ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች @doctorfasil Channel on Telegram

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

@doctorfasil

📢 ማንኛዉም አይነት የህፃናት ሕክምና(የቆዳ፣ የአይን፣ የነርቭ ፣የአንገት በላይ እና ሙሉ የህፃናት የዉስጥ ደዌ ሕክምና ቀጠሮ ለማስያዝ ይደውሉ::
👉 0984650912 / 0939602927 / 0996505319

ብሩህkids (Amharic)

ብሩህkids ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) ለይህ ሻንክል ለህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች ነው። የቴሌግራም ወቅታዊ እና ሠራተኛ አዳዲስ መረጃዎችን ለመስማት የቴሌግራም እሯቸው። ህፃናት የጤና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸውን፣ ጨቅላ ህፃናትን እና ታዳጊ ህፃናትን፣ ህፃናት አመጋገብን፣ እና ህፃናት አስተዳደግ ወሳኝ መረጃዎች ይቀርባሉ። ህፃናትን ከእርምጃ መራራ የቀረቡትን የዉስጥ ደዌ ሕክምና ነኝ። ንግድ እና ማህበረሰብ ጠብታ ሆነላቸዉ። ብሩህkids እናዝናሏል! ጥጃዎቹን ከመመልከት ወደ ተመዘገብ ባዶ አለቃቸዉን ማሰልፈን አሉን።

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

09 Jan, 20:04

ለልጄ የአሳ ዘይት መቼ ላስጀምረው ምን አይነት የ አሳ ዘይት ልጠቀም

📢ሙሉ መረጃውን ብሩህkids youtube ላይ ያገኙታል 👇👇👇
https://youtu.be/hDZG34SqhWs?si=e42OqXj5jkQKRMhO

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

06 Jan, 19:38

እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

06 Jan, 15:10

ለመላው #ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ

#ብሩህkids የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች ልዩ #ክሊኒክ ስራ ከጀመረ ሁለት ሳምንታትን አስቆጠረ።

በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንሎት ከወዲው ተመኘኝ።እርሶም፣ ልጆትም ከምግብ ቅባት መብዛት ጋር ተያይዞ ከሚመጣ የምግብ አለመስማማት በመጠንቀቅ ሰናይ ቀን ያሳልፉ።

#ብሩህኪድስ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች ልዩ ክሊኒክ የሚሰጡ አገልግሎቶች

👉 አጠቃላይ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች(0-18 ዓመት) ከፍተኛ ምርመራ እና ህክምና
👉 የንግግር እና አፍ መፍታት ችግር ላለባቸው ህፃናት ልዩ ምርመራ
👉 የምግብ ፍላጎት እና የክብደት ችግር ላለባቸው ህፃናት ልዩ ምርመራ
👉 አጠቃላይ አመታዊ ምርመራ
(Medical checkup)
👉 የድንገተኛ ህክምና
👉 የአየር ቧንቧ አለርጅ ምርመራ እና ሕክምና
👉  የሳምባ ምች ና ቲቢ ምርመራ
👉 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ምርመራ
👉 የህፃናት አመጋገብ ምክሮች
👉 የኦቲዝም እና ዳውን ሲንድሮም ምርመራ
👉 የህፃናት እና ታዳጊዎች የእድገት ክትትል
👉  የጉበትና የኩላሊት ምርመራ
👉 የታይሮይድ ሆርሞን
👉 ቪታሚን ዲ ምርመራ
👉 የኮሌስትሮል ምርመራ
👉 የስኳር ምርመራ
👉 የጨጓራ ህመም ምርመራ እና ሕክምና
👉 የHIV ምርመራ
👉 የሽንት እና ሰገራ ምርመራ

🏥 አድራሻ ጦር ኃይሎች አውግስታ የእግረኛ ድልድይ ከሕብር አካዳሚ ት/ቤት ፊት ለፊት ያገኙናል

GoogleMap: https://maps.app.goo.gl/JMxWZbWBWavW2ifp7

☎️ የቀጠሮ ስልክ፦
0984650912
0996505319
0939602927 ይደውሉ።

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

05 Jan, 14:27

🔊 የቶንሲል ህመምን ቤት ዉስጥ ማከም የምንችልበት 10 መንገዶች ‼️

❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ በቅንነት #share ያድርጉት❗️🙏

👉 በመጀመሪያ ልጅዎ ቶንሲል ህመም እንደያዘው በምን ያውቃሉ?

👉 #የቶንስል ህመም የሚከተሉትን ምልክቶች ህፃናት ላይ ያሳያል
🔺 ትኩሳት
🔺 ለመዋጥ መቸገር
🔺 የጉሮሮ ህመም
🔺 ራስ ምታት
🔺 የአፍ መጥፎ ሽታ
🔺 የቶንስል ማበጥ እና መቅላት
🔺 የእንጥል እና ጉሮሮ መቅላት
🔺 ቶንሲል ላይ የሚታይ ነጭ ወይም ቢጫ ሽፋን
🔺 የአንገት አካባቢ ንፍፊት/እብጠት
🔺 ማንኮራፋት እና በአፍ መተንፈስ
🔺 እነዝህ ምልክቶች 2-4 ቀናት ሊቆዩ ይቺላሉ ሆኖም ጠንከር ያለ ሲሆን እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይቺላል

