Addis Media Network-AMN @addismedianetwork Channel on Telegram

Addis Media Network-AMN

@addismedianetwork


This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be voice of generation, as our motto stands for.
የትውልድ ድምፅ !!
contact us via:- E-mail:- [email protected]
twitter.com/AmnAddis

AMN (Addis Media Network) (Amharic)

የAMN (Addis Media Network) በማህበረሰብ ታሪኩን እና መረጃዎችን የታላቅ ቤተሰብ ለማድረግ የተከበረው በአማርኛ መተረብህን ለቀብን፡፡ AMN እናቱ ካለፉት አንባቢዎች ወደ ቤተሰቡ ስለማስደሰት ትምህርት ይቀላቀሉን፡፡ እንደ ቱልን ድምፅ እናታችን:- ኢ-ሜይል:- [email protected] twitter.com/AmnAddis

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 15:01


ቅዳሜ ማለዳ በሚደረገው የራስ አልካይማህ ግማሽ ማራቶን በሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

AMN - ጥር 22/2017 ዓ.ም

18ኛው የራስ አልካይማህ ግማሽ ማራቶን ቅዳሜ ማለዳ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ራስ አልካይማህ ከተማ ይካሄዳል፡፡ በሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የማሸነፍ ግምት አግኝተዋል፡፡

እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ ቀዳሚዋ ናት፡፡ በትራክ ውድድር ኢትዮጵያን በኦሊምፒክና ዓለም ሻምፒዮና የወከለችው እጅጋየሁ ለማሸነፍ ቀዳሚ ግምት ያገኘች አትሌት ናት፡፡

የቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የ10 ሺ ሜትር ነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ እጅጋየሁ በራስ አልካይማህ የምትጠበቅ አትሌት ናት፡፡ ከሶስት ወራት በፊት የቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶንን በአራተኛነት ስታጠናቅቅ ያስመዘገበችው አንድ ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ የራሷ የርቀቱ የምንጊዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡

የባለፈው ዓመት የራስ አልካይማህ ግማሽ ማራቶን አሸናፊዋን ጽጌ ገብረ ሰላማን አስከትላ ቫሌንሲያ ላይ የደመቀችው እጅጋየሁ፣ የራስ አልካይማህ ግማሽ ማራቶን ሪከርድን የተተስተካከለ ፈጣን ሰዓት ይዛ ትሮጣለች፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ
👇
https://web.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02GEaL14rsBrGg7cKQxSyxPm15FE2JbvW2r9qucXdZXedjUnFpx61RoiNaaYkkWrwJl&id=61557351622843

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 10:43


የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላትን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመረቀ

AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም

በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሠልጣኞችን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመርቋል።

የኮማዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለተመራቂ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት የአየር ወለድ ልዩ ምልክት የሆነውን የደረት ክንፍ አልብሰዋል።

የአየር ወለድ ስልጠና የወሰዱት የክፍሉ አባላት ቀደም ብለው እጅግ ፈታኝና ውስብስብ የሆነ የልዩ ሀይል ፀረ- ሽብር ስልጠና መውሰዳቸውን ሌተናል ጄኔራል ሹማ ተናግረዋል፡፡

የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጣቸውን ውስብስብና ልዩ ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችላቸው አቅም እንዲኖራቸው ተደርገው በላቀ ደረጃ መሰልጠናቸውን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ፣ ተመራቂዎችም የሀገሪቷ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የዜጎቿን ህይወት የመቀየር ልማታዊ ጉዞ እንዳይደናቀፍ የተዘጋጁበትን ልዩ ግዳጅ በፍፁም ዲሲፕሊንና ፅናት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0urp6fzsdJbez1HXSZeiDKX8RDNiksvCQy2Y3P6ovVQmjH2uNo9XvGKQurXjV69R4l

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 10:40


የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

AMN - ጥር 22/2017 ዓ.ም

ከጥር 23 አስከ 25 በሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የሚሳተፉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በ8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ግንባታው የተጠናቀቀው የአቃቂ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክላስተርን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡና በመገንባት ላይ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያዘምኑ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እንዲሁም የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልሉ ፕሮጀክቶችን ስለመመልከታቸው ጎብኚዎች ተናግረዋል።

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በሚካሂደው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤ ላይ 1 ሺ 700 በድምጽ የሚሳተፉ የፓርቲው አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በካሳሁን አንዱዓለም እና አንዋር አህመድ

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 10:39


የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር እና የሪፎርም ስራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN - ጥር 22/2017 ዓ.ም

ከጥር 23 አስከ 25 የሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር እና የሪፎርም ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባስጀመሩት ጉብኝት በአዲስአበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች እየተጎበኙ ነው።

የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው በመሬት ልማት ዙሪያ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ባብራሩበት ወቅት እንዳሉት በሪፎርሙ ተቋሙን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በማሻገር ከብልሹ አሰራር ጋር ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ማስቀረት ተችሏል።

በቢሮው በሪፎርም የተሰሩ ስራዎችን የጎበኙት የብልጽግና ጉባኤ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ያገኙትን ተሞክሮ ወደ መጡበት ሲመለሱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል።

በአሸናፊ በላይ

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 10:37


የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ከሞሮኮው ናሽናል ራሊ ኦፍ ኢንዲፔንደንትስ(አር ኤን አይ) ፓርቲ ተወካይ ፕሮፌሰር መሀመድ ሳዲኪ ጋር ተወያዩ

AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ከሞሮኮው ናሽናል ራሊ ኦፍ ኢንዲፔንደንትስ(አር ኤን አይ) ፓርቲ ተወካይ ፕሮፌሰር መሀመድ ሳዲኪ ጋር ተወያይተዋል።

የሞሮኮ ናሽናል ራሊ ኦፍ ኢንዲፔንደንትስ ፓርቲ ተወካይ ፕሮፌሰር መሀመድ ሳዲኪ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመታደም ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

በዛሬው እለትም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

በውይይታቸውም የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጽናት ለቀጣይ ቁርጠኝነታችንን የምናድስበት ነው ብለዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02oHtPysTZiUtWdsfrysiskrZ6qVYXH9itKEbGS4PjowcxNjHXggDFit7cSkP5zCyPl

Addis Media Network-AMN

30 Jan, 10:35


በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተመልክተናል:- የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች

AMN - ጥር 22/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተመልክተናል ሲሉ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚደካሄደውን የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁና በመገንባት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከጎበኟቸው የልማት ስራዎች መካከልም የለሚ እንጀራ ማዕከል ፣ የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቪሽንና ኮንቬሽን ማዕከል እና የለሚ ኩራ የገበያ ማዕከል ይገኙበታል።

የልማት ስራዎቹ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የኑሮ ውድነትን የሚያረጋጉ እና የከተማዋንም ገጽታ ከፍ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

እነዚሁ የልማት ስራዎች ፓርቲው ቃል የገባቸውን በተግባር ያረጋገጠበት ማሳያ ነው ብለዋል።

በፍቃዱ መለሰ

Addis Media Network-AMN

28 Jan, 17:17


ከተናጥል ትርክት ይልቅ የጋራ ፤አሰባሳቢ የወል ትርክት ላይ በማተኮር አገርን ወደ ከፍታ ማሻገር ይገባል፡-አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN - ጥር 20/2017 ዓ.ም

ከተናጥል ትርክት ይልቅ የጋራ ፤አሰባሳቢ የወል ትርክት ላይ በማተኮር አገርን ወደ ከፍታ ማሻገር ይገባል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡

አቶ ሞገስ ባልቻ የብልጽግና ፓርቲ ቅድመ ጉባኤን አስመልክተው ማብሪያ ሰጥተዋል
በሀገሪቱ የነበረው የፖለቲካ ትርክት ጽንፍ ላይ የተመሰረተ እና ልዩነት ላይ አነጣጥሮ ይሰራ የነበረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ይህም ለዕርስ በዕርስ ግጭት መነሳሳትን የጋበዘ እና ለዛሬው የኢትዮጵያ ዋነኛ ምክንያት ፈተና መሆኑን አውስተዋል፡፡

ይህንን ሊያክም የሚችል አስታራቂ እና የሀገሪቱን ሁኔታ እና የፖለቲካ አኗኗር እና ስሪት መሰረት ያደረገ እንዲሁም የህዝቡን ሁኔታ ያማከለ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02iEL48dTAaiEPvdfLRYELiB6ZjhBmHzpBtGfsUjsurjfb2Jb59fXu18Scp1LxuJDml

Addis Media Network-AMN

28 Jan, 17:15


በዲፕሎማሲው መስክ የተከናወኑ የፖሊሲ ለውጦች የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ከፍ አድርገዋል- አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

AMN - ጥር 20/2017 ዓ.ም

በዲፕሎማሲው መስክ የተከናወኑ የፖሊሲ ለውጦች የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ከፍ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናገሩ።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በዲፕሎማሲው መስክ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትንና የተገኙ ስኬቶችን በማስመልከት አምባሳደር ብርቱካን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም፥ ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህ በመተግበር ከጎረቤት ሀገራትና በቀጣናው ትብብርን በማስቀደም መስራቷን አጠናክራ መቀጠሏን አንስተዋል።

ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ በሚሰጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በጋራ ተጠቃሚነትና በሰጥቶ መቀበል መርህ የልማት ትስስሮችን የማጠናከርና ቀጣናዊ ሰላምን የማስጠበቅ ስራዎች በስፋት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በንግድና የምጣኔ ሃብት ትስስር፣በኤሌክትሪክና የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲሁም በውሃ እና በሌሎች መስኮች የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን ተወጥታለች ብለዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0Hwr7a3Xxq7BgQpyXiYDZgxnv2eEPTkS74Cqv54JLP5y1GWv9gqqct6mjBMFY2QsJl

Addis Media Network-AMN

28 Jan, 17:12


ከለውጡ ወዲህ የተወሰዱ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ኢኮኖሚውን ከቀውስ ታድገዋል- ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ

AMN - ጥር 20/2017 ዓ.ም

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ገቢራዊ የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ከቀውስ መታደግ ማስቻላቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በኢኮኖሚው መስክ የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎችና የተገኙ ስኬቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ከለውጡ በፊት የነበረው አሰራር ኢኮኖሚውን በአግባቡ መምራት ባለመቻሉ በከፋ ችግር ውስጥ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ከለውጡ በፊት የመንግሥት ገቢ የተቀዛቀዘበት፣ የዕዳ ጫናው የናረበት፣ የባንኮች የማበደር አቅም ያሽቆለቆለበት በአጠቃላይ የፋይናንስ ስርዓቱ ጤናማ ያልሆነበት ወቅት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከለውጡ በኋላ በተወሰዱ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ችግሮችን ተቋቁሞ ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ የሚያስችል ጤናማ ኢኮኖሚ በመገንባት ከቀውስ መታደግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የፊሲካልና ሞኒቴሪ ፖሊሲ እርምጃዎች፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማሻሻያዎች፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያሳድጉ አሰራሮች ገቢራዊ መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኢኮኖሚው በውስን ዘርፎች ላይ የተንጠለጠለ እንደነበር በማንሳት፤ ከለውጡ በኋላ ለብዝሃ ኢኮኖሚ የተሰጠው ትኩረት ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02uL1iwvDiYuagZc3qnnNPSZxqtgwJ96zHT829DbgPxwEeut9UEnHaQSGDUpZ1ds6ql

Addis Media Network-AMN

28 Jan, 17:08


ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የጣሊያን ከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ሚኒስትር አና ማሪያ ፈርመውታል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በሁለቱ ሀገራት የተደረገው ስምምነት በትምህርቱ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ነው።

በትምህርት ዘርፉ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልጸው የሚደረገው ድጋፍ ፍትሃዊና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለውን ሥራ እና በትምህርቱ ዘርፍ ትብብር የሚሹ ጉዳዮችን ለሚኒስትሯ አብራርተውላቸዋል።

ሚኒስትር አና ማሪያ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጣሊያን አጋር መሆኗን አንስተው ሁለቱ ሀገራት በትምህርቱ ዘርፍ በላቀ ትብብር እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

የተፈረመው መግባቢያ ስምምነት በጣሊያን እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ቀጥተኛ ትብብር እንዲኖር የሚያበረታታ ነው መባሉን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

28 Jan, 10:42


ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ሊገዛ እየተደራደረ መሆኑን ገለጹ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቲክቶክን ለመግዛት ውይይት ላይ እንዳለ እና በማህበራዊ ሚዲያው ሽያጭ ላይ የሚደረጉ ፉክክሮችን ማየት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ግዙፉ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ለጨረታ ዝግጁ ስለመሆኑ በጋዜጠኞች የተጠየቁት ፕሬዚዳንቱ፣ “አዎን” በሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በርካታ ኩባንያዎችም ቲክቶክን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን አክለዋል፡፡

ትራምፕም ሆኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከብሔራዊ ደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የቻይናው ኩባንያ ቲክቶክ እንዲሸጥ ለዓመታት ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በአሜሪካ 170 ሚሊየን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ መተግበሪያ እንዲታገድ ባለፈው ሳምንት የባይደን አስተዳደር ያሳለፈውን ውሳኔ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለ75 ቀናት እንዲራዘም ማዘዛቸው ይታወሳል፡፡

ለቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ለ75 ቀናት እንዲራዘም የፈቀዱት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ባይትዳንስ መተግበሪያውን እንዲሸጥ ግፊት ያደረጉ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት እንዳደረጋቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 16:14


ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

AMN- ጥር 19/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።

የተባበሩት መንግስታት ቱሪዝም(UN Tourism) ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሞሮኮንና ግብጽን በማስከተል ባለፉት አምስት አመታት የጎብኝዎች ቁጥር ከነበረበት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።

ከአለም ደግሞ ኳታርን፣ ኤል ሳልቫዶርን፣ አልቤንያን፣ ሳዑዲን እና ኩራካዎን በመከተል ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 12:36


ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ በሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ

AMN-ጥር 19/2017 ዓ.ም

ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሰሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከዚሁ ልማት ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ መልዕክት አስተላልፏል።

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 10:43


'የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል' ፡- አቶ አደም ፋራህ

AMN - ጥር 19/2017 ዓ.ም

ከጥር 23 አስከ 25 በሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይላለፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጉባኤውን የተሳካ ለማድረግ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅትም ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

“ከቃል እስከ ባህል” የሚለው የጉባኤው መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮን በአግባቡ የሚገልጽና ፓርቲው በጉባኤው፣ በፕሮግራሞቹ እና በምርጫ ወቅት የገባቸውን ቃሎች እና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በስኬት ተግባራዊ ማድረጉን እና የፓርቲውን ቀጣይ አቅጣጫ አመላካች መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ጉባኤው በሶስት ምክንያቶች ከፍተኛ ትኩረትን እንደሚስብ የገለጹት አቶ አደም ታላቅ ህዝብና ሀገርን የሚመራ ፓርቲ የሚያደርገው ጉባኤ መሆኑ አንዱ ትኩረት የሚስብበት ምክንያት ነው ብለዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0384i8oXcCCmU8fxkb2HW82sZw2bZdDz6gAguADi1m7M3yi25VirEnNncgcpjPbKKzl

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 10:41


በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ሺህ 300 ሊትር በላይ ቤንዚን ተያዘ

AMN - ጥር 19/2017 ዓ.ም

በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ሺህ 300 ሊትር በላይ ቤንዚን መያዙን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ሰንጋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

መንግስት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ በህጋዊ መንገድ እንዲደረግና ግብይቱም በቴሌ ብር ብቻ እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ይሁንና አንዳንድ ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን ብቻ ታሳቢ በማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ ግብይት በመፈፀም ህጋዊ የግብይት ሰንሰለቱን ወደ ጎን በመተው የሀገር ሀብት የሆነውን ነዳጅ በማሸሽ በውድ ዋጋ ለመሸጥ ሲታትሩ ይስተዋላል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ፖሊስ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የዚሁ ስራ አካል የሆነው የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ የነበረ 2ሺህ 360 ሊትር ቤንዚል ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ መንግስት ያወጣውን የነዳጅ መመሪያ በመተላለፍ የሀገር ሀብት የሆነውን ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጡ ሲሉ መያዛቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል ።

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 10:40


ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው

AMN - ጥር 19/2017 ዓ.ም

ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የልማት አጋሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ፣ የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ እና የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ በስብሰባው ከተገኙ የሀገራት መሪዎች መካከል ይገኙበታል።

በኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሚመራው ስብሰባ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።

ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ በተለይም በህብረቱ ዘላቂ ፋይናንስ እና የስራ መዋቅር ማሻሻያ እንዲሁም ህብረቱ ለአህጉራዊ ፈተናዎች መፍትሄ በመስጠት ግቦቹን ማሳካት የሚችልበት አቅም መገንባት ላይ ያተኮረ ነው።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እ.አ.አ በየካቲት ወር 2024 የአፍሪካ ህብረት የተቋማዊ ማሻሻያ ስራ እንዲመሩ መመረጣቸው እንደሚታወስ ኢዜአ ዘግቧል።

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 10:39


ኤም ኤን አር ሲ የተባለ ኩባንያ 3 የመንገድ ጠርዝ (curve stone ) መስሪያ ማሽኖችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ድጋፍ አደረገ

AMN - ጥር 19/2017 ዓ.ም

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማሽኖቹ በከተማዋ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት እና ሌሎችም የመንገድ ስራዎች የመንገድ ጠርዞችን በጥራት እና በፍጥነት ለመገንባት ያግዛሉ ብለዋል።

ኤም ኤን አር ሲ ኩባንያ እና ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ማህደር ገብረ መድህን የከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው የተለያዩ የበጎ አድራጎት እና ሰው ተኮር የልማት ተግባራት በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸው በኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሠማራትም አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ በማምጣት እና በሀገራችን በማስተዋወቅ ረገድም ሚናቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በመንገድ ስራ እና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ያለውን የመንገድ ጠርዝ መስሪያ ማሽን እጥረት በመመልከት ለከተማ አስተዳደሩ የማሽን ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች ስንተባበር ሀገርን መገንባት እና ማሳደግ እንችላለን ብለዋል።

ለከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ከተደረጉት የመንገድ ጠርዝ መስሪያ ማሽኖች አንዱ ለዋና መንገድ ጠርዝ መስሪያ የሚያገለግል ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ለአረንጓዴ መናፈሻ ጠርዝ ስራ የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።

በሰብስቤ ባዩ

Addis Media Network-AMN

27 Jan, 10:38


ኢትዮጵያ በአካታች የዲጂታል መሠረተ ልማትና ኢኮኖሚ ግንባታ ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN - ጥር 19/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከለውጡ ማግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በመተግበር አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባትና የመንግሥት አገልግሎትን ለማሻሻል ወሳኝ መሠረት ማስቀመጧን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን የተመለከተ ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናትን በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምረዋል።

ኢትዮጵያ ከለውጡ ማግስት የቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድሎችን ለመጠቀም እና ፈተናዎቹን ለማለፍ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እየተገበረች እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

መንግስት የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሰረተ ልማት ማስፋፋቱን የጠቀሱት አቶ ተመስገን፥ የህግ እና የአሰራር ማዕቀፎችን ስራ ላይ በማዋል የመንግሥት ተቋማት አገልግሎትን በዲጂታል የማዘመንና ለዜጎች ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።

በስትራቴጂው የትግበራ ዓመታት የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትና ክፍያ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን አንስተዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0ZKsitCa1uy1CHsRMH5ysGqDMhi83ddqBLw37aAtmib5radzxTPq1ZbmxZ6ibdZrBl

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 14:55


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ መከተል የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎችን ይፋ አደረጉ

AMN - ጥር- 18/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች ብለው የዘረዘሯቸው

1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣
2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጂማ ላይ ማቀነባበር፣
3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣
4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣
5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣
6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣
7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣
8. የጂማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣
9. የጂማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣
10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል፣ የሚሉ ናቸው ፡፡

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 14:44


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው

AMN - ጥር- 18/2017 ዓ.ም

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ምክር ቤቱ በነገ ልዩ ስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያደምጥ ሲሆን፤ 2 የብድር ስምምነቶችን መርምሮ ያፀድቃል።

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 13:49


የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ 13 የአምቡላንስ ተሸከርካሪዎችን በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት አስተለላፈ

AMN - ጥር- 18/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለወሊድ እና ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ 13 የአምቡላንስ ተሸከርካሪዎችን በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት አስተለላፈ፡፡

ቢሮው አምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘ ሲሆን በከተማዋ የሚሰጠውን የወሊድ እና ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት ያግዛልም ተብሏል፡፡

አምቡላንስ ተሸከርካሪዎቹን ለየክፍለ ከተሞቹ ያስረከቡት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ አዳዲሶቹን ጨምሮ በከተማ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶች ቁጥር ከ106 መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ይህም ከ5 ዓመታት በፊት በከተማዋ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩ አምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ቁጥር በሶስት እጥፍ የሚበልጥ ነው ብለዋል፡፡

አምቡላንሶቹን የተረከቡ የጤና ተቋማት ተሸካሪዎቹን ለታለመላቸው አላማ በማዋል የሚሰጡትን የወሊድ እና ድንገተመኛ ህክምና አገልግሎት እንዲያሻሽሉም የቢሮ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡

ተሸክርካሪዎቹን የተረከቡ የየክፍለ ከተሞቹ የጤና ፅ/ቤት ቤት ኃላፊዎች በበኩላቸው ድጋፉ የሚሰጡትን የጤና አገልግሎት ለማቀላጠፍ የሚረዳ መሆኑን ገልፀው ለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሰግድ ኪዳነማርያም

