Ministry of Education Ethiopia @ethio_moe Channel on Telegram

Ministry of Education Ethiopia

@ethio_moe


This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ministry of Education Ethiopia (English)

Are you looking for the latest updates and information from the Ministry of Education in Ethiopia? Look no further than the official Telegram channel, @ethio_moe! This channel is your one-stop destination for news, announcements, and important updates directly from the Ministry of Education. Stay informed about new education policies, initiatives, and programs that are being implemented in Ethiopia. Whether you are a student, parent, teacher, or education enthusiast, this channel is a valuable resource for staying connected with the education sector in Ethiopia.
Be sure to also visit the official Ministry of Education Facebook page at www.facebook.com/fdremoe for even more updates and information. Join the @ethio_moe Telegram channel today and stay informed with the latest news and updates from the Ministry of Education in Ethiopia!

Ministry of Education Ethiopia

10 Jan, 08:25


ማስታወቂያ
የድህረምረቃ ፕሮግራሞች (NGAT) የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ የተመዘጋባችሁ በሙሉ ይህንን ሊንክ ( https://ngat.ethernet.edu.et) በመጫን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

Ministry of Education Ethiopia

08 Jan, 13:13


ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የድርሻውን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ።
===========================
(ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛና በአገራችን ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም!!” በሚል መሪ ቃል በተከበረው ቀን ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በውይይት መድረኩ ባቀረቡት ገለጻ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተፈጠረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሻሻሎች ቢኖሩም በማህበረሰባችን ላይ በርካታ ጾታዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም በሚገባ ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በአጠቃላይ ትምህርትም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበር የጸረ ጾታዊ ጥቃት መመሪያ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን አንስተዋል፡፡

ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ጨምረውም ጾታዊ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ መከላከልና ግንዛቤ መፍጠር የመጀመሪያ ርምጃ መሆኑን ጠቅሰው ተፈጽመው ሲገኝ ለተጠቂው አካል የህክምና፣የሥን፟ልቦናና የፋይናንስ ድጋፍ ከማድረግ ጎን ለጎን አጥቂው አካል የሚፈጸመውን ወንጀል የሚመጥን ቅጣት እንዲያገኝ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።


በውይይት መድረኩ የተገኙ ወንዶች ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ነጭ ሪቫን በማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ውይይት ተካህዶ፣ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የነጭ ሪቫን ቀን ቀደም ሲል በትምህርት ማህበረሰቡ ሲከበር የቆየ ሲሆን ይህ የማጠቃለያ ውይይት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

Ministry of Education Ethiopia

04 Jan, 11:27


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚገባ ተጠቆመ፡።
…………………………………………………………………………
(ታህሳስ 26/04/2017 ዓ.ም) ከ47 ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች ስልጠና ተሰጥቷል።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተወካይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሃንዲሶ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፣ ሙያዊ ፣ ሳይንሳዊና ችግሮችንም በአግባቡ የሚፈቱ ሊሆን ይገባል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DWPGFwYMo/

Ministry of Education Ethiopia

04 Jan, 11:24


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጋምቤላ ክልል የሚስተዋለውን የትምህርት ጥራት ችግር ለማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና የካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ።
-------------------------------
(ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በጋምቤላ ክልል የትምህርት ጥራት በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ዑሞድና ካቢኔዎቻቸው በተገኙበት ምክክር አካሂደዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘይ ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/15sd44DPED/

Ministry of Education Ethiopia

03 Jan, 14:01


በጅማ፣ በአጋሮና በኮንታ ዞኖች የት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች መጀመራቸው ተገለጸ።
------------------------------------------

(ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም) በዘጠኝ ቀጠናዎች ተከፋፍሎ በመካሄድ ላይ ያለው የት/ቤቶች የስፖርት ውድድር ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ቀጣና የተደለደሉት በጂማ ፣ በአጋሮ፣ በካፋ እና በኮንታ ዞኖች ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ውድድር ጀምረዋል።

በስፖርታዊ ውድድሩ ተስፋ ሰጭ የተማሪዎች ክህሎቶች የታዩ ሲሆን ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውድድሩ ወቅት ተገልጿል።

