የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch @theideaofs Channel on Telegram

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

@theideaofs


እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch (Amharic)

የዘር ሐሳቦች በTelegram በተጠቃሚ ቤት በመቀበል እና በመባል የሚከፈለኝ እርምጃዎችን በሚመለከት የተለያዩ ዘር ሠራተኞችን በመረዳጃ ነው፡፡ የሚሸከፉትን የህብረትና የሴት ሓፍት ወይም ቀንስትና በአሉባቤ የተገኘባትን ወቅታዊ እርምጃዎቹን ይምረጡ፡፡ የመስራች እና ለማቆያ ደረጃም ያስችሉ፡፡ ሌሎች ከሌሎች ጠንካሮችን በመጠቆም ለምሳሌ፣ ለሚወስዳቸው ምሳሌዎች እንደገመቱና አገልግሎት፣ ነገር ግን ለነዋሪትና ለልማት ትክክለናል፡፡

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

09 Feb, 14:03


ሰዎች እንዲሰሙን እንፈልጋለን፣ እኛ ግን ሰዎችን እንሰማለንን?፣ ሰዎች እንዲወዱን እንፈልጋለን፣ እኛስ ሰዎችን እንወዳለን?፣ ሰዎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን፣ ሰዎችን ለማክበር ዝግጁ ነንን? የእኛ ነገር እንዲቀድም እንፈልጋለን፣ እኛስ ሰዎችን እናስቀድማለን?፣ ታናናሾቻችን እንዲታዘዙን እንጠብቃለን፣ እኛ ለታላላቆቻችን ታዛዥ ነን? ያልዘራነው ያጨደ፣ ያልተጋበትን የወረሰ፣ ያላሸነፈውን የገዛ ማነው? ያልዘራነውን የምንጠብቅ ሞኝ እንዳንሆን፣ እኛ እንዲደረግልን የምንፈልግ ለሌሎች እናድርግ።
..
ዘሪሁን ግርማ

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

04 Feb, 14:09


#የውሸት_ምላስ_ቀስቶች

"የሰዎችን ህይወት 'በውሸት' ለማጥፋት አንሞክር፣ እኛ 'በእውነት' ሊጠፋ የሚችል ማንነት አለንና።"

በሰዎች ላይ የሚዋሽ ውሸት መልኩ ብዙ አይነት ነው። ስለ ሰዎች መዋሸትና በሰዎች ላይ የምን ዋሸው ውሸቶች ምክንያታቸው ብዙ አይነትም ነው። የሰዎችን መልክ (Image) ማጠልሸት፣ ሙሉ እውነት ሳይኖረን የምንናገራቸው ግምታዊ ወሬዎች ጭምር ምንም ስለ እነዚያ ሰዎች ሙሉ እውቀት በሌላቸው ሰዎች ዘንድ የተሳሳተ እይታን ይፈጥራል። ስም መለጠፍ ቀላል በሆነበት በዚህ ጊዜ ደግሞ በማናውቀው ነገር ስለ ሰዎች የምንናገራቸው ውሸቶች ቀላል አይደሉም።

አንዳንድ ሰዎች ስለ እናንተ በጥላቻ፣ ወይም በግምት ዋሽተውባቸው፣ ውሸትን አውርተውባችሁ ያውቃሉን? አዎ ያጋጥመናል ወይም እኛም በሰዎች ላይ ዋሽተን ይሆናል።
ውሸት የሰዎችን መልክ ከማጠልሸት በላይ፣ የሰዎችን ስራ፣ አገልግሎት እና ትዳርና ግንኙነት ጭምር ያበላሻል። በጣም የሚገርመን በስህተት ተገኝተን ስለ እኛ ከሚነገር እውነት ይልቅ፣ በውሸት የሚዘራ ዘር ብዙ ነገራችንን ያበላሻል።

'ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው' እንደሚባለው አንዳንድ ውሸት ተወርቶ፣ ስር ሰዶ፣ ዞሮ ዞሮ፣ ተዘርቶ በቅሎ ፍሬን አፍርቶ ሲያበቃ የምንሰማቸው ብዙ ውሸቶች ይኖራሉ። ከጦር መሳሪያ በላይ የውሸት ወሬ ሰዎችን ከቤተ ክርስቲያን ያሳድዳል፣ ከአገልግሎት ያሰናክላል። ከህይወት ጭምር ያጎድላል።

የስም ማጥፋት ትልቁ መሳሪያ ውሸት ነው። ስም ደግሞ የሰው መልክ ነው። አንዳንድ ሰዎች ገምተን፣ አስበውና፣ ውሸትን ጸንሰው ስለ እናንተ የሚዋሹትን ውሸት አምነው የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ። ውሸት ነገ በእኛ ህይወት ላይ በክፉ የሚበቅል ክፉ ዘር ነው። ውሸት በቤተ ክርስቲያን መካከል ትልቁ የሰይጣን መሳሪያ ነው፣ ጥይቱም ውሸተኛ ሰው ነው።

ከላይ የጠቀስኩት አባባል ከቲክቶክ መንደር ስትዘዋወር ያገኘኃት ናት። "የሰዎችን ህይወት 'በውሸት' ለማጥፋት አትሞክሩ፣ እኛ 'በእውነት' ሊጠፋ የሚችል ማንነት አለንና።" ይላል ማለትም እኛ የእግዚአብሔር ምህረት የሸፈነው ቢገለጥ ሊያጠፋን የሚችል ብዙ እውነተኛ የሆነ ድካም አለብን። አደባባይ ላይ ቢገለጥ ማንም በእኛ ላይ ሳይዋሽብን ልንጠፋበት የምንችል እውነተኛ ድካም አለን። በሰዎች ላይ ዋሽተን የሰዎችን ህይወት በመኮነን የሚገኝ ራስን የማጽደቅ ስራን መስራትና የሰዎችን ስምና ማንነት ማጠልሸት መልሶ ክፋቱ ለእኛው ነው።

ውሸት ውሸት ሆኖ አይቀርም መገለጡና ወደ ብርሃን መምጣቱም አይቀርም። ስለ ውሸት መልስ የሚሰጡ ሁለት ነገሮች አሉ እነርሱም፦ እግዚአብሔር እና ጊዜ ናቸው። እግዚአብሔር ውሸትን ወደ ብርሃን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ በእውነት ጌጥ የተለበጡ ውሸቶችን ጭምር በእውነተኛው እውነት ይገልጣቸዋል።

እግዚአብሔር ከሚጸየፋቸው ነገሮች መካከል
"በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።" ምሳሌ 6፥19

በጥላቻ መዋሸት፣ በቅናት መዋሸት፣ ለማጣላት መዋሸት፣ ሰዎችን ለመጉዳት መዋሸት፣ ራስን የተለየ አድርጎ ለማሳየት ስለ ሌሎች መዋሸት፣ ሰዎች ባልተገኙበት ማስቀመጥ፣ የሌላቸውን ማናንነት በውሸት ማሰጠት፣ ስማቸውን ማጥፋት፣ በአገልግሎታቸውና በነገራቸው ላይ የውሸት ቃላትንና ዘርን መዝራት መልሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲመጣ አዝመራው ከባድ ነው። በሰዎች ላይ የምንዘራቸው ክፉ ዘሮች አዝመራው የሚታጨው በእኛ ቤት ነው።

ሳናውቅ ተነድነተው፣ አውቀንም በክፉት፣ አልፈን በአመጻ ሰዎች ላይ ስለ ተናገርናቸው ውሸቶች ጌታ ይቅር ይበለኝ። በማናውቀው ነገር ገምተን፣ መዋሸት ሱስ ሆኖብንም ብንሆን ጌታ ይቅር ይበለን። እኛ በጀመርነው ውሸት ወይም ከሌሎች ውሸት ጋር ተባብረን ውሸትን ስላገነንን ይቅር ይበለን። ማናችንም በዚህ በደል ልንገኝ እንችላለን፣ ይህ ጽሑፍ ራሳችንን እንድናይ ማንቂያ ነው እግዚአብሔር ይቅር ይበለን።

..
ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

15 Jan, 01:23


#እግዚአብሔር_ያያል!!