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 12:44


የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በዓለም አቀፍ የ2025 የSWAT ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ዱባይ አቀና

AMN - ጥር- 18/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን (SWAT) የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባዘጋጀቺው ዓለም አቀፍ የ2025 የSWAT Challenge ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በቂ ዝግጅት አድርጎ ዱባይ በአል ሩዋይ ከተማ እ.ኤ.አ. የካቲት 1 ቀን 2025 በሚጀምረው የSWAT Challenge ውድድር ላይ፤

በታክቲካል ኦፕሬሽን ቻሌንጅ ፣ በጥቃት ቻሌንጅ ፣ በVIP አመራር የማዳን ተልዕኮ ፣ በከፍተኛ ታወር መውጣትና መውረድ ፣ በመሰናክል ኮርስ እንደሚወዳደር ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቡድኑን በሸኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ቡድኑ ተወዳድሮ ከማሸነፍ ባለፈ በፈጣን ምላሽ ሰጭነት ላይ ተሞክሮውን ለማካፈል፣ ከዓለምአቀፍ ልምምዶች ጋር ለመተዋወቅ፣ ከተለያዩ ሀገራት ጥሩ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም እና ዝግጁነቱን የበለጠ ለማሳደግ ውድድሩ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።

በውድድሩም አሜሪካና ቻይናን ጨምሮ ከ50 ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ የSWAT ቡድን እንደሚሳተፉ የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 12:17


ብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

AMN - ጥር- 18/2017 ዓ.ም

ብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያ ጉባኤው በገባው ቃል መሰረት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ ፓርቲው በመጀመሪያው ጉባኤ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች የፈጸማቸውን ተግባራት በተመለከተ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ራዕያችን በ2022 የዜጎች መብትና ጥቅም የተከበረባት፤ ማህበራዊ ጥበቃ የተስፋፋበት የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው።

ከዚህ በመነሳትም ብልፅግና ፓርቲ የሴቶችንና ወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች በህግ አውጪ፣ በህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚ አካላት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ከለውጡ በፊት ከነበረበት 23 በመቶ ወደ 35 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ዜጎች በመረጡት አደረጃጀት የመደራጀት መብትና ጥቅማቸውን ማስከበር እንዲችሉ ባከናወናቸው ተግባራት የመደራጀት ምጣኔ ከ10 ወደ 40 በመቶ አድጓል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃውን ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://www.facebook.com/100064901462046/posts/pfbid02aHMP1ToAQyc1S58Jura9BT5a9mCZfugZfDw2nUgLyHEo3LYNr6fzMJGvZFnp32Yfl/?app=fbl

Addis Media Network-AMN

26 Jan, 10:27


ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አላከበረም በሚል እስራኤል ወደ ሰሜናዊ ጋዛ የሚወስደውን መንገድ መዝጋቷ ተገለጸ

AMN-ጥር 18/2017 ዓ.ም

ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፍርሷል በሚል እስራኤል ከከሰሰች በኋላ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በሰሜናዊ ጋዛ ወደቤታቸው እንዳይመለሱ ተከልክለዋል፡፡

ሃማስ ከፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ አስሯቸው የነበሩ አራት የእስራኤል ሴት ወታደሮችን በትናንትናው ዕለት በ200 ፍልስጤማውያን እስረኞች ተለዋውጧል።

ይሁን እንጂ ሃማስ ወታደር ያልሆኑ ተጨማሪ ሰዎችን ለመልቀቅ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣አርቤል ይሁድ የተባለች እስራኤላዊት ከተለቀቁት መሀል አለመካተቷ አለመግባባት ቀስቅሷል።

ሃማስ፣ ይሁድ በሕይወት እንዳለች እና በሚቀጥለው ሳምንት እንደምትለቀቅ ቢገልፅም፣ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ቤታቸው እንዲመለሱ ለመፍቀድ እስራኤል የተወሰኑ ወታደሮቿን ከጋዛ ለማስወጣት የታቀደውን እቅድ በማዘግየት ምላሽ ሰጥታለች፡፡

በማዕከላዊ ጋዛ አል ራሺድ መንገድ ወደ ቤታቸው ለመመለስ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ተኩስ እንደተሰማም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

25 Jan, 17:59


ኢዜአ የኢትዮጵያን እውነት፣ ታሪክና ትርክት ለዓለም በሚገባ ለማሳወቅ በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል - አቶ አደም ፋራህ

AMN - ጥር 17/2017 ዓ.ም

ኢዜአ የኢትዮጵያን እውነት፣ ታሪክና ትርክት ለዓለም በሚገባ ለማሳወቅ በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊና የኢዜአ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ኢዜአን ጎብኝተዋል።

አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኢዜአ ተልእኮውን ለመወጣት እያከናወነ ያለው የሪፎርም ስራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ተቋሙ በአደረጃጀት እንዲሁም በሚዲያ ቴክኖሎጂ ልማት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት በአርአያነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አንስተዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...


https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02sN76Nq7Uk79DZegZ3E9wK8nMQaDji6NMh5tD4VyCFm7tu7j4RQStZu2S5XGDJQjal

Addis Media Network-AMN

24 Jan, 17:12


በመተባበር የተቀየረው የፀሐይ ሕይወት…

ሶስት ልጆቿን ይዛ ለልመና ጎዳና ላይ የወጣች አንዲት እናት ፎቶ የማኅበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የታየው ፎቶዋ የብዙዎችን ቀልብና ትኩረት ስቧል፡፡ ይህች ብርቱ እናት ፀሀይ ተሻለ ትባላለች፡፡

አራት ልጆቿን ብቻዋን ካለስራ የምታሳድገው ብርቱዋ እንስት የህይወት አስከፊና የደስታ ገጾች ተፈራርቀውባታል፡፡

ትዳር መስርታ ያፈራቻቸውን ልጆች ያለአባት ብቻዋን የምታሳድገው ወ/ሮ ፀሃይ ካለአባት ህመም ጋር ተዳምሮ ኑሮ ቢፈትናት ለልመና እጇን ዘርግታለች፡፡

ሙሉ መረጃውን እዚህ ያገኙታል
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0XEYKQrruJEMhY7HgBvZ5nc1ZxhJgcAnGd7SvagPFmDn4c71Gngyq26mfXEXJc1e4l

Addis Media Network-AMN

24 Jan, 14:58


ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀ ሆቴል 300 ሺህ ብር ተቀጣ

AMN - ጥር 16/2017 ዓ.ም

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተር ሌግዢሪ የተባለ ኢንተርናሽናል ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን እና ቦታውን እንዲያጸዳ መደረጉን የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶች እና ግንባታ ገንቢዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ደንብ በሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

Addis Media Network-AMN

24 Jan, 13:32


ሩሲያ የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነች-ክሬምሊን

AMN - ጥር 16/2017 ዓ.ም

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።

ፔስኮቭ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሩሲያ ለሚደረገው ውይይት የዋሽንግተንን ምላሽ እየጠበቀች ነው ብለዋል፡፡

የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን በተመለከተ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች የሆኑት ብሪታንያ እና ፈረንሳይን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት ለማድረግ ሩሲያ ፈቃደኛ መሆኗን ፔስኮቭ ማረጋገጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት በፍጥነት ለማስቆም እንዲሁም የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን በተመለከተ ከሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Addis Media Network-AMN

24 Jan, 11:53


ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡-ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

AMN - ጥር 16/2017 ዓ.ም

ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የንግድ እኛ ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሃገራት ዋና ኃላፊ አምባሳደር ሃሚድ አስጋር የሚመራ ልዑክ ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገር ሁለንተናዊ ግንኙነት እንዳላቸው የገለጹት ሚኒስትሩ ሁለቱ ሃገራት ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የጋራ ግንዛቤ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ሃሚዲ ኢትዮጵያ ላሳየችው የውጭ ንግድ ዕድገት አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ የኢትዮጵያ ምርቶች በፓኪስታን ገበያ በስፋት እንዲቀርቡ ለማመቻቸት ቃል መግባታቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው ግንቦት ወር ፓኪስታን በአዲስ አበባ ለምታዘጋጀው ኤክስፖም ድጋፍ እንደሚደረግም አስረድተዋል ፡፡

Addis Media Network-AMN

24 Jan, 11:52


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መርቀው ስራ አስጀመሩ

AMN - ጥር 16/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

Addis Media Network-AMN

20 Jan, 04:30


የእስራኤልና ሃማስ ስምምነት እስረኞችን በመለዋወጥ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ

AMN-ጥር 12/2017 ዓ.ም

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን በዚህም ሃማስ ሶስት ታጋቾችን ሲለቅ በምላሹ እስራኤል ዘጠና የፍልስጤም እስረኞችን መፍታቷን አስታውቃለች።

ፍልስጤማውያኑ እስረኞች ኦፈር ከተባለው እስር ቤት በመውጣት በቤይቱኒያ ከዘመዶቻቸው ጋር ሲገናኙ ደስታቸውን ገልጸዋል።

በሀማስ የተለቀቁት ታጋቾች የ31 ዓመቷ ዶሮን ስታይን ብሬቸር፣ የእንግሊዝና እስራኤል ዜግነት ያላት ኤሚሊ ዳማሪ እና ሮሚ ጎነን የተባሉ ሶስት ሴቶች በቴል አቪቭ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ስምምነት መሰረት በሃማስ ለታገቱ ለእያንዳንዱ ታጋች 30 የፍልስጤም እስረኞች ከእስራኤል እስር ቤቶች ይለቀቃሉ ተብሏል።

ስምምነቱን ተከትሎ የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው በመመለስ የምግብ እና የህክምና ዕርዳታ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

Addis Media Network-AMN

19 Jan, 13:45


ታቦታት ከማደሪያቸው በምዕመናን ታጅበው ወደ መንበረ ክብራቸው እየተመለሱ ነው

AMN - ጥር 11/2017 ዓ.ም

በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች ታቦታት ከማደሪያቸው በመዕመናን ታጅበው ወደ መንበረ ክብራቸው በመመለስ ላይ ናቸው፡፡

#Ethiopia
#Addisababa
#Ethiopia

Addis Media Network-AMN

19 Jan, 12:18


አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

AMN - ጥር 11/2017 ዓ.ም

እውቁ አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን ከራስ ቲያትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

19 Jan, 07:04


በጃንሜዳ የተካሄደው ስርአተ ጥምቀት ፡- በምስል

AMN ጥር 11/2017 ዓ.ም

ፎቶ በመባፅዮን ሀ/ገብርኤል

Addis Media Network-AMN

19 Jan, 06:39


የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በአል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊትቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል

AMN ጥር 11/2017 ዓ.ም

የዘንድሮው የጥምቀት በአል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል

በበአሉ ላይ በቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ መሰረት ብፁዕ አባ ካርዲናል ብርሃነ የሱስ ሱራፌል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የጥምቀት መርሀግብሩን በስርአተ ቅዳሴ አስጀምረዋል።

በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊካዊት ካቴድራል የሀይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮች ምዕምናንና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በቅዳሴ፣ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በአሸናፊ በላይ

Addis Media Network-AMN

19 Jan, 06:38


የውጭ ዜጎች በጃንሜዳ የጥምቀት በዓል ላይ ፡- በምስል

AMN ጥር 11/2017 ዓ.ም

ፎቶ በመባፅዮን ኃ/ገብርኤል

Addis Media Network-AMN

11 Jan, 14:56


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ተቀበሉ

AMN - ጥር 03/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት "የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ።" ብለዋል።

Addis Media Network-AMN

11 Jan, 11:25


በአዲስ አበባ ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ ነው

AMN - ጥር 3/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ 5 ሚሊዮን ዜጎችን የዲጅታል ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የኮደርስ ኢኒሼቲቭ እየተተገበረ ይገኛል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰጠው ስልጠናም የዳታ ሳይንስ፣ ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ ሞባይል አንድሮይድና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎችን ያካትታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ እንዳሉት የኮደርስ ስልጠና በአዲስ አበባ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

በተለይም የዲጂታል እውቀትና ክህሎታቸው ያደገ ሙያተኞችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በ2017 በጀት ዓመት እስክ ታህሳስ 30 ድረስ ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከልም እስከ 30 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በሚገባ በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል።


ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙያተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መሰጠት መጀመሩን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሁሉም ቢሮዎች የኮደርስ ኢኒሼቲቭን የሚከታተል ቡድን አቋቁመው እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው አስታውቀዋል።

Addis Media Network-AMN

11 Jan, 09:36


የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 በታሪክ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገለጸ

AMN - ጥር 3/2017 ዓ.ም

ዓለም ዓቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ትላንት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ከፍተኛ የሙቀት መጠን አስተናግዷል፡፡

በዓመቱ በአማካይ ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሼስ በላይ የሆነ የሙቀት መጠን የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከቅድመ ኢንዱስትሪ ዘመን የሙቀት መጠን አንጻር ትልቁ ነው ተብሏል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ እጅግ ፈታኝ እና ትኩረት የሚሻ ወቅት ላይ እንደሚገኝ ያሳሰበው ድርጅቱ ያለፉት ዓሥር ዓመታት የተስተዋለው ሙቀት ቀደም ሲል ከነበሩት ዓመታት ይልቅ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዓለም ዓቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ፀሀፊ ሴሌስቶ ሳውሎ፣ የሙቀት መጠን መጨመር ዓለም ለተዛባ የአየር ንብረት እንድትጋለጥ ማድረጉን፣ ጥፋት ማስከተሉን እና ለበረዶ መቅለጥና ለባህር ውሀ መጠን መጨመር ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ2024 የተመዘገበውን ከፍተኛ መጠን ያለው የሙቀት መጠን በ2025 ቅድሚያ በመስጠት ለመሥራት አሁንም ጊዜ አለ ያሉት ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ናቸው፡፡ ነገር ግን የመሪዎችን ተግባራዊ ምላሽ የሚሻ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የ2024ቱ የሙቀት መጠን የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ተጥሷል ለማለት አያስደፍርም ያሉት ጉቴሬዝ ስምምነቱ የአንድ አመት ብቻ ሳይሆን በዓሥር ዓመታት ውስጥ ያለውን የአየር ሁኔታ የሚገመግም ነው ብለዋል፡፡

እያንዳንዱ የሙቀት መጠን በዓለማችን ዙሪያ የሚያሳድረውን ሁለንተናዊ ቀውስ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅ መገለጹን የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

Addis Media Network-AMN

10 Jan, 20:25


በትናንትናው ዕለት ከሰማይ እያበሩ የወረዱት ቁሶች የሳተላይት ወይም የሮኬት ቁርጥራጮች ሊሆኑ ይችላሉ - መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

AMN - ጥር 2/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ክፍሎች የታዩት ቁስ አካላት ከእይታቸው አኳያ የሳተላይት ወይም የሮኬት ቁርጥራጮች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ደራሲ፣ የሃይማኖት ምሁር እና የሥነ ፈለክ ባለሙያ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ሕዋው ከምድር ወደ ጠፈር በሚላኩ እና የጠፈር ላይ ተመራማሪዎች በሚጥሏቸው ቁሶች በመቆሸሹ መሰል ክስተቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉም አስረድተዋል።

ባለፈው በታኅሣሥ 21 ቀን 2017 በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ በግምት 2.5 ሜትር ስፋት እና 500 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ብረታማ ነገር መከስከሱንም አስታውሰዋል።

ዶክተር ሮዳስ ለኤኤምኤን ዲጂታል እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በምድር ካሉ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ክስተቶችን ልታስተናግድ ትችላለች።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0aEPu1GtJ9bEmVM8b58sT9GHBvMPtZcrUeLv9ksyqtYk8HaXGLMwNzRP5h1DkrBgLl

Addis Media Network-AMN

10 Jan, 17:22


የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የቀብር ስነ-ስርዓት የፊታችን እሁድ ይፈፀማል

AMN - ጥር 2/2017 ዓ.ም

የአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የቀብር ስነ-ስርዓት በመጪው እሁድ ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ይፈፀማል፡፡

በዕለቱ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ የእርሳቸውን ክብር በሚመጥን መልኩ የአስክሬን ሽኝት እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

ከሽኝቱ በኋላ የቀብር ስነ-ስርአቱ ቤተሰቦቻቸው፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እሁድ ከቀኑ 7 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈፀም ታውቋል፡፡

Addis Media Network-AMN

10 Jan, 17:21


የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሻልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN - ጥር 2/2017 ዓ.ም

የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሻልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት ልዩ ልዩ የገበያ አይነቶችን የሚያቀርብ ነው፡፡

እነርሱም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስብራት ብሎም የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid07JoNHKvuPprRyTmzZ9JMj4ZnQGnBfw6UkXsPocL4RJUXi9M4vMnhRC6KNqL1dc4Nl

Addis Media Network-AMN

10 Jan, 17:20


በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በተቋማቱ የተሰሩ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራዎች ብልሹ አሰራሮችን የሚቀርፉ ናቸው፦ የክልል የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች

AMN - ጥር 2/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በተቋማቱ የተሰሩ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራዎች ብልሹ አሰራሮችን የሚቀርፉ ናቸው ሲሉ የክልል የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ከትራንስፖርት ና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለክልል የትራንስፖርት ዘርፍ ተቋማት ተሞክሮ ማጋራት የሚያስችል መድረክ አካሂዷል።

እስከ ጥር 4/2017 ዓ.ም በሚቆየው መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ በትራንስፖርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ገለፃና ውይይት ከተደረገ በኋላ በከሰዓቱ መርሃ ግብር በከተማዋ የተሰሩ ጊዜውን የዋጁ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫና በመሰራት ላይ የሚገኙ ተቋማትን የክልል ትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን የሰጡት የተለያዩ ክልል የትራንስፖርት ዘርፍ የስራ ሀላፊዎች በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በተቋማቱ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራዎች ብልሹ አሰራሮችን የሚቀርፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0UdAh1jHTTvKmg1dELtkFBFPi7JER81DwfziixMs4hviFPyq5UaP8ZucQzCCv2aBql

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 15:59


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለው አፈፃፀም ግምገማ ላይ ተወያየ

AMN - ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ ነበር ።

ይኽን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ስብሰባ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።

በስብሰባው የመስክ ምልከታና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን ማቅረባቸው ተመልክቷል።

የሱፐርቪዥን እና የግብረመልስ ሂደት ሰፋ ያለው ሥርዓትን የማጠናከር ተግባር አካል ሲሆን አፈፃፀሞችን በዞን እና ወረዳ ደረጃ በመመልከት ክፍተቶችን መለየትን አላማ ማድረጉን የፅህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 13:58


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነገ ይወያያል

AMN - ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም

6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ጉባዔው፤ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 12:27


የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ሲያከናውን የቆየውን ምልከታ አጠናቀቀ

AMN - ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም

በፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የተቋቋመው የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እና በክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤቶች ላይ ሲያከናውን የነበረውን ሱፐርቪዥን በዛሬው እለት አጠናቀቀ።

ቡድኑ በእቅድ ዝግጅት፣ በይዘት ቀረፃ፣የሚዲያ ግንኙነት ፣የህዝብ ግንኙነት፣በዲጅታል ሚዲያ አጠቃቀምና ሞኒተሪንግ ዘርፍ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ዘርፍን በአጠቃላይ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ምልከታ አከናውኗል።

የፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ በምልከታቸዉ እንደተናገሩት ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናው ላቅ ያለ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከተማዋን በሚመጥን መልኩ ለሌሎችም ተሞክሮ መሆን የሚችል ሰፊ ስራዎች በአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መመልከታቸውንና ይህም ለሌሎች ክልሎች ጭምር ተሞክሮ ሊሰጥ በሚችል ደረጃ የተደራጀ የተግባቦት ሂደት መሆኑን ገልፀዋል።

የሱፐርቪዥኑ ቡድኑ አባላት በከተማ ፣ በክፍለ ከተማ እንዲሁም በሴክተር ተቋማት የጋራ የተቀናጀና የተናበበ የተግባቦት ተግባር እጅጉን መደሰታቸውን ጠቁመው ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

ቡድኑ በአዲስ ከተማ ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ እና የልደታ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤቶች በመገኘት ሱፐርቪዥን ያካሄደ ሲሆን የጉለሌ ክፍለ ከተማ እስቱዲዮ ጉብኝትም ማካሄዱን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 10:50


በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት በዲጂታል አማራጮች የ5 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈፅሟል

AMN - ታኅሳስ 30/2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት በባንኩ የዲጂታል አማራጮች የ5 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ዝውውር መፈፀሙን አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት 79 በመቶ የባንኩ የገንዘብ ዝውውር ሥራዎች በዲጂታል አማራጮች እየተከናወኑ መሆኑንም ባንኩ ገልጿል።

የዲጂታል ባንኪንግ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በእጅ ስልክና በካርድ ተጠቅመው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው አማራጭ ነው።

የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዲቪዥን መርቻንትና ኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ብሌን ኃይለሚካኤል እንዳሉት ባንኩ 30 ሚሊየን የሲቢኢ ብር እና 9 ሚሊየን የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች አሉት።

እንዲሁም 21 ሚሊየን የካርድ ባንኪንግ እና 4 ሺህ በላይ የፖስ ማሽን ተጠቃሚዎች እንዳሉት ገልጸዋል።ተጨማሪ ያንብቡ... https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0TdPqCp7NqYaHGpN3QfJjwGNUrfAHXUSBoTiPXUsgT4yZ68nsSqMteUyg8ZWtm6ufl

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 10:48


በቻይና ቲቤት ግዛት በደረሰ ከባድ ርዕደ መሬት የ126 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

