለኝ፡፡
ከጀመርኩ፡፡ እያለቀልኝ ነው፡፡ ከተሳካልኝ፡፡ የምመለስ አይመስለኝም፡፡
አያችሁት አይደል!

የእሱ ነገር እንዲህ ነው፡፡

ራሱን ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ አንድም ቦታ ስለ እኔ አላሰበም፡፡ እቅዱ ውስጥ አልደመረኝም፡፡

ልክ እንዲህ ሲለኝ በቃ እንለያይ ማለት ነበረብኝ ግን መልሼ ሳስበው ቪዛ አግኝቶ በቅርቡ መሄዱ ላይቀር ለምን አፌን አበላሻለሁ …? ለቅሶው ላይ እንደዛ ሲሆንልኝ ያየስ ሰው ምን ይላል…ልታግስና ካናዳ ወስዳ ትገላግለኝ ምናምን ብዬ ዝም አልኩ፡፡

ዝም ብልም ራስ ወዳድነቱ ለእሱ የነበረኝን ስሜት ከፍቅር ወደ ተራ ጓደኝነት፣ ከተራ ጓደኝነት ደግሞ ወደ ‹‹መቻል›› በፍጥነት ያወርደው ጀመረ፡፡

‹‹በቅርብ ይሄድና ሁሉ ነገር ያበቃለታል›› ብዬ መጠበቄን ቀጠልኩ፡፡

ግን አልሄደም፡፡

ጭራሽ የዛሬ ወር የቪዛ ፕሮሰሱ እንዳሰበው እንዳልሄደለትና ተጨማሪ መረጃ አሟላ ብለው እንደጠየቁት፣ በዚህ ምክንያት ከዘገየ ለአንድ ዐመት እዚሁ እንደሚቆይ አይነግረኝም?

ኤጭ!

ለዚህ ነው ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ እንለያይ ልለው የቀጠርኩት፡፡ ከዚህ በላይ መጠበቅ አልፈልግም፤ አልችልም፡፡

ይቀጥላል . . .
Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

05 Oct, 07:34


ባሻዬ! ከሚስትህ ጋር ኳስ ጨዋታ አትመልከት ብዬ ከአንዴም ሁለቴ መክሬህ ነበር። ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ልንገርህ።

የማንቼን ጨዋታ ለማየት ትናንት ማታ ቁጭ ባልኩበት ሚስቴ ከባድ ጥያቄ ጠየቀችኝ፣

"ስንት ደቂቃ ነው የሚጫወቱት?"

"በመጀመሪያ 45 ደቂቃ"

"ለምን 45 ደቂቃ ሆነ?"

በጥያቄዋ ደንግጬ ትንሽ ካሰብኩ በኋላ፣

"ሜዳ ውስጥ ያለ ማቋረጥ የሚንቀሳቀሱ 45 ድቡልቡል ነገሮች ስላሉ ነው"

"ምንድን ናቸው?"

"በአንዱ ቡድን ውስጥ 11 ተጫዋቾች ስላሉ በሁለቱም ቡድኖች ውስጥ 22 ተጫዋቾች ይኖራሉ። እያንዳንዱ ተጫዋች ሁለት ሁለት የዘር ፍሬ ስላለው በአጠቃላይ 44 ድቡልቡል የዘር ፍሬዎች በከባድ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ"

"አንድ ይጎድላል እኮ!"

"አንዷማ ኳሷ ነች"

Tesfaye Hailemariam

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

04 Oct, 05:25


ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት
(በእውቀቱ ስዩም)

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው ራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድር ለማምለጥ አይመችም፤ ከዚያም አልፎ፤ በንቁና አስፈሪ ዘበኞች ይጠበቃል፤ በአክሱም ዘመን ደብረዳሞ የልኡላን ማጎርያ ሆኖ አገልግሏል፤ የሸዋ ነገስታት በተራቸው ሲገዙ፤ ለዚህ ተግባር የመረጡት ቦታ፥ ወሎ ዛሬ ግሼን ማርያም የምትገኝበትን አምባ ነበር፤ የጎንደር ነገስታት በበኩላቸው ዘመዶቻቸውን “ወህኒ” ወደ ተባለ ስፍራ ማጋዝ ጀመሩ፤ ወህኒቤት የሚለውን ቃል የወረስነው ከዚህ ስፍራ ነው ፤ ወህኒ በመሰረቱ የፖለቲካ እስር ቤት ሲሆን ፥የመጀመርያው የፖለቲካ ወንጀል ከንጉስ መወለድ ነበር፤

ንጉሱ ድንገት ወራሹን ሳያሳውቅ በጦር ሜዳ ይገደላል እንበል፥ አንዱ የቤተመንግስት መኮንን ብድግ ይልና አንዱን ልኡል ከማጎርያ ቤት አውርዶ ዙፋን ላይ ያወጣዋል፤ ሌላው የጦር አዝማች ደግሞ የኔን ምርጫ ካላነገስኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ይነሳል፤ ባንጋሾች መካከል የሚደረገው ፉክክር መዲናይቱን ባንዴ ወደ ፍርስራሽ እና ያስከሬን ክምር ይቀይራታል::

የቀድሞ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ብሄራዊ አደጋ ለመቀነስ የፈጠሩት “ዘዴ “ የንጉስን ሞት መሰወር ነበር ፤ የንጉስ ሞት ቀርቶ ህመሙ እንኳ ለህዘብ ይፋ አይደረግም፤ በዘመነ መሳፍነት ጊዜ ፥ የየጁው ራስ አሊ ሲሞት ፤ አንድ አሳባቂ ( የዘመኑ ፓፓራዚ) ወሬውን አሾለከው፤ ወድያው የረጋው አገር መላወስ ጀመረ፤ ጉዳዩ ያሳሰባት አንዲት አልቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፥

“ እሻ እሻ ነው እንጂ የእስራኤልን ሞት
እንዲያልቅሰው አሊን ለምን ቀበሩት “

“ እሻ እሻ “ ማለት ዝም በሉ ጸጥ በሉ ማለት ነው ፤ በዘመኑ የንጉስ ወገን ነን የሚሉ ሰዎች ዘራቸውን ከሰለሞን ስለሚመዝዙ “ እስራኤል “ በሚል የወል ስም ይታወቃሉ፤
በግጥሙ መስመር ላይ ያለው ህብረቃል “ እንዲያልቅሰው “ የሚል ነው፤ ሰሙ “ እንዲህ አልቅሰው “ ሲሆን ወርቁ “ ሰው እንዲተላለቅ” የሚል ትርጉም አለው ፤

ባጭሩ አልቃሺቱ፥
“ ህዘብ እንዳይተላለቅ
የንጉስ ሞት ይደበቅ “ ማለት ነው የፈለገችው ፤

ከጥንት እስከዛሬ አገረ -መንግስታችን የሚቆመው ባንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው ፤ መሪ ሲታመም አገር ይታመማል፤ መሪ ሲሞት አገር በጥቂቱ ይሞታል፤ ይህንን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው? የማይሞቱ ተቋሞችን በመገንባት ፤ የማይታመሙ ህጎችን በመመስረት? ወይስ ሌላ መላ አለ?