👨‍⚕️🛑 #ለታዳጊ #ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናዎቹ ምንድናቸው❓️

🔹 የዝንጅብል ሻይ መጠቀም
🔹 ሙቅ ዉሃ ዉስጥ ጨው አርጎ ጉሮሮን ላይ መያዝ ወይም ጉሮሮን ማጠብ ወይም መጉመጥመጥ
🔹 ተደጋጋሚ ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን መውሰድ
🔹 በቂ እረፍት ማድረግ
🔹 ሻይ በማር መጠጣት
🔹 ነጭ ሽንኩርት መጠቀም
🔹 የውሃ ኢንፋሎት መታጠን
🔹 የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ
🔹 ቀለል ያሉ የህመም ማስታገሻዎች መውሰድ
🔹 ለምሳሌ ፓራሰታሞል 💊💊
🔹 ጠንካራ እና ግሮሮ ልረብሹ የሚቺሉ ምግቦችን ማስወገድ ለምሳሌ ቺፕስ እና የተጠበሱ ምግቦች

🔊 #ሆስፒታል መሄድ ያለብን መቼ ነው❓️

👉 የቶንስሉ ህመም በባክቴርያ ምክንያት የመጣ ከሆነ (የቫይረስ ከሆነ ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ ሕክምና ልድንም ይቺላል::
👉 የህመሙ አይነት ከፍተኛ ከሆነ
👉 ቶንስል ላይ ነጭ ሽፋን ካሳየ
👉 በቤት ውስጥ ሕክምና ቢያንስ በ ሁለት ቀን ለውጥ ከሌለው
👉 ማንኮራፋት እና እንቅልፍ መንሳት ካለ
👉 ምግብ ሙሉ ለሙሉ ካልበሉ (መዋጥ ካልቻሉ)
👉 የታወቀ የልብ ህመም ካለ

⛔️ ማሳሰቢያ : ህፃናት ጠንካራ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን እና ፀረ ባክቴርያ መድሃኒቶች💊 ያለ ሀኪም ትእዛዝ በፍፁም መወሰድ የለባቸውም ‼️

🛑 👉 #ለጨቅላ ህፃናትስ ምንድነው የምናረገው?

🔹 ጨቅላ ህፃናት(ከሰላሳ ቀናት በፊት) ላይ የቶንስል ህመም በፍፁም ሊከሰት አይቺልም❗️ ምክንያቱ ደሞ ጨቅላ ህፃናት የበሽታ መከላከል አቅማቸው በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ኢን ፌክ ሽን ሲይዛቸው በተወሰኑ ቦታዎች ላይ መቆጣጠር ስለማይቺሉ በደማቸው ዉስጥ ባክቴርያው ወደ ተለያዩ የሰውነት አካላቸው ይዛመታል ይሄም neonatal sepsis ("በደም ዉስጥ የተሰራጨ ኢንፌክሽን") ይባላል ::

🔹 አንዳንድ እናቶች ደሞ ጨቅላ ህፃናት ማልቀስ እና ትኩሳቱን አይተው እንጥሉ ወረደ ብለው ሲናገሩ ይሰማሉ :: ቀጥሎ ደሞ እንጥሉ መቆረጥ አለበት ይላሉ ይሄ በዘመናዊ ሕክምና ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ጎጂ ባህላዊ አስተሳሰብ ነው ❗️ጨቅላ ህፃናትም ሆነ ታዳጊ ህፃናት ህመም ምልክት ካሳዩ በ ቀጥታ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም ጋር መሄድ እና ማሳየት ያስፈልጋል ‼️

🔊  #ቶንስል ኢንፌክሽን እና የልብ ህመም ያመጣል ወይስ አያመጣም ❓️

🔊 ለቶንስል ተብሎ የሚሰጠው መርፌ (ቤንዛንቲን - Benzanthine )  የልብ ህመም ያመጣል ወይስ አያመጣም❓️

🔊 ቶንስል በቀዶ ሕክምና መውጣት ያለበትስ መቼ እና ምን አይነት የሕክምና ቦታ ነው❓️

🔊 ሙሉ ማብራሪያውን ብሩህkids youtube ላይ ያገኙታል

🏥 በአካል ሆስፒታል መተው ለልጅዎ ሕክምና እና ምርመራ ከፈለጉ ቀጠሮ በእነዝህ ስልክ ቀጠሮ ማስያዝ ይቺላሉ
👇👇👇👇👇👇👇

☎️  0984650912
☎️ 0963555552
☎️  0939602927

🏥 ብሩህኪድስ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች ልዩ ክሊኒክ

አድራሻ: ጦር ኃይሎች አውግስታ የእግረኛ ድልድይ በአዲሱ የ ቤተል መንገድ ላይ ያገኙናል

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

24 Dec, 20:03

#ስራ_ጀምረናልብሩህኪድስ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች ልዩ ክሊኒክ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል

#ብሩህኪድስ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች ልዩ ክሊኒክ የሚሰጡ አገልግሎቶች