AMN - ታኅሳስ 30/2017

በቻይና በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ እና ቲቤት ግዛት የደረሰ ከባድ ርዕደ መሬት ባስከተለው ጉዳት የ126 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከ14 ሺህ በላይ የነብስ አድን ሠራተኞች ፍለጋ መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ የመንግስት ሚዲያ እንደዘገበው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ያወደመው አደጋ ከደረሰበት ከትናንትናው ዕለት አንስቶ እስከ አሁን ከ4 መቶ በላይ ሰዎችን ማትረፍ ተችሏል፡፡

የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዣንግ ጉኪንግ አደጋው በደረሰበት ሥፍራ በመገኘት እተሰራ ያለውን የነብስ አድን ሥራ ተመልክተዋል፡፡

በአካባቢው የርዕደ መሬት ክስተት የተለመደ ቢሆንም፣ ይህኛው ግን በቻይና በቅርብ ከተከሰቱ አደጋዎች አስከፊው መሆኑ ተነግሯል፡፡ተጨማሪ ያንብቡ.... https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0yV93mkajqGSjN1jYZBNGcdy8CafEVoqH7qCh2p3Qgo2N76PekdGLTvXg4zJWLUDMl

Addis Media Network-AMN

08 Jan, 10:46


በኢትዮጵያ የልብ ሕመም ምርመራ ኤሌክትሮካርዲዮግራም (ኢ.ሲ.ጂ) ውጤት ማንበብ የሚችል ሥርዓት ለማ

AMN - ታኅሳስ 30/2017

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የልብ ሕመም ምርመራ ኤሌክትሮካርዲዮግራም (ኢ.ሲ.ጂ) ውጤት ማንበብ የሚችል ሥርዓት ማልማቱን አስታወቋል፡፡

በኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና ሜዲካል ኤክስፐርት ታሪኩ ፍቃዱ (ዶ/ር) የልብ እንቅስቃሴን በወረቀት ላይ አስፍሮ የሚያሳይ መሳሪያ ሲሆን በየቦታው የልብ ስፔሻሊስት ባይኖርም በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ አማካይነት የሚያነብ ሞዴል ማልማቱን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንቲትዩት ማልማት የቻለው ሥርዓት በከተሞች እና በሆስፒታሎች ብቻ የሚገኙትን የልብ ስፔሻሊስቶች እውቀት በገጠር ጤና ጣቢያ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስታውቋል፡፡

የልብ እንቅስቃሴን በወረቀት ላይ አስፍሮ የሚያሳየው የኤሌክትሮካርዲዮግራም (ኢ.ሲ.ጂ) መሳሪያ ባለበት፣ የልብ ስፔሻሊስት ባይኖርም ያንን ማንበብ የሚችል አርተፊሻል ኢንተሌጀንስ ሞዴል መስራቱን ነው ያስታወቁት፡፡

ሥርዓቱ የኤሌክትሮካርዲዮግራም (ኢ.ሲ.ጂ) ውጤትን ከአሥር ሰከንዶች ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማንበብ እንደሚያስችልም አመላክተዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ... https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0eckAgpPCeC66UZT7cARbXVrA3czBeYdogYYPkopSQjEKeNcv4w9vAngarAP2Vbmxl

Addis Media Network-AMN

07 Jan, 15:26


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል

በዚሁ መሰረት ከታህሳስ 29/ 2017 ዓ.ም (ዛሬ) ከምሽቱ 12፤00 ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሰረት ከታህሳስ 29/ 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ፤00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው እንዲሸጥ በመንግስት ተወስኗል።

1-ቤንዚን -በሊትር 101ብር ከ 47 ሳንቲም
2-ናፍጣ -በሊትር 98 ብር ከ 98 ሳንቲም
3-ኬሮሲን - በሊትር 98ብር ከ 98 ሳንቲም
4-የአውሮፕላን ነዳጅ- በሊትር 109 ብር ከ 56 ሳንቲም
5-ከባድ ጥቁር ናፍጣ- በሊትር 105 ብር ከ 97 ሳንቲም
6-ቀላል ጥቁር ናፍጣ- በሊትር 108 ብር ከ 30 ሳንቲም ሆኖ እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 10:05


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀን 10 የጄቱር መኪናዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ጎበኙ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርበውን የጄቱር መኪናዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

በጂግጂጋ የሚገኘው በቀን 10 መኪናዎች መገጣጠም የሚችለው ፋብሪካ በ22 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 09:29


ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር በነገው ዕለት ይካሄዳል፡- ሥራና ክህሎት ቢሮ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና የስራ ፕሮጀክት ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የተሻገሩ ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር ሥነ ስርዓት በነገው ዕለት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ በሁለተኛው ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለታቀፉ ዜጎች ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የገንዝብ ድጋፍ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል።

በከተማዋ በድህነት በዝቅተኛ ገቢ ይተዳደሩ የነበሩ ወገኖች ላለፉት ሶስት ዓመታት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት ታቅፈው ሲሰሩ መቆየታቸው ተነስቷል።

በፕሮጀክቱ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖች ከ2014 እስከ 2016 ዓ.ም በነበራቸው ቆይታ በልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ወርሃዊ ክፍያ ሲያገኙ ቆይተዋል።

ተጠቃሚዎችም ከሚያገኙት ገንዘብ 20 በመቶውን በመቆጠብ ተቀማጭ የተደረገላቸው መሆኑን በማመላከት በፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በዘላቂነት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር በተደረገው ጥረት የሕይወት ክህሎትና ገንዘብ አጠቃቀም ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ገቢ ማስገኛ ስራዎች፣ የንግድ ክህሎት ስራ ዕቅድ አዘገጃጀትን ጨምሮ የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉም ነው ቢሮው በመግለጫው ያስታወቀው።

በነገው እለትም ''ከተረጂነት ወደ ምርታማነት'' በሚል መሪ ሃሳብ የሽግግር መርሃ ግብሩ የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 09:21


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአቋም መለኪያ ውድድር ተጠናቀቀ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የአቋም መለኪያ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

በአጭር ፣መካከለኛ ፣ 3000 መሰናክል ፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድርን ያቀፈው መርሃ ግብር ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተከናውኖ ተጠናቋል።

ዛሬ በመጨረሻው ዕለት ሰባት የፍፃሜ ውድድሮች ተደርገዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም ተገኝተው ለአሸናፊዎች ሽልማት አበርክቷል።


በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲከናወን በቆየው በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባስመዘገበው 319 ነጥብ የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

መቻል በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ ሸገር ከተማ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ፈፅሟል።

በውድድሩ 21 ክለቦች ፣ ሁለት ማሰልጠኛ ማዕከላት እና አንድ አካዳሚ ተሳትፈዋል። በአጠቃላይ በሁለቱም ፆታ 747 አትሌቶች የውድድሩ አካል ነበሩ።


በሸዋንግዛው ግርማ

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 09:00


ወቅታዊ መረጃ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው ይታወቃል።

ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ ይገኛሉ።

በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ።

መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሞያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል።

በተጨማሪም በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል (epicenter) የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል።

በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው።

በተጨማሪም ርዕደቱ በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ በመከታተል ላይ እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ እንዲተገብሩ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑን መንግሥት ያስታውቃል።


በኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታኅሣሥ 26 ቀን 2017

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 07:55


አበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ38ኛ ጊዜ በምግብ ዝግጅትna በቤት አያያዝ ያሰለጠናቸውን 147 ተማሪዎች አስመረቀ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

አበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ38ኛ ጊዜ በምግብ ዝግጅት እንዲሁም በቤት አያያዝ ያሰለጠናቸውን 147 ሴት ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተማሪዎቹ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ሲሆኑ ለ6ወር ስልጠናውን ተከታትለው ዛሬ ለምረቃ መብቃታቸው ታውቋል ፡፡

በምረቃው ላይ የድርጅቱ አመራሮች ፣ መምህራን ፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ተማሪዎቹ ተመርቀው ሲወጡ መንግስታዊ እና የግል ድርጅቶች ጋር የስራ እድል እንደሚመቻችላቸው እና የግል ስራ መስራት ለሚፈልጉም ድጋፍ እንደሚደረግላቸው በምረቃው ላይ ተገልፆአል።

የስልጠና ማእከሉ እስካሁን 3 ሺህ 715 ተማሪዎችን እንዳስመረቀ ለማወቅ ተችሏል ፡፡

በሄዋን ታዬ

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 07:21


ሞዴል የአርብቶ አደሮች መንደር መገንባቱ የአርብቶ አደሩን ኑሮ ከከተሜነት ጋር በማስታረቅ ረገድ የእሳቤ ለውጥን ያመጣል፡- አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የጅግጅጋውን ሞዴል የአርብቶ አደሮች መንደር አስመልክተው አስተያየት ሰጥተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በሰጡት አስተያየትም ሞዴል የአርብቶ አደሮች መንደር መገንባቱ የአርብቶ አደሩን ኑሮ ከከተሜነት ጋር በማስታረቅ ረገድ የእሳቤ ለውጥን ያመጣል ብለዋል።

የአርብቶ አደሩ ሕይወት እየተለወጠ እና የከተሜነት ተፅእኖው እየመጣ መሆኑን ያመለከቱት የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አርብቶ አደሩ ወደ ከተሞችና አካባቢው እየፈለሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር እያጋጠማቸው ያለውን የውኃ እና ግጦሽ እጥረት ለማቃለል የከተሜነት ፍላጎትን እና የአየር ንብረት ለውጡን ተፅእኖ ታሳቢ በማድረግ ችግሩን የሚፈታ ሞዴል የአርብቶ አደር መንደር ተገንብቷል ብለዋል።

መንደሩ አርብቶ አደሩን የውኃ፣ መብራት እና መንገድን የመሰሉ የመሠረተ ልማቶች ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው ሲሆን በመንደሩ ከአርብቶ አደሮቹ በተጨማሪ ለእንስሳቱም ቤት መገንባቱን አመልክተዋል።

በክልሉ እየተመዘገበ ካለው ፈጣን ዕድገት አርብቶ አደሩም ተጠቃሚ በመሆን የትምህርት፣ የመብራትና መሰል ልማቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የዘመናዊ መንደሮቹ መስፋፋት ጠቀሜታው የጎላ ነው።

ይህ ሞዴል ዘመናዊ መንደር የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን የገበያ ፍላጎት በማቀራረብ ትስስር ይፈጥራልም ብለዋል አቶ መስጠፌ።

በሽመልስ ታደሰ

Addis Media Network-AMN

04 Jan, 07:06


የጋራ እድገታችን ለዘላቂ ልማት እና ብልጽግና መሠረት የሆነውን ሰላምን በመጠበቅ ላይ የተመሠረተ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN - ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

“380 ሄክታር የሚሸፍነውና በሶማሌ ክልል የሚገኘው የገበታ ለሀገር ሥራ አንዱ አካል የሆነው የሸበሌ ፕሮጀክት ለወደፊት የመስፋፋት ከፍተኛ አቅም አለው።“ ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የትኛውንም የሀገራችን ጫፍ ስንጎበኝ ኁልቆ መሳፍርት ከሌላቸው እድሎች እና ተስፋዎች ጋር እንገናኛለን“ ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያ እያንሰራራች ነው። በፈተናዎች ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች በሚታዩ አስደናቂ እድገቶች ከፍ እያለች ትገኛለች። የጋራ እድገታችን ለዘላቂ ልማት እና ብልጽግና መሠረት የሆነውን ሰላምን በመጠበቅ ላይ የተመሠረተ ነው።

ለትውልድ ሁሉ የፈካ መፃዒ እድል ሰላማችንን እንጠብቅ።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስት ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 09:52


በሸገር ከተማ 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተሰራ ነው፡-ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)

AMN - ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም

በሸገር ከተማ በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የተቀናጀ የኮሪደር የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም በመስፋት ላይ ነው።

የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በመጀመሪያው ዙር 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት በሸገር ከተማ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን የሚያዘምኑ እና ለረጅም ዓመታት የሚያገለግሉ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።

የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮም እንዲሁም የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የህዝብ መዝናኛና ሌሎች ወሳኝ መሰረተ ልማቶች የሚገነቡበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በከተማዋ የሚያልፉ ዋና ዋና መንገዶች በመኖራቸው ከፌዴራል ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍለ ከተሞች ያላቸውን ጸጋ መሰረት በማድረግ የተለየ አደረጃጀት እንዲኖራቸው መደረጉን ነው ያብራሩት።

በዚህም መሰረት ኮዬ የፋይናንስ ማዕከል፣ ገላን የኢንዱስትሪ ማዕከል፣ እንዶዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል፣ ሰበታ የወጪና ገቢ ምርቶች ማቀነባበሪያ ዞን፣ ሱሉልታ እና መነአቢቹ የግሪን ቤልት ዞን ይሆናሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 09:38


አፈ ወርቆች - ልዩ የንግግር ክህሎት ውድድር!

ቅዳሜ ከሰዓት 9:00 እና እሑድ በድጋሚ 11:30 ይጠብቁን!

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 09:06


አትሌት በሪሁ አረጋዊ የ10 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰን ሰበረ

AMN - ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም

በስፔን ማድሪድ በሳን ሲልቬስተር በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ አዲስ ክበረወሰን በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡

አትሌቱ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ክብረ ወሰኑን ማሻሻል የቻለው።

በተያያዘ በጣልያን ቦላንዞ ከተማ በተካሄደ ዓመታዊው የቦክላሲክ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ጥላሁን ሃይሌ ቀዳሚ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል፡፡

አትሌት ጥላሁን ርቀቱን ለመሸፈን 27 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ የሆነ ጊዜ መውሰዱን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 07:23


በአዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

AMN - ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።

ብሔራዊ መታወቂያ ባንኩን ጠቅሶ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ፣ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የፋይዳ ቁጥር ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ የሚቀመጥ መሆኑን አስታውቋል።

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 05:19


የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን ለነገ ትውልድ የማበጀት ተግባር ነው፡- ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ

AMN - ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም

የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን ለነገ ትውልድ የማበጀት ተግባር መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ ተናገሩ።

በአንደኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን እና የቱሪዝም መዳረሻነቷን በሚመጥን ደረጃ የ2.2 ኪሎሜትር ስራ መከናወኑንም ገልፀዋል።

በዚህ የእግረኛ የተሽከርካሪ እና የብስክሌት መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋን ደረጃ ከፍ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ከተማ በተቀመረ ተሞክሮ አሁንም በሁለተኛው ዙር ስራው መቀጠሉን የገለፁት ከንቲባው የ5.6 ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራን በቀጣይ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ስራው የክልሉን ባህል እና ትውፊት የሚያንፀባርቁ ጉዳዮች ተካቶበት በ2.6 ቢሊየን ብር እየተከናወነ መሆኑም ተጠቅሷል።

የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር :የስራ ባህል መሻሻል :ዜጎች ከምን ጊዜውም በላይ የልማቱ ተሳታፊ መሆናቸውም የልማት ስራው ትሩፋቶች ውስጥ የሚካተት መሆኑን አቶ መኩሪያ ገልፀዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም የመንገድ መሰረተ ልማቱ ምቹ በመሆኑ በእግር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጤናቸውን እየጠበቁ መሆናቸውን እና አማራጭ የመዝናኛ ስፍራ እንደሆነላቸው ተናግረዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

Addis Media Network-AMN

01 Jan, 04:54


Happy New Year (2025 G.C)

Addis Media Network-AMN

31 Dec, 19:59


ዓመቱን ሙሉ በየቀኑ የአንድ ማራቶን ርቀት የሮጠችው ቤልጂየማዊት መነጋገርያ ሆናለች

AMN - ታኀሣሥ 22/2017 ዓ.ም

በፈረንጆቹ 2024 ዓመቱን ሙሉ በየቀኑ የአንድ ማራቶን ርቀት የሮጠችው ቤልጂየማዊት ስሟን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ጥያቄ አቅርባለች፡፡

ሂልደ ዶሶግኒ የተባለችው ቤልጂየማዊት በዓመቱ በየቀኑ ማራቶን በመሮጥ የመጀመሪያዋ ሴት ለመሆን የሚያስፈልገውን አድርግያለው ብላለች።

ዛሬ በሩጫዋ የመጨረሻ ቀን የፍጻሜውን መስመር ስታልፍ በሰጠችው አስተያየት፣“ ሩጫውን በማጠናቀቄ እድለኛ ነኝ” ስትል ተናግራለች፡፡

የ55 ዓመቷ ሂልደ ዶሶግኒ በአንድ ዓመት ውስጥ በትንሹ 15 ሺ 444 ኪሎ ሜትር (9 ሺ 596 ማይል) መሮጥ ችላለች፡፡

ከሩጫው ባለፈም ለጡት ካንሰር ምርምር የሚውል 60 ሺ ዩሮ ወይም 62 ሺ 438 የአሜሪካ ዶላር አሰባስባለች።

የጂ ፒ ኤስ ፣ ፎቶ እና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ጨምሮ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለመስፈር የሚያስችላትን ማስረጃዎች ማሟላቷንም ገልጻለች፡፡

ጥያቄዋ ተቀባይነት ካገኘ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እውቅና እንደሚሰጣት ተመላክቷል ።

በዚህም 366 ቀናት በተከታታይ በመሮጥ የወንዶችን ክብረ ወሰን የያዘውን ብራዚላዊ ሁጎ ፋሪያስን ትቀላቀላለች ተብሏል።

በሴት ምድብ አውስትራሊያዊቷ ኤርካና ማሬ ባርትሌት በተከታታይ 150 ቀናት በመሮጥ ያስመዘገብችውን ክብረወሰን እንደምትሰብርም ይጠበቃል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

31 Dec, 15:08


በፈረንጆቹ 2024 በኢትዮጵያ የተከሰቱ ዐበይት ጉዳዮች

AMN - ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም

ለመጠናቀቅ የአንድ ቀን ዕድሜ በቀረው የፈረንጆቹ 2024 የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች ሥራ መጀመር እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና ማግኘትን ጨምሮ በርካታ ዐበይት ሁነቶች ተከናውነዋል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄዋ በይፋ ተቀባይነት አግኝቶ ሙሉ አባልነቷን ያረጋገጠችውም በዚሁ የፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ ነበር።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ 132 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው እና ስምንት ኮሪደሮች የሚለሙበት ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ኮዬ አደባባይ፣ ጎሮ እና ሰሚት ባሉ የከተማዋ መግቢያ እና ማስፋፊያ ላይ በሚገኙ አካባቢዎች ያስጀመረውም በዚሁ ዓመት ነው።

ዝርዝሩን እዚህ ያገኙታል
👇
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0nqmczV2fXUkGEsnVsQEQesZgxtdipNNEk6cCsrKvMAvAKu7tXfSLhZbMdzUjJZfUl

Addis Media Network-AMN

26 Dec, 17:38


በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልጽግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎበኙ

AMN - ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ዛሬ በፓርቲችን ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ የሚዘልቀውን 21 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የግንፍሌ አካባቢ 19 ነጥብ 5 ኪሜ የሚሸፍን ወንዝ ዳርቻ ልማት ፣የካዛንቺስን መልሶ ማልማት ፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና 40 ነጥብ 4 ኪ ሜ የሚሸፍን ኮሪደር ልማት እንዲሁም የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር እና የአካበባቢ ልማት ፤ የፒያሳ ልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶች መኖሪያ መንደር ፤ የቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ተርሚናል እና የአቃቂ አዲሱ መንገድ የ37 ኪ.ሜ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ፤ “የብርሃን አዳሪ ት/ቤት" እና የ "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተናል ብለዋል።

Addis Media Network-AMN

26 Dec, 17:36


ባለስልጣኑ የህዝብና የመንግስትን መሬት የወረረን ግለሰብ ተጠያቂ ማድረጉን አስታወቀ

AMN - ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ቶልቻ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሬት ባንክ የገባን የህዝብና የመንግስትን መሬት በህገወጥ መንገድ ለግል ጥቅም ለማዋል የተወረረን መሬት ማስመለሱ አስታውቋል።

ግለሰቡ በሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ 477.61ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ በማጠር የወረረ መሆኑን በባለስልጣኑ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር አባላቱ በተደረገው ክትትል የተደረሰበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ባለስልጣኑ መረጃውን በማጣራት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል በሊዝ አዋጅ ተጠያቂ እንዲቀጣ ክስ እንዲመሰረት በማድረግ የታጠረውን ቦታ በማፍረስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረጉ ገልጿል።

ባለስልጣኑ በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽና ስግብግብ ግለሠቦችን ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

Addis Media Network-AMN

26 Dec, 17:35


የመኪና ዕቃዎችን ሰርቀው በመሸሸግ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN - ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ከተለያዩ አካባቢዎች የመኪና ዕቃዎችን ሰርቀው በመሸሸግ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ጎማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ 5 ግለሰቦች የንግድ ሱቆች ላይ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተሰረቀው የተሸሸጉ የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች እና 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ፖሊስ አመልክቷል።

በተደረገው ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር ከተለያዩ አካባቢዎች ከሌቦች እጅ ተገዝተው በ5ቱ ተጠርጣሪዎች የንግድ ሱቅ ውስጥ የተከማቹ ከ 2መቶ በላይ የተለያዩ ጎማዎችና 78 የመኪና ቸርኬዎች በቁጥጥር ስር ውለው በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል ።