Bewuketu Siyuom

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

03 Oct, 10:47


‹‹እናትህ----››
----------------

አዲስ አበባ፡፡ የመንግስት ትምህርት ቤት፡፡ ዘጠነኛ ከፍል ታሪክ ክፍለ ጊዜ፡፡

‹‹ቲቸር…እንቅልፍ ሊወስደን እኮ ነው…ትንሽ ነቃ እንድንል እያደረጉ አስተምሩን እንጂ…››አለ ናትናኤል ዴስኩ ጠረጴዛ ላይ ተኝቶ እያዛጋ፡፡

ቲቸር በላይነህ አይናቸው ደም ለበሰ፡፡

‹‹ይሄ ቲክቶክህ መሰለህ…? ትምህርት ነው አንተ ደደብ!›› አሉ በንዴት፡፡
‹‹አትሳደብ ሰውዬ…!››አለ ናትናኤል ከተኛበት ቀና ብሎ፡፡
ቲቸር በላይነህ ለወትሮም የማይፈታው ግንባራቸው ታይቶ የማይታወቅ ግንድ ግንድ የሚያካክል የደም ሥር አበቀለ፡፡
‹‹ውጣ አንተ ዱርዬ.! ውጣልኝ!›› አሉ በጩኸት፡፡

የዛሬ ልጆች፡፡ የዘንድሮ ተማሪዎች፡፡ ታላቅ አያከብሩ፡፡ አስተማሪ አይፈሩ፡፡ በእኛ ጊዜ ቢሆን እንዲህ የተናገረ ተማሪ ተመንግሎ ነበር ከትምህርት ቤት የሚባረረው…ሊያውም አርባ ተገርፎ…ሊያውም ቀኑን ሙሉ እጅ በጆሮ ይዞ እያሉ ያስባሉ፡፡

የበሰበሰ ጊዜ፡፡

ይሁን ብቻ፡፡ አንድ አመት ነው የቀረኝ በጡረታ ልገላገል፡፡ ከዚህ ሲኦል ላመልጥ፡፡ የማያልቅ ስራ፡፡ ሆድ እንኳን የማይሞላ ደሞዝ፡፡ እነዚህ ስድ ለወላጅ ያስቸገሩ አግድም አደግ ልጆች፡፡ ትምህርት አይገባቸው፡፡ መምህር አያከብሩ፡፡ በእኛ ጊዜ እኮ አስተማሪ በሽቶ እግሬን እጠበኝ ቢል እንኳን እናጥብ ነበር፡፡

የበሰበሰ ጊዜ፡፡

ቲቸር በላይነህ ናትናኤል ከዴስኩ ተነስቶ በሩ ጋር እስኪደርስ ይሄን ሁሉ አሰቡ፡፡

ናትናኤል በሩ ጋር ሲደርስ ክፍል ውስጥ ያሉት ልጆች ጩኸት በረታ፡፡

‹‹ዝም በሉ ብያለሁ እናንተ ደግሞ! ›› ሲሉ ግን ድንገት ረገበ፡፡
ያኔ ነው ጆሯቸውን ያደማው ነገር ከናትናኤል አፍ በለሆሳስ ሲወጣ የሰሙት፡፡
‹‹እናትህ…››

ንዴት የሚደርጋቸውን አሳጣቸው፡፡ አፋቸውን ከፍተው ሊናገሩ ሞከሩ ግን ቃላት ማውጣት አቃታቸው፡፡

ህመም ብቻ፡፡ ቀሳፊ የደረት ላይ ህመም፡፡

ደረታቸውን እንዳቀፉ የሲሚንቶው ሊሾ ወለል ላይ ዝ-ር-ግ-ፍ አሉ፡፡

በወደቁበት ከበው የሚያዩዋቸውና የሚንጫጩትን በርካታ ተማሪዎች ፊቶች ይመለከታሉ፡፡ በጡረታ ለመገላገል ይሄ አመት ብቻ ነበር የቀራቸው፡፡

ራሳቸውን ለመሳት ሲቃረቡ፣ አንዴ አፉን በእጁ ሸፍኖ በከባድ ድንጋጤ የሚያያቸው ናትናኤልን አንዴ ደግሞ የክፍሉ ኮርኒስ ጥግ ላይ ተስሎ የሚገኘውን ከሰላሳ አመታት በፊት ያረፉት የእናታቸው ውብ መልክና ‹‹ና ልጄ!›› በሚል የተዘረጉ ሁለት ቀጫጭን
ክንዶቻቸውን እያዩ እንዲህ አሉ፡፡

‹‹እናቴ…እማዬ…እማዬ…!››

ተማሪዎቹ ግራ በመጋባት ይባስ ተንጫጩ፡፡

ቲቸር በላይነህ እንስፍስፍ እናታቸውን ሲመለከቱ ተማሪያቸው ናትናኤል የሰደባቸው አፀያፊ ስድብ እንደቅድሙ አላናደዳቸውም፡፡

ይልቁንም ከወዲያኛው ዓለምም ልጇን ለመቀበል የማይደክም እጆችዋን የምትዘረጋውን እምዬን በእንዲህ ያለ ስድብ በማርከሱ አዝነውለት ነበር፡፡

Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

02 Oct, 06:53


‹‹ውድድር››
————————-

‹‹ባይሽ ባይሽ ቁምነገር አጣሁብሽ›› ብሎ ስለተወኝ ከተለየሁት የቀድሞ ፍቅረኛዬ ጋር ከዓመት ተኩል በኋላ በአጋጣሚ ባንክ ተገናኝተን ነው፡፡

ብዙም ሳይዘገይ በሌላ እንደተካኝ ሰምቻለሁና፤ ከሰላምታ በኃላ፣

‹‹አዲሷ እኔ እንዴት ናት?›› አልኩት፡፡

‹‹በጣም ደህና ናት ግን ፈፅሞ እንዳንቺ አይደለችም›› አለኝ፡፡

ይሄ ጭካኔው አሁንም አልለቀቀውም፡፡ አሁንም ራሱ የሰጠኝ ያልሻረ ቁስሌ ውስጥ እንጨት ይሰዳል፡፡

‹‹ደህና ናት›› ብሎ መተው ማንን ገደለ?

‹‹ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ላይ ብፈልጋት ብፈልጋት ላገኛት አልቻልኩም…የገጠር ልጅ ናት እንዴ ?›› አልኩት በጭካኔ አፀፋውን ለመመለስ ነገር አድርቼ፡፡

የተወጋ ሰው መልሶ የመውጋት መብት የለውም ?