በዚሁ አደረጃጀት ስር የሚገኘው የጋምቤላ ክልል የማጃንግ ብሔረሰብ ፣ የኑዌርና የአኝዋ ብሔረሰብ ዞኖች ትምህርት መምሪያዎች ከክልሉ ት/ቤቶች ስፖርት ሊግ ባለሙያዎች ጋር በውድድሩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን በቅርቡም ውድድሩ በሁሉም ት/ቤቶች እንደሚጀመር ታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ስር ያሉ ት/ቤቶችን በዘጠኝ ቀጠናዎች ከፍሎ ውድድር ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።

Ministry of Education Ethiopia

03 Jan, 05:46


ዩኒቨርሲቲዎች እውቀትና እውነት የሚገበይባቸው ትክክለኛ የማስተማሪያና የምርምር ተቋማት ሊሆኑ ይገባል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።
------------------//-----------------------------------
(ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም) የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው አመት የአመራር ለውጥ በማድረግ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ምን ለውጥ አመጣ በሚል የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአካባቢያዊና በመንደር የሚመድቡበት ሥርዓት መቆም አለበት በሚል በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን አንስተዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/15dvdQt6Hu/

Ministry of Education Ethiopia

02 Jan, 06:42


ውድ መምህራን
መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ
https://forms.gle/NTMzLQK6pohUpvkq6

Ministry of Education Ethiopia

30 Dec, 12:48


የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመመዝገን ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET

Ministry of Education Ethiopia

29 Dec, 06:32


የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን ማጠናከር ለመደበኛ ትምህርት መሻሻል ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
……………………………… // …………………………….
ሀገር አቀፍ የመሰረተ ትምህርት ቀን “የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ለጋራ መግባባትና ሰላም “በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደ ሀገር የጎልማሶች ትምህርት አፈጻጸም በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉን ጠቅሰው ይህንን ዘርፍ ማጠናከር ለመደበኛ ትምህርት መሻሻል ሚናው የጎላ እንደሆነ ጠቁመዋል። ሙሉው መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/18LhCBqLMs/

Ministry of Education Ethiopia

27 Dec, 05:47


የሙያና ተግባር ትምህርት ለሚያስተምሩ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
…………………………… // …………………………

(ታህሳስ 18/2017) የትምህርት ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል የሙያና ተግባር ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን በአስራ ዘጠኝ የስልጠና ጣቢያዎች አራት ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየሠጠ ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/1AKexTYj6X/

Ministry of Education Ethiopia

25 Dec, 15:02


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአገሪቱን እድገትና የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
--------------------- // -------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባ ሰባት (47) የመንግስተት ዩኒቨርስቲዎች ጋር በ2017 የሚተገበር ቁልፍ የአፈጻጸመም ውል ተፈራርሟል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስምምነቱ ወቅተት እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው ምርምሮችና የሚያፈሯቸው ዜጎች አገር የሚለውጡና ከዓለም ጋር ተወዳድረው ማሸነፍ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ያግኙ። https://www.facebook.com/share/p/1EsCqztYFf/

Ministry of Education Ethiopia

24 Dec, 11:32


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ስራ በውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው።
…………………………………… // ……………………………..
በትምህርት ሚኒስቴርና በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ነገ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም የሚፈረመው ስምምነት ተቋማት ብቃትና ችሎታ ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ሂደት ውስጥ ተጠያቂነትን ከማስፈን ባለፈ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/1DBLkMNhYa/

Ministry of Education Ethiopia

23 Dec, 11:03


የት/ቤቶች ስፖርት ውድድር ለሀገራዊ ስፖርት ውጤታማነት የላቀ ሚና እንዳለው ተጠቆመ።
-------------------- // -------------------
(ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም) የ2017 የት/ቤቶች የስፖርት ውድድር ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መሰረተ ልማትና አገልግሎት ዴስክ ሃላፊ አቶ ታየ ግርማ እንደገለጹት የት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድርን ማጠናከር ሳይቻል ሀገራዊ የስፖርት ውጤት መጠበቅ አይቻልም።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫሙ። https://www.facebook.com/share/p/19xVnQPMZj/

Ministry of Education Ethiopia

13 Dec, 12:42


የትምህርት ሚኒስቴር ከICDL Africa እና kepler ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም) ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን የዲጂታልና ሶፍት ሰኪል በማጎልበት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በሂደትም የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትብብርን በማሳደግ ምሩቃን የተሻለ ክህሎት እና የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ያለባቸውን የዲጂታልና ሶፍት ስኪል ክህሎት ክፍተቶች በመለየት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስተር ድኤታው አክለው እንደገለጹት የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ጋር ያላቸውን ትስስርና ትብብር በተለየ መልኩ ለመደገፍ እገዛ እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