በተለያዩ ጊዜያት መሰል የወንጀል ድርጊቶች ተፈፅሞባቸው ንብረታቸውን ያላገኙ ግለሰቦች መርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ንብረቶች መካከል መርጠው መውሰድ እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ህጋዊነት የጎደለውን አሰራር ህጋዊ በማስመሰል ወንጀል የሚፈፅሙ መሰል ግለሰቦችን በመከላከል ትክክለኛ ህጋዊ አሰራርን ለመፍጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ረገድ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን መረጃና ጥቆማ በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

Addis Media Network-AMN

26 Dec, 17:34


በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት እና አጠቃላይ የከተማ ልማት ስራ ከተማዋን ከማዘመንና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪውን ህይወት በተጨባጭ የሚያሻሽል ሰው ተኮር ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN - ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት እና አጠቃላይ የከተማ ልማት ስራ ከተማዋን ከማዘመንና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪውን ህይወት በተጨባጭ የሚያሻሽል ሰው ተኮር መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የከተማ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ የቆዩት የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የከተማ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ የልማት ስራዎች ትላልቅ ከተሞች ሲገነቡ እንዲሟሉ የሚጠበቁ መሰረተ ልማቶች መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

Addis Media Network-AMN

26 Dec, 17:32


ህዝቡ ለአንድነት፣ ለሰላምና ለፍቅር መትጋት ይኖርበታል- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

AMN-ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ህዝቡ አንድነትና ፍቅሩን በመጠበቅ ለአገር ዘላቂ ሰላም መትጋት እንዳለበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ።

በፓትርያርኩ የተመራ የቤተክርስቲያኗ አባቶች ቡድን ከነገ በስትያ ለሚከበረው ለቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ዛሬ ከሰዓት ድሬዳዋ ገብቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ተገኝተው ለፓትርያርኩ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የእምነት አባቶች ህዝበ ክርስቲያኑ ከፈጣሪው ጋር ያለውን ፍቅር እና ሕብረት ጠብቆ እንዲጓዝ በትጋት ያስተምራሉ፤ ይመክራሉ።

ህዝቡም ኃይማኖቱን፣ ምግባሩን እና ከአምላክ ጋር ያለውን ቅርበት በመጠበቅ ለሰላም፣ ለፍቅርና ለአንድነት መትጋት እንደሚገባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በጋራ ሰላም በመስራትና ለሚከሰቱ ችግሮች ፈጣን ምላሽ በመስጠት እያደረገ ላለው ትብብርም አመስግነዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ ከተማ አስተዳደሩ ለቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓል በድሬዳዋ በኩል ለሚመጡ እንግዶች አስፈላጊውን ድጋፍና መስተንግዶ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ፓትርያርኩ በድሬዳዋ ቅዱስ ዑራኤል ወበዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በ20 ሚሊዮን ብር ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነውን ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ ህንፃ ዛሬ ይመርቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል ።

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 18:27


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 19ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በስኬት እንዲከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጣቸው

AMN-ኅዳር 28/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 19ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በድምቀት እና በስኬት እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተለያዩ አካላት እውቅና ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክም 19ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በስኬት እንዲከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከምክር ቤቱ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የበዓሉን ሁነቶች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ነው እውቅና የተቸረው።

ኤ ኤም ኤን ከዚህ ቀደም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተከበረው 18ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ከምክር ቤቱ እውቅና ማግኘቱ ይታወሳል።

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 18:01


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርባምንጭ ጎዳናዎች

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 17:21


https://youtu.be/pfz1lVU7fVs?si=iK7pSDAt9HQ7NMhl

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 16:10


የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ
ሆና ተገኘች


AMN-ኅዳር 28/2017 ዓ.ም

የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ ሆና እንደተገኘች የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ዝርዝሩን እዚህ ያገኙታል

👇
https://www.facebook.com/share/p/18jgzQfX7s/

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 15:55


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

AMN-ኅዳር 28/2017 ዓ.ም

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መልዕክት አስተላልፏል።

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 15:16


https://youtu.be/m3SWxNTs9mI

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 12:13


"ሳምንቱ በታሪክ ውስጥ"

1.ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ የልብ ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና የተካሄደው እ.ኤ.አ ታህሳስ 3 ቀን በ1967 በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የልብ ንቅለ ተከላ የተደረገለት ግለሰብም በደቡብ አፍሪካ፣ በኬፕታውን ነዋሪ የሆነ ሉዊስ ዋሽካንስኪ የሚባል የ53 ዓመት እድሜ ያለው ሰው እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከባድ የልብ ህመም  እንደነበረበት የሚነገርለት  ዋሽካንስኪ፣ የልብ ንቅለ ተከላውን የተቀበለው የ25 ዓመት እድሜ ካላት እና በከባድ የመኪና አደጋ ጉዳት ከደረሰባት በዴኒስ ዳርቫል ከተባለች ሴት እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የቀዶ ህክምናውን ያደረገው ዶክተር  ደግሞ በኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ እና በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሰለጠነው የቀዶ ጥገና ሀኪም የሆነው ክርስቲያን ባርናርድ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ዝርዝሩን እዚህ ያገኛሉ
👇
https://www.facebook.com/share/p/14rLyP2rVn/

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 10:24


የቅጥር ማስታወቂያ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት እና በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል።

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 10:19


ከ575 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

AMN - ህዳር 28/2017 ዓ.ም

የጉምሩክ ኮሚሽን ከህዳር 20 እስከ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 528.3 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 47 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 575.3 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማእድናት፣ ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 241 ሚሊዮን፣ 94 ሚሊዮን እና 86 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በደፈጣ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 17 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና አምስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

07 Dec, 10:18


የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አርባምንጭ ከተማ ገቡ

AMN - ህዳር 28/2017 ዓ.ም

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ወደ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቀው የጋሞ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለመታደም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ አርባምንጭ ከተማ እየገቡ ይገኛል፡፡

በሁሉም የእንግዶች መግቢያ አቅጣጫ ደማቅና ባህላዊ አቀባበል እያደረገ የሚገኘው የጋሞ ህዝብ ዛሬም የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ሲገቡ በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 17:10


የቦሌ ክፍለ ከተማ የይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

AMN - ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት የይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ የሆነው አሸብር አበባው ታደሰ የተባለ ግለሰብ ሆን ብሎ መረጃ በማጉደል፣ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል እና ጉቦ በመቀበል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የወ/ሮ ሙሉ ካህሺን ሕጋዊ ወኪል የሆኑት አቶ ደራራ ዲንሳ ኢረና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚገኝ የቦታ ይዞታቸው በመሬት ይዞታ ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲረጋገጥላቸው ለአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት አመልክተዋል፡፡

በዚህም ተጠርጣሪው የማይገባ ጥቅም በመፈለግ ከአመልካች ማኅደር ላይ መረጃ በማጉደል እና ጉዳያቸውን በማጓተት ሲያጉላላቸው ከቆየ በኋላ መረጃውን አሟልቶ ወደሚመለከተው አካል ለመላክ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር ጉቦ መጠየቁን የምርመራ ቡድን ደርሶበታል፡፡

ባለጉዳዩ አቶ ደራራ ዲንሳ የተጠየቁትን ገንዘብ በአዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01320082310801 ወደ ተጠርጣሪው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000218526121 ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ያስገቡ መሆናቸውን ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለምርመራ ቡድኑ ጥቆማ አቅርበው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል፡፡

የምርመራ ቡድኑ የተጠርጣሪውን የእምነት ክህደት ቃል በመቀበል፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ10 ቀን የምርመራ ማጣሪያ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መፍቀዱ ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 14:52


ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላቱ የከተማዋ ነዎሪዎችን ይቅርታ በመጠየቅ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ ለመካስ ቃል ገቡ

AMN - ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዎሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁ ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በጥራት እና በፍጥነት ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የተገኙ ልምዶችን ቀምረን የጀመርነው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች አገልግሎት ክፍት ማድረግ በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት፣ ከኮንትራክተሮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተናልም ብለዋል።

በውይይታችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከመጀመሪያ ዙር አንጻር ሰፊ እና የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትብብር፣ በተያዘለት ጊዜ፣ በጥራት እና ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲያጠናቅቁ ተግባብተናል።

በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዎሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁም ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 14:25


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና የፌደራል ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የታክስ ስወራን መከላከል የሚያስችል ስምምነት ፈፀሙ

AMN - ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷ እንዲጨምር ለማስቻል በሚደረገው የገቢ አሰባሰብ ጥረት እንቅፋት እየሆነ ያለውን የታክስ ስወራ መከላከል የሚያስችል ስምምነት በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በፌደራል ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መከላከል ተፈፀመ ፡፡

ከተማዋ በምታካሂደው የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ላይ የታክስ ስወራና ለረዥም ዓመታት በተገቢው ሁኔታ ግብራቸው ባልከፈሉ ግለሠቦችና ድርጅቶች የሚስተዋለው የእዳ ክምችት ችግር ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ከነዚህም ችግሮች መካከል የታክስ ስወራ ተጠቃሽ ሲሆን ይህንን ለመከላከልና ተገቢ የመረጃ ስርዓት እንዲኖር ነዉ ስምምነቱ የተደረገው::

ሰምምነቱን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እንዲሁም የፌደራል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ፍትሃዊ የሆነ የንግድ ስርዓትና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት እንዲሰፍን በማድረግ ከተማዋ የገቢ እቅዷን እንድታሳካና የነዋሪው የልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ያስችላል ተብሏል፡ ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት 230 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱ ይታወሳል::

በአንዋር አሕመድ

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 12:50


https://youtu.be/vpACFh6PgrM?si=rnYobuvR27Z3chNm&sfnsn=scwspmo

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 12:40


የሰላም መንገድ የመረጡ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ወደተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ ነው

AMN - ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ አባላቱ ወደተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የሆኑት አቶ ሰኚ ነጋሳ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 10:37


አዲስ አበባ ከተማ እያሳየች ያለችውን ዕድገትና ለውጥ እንደ ተሞክሮና ልምድ በመውሰድ የሸገር ከተማ አስተዳደር በትኩረት ይሰራል፦ አቶ ጉግሳ ደጀኔ

AMN-ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ እያሳየች ያለችውን ዕድገትና ለውጥ እንደ ተሞክሮና ልምድ በመውሰድ የሸገር ከተማ አስተዳደር በትኩረት እንደሚሰራ የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የአስተዳደር አገልግሎት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጉግሳ ደጀኔ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የአስተዳደር አገልግሎት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጉግሳ ደጀኔ አዲስ አበባ ከተማ እያሳየች ያለችውን ዕድገትና ለውጥ እንደ ተሞክሮ እና ልምድ በመውሰድ የሸገር ከተማ አስተዳደር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ዕድገት የሸገር ከተማ እድገት ነው ያሉት አቶ ጉግሳ ለዚህ ደግሞ ሁለቱ ከተሞች በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዘርፎች በቅንጅት በመስራት የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ አደጋ ሀገር አቀፋዊ እና ዓለም አቀፋዊ ነው ሲሉ ገልጸው ለዚህ ደግሞ የአደጋ መንሴዎችን በመለየት መቀነስ ይቻላል ብለዋል።

የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነር ፍቅሬ ለዚህ ደግሞ ቅንጅታዊ ስራ ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 10:16


ኢትዮ ቴሌኮም ከጁቡቲና ከሱዳን የቴሌኮም ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

AMN-ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም ከጁቡቲ ቴሌኮምና ከሱዳቴል ቴሌኮሙኒኬሽን ግሩፕ ጋር ለአፍሪካ ድንበር ዘለል የቴሌኮም ትስስር ወሳኝ ሚና ያለውን የሆራይዘን ፋይበር ኮኔክቲቪቲ ኢኒሼቲቭን በጋራ ለመተግበር የመግባባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ኢኒሼቲቩ አፍሪካውያንን በቴሌኮም ለማስተሳሰርና የአፍሪካ ቀንድን ከእስያ፣ ከአውሮፓ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፥ ኢኒሼቲቩ በመሬት ላይ በሚዘረጋ ኬብል ድንበር ዘለል የቴሌኮም ትስስር ማሳለጥን ታሳቢ ያደረገ ነው።

ስምምነቱን ለመተግበር ሶስቱ ኦፕሬተሮች ያላቸውን መሰረተ ልማት አቀናጅተው እንደሚጠቀሙ አብራርተዋል።

ስምምነቱ በ2030 ዲጂታል አፍሪካን እውን ለማድረግና አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከር የተያዘውን ግብ ለማሳካት አወንታዊ አስተዋጽኦ አለው ነው ያሉት።

ኢኒሼቲቩ ለመረጃ ማስተላለፊያ የሚረዱ ውጤታማ መስመሮችን ማቅረብ፣ ቀልጠፋ ጥገና በማድረግ የኔትወርክ መቆራረጥን መቀነስን ግብ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

03 Dec, 10:15


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ከ105 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል

AMN-ኅዳር 24/2017 ዓ.ም

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ ባለፋት አምስት ወራት በህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ከ105 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለፁ።

ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መተግበር ከጀመረ ወዲህ በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ ይታይ የነበረው የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

ማሻሻያውን ተከትሎ በንግድ ስርዓቱ ላይ ህገወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን በመጥቀስ።

በዚህም በምርቶች ላይ ያልተገባ ዋጋ በመጨመር የዋጋ አለመረጋጋትን ለመፍጠር የሞከሩና ህብረተሰቡን ለምሬት የዳረጉ ከ105 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል ከ1 ሺህ የሚልቁት በእስራት የተቀጡ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ድርጅታቸውን እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ህገወጥ ደላሎች በመሰረታዊ ሸቀጦችና በቁም እንስሳት ግብይት ላይ እያሳደሩ ያለውን ጫና ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የእሁድና ቅዳሜ ገበያዎችን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስፋፋት የገበያ መሰረተ ልማት ማሟላት ላይ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

Addis Media Network-AMN

01 Dec, 07:47


19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል በአምቦ ከተማ እየተከበረ ነው

AMN - ህዳር 22/2017 ዓ.ም

19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአምቦ ከተማ እየተከበረ ነው።

19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአምቦ ከተማ በሚገኘው የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ካምፓስ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የዘንድሮው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል "አገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሐሳብ በክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተሞች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ እየተከበረ ባለው በዓል ላይም በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በባህል አልባሳት ደምቀው እና በፈረሰኞች ታጅበው በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማው እየተመሙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ከተማ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበርም ይታወቃል።

Addis Media Network-AMN

01 Dec, 07:35


የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጂቡቲ የሚኖሩ አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት ተከበረ

AMN - ህዳር 22/2017 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በጂቡቲ የሚኖሩ አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት ተከብሯል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እና የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ምክትል ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተገኝተዋል፡፡

በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በዚህ ጊዜ እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ ቀደም ሲል በሀገሪቱ በነበሩት ቁልፍ ችግሮች ምክንያት የተነሳውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የተመሰረተ ፓርቲ ነው፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ምክትል ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በበኩላቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በብዙ ተግዳሮቶች መካከል በጽናት በመስራት ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበ ፓርቲ እንደሆነም ገልጸዋል።

በመድረኩም “የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ እድገት” በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ ለታዳሚው የቀረበ ሲሆን፣ ፓርቲው ያጋጠሙት ተግዳሮቶች፣ ያስመዘገባቸው ድሎች፣ አሁን ያሉ ተስፋዎች እና የወደፊት ራዕዮች ላይ በዝርዝር ውይይት ተደርጓል።
ተጨማሪ ያንብቡ https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02jtWZt57rpwUbuFZah8ZYRYe8REDpE9xEpwXHypCcpc7QUMCxXewXZyTb7x6tUXZal

Addis Media Network-AMN

01 Dec, 07:31


የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የአዘርባጃኑ አላት ነፃ የንግድ ቀጣና በትብብር ለመስራት ተስማሙ

AMN - ህዳር 22/2017 ዓ.ም

ስምምነቱ የተደረሰው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመራ የልዑካን ቡድን በአዘርባጃን የአላት ነፃ የኢኮኖሚ ዞንን በጎበኙበት ወቅት ነው ::

ጉብኝቱ በቅርቡ ወደ ሙሉ ትግበራ ለገባዉ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አሰራሮች ፤ ልምድና ተሞክሮዎች የተቀሰሙበት ነበር::

የመስክ ምልከታዉ በአላት እና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና መካከል ተቋማዊ ግንኙነት በመፍጠር በቀጣይ በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል መደላድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል ::

ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተወጣጣዉ ልዑካን ቡድኑ ከአላት ነፃ ኢኮኖሚ ዞን በተጨማሪ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ተቋማት ከጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይትና የመስክ ምልከታ አድርገዋል::

የአላት ነፃ ኢኮኖሚ ዞን በአዘርባጃን ርዕሰ መዲና ባኩ በ719 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርክነት ወደ ነፃ የንግድ ቀጣና በማደግ የመጀመሪያ መሆኑ ይታወቃል።

Addis Media Network-AMN

30 Nov, 16:47


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል

AMN ህዳር 21/2017 ዓ .ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል
በዚህም መሰረት:-

1. አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
3. ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ⁠ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ
5. ⁠⁠አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ
6. አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
7. አቶ ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ⁠ ሆነዋል

Addis Media Network-AMN

30 Nov, 09:23


በፈረንሳይ ድጋፍ የሚከናወነው የዘላቂ ቅርስ ልማት ይፋ ሆነ

AMN-ኅዳር 21/2017 ዓ.ም

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የአውሮፓ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮት በፈረንሳይ ድጋፍ የሚከናወነውን የዘላቂ ቅርስ ልማት ይፋ አድርገዋል ።

በላሊበላ አካባቢ፣ በተንቤን እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚከናወኑ የዘላቂ ቅርስ ልማት ይፋ የተደረጉ ሲሆን፤ የማሻሻያ ሥራ እየተከናወነለት ያለው የፓሊዮኦንቶሎጂ እና የቅድመ ታሪክ የአርኪዮሎጂ ክፍል እንዳሁም በቅርቡ የአርት ጋለሪው ጥገና እንደሚጀምር መጠየቁም ተመልክቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮ እና የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ የታሪክ ዘመን አርኪዮሎጂ ክፍልን የጎበኙ ሲሆን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1960ዎቹ ከመልካ ቁንጥሬ የዓለም መካነ ቅርስ ለምርምር ወደ ፈረንሳይ ሀገር ተወስደው የነበሩ ጥንታዊ የሰው ዘር የተገለገለባቸው የድንጋይ መሣሪያዎችን ሚኒስትሩ ለቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ማስረከባቸውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

Addis Media Network-AMN

30 Nov, 09:22


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ የሚያደርገውን በረራ ዳግም አስጀመረ

AMN-ኅዳር 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ በረራ ዳግም ዛሬ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣በኢትዮጵያ የላይቤሪያ አምባሳደርና ሌሎች የአየር መንገዱ የስራ ሃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል።

አየር መንገዱ በ2020 ላይ አቋርጦት የነበረውን በረራ ነው እንደገና ዛሬ ያስጀመረው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ወደ ላይቤሪያ በረራ መጀመሩ የምጣኔ ሀብት፣ የቱሪዝምና ንግድ፣ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የA350 -1000 አውሮፕላን ከኤር ባስ ኩባንያ መረከቡ ይታወሳል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ባሉት 147 አውሮፕላኖች 140 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን የሚሸፍን ሲሆን እ.አ.አ በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር በማሳደግ በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ ሰንቆ እየሰራም እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል ።

Addis Media Network-AMN

30 Nov, 09:21


በመዲናዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት የተከናወኑ ተግባራት እና በአምራች፣ በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈጻጸም የተሻለ ነው፦አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN-ኅዳር -21/201 7ዓ.ም

በመዲናዋ አዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በገበያ ማእከላት፣በእሁድና በቅዳሜ ገበያ፣በመጋዘን ክምችት፣ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ያለዉ የግብይት ስርዓት እንዲሁም በአምራች በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈፃፀሙ የተሻለ መሆኑን ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ህገ ወጥነትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የተቋቋመዉ የገበያ ማረጋጋት እና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሀይል ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ሴክተር ተቋማትና አመራሮች ጋር እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ ።

ግብረ ኃይሉም በመሠረታዊነት በምርት አቅርቦትና ስርጭት ፣ የገቢ ምንጭ ማስፋትና ገቢ መሰብሰብ፣ የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የህግ ማስከበር ስርዓት እንዲሁም የመረጃ ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል ።

በግምገማዊ ዉይይቱም ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከቀረበዉ ሪፖርትና ከቀረበዉ አስተያየት በመነሳት እንደተናገሩት ግብረሁይሉ የተደራጀዉ ችግሮችን እንዲፈተና አቅጣጫ እያስቀመጠ እንዲመራ መሆኑን ጠቁመዉ በዚህ ረገድ ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች ማስመዝገብ ቢቻልም ስራዉ የአመራሩን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ይበልጥ በየደረጃዉ ስራዉ እየተገመገመ ፖለቲካዊ ዉሳኔ አየተሠጠ መመራት አለበት ብለዋል ።

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 14:10


ህብረተሰቡ ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው ከሚያጭበረብሩ ወንጀለኞች ራሱን እንዲጠበቅ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

AMN ህዳር 18/2017 ዓ .ም

ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ሚስጥር ቁጥር በመቀበል በማጭበርበር ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ህብረተሰቡ እንዲጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ የባንክ ስሞችን በመጠቀም ለግለሰቦች በመደወል የባንክ አካውንቱን በመናገር ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የባንካችን ተሸላሚ ደንበኛ በመሆንዎ በማለት እና የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም የሞባይል ባንኪግ ኮድ እንዲያስገቡ በማግባባት በአካውንት የተቀመጠ ገንዘብን ወደራሳቸው የሚወስዱ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ደርሶበታል።

ሕብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የመጭበርበር ወንጀል እራሱን በመጠበቅ ከዚህ በታች በስምና በፎቶ ግራፍ የተገለጹትን ጠርጣሪዎች ሲመለከት ተቋሙ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባሰራጨው መረጃ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 11:27


የፕሮግራም ጥቆማ

ነገ ሐሙስ ምሽት 2:00 በቀጥታ በሚተላለፈው ‘አገልጋይ’ ፕሮግራማችን ከአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቆይታ እናደርጋለን፤ ይጠብቁን!