እኔ ፌስቡክ እና ኢንስታግራምና ላይ ተደምሮ ከዘጠና ሺህ በላይ ተከታይ እንዳለኝ ያውቃል፡፡ ቲክቶኬም በፍጥነት እያደገ ነው፡፡

ስሜቴን እንደ ጎዳው ስሜቱን ጎዳሁት ብዬ እርካታዬን አጣጥሜ ሳልጨርስ..
ድንገት ካገኘኋት እንዲህ እላታለሁ ብሎ አጥንቶ ሲያፈላልገኝ የከረመ በሚያስመስል ፍጥነትና ቅልጥፍና፣

‹‹ያዲሳባ ልጅ ናት ግን የማያውቃት ተከታይ ሳይሆን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያውቋት ጓደኞች፣ ከሩቅ ኑሮዋን እያዩ የሚያደንቋት የማታውቃቸው ሰዎች ሳይሆኑ ሁሉንም የምትካፈላቸው ወዳጆች፣ በፎቶና በቪዲዮ አይተዋት የሚሻፍዱባትና ወዲያው ከነ መኖሯ የሚረሷት ሺህ ወንዶች ሳይሆኑ ልቡን እንቺ ብሎ ያስረከባት እጮኛ ስላላት የእኔዋ ኢንስታግራምና ፌስቡክ ላይ አትገኝም፡፡ ለዚህ ነው አንቺን አትመስልም ያልኩሽ›› አለኝ፡፡

ይሄ ሰውዬ ከዚህ ሁሉ ሃተታ ከባንኩ ጥበቃ ጠመንጃ ተውሶ ተኩሶ የማይገድለኝ ለምንድነው ?

ፊቱ ላይ ያለው የ‹‹ልክ ልኳን ነገርኳት›› የደስታ ስሜት አቃጠለኝ፡፡

ጉዳዬን ሳልጨርስ ከእምባዬ እየታገልኩ ከባንኩ ሮጨ ወጣሁ፡፡

Hiwot Emshaw

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Sep, 13:24


‹‹እዛ ነገር ላይ አሪፍ ከሆንሽ …››
(አሌክስ አብርሃም) ማስታወሻ

‹‹ወይኔ ይሄ ባል አይደለም  እናትኮ ነው  እናት... ›› ትለኛለች  በተገናኘን ቁጥር ! ስለባሏ አውርታ አትጠግብም ! አንዴ ከጀመረች ሰው የሚሰለች አይመስላትም ! ጧት ተነስቶ  ቁርስ ሰርቶ ፣ ልጆቹን አለባብሶ …በቃ መንገድ ላይ ሲያልፍ ልብስ ካየ  ለራሱ እንኳን አይገዛም …ልበሽ ነው ይመርብሽ ነው …ፀጉርሽን ተሰሪ ነው …አመመኝ ካልኩ ቀድሞ ነው የሚታመመው …ማታ  ከስራ ሲወጣኮ ብታየው  በቃ ብን ብየ የምጠፋበት ነው የሚመስለው ወደቤት ነው …እንደውም ባለፈው ወደቤት ሲመጣ ከፍጥነት በላይ ነድቶ ትራፊክ ፖሊስ ሲያስቆመው ምን ቢል ጥሩ ነው?

‹‹ትንሽ ካመሸሁ የሚስቴ ምላስ  ሳማ ነው  አለው ?››

‹‹ሒድ ወደዛ  ሞዛዛ ‹ ሚስቴ ናፍቃኝ ነው›  ብሎ  ትራፊክ ፖሊሱን አሳቀው ሂሂሂሂ …ወንዶች ብዙ ነገር ከሱ መማር ትችላላችሁ ….ፀጉሬን ሁሉ ይሰራኛል ብልህ ታምናለህ ….?!>>  እና ሞልቀቅ ብላ …<<የኔ ጀግና እዛ ነገር ላይስ ቢሆን አንበሳኮ ነው>>  ከእኔ አልፋ ፌስቡክ ላይ  ባሏን ….ሰማይ ስታደርሰውና  ሆድ ለባሰው ባለትዳር ሁሉ  ምክር ስትሰጥ  ትውላለች ….የበሉት የጠጡት .. ባሏ የተነፈሰው ያስነጠሰው ሁሉ አይቀርም  ….እንደጉድ ትፅፈዋለች ! ባሏም እሷም ጓደኞቸ ናቸው ! በተቃራኒው ባሏ ፌስቡክ የሚባል ነገር ይዘፈንበት ይለቀስበት አያውቅም ! የስራ ሰው ነው ! ወሬው ቁጥብ ለዛውም ስለስራ ብቻ ! አለፍ አለ ከተባለ ስለልጆቹ ትምህርት !

   አንድ ቀን ታዲያ  ባሏ እፈልገሃለሁ አለኝ …ንጭንጭ ብሎ
‹‹ምነው በሰላም ?››  አልኩ! ሰዓቱ የስራ ሰዓት ስለነበር ግርር ብሎኝ ! 
‹‹ባክህ ምን ሰላም አለ ይች ልጅ አስመረረችኝ …››
‹‹  የቷ ልጅ? ዛሬም ስልክህን ሰበረችው? ›› ብየ ሳኩ... ትልቋ ልጁን ነበር ያሰብኩት
‹‹ስለእናቲቱ ነው የማወራህ ›› አለ በስጨት ብሎ ተገናኘን !

‹‹ ጓደኛ ነህ … ሚዜ ለመሆን ከመንከርፈፍ ተው አትሆንህም ብትለኝ  ምን ነበረበት  …?›› አለ እንባ እየተናነቀው …ጉድ ፈላ አልኩ !

‹‹ማለት …››

‹‹ስማኝ ስማኝ …አታቋርጠኝ … እኔ ያገባሁት እሷን ነው ወይስ የፌስቡክ ጓደኞቿን ?… እኔኮ እቤት ውስጥ ለስሙ እኖራለሁ …ለስሙ ገመናየን ለመሸፈን የቤት ኪራይ እከፍላለሁ እንጅ ''ኦፊሻሊ'' በረንዳ አዳሪ ነኝ …አላፊ አግዳሚው ምን እንደምበላ …ምን እንደምለብስ …ስተኛ ምን ፒጃማ እንደምለብስ …ልጆቸ ጋር ምን እንደማወራ … ወጣ ብየ ቤተሰቤ ጋር የት እንደምዝናና አገር ነው የሚያውቀው … አዲስ ልብስ ገዝቸ ለብሸው ስወጣ ጓደኞቸ ኦ ይሄን ነገር ከዚህ በፊት ለብሰኸ አይቸዋለሁ ልበል ? ይሉኛል …ያው ፌስቡክ ላይ እሷ ለጥፋው ነው ….ምንድናት ?…ጋዜጠኛ ናት ሚስት ?… የራሷንም የቤተሰቧንም ገመና አደባባይ ላይ በማስጣት በላይክና ኮሜንት ነፍሷን የምታስታምመው ለምንድነው …?ትዳራችን ደብሯታል …?››