፨ በማይመች የህይወት መንገድ ላይ እያለፋችሁ እንኳ ጸንታችሁ እያገለገላችሁ ላላችሁ፣ እግዚአብሔር ያያል። ጽኑ።

፨ ስለ ወንጌል ብላችሁ፣ ክብራችሁ እንደ ነውር የተቆጠረባችሁ እናንተ እግዚአብሔር ያላችሁበትን ያያል። ጽኑ።

፨ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈጸም ታዛችሁ በመንገዳችሁ ወደ ኃላ የቀራችሁ የመሳላችሁ በማይመስል መንገድ ላላችሁ፣ መዘግየት ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ የለም፣ እግዚአብሔር የምታልፉበትን ያያል። ጽኑ።

፨ በቅንነት መንገድ እየሄዳችሁ ቅን ባልሆኑ ሰዎች ክፋት የተጎዳችሁ። እግዚአብሔር ያያል። ጽኑ።

፨ ነፍሳችሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ በመፈጸም ጠባብ መንገድ ውስጥ እያለፈች፣ በሰፊው መንገድ ላይ በሚመላለሱ ስኬትና ተድላ በሚመስል ጎዳና በሚሯሯጡ ሰዎች አመጻ የተጨነቃችሁ እግዚአብሔር ያያል። ጽኑ።

፨ የፍሬያማነት ዘመናችሁ እስኪመጣ፣ በመካንነት ስድብ ውስጥ እያለፋችሁ ያላችሁ እግዚአብሔር ያያል። ጽኑ።

እግዚአብሔር ያያል፣ የማያየን በሚመስለን ጊዜ ራሱ እያየን ነው። የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በፊቱ የተረሱ አይደሉም። ትግላችን ማብቂያ አለው፣ የተናገረን ቃል ፍጻሜ አለው። ይህ መልዕክት እግዚአብሔር በተናገራችሁ ነገር ላይ ቆማችሁ፣ በታማኝነት አሁንም ድረስ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ቦታ ላይ እያገለገላ ችሁና እና እየተመላለሳችሁ ላላችሁ ለእናንተ ነው። እግዚአብሔር ያያል ጽኑ። ምላሽ አለው፣ በጊዜው ሁሉም ውብ ይሆናል። የስንፍና ቃል አትናገሩ፣ ለሁሉም ድልን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ያያል።

ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

21 Dec, 18:50


#ይህችስ_ጉዳይ_ከፍየሏ_ያለፈች_ናት😁

አንዲት ልጃገረድ በድብቅ የምታፈቀረው ጓደኛ ነበራት ያንን ጉዳይ ቤተሰቦቿ አያውቁም ነበር። በዚያ ሁኔታ ውስጥ በድብቅ የምታፈቅረው ሰው ይሞታል። የነበራትን ድብቅ የፍቅር ግንኙነት ስለማይታወቅ እና ምንም ማለት ስላልቻለች ዝም አለች። በዚህ በቤታቸው ያለች አንድ ፍየል ሞተች። ልጃገረዲቱ በፍየሏ እያሳበበች ጠዋት ማታ ማልቀሷን ቀጠለች። አባቷ "በእርግጥ ያሳዝናል ለፍየል ይህን ያህል አይለቅስም" አሏት። ልጅቷም አላቆመች በየጊዜው ማልቀሷል ቀጠለች አባቷም "ይህስ ጉዳይ ከፍየሏ ያለፈች ናት" አሏት። አንዳንድ ጉዳዮች ከጀርባቸው ከታየው ሁኔታ በውስጥ የተለየ ምክንያት ያላቸው ይሆናሉ😁😁

( ታሪኩን አንድ ወዳጄ እንዳጫወኝ)

Repost

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

07 Dec, 07:54


#የአምልኮ_መሪዎች_የመዝሙር_ሩጫ!!

የዛሬ ወር ገደማ አንዲት ቤተክርስቲያን ለመታደም ሄድኩ፣ በመድረኩ ላይ ያለው የቤተክርስቲያኒቱ ወጣት የአምልኮ መሪው እየዘመረ ደረስን። እኛም በተገኘንበት ጉባኤ ለማምለክ ቆምን፣ ዝማሬውን የሚመራው ወጣት፣ የሚዘምረው የመጋቢ ተከስተ ጌትነት "ልሰዋ የምስጋናን መስዕዋት" የሚለውን first/ walz መዝሙር ነበር። ያለማገነን ወዲያው መዝሙሮቹ በቅጡ ሳናመልክባቸው ወዲያው ወዲያ መቀያየር ጀመሩ። የመልዕክት ፍሰት መጠበቁን እንተወውና ዝማሬውን በቅጡ አስተውለን ሳንዘምረው ወደ ሌላ ዝማሬ 'የልቤ ደስታ ጌታ' ' አይገርምም ወይ' 'ፍቅር ነህ' ኦ እኔ ማነኝ' በዝማሬው ምን ቀረን 'የመዝሙር አልቀሞችን' አስጎበኘን።

አምልኮ ብዙ ዝማሬ ማወቅ ወይም መዘመር አይደለም። የአምልኮ ዝማሬዎቻችን ድሮ ቡሌ እንደምንለው አይነት ምግብ የተለያዪ መልዕክትና የተለያዩ 'ስታይል' የምናይባቸው ከመሆን ይልቅ የዝማሬ ብዛት መደርደርና የድምጽ መስረቅረቅ (በራሱ ችግር ባይሆንም) ብቻ ላይ ያተኮረ እንዳይሆን ብዬ እሰጋለሁ።

በመዝሙር አንደነቅም፣ በመዝሙር ጌታን እናመልካለን እንጂ። በ First ወይም በ Sixth የምናውቃቸውን ሁሉ መዝሙሮች ስለገጡሙ ብቻ መዘመር የለብንም። መጽሐፍ ቅዱሳችን በመዝሙር 47:7 ላይ "በማስተዋል ዘምሩ" ይለናል። እንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱሱ "Sing with Understanding." ይለናል። በመረዳት መዘመር ያስፈልገናል። የምናመልከውን አምላክ በመረዳት፣ የሞናቀርብለትን ዝማሬ በመረዳት ሲሆን ጥሩ ነው።