በክፍለ ከተማው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለዎትን ጥያቄ እና አስተያየት በስልክ ቁጥሮቻችን 011-1-71 00 16 እና 011-1-56 43 53 በመደወል ያቅርቡ፣ ምላሽ እና ማብራሪያ ያገኛሉ።

በተጨማሪም ጥያቄ እና አስተያየትዎን በቪዲዮ ወይም በድምፅ ቀርፀው በፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amnaddistv በውስጥ መልዕክት ይላኩልን (ኢንቦክስ ያድርጉል)፤ ለዋና ሥራ አስፈፃሚው እናደርሳለን!

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ - የትውልድ ድምፅ!

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 10:52


በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚተላለፉ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ዘገባዎች የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱ ናቸው፡- መምህር መኩሪያ መካሻ

AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም

የትውልድ ድምጽ በሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚተላለፉ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ዘገባዎች የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን መምህሩ መኩሪያ መካሻ ገለጹ ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል ፡፡

በሚዲያው የሚተላለፉ እንደ አገልጋዩ እና ዋርካ መሰል ፕሮግራሞች በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ነቅሰው በማውጣት ችግሮቹ እንዲፈቱ እያደረጉ ይገኛሉ ያሉት አቶ መኩሪያ መካሻ ይህም ጅምር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡

ሚዲያው በቀጣይ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማስፋት በተሟላ የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ አቅም እየሰራ እንደሆነ የሚናገሩት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ሀላፊ ሰለሞን ዲባባ ተቋሙ በጀመራቸው አዳዲስ ፎርማቶች የከተማዋን ነዋሪዎች ከአገልግሎት አሰጣጥ እና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ በዘለለ የመዝናኛ አማራጭ በመሆንም እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 07:49


የኢትዮጵያ መከላከያ ሶስት ወርቅ በማግኘት የሜዳሊያ ብዛቱን ወደ አምስት አሳድጓል

AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም

በናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘው የጦር ሃይሎች ስፖርት ፌስቲቫል የኢትዮጵያ መከላከያ ሶስት ወርቅ በማግኘት ብዛቱን ወደ አምስት አሳድጓል።

በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመላው አፍሪካ የጦር ሀይሎች ስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮጵያን የወከለው የመቻል ስፖርት ክለብ አትሌቲክስ ቡድን አባላት በአንድ ቀን ሶስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት የወርቅ ሜዳሊያ ብዛቱን ወደ አምስት ከፍ ያደረጉበትን ድል አስመዝግበዋል።

ሀምሳ አለቃ ትግስት ግርማ በ1500 ሜትር አንደኛ በመውጣት ወርቅ ስታገኝ ፤በወንዶች አሎሎ ውርወራ ምክትል አስር አለቃ ነነዌ ጌንዳቦ ወርቅ አስገኝቷል፤ በሱሉዝ ዝላይ ሴት ምክትል አስር አለቃ በፀሎት አለማየሁ ሌላኛውን ወርቅ ለሀገሯ አስገኝታለች።

በወንዶች 1500 ሜትር ሀምሳ አለቃ ደጀኔ ተሾመ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ሲያገኝ በሴቶች አሎሎ ውርወራ ምክትል አስር አለቃ ዙርጋ ኡስማን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

እስካሁን ባለው ውድድር አጠቃላይ የመቻል ስፖርት ክለብ አምስት የወርቅ ስባት የብር ሁለት የነሀስ አጠቃላይ አስራ አራት ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።

ዛሬ በጉጉት የሚጠበቀው የ3000 ሜትር መሠናክል በሴትም በወንድም ይካሄዳል ሱሉዝ ዝላይ ወንድ 200 ሜትር ሴት ፍፃሜ ይከናወናል።

የመከላከያ ሠራዊት የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን እና የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ አመራር አባል አቶ ታዬ ሙሉጌታ ውድድሩን ለመታደም አቡጃ መግባታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 07:36


የዓለም የቀድሞ ሻምፒዮኑ አትሌት ኢብራሂም ጀይላን የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኅበርን ለመምራት በእጩነት ቀረበ

ሙሉ መረጃውን ከስፖርት ገጻችን ለማግኘት ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) ይጫኑ

https://web.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02U3Hbe3KKYYYCB6yrUFovxrPSRRt5aBPqbq5VekWzLDMaMBbfrsYdxdcFdt7UD6REl&id=61557351622843

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 07:34


የፈረንሳዩ ምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም

የፈረንሳዩ ምግብ ማቀነባበሪያ ዴላሞት ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድረው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጿል፡፡

ኩባንያው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ለመስራት ላሰበው ጣፋጭና ደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዋናነት ከሚያስፈልጉ ግብአቶችን ውስጥ ስንዴ፣ የቅባት እህሎች እና የእንስሳት ተዋጽኦ መሆናቸውን የኩባኒያው መስራች ሴባስቲያን ዴላሞት አብራርተዋል፡፡

የኢዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኩባንያው ባለቤቶች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ኢትዮጵያ የስንዴ ምርቷን ለማሳደግ ከፍተኛ ስራ እየሰራች ባለበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው ሀገሪቱ በበጋ እና በመኸር ስንዴ ምርት ፍላጎቷን ከሟሟላት አልፋ ለውጪ ሀገር ገበያ ልታቀርብ ስራ በጀመረች ወቀት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዩክሬንና የራሽያ ግጭትን ተከትሎ በዓለም ላይ የተፈጠረው የስንዴ ምርት አቅርቦት መስተጓጎል ተጽእኖ እንዳያሳርፍባት መንግስት ቀድሞ በወሰደው ፈጣን እርምጃ ሀገሪቱ ከውጪ ስንዴ ለማስገባት ታወጣ የነበረውን ከ750 ሚሊየን ዶላር በላይ በሀገር ውስጥ መተካት መቻሏን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ስንዴ ምርት አቅርቦትን በበላይነት መምራት እንደቻለች ጠቁመዋል፡፡
ኩባኒያው የሚያስፈልገውን ምርት በኮንትራት ፋርሚንግ ቀጥታ ከአርሶ አደሮች ሊወስድ እንደሚችል ያብራሩት ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ናቸው፡፡

Addis Media Network-AMN

27 Nov, 07:30


ሮቦቷ ውሻ የማራቶን ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሮቦት ለመሆን በቃች

AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም

ሮቦቷ በደቡብ ኮሪያ ሳንጁ በተካሄደው 22ኛው የማራቶን ውድድር ላይ 4 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈችው፡፡

በደቡብ ኮሪያ የተሠራችውና ሌቦ-2 የሚል ስያሜ የተሰጣት ሮቦቷ አንድ ጊዜ ብቻ በተደረገ ቻርጅ ከ 42 ኪሎ ሜትር በላይ ሮጣ በማሸነፍ የዓለማችን የመጀመሪያዋ ሮቦት ሆናለች፡፡
ሮቦቷ ውሻ በደቡብ ኮሪያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ውስጥ በፕሮፌሰር ዋንቦን ጄሚን በሚመራው ቡድን መሠራቷ ተገልጿል፡፡

አምና በተካሄደው ውድድር ላይ ከተወዳዳሪዎቿ አንጻር በእጅጉ ለመፍጠን ባደረገችው ጥረት ከ37ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ኀይል ወይም ባትሪ በማለቁ ምክንያት ድል አልቀናትም ነበር፡፡

ፈጣሪዎቿ ከአምናው ድክመት ትምህርት በመውሰድ ዘንድሮ በብዙ መልኩ በማሻሻል እና ሌቦ-2 የሚል ስያሜ በመስጥት ስኬታማ መሆን ችለዋል፡፡

ሮቦቷ ውሻ በፊት በኩል ሁለት ካሜራዎች የተገጠመላት መሆኑና ጅራቷ የመሬት አቀማመጥን እንዲያጤን ተደርጎ በመሠራቱ ምክንያት በ42 ኪሎ ሜትሮች ውስጥ የሚያጋጥሟትን አባጣ ጎርባጣዎችን በጥንካሬ ማለፍ አስችሏታል፡፡

እንደ ፈጣዎቿ ገለጻ የተደረገላት ማሻሻያ ቀጥ ያለ መንገድ ላይ እስከ 67 ኪሎ ሜትር መሮጥ የሚያስችላት ነው፡፡

በአንድ ጊዜ የባትሪ ሙሌት(ቻርጅ) እስከ 8 ሰዓት ድረስ መዝለቅ ትችላለችም ማለታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡

በማሬ ቃጦ

Addis Media Network-AMN

13 Nov, 10:05


አፈ ወርቆች - ልዩ የንግግር ክህሎት ውድድር!

ከኅዳር 15 ጀምሮ ዘወትር እሑድ ምሽት 2:30 ይጠብቁን!

Addis Media Network-AMN

13 Nov, 09:30


ዶናልድ ትራምፕ ቱጃሩን ኢሎን መስክ ለሹመት አጩ

AMN - ኅዳር 4/2017 ዓ.ም

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሊየነሩን ኢሎን መስክ እና ቪቬክ ራማስዋሚ የፌዴራል ተቋማትን ወጪ እንዲቆጣጠር ለሚያቋቁሙት አዲሱ “የመንግሥት አፈጻጸም ዲፓርትመንት” እንዲመሩ ለሹመት አጭተዋል።

እነዚህ ሁለቱ አስደናቂ አሜሪካዊያን በአስተዳደራቸው የመንግሥትን ቢሮክራሲ ለመስበር፣ ለቁጥር የበዙ ሕግ እና መመሪያዎችን ለማጠፍ፣ የወጪ ብክነትን ለማስቀረት ሁነኛ ሰዎች መሆናቸውን የገለጹት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራል ተቋማትን አወቃቀር በአዲስ መልክ በማዋቀር የአሜሪካን የወደፊት ግስጋሴ የሚያስቀጥሉ ናቸው ብለዋል።

"ኢሎንና ቪቬክ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ እና የሁሉንም አሜሪካዊያንን ህይወት በሚያሻሽል መልኩ የፌዴራል ቢሮክራሲን እንደሚቀይሩት እምነቴ ነው" ሲሉ ነው የገለጹት።

ይህ አዲሱ ተቋም በፌዴራል መንግሥት ወይም ከፌዴራል መንግሥት ውጪ እንደሚቋቋም የተገለጸ ነገር የሌለ ሲሆን፣ በሌላ በኩል አንድ ኦፊሴላዊ ተቋም ከጎንግረሱ እውቅና ውጪ ሊቋቋም እንደማይችል የሀገሪቱ ሕግ ይደነግጋል።

ትራምፕ ለፖለቲካው አዲስ የሆኑ የቢዝነሱን ዓለም ሰዎች ወደ ሥልጣን በማምጣት ለፖለቲካው ባህል አዲስ ነገር ይዘው መምጣታቸው እየተነገረላቸው ነው።

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02CeNpZZT4EwRZuMuHCiRmocqP4Zvo61R3kvY8VXUYgaeVxfndEV1vDpRVJ5cfBq12l

Addis Media Network-AMN

12 Nov, 16:53


በሳንባ ምች በሽታ የሚከሰት የታዳጊ ህፃናትን ሞት 67 በመቶ መቀነስ ተችሏል
AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም
የሳንባ ምች በሽታን የመከላከሉ ተግባራት በበሽታው የሚሞቱ ህፃናትን ቁጥር በ67 በመቶ መቀነስ መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሳንባ ምች ቀን ምክንያት በማድረግ ውይይት ተደርጓል፡፡
ቀኑ "የሳንባ ምችን ለመግታት ግንባር ቀደም እንሁን" በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር ተገልጿል።
በውይይቱ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክልል ጤና ቢሮዎች የስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።
በውይይት መድረኩ በሳምባ ምች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የሳንባ ምች በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃና መከላከል የሚቻል የመተንፈሻ ኢንፌክሽን ነው።
የሳምባ ምች በተለይም ህፃናት እና እድሜያቸው የገፉ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ የሳንባ ምችን ጨምሮ ተላላፊ ህመሞችን ለመከላከል የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጨማሪ ስራ የሚጠይቁ እንደሆኑም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በሽታውን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት በበሽታው የሚከሰት የታዳጊ ህፃናትን ሞት በ67 በመቶ መቀነስ መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

12 Nov, 16:51


ልበ ቀናነት የወለደዉ የፈጠራ ሥራ
AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም
ልበ ቀናነት የወለደዉ የፈጠራ ሥራ በ9ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ዉጤቶች ላይ ለእይታ በቅቷል፡፡
ተማሪ ፀጋአብ ሚሊዮን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን የፈጠራ ዉጤቱን ለእይታ አብቅቷል፡፡
ነገሩ እንዲህ ነዉ፤ ተማሪ ፀጋአብ ባደገበት መንደር የአካል ጉዳት ያለባቸዉ ጎረቤት አሉት፡፡
እኝህ አካል ጉዳተኛ ከፍተኛ የመንቀሳቀስ እና አብዝቶ ስራ መስራትን ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ጉዳቱ ይህን እንዳያደርጉ ያስቸግራቸዋል፡፡
ህፃኑ ፀጋአብ በለጋ እድሜዉ ይህን በዉል አስተዋለ፡፡
አካል ጉዳተኛ ጎረቤቱን ለማገዝም አብዝቶ ማሰብ ጀመረ፤ በዚህም አካል ጉዳተኛን ማገዝ ማንቀሳቀስ የሚችል ፈጠራን እዉን አደረገ፡፡
በዛሬዉ እለትም ለእይታ አበቃ፡፡ ህፃኑ ነገን አልሞ አሁን በጅምር ያለን ፈጠራ ማሳደግ ጎረቤቱንም ማገዝ ፍላጎቱ ነዉ፡፡
በተመስገን ይመር

Addis Media Network-AMN

12 Nov, 16:51


ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችው ውጤታማ ተግባር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው
AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችው ውጤታማ ተግባር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን "ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባኤ የተሳተፉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አፍሪካውያን ባለሃብቶች ገለፁ።
"ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል።
አፍሪካውያን የግብርና ዘርፍ ኢንቨስተሮች እንዳሉት ጉባኤው ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወነች ካለው ስራ ልምድ ለመቅሰም አስችሏቸዋል።
የአፍሪ ፉድስ ዋና ዳይሬክተር ካኪና ሁሴንጂማና በሩዋንዳ የሚገኘው ድርጅታቸው ምግብና አትክልቶችን ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡
ድርጅታቸው በአገሪቱ ካሉ 4ሺህ ወጣት አርሶ አደሮች ጋር በግብርናና እንስሳት ልማት በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የተደረገው ጉባኤ ለአለም በተለይ ደግሞ በችግር እየተፈተነች ላለችው አፍሪካ ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል።
በካሜሮን የሚገኘው ቴልካር ኮኮዋ ድርጅት የደንበኞች አገልግሎት አስተባባሪ አልበርት ቬጋህ በበኩላቸው ድርጅታቸው የካካዋ ምርትን ከአርሶ አደሮች በመረከብ ለውጭ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛችና በነፃነት የኖረች አገር ከመሆኗ ባሻገር በአሁኑ ወቅት በግብርናና ሌሎች ዘርፎች በራሷ አቅም ባከናወነችው የልማት ስራ ውጤት እያስመዘገበች መሆኑንም አንስተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02oLMXyJw1bVdo1sAgvC3gcJFK2kTbEbJFSvVcw4vWcYdku7B8s6UsUByD67w7AxS2l

Addis Media Network-AMN

12 Nov, 16:48


በመሻሻል ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደንብ ዘመኑን የዋጀ እና ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግል ታስቦ የሚዘጋጅ ነው-ታገሠ ጫፎ
AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም
በመሻሻል ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ዘመኑን የዋጀ እና ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግል ታስቦ እየተሰራበት እንደሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴና አስተባባሪ ኮሚቴ ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ፣ እየተሻሻለ ባለው ደንብ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ደንቡ ከስያሜው ጀምሮ ዘመኑን የዋጀ፤ ለውጥን መሰረት ያደረገ እና በምክንያት ላይ ተመርኩዞ እየተሻሻለ እንደሆነ ነው አፈ-ጉባኤ ታገሠ ያብራሩት፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ፣ በደንቡ ላይ ማሻሻያ መደረጉ የምክር ቤቱን አሠራር ቀልጣፋ እና ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምሕረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በመሻሻል ላይ የሚገኘው ደንብ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎች የተካተቱበትና የምክር ቤቱን አሰራር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0hvNnSdL28Byiyyq3Av4hGeK97sj9xCuf5XwiXEXWV1EM1R1YF1SzcsDUqeHMNfigl

Addis Media Network-AMN

12 Nov, 14:21


ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለሚጥል እና የተለያዩ የአእምሮ ችግሮች ምርመራ የሚውል የህክምና መሳሪያ ለሆስፒታሎች ለገሱ
AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው 41 የአእምሮ ሁኔታን በተለይም የሚጥል በሽታ ለመለየት እና ሌሎች የአእምሮ ችግሮችን ለመመርመር የሚችል የህክምና መሳሪያ (EEG) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ 7 ሆስፒታሎች በዛሬው እለት በስጦታ ለግሰዋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ፤ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የተለያዩ ሆስፒታል ዳይሬክተሮች በተገኙበት ነው ስጦታውን ያበረከቱት፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ከሚሰራቸው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ውስጥ አንዱ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማሳደግ፣ ጥራቱንና ተደራሽነቱን የጠበቀ የህክምና እና ክብካቤ አገልግሎት እንዲሰጥ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ መሆኑም ተወስቷል፡፡
በመሆኑም ጽ/ቤቱ በዚህ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን በመሰራት ላይ እንደሚገኝና ከዚህ በፊትም ለአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለጎንደር ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎችን ድጋፍ ማድረጉን የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት መረጃ አስታውሷል፡፡
በዛሬው እለት የተደረገው ይህ ከፍተኛ ድጋፍም ሆስፒታሎቹ እየሰጡ ያለውን የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የተደገፈ እና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ያስችላል ተብሏል፡፡

Addis Media Network-AMN

11 Nov, 14:00


መጽሐፍት ለትውልድ!

ይህ በየሳምንቱ ሰኞ ዕለት ጠቃሚ ናቸው ያልናቸውን መጽሐፍት ለተከታዮቻችን የምንጋብዝበት አምዳችን ነው።

የመጽሐፍቱ ምርጫ የእናንተ የውድ ተከታዮቻችንም ጭምር ነው፤ አንብባችሁ የወደዳችሁትን መጽሐፍ ብትጠቁሙን እኛም አንብበን ያላነበቡ እንዲያነብቡት መልሰን እንጋብዛለን።

ለዛሬ "ኤፒክቲተስ"ን በጨረፍታ ዳስሰን ሙሉውን እንዲያነብቡት ጋብዘናችኋል። እነሆ!!

ርዕስ - ኤፒክቲተስ

ትርጉም - ክብረ ወሰን ገብረአምላክ

የታተመበት ጊዜ - 2013 ዓም

በዓለማችን ጥሩ ተቀባይነትን ካተረፉ ዝነኛ መጽሐፍት መካከከል የጥንቱ ግሪኮ-ሮማ ተወላጁ ኤፒክቲተስ የጻፈው “ኤፒክ” የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ይገኝበታል። ኤፒክቲተስ የአዕምሮአዊ ፍልስፍናን፣ ውስጣዊ የሕይወትን እና አስተሳሰብን ማንበብን እና ማሰላሰልን እንዲሁም ወደ ውስጥ መመልከትን ብሎም ራስን የመግራትን መልካምነት ይሰብካል።

ታዲያ ይህ ውስጣዊ ፍልስፍና ከዛሬ 2000 ዓመት በፊት የተጻፈ ድንቅ ሕገ-ህሊና መጽሐፍ ሲሆን በደራሲው በኤፒክቲተስ ስምም ተሰይሟል።

ምክንያቱም ...