👉 አጠቃላይ የህፃናት እና ታዳጊ ልጆች(0-18 ዓመት) ከፍተኛ ምርመራ እና ህክምና
👉 የንግግር እና አፍ መፍታት ችግር ላለባቸው ህፃናት ልዩ ምርመራ
👉 የምግብ ፍላጎት እና የክብደት ችግር ላለባቸው ህፃናት ልዩ ምርመራ
👉 አጠቃላይ አመታዊ ምርመራ
(Medical checkup)
👉 የድንገተኛ ህክምና
👉 የአየር ቧንቧ አለርጅ ምርመራ እና ሕክምና
👉 የሳምባ ምች ና ቲቢ ምርመራ
👉 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ምርመራ
👉 የህፃናት አመጋገብ ምክሮች
👉 የኦቲዝም እና ዳውን ሲንድሮም ምርመራ
👉 የህፃናት እና ታዳጊዎች የእድገት ክትትል
👉 የጉበትና የኩላሊት ምርመራ
👉 የታይሮይድ ሆርሞን
👉 ቪታሚን ዲ ምርመራ
👉 የኮሌስትሮል ምርመራ
👉 የስኳር ምርመራ
👉 የጨጓራ ህመም ምርመራ እና ሕክምና
👉 የHIV ምርመራ
👉 የሽንት እና ሰገራ ምርመራ

🏥 አድራሻ ጦር ኃይሎች አውግስታ የእግረኛ ድልድይ ከሕብር አካዳሚ ት/ቤት ፊት ለፊት ያገኙናል

GoogleMap: https://maps.app.goo.gl/JMxWZbWBWavW2ifp7

☎️ ቀጠሮ ስልክ : 0984650912 / 0996505319 / 0939602927 ይደውሉ

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

23 Dec, 20:05

" ወላጆች የልጆቻችሁን ውሎና ሁኔታ እንድትከታተሉ አደራ እንላለን " - የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ

ህፃናትን የደፈረው ወንጀለኛ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። 

ወንጀለኛው የደፈራቸው ሁለት ሴት ህፃናት በማጣባቂያ ማስትሺና በጨርቅ በማፈን እንደሆነ ተሰምቷል።

ወንጀሉ መቼ እና እንዴት ተፈፀመ ? 

ወንጀሉ የተፈጸመው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን ቦታው ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 04 ነው። 

የድርጊቱ ፈፃሚ ወንጀለኛ የ28 ዓመቱ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ሲሆን ፤ ነውረኛ ድርጊቱን የተፈፀመው  የ11 እና 12 ዕድሜ ባላቸው እንስት ህፃናት ላይ መሆኑ የጥፋተኛው የክስ የውሳኔ ማስረጃ ያስረዳል።

ወንጀለኛው እድሜያቸው ከላይ የተጠቀሰውን ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ፣ ክፉ ደጉን እንኳን የማይለዩ ሁለት ህፃናትን በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መደለያዎች በመስጠት #እንዲቀርቡትና #እንዲለምዱት ካደረገ በኋላ ፤ ቀን መርጦ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስትሺ ተጠቅሞ ድምፅ እንዳያሰሙ በማፈን አስገድዶ የመድፈር ተግባር ፈፅሞባቸዋል።

ይህ እጅግ ለመስማት የሚቀፍ አፀያፊ ደርጊት ለወራት ሲያጣራ የቆየው የፓሊስና የፍትህ አካል በመቀበል የግራና ቀኝ ምስክሮች ያዳመጠው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ በ16 ዓመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። 

ጉዳይ በማስመልከት ለሚድያ መገለጫ የላከው የትግራይ ፍትህ ቢሮ ፤ ወላጆች በህፃናት ላይ ይህንን መሰል አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙትን እንዲያጋልጡና የልጆቻቸው ውሎና ሁኔታ እንዲከታተሉ አደራ ብሏል።

በሀገራችን ሴቶች ላይ ለሚፈጸሙ ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የሚሰጠው ፍርድ ምንም የማያስተምር ፤ ይልቅም ወንጀልን የሚያበረታታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ ከፍተኛ ቅሬታ ነው።

በተለይ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንጀለኞች ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ብዙ ጊዜ ዜጎችን የሚያስቆጡ እንደሆኑ በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ ነው።

ምንጭ : tikvahethiopia            

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

22 Dec, 07:57

Channel name was changed to «ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች»

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

22 Dec, 05:10

Channel name was changed to «ብሩህkids Clinic - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች»

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

22 Dec, 05:08

Channel photo updated

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

22 Dec, 05:07

Channel photo removed

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

21 Dec, 04:27

🏆 Tiktok #Creative Awards በተለያዩ ዘርፎች እጩዎችን አውጥቶ ህብረተሰቡ እንዲመርጥ መንገድ ዘርግቷል።

እኔም በእናንተ ቤተሰቦቼ እርዳታ የዓመቱ ምርጥ ጤናና ህክምና ነክ ይዘት/ Best Health and Medical ዘርፍ ዉስጥ ታጭቻለዉ።

የሚከተለዉን ቀላል መንገድ በመጠቀም ድመፃቹን እንድትሰጡኝ በትህትና እጠይቃለዉ።
1. በመጀመሪያ ይህን ሊንክ መጫን https://tiktokcreativeawards.com/categories/6
2. ወደታች ስትወርዱ መጨረሻ ላይ ሙሉ ስሜን ከፎቶዬ ጋር ያገኙታልና እሱን TAP ማድረግ/መጫን።
3. በመቀጠል SUBMIT የሚለዉ አማራጭ ሲመጣ እሱን መጫንና የስልክ ቁጥሮን ማስገባተና በፅሁፍ መልዕክት የሚላክሎትን ቁጥር በማስገባት VOTE ማድረግ ይችላሉ።