የአይሲዲኤል አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶሎንዥ ኢሚዩሊሳ በበኩላቸው ድርጅታቸው አፍሪካውያን ተገቢውን የዲጂታል ክህሎት የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራ ደርጅት መሆኑን በመጥቀስ ባለው አቅም ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኪፕለር ዳይሬክትር በበኩላቸው የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን በመደገፍና በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

Ministry of Education Ethiopia

12 Dec, 16:51


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጀኔራል ዋቁ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
----------------------//--------------

(ታህሳስ 03 / 2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የሚገኘውን ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የሚፈልገው ጥረት መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ተማሪዎች ጠንክረው መማርና ማጥናት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በትምህርት ሥርዓቱ የፈተና አስተዳደር ስርዓቱን ማስተካከል ያስፈለገው የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ሀገር የሚረከቡ እውነተኛ ዜጎችን ለማፍራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኩረጃ ለጊዜው የሚጠቅም ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሄዶ ሄዶ ራስንም ሀገርንም ይጎዳል ያሉት ሚኒስትሩ ኩረጃን የሚጸየፉ በራሳቸው የሚሰሩና የሚተማመኑ ተማሪዎች መሆን እንዳለበቸውም አሳስበዋል።

የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ትውልዱ ይህችን ሀገር የመገንባት የወደፊት ሀላፊነቱን በታማኝነት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በትምህርት ሴክተሩ እየተከናወኑ መሆኑንም አብራርዋል ።

አክለውም ነገ ብቁ ሀገር ተረካቢ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲማሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለበለጠ መረጃ
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ።

Ministry of Education Ethiopia

09 Dec, 09:19


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
------------------- // -------------------

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ያደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።

Ministry of Education Ethiopia

07 Dec, 07:01


የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
------------------------//---------------------------
(ሕዳር 28/ 2017 ዓ.ም) በትምህርት ሥርዓቱ የሚስተዋለውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር ለመቅረፍ በሚቻልበ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/18CXM6xwpC/

Ministry of Education Ethiopia

06 Dec, 12:59


የአምስት የዘርፍ ኢንዱስትሪዎች የትስስር ፎረም ተመሰረተ።
በቀጣይ ሁለት አመታት የየዘርፉን ፎረም የሚመሩ አመራሮችም ተመርጠዋል።

-------------------- // ---------------------

(ሕዳር 27/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በፎረሞቹ ምስረታ ላይ ባደረጉት ንግግር የትምህርትና ስልጠና ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ተወዳዳሪ ዜጋና ሀገርን ለማበልጸግ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ የዘርፉ ተዋንያኖች ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው እንደገለጽት ትስስሩ ሀብትን በጋራ በማመንጨትና በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል በመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ስልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪው ተጣምረው በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተ/ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በበኩላቸው በዘርፍ የሚቋቋሙት የትስስር ፎረሞች የከፍተኛ ትምህርት ፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪው በመቀናጀትና በመተባበር ሀገር የጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል የፎረሞቹ መቋቋም የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት፣ ምርምር ተቋማት እና ከኢንዱስትሪው ልምድና ተሞክሮዎችን እንዲቀስሙ የሚያስችል መሆኑን የገለጹ ሲሆን ኢንዱስትሪዎች በተመሳሳይ የሚመነጩ የምርምር ሀብቶችና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም የሚያስችላቸው እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

Ministry of Education Ethiopia

04 Dec, 08:26


በ2030 የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለማስቆም የተጣለው ግብ እንዲሳካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትኩረት ሊሰሩ አንደሚገባ ተጠቆመ ።
-------------------- // -----------------------
(ሕዳር 25/2017 ዓ.ም )ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች የተገኙበት የኤች አይቪና የስነ ተዋልዶ ጤና አውደጥናት ተከፍቷል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/1AaKhjYTxL/

Ministry of Education Ethiopia

30 Nov, 16:31


በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት መካከል በትምህርት መስክ ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን የፈረንሳይ እና የአውሮፓ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ኖኤል ባሮት አስታወቁ፡፡
-------------------- // ------------------------
(ህዳር 21/ 2017 ዓ.ም) ሁለቱ አገሮች በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት አስር በመቶ ነጻ የትምህርት እድል የሚያስገኝ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ https://www.facebook.com/share/158icUGCJB/