‹‹እሱ እንኳን በትዳሯ መደሰቷን በቤተሰቧ መኩራቷን ለማሳየት ይመስለኛል …ስንቷ ናት የባሏን ፎቶ መለጠፍ ቀርቶ አግብቻለሁ ማለት የምታፍር ...?›› አልኩ …

‹‹  ኩራት እንደአፋልጉኝ  ማስታወቂያ  ፎቶህ በየአደባባዩ ስለተለጠፈ ነው እንዴ ….ይሄ እንደውም  በትዳር አለመደሰት አለመርካትና ይሄን መሰላቸት  በዚህ ለመሸፈን የሚደረግ ጥረት ነው ! ሰው እንዴት የምኝታ ቤቱን ፎቶ ይለጥፋል? …ህዝቡኮ አብሮኝ አንሶላ ውስጥ መግባት ነው የቀረው …. ልጆቸ ራሳቸው ሰለቻቸው …ሲስቁ ፎቶ ፌስቡክ ላይ …ሲያለቅሱ ፎቶ ፌስቡክ ላይ …ውጤታቸው ዝቅ ሲል የፈተና ወረቀታቸው ፎቶ ፌስ ቡክ ላይ …አጥፍተው ሲቀጡ ፎቶ ፌስቡክ ላይ ….ወድቀው ሲፈነከቱ ከሆስፒታል ቀድማ ፎቷቸውን ፌስቡክ ላይ …አከራያችን ኪራይ ዘገየብኝ ሲሉ አገር ይስማ ፌስቡክ ላይ …..ሌላው ይቅር በየወሩ ደመወዝ ስቀበል አዋጅ ፌስቡክ ላይ ‹‹ዛሬ የደመወዝ ቀን ነው ፈታ ልንል ነው ›› ምንድነው ይሄ ?…እንቁልልጭ ነው ?…ትዳር እንደፌስቡክ ብሎክ አድርገህ አትገላገል ነገር !መሮኛል !

‹‹መነጋገር እና ነገሮችን በልክ ማድረግ ነው ...ቀላል ነው ….››

‹‹ትቀልዳለህ ?  ልጆች  ወለድን …ስንት ዓመት ተናገርኩ … አጉል ተናንቀናል …በተናገርኳት ቁጥር  ሁለት ቀን ሶስት ቀን ኩርፊያዋ አይጣል ነው …ቤቱ መቃብር ቤት ነው የሚመስለው ! ታውቃለህ ኩርፊያ አልወድም ነፍሴ ይጨንቃታል ...እቤት ስገባ ጧት ቁርስ የተበላበት ሰሃን ተከምሮ ነው የሚጠብቀኝ …ስለሚደብረኝ  ደክሞኝ ከስራ መጥቸ አጥባለሁ …ሳጥብ ፎቶ አንስታ ‹‹ውዱ ባለቤቴ እቃ በማጠብ ሲረዳን ›› ትላለች … ላይክና ኮሜንት ይጎርፋል ‹‹ዋው ›› ይባላል ….እኔም በውስጤ ርግማንና እንባ ይጎርፋል …

ማታ ጉልት ብላ ስልክ ስትጎረጉር እስከእኩለ ሌሊት አትናገር አትጋገር …ልጆቹን ራሱ ስለምታመናጭቃቸው ነገ ስንት ስራ እያለብኝ …እነሱን የቤት ስራ ሳሰራራ …ሳስተኛ አመሻለሁ … ቀና ብላ ስታየን ፎቶ ታነሳና ‹‹ማሚ ራት እስከምታዘጋጅ አባትየው ልጆች ሲያስጠና ›› ብላ ትለጥፋለች …እንኳን ራት ወፍ የለም … ‹‹ለምሳ የተሰራ ወጥ አለ ፍቅር.... አሙቅና ብሉ ›› ትልቅ ስራ እንደሚሰራ ሰውኮ ነው በቃ ቢዚ የምትሆነው !

ልጆች ተኝተው … በቃ ብቻችንን ሁነን እጠብቃታለሁ እንቅልፍ እያዳፋት  ቫዘሊኗን ተደፍልቃ መጥታ ትወድቃለች …ጎኗ አልጋ እንደነካ የለችም  እንቅልፍ ! ይታይህ አብሪያት ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ … ጧት ስነሳ እንደተጋደመች ነው …ተነስቸ እየተነጫነጭኩ ያደረ ነገር ካለ ቀምሸ እወጣለሁ …! ልጆቸ ራሳቸው ተጎዱ ….ከስራ ስመጣ ስሞታ ነው … ቴሌቪዥን ከፍታ ትጥዳቸዋለች አይናቸው ቡዞ ነው የሚጠብቀኝ  ! ጭራሽ ፌስቡክ ላይ ስለልጅ አስተዳደግ ፌስቡክ ላይ ካልመከርኩ ስትል ታገኛታለህ !

ልጆቸ ቴሌቪዥን ላይ ከመጎለታቸው የተነሳ ይሄው ዜና እንደሙዚቃ ...አንባቢው ጋር አብረው ማነብነብ ሁሉ ጀምረዋል !  ወይ አታጫውታቸው … ወይ ይዛቸው አትወጣ … በዚህ ቀልቧ ይዛቸው ብትወጣም ስልኳን ስትጎረጉር መኪና ውስጥ ነው የምትማግድብኝ !  መረረኝ …››  ብሎ ትክዝ አለ ….አይኔ ሸሚዙ ላይ አረፈ አንዱ ቁልፍ ተበጥሷል …ባለፈው ሚስቱ ይሄንንም ሸሚዝ  ፖስት አድርጋው ነበር  ‹‹ወንዶችኮ ኬርለስ ፍጥረቶች ቁልፉ ተበጥሶ ለብሶት ስራ ይሄዳል እንደፈረደብኝ ልትከል ›› ብላ እስካሁን ቁልፉን አልተከለችውም !

‹‹… በእውነት ስልችት ነው ያለኝ … ፌስቡክ መጠቀም ይቅርና ማንበብና መፃፍ የማትችል ሴት ባገባሁ ብየ እመኛለሁ ! ጉራ ብቻ … ከማንኪያ እስከሶፋ አንጀቴን አስሬ አንዲት ነገር ልግዛ …ብራንዱን ፎቶ እያነሳች መለጠፍ እና መጎራት ነው ! ይሄ ነው ቤተሰብ …ይሄ ነው በቃ ሕይዎት …. የሁለታችንም  ጓደኛ  ነህ አንድ ነገር በላት …አለበለዚያ  የእኔና የእሷ እህል ውሃ አበቃ …ብሎኝ ቻው እንኳን ሳይለኝ ተነስቶ ሄደ !