ድምፅ መስጠቱ ፕሮግራም ቶሎ ሊዘጋ ስለሚችል ቀድመው ድምፅ ይስጡ

እናመሰግናለን 🙏

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

18 Dec, 15:08

#አስደሳች ዜና ብሩህኪድስ የህፃናት እና የታዳጊ ልጆች ልዩ ክሊኒክ ታህሳስ 16 2017 ዓ.ም በይፋ ስራ ይጀምራል

ይምጡ ይጎብኙን 👇👇

🏥 አድራሻ ጦር ኃይሎች አውግስታ ድልድይ ከሕብር አካዳሚ ት/ቤት ፊት ለፊት ያገኙናል

GoogleMap: https://maps.app.goo.gl/JMxWZbWBWavW2ifp7

☎️ ቀጠሮ ስልክ : 0984650912 / 0996505319 / 0939602927 ይደውሉ

ብሩህkids ክሊኒክ ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

14 Dec, 19:27

ለአካውንታቶች #ክፍት የስራ ቦታ 👇

📢 #ብሩህኪድስ የህፃናት እና ታዳጊዎች ልዩ #ክሊኒክ ልምድ ያላቸውን አካውንታንቶች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
👉 ብዛት : 1
👉 ስራ ልምድ : ሁለት ዓመት እና ከዛ በላይ
👉 ተፈላጊ ችሎታ : አካውንቲንግ የተመረቀ/ች peachtree አካውቲንግ የሰለጠነ/ች እና መስራት የሚችል /የምትችል
👉 በቂ የኮምፒውተር እውቀት ያለው/ያላት እና በፅህፈት ስራ በቂ ልምድ ያለው/ያላት
👉 የተጣራ ደሞዝ : 10,000
👉 የስራው አይነት : የሙሉ ሰዓት (8 ሰዓት በቀን )

🌍 የስራ አድራሻ : አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች
👉 የስራው ቦታ : የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

🔊 አመልካቾች CV እና ፎቶዋቸውን ከታች ባስቀመጥነው ቴሌግራም ሊንክ ላይ ይላኩ 👇👇👇

☎️ ቴሌግራም : @PediDr
ወይም https://t.me/PediDr ላይ CV ከፎቶ ጋር ይላኩ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

07 Dec, 08:47

አስደሳች ዜና ! ከአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ  Smile train ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር  የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት  ሳምንቱን ሙሉ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?

እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር Cleft lip  እና Cleft palate ያለባችሁ በመሉ  በ 0948898286 በመደወል ወይም ወደ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  በመሔድ  መመዝገብ  ይችላሉ::

ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም  ለሚያድሩት የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

30 Nov, 03:13

📢 ስለጉንፉን መሰል #ወረርሺኝ #EBS ቻናል ላይ ነገ ቀን "እሁድን በEBS" ፕሮግራም ላይ ከመቅዲ ጋር ያደረኩት ውይይት ይቀርባል እንዲከታተሉት ተጋብዘዋል!

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

11 Nov, 13:37

ክፍት የስራ ቦታ 👆👆
CV ለመላክ @PediDr ላይ ይላኩ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

04 Nov, 19:42

🔊 ተጨማሪ #ክፍት #የስራ #ቦታ 👇👇
1. ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂስት
ብዛት : 1
ልምድ : 2 ዓመት
👉 በህፃናት ሕክምና ላይ የሰራ
👉 ከጨቅላ ህፃናት እና ታዳጊ ህፃናት ላይ የደም ናሙና የመውሰድ በቂ ልምድ ያለው/ያላት
👉 ትልልቅ የላቦራቶሪ ማሽኖች ላይ ልምድ ያለው/ያላት
👉 ደሞዝ የተጣራ : 10,000
(ሌሎች ጥቅማጥቅም ሳይጨምር)

2.የህፃናት ነርስ
ብዛት : 1
ልምድ : በህፃናት ሕክምና 2-3 ዓመት ልምድ ያላት
ፆታ : ሴት

👉 ትምህርት ደረጃ : Nursing ዲፕሎማ / ዲግሪ
👉 የተጣራ ደሞዝ : 10,000 (ጥቅማጥቅም/duty ሳይጨምር)

👉 ታካሚዎችን በትዕግስት እና በፍቅር ማስተናገድ የምትችል

👉 በህፃናት ሕክምና ላይ በቂ ልምድ ያላት

3. አስተዳዳር እና የሰዉ ኃይል ባለሙያ
ብዛት : 1
ልምድ : 5 ዓመት
ፆታ : ወንድ
👉 በ Human resource managment / Marketing / Managemnet / Accounting ትምህርት ዘርፍ በዲግሪ / ዲፕሎማ የተመረቀ

👉 ድርጅት በመምራት እና ማስዳደር በቂ ልምድ እና እውቀት ያለው

🌍 የስራ አድራሻ : አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች
👉 የስራው ቦታ : የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

🔊 አመልካቾች CV እና ፎቶዋቸውን ከታች ባስቀመጥነው ቴሌግራም ሊንክ ላይ ይላኩ 👇👇👇

☎️ ቴሌግራም : @PediDr
ወይም https://t.me/PediDr ላይ CV ከፎቶ ጋር ይላኩ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

03 Nov, 08:09

🔊 ክፍት የስራ ማስታወቂያ 👇👇👇

1. እንግዳ ተቀባይ (Receptionist )
ብዛት : 3
ልምድ : 1 ዓመት
ፆታ : ሴት

👉 ትምህርት ደረጃ : በNursing ዲፕሎማ ወይም Level 3-4 ያላት

👉 የተጣራ ደሞዝ : 5000 (ጥቅማጥቅም ሳይጨምር)