Ministry of Education Ethiopia

28 Nov, 12:16


የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በዓል ህብረብሄራዊ አንድነታችንንና የጋራ እሴቶቻችንን የምናጠናክርበት በዓል መሆኑ ተገለጸ።
-------------------------- //------------------------
ሕዳር 19/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አክብረዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0361dwcH3znyK8NZmKK7eS3o6tEZSsHRpgZsD1zEm19uS7PJcMg23X6ujhAvtNPsULl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz

Ministry of Education Ethiopia

19 Nov, 13:56


ሀንጋሪ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን የትብብር ግንኙነት ለማሳደግ እየሰራች መሆኑ ተጠቆመ።
-----------------------------------------
(ሕዳር 10/ 2017 ዓ.ም) የሀንጋሪ ሪፐብሊክና የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ለመቶ ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት እድል የሚያስገኝ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።https://www.facebook.com/share/p/1CWBVN6JoK/

Ministry of Education Ethiopia

18 Nov, 08:34


የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ተጀመረ።
____________ // ______________
(ህዳር 09/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግን አስጀምሯል።
ተማሪዎች መደበኛ የትምህርት ጊዜያቸውን ሳይጎዱ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የስፖርት ሊግ መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቶ ወደተግባር ገብቷል። የተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርትቸው ጎን ለጎን በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ የተማሪዎችን አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው።
ከዚህ አኳያም በ2017 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ቀጣና የተደራጀው የሀረሪ ክልል በሁሉም ትምህርት ቤቶች በቮሊቦል፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በአትሌትክስ፣ በጂምናስቲክስ፣ በጠረዼዛ ኳስ እና በባህላዊ ስፖርት አይነቶች የክልሉ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የትምህርት ቤት አመራሮች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀትተከፍቷል።
ስፖርታዊ ውድድሩ አመቱን ሙሉ የሚቀጥል ሲሆን ከሀረሪ ክልል በተጨማሪም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመሪያ መድረክ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ደግሞ በደቡብ ቀጣና ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞንና በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቮሊቦልና በእግር ኳስ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ ፣ በቮሊቦል እና በአትሌትክስ ስፖርት በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

በሌሎች የቀጣና አደረጃጀቶች ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮቹን በቅርቡ የሚያስጀምሩ ይሆናል።

Ministry of Education Ethiopia

13 Nov, 00:45


9ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና አውደርዕይ ተጀመረ
ለዝርዝሩ ይህንን ሊንክ ይጫኑ
https://www.facebook.com/share/p/17Ww2ZZ5Hw/
ለበለጠ መረጃ
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

Ministry of Education Ethiopia

08 Nov, 11:26


ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
----------------------------//-------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውዴሽን ጋር ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የስምምነት ሰንዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰባስቲያን ብራንዲስ ተፈራርመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱም ሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመገንባት ካቀዳቸው 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱን የሚገናባ መሆኑ ተጠቅሷል።

የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚካሄድው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው አዲስ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዲዛይን መሰረት ሲሆን ሙሉ የግንባታ ወጪን በመሸፈን እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አሟልቶ ፋውንዴሽኑ የሚያስረክብ መሆኑም ተገልጿል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች በአፋር፣ ሶማሌ እና ደ/ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገነቡ ሲሆን ግንባታቸውም ከ2025 እስከ 2029 እ.ኤ.አ የሚጠናቀቅ መሆኑም ተመላክቷል።

በስምምነት ሥነ ሥረዓቱ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከዚህ ቀደም በርካታ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች በመገንባት ለመማር ማስተማር ስራው ከፍተኛ አስተዋጻኦ ማበርከቱ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያመጡና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች ተመርጠው የሚገቡባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ለመገንባት አቅዶ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

Ministry of Education Ethiopia

07 Nov, 14:19


የትምህርት ሚኒስቴር ከራሽያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
---------------------------//---------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር ከራሽያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የተፈረመው ስምምነት ሰነድ በእኩልነት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና ውጤታማነት መርህ ላይ በመመስረት ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።
ሙሉውን መረጃ ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/18KC1SrJMV/

Ministry of Education Ethiopia

04 Nov, 12:31


Website: https://placement.ethernet.edu.et
Telegram: https://t.me/moestudentbot

Ministry of Education Ethiopia

01 Nov, 11:46


ትምህርት ሚኒስቴር ከሁዋዌና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር የሚያዘጋጀው የአይሲቲ ውድድር አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