በተቀመጥኩበት  የፌስቡክ አካውንቷን  ቸክ አደረኩ  ከሶስት ደይቃ በፊት  ከሰፊ አልጋ ምስል ጋር እንደዚህ የሚል ፅሁፍ ለጥፋለች

((ባልሽን እዛ ነገር ላይ ካስደሰትሽው  ትዳርሽ ገነት ይሆናል  ሂሂሂ ))

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

26 Sep, 07:58


የሆነ ቀን ሶስት ቲሸርት ከድሬዳዋ አመጣችልኝ ። የገዛችልኝ ቲሸርት ቀለም እና ስታይል ያምራል።ልጅ እያለሁ ለበዓል ልብስ ሲገዛልኝ እንደሚሰማኝ አይነት ደስ አለኝ ፦

የሆነ ቀን በስልክ እየተወራጨው ሳወራ ቀስ አድርጋ ስልክ ያልያዘውን እጄን ይዛ አይበሉባዬን ዳበሰቺው እያረጋጋቺኝ ነበር

የሆነ ቀን ተስፋ የቆረጥኩ ሲመስላት አንገቴ ስር ሳመቺኝ አለሁልህ ያለቺኝ መሰለኝ ።

የሆነ ቀን ሁለት ሰዓት አርፍጄባት ስመጣ ፊቷ ፍም መስሎ ቆየኝ "አሁን መጣው አሁን መጣው" እያልክ እንዲ አታድርግ እንደዚህ አይነት መጠበቅ አልወድም አለቺኝ ። ከዛን ቀን ጀምሮ እንደዛ ማድረግ አቆምኩ

የሆነ ቀን ቀንቼ ጨቀጨኳት ፎከርኩ አብራራሁ በትህትና አስረዳቺኝ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲ የሚያናድድህ ጉዳይ ውስጥ አልገባም አለቺኝ እውነቷን ነው አልደገመቺውም

የሆነ ቀን ትወጂኛለሽ ወይ አልኳት እስከ ሰማይ ድረስ ብዙ ነው የምወድህ አለች ። የሆነ ቀን ትወደኛለህ ወይ አለቺኝ ሊያውም እንደሞኝ ሊያውም ምንም ክፋት አይቶ እንደማያቅ
ሊያውም ምንም ምርጫ እንደሌለው ሰው አይነት ነው የምወድሽ አልኳት ።

ለካ ኑሮን ከሚያሳምሩት ግምባር ቀደሙ መዋደድ ነው ። እርስበርሳቹ ተዋደዱ እንዲል ቃሉ ።
ሃዬ
© Adhanom Mitiku

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

25 Sep, 04:39


የምወደው ልጅ ነበር ። እርጋታው ህልሙ መልኩ ሁኔታውን
እወደዋለሁ ስህተቱን ድክመቱን ሳይቀር ነበር የምታገሰው ።

ብጥር ...ብጥር... ከኔ ጋ ማቆየት አልቻልኩም ።

ጊዜ ሄደ ...

እኔም ሄድኩኝ

ሌላ መስመር ሌላ ኑሮ ሌላ ጠዓም አየሁኝ እሱ
ዘግይቶ ወደ ምፈልገው መንገድ መጣ

ዳር ዳር አለ እንዳልገባኝ ሆንኩኝ እብረን እንድንሆን ጠየቀኝ ..ዋጋሽ ገብቶኛል ወድጄሻለሁ አለኝ ።

አልታበይኩም አልጎረርኩም ሰነፍ ነው ቀድሞ ደርሶ ባረፈደ የሚያሾፈው ። ብስለት የሚለካው የሆነልን ሲመስለን በያዝነው አቋም እና ሁኔታ ነው ።

በትህትና አልችልም አልኩት ።

Timing is every thing ፀሎቴ ውስጥ ህልሜ ውስጥ ቅዠቴ ውስጥ ማሳካት የምፈለገው ውስጥ እምይዘው አቋም ውስጥ እሱ ነበር ። ጊዜ ሁኔታ አጋጣሚ ተደራረበ እና አንዱም ውስጥ ጠፋ !!

ምንም ስላላዋጣ ግዜ ልቤ ውስጥ የተወለደውን ፍቅር አደብዝዞት ነበር ። ልቤ ውስጥ የተከማቸውን ፍቅር ስላልወደደው ፍቅሬን ፊት ነስቼው በግዜ ብዛት ተነነ ።

ብቻ መወደድ ከብዶኝ ስለነበር ሳስታውሰው እረፍት አይሰማኝም ነበር ። እረፍት የሌለው ፍቅር ምኑን ፍቅር ነው ??

ናፍቆኝ ጓጉቼ ሳገኘው አይኑ ለኔ ስሜት አልባ እንደሆነ ስለሚነግረኝ ናፍቆቴ ወደ ድብርት ይቀየራል ።

የሚለኝን ያደረገውን የሆነውን ሁኔታውን ትርጉም አየሰጠው ስቀምር የማድር እንደነበርኩ እኔን ካልሆነ አይገባውም !!

ዛሬ ሁኔታሽ አንቺነትሽ ሁሉ ትርጉም ሰጠኝ አብረን እንሁን አለኝ ። ዘግይቶ ነበር Timing is every thing

እንደማይሆን እያወኩ ፍላጎት እንዳለኝ ምልክት ሰጥቼ አልበድለውም !!

" አልችልም" አልኩት

ቁርጣችንን አልነግር እያሉ እንደሚበድሉን መሆን አልፈለኩም ተፈላጊ የመሆኔን እርሃብ ለማስታገስ ወለም ዘለም እያልኩ አልበድለውም

በትህትና " አልችልም ሌላ የህወት መንገድ ላይ ነኝ " አልኩት ። እየመከርኩ አልተመፃደኩም ። መልካሙን ሁሉ እንዲገጥመው ግን በልቤ ተመኝቼለታለሁ ።

ትክክለኛ ነገር ትክክለኛ የሚያደርገው timing ነው !
timing is every thing እንዲሉ አበው!!
© Adhanom Mitiku