👉 ታካሚ በትዕግስት እና በፍቅር ማስተናገድ የምትችል
2. ካሸር
ብዛት : 2
ልምድ : 1 ዓመት
ፆታ : ሴት

👉 ትምህርት ደረጃ : በIT ወይም በሌላ ስራ ዘርፍ Level 3-4

የተጣራ ደሞዝ : 5000 (ጥቅማጥቅም ሳይጨምር)

👉 ታካሚ በትዕግስት እና በፍቅር ማስተናገድ የምትችል

3. አካውንታንት

ብዛት : 1
ልምድ : 2 ዓመት
ፆታ : ሴት
ትምህርት ደረጃ : በ Accounting ዲፕሎማ

👉 የተጣራ ደሞዝ : 7000 (ጥቅማጥቅም ሳይጨምር)

👉 አመታዊ ሂሳብ መዝጋት የምትችል

4. ሜትረን የህፃናት ነርስ
ብዛት : 1
ልምድ : በህፃናት ሕክምና 3 ዓመት ልምድ ያለው
ፆታ : ሴት

👉 ትምህርት ደረጃ : Nursing ዲፕሎማ / ዲግሪ
👉 የተጣራ ደሞዝ : 10,000 (ጥቅማጥቅም/duty ሳይጨምር)
👉 ታካሚዎችን በትዕግስት እና በፍቅር ማስተናገድ የምትችል

5. የ IT ባለሙያ
ብዛት : 1
ልምድ : 1 ዓመት
ፆታ : አይመርጥም

👉 ትምህርት ደረጃ : IT ዲፕሎማ / Level 3-4
👉 የተጣራ ደሞዝ : 7,000 (ጥቅማጥቅም ሳይጨምር)

🌍 የስራ አድራሻ : አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች
👉 የስራው ቦታ : የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

🔊 አመልካቾች CV እና ፎቶዋቸውን ከታች ባስቀመጥነው ቴሌግራም ሊንክ ላይ ይላኩ 👇👇👇

☎️ ቴሌግራም : @PediDr
ወይም https://t.me/PediDr ላይ CV ከፎቶ ጋር ይላኩ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

17 Oct, 10:45

ወቅታዊ ጉንፋን እና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመም በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
___

የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና  ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ2003 ዓ ም ጀምሮ የእንፍሉዌንዛ እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እየተሰራ ይገኛል። ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን  ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል1፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡  ስለዚህ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል የሚቻል መሆኑን እያስታወስን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እና መረጃዎችን በየጊዜው የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

ምንጭ : ጤና- ሚኒስቴር

Youtube : ሙሉ ቪዲዮ👇👇 https://youtu.be/X4J5o3_OuHk?si=bT_GQ5NcsHB8oOrl

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

06 Oct, 06:22

🗣️የሰሞኑ #ጉንፋን ህፃናት ላይ ምን አይነት ምልክት አለዉ የቤት ውስጥ መፍትሄዎችስ ምን ምን ናቸው

🔊 ሙሉ መረጃውን ብሩህkids youtube ቻናልችን ላይ ያገኙታል
🔊 👇👇👇👇
https://youtu.be/X4J5o3_OuHk?si=bT_GQ5NcsHB8oOrl

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

26 Sep, 18:11

🔊 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የመስቀል እና ደመራ በዓል ይሁንላችሁ
#ብሩህkids

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

23 Sep, 05:31

🔊 የሕክምና ፕሮግራም ለውጥ 👇
ውድ ቤተሰቦቻችን በደመራ በዓል ምክንያት የሃያሁለት (semah MCH) ያለን ፕሮግራም ወደ እሮብ ከሰዓት 9:30 የቀየርን መሆን በአክብሮት እናሳውቃለን ::
👉 ለህፃናት ሕክምና ቀጠሮ ለማስያዝ በዝህ ስልክ ይደውሉ
☎️ 0984650912 ወይም 0939602927

👉 በስልክ ለማማከር ከፈለጉ ☎️ 0984650912 ይደውሉ እና ቀጠሮ ያስይዙ

🔊 መልካም የስራ ሳምንት

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

16 Sep, 18:05

🔊 ትምህርት ቤት የሚሄዱ ጀማሪ ህፃናት ላላቸው ወላጆች ጠቃሚ ምክሮች 👇👇👇

🇪🇹 በዝህ ሳምንት እና በሚቀጥለው ሳምንት ብዙ ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው ሌሎቹም በጥቂት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይጀምራሉ ።

💔💔 ልጆቻችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት መላክ ደስ የሚል እንዲሁም ፍርሃት የቀላቀለበት ስሜት በልጆችም በወላጆችም ይፈጥራል

ይህን የሽግግር ወቅት ቀለል ለማድረግ የሚረዱን ነገሮች ከዚህ ቀጥለን እናያለን ።

1.አስቀድመን ስለትምህርት ቤት ለልጆቻችን ማውራት
       👉ትምህርት ቤት ምን እንደሚሰሩ?
      👉ስለጓደኞቻቸው
      👉ምን ያህል እንደሚቆዮ ?
      👉ሲመለሱ ስለሚኖራቸው ነገር ቀድሞ በማውራት ማለማመድ

