ትምህርት መረጃ( academic info) @academic_info Channel on Telegram

ትምህርት መረጃ( academic info)

@academic_info


ትምህርትነክ እና ትክክለኛ መረጃዎች ይስተናገዱበታል።

ትምህርት መረጃ( academic info) (Amharic)

የታሪክ ቅጾች እና ስለዚህ የተለያዩ የትምህርት መረጃዎችን በተመለከተው ቦታ አስተካክላችሁ። ይህ መረጃው በመስመር ስሞችና ምርት ስንት የምስላቸው ተቋም እንደሆነ ይከፈትሉ። ይህ ትምህርት መረጃ በምንዝህ ነገሮችን በግልፅና በቀጥታ ወደ ታሪክ መጨመሩ። የዚህ መረጃ ትምህርትነክ እና ትክክለኛ መረጃዎች ይስተናገዱበታል። በመረጃው በተመለከተበት ቀን ስፖርትላይዜ እና ተጠናቋዩን ትምህርት መሰረታችንን እንድናገፈ ማንም በተመለከተበት ቀን የሚጠቀመው በኤፍ ኤም (academic info) ገና ይገኛል።

ትምህርት መረጃ( academic info)

05 Dec, 12:57


ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የስራ ማስታወቂያ

ትምህርት መረጃ( academic info)

03 Dec, 04:16


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12,000ሰራተኞቹን ሊቀንስ መሆኑ ተሰምቷል::
ምንጭ:መሠረት ሚዲያ

ትምህርት መረጃ( academic info)

27 Nov, 16:07


መምህር በመሆኔ አዘንኩ” - የኢትዮጵያ መምህራን እሮሮ

በደቡብ ምዕራብ ክልል ካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ለልማት በሚል መምህራን “ያለፈቃዳቸው” የአንድ ወር ደሞዛቸው ለመዋጮ እንደተቆረጣባቸው ገልጸዋል።

መምህራኑ “ለገጠር መንገድ ግንባታ” ይውላል የተባለ እና በአንድ ዓመት የሚቆረጥ የአንድ ወር ደሞዝ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ “በጅምላ” እና “በማን አለብኝነት” መቆረጡን ይናገራሉ።

“ከ50 በመቶ በላይ [የመንግሥት ሠራተኞች] ደገፉት ስለተባለ በጅምላ ይቆረጣል” ተብሎ መወሰኑን የተናገሩ አንድ የአንደኛ ደረጃ መምህር፤ ፈቃደኝነታቸው እና አቅማቸው ውሳኔው ላይ ሚዛን እንዳልደፋ ተናግረዋል።

“መምህራን የልማት ተቋዳሽ አይደሉም ሳይሆን፤ አቅማችን የማይፈቅደውን አትጠይቁን ነው እያልን ያለው” ሲሉ አንድ መምህር ምሬታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

መዋጮው መምህራን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልሆነ የጠቆሙ ሌላ መምህር አነስተኛ ገቢያችንን እና የኑሮ ጫናን አገናዝቦ “በአቅማችን ይሁን” የሚል ሀሳብ እንዳለ ተናግረዋል።

“የአራት ሺህ ብር ደሞዝተኛ ነኝ። አራት ሺህዋን ብር ከምትወስዱብኝ እባካችሁ 1500 ብር በእጄ ልስጣችሁ [ብዬ] ለመንኩ” ብለዋል የወረዳው ባሺ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር።

“እርዳታ ነው፤ አስተዋጽኦ ነው፤ ለልማት አሻራችሁን አሳርፉ ነው የሚባለው። ሰው በቻለው ነው። . . . የሚችል ነው የሚደግፈው” ሲሉ በአቅማቸው ለማዋጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም የወረዳው አስተዳዳሪዎች ግን “የአንድ ወር ደሞዝ ሙሉ ካልሆነ አይቀበሉም” ብለዋል።

የጥቅምት ወር ደሞዝ የተቆረጠባቸው መምህራን አቤቱታ ለማቅረብ ወደ መንግሥት ተቋማት ሲያቀኑ እንግልት እንደደረሳቸው አንድ መምህር ሲናገገሩ፤ ሌላ መምህር ደግሞ “በፖሊስ ታፍነን ነበር” ብለዋል።

“ሰርቆ እንደሄደ ሰው [በፖሊስ] ታጅበን ነው የሄድነው” ሲሉ አንድ መምህር ክስተቱን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በወረዳው ለሁለት ቀናት ያህል ትምህርት ተቋርጦ እንደነበር የተናገሩት መምህራን፣ ከዞኑ አስተዳደር ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው ስለተነገራቸው ማስተማር መጀመራቸውን ተናግረዋል።

“መምህር በመሆኔ በጣም ነው ተቆጨሁት። መምህር ከወር ደሞዝ ውጪ የሚያገኘው አንዳች ነገር የለም። አዲሱ ክልል ከተመሠረተ ወዲህ እስከ 50 ቀን ድረስ ቆይቶ ነው ደሞዛችን የሚከፈለን። ይህን ታግሰን፤ ሆድ እና ጀርባችን ተጣብቆ፣ ስቃይ አይተን ደግሞ ይሄ ደሞዝ ሲቆረጥ፤ መብታችንን ማንም ሳያስከብርልን ሲቀር. . . መምህር በመሆኔ በጣም አዝናለሁ” ሲሉ በምሬት ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