ይህው ወጣት ልጅ አምልኮን ቀጥሏል፣ የመዝሙር ስልቱን ወደ Welo ምት ወደ ምንለው ተለወጠ። መዝሙር ሲዘምር እንዳደገና ሰው ዝማሬም፣ ዘማሪዎችን እንደሚወድና እንደሚያከብር ሰው በቤተክርስቲያን አገልግሎት የቆዩትንም ወጣቶቹንም ዘማሪያን ሲያገለግሉ ሳይ ደስ ይለኛል። ወጣቱ 'ከፊት ከፊቴ ጌታ ወጣና' የዘማሪ ዮሴፍ አያሌው ዝማሬን በወሎ ምት በመዘመር ጀመረና፣ ከላይ እንዳየነው ከአንዱ መዝሙር ወደ ሌላ መዝሙር ይቀያየር ጀመር። መልዕክቱ ተያይዞ አይፈስም፣ ስለ አምልኮ፣ ስለ ምስጋና፣ ስለ ድል፣ ስለ ውጊያ በአንድ መድረክ ላይ አቀረበልን።

ይህ ጽሑፍ ስለ ወጣቱ ልጅ አገልግሎት ለትችት የተጻፈ አይደለም። ነገር ግን በዝማሬ ጉባኤውን በአምልኮ የሚመሩትን ለማንቃት የተጻፈ ነው። መድረኩ የጌታ ነው፣ ህዝቡም የጌታ ነው፣ አምልኮውም የሚቀርበው ለጌታ ነው። ምስጋና (Praise) ሲቀርብ የሚመሰገነው እግዚአብሔር ቢሆንም፣ ህዝቡ ሁሉ ስለተደረገለት ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግናል። አምልኮ ሲቀርብ ደግሞ ከእግዚአብሔር ማንነት ብቻ ተነስተን ስለሚገባው ብቻ የምናቀርበው መስዕዋት ነው። ስለዚህ በመድረኮቻችን ላይ ለእግዚአብሔር የምናቀርበው መስዕዋት ዙሪያ ላይ ምን ማቅረብ እንዳለብን ማወቅ አለብን ባይ ነው።

አምልኮ ለጌታ ነው! ለጌታ የምንሰጠውን ነገር አክብረን እንስጠው። ከዚያ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም እግዚአብሔር የሚመለከው በፈጣን መዝሙሮች ነው ወይም አይደለም ረጋ ባሉ መዝሙሮች ነው የሚሉ ውይይቶች ሰምቼ አውቃለሁ። እኔ ከሁለቱም ጋር የለውም። ለእኔ እንዴትም አምልክ ለእግዚአብሔር ክብር የሆነ ነገር ሁሉ አምልኮ ነው። የዚህ ጽሑፍ አላማ የመድረክ አገልጋዮች እንዲህና እንዲያ ያገለግሉ ለማለት አይደለም። የምናቀርበው መልዕክት፣ ፍሰትና የአዘማመርና መልዕክትን የምናቀርብበትን መንገድ ነው። አምልኮ እኮ ለጌታ ነው ስለዚህ እንዴትስ ቢዘመር የሚል ጥያቄ ድንገት ከተነሳ፣ አምልኮ ለጌታ ነው ነገር ግን የአምልኮ መሪው እያገለገለ ያለው በጉባኤው መሐል ነው ለብቻው አይደለም። ቅዱሳኑ አብረውት እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ የማድረጉ ስራ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ የአገልጋዩ ነው።
......

ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

26 Nov, 08:49


እገሌ እንትና ከኦርቶዶክስ ወደ ወንጌላውያኑ ቤተ እምነት መጣ ተብሎ የሚጨፈረውን ጭፈራ ሁልጊዜም ያስፈራኛል። የሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስ ማግኘትና የድነት ጉዳይ ቢያስደስተኝም ግርግሩ ደግሞ ተገቢነት ያለው ነገር እንዳልሆነ ይሰማኛል መዳን የግል ነው፣ የቤተ እምነቶች በላጭነት የምናሳይበት መጠቀሚያ የምናደርገው አይደለም። ፉክክርና ውድድር የለንም።

የአንዱ ነፍስ ከአንዱ የበለጠ አይደለም፣ የተለየም አይደለም ኢየሱስ ለማይታወቀውም ሰው ለሚታወቀውም ሰው እኩል ነው የሞተው ነፍስም እኩል ነው። አንዳንዴ ቀድሞ በተለያየ ምክንያት የሚታወቁ ሰዎች ወደ ድነት ሲመጡ ብዙዎች ወንጌል እንደርሳቸው ሊጠቀምበት እግዚአብሔር ይችላል። ያም ቢሆን 'አዋራው ጨሰም' ተገቢ አይደለም። በእግዚአብሔር ዘንድ ታዋቂም አዋቂም የለም፣ ሁሉም ነፍስ በፊቱ እኩል ናቸው።

የምንወደው ዘማሪ የሐዋዝ ወደ ኦርቶዶክስ እመለሳለሁ ማለቱ በራሱ ችግሩ ባይታየኝም መብቱም እንደሆነ ባውቅም፣ ጥያቄዬ ግን ለዘማሪ ሐዋዝ "ምን አግኝተህ ነበር ወደ ወንጌላውያኑ ክርስትና የመጣህው?" ደግሞስ " ከወንጌላውያኑ ምን ስታጣ ነው ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሻለሁ?" ያልከው ለምንድነው የሚለውን ብናውቅ ጥሩ ነው።

ከእውነት ገብቶን ያልሆነ ወደ ኦርቶዶክስ በመሔድ ወይም ከኦርቶዶክስ ወደ ወንጌላውያኑ በመምጣት የሚደረግ ግርግር ፈጠራ እየተበራከ እንዳለ እያየን ነው። በጣም የሚገርመው እዚሁ እኛ ቤት የሆነ ፌመስ ሰው መጣ ሲባል ያለው ግርግር ያስፈራኛል። ታዋቂ ሰዎች ወደ ጌታ ስለመጡ ብቻ በእነርሱ ግርግር መፍጠርም ተገቢነት ያለው ስራ አይመስለኝም። ይህ መታረም ያለበት ነው። ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ የሚባሉ ሰዎችን በመያዝ ወንጌላውያኑን ለማቃለል የሚደረግም ጭፈራ ተገቢነትም፣ ተቀባይነትም አይኖረውም።

እንደ ዘማሪ ሐዋዝ ሁሉ ነገ ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሰናል የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ እንዲሁም ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ወንጌላውያን በመቀላቀል ወንጌልን የሚቀበሉ ነገም ሊመጡ ይችላሉ። በሁሉም ረገድ ማጯጯህ የክርስትና መርህ አይደለም።

ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

20 Nov, 00:47


'ጊዜው' የእኔ ብሎ የሚያስብ ሰው፣ ጊዜውን የተቀበለው በሌሎች ጊዜ ውስጥ ነውና፣ የቀደሙትን ጊዜ ማክበር አለበት። የእርሱ ጊዜ እንዲጸናና እንዲዘልቅ ነገ ጊዜውን የሚረከቡትንም ተተኪዎችን ማክበር አለበት። ከምንም በላይ የጊዜ ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር መሆኑን በመረዳት ክብሩን ለእግዚአብሔር መስጠት ያስፈልገዋል።

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

27 Oct, 19:39


ንጹህ ልብ ያላቸው ሰዎች ያስቀኑኛል፣ ቅኖች ይገርሙኛል፣ እውነተኞች ያጀግኑኛል።

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

06 Oct, 04:22


#የማያድግ_ልጅ_አባቶቹን (#ታላላቆቹን) #ይሳደባል!!