2.ከተቻለ አብረውን ሄደው
    👉የምሳ እቃቸውን የውሃ መያዣቸውን
   👉የትምህርት መሳሪያዎቻቸውን
   👉ልብስ/ዮኒፎርማቸውን፣ጫማ፣ካልሲ የመሳሰሉትን አብረው እንዲገዙ መፍቀድ

3.ትምህርት ቤት የሚመገቧቸውን የምግብ ዝርዝሮች ላይ እንዲሳተፋ ማድረግ

   👉የተመጣጠነ ምግብ አትክልትና ፍራፍሬ ያካተተ ቢሆን ይመረጣል

👉 ቺፕስ እና የታሸጉ ምግቦችን እንደምግብ ምሳ ዕቃ ውስጥ ባናስራለቸው ይመከራል

    👉 ለመጠጥ የታሸገ ጁስ እና ሻይ ባንልክላቸው ይመረጣል

     👉 ምግብ ስናስይዛቸው ሊጨርሱት በሚችሉት መጠን ይሁን

    👉 አቀራረባችን ማራኪ ከሆነ ልጆች ደስ ብሎቸው ይመገባሉ ።

4.አስቀድመን የምኝታ ሰዓታቸውን ማስተካከል አለብን ።

    👉ህጻናት ቢያንስ 9/10 ሰዓት መተኛት ይኖርባቸዋል።

  👉 ከጥቂት ቀናት አስቀድመን ይህን እንዲለምዱ ቀድመን ኤሌክትሮኒክስ  (ቲቪ ፤ሙዚቃ...)በማጥፋፋት ለምኝታ ማዘጋጀትን ማስለመድ

👉በጊዜ ራታቸውን ማብላት ከጥቂት ቀናት ቀድመን መጀመር ለእኛም ለልጆችም ይጠቅማል

5.ትምህርት ከመከፈቱ በፊት ከተቻለ አብሯቸው የሚማር ተማሪ ቀድመው ማግኘት ከተቻለ ማገናኘት ደስተኛ ሆነው እንዲሄዱ ያግዘናል ።

6. እንደወላጅ ትምህርት ሲከፈት የሚያስፈልጉትን ቀድሞ ማዘጋጀትን መልመድ
  👉የሚወስዱትን ነገር ሰርቶ ማደር
  👉የምሳ እቃቸውን ፣የውሃ መያዣቸውን
👉የመማሪያ መሳሪያቸውን
👉የሚለብሱትን መዘጋጀቱን አረጋግጦ መተኛትን ልማዳችን ማድረግ
👉ቀድመን ለመንቃት ና ልጆቻችንን በሰዓቱ ለመቀስቀስ ሰዓታችንን አላርም መሙላት መረሳት የለበትም።

7.ልጆቻችን በተለይ ጀማሪ ከሆኑ ብዙ በማስጠናት የበለጠ ትምህርት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አለማስጨነቅ
👉ይህ የበለጠ ትምህርቱን እንዲጠሉትና እንዲጨነቁ ያደርጋቸዋል ።
👉ሌላው መረሳት የሌለበት ልጆች ስለሆኑ መጫወት እንዳለባቸው መረሳት የለበትም

ሁሉም ወላጅ የተሳካ ፣ደስተኛ ፣ጤነኛ ልጆች እንዲኖሩን ከላይ የተዘረዘሩትን በመጠቀም ደስተኛ  የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆችን እናፍራ ።
መልካም ቤተሰብ የሀገር መሠረት
🌼🌼መልካም የትምህርት  ዘመን 🌼

🔊 youtube :
https://youtube.com/@bruhkids-t1e?si=zNP_thRi4mRnN6ውት

🔊 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil

☎️ ቀጠሮ ስልክ 👇👇👇 : 0984650912 ወይም 0939602927

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

15 Sep, 06:50

🔊❤️ ለመላው #የእስልምና #እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል ይሁንላችሁ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

11 Sep, 09:20

🌻🌻 ውድ የብሩህkids ቴሌግራም እና youtube ቤተሰቦቻችን እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ 🌻🌻🌻

🇪🇹 አዲሱ ዓመት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የሚታገኝበት ህዝቦቿም በሰላም የሚኖሩበት በሰላም ወተን በሰላም የምንገባበት፣ ወልደን የምንስምበት፣ ሰርተን የምናተርፍበት፣ ዘርተን የምናጭድበት ዓመት ያድርግልን
☎️ 0984650912
☎️ 0939602927

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

06 Sep, 19:53

🔊 ለህፃናት 6 ወር ላይ መጀመር ያለባቸው ምግብ አይነቶች 👇👇👇
https://youtu.be/hi0LI89Z__Q?si=6zhJOVCI0LB_Z_4w

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

30 Aug, 15:33

#አስደሳች_ዜና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ከ Operation Smile ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት ሳምንቱን ሙሉ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር #Cleft lip እና #Cleft palate ያለባችሁ በመሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ 976 የነጻ መስመር ወይም በስልክ ቁጥር 0903573176 በመደወል እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን፡፡ በተጨማሪም ወደ ሆስፒታሉ በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ;;
ሕክምናውን ለማግኘት የተመዘገቡ በሙሉ ዘወትር ሰኞ : ረቡዕእና አርብ ቅድመ ምርመራ ለማድረግ በኮሌጁ የተመላላሽ ሕክምና ማዕከል መገኘት አለባቸው፡፡
ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም ለሚያድሩት ;የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና Operation smile