ትምህርት መረጃ( academic info)

26 Nov, 09:39


ደምወዝ አልተከፈለንም ያሉ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ ☄️☄️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን፣ የጥቅምት ወር ደምወዝ አልተከፈለንም ያሉ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በርካታ የአንደኛና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ሥራ አቁመው ተማሪዎቻቸውን በትነዋል። በወረዳው ቀዩ ዳሪያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ካንድ ወር በፊት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ትምህርት ቤቱ ወድሟል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሐይ ወረዳም፣ የጥቅምት ወር ደምወዝ ይከፈለን ያሉ በርካታ መምህራን መታሠቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ጊምቢቹ ከተማ አስተዳደርም፣ መምህራን በተመሳሳይ ጥያቄ ሥራ አቁመው ተማሪዎቻቸውን እንደበተኑ ዋዜማ ተረድታለች። #Wazema

ትምህርት መረጃ( academic info)

23 Nov, 16:25


አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ሙሉ ዶክመንት

ትምህርት መረጃ( academic info)

19 Nov, 12:51


የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ለመፈተን እየተዘጋጀሁ ነው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ

ትምህርት ሚኒስቴር ባሻሻለው ስርዓተ ትምህርት መሠረት የመውጫ ፈተና በሚል ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና መስጠት መጀመሩ ይታወቃል። በዚህ መመዘኛም የማለፊያ ውጤት ሳያመጡ የሚቀሩ #ተመራቂ_ተማሪዎች ቁጥርም ጥቂት የሚባል አይደለም።

ይህንን ተከትሎም ብዙዎች መጀመሪያ መመዘን ያለበት መምህሩ ነው፤ ተፈትኖ ብቃቱ በታወቀ #መምህር የተማረን ተማሪ ነው መፈተን የሚገባው ሲሉ ይደመጣሉ። ሸገር ራዲዮ ይህንን ጥያቄ ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘንም ፈተና ሊፈትናቸዉ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሰምቷል።

ይህንን የነገሩን በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ናቸው።‘’የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም’’ ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለ #ከፍተኛ_የትምህርት_ተቋማት_መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

እስካሁን ባለው ስርአት የዩኒቨርስቲ መምህራን ማስተማር ከመጀመራቸው በፊት ያለው አንድ ዓመት፤ እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት እንዲያገኙ ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህ በቂ ስላልሆነ ማሻሻያ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።
#ሸገርኤፍም #MoE

ትምህርት መረጃ( academic info)

15 Nov, 16:07


2025 Berlin Fellowship Program in Germany 🇩🇪 (Fully Funded)

Fully Funded 6 Months Fellowship in Germany for International Applicants.

The Program Covers Airfare, Meals, Accommodation, Monthly Stipend, Living Expenses, Health Insurance.

Visit: https://carraadesk.com/2025-berlin-fellowship-program-in-germany/

ትምህርት መረጃ( academic info)

04 Nov, 12:37


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን
Website: https://placement.ethernet.edu.et 
Telegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia

ትምህርት መረጃ( academic info)

28 Oct, 13:54


#Update

🔵 “ መምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን ” - የወላይታ ዞን መምህራን

🔴 “ ከ10,500 በላይ መምህራን ደመወዝ አልተፈጸመላቸውም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ በፓሊስ መታሰራቸው ” ተሰምቶ ነበር።

የደመወዝ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ የመብት ጥያቄ ለማንሳት ባደረጉት ፒቲሽን የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ነበር ፓሊስ “ አመጽ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል። የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል ” በሚል ያሰራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የታሰሩት መምህራን ተፈቱ ? የደመወዝ ቅሬታችሁስ መፍትሄ አገኘ ? ሲል ዛሬ ቅሬታ ያላቸው መምህራንን ጠይቋል።

ምን መለሱ ?

“ ምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። ሦስቱም መምህራን ተፈትተዋል። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን።

‘ መንግስትን ከሕዝብ አጣልታችኋል ’ የሚለው ክስ በፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም መረጃ የላቸውም። ከዚያ ጋር ተያይዞ ነው ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው።

የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።

አሁንም ደመወዝ እንዲከፈለን እንፈልጋለን።

መምህራን ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ሥራ ስለሚሰሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በትክክል እንዲተገብሩ ደመወዝ መከፈል አለበት።

የሐምሌ ደመወዝ እስካሁን አልተከፈለም። ለመምህራንና ለጤና ባለሙያ 40 በመቶ፣ ለፓሊስ 20 በመቶ እንጂ ከዚህ ውጪ ደመወዝ አልተከፈለም።

አሁን እንደገና አጠቃላይ የትምህርት ባለሙያም ወደታች ወርዶ ‘የሐምሌን ደመወዝ እንከፍላለን’ በማለት አመራርም በአጠቃላይ ተረባርቦ መምህራን ወደ ስራ አስገብተዋል።