በቀደሙት ዘመናት በአገራችን እናትና አባትን እንዲሁም ትልልቆችን ማክበር ባህልና እሴታችን ነበር። አሁን ጨርሶ ጠፍቷል ባልልም፣ እየጠፋ እንዳለ እሙን ነው። አንደኛው ምክንያቱ ምሳሌ የሚሆኑ አባትና እናት መብዛት እንዳለባቸው ያመላክታል። ግብረ ገብ ተብሎ በፊት በትምህርት የሚሰጠው ትምህርት ብዙዎቹን በስነ ምግባር የታነጹ እንዲያድጉ እንዳደረገ የታወቀ ነው። ሰው እግዚአብሔርን ካላስቀደመና ታላላቆቹን ካላከበረ ተማረም አልተማረም የህይወቱ ፍጻሜ አያምርም።

አሁን አሁን አዲሱ ትውልድ ደግሞ እናትና አባትን አለማክበር ብቻ ሳይሆን በዕድሜ ትላልቅ እንዲሁም በስራቸው ታላላቅ የሆኑትን ማክበርን እየረሳ እየመጣ ነው። ይህን በስርአቱ በማስተማር ረገድ ቤተሰቦች፣ መምህራን፣ ለአገር ታላላቅ ነገር ያበረከቱ ታላላቅ ሰዎችን፣ የቤተክርስቲያን አባቶችን እንዲያከብሩ ማስተማር ማህበረሰቡ ሐላፊነት የነበረበት ቢሆንም፣ አሁንም ይህ ትውልድ ነቅቶ ራሱን ማረም አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ “አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።” ይለናል።

የምናፍራቸው አባቶች፣ ታላላቅ ሰዎች ያስፈልጉናል። ይህን ነገሬን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? ብለን የምናፍራቸው፣ የምንሰማቸው፣ የሚመክሩን ሰዎች ያስፈልጉናል። የምንገሰጽላቸው ታላላቅች ያስፈልጉናል፣ የምንሰማቸው ታላላቆች ያስፈልጉናል።

በሩቅ ምስራቅ "ሽማግሌ በእግዚአብሔር ይመሰላል" ይላሉ። ታላላቆች ህይወትን በብዙ መንገዴ አልፈው በትናንት ዛሬን ወልደው ትልውዱን እዚህ አድርሰዋል። በህንድ አገር ያለ ታላቅ ስርአት አለ። ይህውም እናትና አባታቸውን ታላላቅ ሰዎችን ዝቅ ብሎ እግር የመንካት ልምድ ነው። ይህ በእነርሱ ቋንቋ "አሺርቫት" ወይም "ምርቃት መቀበል" ይሉታል። ታላላቆች ላይ አፍን መክፈት ይቅርና አለማክበር በራሱ ክፍያ አለው። ሽማግሌዎች (አባቶች) አያጠፉም የሚል አመለካከት ባይኖረኝም፣ አይናቁም ወይም እነርሱን ከማክበር መጉደል የለብንም።
አባቶችም፣ መከበር በሚገባቸው መስመር መኖር እንዳለባቸው አምናለሁ። በአኪያሄዳቸው የማንከተላቸው አባቶች ቢኖሩ እንኳ፣ በአባትነታቸው (በሽምግልናቸው) መከበር አለባቸው።

አንዳንዴ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጭ ብለው በዕድሜ የሸመገሉትን የሚዘረጥጡ፣ ብዙ አመት ያገለገሉት ላይ አፍ የሚያላቅቁን ሳይ ስለ ነገአቸው እፈራለሁ። አባትና እናትን ያለማክበር አደጋዎች ብዙ ናቸው። ከእነዚህ መሐል ሁለቱን ላንሳ፦ ያለ ማክበር አደጋዎችን ሳነሳ በማክበር ውስጥ ያለን በረከትና ተስፋ በተቃራኒው እንረዳለን።

፨ አጭር ዕድሜ (ያለ ጊዜ መሞት)

መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንም በአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት ውስጥ ካስቀመጣቸው መሰረታዊ ህግጋት መሐል አባትና እናትን (በስጋም የወለዱንን እንዲሁም መንፈሳዊ አባቶችን) በማክበር ያሉትን መርህ ይናገራል።
እግዚአብሔር አስርቱን ትዕዛዛት ለሙ ሲጀምር የጀመረው በዚህ ወርቃማ መርህ ነው።
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።”
ዘጸአት 20፥12
“መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።”
ኤፌሶን 6፥2-3

ከላይ ያየናቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ይሰራል። ወጣቱ ትውልድ አባትና እናቱን ባለ መክበር የሚርስበት ነገር አንደኛው Premature Death ወይም "ያለ ጊዜው መሞት ነው። አባትና እናቱን የማከብር ልጅ እያድግም፣ አያፈራም። በምድር ላይ ላይ የምንኖረው ዕድሜ ፍሬያማና፣ ረጅም እንዲሆን አባትና እናትህን ማክበር መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው።

፨በረከታቸው ያስፈልገናል!!

አባትና እናት ላይ እግዚአብሔር ስልጣን አስቀምጧል። አንደኛው ስልጣን የመባረክ ስልጣን ነው። ያዕቆብ "በዘመናችሁ የሚያገኛችሁን እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ" አላቸው። ዘፍ 49:1 ተሰበሰቡም። ያዕቆብም በሁሉም ላይ የሚሆነውን ነገራቸው። እግዚአብሔር ነገአቸውን በያዕቆብ አፍ ሆኖ ለሁሉም ነገራቸው። ሁሉም ያዕቆብ ከነገራቸው ነገር ውጪ የተለየ የኖረ የለም።

በተጨማሪነት የያዕቆብንና የኤሳውንም የመባረክ ሒደት ስንመለከት ያዕቆብ በይስሐቅ በረከት እንዲባረክ ርብቃ ያደረገችበት መንገድ ከዚያም ኤሳው ሊባረክ ሲመጣ በረከቱ ወንድሙ መውሰዱን ስናይ በአባት ያለ በረከት የህይወታችን ፍጻሜ እንደሚወስነውና እንረዳለን። በአባቱ እና በእናቱ የተባረከ ትውልድ ብሩክ ነው። መንፈሳዊ አባትና እናት እግዚአብሔር ከሰጠን፣ እነርሱንም ማክበር እንዲያው ለበረከት ይዳርገናል። ሽበታሙንም ማክበር እንዲያው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያሰጠናል።

.....
ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

01 Oct, 15:52


አንዳንድ መጨረሻቸው የሚመስሉ ነገሮች ታላቅ ጅማሬን ይሰጡናል!!

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

01 Oct, 05:07


#ወይ_ምላስ!

ምላስ የስንቱን መንገድ አስቀየረ! የስንቱን ህይወት አጠፋ! ስንቱን በፍርሃት ወጥመድ ውስጥ ጣለ! የስንቱን መልካም ስም አጠለሸ! የስንቱን አገልግሎት አበላሸ! ምላስ። ስንቶች የሰዎችን ምላስ ፍራቻ የማይፈልጉትን፣ የማያምኑበትን ህይወት ሲኖሩ፣ የሚያምኑበትን ሲደብቁ አየን። ወይ ምላስ።

መጽሐፉ እንደሚል “አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።”
ያዕቆብ 3፥6

አንደበት እሳት ነው ማለቱ የምናነገረው ነገር የሰዎችን ነገር ይበላል ማለቱ ነው። በሰዎች የምላስ አንደበት መገረፍ የህይወት ዘመን ፈሪ ያደርጋል። መጽሐፉ አንደበቱን የገዛ ሁለንተናውን የገዛ የበሰለ ሰው ያለው ያለ ምክንያት አይደለም። ስንታይ ጨዋና ትሁት የምንመስል ስንነካ፣ ከአንደበታችን ሰዶምና ገሞራን እናዘንባለን። አንደበቱን የገታ በሳል ሰው ነው።
ምላስ እኛም፣ ሰይጣንም፣ እግዚአብሔርም ይጠቀሙበታል።

በሌላ መልኩ ደግሞ ምላስ የብዙዎችን መንገድና ህይወት ያቀናል። መልካም ምክሮች፣ ጥበቦች፣ እውቀቶች፣ ፍቅር በረከትም በምላስ ላይ ናቸው። በምላስ ላይ በረከትም እርግማን፣ ፍቅርም ጥላቻም፣ ጥበብም ውድቀትም፣ ስንፍናም ትጋትም፣ ቅንነትም ጥመትም፣ መደገፍም መጣልም አሉ። ህይወታችንን የተከራየው የትኛው ይሆን? የሚያንጸው ወይስ የሚያፈርሰው?