👉 youtube : https://youtube.com/@bruhkids-t1e?si=zNP_thRi4mRnN6ውት

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

27 Aug, 16:56

🔊 ለልጄ #የላም #ወተት እና እርጎ መቼ ልጀምር👇👇
https://youtu.be/wm2fvMcnKAU?si=RLLGg6L_MQbBuRoA

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

24 Aug, 10:43

🔊 ልጆችን ስለ ጾታዊ ጉዳዮች እና ጥቃቶች እንዴት እናስተምራቸው

ልጆችን ስለ ጾታዊ ጉዳዮች የማስተማር እና ያለማስተማር ጉዳይ ብዙዎችን ያከራከረ ጉዳይ ነው::

የተለያዩ ጥናቶች : ልጆች እድሜያቸውን እና የማገናዘብ ደረጃቸውን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ትምህርት ቢሰጣቸው የተሻለ ነው ይላሉ:: ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው: ይህን መረጃ ከወላጆቻቸው ካላገኙት ሌሎች የመረጃ ምንጮችን (ማለትም ከአቻዎቻቸው፣ ከበይነመረብ..) ማወቃቸው አይቀርም: ከነዚህ ምንጮች የሚገኙ መረጃዎች ደግሞ ላፈነገጡ ዝንባሌዎች ሊዳርጓቸው ይችላል የሚል ነው:: ስለ ጾታዊ ጉዳዮች አስቀድመው ማወቃቸው ራሳቸውን ከጥቃቶች እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ያግዛቸዋል የሚል አመክንዮም የሚያቀርቡ አሉ::

የልጆች የአስተሳሰብ እና የማገናዘብ ችሎታ ልክ እንደ አካላዊ እድገት ሁሉ በእድሜ ሂደት የሚገነባ ነው::

🔹ከ 2-7 አመታቸው ድረስ ያለው Preoperational stage ይባላል:: በዚህ እድሜያቸው:: በአመክንዮ የማሰብ እና ውስብስብ ነገሮችን የመገንዘብ ችሎታው አይኖራቸውም፤ ሁኔታዎችን በራሳቸው አረዳድ ከመመዘን በዘለለ ሌሎች እንዴት ይቃኙታል ብለው አያገናዝቡም:: egocentric ናቸው::

ነገሮችን የሚማሩት በትዕምርት(Symbolic representation) ነው::
ስለዚህም በዚህ እድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ልጆች ነገሮችን በጨዋታ አስታኮ ማስተማር የተሻለ ነው::

በዚህም መሰረት:-

▪️ህጻናት ከእናቶች እንደሚወለዱ
▪️ወንዶች እና ሴቶች በጾታዊ አካሎቻቸው እንደሚለያዩ
▪️አካላዊ ስያሜዎችን በቀላል ቃል ማስረዳት
▪️የራስ አካል የግል እንደሆነና: ሌሎች በፍጹም ሊነኳቸው የማይገቡ አካሎች የትኞቹ እንደሆኑ
▪️ከቤተሰብ የሚደበቅ ሚስጥር መኖር እንደሌለበት ማስረዳት አስፈላጊ ነው::

🔹ከ7-11 አመታቸው ድረስ ያለው ጊዜ Concrete Operational stage ይባላል:: ምክንያታዊ የሚሆኑበት እና በአመክንዮ ማሰብ የሚጀምሩበት እድሜ ነው:: ምክንያታዊነታቸው ታድያ ለቁስ አካሎች ብቻ ነው:: ምናባዊ የሆኑ ጉዳዮችን በጥልቀጥ ለመመርመር ይቸገራሉ::

Inductive reasoning በብዛት ይጠቀማሉ:: ነገሮችን ከራስ ተሞክሮ በመነሳት ወደድምዳሜ ያመራሉ::

ማፈር እና ስለ ጾታዊ ጉዳዮች በመጠኑ ማሰብ የሚጀምሩበት እድሜ ነው::

በዚህ እድሜያቸው:-

▪️ስለ ወሲብ፣ እርግዝና እና ወሊድ
▪️ስለ ጉርምስና አካላዊ ለውጦች
▪️ስለ ወሲብ ጥቃት ምንነት/ በሚያውቁት ሰውም ሊደርስ እንደሚችል
▪️ጥቃት ቢደርስ የነሱ ጥፋት እንዳልሆነ እና መናገር እንዳለባቸው
▪️ ሰዎች ያለ አግባብ ሲደርሱባቸው እምቢ ማለት እንዳለባቸው፣ ከአሳቻ ስፍራ መራቅ እንዳለባቸው ማስረዳት ተገቢ ነው::

🔹ከ 11 አመታቸው በኋላ ያለው Formal Operational stage ይባላል:: Deductive reasoning ይጠቀማሉ:: ማለትም ከሰፊው አለም ተሞክሮ በመነሳት የራሳቸውን ባህርይ መገምገም ይችላሉ:: ምናባዊ ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመር ይጀምራሉ::

ማንነት የሚገነባበት ወሳኝ እድሜ ነው:: ጠንካራ ማንነትን መገንባት ካልቻሉ ለአቻ ግፊት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ::

የጉርምስና እድሜ እንደመሆኑ በአካል ላይ የሚታዩ ለውጦች አሉ:: ጾታዊ ፍላጎታቸውም ይጨምራል:: በተለያዩ ምክንያቶች(ተታለው፣ በስሜታዊነት፣ በአቻ ግፊት..) ለጾታዊ ጥቃቶች ሊጋለጡ ይችላሉ:: ታዲያ በዚህ እድሜያቸው እንቁላል መለቀቅ ስለሚጀምር እርግዝና ሊፈጠር ይችላል:: ስለዚህ ውይይታችን እነዚህን ጉዳዮች ያቀፈ መሆን ይኖርበታል::