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Sep, 14:08


ቤተዘመድ ጋር አብረን ስንሄድ ግን እንደ መልካም ሚስት- እናት እና አባቱ እንደሚፈልጓት አይነት- እሆንና ምግብ አቀርበለታለሁ፡፡ እናቱ ልጃቸው እንዲህች አይነት ድንቅ ሚስት አግብቶና በትዳሩ ተደላድሎ ስለሚኖር ኩራት ኩራት ይላቸዋል፡፡
የማያደንቀን ሰው የለም፡፡ ‹‹ድንቅ ጥንዶች›› ይሉናል አንዳንዶቹ፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡
አናወራም፡፡
አንጣላም- ለጠብ የሚሆን ጉልበት እንኳን አልነበረንም፡፡
ውድቅት ላይ ቤት ቢመጣ ግድ አይሰጠኝም፡፡
ውጪ ያስቀመጣት ሴት ብትኖር እንኳን ደንታ የለኝም፡፡
ያስቀመጣት ካለችውም የወንድ ቅርፊት እንጅ ደህና ወንድ እንዳላገኘች ስለማውቅ አይቆረቁረኝም፡፡ የወንድ ልጣጭ ነው ያገኘችው፡፡ የወንድ ጭራ፡፡

የባለቤቷን ጉድለቶች አንድ በአንድ የምትቆጥር፣ ኩንታል ስህተቶቹን ተሸክማ የምትኖር፣ የወንድነት ጥላ የራቀው እርቃን እና ደካማ ባሏን አብጠርጥራ የምታውቅ ሚስት ሆኛለሁ፡፡
እርግጥ ነው- እኔም ደካማ ጎን አለኝ- ምን ጥያቄ አለው? እዚህና እዚያ ምላሴን ያዳልጠኝ ይሆናል፡፡ ነገረኛ ብጤም ሳልሆን አልቀርም፡፡ እሱም ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ጨቅጫቃ መሆኔን ነግሮኛል፡፡

እንዲህ ስለመሆኑ እና እንዲህ እንዲሆን ምክንያት ስለሆኑት ነገሮች የማወቅ አንዳችም ፍላጎት ግን የለኝም፡፡

አንዴ የሆነ አውሮፓ ያለ ኤርፖርት ውስጥ ሆኜ በጉዞ የተዳከሙ እና ጥውልግ- ትክት ያሉ ሰዎች- አይኖቻቸውን ባዶ አየር ላይ ተክለው-- ዝም ብሎ በራሱ የሚሄደው ተንቀሳቃሽ ደረጃ ላይ በደመነፍስ ሲሳፈሩና በድንዛዜ ሲሄዱ ሳይ ‹‹ትዳሬ ልክ እንደዚህ ነው››› ስል ትዝ ይለኛል፡፡

በቅርቡ የሆነ ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ አግኝቼ ነበር፡፡ ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናና አምሽቶ የከፈለበት ነው፡፡ ለአንድ ጠርሙስ ውስኪ እና ለሚበላ ነገር ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ከፍሏል፡፡ በአንድ ምሽት ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር! ያውም በአዘቦት ቀን፡፡
ደረሰኙን ሳይ ልቤ በጩቤ የተወጋ መሰለኝ፡፡ የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ አልከፍልም የሚል ግን ለመጠጥ ይሄን ያህል ብር የሚያወጣ ወንድ ሆኗል፡፡
ስለ ልጆቹ ጉብዝና ለወላጆቹ፣ ለዘመድ አዝማድ የሚጎርር ግን ተማሩ አልተማሩ ግን የማይሰጠው ሰው ሆኗል፡፡ ያውም ከእኔ በስንት እጥፍ የሚበልጥ ደሞዝ እየበላ፡፡

እርግጥ ነው እንዳሻው እንዲሆን ፈቅጄለታለሁ፡፡ የውሸት እንዲኖር ተባብሬዋለሁ፡፡ ጥሩ አባት እና መልካም ባል ነኝ ብሎ የሚያምንበትን የቁጩ አለም ገንብቶ የውሸት እንዲኖር ይሁንታዬን ሰጥቼዋለሁ፡፡
እዋሽለታለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ ነገር የሚስጠላው ነገር ግን የእሱ ውሸታምነት እኔንም የውሸት የምኖር ውሸታም ማድረጉ ነው፡፡ ሁለመናዬ ውሸት የሆነ ሰው አድርጎኛል፡፡

ምናልባት ጠርጥራችሁ ከሆነ ከሌላ ሰው ጋር መውጣት አልጀመርኩም፡፡ ሰው ጠፍቶ አይይለም፡፡ መግቢያ መውጫ ያሳጡ ብዙ ወትዋቾች አሉኝ፡፡
ግን በህግ ባለትዳር ነኝ፣ ትዳር ያለኝ ላጤ ብሆንም፡፡ ከባለቤቴ ጋር ‹‹ትዳር›› የሚባል ለትርፍ የተቋቋመ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የምንመራ ሁለት ሰዎች ብንሆንም፡፡

እንደሚስት በምንም ነገር እንዲያግዘኝ መጠየቅ ካቆምኩ ቆየሁ፡፡
እንደ ቤቱ ራስ፣ እንደ አባዋራ እሱን መከተል ከተውኩ ቆየሁ- መምራት አቁሟላ!

ግርማ ሞገሱ ጠፍቶ አይኔ ላይ ከኮሰሰ፣ ለእሱ ያለኝ ክብር ብን ብሎ ከጠፋ ሰነባበተ፡፡
በፊት በፊት ያማልለኝ የነበረ ያ ወንዳወንድነቱ….ለምሳሌ ጠዋት ጠዋት ከወገቡ በላይ ራቁቱን ሆኖ ጥርሱን ሲፍቅ ሳየው የሚሰማኝ ሞቅታ በፀፀት ተተክቷል፡፡

እስከ መቼ ነው እንደዚህ የምኖረው ግን?
እኔስ እስኪያንገሸግሸኝ፣ እስኪያቅተኝ ድረስ እዚህ ያጋደለ፣ ጣራው የሚያፈስ ጎጆ ውስጥ መኖር እችላለሁ፡፡
ከሁሉ የሚያንገበግበኝ ግን ልጆቼ የአባታቸውን ሁኔታ መረዳት መጀመራቸው ነው፡፡
አባታቸው ለቤተሰቡ ጥላ ከለላ የሚሆን ጠንካራ አባወራ አለመሆኑን ማየት መጀመራቸው ነው፡፡በተለይ ለወንድ ልጆቼ አብዝቼ እጨነቃለሁ፡፡ የአባወራ ምሳሌ አድርገው ለሚስሉት ምስኪን ልጆቼ፡፡
የወንድነት አርአያ አድርገው የሚቆጥሩት - እሱን በሆንኩ የሚሉት ሰው ይሄ በመሆኑ፣ ልጆቼ አውላላ ሜዳ ላይ ስለቀሩብኝ አዝናለሁ፡፡