ጌታ እግዚአብሔር ይርዳን፤ በጸጋው ይደግፈን።

ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን?
ያዕቆብ 3:11
..
ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

01 Oct, 04:47


አንደበትህን ለክፉ ነገር አታሰልጥን፣ ልብህን ለጥመት አታስገዛ፣ አዕምሮህን በከንቱ ሐሳብ አትጥመድ።

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

29 Sep, 16:45


"ያየሃቸው ህልሞችህን የሰው ውሳኔ አይሽራቸውም።

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

25 Sep, 16:27


#የመሻሸቂያ "ወንጌል" የለም!!

መድረኮቻችን ወንጌል ተኮር ከመሆን ይልቅ ለተለያዩ ሰዎች የመልስ ምት ማስተላለፊያ እየሆኑ ከመጡ እየሰነበቱ ነው። ምስባኩ የወንጌል፣ አላማውም ቅዱሳንን ለማነጽ መሆን ተገብቶት ሳለ፣ አንደኛው ለአንደኛው አገልጋይ፣ አንደኛው አገልጋይ የሌላኛውን ስም ማጠልሻ መንገድ እየሆኑ ነው። ስጋ ስጋ የሚሸቱ ትምህርቶችና እንቅስቃሴዎች በግልጽ በየ ምስባኩ ይገለጣሉ።

በተለያየ የህይወት ምዕራፍ እያለፈ ያለው ምዕመን እግዚአብሔር በቃሉ ቢናገረኝ፤ ከዚህ ህይወቴ የምሻገርበት የእግዚአብሔርን ጸጋ እካፈላለሁ ብሎ ወደ ጉባኤ ሲገባ፣ እርሱ በማያውቀው ጦርነት መድረኩ ተሞልቶ ይጠብቀዋል። የመበሻሸቂያ ስብከት ብቻ ሳይሆን የማብሸቂያ መዝሙሮች፣ ጸሎቶችና አዋጆች ጭምር መድረኮች ማየት ጀምረናል።


ምስባኩ የእግዚአብሔር ነው፣ እጅግም የከበረ ስፍራ ነው። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እጥረት (ድርቀት) ሲኖረን፣ ወይም ከሌሎች ጋር ፉክክር እና መገፋፋት ሲኖር የውድድር "ስብከት" በተለያዩ መንገዶች ይተላለፋል። ወደ መድረክ ለመስበክ ከመውጣታችን በፊት የዝግጅትና የጸሎት ጊዜ፤ የእግዚአብሔርን መንፈስ ምሪት የማዳመጥ ጊዜ፣ ለጉባኤው ለመጣው ህዝብ የእረፍትና የመመለስ መልዕክቶች ለማስተላለፍ በተቻለው መጠን ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

የምንመራው ህዝብ ለእኛ የግል ጦርነት መሳሪያ ማድረግ እጅግ ታሪካዊ ክስተት ነው። አንዱ በመድረክ ቆሞ የሚናገረው ነገር ለማን እንደሆነ ግልጽ በሆነ መልኩ ሲተላለፍ ይታያል። ምዕመኑም በግልጽ እስኪያውቅ ድረስ። ያ ጉዳይ ለምዕመናኑ ምንም ፋይዳ የለውም።

እውነት ለመነጋገር የተለየ ጥቅም ከሌለ በቀር አንዳንዶች ለምን እንደሚገፋፉ መረዳቱ ራሱ ይገመርኛል። ሁሉም በተሰጠው ስፍራ የተሰጠውን የእግዚአብሔር አደራ መልዕክት ማስተላለፍ ሲገባ ምስባኩን ሰው ሰው የሚሸት መንፈስ ቅዱስ የሌለበት ከማድረግ ልንቆጠብ ንስሐ ልንገባም ጭምር ያስፈልገናል። መልዕክት ከሌለን የግድ መጨነቅ እኮ የለብንም መድረኩን በትክክል ለሚያገለግሉ ማስተላለፍ ይቻላል።

ይህ አይነቱ ችግር እያደገና እየሰፋ አንዱ ከአንዱ በሚኖረው የግል ጦርነት ውስጥ ሌሎች የሚመስሉትን አገልጋዮች በመፈለግ የራሱን ጎራ ለማደራጀት ይጠቀማል። ጎራና ግለኝነት እነዚህ ሁለቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግሮች እየሆኑ ነው።

በቅንነት ለመናገር ያህል እነዚህ ነጥቦችን ብናስተውላቸው መልካም ነው

፨ መድረኩ የእግዚአብሔር ከሆነ ህዝቡም የእግዚአብሔር ነው!!

፨ የተሰጠን ህዝብ የእግዚአብሔር አደራ ነው!

፨ የተሰጠን መድረክ የእግዚአብሔር ወንጌል ለመስበክ ታላቅ እድል ነው!

፨ ብዙ ምዕመን በብዙ ችግር ውስጥ እያለፈ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ካለበት ነገር የሚያወጣው መልዕክት ይፈልጋል (ያስፈልገዋልም)

፨ በየ መድረኮቻችን የምንናገረው ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት የሚያስጠይቁን ናቸው

፨ አለማዊነትና ስጋዊነት በውጪ ሞልቶ ሳለ ህዝቡ የእግዚአብሔር የሆነን ነገር ከቤቱ ለማግኘት ፈልጎ ይመጣል።

ስለዚህ በየ ምስባኮቻችን ላይ ቃሉን እንስበክ እናስተምር፣ መበሻሸቂያና ሌሎች አገልጋዮችን መቃወሚያ ጥቅስ አይጠቀም። በሾርኔም በእግዚአብሔር መድረክ ሰዎችን አንማ።
.....
ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

20 Sep, 05:11


What attracts God is not your speaking ability and activity, but the soundness of your heart (Motive).