ከሁዋዌ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ፍጻሜ ለተወዳደሩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

ሽልማቱ የተበረከተው የሁዋዌ የ2024/25 አይሲቲ የውድድር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ ባስተላለፉት መልእክት ውድድሩ ለተማሪዎች የስራ እድልን በማመቻቸት እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን ከማጎልበት አኳያ ሰፊ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ዘላለም አክለውም ሁዋዌ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎችን ክህሎት ለማዳበር እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን መሠል ጥረቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢትዬጵያ ሚስተር ሊሚንግየ በበኩላቸው ውድድሩ ለወጣቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

Ministry of Education Ethiopia

29 Oct, 13:32


የትምህርት ሥርዓቱን የምናሻሽለው ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ኢኮኖሚውን የሚሸከም ትውልድ ለመፍጠር ነው፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
----------------------------//----------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የሚኒስቴሩን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ሥርዓቱ ሪፎርም ማካሄድና ማሻሻል ያስፈለገው ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ኢኮኖሚውን የሚሸከም ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።
ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ አሁን መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህ ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች እየተካሄዱ ላሉ ሀገራዊ የለውጥ እርምጃዎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ስልጣኔ በጣም ውድ ነገር በመሆኑ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ያነሱት ሚኒስትሩ እንደ ዜጋ ቁጭት ሊሰማን የሚገባው በዚህ ዘመን ከዓለም ጋር እኩል መራመድ አለመቻላችን መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። በድህነት ስር ሆነን ከዚህ በላይ መኖር ይህን ሀገር የማይመጥን በመሆኑ ለለውጥ መትጋት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አያይዘውም እንደ ሀገር የተደረጉ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያዎች መሰረታዊ የሆነ የኢኮኖሚ ለውጥ በማስፈለጉ መሆኑን አብራርተው እንደ ሀገር በሚተገበሩ የለውጥ ስራዎች ውስጥ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ሁል ጊዜ በዛሬና በነገ መካከል የሚኖር ልዩነትን በማሰብ መሆኑን ገልጸው በትምህርት ሴክተሩም ይሁን እንደ ሀገር እየተተገበሩ ባሉ ሪፎርሞች በትክክልና በፍትሃዊነት ተግባራዊ እንዲደረጉ በማድረግ ቢያንስ ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ ይኖርብናል ብለዋል።

Ministry of Education Ethiopia

24 Oct, 12:26


https://placement.ethernet.edu.et
https://t.me/moestudentbot

Ministry of Education Ethiopia

16 Oct, 14:02


ፈጣን ፣ ውጤታማና ቅቡልነት ያለው አገልግሎት በመስጠት ሙስናን መከላከልና የአገርን እድገት ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የአገርን እድገት ለማስቀጠል ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በማስፈን በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡

ሙስና አገልግሎት አሰጣጥን በማስተጓጎልና ገጽታ በማበላሸት በአገር እድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ቀልጣፋ ውጤታማና ቅቡልነት ያለው አገልግሎት በመስጠት መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአገልግሎት መስፈርትንና የሚሰጥበትን ጊዜ ለተገልጋዩ አስቀድሞ በማሳወቅና በወጣው መስፈርትና የጊዜ መጠን አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከል ለብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ ክፍተቶችን በማረም ተገቢ አገልግሎት መስጠት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን ማዘመን ይገባል ብዋል፡፡
የአሰራር ስርዓትን በማዘመን ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻልና ብቃትና ጥራት ያለው ሰው ሀይል ማፍራት ፣ ተጠያቂነትና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የስነ መግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ደጀኔ ደሱ በሙስና መንስኤዎች፣ ተጋላጭነቶች እና መከላከል ዙሪያ ጥናታዊ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Ministry of Education Ethiopia

15 Oct, 14:36


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የተመራ የፈረንሳይ የልኡካን ቡድንን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የተከበሩ አሌክሲስ ማሌክ (Alexis Malek) የተመራ የፈረንሳይ የልኡካን ቡድንን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚህ ወቅትም በትምህርት ዘርፉ ላይ ስለሚኖሩ የትብብር መስኮች ዙሪያ ከክቡር አምባሳደሩ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ሚኒስትሩ የኢትዮ-ፍሬንች ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤትን በተመለከተ Mission Laique Francaise (MLF) ፕሬዚዳንት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ትምህርት ቤቱን በተመለከተ በቀጣይ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