ስለ ልጆቼ እጣ ፈንታ የምጨነቀው እኔ ብቻ፣ ለቤተሰቤ የምወጋው እኔ ብቻ መሆኔ ልቤን በሃዘን ያደማዋል፡፡ ውስጤን ይሰረስረዋል፡፡ ያበግነኛል፡፡
ከዚህ ግራ የገባው ሁኔታ እንዴት ማምለጥ እንዳለብኝ አላውቀም፡፡
ምክንያቱም….የቤቴን ወጪ መሸፈን እችል ይሆናል፣ ከልጆቼ ጋር ማውራት እና መጫወት እችል ይሆናል፣ የቤት ሥራቸውን አብሬያቸው መስራት፣ ሲጎብዙ ማበረታታት፣ እንደ እናት ስለ እነሱ መፀለይ አያቅተኝ ይሆናል፡፡ ግን እንዴት መልካም አባወራ መሆን እንዳለባቸው ላሳያቸው፣ አርአያ ሆኜ ልመራቸው አልችልም፡፡ ያንን ሊያደርግ የሚችለው አባወራው ብቻ ነው፡፡ የእኔ አባ ወራ ተብዬ ደግሞ ሃላፊነቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ፣ ወንድነቱን እንደ አሮጌ ካፖርት አውልቆ ወንበር ላይ ማንጠልጠልን መርጧል፡፡
-----አበቃ------

by Hiwot Emshaw

@AlexAbreham

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

24 Sep, 14:08


ሴት እና ትዳር- ‹‹እርቃን››- ክፍል ሁለት

-------------------
ትዳራችን ይነፍስበት የጀመረው እዚህ ግባ በማይባሉ ጥቃቅን ነገሮች መነሻነት ነበር፡፡

አለ አይደል…ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ እንዴት አደርሽ ማለት ሲተው…(ባሎች፣ እባካችሁ..ሁሌም ሚስቶቻችሁን እንዴት አደርሽ ብላችሁ ጠይቁ….በክር ከተሰራች አሻንጉሊት ጋር አይደለም እኮ ተኝታችሁ ያደራችሁት! አንድ ቀን እንዴት አደርሽ ብላችሁ መጠየቅ ስትረሱ ነገም አታስታውሱም…ከዚያ ይለምድባችሁና ልክ አዳሪ ትምህርት ቤት እንደሚኖር ተማሪ ብድግ ብላችሁ ካልጋ መውጣት ትጀምራላችሁ፡፡ )

እና እንዳልኳችሁ ጠዋት መነሳትና ሰላም ሳይለኝ ወደ ሽንት ቤት መሄድ ጀመረ፡፡
ሁልጊዜ እንዴት አደርህ የምለው እኔ ሆንኩ፡፡ ከዚያ እኔ ብቻ እንዴት አደርህ ማለቱ ታከተኝ፡፡ እየቆየ ሲሄድ ጠዋት ጠዋት እኔን ማየት እንኳን እንዳቆመ ማስተዋል ጀመርኩ፡፡

ልብስ እየለባበስን ስናወራ እንኳን ጭራሽ አያየኝም፡፡ ለማየት የማስቀይም አይደለሁም፤ ሁሌም ራሴን በመስታወት ስለምመለከት ይሄንን አውቃለሁ፡፡ እና ታዲያ ምን ሆኖ ነው የማያየኝ? እኔ ደግሞ ሰው ካላየኝ ኖርኩ አልኖርኩ ግድ እንደሌለው ነው የሚሰማኝ፡፡ ካላየኸኝ የለሁም ማለት ነው…ድምጽ ብቻ ያላት መንፈስ ሆንኩ ማለት ነው…(.ወንዶች፣ እባካችሁ ሚስቶቻቸሁን እዩ፡፡ )

ጠዋት ጠዋት ሰላም ማደሬን ባይጠይቀኝም፣ ባያየኝም ግን ትዳራችን ጥሩ የሚባል ነበር፡፡ ቤቱን ማስተዳደር ላይ አልሰነፈም፡፡ ለልጆቹ መጫወቻ እና ልብስ ይገዛል፡፡ አንዳንዴም አብሯቸው ይጫወታል፡፡

ከዚያ ሕይወት በማይታሰብ ፍጥነት መክነፍ ጀመረች፡፡ ልጆቻችን ትምህርት ቤት ሲገቡ የትምህርት ቤት ክፍያ ራስ ምታት እና ለነገ ጥሪት የመቋጠር ጭንቀት ይወጥረን ጀመር፡፡ ባለቤቴ ትልልቆቹን ወጪዎች ሲችል እኔ ደግሞ ጥቃቅን የቤት ቀዳዳዎችን እየደፈንሁ ኑሮ ቀጠለ፡፡

ከዚያ ሳይታወቀን ሁለታችንም በየራሳችን ዛቢያ የምንሽከረከር፣ በማይገናኙ መንገዶቻችን አለእረፍት የምንሮጥ እና የምንባዝን ሰዎች ሆንን፡፡

እሱ ቤት ከሚኖርበት ጊዜ ስራ ላይ የሚያሳልፈው ጊዜ እየበዛ፣ ቤት ሲመጣም በድካም ብትንትን ብሎ እና ልጆቹን እንኳን ማናገር እንዳይችል ሆኖ፣ ለመኝታ ብቻ ሆነ፡፡
እሁድ እሁድ ቤት ይሆናል ግን ከቅዳሜ የዞረ የመጠጥ ድምሩን ስለሚያወራራድ እንዳለ አይቆጠርም፡፡ ሁሌም በስራ ደክሞ ስለሚገባ ልጆቼን ብስክሌት መንዳት እንኳን ያስተማርኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ለነገሩ ጭራሽም ለማድረግ አልሞከረ፡፡

እያደር እሱ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ስራዎችን ፣ ሊወጣቸው የሚገቡ ሃላፊነቶችን እኔ ማድረግና መወጣት ጀመርኩ፡፡ የቧንቧ ሰራተኛ ፈልጎ ማግኘት…የልጆቹን ትምህርት ቤት መምረጥ፡፡

ልጆቻችን እያደጉ ሲሄዱ አብሯቸው ማሳለፍ ያለበትን ጊዜ ሳያሳልፍ እድሜያቸው እንዳያልፍና እንዳይቆጨው ብዬ ጊዜ እንዲሰጣቸው የምችለውን ሁሉ ጣርኩ፡፡ እስቲ መናፈሻ ወይ መጫወቻ ቦታ ውሰዳቸው…ብስክሌት አብረሃቸው ጋልብ….አዋራቸው፣ ወንዶቹን ደግሞ እንዴት አይነት ወንድ…እንዴት አይነት አባት መሆን እንዳለባቸው አሳያቸው ስል ወተወትኩት፡፡

እሱ ግን ሁሌም ጊዜውን የሚሻማ ነገር አያጣም፡፡ ሁሌም ከዚህ የሚበልጥበት ነገር አይጠፋም፡፡

ከዚያ የቤተሰቡ ራስ እኔ ሆንኩ፣ ውሳኔ አሳላፊዋ ሆኜ አረፍኩ፡፡ ከጊዜ በኋላ የትምህርት ቤት ክፍያ በጊዜ መክፈል አቆመ፡፡ ጭራሽ ትምህርት ቤቱ ደውሎ ክፍያ ይጠይቀኝ ጀመር፡፡ ያን ጊዜ የዚያኛውን ሴሚስተር ራሴ እከፍልና የሚቀጥለውን እንዲከፍል ባየው ባየው እሱ እቴ!