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

20 Sep, 05:05


እግዚአብሔርን የሚማርከው የንግግር ችሎታህና እንቅስቃሴህ ሳይሆን የልብህ (Motive) ጤናማነት ነው።

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

17 Sep, 20:15


#የመሪ_ስነ_ምግባር

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለአገር ለቤተክርስቲያን ለቤተሰብ መሪን ይሰጣል። እግዚአብሔር መሪዎችን በመስጠት በረከትን ይሰጣል። እግዚአብሔር መሪዎችን በመስጠት የሚታወቅ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ሲባርክህ ትክክለኛ መሪን ይሰጠናል። እግዚአብሔር የሚመራን በሚሰጠን መሪዎች ጭምር ነው። ጤናማ መሪ ያላት ቤተክርስቲያን እና ሃገር የተባረከች ናት።

መሪ የራሱ ስነ ምግባር አለው። መሪ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምንም ቢሆን እንኳ መሪዎች ስነ ምግባር ሊኖረው ይገባል። መሪ የስነ ምግባር መርሆችን ካልተከተለ የሚመራው ተቋም ላይ መከፋፈልና፣ አለማደግን ይመጣል።

የመሪ ስነ ምግባር ከሌለ ውጤት የለም። በጸጋ ብቻ የሚመጡ ውጤቶች ዘላቂ አይሆኑም ጸጋውን ይዘን የምንቀጥልበት የበሰለ መሪነት ያስፈልገናል፣ ስነ ምግባር ከሌለ እውነተኛ ለውጥ የለም። መሪነት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ሲሆን፣ ራሳችን ላይ በመስራት የምናሳድገው ጭምር ነው። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንደኛው ተግዳሮች በስነ ምግባር የታነጹ መሪዎች ጉድለት ነው። ስነ ምግባር ማለት እግዚአብሔር ለሰጠን የመሪነት አደራ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃልና በበሰለ አመራር የምናበቃት መንገድ ማለት ነው።

እንከን አልባ መሪ የለም። አይኖርምም። አንድ እንከን አልባ መሪ ኢየሱስ ብቻ ነው። ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችን ላይ በመስራት በተሰጠንን አደራ ራሳችንን በማብቃት ከሰራን፤ ጥሪው ካለንና ጥሪያችንን ካሳደግን ውጤታማ መሪ እንሆናለን።

መሪ ስነ ምግባር አለው ስንል ከመሪ የሚጠበቁ መሰረታዊ ነገሮች አሉ ማለታችን ነው። መሪ ቀዳሚ እንደመሆኑ ምሳሌ መሆንና ለሚመራቸው ትክክለኛ መሪ መሆን አለበት። እስቲ በጥቂቱ የመሪ ስነ ምግባር የሆኑትን እንመልከት።

የመሪ ስነ ምግግባር

1፣ መሪ ይቅርታ አይራጊ ነው። መሪ ምሬትና ጥላቻ የተሞላ መሆን የለበትም። መሪ በተለያዩ ሰዎች ከቅርብም ከሩቅም፣ በውሸት፣ በመከዳት ጥለውት በሚሄዱ ሰዎች፣ በተለያዩ መንገድ ውስጥ ሊያልፍ ይችላል። መሪ በይቅርታ ለመመላለስ ራሱን ማዘጋጀት አለበት። መሪነት ሰዎች ብዙ በደል በመሪው ላይ የሚፈጽሙበት ስፍራ ነው፣ ይቅርታ ለማድረግ ካልፈቀደ መሪነቱን ቢለቅ ይሻለዋል። ስለዚህ ከመሪ መለየት የሌለበት ይቅርታ ማድረግ ነው።

2፣ አመስጋኞች መሆን አለብት። መሪ እግዚአብሔር ስለ ሰጠው ሰዎች፣ ስለ ተሰራው ስራ፣ በአገልግሎቱ ወይም በሚያስፈልገው ነገር አብረውት ስለቆሙ ሰዎች ተገቢ ምስጋና መስጠት አለበት፣ ከምንም በላይ አምላኩን አመስጋኝ መሆን አለብት። ማጉረምረምና መሳበብ መሞላትም የለበትም። ሰዎች ስላደሰጉለት ጥቂት ነገር አመስጋኝ የሆነ መሪ ውጤታማ መሪ ነው።

3፣ ትሁት መሆን አለበት። ከመሪ ህይወት የሚጠቀቀው ሌላኛው ነገር ትህትና ነው። ሁለቱ መሪዎች ማለትም ኢየሱስ እና ሙሴ ትሁቶች ነበሩ። ትህትና ለመሪነትን ሞገስ የሚጨምር በንግግር እና በስብከት ብቻ የማይገለጥ ነገር ግን በመኖር የሚታይ ህይወት ነው ትህትና። እግዚአብሔር ትሁት መሪዎችን ይስጠን።

4፣ አማኝ መሆን መቻል አለበት። መሪ በምንም መንገድ ውስጥ ቢያልፍ በእግዚአብሔር ማመን እና ለሚመራቸው እምነቱን ማጋራት አለበት። መሪው ያላመነውን ነገር ሌላው እንዲያምነው አይጠበቅም። ማለትም መሪው ያልኖረውን ህይወት ሌሎች እንዲኖሩት ግድ አይባልም።

5፣ የጸሎት ሰው መሆን አለበት። መንፈሳዊ መሪ የጸሎት ሰው፣ የራሱም ለሚመራት ቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመናን፣ ለአገልግሎቱ ጭምር የሚጸልይ መሆን አለበት። መሪ የምዕመኖቹን መንፈሳዊ ህይወት በጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ፣ በድምጽ ምዕመናኑን የሚመራ ነው። የማይጸልይ መሪ አገልግሎቱን በትግልና በሰው ምድራዊ ጥበብ ይመራል።

6፣ መሪ ሰጪ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ መሪ የምናውቀው ሰጪ ነው። ንፉግነት የመሪ መገለጫ አይደለም። መሪ ገንዘቡን፣ ጊዜውን ያለውን ነገር ሁሉ የሚሰጥ ነው። መቀበል ላይ የተመሰረተ አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፣ በመስጠት ውስጥ ያለ መቀበል እንጂ። መሪ ሰጪ ሲሆን እግዚአብሔር በሚሰጡት ሰዎች ይባርከዋል።

7፣ መሪ ትጉህ ነው!! መሪ ብሎ ሰነፍ ከሆነ አረም የሞላበት ተክል የሚጠብቅን ጠባቂ ይመስላል። መሪ ትጉህ ካልሆነ በመንጋው መካከል፣ አረም፣ ያልተገባ ነገር ይኖራል። ስንፍና ምንባቸው ይሆናል። ምክንያት እየፈጠረ ከሐላፊነት የሚሸሽ መሪ አይደለም። መሪ ትጉህ ነው፣ በተሰጠው ነገር በመትጋፍ ፍሬያማ ነው። የመሪ ሐብቱ ያቀደውን ነገር ለማስፈጸም መትጋቱ ነው። ምክንያት ደርዳሪነትና ስንፍና የመሪ መገለጫዎች አይደሉም።

8፣ መሪ የፍቅር ሰው ነው። መሪ የፍቅር ሰው መሆን ይጠበቅበታል። መንፈሳዊ መሪ ሲሆን ደግሞ ዋናው መሪ ኢየሱስ የፍቅር ሰው እንደ መሆኑ የእርሱ ፈለግ የተከተለ መሪ መሆን አለበት። መሪ ሁሉም ሰው ሊወደው አይችልም፣
ነገር ግን ሁሉን የመውደድ ግዴታ ግን አለብን። መሪ ከፍቅር ከጎደለ አመራሩ ሁሉ የወደቀ ይሆናል። የመሪነት ዋነኛው ቁልፉ ፍቅር ነው።

9. ሌሎችን የሚያነሳሳ ነው። መሪ የሚመራቸውን አካላት ለተሻለ ስራና አገልግሎት የሚያነሳሳ መሆን አለበት። ሌሎች መሪዎች ወደ መሪነት እንዲመጡ የሚያነሳሳ፣ ምዕመናኑን ለተለያዩ መንፈሳዊ ሐላፊነቶች እንዲበቁ የሚያነሳሳ መሆን አለበት። ትክክለኛ መሪ ሌሎች ለስራ ሲነሳሱ ደስተኛ ነው።