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ሊንኩን (ማስፍንጠሪያውን) ይጫኑ

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02pRuytnueE8Zd8878Jk1FHKqrkzdG9Lr2f96K1DXqLgE1gG7ecFzMwuTwn9xYXPXBl

Addis Media Network-AMN

11 Nov, 13:23


500 ኪሎግራም የሚመዝነው የአዘርባጃን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

AMN - ህዳር 2/2017 ዓ.ም

500 ኪሎግራም የሚመዝነው እና 72 ሜትር ርዝመት እንዲሁም 36 ሜትር ስፋት ያለው የአዘርባጃን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም ትልቁ ሰንደቅ ዓላማ በመባል በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

ሰንደቅ ዓለማው በዋና ከተማዋ ባኩ በሚገኘው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓለማ አደባባይ ከፍ ብሎ እየተውለበለበም እንደሚገኝ አናዶሉ ዘግቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

11 Nov, 12:10


የፀረ-አበረታች ቅመሞች የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ አትሌቶች ተቀጡ

AMN - ህዳር 2/2017 ዓ.ም

የፀረ-አበረታች ቅመሞች የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ አትሌቶች መቀጣታቸውን የኢትዮጵያ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ፣ ሳሙኤል አባተ ዘለቀ እና ፀሐይ ገመቹ በያን የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) በመጠቀም የሕግ ጥሰት መፈማቸው መረጋገጡ ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሠረት አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ከጥቅምት 30 ቀን 2024 ጀምሮም ለ4 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍም ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም ከ2020 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2024 ጀምሮ ያስመዘገበችው ውጤት እንዲሰረዝ ቅጣት እንደተጣለባት ተገልጿል።

እንዲሁም አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ቻይና ሀገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ በተካሄደው ምርመራ Triamcinolone acetonide የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሟ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በዚህም መሠረት በፈረንጆቹ ከሰኔ 3 ቀን 2024 ጀምሮ ለ2 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ እገዳ እንደተጣለባት የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ በፈረንጆቹ የካቲት 29 ቀን 2023 በተካሄደው ምርመራ EPO (Erythropoietin) የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡

በመሆኑም በፈረንጆቹ ከሚያዝያ 17 ቀን 2024 ጀምሮ ለ2 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል፡፡

በቀጣይም በኢትዮጵያ በየደረጃው የሚደረገው ምርመራና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ይሁን በተለያዩ መልኩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው በሚተባበሩ ሌሎችም ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን የእርምት ርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡

Addis Media Network-AMN

10 Nov, 15:08


የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት 5 ዓመታት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ከማከናወኑም ሌላ አዲስ አበባ ከተማን ከዓለም ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ ሠፋፊ ሥራዎችን ማከናወኑ ተገለጸ

AMN- ህዳር 1/2017 ዓ.ም

“የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ ባለፉት 5 ዓመታት በሀገር አቀፍና በከተማ ደረጃ በተከናወኑ ጉዳዮች ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብራራው እሸቴ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት 5 ዓመታት በርካታ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን በማከናወን ታላላቅ ድሎችን አስመዝግቧል ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በአምስት ዓመታቱ በሀገር ደረጃ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ከማከናወኑም ሌላ አዲስ አበባ ከተማንም ከዓለም ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ ሠፋፊ ሥራዎችንም አከናውኗል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው።

ፓርቲው በተለይም በመሠረተ ልማት ግንባታና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋትና ዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የመኖሪያ ቤቶችን በማደስና በመገንባትም የበርካቶችን ህይወት የመለወጥ ሥራ አከናውኗልም ብለዋል።

እነዚህ ሁሉ ውጤቶች የተመዘገቡትም የመረጠን ህዝባችን ጠንካራ ድጋፍ ከጎናችን በመሆኑ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በቀጣይም ብልጽግና የወጠናቸውን ራዕይዎች ከግብ ለማድረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መቀጠል አለብን ነው ያሉት።

ባለፉት 5 ዓመታት መንግስት በርከታ የልማት ሥራዎችን ሲሳራ ቆይቷል ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይም በኮሪደር ልማት፣በምገባና የአቅመ ደካሞችን የቤት ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ የሚደነቁ ስራዎችን መሥራቱን ተናግረዋል።

Addis Media Network-AMN

10 Nov, 15:06


በግለሰብ ቤት በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ ተያዘ

AMN- ህዳር 1/2017 ዓ.ም

በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የካራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተከማቹ በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፖል ላይ የሚታሰር የገመድ ማቀፊያ ይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ ሥራ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

Addis Media Network-AMN

10 Nov, 15:04


15ኛው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ጉባኤ በአህጉሪቱ የንግድ ጉዳዮች ላይ ስኬታማ እና ፍሬያማ ውይይቶች የተካሄደበት ነው

AMN- ህዳር 1/2017 ዓ.ም

15ኛው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ጉባኤ በአህጉሪቱ የንግድ ጉዳዮች ስኬታማ እና ፍሬያማ ውይይቶች የተካሄደበት እንደነበር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለፁ።

15ኛውን የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ጉባኤ ለመታደም የመጡ ሚኒስትሮች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚገኘውን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከል እና በገላን የሚገኘውን ኤኤምጂ የቡናና የብረታብረት ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የወጪ ንግድ አቅም ለጎብኚዎቹ አስረድተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ 15ኛውን የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ጉባኤ በአፍሪካ ንግድ ጉዳዮች ዙሪያ ስኬታማ እና ፍሬያማ ውይይቶች የተካሄደበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ ሀገራት የንግድ ልውውጥና የእሴት ሰንሰለት ልማትን በሁሉም ዘርፎች ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉንም አንስተዋል።
በአህጉሪቱ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ በቅርቡ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሙከራ ትግበራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቋን እንደገለጸችም ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ፅህፈት ቤት ዋና ጸሀፊ ዋምኬሌ ሜኔ እና የታንዛኒያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሰሌማኒ ጃፎ በጉብኝቱ በተመለከቱት ስኬት መገረማቸውን ገልጸዋል።

Addis Media Network-AMN

10 Nov, 13:05


ቅድመ ምረቃ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሚኒስትር ድኤታ፣ የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ሀላፊ፣ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ኃላፊ፣ የእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና አምባሳደሮችን ያስተናገደችው ቤኑና
'ቦታ ሲመረጥ
ያገር ልጅ ሲሮጥ
ውበት ሲገለጥ
ይኼ ነው መብለጥ' አስብላለች።
ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

Addis Media Network-AMN

09 Nov, 11:10


የሰላምና ጸጥታ አገልግሎት ለዜጎች በሰላም ወጥቶ መግባት ዋስትናና መሰረት በመሆኑ ትልቅ ክብር እንሰጣለን ፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የሰላምና ጸጥታ አገልግሎት ለሁለንተናዊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ስኬት እንዲሁም ለዜጎች በሰላም ወጥቶ መግባት ዋስትናና መሰረት በመሆኑ ትልቅ ክብር እንሰጣለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በ2016 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የፖሊስ መምሪያዎች፣ አመራሮች፣ አባላት እና አጋር አካላት እውቅና ሰጥቷል።

የሰላምና ጸጥታ አገልግሎት ውጭ ውሎ ከማደር እስከ አካል መጉደል እና የህይወት መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዴነች አቤቤ ይህ በከፍተኛ መሠጠት የሚከናወን ተግባር በመሆኑ ክብር መስጠት ይገባል ነው ያሉት።

አዲስ አበባን የሁከትና ብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ታቅዶ በርካታ ፈተናዎች ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ሲያጋጥሙ ቢቆዩም የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላትና ከህዝቡም ጋር በመቀናጀት በጀግንነት ፈተናዎቹን ማለፍ ችሏል ያሉት ከንቲባ አዳነች በዚህም ውስጥ በርካታ ትምህርቶች ፣ የወንጀል መከላከል ስልቶችና ታክቲኮች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

Addis Media Network-AMN

09 Nov, 10:46


የሀገራችን ውበት ሀብት ነው::
የበሰቃ ሐይቅ ምሥጢሮች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Addis Media Network-AMN

09 Nov, 10:00


የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም የካፍንና የፊፋን ስታንዳርድ ባሟላ መልኩ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል፡-የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም የካፍንና የፊፋን ስታንዳርድ ባሟላ መልኩ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።

ስታዲዮሙ የዲዛይን ማሻሻያ ተደርጎለት 2000 ቪ.አይ.ፒ እና 25 ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ሆኖ መሰራ ተገልጿል።

አጠቃላይ 87% አፈጻጸም ያለው ፕሮጀክቱ የካፍንና የፊፋን ስታንዳርድ በማሟላት በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ መገለጹን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

09 Nov, 09:45


የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቷን ዘላቂ እድገት የሚያረጋግጥና ወደ ብልፅግና የሚያሻግር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቷን ዘላቂ እድገት የሚያረጋግጥና ወደ ብልፅግና የሚያሻግር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ መረባረብ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

15ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የንግድ ሚኒስትሮች ጉባዔ በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴን ጨምሮ የአፍሪካ የንግድ ሚኒስትሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በዚህ ወቅት፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የጋራ ራዕያችንን የምናሳካበት የበለጸገች አፍሪካን እውን የምናደርግበት ነው ብለዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ንግድና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ አህጉራዊ ትስስርና ትብብር የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።

ነፃ የንግድ ቀጣናውን ገቢራዊ ለማድረግ ውይይት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው፣ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ ቀጣናዊ ትስስሩን ማቀላጠፍ ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ከንግድ ቀጣናነት ባለፈ የአፍሪካ ዘላቂ እድገት ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አህጉር 1 ነጥብ 4 ቢሊየን አፍሪካውያንን የበለጠ በማስተሳሰር ፈጣንና ወደ ብልፅግና የሚያሻግር ኢኮኖሚያዊ እድገት ማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ድህነትን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Addis Media Network-AMN

09 Nov, 09:44


ዘላቂ ሠላምን ማስፈን አማራጭ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው - የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

ዘላቂ ሠላምን ማስፈን አማራጭ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ሲሉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን እንዲሁም የግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴዎች እና የሐገር ልማትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ለጋዜጠኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ “ሠላም ለልማት” በሚል ርዕስ ፅሑፍ ያቀረቡት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ለአገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ሠላም ተኪ የሌለው መሆኑን የገለፁ ሲሆን የሠላምን መሰረታዊያን መገንዘብ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ሠላም በማሕበረሰቦች መካከል መተማመንን የሚያሳድግ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ዮናስ መተማመንን መገንባት የቻለ ማህበረሰብ ለጋራ ተጠቃሚነት እና በጋራ መስራት የሚችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በሐገር እድገት ውስጥ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን መገናኛ ብዙኃን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል፡፡

Addis Media Network-AMN

07 Nov, 20:21


የአሜሪካው ኮንግረንስ እአአ ጥር 6 ተገናኝቶ የዶናልድ ትራምፕን አሸናፊነት ያፀድቃል

AMN - ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ኮንግረንስ እአአ በመጪው ጥር 6 ተገናኝቶ ዶናልድ ትራምፕ የ2024ቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን እንደሚያፀድቅ ተገልጿል።

በአጠቃላይ እአአ ታኅሣሥ 17/2024 ሁሉም ግዛቶች የተሰጡ ድምጾችን ውጤት በማስረከብ አሸናፊው ተወዳዳሪ ይፋ ይሆናል።

ከዚያም የአሜሪካ ኮንግረንስ እአአ ጥር 6/2025 ተገናኝቶ በተሰጠው ድምፅ መሠረት የአዲሱን ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሥልጣን ያጸድቃል።

ተሸናፊዋ ተወዳዳሪ ካማላ ሐሪስ በዚህ ሥርዓት ላይ በመገኘት ሥርዓቱን ይመራሉ ተብሏል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) ይጫኑ ...

https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid02h8qDjUsEXMxVzT2yFEeziovyGSw9emFHxZcSfcHRjvZkSBJfcDEmnHFBej4sETYal

Addis Media Network-AMN

07 Nov, 16:35


ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ከደሴ ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ

AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በደሴ ከተማ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት ከደሴ ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተለያዩ የክልል ከተሞች እንደሚከናወኑ መገለጹ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምከትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በአዲስ አበባ ከሚያስተባብሩት የኮሪደር ልማት በተጨማሪ በደሴ እና ሠመራ ከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶችን በአስተባባሪነት ይመራሉ፡፡

ምክትል ከንቲባው ከወር በፊት በደሴ ከተማ ተገኝተው በዲዛይኑ ላይ በመምከር ተጨማሪ መካተት ያለባቸው ተግባራትን በመለየት ግብረ መልስ እንደሰጡና ዲዛይኑን ለከተማ አስተዳደሩ እንዲልኩ መደረጉ ይታወሣል።

ምክትል ከንቲባው ስራውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከክልሉ ፕሬዚደንት ጋር ተወያይተው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በደሴ ከተማ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት ሐብት ማሰባሰብ ላይ ከከተማው ከንቲባ ጋር ዉይይት ማካሄዳቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Addis Media Network-AMN

07 Nov, 16:34


በኮልፌ ቀራኒዎ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የአቅመ ደካማ ቤቶች ተመረቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ

AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዎ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 የ2016 የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የ2017 የበጋ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ- ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ በአዲስ አበባ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አስተባባሪነት ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና በባለሀብቶች ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች ቤት የምረቃ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሀግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ በአዲስ አበባ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሒም ፣የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙልጌታ ጉልማ፣የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሒም መሀመድ እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው የወረዳው ነዋሪዎች እና ቤቶችን ያስገነቡ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር የሆኑ ኘሮጀክቶችን አስፍቶ በማቀድና በመፈፀም የህብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛ ያሉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አማካኝነት በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 አስተዳደር የተገነቡ ቤቶች መመረቁን አስረድተዋል፡፡

ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አማካኝነት የአቅመ ደካሞችን ህይወት የቀየረ የቤት እድሳት በማድረጉ አመስግነዋል።

Addis Media Network-AMN

07 Nov, 16:32


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብን ፍላጎት ያማከሉ እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያጋልጡ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ለአድማጭ ተመልካች ማድረሱ የተቋሙን የህዝብ ድምጽ መሆን እና ተዓማኒነቱን የሚያረጋግጥለት ነው፡- ቋሚ ኮሚቴው

AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብን ፍላጎት ያማከሉ እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያጋልጡ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ለአድማጭ ተመልካች ማድረሱ የተቋሙን የህዝብ ድምጽ መሆን እና ተዓማኒነቱን የሚያረጋግጥለት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

በተቋሙ የተከናወኑ ሪፎርሞች እና የሪፎርም ውጤቶች፣በተለያዩ መንገዶች አድማጭ ተመልካች ጋር እየደረሱ ያሉ ስራዎች እና ሌሎች አገልግሎቶች በአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በምልከታው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መዲናዋን እና ነዋሪዎቿን የሚመስል ተቋም ለመሆን እያደረገ ያለውን ጥረት እና በቴክኖሎጂ ብሎም በሰው ኃይል ልማት እያደረገ የሚገኘውን አበረታች ስራዎች አድንቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብን ፍላጎት ያማከሉ እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያጋልጡ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ለአድማጭ ተመልካች ማድረሱ የተቋሙን የህዝብ ድምጽ መሆን እና ተዓማኒነቱን የሚያረጋግጥለት ነው ብለዋል፡፡

በተለይም ዋርካ፣አገልጋይ፣በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እያደረገ የሚገኘው ድንገተኛ ቅኝት እና ሌሎች ፕሮግራሞች ማሳያ መሆናቸውንም ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

07 Nov, 16:30


በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ የውንብድና እና የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN - ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ የውንብድና እና የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የተለያዩ ንብረቶችም ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ የሃይል ተግባር በመጠቀም በተለያዩ ግለሰቦች ላይ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአድዋ ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-30785 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ ምሽት ላይ አንድን ግለሰብ ከቦሌ ጌታሁን በሻህ ህንፃ አካባቢ ጭነው ከወሰዱ በኋላ አመቺ ቦታ ሲደርሱ የግለሰቡን እግር በጫማ ገመድ አስረው እና በስለት አስፈራርተው ሞባይል ስልክ እና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ በአጠቃላይ 21ሺህ 500 ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ወስደው ተሰውረዋል፡፡

አቤቱታው የደረሰው ፖሊስ ጣቢያው የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ የተፈፀመበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የወላጆቹ በሆነው ተሽከርካሪ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ ውሎ ምሽት ላይ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ እየተቀበለ መኪናውን አሳልፎ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ሲሰጥ የነበረ ግለሰብን ጨምሮ በወንጀሉ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 17 ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

06 Nov, 07:07


ኬንያ ብሪክስን ለመቀላቀል የቻናን ድጋፍ ጠየቀች

AMN - ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር በናይሮቢ ባደረጉት ውይይት ኬንያ ብሪክስን ለመቀላቀል ለምታደርገው ጥረት ቻይና ድጋፍ እንድትሰጥ ጠይቀዋል።

"ከቻይና ጋር ያለን አጋርነት በአፍሪካ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኬንያ ቁርጠኛ መሆኗን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" ሲሉ ሩቶ ለቻይና ልዑካን ገልጸዋል።

በተለይም ኬንያ የዓለማችንን 28 በመቶ ኢኮኖሚ የሚሸፍኑ ሀገራት ያሉበትን የብሪክስ ስብስብን ለመቀላቀል የጀመረችውን ጉዞ ቻይና እንድትደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ቻይና እና ኬንያ ያላቸውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ተጠቅመው በሀገራቱ የልማት ፐሮጀክቶች እያሳለጡ እንደሚገኙ አፍሪካ ኒውስ ነው የዘገበው።

ብሪክስ በፈረንጆቹ 2006 በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ እና ቻይና ሀገራት ነው ‘BRIC’ በሚል ስያሜ የተመሠረተው። ደቡብ አፍሪካ ስብስቡን በ2010 ስትቀላቀል ስሙ BRICS’ ሆነ።

ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት በ2024 የዚሁ ኅብረት አባል መሆናቸው የሚታወስ ነው።

በማሬ ቃጦ

Addis Media Network-AMN

06 Nov, 06:46


በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ለማሸነፍ ተቃርበዋል

AMN - ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፉክክሩን አሸናፊ የሚበይኑት ሰባት ግዛቶች መካከል ሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ ላይ ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈዋል።

በቀጣይ አሪዞና፣ ኔቫዳ፣ ሚሺጋን፣ ፔንሲልቫኒያ እና ዊስከንሰን የምርጫው የፉክክር ማዕከል ናቸው።

የምርጫው ፉክክር ዋንኛ ትኩረት የሆኑት በእነዚህ ሰባት ግዛቶች እስካሁን ባለው ሁኔታ ዶናልድ ትራምፕ በተቀሩት አምስቱም ግዛቶች እየመሩ ነው።

በተለይ 19 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ባለው ፔንሰልቨኒያ ላይ ዶናልድ ትራምፕ የሚያሸነፉ ከሆነ ምርጫው ለመሸነፍ ወደሚረዳቸው 270 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ለማግኘት ይቃረባሉ።

ትራምፕ በፔንሲልቨኒያ ግዛት ላይ የሚያሸንፉ ከሆነ ከወሳኞቹ ግዛቶች አንድ ተጨማሪ ግዛት ብቻ ነው ማሸነፍ የሚጠበቅባቸው።

እንድ ቢቢሲ ዘገባ ይህ ከሆነ ደግሞ የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት የሚደመደም ይሆናል።

በአሳየናቸው ክፍሌ

Addis Media Network-AMN

05 Nov, 16:00


የአሜሪካ ምርጫ የፍልሚያ ሜዳ የሆኑት ሰባት ግዛቶች

AMN - ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአሜሪካ ምርጫ ተጀምሯል፡፡

የምርጫው ፉክክር ዋንኛ ትኩረት የሆኑት ደግሞ ድምፃቸው ለማን እንደሚሰጡ ያለየላቸው ሰባት ዋዣቂ ግዛቶች ላይ ነው፡፡

አሪዞና፤ ጆርጂያ፤ ኔቫዳ ፤ሚቺጋን፤ ሰሜን ካሮሊና፤ፔንሲልቫኒያ እና ዊስከንሰን የምርጫው የፍክክር ማዕከል ናቸው፡፡

እነዚህ ሰባት ግዛቶች በአጠቃላይ ድምር 93 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ያላቸው ሲሆን ከአጠቃላዩ የ538 ኤሌክቶራል ኮሌጅ 270 ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ግዛቶች ናቸው፡፡

እነዚህ ግዛቶች በካማላ እና ትራምፕ መካከል የሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ፉክክር አሸናፊን የሚበይኑት የአሜሪካ ግዛቶች ሲሆን መራጭች ድምጽ መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ ሁሉም ትኩረቱን ያደረገው በእነዚህ ግዛቶች ላይ ነው፡፡

Addis Media Network-AMN

05 Nov, 10:08


የምርጫ ቀን በአሜሪካ

AMN - ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም

አሸናፊውን በቀላሉ ለመገመት አደጋች የሆነው የ2024 የአሜሪክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፣ የምርጫ ጣቢያዎች ወደ መከፈቱ ናቸው።

ከ78 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ግን መደበኛው የምርጫ ሥነ-ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት አስቀድመው ድምፃቸውን መስጠታቸው ተመላክቷል።

አሁን ባለው የምርጫ ቅድመ ግምት ትንተናዎች ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሐሪስ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል።

ካማላ ሐሪስ ጽኑ የዴሞክራት ደጋፊ ግዛቶች 226 ኤሌክቶራል ኮሌጅ አስተማማኝ መነሻ ድምፅ ያላቸው ሲሆን፣ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ጽኑ የሪፓብሊካን ደጋፊ ከሆኑ ግዛቶች 219 ኤሌክቶራል ኮሌጅ አስተማማኝ መነሻ ድምፅ እንዳላቸው ተነግሯል።

ከዚህም የተነሣ ዋዣቂ ግዛቶች ላይ በሚደረገው ፈልሚያ የምርጫው ሙጤት የሚወሰን ይሆናል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ) ... https://web.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0nYbKhGCbeQ68ryZTCXzcVzFpKxVNqBSFfT2JpA8m3WkGBRFvzhqgxiZbD6LNucFWl

Addis Media Network-AMN

05 Nov, 07:56


የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፈጠራ የታከለበት መፍትሔን ይሻል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN - ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም

የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፈጠራ የታከለበት መፍትሔን እንደሚሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከረሀብ ነፃ ዓለም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

በእንኳ ደህና መጣችሁ መልእክታቸውም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ፣ የቡና መገኛ፣ የራሷ የቀን ቀመር እና ፊደል ያላት ምድረ ቀደምት መሆኗን ለኮንፈረንሱ ታዳሚዎች አስታውቀዋል። ኮንፍረንሱን ላዘጋጁ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዓለምን ከረሀብ ነፃ ለማድረግ በምናደርገው ጥረት የአየር ንብረት ለውጥ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግጭቶች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እና ኮቪድ-19 የተፈታተኑን ቢሆንም ከዚህ ወርቃማ ዓላማችን ሊያቆሙን አልቻሉም፤ ይልቁን ጥረታችንን በእጥፍ እንድንጨመር አደረጉን እንጂ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

አክለውም፣ አሁን ባለው የዓለም ቀውስ እና እየጨመረ ከመጣው የሕዝበ ቁጥር ጋር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፈጠራ ታከለበት መፍትሔን የሚሻ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ያልተቋረጠ ጥረት፣ ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴን ማሳደግ፣ ወሳኝ የግብርና ግብዓቶችን ማስፋት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በመቆጣጠር ምርታማነትን መጨመር እንደሚገባ አብራርተዋል።

ዓለምን ከረሀብ ነፃ ማውጣት ምርታማነትን ከመጨመርም ያለፈ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ድህነትን፣ ኢ-ፍትሐዊነት እና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችንም በሁለንተናዊ መልኩ መፍታትን ይጠይቃል በለዋል።

ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገንም ተናግረዋል።

በማሬ ቃጦ

Addis Media Network-AMN

05 Nov, 07:15


"በAMN በሚተላለፈው ቤተኛ ሲትኮም ድራማ ምክንያት ብዙ ሰው የተጋባን መስሎት ነበር "
የቤተኛ ድራማ ተዋንያን በሰይፉ ሾው ላይ ከተናገሩት!!