---
አባቴ ለእናቴ ምን አይነት ባል እንደነበር አላውቀም፡- ምናልባት እንደ ባል ያጎደለባት ነገር ይኖር ይሆን አላውቅም፡፡፡ ለእኔ ግን ምን አይነት አባት እንደነበር ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ሃላፊነቱን የሚያውቅና በአግባቡ የሚወጣ አባት ነበር፡፡ በዚያ ላይ ኩሩ ነበር- የእኔ አባት፡፡

አንዴ አስታውሳለሁ- አስር ወይ አስራ አንድ አመቴ እያለ- ቅዳሜ ቀን ነው…. ጠዋት ቁርስ እየበላን በልጅነት አእምሮዬ ያኔ- ምክንያቱ አልገባኝም ግን የሆኑ የባንክ ሰራተኞች ወደ ቤታችን መጡ፡፡ አባዬ እኔና እማዬን ካለንበት ትቶን ሊያናግራቸው ይሄዳል፡፡

በሳሎኑ መጋረጃ ውስጥ ውጭ ቆሞ ሲያዋራቸው አያለሁ፡፡ ከአጥራችን ውጪ የቆመው የጭነት መኪና የቤት እቃችንን በሙሉ ለቃቅሞ ለመሄድ የጓጓ ይመስላል፡፡ እማዬ ከተቀመጠችበት ሳትነሳ፣ አንዴ እንኳን ሳትንቀሳቀስ፣ ተነስታ ወደ አባዬ ሳትሄድ እዛው ቁጭ ብላለች፡፡
የእሷ ተረጋግቶ መቀመጥ እኔንም ሲያረጋጋኝ አስታውሳለሁ፡፡ እሷ እንደዛ ረጋ ብላ ቁጭ ካለች ውጪ እየሆነ ያለው (መጥፎ ነገር ይመስላል) ምንም ነገር ቢሆን አባዬ መላ እንደማያጣለት እና ወደ ቁርሱ እንደሚመለስ ነገረኝ፡፡
እናም ልክ እንዳሰብኩት ሆነ፡፡ አባዬ ያንን ቀን ልክ ሌሎች ቀኖችን እንደሚያሳልፈን በብልሃት አሳለፈን፡፡
ከዚያ በኋላ ስለ ወንድነት ያለኝ ግምት አባቴን ተደግፎ የተሳለ ሆነ፡፡ ወንድ ልጅ፣አባወራ ሲሆን ቤተሰቡ የሚገጥመውን ችግርን ወጥቶ እንደ ወንድ መጋፈጥ እንዳለበት፣ ከዚያም በኩራትና በልበ ሙሉነት መቆም እንዳለበት ከአባዬ ተማርኩ፡፡
.

እናትና ሚስት ሆኜ ቤቴን ማስተዳደር ምኞቴ ነበር፡፡ ባሏን የምትከተል፣ ታታሪና ጨዋ ሚስት መሆን ነበር ፍላጎቴ፡፡ ሚስት፡፡ ቀስ በቀስ ግን የአባወራውን ስራ መረከብ ጀመርኩ፡፡ ባል ሆንኩ፡፡ እሱ መወሰን ያለበትን ነገር መወሰን፡፡ የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል፡፡

ያን ጊዜ በሌላ አይን እመለከተው ጀመር፡፡ በፊት የምመካበት እና የማደንቀው ወንድ መሆኑን አቆመ፡፡ አቅጣጫው ጠፍቶበት የሚማስን ሰው ሆኖ አገኘሁት፣ አቅጣጫው የጠፋበት ሰውን ደግሞ መከትል አልችልም፡፡

ከጊዜ በኋላ አንዳችን ለአንዳችን ጭራሹን ባእድ ሰዎች ሆነን አረፍነው፡፡
የባል እና ሚስት ወጋችን እንደ በርሃ ዝናብ በጭንቅ የሚመጣ እና በስንት ጊዜ የሚከሰት ነገር ሆነ፡፡
ከስንት አንዴ ሆኖልን ፍቅር ስንሰራ እንኳን ሃሳቤ ወደማልመው የእንጆሬ እርሻዬ እየሄደ ያስቸግረኛል፡፡
ስናወራ ከሌላ አለም እንደመጣ ሁሉ፣ ሁሉ ነገሩ እንግዳ ይሆንብኝ ጀመር፡፡ የማላውቀውን ቋንቋ እንደሚናገር እንግዳ ሰው፡፡

ይሄ ሁሉ የሆነው አሪፍ ሚስት መሆኔን ስላቆምኩ ይሆናል፡፡ እንደ በፊቱ አምሽቶ ሲመጣ እና እራት እየበላ የዚያን እለት ቢሮ ስለተፈጠሩ አስደናቂ ነገሮች ሲያወራኝ እያዳመጥኩ፣ ቁጭ ብዬ አላየውም፡፡

ይልቅ ለጥቂት ቀናት ፊልድ ሲሄድ ልቤ ጮቤ ይረግጣል፡፡፡
ያን ጊዜ ቤቱ ይሰፋኛል፣ ክፍሎቹ ወደ ጎን ልጥጥ ይላሉ… ያኔ.መተንፈስ እችላለሁ፡፡
ከፊልድ የሚመለስ ቀን ቀድሜው ገብቼ ደህና የሚበላ ነገር አዘጋጅቼ (ድሮ ቢሆን የምበላው ነገር እኔ ነበርኩ!) ለመጠበቅ አልቸኩልም፡፡ በፊት በፊት በየትኛው አውሮፕላን እንደሚመጣ፣ ትራንዚቱ የት እንደሆነ፣ ስንት ሰአት የት እንደሚደርስ አውቅ ነበር፡፡ አንዳንዴማ ኤርፖርት ሁሉ ሄጄ እቀበለው ነበር- ያውም ምን እንደሚናፍቀው ስለማውቅ ትኩስ ቡና በፔርሙስ ይዤ!
አሁንስ? አሁንማ ደስ የሚለኝ ሲሄድልኝ ነው፡፡ ምክንያቱም ቤት ውስጥ ሆኖ ልክ እንደ ወንዶቹ፣ ልክ እንደ ቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ እንደ ደህና አባወራ ወዲህ ወዲያ ሲል ላየው ስለማልፈልግ ነው፡፡ በዚያ ላይ…የሚያገኘውን ገንዘብ የት እንደሚያደርገው ሳላውቅ ወይ ሳይነግረኝ…