10፣ መሪ ሌሎችን አክባሪ ነው!! የማያከብር ሰው አይከብርም፣ ሌሎችን የሚያጣጥልና የሚያናንቅ መሪ ነገ በተከታዮቹ ያ ዕጣ ይደርሰዋል። መሪ የሚቀበለው ሁሌም የሰጠውን ነውና። ሰዎችን ባወቅን ቁጥር ማክበር ይበልጣል። ማክበር የመሪ ባህሪ ነው። የሚያከብር መሪ የሚከባበሩና፣ የሚያከብሩት ምዕመናንን ያበዛል። አገልጋዮችን ላይ የሚቀልዱ፣ በመንፈሳዊ ነገር የሚሳለቁ መሪዎች ልቅ ትውልድ ያፈራሉ። መሪ አክባሪ ነው።

11፣ መሪ መልካም ምክር ሰጪም ተቀባይም ነው። መሪ ለሚመራቸው መልካም ምክርን ይሰጣል። ምክርን በተገቢው ቦታ ለተገቢው ሰው ይሰጣል። ከሌሎች ምክርን ይቀበላል። ምክርን ላለመቀበል ግትር አይደለም። ጠቃሚ ምክሮችን ለመቀበል ትሁት ነው።

12 መሪ ገበና ሸፋኝ ነው!! መሪ በሚመራቸው ምዕመናን ህይወት የሰማውን ነገር ለስብከት ማጣፈጫ አያደርግም፣ ለሌሎች ለማይመለከታቸው የሰዎችን ማንኛውን ገመና አደባባይ አያሰጣል። መሪ ገመና ሸፋኝ ነው።

13, መሪ አንባቢ ነው፣ መሪ ራሱን ላይ በንባብ እና በትምህርት የሚሰራ ነው። ትናንት የተረዳውን ሰምቶ የመጣን ትውልድ የትናንቱን ስብከት በመደጋገም አያጸናውም። ከዚያ ይልቅ ቃሉን ያነባል ይቆፍራል። ያስተምራል፣ ይመራል።

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

17 Sep, 19:22


Surround yourself with people whose eyes light up When see you coming

አንተን ሲያዩ ደስ በሚላቸው ሰዎች ራስህን ክበብ!!

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

11 Sep, 08:01


ቀኖችን ፈጥሮ የሰጠን፣ ዘመናትን ያቀዳጀው እርሱ እግዚአብሔር ነው። በቀኖቹ ስንሰራባቸው እንለወጥባቸዋለን፣ ቀኖቹ ላይ ካልሰራንባቸው ቀኖቹ በላያችን ላይ ይለዋወጣሉ። በ 2017 ምን ብንጨምር ወይም ብንተው የምንላቸው ነገሮችን ምን ይሆኑ ብዬ ከራሴ ያወራሁትን ላጋራችሁ፤ እግዚአብሔር ዘመንና ጊዜን ከሰጠን አይቀር፣ መጨመር ያለብን፦

፨ እግዚአብሔር በሰጠን ዕድል ሁሉ አመስጋኝ መሆንን፣
፨ ባለራዕይነትንና ትጋትን፣ ራስ ላይ መስራት
፨ ፍቅርንና አብሮሰራተኝነትን
፨ መልካምነትንና ካለን ማካፈልን
፨ የሰዎችን ዋጋ መረዳትንና ማክበርን
፨ ቅንነትንና እውነተኛነትን
፨ አገልጋይነትና ጽናትን
፨ ሰላም ወዳድነት በሰላም መኖርን

መተው ያለብን

፨ አስመሳይነትና ሽንገላን
፨ ስንፍንና ማመካኘትን
፨ ጥላቻና ግለኝነትን
፨ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት
፨ ጥቅመኝነትና ብልጣብልጥነት
፨ ሁከትንና ሰላም ጠልነትን
፨ እኔነትና (Ego) ስሜታዊነትን

ቀኖች ልክ እንደ ደም ጠብታ ናቸው፣ ጊዜያቶች ሁልጊዜም ውድ ስጦታዎች ናቸው። ራሳችን ላይ ስንሰራባቸው ቀኖችና አመታት የእኛ ሜዳ ይሆናል። እናንተም ብንጨምር ወይም ብንተዋቸው የምትሉትን ሐሳብ አካፍሉን። ለሁላችሁም መልካምና የበረከት አመት ይሁንላችሁ። ብሩክ 2017።

ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

07 Sep, 07:07


በሰዎች መከናወን ስትቀናና ስትናደድ በረከትህ ይያዛል፣ በሰዎች መከናወን ደስ ሲልህ እግዚአብሔር ይባርክሃል። የሰዎች ክንውን የአንተን መንገድ በምንም መልኩ ሊዘጋው አይችልም። በሰዎች ደስታ ውስጥ የአንተን ደስታ ተመልከት፤ በአንተ ደስታ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲከብር። ይህን የህይወት ዘመንህ መርህ ስታደርገው በሁሉም ነገሮችህ ሞገስ ይሆንልሃል።

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

04 Sep, 18:35


በቦታህ መምህር ያለ ቦታህ ተማሪ ሁን!!

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

04 Sep, 05:17


የቄስ በሊናን "የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ" ያላነባችሁ ታነቡ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ።

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

04 Sep, 05:16


https://t.me/theideaofs
የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ
በቄስ በሊና ሳርካ!!

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

04 Sep, 03:41


#ዋጋችን_በተገኘንበት_ቦታ_ይወሰናል!!

አባት ለሴት ልጁ እንዲህ አላት "በክብር ከዩንቨርስቲ ከተመረቅሽ ለብዙ አመታት ያስቀመጥኳት መኪና አለችን የብዙ አመታት ዕድሜ ያላት ለአንቺ እሰጥሻለሁ። ለአንቺ ከመስጠቴ በፊቴ ወደ ዳውንታውን ውሰጅና ስንት እንደምታወጣ ጠይቂያቸው" አላት።

ልጅቷ የአባቷን ቃል ሰምታ ወደ አንድ መኪና መሸጫ ወሰደችው ተመልሳም ለአባቷ "$1000 ብር ገመቱልኝ አለችው።" አባትየውም ወደ ሌላ የመኪና መሸጫ ውሰጂው አላት። ልጅቷም አባትየው "መኪናዋ አሮጌና ያረጀች ስለሆነች $100 አሉኝ" አለችው።

በመጨረሻም አባትየው "ወደ ቆዩት መኪና ማሳያ (Car Club) ውሰጂው" አላት። ወሰደችው ሰዎቹም "$100.000 ገመቱልኝ ይህች Nissan Skyline R34, መኪና ታሪካዊ መኪና ናት ብለው።" አለችው። አባትየውም ልጁ እንዲህ አለት "ትክክለኛ ቦታሽ ትክክለኛ ዋጋሽን ያሰጥሻል። ሰዎች ትክክለኛ ዋጋ ካልሰጡሽ አትናደጁ በትክክለኛው ቦታ አይደለሽም ማለት ነው። ዋጋሽን የሚያውቁ ያከብሩሻል። መርሳት የሌለብሽ ሁሌም ለአንቺ ዋጋ (value) ከማይሰጡ ሰዎች ጋር መቼም እንዳሆኚ።" አላት። ዋጋችን ባለን ነገር ብቻ ሳይሆን ባለንበትም ቦታ ጭምር ይወሰናል። ምን ይዘን የት ነን?