Reference : Kaplan and Sadocks comprehensive textbook of Psychatry እና kelela guide

✍️ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

☎️ የህፃናት ሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

Youtube : https://youtube.com/@bruhkids-t1e?si=zNP_thRi4mRnN6ውት

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

15 Aug, 18:47

ከ7 ወር ጀምሮ ቁርስ ምሳ እራት እና መክሰስ ፕሮግራም ለህፃናት 👇👇👇
https://youtu.be/WhlGM8XkoAo?si=59NgvlFtHQ2bFWx0

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

03 Aug, 09:06

🔊 ስለ ሄፓታይትስ (#ጉበት #ቫይረስ ) መረጃ አለዎ ይሄንን ከታች ያለው ብሮሸር ያንብቡ
👉 ምርመራ እና ሕክምና ከፈለጉ ይደውሉ
☎️ 0984650912

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

31 Jul, 05:24

#ሻይ በተደጋጋሚ ለልጆች የምትሰጡ ወላጆች ጥንቃቄ አድርጉየሻይ ጥቅሙን እና ጉዳቱን እዝህ ቪዲዮ ላይ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/1d4dJfGjIDo?si=aPu4baT5TnRTGGOO

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

27 Jul, 08:17

😪 ልጄ 4 አመቷ ነው ግን አታወራም ምን ይሻላልችግሩ ምንድነው መፍትሄውስ 👇👇👇👇
ሙሉ መረጃው "ብሩህkids" youtube ቻናልችን ላይ ያገኙታል 👇👇👇
https://youtu.be/jD9RNHdZINE?si=G2sTojcNF-_N-dGE

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

18 Jul, 18:26

🔊 ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ !!

በክረምት የእረፍት ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸው በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል አሳሰበ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ዛሬ (ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም) ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ውሃ ባቆረ ጉድጓድ የገባ ታዳጊ ህይወቱ ማለፉን ገልጸዋል።

" ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ዋና ለመዋኘት የገባ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አልፏል" ያሉት አቶ ንጋቱ፣ "የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊውን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ አስረክበዋል " ብለዋል።

" በአዲስ አበባ ታዳጊዎችና ወጣቶች በቂ የዋና ችሎታ ሳይኖራቸው ለዋና በሚል ውሃ ባቆሩ ጉድጓዶች እየገቡ ህይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።

አሁን ትምህርት ቤቶች ዝግ ስለሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች ለጨዋታ በሚል ድርጊቱን ስለሚፈጽሙ ወላጆች በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ አደጋውን ለመከላከል የሚያሰችሉ በሚል በተደጋጋሚ የሚያስተላልፋቸውን የጥንቃቄ መልዕክቶች ህብረተሰቡ፣ በተለይ ወላጆች፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች  እንዲተገብሩ ጠይቋል።

👉 ህፃናት በክረምት ወቅት ምን ማድረግ አለባቸው ይሄንን ቪዲዮ ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/B14C3TjjS7E?si=7k3T7VSpen442Drn

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

15 Jul, 14:06

#ምግብ አልበላም ብለው ለሚያስቸግሩ ህፃናት 8 መፍትሄዎች 👇👇👇

ሙሉ መረጃውን ብሩህkids youtube ቻናልችን ላይ ያገኙታል ሊንክ 👇👇👇
https://youtu.be/r7v5RhqREmQ?si=NKmX8lfKFBC8UteD

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

13 Jul, 11:36

🔊 ልጅዎ ላይ #ራስመሳት #ማንቀጥቀጥ አጋጥሞት ያቃል ኢፕለፕሲ ምንድነው በምን ይከሰታል ሙሉ ማብራሪያውን እዝህ ቪዲዮ ላይ ያገኙታል 👇👇👇

https://youtu.be/owjfZm4CeWA?si=WtclKRwMaTT2Fvlx

🔊 #ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ሰኞ እሮብ እና አርብ 7:00 ላይ እናቀርባለን 👍

👉 Subscribe አርገው የደወል ምልክቱን click ያርጉ ሁሉም ቪዲዮዎች ይደርሶታል

🔊 በነፃ ይማሩ ልጅዎን ጤና ይጠብቁ

☎️ ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

☎️ በመጠነኛ ክፍያ ቀጥታ ማማከር ከፈለጉ 0984650912 ይደውሉ

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

09 Jul, 04:33

⚠️ #ኮኮሜሎን ካርቱን ግብረሰዶማዊነት እንደሚሰብክ ያቃሉ

ሙሉ መረጃውን youtube ቻናላችን ላይ ያገኙታል 👇👇👇👇
https://youtu.be/f3W5gdeArPQ?si=l1zkk_YN6yhjE6Iu

🔊 #ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ከዝህ ሳምንት ጀምሮ ሰኞ እሮብ እና አርብ 7:30 ላይ እንቀርባለን 👍

👉 Subscribe አርገው የደወል ምልክቱን click ያርጉ ሁሉም ቪዲዮዎች ይደርሶታል

🔊 በነፃ ይማሩ ልጅዎን ጤና ይጠብቁ

☎️ ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

☎️ ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 0984650912 ይደውሉ

34,176

subscribers

248

photos

3

videos