🏫👬 ቤተኛ አዝናኝ ሲትኮም ድራማ ዘወትር እሁድ ምሽት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በAMN ላይ ይቀርባል።

የባለፈው ሳምንት ሲትኮም ድራማን ሙሉውን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/v8Mxn_uCC5M

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 17:47


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የነበሩ ጥንካሬዎች በማስቀጠል ውስንነቶችን ደግሞ በልዩ ትኩረት እየቀረፈ እንዲሄድ ተጠየቀ

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሱፐርቪዥን ስራ አካሂዷ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በኤጀንሲው በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅትና ሌሎች የምዕራፍ ተግባራትን ዝርዝር ሪፖርት በማዳመጥ ገምግሟል።

ኤጀንሲው የነበሩ ጥንካሬዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ውስንነቶችንም በልዩ ትኩረት እየቀረፈ እንዲሄድ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:50


አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ በሚገኙ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:26


የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የውሃ ሃብትን ለማጎልበት ትልቅ ሚና እያበረከተ ነው

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለውሃ ሀብት መጎልበት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የአፈር መሸርሸርን ለመጠበቅ ትልቅ ጠቀሜታ እያስገኘ መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

"የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ለቀጣናው ዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደር ያለው ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ዓለም አቀፍ የሀይድሮ ሜት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) የኮንፍረንሱን የመጀመሪያ ቀን ውሎ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ በኮንፍረንሱ የአረንጓዴ አሻራ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብትና በቀጣናው ያመጣው ለውጥ መቅረቡን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ጉባዔው በዓለም ላይ እያጋጠመ ያለውን ድርቅ መቋቋም በሚያስችል ሁኔታ ላይ መረጃዎችን መለዋወጥ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በመወያየት መግባባት ላይ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት 40 ቢሊዮን ችግኞችን መትከሏን የተናገሩት ሚኒስትሩ የተተከሉ ችግኞች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና ከስራ ዕድል ፈጠራ ባሻገር ለውሃ ሃብት መጎልበት አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደራቸውን ገልጸዋል፡፡

በአባይ ተፋሰስ፣ በስምጥ ሸለቆ እና በላይኛው የአዋሽ ተፋሰስ ላይ በተከናወኑ የምርምር ስራዎች ከዚህ ቀደም የተራቆቱ ቦታዎች በደን መሸፈን መቻላቸውን አብራርተዋል፡፡

በአባይ ተፋሰስ ከአራት እስከ አምስት በመቶ የደን ሽፋን እንዲጨምር ማስቻሉን ጠቁመው በሁሉም ተፋሰሶች ላይ የሚታዩ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:25


የኮርፖሬሽኑን ስኬታማ ጉዞ ለማስቀጠል በትጋት መስራት ይገባል - የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ስኬታማ ጉዞ ለማስቀጠል በትጋት መስራት እንደሚገባ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል ገለጹ።

ዓመታዊው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሰራተኞች ቀን ዛሬ ተከብሯል።

በአከባበሩ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፣ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ተላቆ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት ስኬት እያስመዘገበ መቀጠሉን አቶ ረሻድ ገልጸዋል።

የተገኘው ስኬት እና ለውጥ መንግስትና ሕዝብ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ለውጤቱ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም አመራሩ እና ሰራተኛው ለኮርፖሬሽኑ የላቀ ስኬት እና ለውጥ መትጋት እንዳለበት አመልክተዋል።

ቀጣይ የኮርፖሬሽኑ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችል አስተማማኝ የለውጥ መሰረት መገንባቱን ገልጸው መጪው ጊዜ የኮርፖሬሽኑ የእድገትና የላቀ አገራዊ አበርክቶ የሚጎላበት ጊዜ ይሆናል ብለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አበባው ዋለልኝ በኮርፖሬሽኑ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሰላም መስፈኑና በሰራተኛውና በአመራሩ መካከል የተግባርና የአመለካከት አንድነት መኖሩ ለስኬቱ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል።

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:14


የኃይማኖት ተቋማት ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነትን ለማጠናከር የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል - ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የኃይማኖት ተቋማት ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነትን ለማጠናከር የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ተናገሩ።

የሰላም ሚኒስቴር በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ከሚገኘው ከመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

በጉባዔው መክፈቻ የኢፌዴሪ የፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፣ የመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ካልፍ ሙባረክ(ዶ/ር)፣ የኃይማኖቶች አባቶች፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ በኃይማኖትና በሰላም ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ዩኒቨርሲቲዎች ተሳትፈዋል።

እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ፣ የሩስያ፣ የሞሮኮና የደቡብ አፍሪካ የኃይማኖት ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባዔው ላይ ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጽንፈኝነትና የመከፋፈል ኃሳብ አብሮ ለመኖር አደጋ እየሆነ መጥቷል።

በመሆኑም የኃይማኖት ተቋማት ለአብሮነትና መቻቻል አደጋ እየሆነ የመጣውን የጽንፈኝነትና የመከፋፈል ኃሳብ ለማስወገድ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት።

የኃይማኖት ተቋማት ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነትን ለማጠናከር የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ለዚህም የኃይማኖት ተቋማት የመቻቻል፣ አብሮ የመኖርና የመተሳሰብ እሴትን በማጠናከረ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑን በመጠቆም።

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:12


የኮሪደር ልማቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ሕብረተሰቡ እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ መቀጠል አለበት

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የኮሪደር ልማቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ሕብረተሰቡ እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

በከተማው የተገነቡ የኮሪደር ልማቶች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መዋል እንዲችሉና ለረዥም ጊዜ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ደንብ በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የወጣው ደንብ እንዲተገበር ለኅብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ቤት ለቤት፣ በሚዲያና በሌሎች ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሕብረተሰቡ በከተማው የተከናወኑ ልማቶችን በመንከባከብና ሰላምን ለማስጠበቅ አበክሮ እየሰራ ነው ብለዋል።

ተቋሙም የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ በጋራ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በከተማው የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ መሬት ማስፋፋት፣ ህገ-ወጥ ንግድና ግንባታ እንዲሁም የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ የመንገድ አጠቃቀም የመቆጣጠርም ሥራ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች ዙሪያና በሕዝብ መዝናኛ አካባቢ ሊስተዋሉ የሚችሉ አዋኪ ተግባራት ለመከላከል ሲሰራ መቆየቱን ሻለቃ ዘሪሁን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የመዲናዋን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ከተማዋን ውብና ፅዱ የማድረግ ስራው ላይም እንዲሁ በጋራ መሰራቱን እንደተቻለ አክለዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:10


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ያካሄዳል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የፌዴራል የፍትህ እና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ሌላኛው የስብስባ አጀንዳ መሆኑም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 16:09


የ ኤ ኤም ኤን ዲጂታል የዕለቱ ዋና ዋና ዜናና መረጃዎች፡-

•የኃይማኖት ተቋማት ለዓለም ፈተና እየሆነ ያለውን የፅንፈኝነትና የመከፋፈል እሳቤን ለማስወገድ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ መናገራቸው፡-

•በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሠራናቸው ሥራዎች ተጽዕኗቸው ድንበር ተሻጋሪ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው፡-

•የልኡካን ቡድናቸው የኳላ ላምፑር ቆይታ የተሳካ እንደነበር ከንቲባ አዳነች አቤቤመግለጻቸው፡-

•ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን እንዲሆን የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሀሚድ ማስታወቃቸው፡-

•ህብረተሰቡን በማሳተፍ የመዲናዋን ሰላምና ፀጥታ ዘላቂና አስተማማኝ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ መግለጹ፡

•የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ትልቅ አቅም በሚፈጥሩ የገቢ ዓይነቶች ላይ አተኩሮ እንዲሰራ በአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማሳሰቡ፡-

•በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ስለመሆኑ፡-

•በአሜሪካ ነገ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጉጉት እየተጠበቀ ስለመሆኑ፡-

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
ጥቅምት 25/2017 ዓ›ም

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 15:21


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት እስከ ዛሬ

ለአፍሪካዊያን ኩራት ለኢትዮጵያ ደግሞ መለያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ታኅሣሥ 21 ቀን በ1938 ዓ.ም ‘ትራንስወርልድ ኤር ዌይስ’ ከሚባል አየር መንገድ ጋር በጋራ እንደተመሠረተ መረጃዎች ያመላክታሉ።

አየር መንገዱ ሲመሠረት የተለያየ መጠን እና ዓይነት ያላቸው ያገለገሉ አምስት DC 3C47 አውሮፕላኖችን ከአሜሪካ በመግዛት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ ያደረገውም መጋቢት 30 ቀን በ1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ በአስመራ በኩል በማቋረጥ ወደ ካይሮ (ግብፅ) እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በወቅቱ የአየር መንገዱ የአስተዳደር ሂደት ይመራ የነበረው የአሜሪካ ዜግነት ባላቸው አካላት እንደነበርም ይነገራል።

አየር መንገዱ ቀስ በቀስ የበረራ አድማሱን በማስፍት በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ማለትም በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በኤዥያ እና በአሜሪካ በረራውን አጠናክሮ መቀጠል ችሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠመውን የሰው ኃይል እና የግብዓት ችግሮችን በድል በመወጣት እያስመዘገባቸው ያሉ ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ አሁን ላይ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ያለው ሲሆን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎችን በማሠልጠን ለአቬሽን ኢንዱስትሪው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

በተጨማሪም አየር መንገዱ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ አየር መንገዶች እና የግል አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት እና ሥልጠናም እየሰጠ ይገኛል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) ይጫኑ ... https://facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0BWC6GNwgr3LWK59oeuT9DGWNpiCUym48jy1C48MWe9KPZWekdhnz177giNaCjEYQl

Addis Media Network-AMN

04 Nov, 14:46


የልኡካን ቡድናቸው የኳላ ላምፑር ቆይታ የተሳካ እንደነበር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በማሌዥያ ጉብኝታችን የኳላ ላምፑር ምክትል ከንቲባ ኢስማዲ ቢን ሳኪሪን እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውልናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ እና ኳላ ላምፑር መካከል ትስስርን በማጠናከር በተለይም በከተማ ፕላን፣ በአረጓዴ ልማት፣ በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ፣ በህዝብ መናፈሻዎች፣ በኢንቨስትመንት፣ በጤና፣ በንግድ እና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ሲሉም አመልክተዋል።

በነበረን ቆይታም የስማርት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከልን እንዲሁም የፐርዲና ቦታኒካል ጋርደንን ጎብኝተን የአዲስ አበባ ከተማ የማስታወሻ ችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂደናል ሲሉም ገልጸዋል።

የማሌዢያዋ ኳላ ላምፑር ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና በቱሪዝም ልማት እያካሄደች ያለው የትራንስፎርሜሽን ስራዎች የምንማርበት በመሆኑ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል።

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 12:45


አዲስ ታለንት ሾው - ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ይጠብቁን!

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 10:41


አፈ ወርቆች

ልዩ የንግግር ክህሎት ውድድር - በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

በቅርብ ቀን!

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 10:22


ከ83 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ስልኮችበኮንትሮባንድ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም


በተሽከርካሪ የተለያዩ ክፍሎች በመደበቅ በኮንትሮባንድ ሊገቡ የነበሩ 83 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ከ4 ሺህ 100 በላይ ስማርት የሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው በተሽከርካሪ ጋቢና ጣራ ውስጥ ሻግ በማሰራት ጅግጅጋ ቦምባስ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሳይደርስ በጫካ በኩል አድርጎ ለማለፍ ሲሞከር በደረሰ መረጃ እና በተደረገ ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 09:57


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ነገ ይጀመራል

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ነገ ጥቅምት 24 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ እና ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በቦንጋ ከተማ ተገኝተው ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነሮቹ በመግለጫቸው ምክክሩ ከነገ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

በሂደቱም በክልሉ የሚገኙ የወረዳ የማኅበረሰብ ክፍሎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ በመኾን በአጀንዳ ሀሳቦቻቸው ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

አክለውም በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ የክልሉን ወኪሎች ይመረጣሉ ብለዋል።

በሂደቱ የሚሳተፉ የማኅበረሰብና የተቋማት ወኪሎች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡት ኮሚሽነሩ፤ ለሂደቱ ስኬት በተለያየ መስክ ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አካላትም በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በሚያከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መድረክ ከ2200 በላይ በክልሉ ከሚገኙ ከ57 ወረዳዎች የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍል ወኪሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተወካዮች መባሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 08:46


በጎንደር ከተማ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ወደ ትግበራ መግባቱ ተገለፀ

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

በጎንደር ከተማ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ወደ ትግበራ መሸጋገሩን የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው አስታወቁ።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ጥንታዊነት በጠበቀ አግባብ እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋት የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት መከናወን መጀመሩን ገልፀዋል።

ሁለተኛው ምዕራፍ 12 ኪሎ ሜትር የመንገድ ክፍል የሚለማ ሲሆን ከፒያሳ እስከ አየር ማረፊያ ያለውን የሚሸፍን መሆኑንና የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ወደ ትግበራ መገባቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የመንገድ ዳር ኮንቴይነሮችንና አጥሮችን የማንሳት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ተነሺዎችንም በሶስት ክላስተሮች በተደራጁ ቦታዎች ዳግም ስራ እንዲጀምሩ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ህንጻዎችን የማስዋብ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን የመገንባት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራቶችን የመትከልና የአስፓልት ማንጠፍ ስራዎችን ያካተተ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የአረንጓዴ ስፍራዎችና የመዝናኛ ፓርኮች ግንባታን ጨምሮ የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክና የኢንተርኔት መስመሮችም አንድ ወጥ በሆነ መንገድ እንደሚዘረጉ ገልጸዋል፡፡

ፒያሳንና የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ዙሪያን ያካተተውና አንድ ነጥብ ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ አዲስ የስራ ባህልን ከመፍጠሩ በላይ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ የልማት መነሳሳትን መፍጠሩን ጠቁመው፤ ለበርካታ ወገኖችም የስራ እድል ለመፍጠር ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ህዝቡ የኮሪደር ልማቱን በሙሉ ልብ በመደገፍ በባለቤትነት ስሜት እየተሳተፈ ነው ያሉት አቶ ቻላቸው ፕሮጀክቱን በፍጥነት ለማጠናቀቅም ምሽት ጭምር በፈረቃ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ በጥር ወር በታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በልዩ ድባብ ለማክበር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ለከተማው የቱሪስት ፍሰት ማደግም አዎንታዊ ሚናው ከፍ ያለ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በከተማው የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ህዝቡ የሰላሙና የልማቱ ባለቤት በመሆን የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል፡፡

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 08:40


የመንግሥት ሠራተኛው የፌደራል ስርዓቱን በመረዳት ማገልገል እንደሚኖርበት ተገለጸ

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

የመንግሥት ሠራተኞች ሀገራችን የምትከተለውን የፌደራል ስርዓትን በመረዳት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ምክትል ኮሚሸነር ወ/ሮ ስሜነሽ ውቤ ገለጹ።

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አስመልክቶ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለመጡ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደሮች የአሠልጣኞች ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

መድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት ወ/ሮ ስሜነሽ ውቤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙት የመንግሥት ሠራተኞች ሀገራዊ ለውጥ ያመጣውን መልካም ዕድል በመጠቀም እና ፌደራል ሥርዓትን በመረዳት የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ሕዝቡን ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ምክትል ከሚሸነሯ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ላለፉት 18 ዓመታት በተለያዩ ክልሎች አስተነጋጅነት በተለያዩ መርህ ቃሎች እና ዝግጅቶች ሲከበር እንደቆየ አስታውሰዋል ፡፡

ኢትዮጰያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቤት መሆኗን ያስታወሱት ምክትል ኮሚሽነሯ በሕብረብሔራዊ የፌደራል ስርዓት ላይ የሚሰጠው ስልጠና የፌደራል ሥርዓቱን ባለመረዳት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ገንቢ ሚና እንዳለው አስረድተዋል ፡፡

የስልጠናው ዓላማም በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ስር ያሉት የመንግሥት ሠራተኞች የፌደራል ሥርዓቱን መረዳት እንዲችሉ እና ብዝሃነትን ባከበረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እንደሆነ ምክትል ኮሚሽነሯ ተናግረዋል::

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ በላይ ወዲሻ በበኩላቸው በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ ያለው የሰዉ ኃይል ትልቅ የሀገር ሀብት መሆኑን በመግለፅ ስልጠናውን እስከ ታች ማውረድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ ኀብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ በሚል ርዕስ የሕገመንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማእከል ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር ኃይለየሱስ ታየ እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በአቶ በላይ ወዲሻ ፅሑፍ ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Addis Media Network-AMN

02 Nov, 07:53


ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከንግዱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከልን ጎበኙ

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት ከንግዱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከልን ጎብኝተዋል ፡፤

በጉብኝቱ የክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እና የንግዱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የገበያ ማዕከሉ አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ መሆኑንና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የህገ-ወጥ ደላሎችን ወሽመጥ የሚቆርጥ የዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ትግበራ ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።

ማዕከሉ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሰብልና ጥራጥሬ ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች እና ዕሴት የተጨመረባቸውን የፋብሪካ ምርቶች መሸጫና ማቆያ መጋዘኖችና ሱቆች እና ዘመናዊ መኪና ማቆሚያ ሥፍራዎችን ማካተቱንም አመልክተዋል።

አርሶ አደሮቻችን ከየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች ምርቶቻቸውን አምጥተው በማእከሉ እንዲሸጡም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

AMN (Addis Media Network)

25 Oct, 07:37


በ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የበርካታ ዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

AMN- ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም

በ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎችን በማሳተፍ የበርካታ ዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያ እና የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃግብር እያካሄደ ነዉ።

በክረምቱ በጎ ፈቃድ አገልግሎት 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መከናወኑ በመድረኩ ተገልጿል።

በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 18 መርኃ-ግብሮች የተከናወኑ ሲሆን፤ የቤት እድሳትና ግንባታን ጨምሮ የደም ልገሳ፣ ማዕድ ማጋራት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የትራፊክ አገልግሎትና ሌሎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በዚህም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ በጎ ፈቃደኞች ተሳትፈዋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ቃል ተግባራዊ የሚሆነው ፕሮግራሙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ የላቀ አበርክቶ እንደሚኖረው ተገልጿል።

አስር ዐበይት መርሃ ግብሮችንና 13 ንዑሳን ተግባራትን ያካተተው ይህ ፕሮግራም ከአንድ ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞችን ያሳትፋልም ተብሏል።

AMN (Addis Media Network)

25 Oct, 07:15


የሠራዊታችን ጥንካሬ የሀገር ጥንካሬ ነው:- አይሻ መሀመድ(ኢንጂነር)

AMN-ጥቅምት 15/2017 ዓ/ም

የሠራዊታችን ጥንካሬ የሀገር ጥንካሬ ነውና መላው ህዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ሊቆም ይገባል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ(ኢንጂነር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

117ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን “በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ(ኢንጂነር) በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ሠራዊቱ ለሀገሩ የከፈለውና እየከፈለ ላለው ዋጋ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፈተና ያለፈ የማይናወጥ ቁርጠኝነት የተላበሰ ሠራዊት በመሆኑ እንዲህ ባለው ቀን ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ሀገርን የመከላከልና የመጠበቅ ሥራ መቼም ቢሆን የሚያበቃ አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ፤ ሰራዊቱ እረፍት የማያውቅ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይህን የማያልቅ ሃላፊነት የተሸከመው ጀግናው ሠራዊትም የጥንካሬ ተምሳሌት ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል፡፡
የሀገር ደህንነት የሚረጋገጠው በጦርነት በሚገኝ ድል ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ባለው የማያቋርጥ ዝግጁነት በመሆኑ ሠራዊቱም ባለው ዝግጁነት ሁሉም ኩራት ሊሰማው ይገባል ነው ያሉት፡፡

AMN (Addis Media Network)