Ministry of Education Ethiopia

08 Oct, 15:39


ማስታወቂያ
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

2. ማስታወቂያ
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

Ministry of Education Ethiopia

19 Sep, 07:30


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬሽን ማዕከላት መጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ
--------------------------------------
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን በማጠናከር ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን ማጠናከር በተቋማቱ ያለውን የተዛባ ሚዛን ያስተካክላል ብለዋል። አሁን ባለው ግምገማ በተቋሞቻችን ያለው የኢንኩንቬንሽን ማዕከላት አሰራር ከዘመኑ ጋር ያልተራመደ በመሆኑ ስልጠና ማዘጋጀት ማሰፈለጉን ጠቁመው በቀጣይ በዚህ ዘርፍ ላይ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል በበኩላቸው ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዩንቨርሲት ኢንዱስትሪ ትስስር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና እንኩንቤሽን ማዕከላት ኃላፊዎች የሚሰጠው ስልጠና ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ጠቁመው ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይህንን የሪፎርም ተልዕኮ በብቃት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። አቶ ተሾመ አያይዘውም ስልጠናው በፈጠራ ስነምህዳር፣ በስራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ማዕከላት እና የምርምር ውጤቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ገበያ ለማስገባት በሚከናወኑ አስተዳደራዊ ስራዎች ላይ የሚስተዋለውን የግንዛቤ እጥረት መፍታትን ትኩረት ያደርገ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ባለሙያች እውቀታቸውን ይጋሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ከየተቋማቱ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ማዕከላቱ በሚጠናከሩበት ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በስልጠናው ብዙ ልምድ እንዳገኙ ጠቁመዋል።

Ministry of Education Ethiopia

17 Sep, 11:16


ማስታወቂያ

በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ የቀረበ ጥሪ

ትምህርት ሚኒስቴር ሥራውን በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ይችል ዘንድ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶችን የመዘርጋትና መመሪያዎችን የማዘጋጀት ተግባራትን ሲከውን መቆየቱ ይታወቃል። ከዚህ አንጻር፣
1. የርቀት ትምህርት ፕሮግራም፣
2. የማታ ትምህርት ፕሮግራም፣ እና
3. የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በአዲስ መልክ አዘጋጅቷል።
በመሆኑም የተዘጋጁትን ረቂቅ መመሪያዎች አፅድቆ ሥራ ላይ ለማዋል በረቂቆቹ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በውይይት የማዳበር ሥራ ተሰርቷል። ነገር ግን ተጨማሪ ግብዓት በማሰባሰብ መመሪያዎቹን የበለጠ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሞቹን በመተግበር ላይ ያላችሁ (የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት፣ የማታ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት እና የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት) አስተያየት ለመስጠት የተጋበዛችሁ ስለሆኑ መስከረም 14/ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው መድረክ በመገኘት እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።

Ministry of Education Ethiopia

17 Sep, 06:01


ማስታወቂያ

ረቂቅ መመሪያን በውይይት ለማዳበር አስተያየት እንዲሰጥ ስለመጠየቅ

የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፍ ሁለንተናዊ እድገት እና ጥራትን ለማረጋገጥ ትክክለኛ እና ጥራት ያለዉ የትምህርት መረጃ የማይተካ ሚና ሰላለዉ በዘርፉ የትምህርት መረጃ አሰተዳደር ስርዓት ግልፅነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል የትምህርት መረጃ አሰተዳደር ስርዓት ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል።
የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ፀድቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት በቀጥታ ህብረተሰቡ በሚሳተፍበት መድረክ አስተያየት እና ግብአት እንዲሰበሰብ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በመሆኑም መሰከረም 08/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የመስሪያቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ይፋዊ የህዝብ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችል ግብአት ይሰጡን ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን።

Ministry of Education Ethiopia

05 Sep, 12:26


የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአሜሪካ የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ቻንስለር በዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በጽ/ ቤታቸው አነጋገሩ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ቻንስለሩንና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ አገራችን ዘመናዊ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት ታሪክና መስፋፋት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የረትገር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂና በሌሎችም የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መክረዋል፡፡

ዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ በበኩላቸው የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ከማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ከሌሎችም የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮቸ በትብብርና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