ፍርድ ቤትም ገና የራሱን ቀጠሮ እየሰጠ ነው የሐምሌ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት ” ብለዋል።

ደመወዛቸው በወቅቱ አለመፈጸሙ ትልቅ ጥፋት ሆኖ እያለ ይህንኑ ቅሬታ መምህራን ታስረው መቆዬታቸው ግፍ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም በዚሁ ቅሬታ ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ የክልሉና የዞኑን መምህራን ማኀበር ጠይቋል።

የክልሉ መምህራን ማኀበር የመምህራንን መታሰር በተመለከተ እስካሁን ሪፓርት እንዳልተደረገለት/ቅሬታ ያደረሰው አካል እንደሌለ ገልጾ፣ በይበልጥ የዞኑ መምህራን ማኀበር እንዲጠየቅ አሳስቧል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወላይታ ዞን መምህራን ማኀበር ሊቀ መንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ፣ “ በቅርቡ ታስረዋል ስለተባሉት መምህራን ለኛ ኦፊሻሊ የቀረበልን ምንም መረጃ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ያመለከተልን አካል የለም። ከውጪ ወሬ ነው እየሰማን ያለነው። ወደ አክሽን እንዳንገባ የመጣልን መረጃ የለም ” ያሉት ሊቀመንበሯ፣ “ እንነጋገርበት ወደኛ መምጣት ይችላሉ ” ብለዋል።

የደመወዝ ክፍያን ቅሬታ በተመለከተም በሰጡን ምላሽም፣ ከ10 ሺህ 500 በላይ መምህራን ደመመወዝ እንዳልተፈጸመላቸው ገልጸው፣ ማኀበሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

የክፍያ አለመፈጸምን በተለመከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከዚህ ቀደም የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎደና፣ “ አራት ወረዳዎች ላይ መሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው ” ብለው ነበር።

@tikvahethiopia

ትምህርት መረጃ( academic info)

28 Oct, 13:38


‹‹በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ናቸው የተከፈቱት›› የዞኑ ትምህርት መምሪያ

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ትምህርት እየተሰተባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ  በዘንድሮ ትምህርት ዘመን 710 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ መመዝገብ የቻሉት 70 ሺህ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተከፍተው ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤቶችም ከችግሮች የጸዱ አይደሉም ያሉት አቶ ጌታሁን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሕጻናት በየመንገዱ “መጽሐፍና ደብተራቸው እየተቀደደባቸው እና እየተደበደቡ አልቅሰው ይመለሳሉ” ብለዋል።

ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንደላኩ የተሰማባቸው ወላጆችም እስከ “15 ሺህ ብር ቅጣት፣ ድብደባን ጨምሮ እስከ ግድያ የደረሰ ግፍም እንደተፈጸመባቸው” የትምህርት መምሪያ ኃላፊው ለአሚኮ ተናግረዋል።

አቶ ጌታሁን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቤት ሲውሉ በተለይም ሴት ልጆች “ያለዕድሜ ጋብቻ እየተፈጸመባቸው ነው” ሲሉ ገልጸው ወንዶቹም ቢኾኑ ዘመን በወለደው አጓጉል ቦታ እየዋሉ ለወላጆቻቸው የጭንቀት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።

ትምህርት መረጃ( academic info)

25 Oct, 00:40


በ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር ብቻ የሚሰጥ ይሆናል

ትምህርት መረጃ( academic info)

24 Oct, 17:13


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የ2017 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ በተለያዩ ዞኖች በአግባቡ አለመጀመሩ ተገለፀ፡፡

በክልሉ የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስካሁን በአንዳንድ ትምህር ቤቶች ትምህርት አለመጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ከግል እና ከጥቂት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውጪ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች እንዳልተከፈቱ፣ ቢከፈቱም ከሁለት በላይ መመህራን ስለማይገቡ ትምህርት አለመጀመሩን አስተያየታቸውን ለቮኦኤ የሰጡ ወላጆች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በወላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን፣ በኮንሶ ዞን እና በጎፋ ዞን በሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚያስተምሩ በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ደመወዝ በወቅቱ እንደማይከፈል የክልሉ መምህራን ማኅበር ገልጿል።

በዞኖቹ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን መኖራቸውን የገለፁት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ፤ መምህራኑ በጣም በመቸገራቸው ኑሯቸውን ለመደጎም የቀን ሥራ ጭምር እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

መምህራኑ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ ሲያቀርቡ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና እስራት እየተፈፀመባቸው እንደሆነም ወላጆች እና መምህራን ገልፀዋል፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣ ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደመወዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ መግለፁ ይታወሳል፡፡ #VOA

ትምህርት መረጃ( academic info)

24 Oct, 13:03


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። #MoE

ትምህርት መረጃ( academic info)

22 Oct, 11:48


በኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ፈቃድ ያላቸው አለም አቀፍ እና የማህብረሰብ ት/ቤቶች ዝርዝር
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም   -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ

ትምህርት መረጃ( academic info)

21 Oct, 17:31


የደሞዝ ጭማሪ