25 Oct, 07:14


117 ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው

AMN-ጥቅምት 15/2017 ዓም

117ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን "በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት!" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት በሃገር ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ወታደራዊ አታሼዎች የሠራዊቱን ታሪካዊ የጀግንነት አመጣጥ እና ያለፋቸውን ፈተናዎች እንዲሁም አሁን ላይ ሠላም እያሰፈነ የዘመናዊነት ግንባታ ሂደቱን እያረጋገጠ የሚሻገር ሠራዊት መሆኑን የሚያመላክት የፖናል ውይይት ተደርጓል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሠው ሠራሽና ተፈጥሯዊ መሠናክሎች ሳይበገር ባሕር ተሻግሮ የመጣን ጠላትም ሆነ የውስጥ ችግር ፈጣሪ ባንዳን እንደ አመጣጡ በመመለስ የሀገሩን፣ የሠንደቅ ዓላማውን እና የህዝቡን ክብር ያሥጠበቀ የሠላምና የልማት ኃይል የሆነ ሠራዊት መሆኑ ተገልጿል።

በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ራሱን እያሳደገና ጠላቱን እየመከተ አቅሙን እያጎለበተ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፣የሀገሩን ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ሁለንተናዊ ዝግጁነት እየገነባ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

AMN (Addis Media Network)

25 Oct, 07:13


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው ማሌዢያ ኳላላምፑር ገቡ

AMN-ጥቅምት 15/2017 ዓም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር ማሌዢያ ኳላላምፑር ገብተዋል ።

በብሪክስ ጉባኤ የነበራቸውን ቆይታ ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ለይፋዊ ጉብኝት ማሌዢያ ኳላላምፑር መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል ።

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 17:38


የአትሌት መዲና ኢሳ የ5000 ሜትር ውጤት በክብረወሰንነት ፀደቀ

AMN -ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም

የአትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የተመዘገበው ውጤት በክብረ-ወሰንነት መጽደቁን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ አትሌት መዲና ኢሳ በ14:21.89 በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በአትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከ20 ዓመት በፊት የተመዘገበው 14:30.88 የውድድሩ ክብረ-ወሰን እንደነበር የሚታወስ ነው።

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 13:50


https://youtube.com/live/EjCcqiCY0uI

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 09:33


አንድ ደላላ እና ሁለት ፈፃሚዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN - ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም


በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሰልፍ በመያዝ እና ተገልጋይ በመመዝገብ ገንዘብ የሚሰበስብ በፓርኪንግ ስራ ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና ከደላላ ጋር ተመሳጥሮ በሌብነት ላይ የተሰማራ አንድ የንግድ ቢሮ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

ለከተማ አሰተዳደሩ ከነዋሪ በደረሰ ጥቆማ መነሻ የኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ባደረገው ክትትል ካድረጉት የስልክ የድምፅ ልውውጥ ጋር በኤግዚቢትነት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

ፖሊስ ጉዳይ ላይ መረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እያደረገ ያለ ሲሆን፤ ጥቆማውን ለሰጠው ነዋሪ ምስጋና ማቅረቡን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 07:47


የሃይማኖት ተቋማት ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩና ትውልድን በስነ-ምግባር በሚያንፁ ስራዎች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ ተገለፀ

AMN - ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ጋር በመተባበር "ሀይማኖታዊ ምክክር ለሰላምና አብሮነት ያለው ፋይዳ" በሚል መሪ ሀሳብ ምክክር እያደረገ ነው።

በምክክሩም የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ዋና ጸሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት መወያየትና መመካከር ይገባል ብለዋል።

ተቋማቱ በውይይት የተለያዩ ችግሮችን መፍታት ችለናል ብለዋል ።

በሠላም እሴት ግንባታ፣ በስነ-ምግባርና የሞራል ግንባታ ላይ በማተኮር መመካከር እንደሚገባም መክረዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩና ትውልድን በስነ-ምግባር በሚያንፁ ስራዎች ላይ አተኩረው በመስራት ለትውልዱ አርዓያ መሆን ያስፈልጋል ሲሉም የሀይማኖት ተቋማቱ ጠቁመዋል ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፃዲቁ አብዶ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ዜጎች እርስ በርስ እንዳይተማመኑና እንዲጋጩ ሀይማኖትን እንደ መሳሪያ ይጠቀማሉ።

ለዚህ ደግሞ ክፍተት ባለመፍጠር መከባበርና መመካከር ይገባል ብለዋል ፕሬዝደንቱ።

የሁሉም ሀይማኖት ቅዱሳት መጽሀፍ እንደሚያዝዙን አንዱ በሌላው ክፉ ባለመስራት ለሰላም መቆም፣ አንዱ የሌላውን ሀይማኖት ማክበር ይገባልም ብለዋል።

በሄለን ጀምበሬ

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 07:21


እ.ኤ.አ. በ2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ስራዎች እንደሚፈጠሩ ተገለፀ።

AMN - ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በጋራ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለማዋል ያለመ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ያለመውን የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን አስመልክቶ የመጀመሪያውን አጠቃላይ ሪፖርት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።

የምጣኔ ሀብት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ተቋማቱ የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በተለይም በተለያዩ ሴክተሮች ምርታማነትን ለማሳደግ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከደንበኞች ጋር ለማስተሳሰር እና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

በ2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ስራዎች እንደሚፈጠሩ እና መንግስት ተጨማሪ 57 ቢሊዮን ብር ከታከሰ ገቢ እንደሚያገኝ ተገለፀ።

እ.ኤ.አ. በ 2023 ዘርፉ 700 ቢሊዮን ብር ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አበርከቶ 57 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ አስገኝቷል።

የኢትዮጵያ ሃገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት ፕሮግራም የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ማሻሻያ በዘርፉ ለሚስተዋለው እመርታ ትልቅ አስተዋጽዎ እያበረከተ መሆኑን Driving Digital Transformation of the Economy in Ethiopia በሪፖርቱ አመላክቷል።

በሪፖርቱ መሰረት የቴሌኮም ማሻሻያ እና የሞባይል ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች በግብርና ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በህዝብ አገልግሎቶች በመሳሰሉት ቁልፍ ዘርፎች እድገትን እንዴት እንደሚያበረታቱ እመላክቷል።

በዚህ መነሻነት እ. ኤ. አ. በ2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ስራዎች እንደሚፈጠሩ እና ለመንግስት ተጨማሪ 57 ቢሊዮን ብር ከታከሰ ገቢ ያስገኛሉ ተበሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በ 2028 ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ላይ ሊጨምር እንደሚችል ጂኤስኤምኤ በተባለ አለምአቀፍ ድርጅት በቀረበው አዲስ ሪፖርት ተመላክቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሩህ የሆነ የተሳሰረ የወደፊት ጉዞ ለማድረግ የጋራ ራዕይ መሰነቃቸውንም አመልክተዋል።


በአሸናፊ በላይ

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 06:51


ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከ23 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል፡- የስራና ክህሎት ቢሮ

AMN - ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በ2017 የትምህርት ዘመን ከ23 ሺህ 800 በላይ አዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ የተሟላ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስጠት የሚችሉ 14 ኮሌጆች ሰልጣኞችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም 23 ሺህ 800 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል ::

ምዝገባዉ ከጥቅምት 15 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በኦንላይን ይከናወናልም ብለዋል ምክትል ቢሮ ሀላፊው ::

ቢሮዉ በ2017 በጀት ዓመት ከሚሰጠው መደበኛ ስልጠና በተጨማሪ ከ300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አጫጭር ስልጠና እንደሚሰጥም ተናግረዋል ::

በቴዎድሮስ ይሳ

AMN (Addis Media Network)

24 Oct, 06:40


ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎች በመሰራታቸዉ ከተማዋ ሰላምና ጸጥታ የተረጋገጠ ሆኗል ፡- የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

AMN - ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎች በመሰራታቸዉ ከተማዋ ሰላምና ጸጥታዋ የተረጋገጠ እና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ማስቻሉን የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ።

ቢሮዉ የበጀት አመቱን ሩብ አመት አፈጻጸም ከህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ጋር ገምግሟል ።

የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ቢሮው 11 ሺህ ወጣት የሰላም ሰራዊት አሰልጥኖ ከነባር የሰላም ሰራዊት ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ፣ በከተማዋ የጫኝ እና አዉራጆችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግረዋል ።

ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የህብረሰብ ክፍሎችን በሰላም ዙሪያ ማወያየቱ በሩብ አመቱ ከነበሩ አንኳር ተግባራት መካከል መሆናቸዉን አንስተዋል ።

በተለይ ህብረተሰቡን ያማከሉ በርካታ ተግባራት መተግበራቸዉ የአዲስ አበባን ሰላም ማጠናከር ተችሏልም ብለዋል ።

የበጀት አመቱ ሩብ አመት በከተማዋ በርካታ የአደባባይ በአላትንና አለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን ያለምንም የጸጥታ ችግር ያከናወነችበት እንደነበርም አንስተዋል ምክትል ቢሮ ሃላፊዉ ።

ለዚህ ስኬት የህብረተሰብ አደረጃጀት የአንበሳዉን ድርሻ ተመጥቷልም ብለዋል ።


በአለማየሁ አዲሴ

AMN (Addis Media Network)

23 Oct, 09:28


በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ ላቀረቡ አመልካቾች አገልግሎቱ ከህዳር 1 ጀምሮ ይሰጣል-የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

AMN - ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ የክፍለሃገር መሸኛ አስገብተው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተገልጋዮች ያቀረቡትን መረጃ የማጥራት ሂደት ማጠናቀቁን የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ከህዳር 1 ጀምሮ ለመጀመር ዝግጅት መደረጉንም ኤጀንሲው ገልጿል።

በመሆኑም ከነገ ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ጀምሮ በነዋሪነት ለመመዝገብ ያመለከቱ ተገልጋዮች የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤት እስከ ጥቅምት 22 ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

ተገልጋዮች የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅና ምዝገባው በኤጀንሲው ጽ/ቤት የሚከናወን በመሆኑ የክፍለሃገር መልቀቅያ ባስገቡበት ወቅት ከጽ/ቤቱ የተሰጣቸውን ማስረጃ ይዘው እንዲቀርቡም ተጠይቋል፡፡

በዚህ የማጥራት ሂደት ያላለፈ አመልካች በነዋሪነት ተመዝግቦ አገልግሎት ማግኘት የማይችል በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዘውትር ከሰኞ እስከ እሁድ ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሳስቧል፡፡

AMN (Addis Media Network)

23 Oct, 08:48


ጥቂት ስለ ብሪክስ

👉የብሪክስ የመጀመርያው ስብሰባ እኤአ በ2009 በሩሲያ ነበር የተካሄደው

👉“ ብሪክስ” የሚለው መጠሪያ የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን የመጀመሪያ ፊደል በመጠቀም የተፈጠረ ነው።

👉የብሪክስ አባል አገራት 45 በመቶውን የዓለም ሕዝብ ይይዛሉ።

👉አምስቱ አገራት በጋራ ያላቸው ምጣኔ ሃብታዊ አቅም ደግሞ የዓለምን 28 በመቶ ይሸፍናል።

👉የብሪክስ አባል ሀገራት የጂ 20 አባላት ሲሆኑ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ደግሞ በህዝብ ብዛት፣ በቦታ እና በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከአለም አስር ግዙፍ ሀገራት መካከል የሚያሰልፋቸው ነው።

👉አባል አገራቱ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ ለመሠረተ ልማት እና ለዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች ሃብት የማሰባሰብ ዓላማ ያለውን ‘ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ’ (ኤንዲፒ) በ2014 አቋቁመዋል።

👉መቀመጫውን ሻንግሃይ ቻይና ያደረገው ይህ ባንክ ትኩረቱን በንጹህ ኃይል፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣ በውሃ እና ንጽህና፣ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ማኅበራዊ መሠረተ ልማት ላይ ያደረገ ነው።

👉ባንኩ በአባል አገራቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የመሠረተ ልማት የገንዘብ አቅርቦት ክፍተት ለመፍታት ያለመ ነው።

👉ኢትዮጵያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን እና አርጀንቲና የብሪክስ አባል ሀገር ሆነዋል።

ከብሪክስ ዋና ዋና ግቦች መካከል ጥቂቶቹ

👉ንግድን ማበረታታት፣ በአባላት መካከል እድገትና ትብብርንና የ BRICSን የገበያ ተደራሽነት ማሻሻል።

👉ለአባል ሀገራት መሰረተ ልማቶች እና የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን መፍጠር።

👉በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ንግግሮችን እና ቅንጅቶችን ማጠናከር፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ልውውጦችን፡ የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ማሳደግ እና አንዱ ለሌላው ባህል መከባበር እና በአባል ሀገራት መካከል ማህበራዊ እና ባህላዊ ልውውጦችን ማሳደግ።

👉በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ዘርፎች አለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ በአባል ሀገራት መካከል የእውቀት ልውውጥን፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ እድገቶችን ማጠናከር።

👉ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በጋራ በመስራት ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እና ዘላቂ የልማት ዘዴዎችን ማስተዋወቅ።

👉እንደ ሽብርተኝነት ያሉ የጋራ የደህንነት ጉዳዮችን እና ስጋቶችን በመፍታት ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነትን በአባል ሀገራትና በአለም አቀፍ ደረጃ ማረጋገጥ።

👉በታዳጊ አገሮች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማካፈል እና ለሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ የSouth-South Cooperation ውጥኖችን መደገፍ ናቸው።

ምንጭ:ቢቢሲ እና ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም

AMN-ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

AMN (Addis Media Network)

22 Oct, 18:38


ይገምቱ፤ ይሸለሙ!

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት 4:00 አርሴናል ከሻካታር ዶኔሽክ የሚያደርጉትን ጨዋታ ትክክለኛ ውጤት ይገምቱ፤ ይሸለሙ!

ትክክለኛ ግምታቸውን በቴልግራም ቻናላችን ብቻ ቀድመው ላስቀመጡ 3 ገማቾች፣ ለእያንዳንዳቸው የ500 ብር የሞባይል ካርድ ሽልማት!

የጨዋታው መስፈርት

የቴሌግራም ቻናላችንን መቀላቀል እና ትክክለኛውን ውጤት ቀድመው በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ ማስቀመጥ።

እስከ 4:30 ባለው ሰዓት ትክክለኛ ግምት ያስቀመጡ ተከታዮቻችን ብቻ ሽልማቱን ያሸንፋሉ፤ ኤዲት የተደረገ ግምት ተቀባይነት አይኖረውም።

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ - የትውልድ ድምፅ!

AMN (Addis Media Network)

22 Oct, 15:26


የዶሮአችሁ ጩኸት ረበሸኝ በሚል የተከሰሱት ጥንዶች

AMN - ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

በፈረንሳይ አይዜር በቦርጎይን ጃሊዩ ነዋሪ የሆኑ ጥንዶች ሪኮ የተባለው ዶሮአቸው ኃይለኛ ጩኸት ረብሾኛል ሲሉ ጎረቤታቸው ያሰሙትን ቅሬታ ተከትሎ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ ሊታይ ቀጠሮ ተይዟል።

"ትኩረት ማድረግ ያለመቻል፣ እንቅልፍ ማጣት፣ በድምፅ መታወክ" እነዚህ በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት ጥር ወር ላይ የሪኮን ባለቤቶች ወደ ፍርድ ቤት ያስጠሯቸው ከሳሽ ከጠቀሷቸው የክስ ነጥቦች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት እና የዶሮው ባለቤቶች ጎረቤቶች አንዱ፤ “አውራ ዶሮው ማታም ሆነ ቀን እንደጮኸ አደንቁሮናል” ሲሉ ያማርራሉ።

ይሁን እንጂ የ5 ዓመቱ ዶሮ ባለቤቶች፤ ሪኮ የተባለው ዶሮ የማደሪያው በር በክረምት ወራት ከጠዋቱ 2፡30 ላይ፣ በበጋ ወራት ደግሞ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ብቻ መክፈት የሚያስችል ዘዴ የተገጠመለት ነው ሲሉ በቅሬታው ዙሪያ ከጎረቤቶቻቸው ጋር እንደሚከራከሩ ተነስቷል።

የሪክ ባለቤት የሆኑት ፍራንክ፤ ዶሮው ጠዋት በሩብ ሰዓት ውስጥ አሥራ አምስት ጊዜ፣ ከዚያም በቀን ውስጥ ጥቂት ጊዜ ይጮኻል በማለትም ፈርጠም ብለው ይከራከራሉ።

ከ25 ዓመት በፊት ለየት ያለ የአኗኗር ዘይቤ ለመምራት ከከተማ ወደ ቦርጎይን ጃሊየ የተባለው አካባቢ የተዛወሩት ጥንዶቹ በጎረቤቶቻቸው በደረሰባቸው ክስ በጣም ደንግጠዋል።

ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ በመንደሩ በሚገኝ አዳራሽ ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት ቢሞክሩም ጎረቤቶቻቸው ግን አሻፈረኝ ብለው ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዷቸው መወሰናቸው ተመላክቷል።

ፍራንክ ከከሳሹ በስተቀር ከሌሎቹ ጎረቤቶቻቸው ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፤ በሪክ ጩኸት ችግር እንዳላጋጠማቸው እና ይልቁንም ዶሮው ሲጮኽ መስማት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ኦዲቲ ሴንትራል በዘገባው አንሥቷል።

ይሁንና ክስተቱ ለሪኮ የማኅበራዊ መገናኛ ባዙኃን ድጋፍ እንዲያገኝ ዕድል ፈጥሮለታል፤ ሰዎች ጩኸቱን እንዲቀጥል የሚያበረታቱበት የፌስቡክ የድጋፍ ገጽ ተዘጋጅቷል፣ ጩኸቱን የሚቃወሙ "ዝማሬውን" ካልወደዱት ከአካባቢውን እንዲለቅቁም ነው አስተያቶች እየተሰነዘሩ መሆኑ ነው የተነገረው።

AMN (Addis Media Network)

22 Oct, 10:03


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር ራሺያ ገቡ

AMN- ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ለብሪክስ ጉባኤ በካዛን ራሺያ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

AMN (Addis Media Network)

22 Oct, 09:15


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

AMN - ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የእሳት ቃጠሎ የደረሰበትን ሕንፃ ግማሽ አካልን ከአደጋው ማትረፍ ተችሏል።

የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ አደጋውን ለመቆጣጠር እና አደጋው እንዳይዛመት ያደረጉት የተቀናጀ ርብርብ የሚመሰገን መሆኑንም ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሠራም አቶ ሞገስ ገልጸዋል።

በዳንኤል መላኩ

AMN (Addis Media Network)

21 Oct, 20:41


መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN - ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ የእሳት አደጋዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ርብርብ ላደረጉ፤ በርካታ ሎጀስትክ በማቅረብ የደገፉ እና ከዚህ በላይ ሊደርስ የነበረዉን ጉዳት የቀነሱ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና መንስኤዉን በማጣራት ቀጣይ ለህብረተሰቡ የምናሳዉቅ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡

AMN (Addis Media Network)

21 Oct, 16:58


ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ አቅም እንዳላት አይተናል- የቀድሞ የአፍሪካ እግር ኳስ ከዋክብት

AMN - ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ አቅም እንዳላት መመልከታቸውን የቀድሞ የአፍሪካ እግር ኳስ ከዋክብት ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሳተፉበት የወዳጅነት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄዷል።

ከ46ኛው የካፍ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተያዙ መርሐ ግብሮች አንዱ የሆነው የወዳጅነት ጨዋታው በአዲስ መልክ በታደሰው በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው የተከናወነው።

በወዳጅነት ጨዋታው ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ፣ የአፍሪካ የቀድሞ አግርኳስ ተጫዋቾች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋቾች እና የካፍ ስራ አስፈፃሚዎች ተካፍለዋል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የቀድሞው የአፍሪካ እግር ኳስ ከዋክብት መካከል የሆኑት አልሀጂ ዲዩፍ እና ጄጄ ኦካቻ ፣ ኢትዮጵያዊያኖች እግር ኳስን አብዝተው ይወዳሉ፣ ፍቅርና መልካም አቀባበልንም አሳይተውናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ አቅም እንዳላት መመልከታቸውን የገለጹት ከዋክብቱ ለዚህም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የእግር ኳስና የታላቅ ህዝብ ሀገር በመሆኗ የአፍሪካን ዋንጫን የማስተናገድ እድል ሊሰጣት ይገባልም ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

AMN (Addis Media Network)

21 Oct, 14:48


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሳተፉበት የወዳጅነት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናወነ

AMN - ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሳተፉበት የወዳጅነት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል፡፡

ከ46ኛው የካፍ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተያዙ መርሐ ግብሮች አንዱ የሆነው የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ በአዲስ መልክ በታደሰው አዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል።

በወዳጅነት ጨዋታው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ /ዶ.ር/ ፣ የአፍሪካ የቀድሞ አግርኳስ ተጫዋቾች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋቾች እና የካፍ ስራ አስፈፃሚዎች ተካፍለዋል።

ከቀድሞ አፍሪካውያን ኮከቦች መካከል ጄጄ ኦካቻ ፣ ሳሙኤል ኤቶ ፣ አልሐጂ ዲዩፍ እና ካሉሺያ ቡዋልያ ተጫውተዋል። በኢትዮጵያ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መካከል ሳላሃዲን ሰይድ ፣ አዳነ ግርማ ፣ ምንያህል ተሾመ በጨዋታው ተሳትፈዋል።

በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ የተመራው ጨዋታ 10 ግቦች ተቆጥሮበት ተጠናቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አንድ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

ከጨዋታው በኋላ ሃሳባቸውን የሰጡት ጄጄ ኦኮቻ ፣ አልሃጂ ዲዩፍ እና ካሉሺያ ቡዋልያ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የወዳጅነት ጨዋታውን በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

32,305

subscribers

27,060

photos

1,111

videos