የምትሰጣቸውን ፍቅር ከሚያጣጥሉ፤ ቅን ስትሆን እንደ ሞኝ ከሚቆጥሩህ፤ በውስጥህ ያለውን ህልም ከሚያጣጥሉ ትልቅ ነገር በውስጥህ እያለ እንደ ምንም በሚቆጥሩህ ሰዎች ዘንድ አትገኝ። አንተ የሆንከውን እንጂ ያልሆንከውን እንድትሆንና ያለቦታህ ከሚመድቡህ ሰዎች ዘንድ አትገኝ። ቦታህ የት ነው በቦታህ ሁን። ዛሬ ምንም የሌለው ቢመስልህ እንኳ ማፍራቱ አይቀርም። ምን ይዘን የት ነን?

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

03 Sep, 05:02


#አውቆ_የተኛን.........

አንድ ልጅ ሞቻለሁ ብሎ ያምን ነበር። ብዙ ሰዎችን "በህይወት አለህ አልሞትክም እኮ" ይሉታል። እሱ ግን "በህይወት የለውም ሞቻለሁ" ይላል። ከዚያው እንዲታይ ወደ ዶክተር ጋር ወሰዱት ዶክተሩም በምን ሊያስረዳው እያሰበ ቆየና "አንተ አልሞትክም በህይወት አለህ" አለው ወጣቱ ልጅም "የለም ሞቻለሁ"። ይላል ከዚያም ዶክተሩ "እንዳልሞትክ ላሳይህ የሞተ ሰው ደም የለውም አንተ ግን በህይወት ስላለህ ደም አለህ" ብሎ በመርፌ ወግቶ ደሙን ሲያሳየው ልጁም "ለካ የሞተ ሰው ደም አለው" ብሎት እርፍ።
(ታሪኩን ያጫወተኝ አንድ ወዳጄ ነው😀)

አንዳንድ ሰው አንተ የምትለው ይገባዋል ግን እሱ የሚለውን አይለቅም ከዚያም አልፎ ያንን ሐሳብ ያሰበበት ጉዳይ እስኪፈጸም ድረስ ምንም ብታስረዳውና የምታስረዳው ምንም እውነት ቢሆን እንኳ ሊቀበልህ አይፈልግ። ይህን አይነቱን ሰው አባቶቻችን "አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነሳም" ይላሉ ውሃ ካልደፉበት በቀር😀

እየገባን እንዲገባን የማፈልግ ከሆነ እና የሚነገረንን እውነት እኛ አስቀድመን በያዝነው ውሸት ምክንያት የምንገፋ ከሆነ እና 'በህይወት አለህ ስንባል' 'የለሁም' ለማለት "የሞተ ሰው ደም አለው" የሚል ትምህርት የምንፈጥር ከሆነ በምንም የማንማር፣ የማንለወጥ ከሰማነው እውነት ይልቅ የተሸከምነው ወሸት ይግደለን ብለን የወሰንን ነን።

©ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

03 Sep, 04:38


#አዲስ_አመትና_የእቅዶቻችን_ነገር......

"ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር ለማግኘት ከዚህ በፊት አድርገህ የማታውቀውን ነገር ማድረግ አለብህ።"
ዴንዚል ዋሽንግተን

አዲስ አመት ሲመጣ ብዙ ሰው ያቅዳል "በዚህ አመት እንዲህ አደርጋለሁ" "እማራለሁ" "ስራ ቀይራለሁ" "አገልግሎቴን አሰፋለሁ" "አገባለሁ" "ይህን እተዋለሁ" "ይህን ጨምራለሁ" እያልን አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ እናስባለን እናቅዳለንም። ማቀድ ጥሩ ነው። ዘመናችን በሁለት ነገሮች እጅ ናቸው የመጀመሪያው በእግዚአብሔር እጅ ሲሆን ሁለተኛው በእኛ እጅ ነው። በእቅዶቻችንን የእግዚአብሔር እጅ እና ጣልቃ ገብነት፤ ምሪትና እርዳታው ያስፈልገናል። እግዚአብሔር አንዳንዴ ባላቀድነው በረከት ሊባርከን እንደሚችል ባምንም ህይወታችን ግን በራዕይ በእቅድ እንዲሆን ይፈልጋል።

እቅድን በተመለከተ በየአመቱ አቅደን ከነበረና በህይወታችን ምንም ለውጥ ካላየን ባቀድነው እቅድ መጠን አልሰራንም ማለት ነው። አሁን ባለንበት የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም የተለየ እንቅሰቃሴ ሳናደርግ ምንም የተለየ ውጤት አናገኝም። እቅድ ካወጣህ ከዚህ በፊት በነበረህ አረዳመድህ አሁን ካለህበት የተሻለ ህይወት ሊኖርህ አይችልም። ከቀድሞ የተለየ አኪያሄድ ካልተራመድክ አሁን ካለህ የተሻለ ውጤት አይኖርም። እቅድ ካወጣህ እቅድህ የሚፈልገው አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብሃል።

የማትተገብረው እቅድ ስላቀድከው ብቻ ምንም ለውጥ አያመጣም። እቅድ የራሱ እንቅስቃሴ ድርጊት (Action) ይፈልጋል። አሁን ከምትሰራው በላይ በትጋት ካልሰራህ ከቀደመው የተለየ ውጤት በህይወትህ አይመጣም። መንፈሳዊ ሆነ ምድራዊ ስራዎች ትጋት ይፈልጋሉ ውጤቶቻቸውም እንደ ትጋታቸው ነው። ህይወት በእድል አይመራም።

በሌላ እሳቤ የተለየ ውጤት ለማግኘት የተለየ እርምጃ ያስፈልጋል። በ2014 ምን አቅደናል? እንደ ቤተክርስቲያን፤ በግል ህይወት፤ በቤተሰብ ምን እንዲሆንልን እንፈልጋለን? ያቀድናቸው ነገሮች በእግዚአብሔር እርዳታና በእኛ ትጋት ውጤትን ይሰጣሉ። እንደ መንፈሳዊ ሰው እንጸልይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ ከዚያም ባቀድናቸው ነገሮች ተግተው እንሰራ። አንድ ነገር በህይወታችን ለመጨመር አኪያሄዳችንን እውቀታችንን አዋዋልና መጨመር እና እቅዳችንን የሚመጥን ማድረግ አለብን። አዲስ ውጤት ለማግኘት አዲስ አረማመድ እና አኪያሄድ ይኑረን። በእቅድ ውስጥ ለሚሰራ ቀኖች ሁሉ የውጤት ድልድዮች ናቸው።

ዘሪሁን ግርማ

https://t.me/theideaofs

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

03 Sep, 04:37


ሁሉም ሰው እንዲቀበልህ ማድረግ አትችልም፣ ሁሉም ሰው እንዲወድህ ማድረግ አትችልም፣ ትክክለኛውን ነገር እያደረክ እንኳ። ሐይልህን ሰዎች እንዲቀበሉህ በመታገል አትጨርስ!! ይህ የህይወት አድካሚው መንገድ ነው። ይልቅ ከራስህ ጋር ተስማማ፣ የመረጠህ አብሮ ይጓዛል፣ የማልፈልግ ይለይሃል። እነዚህ ሁለት የህይወት መንገዶች ናቸው። አንተ ብቻ ከራስህ ጋር ተስማማ።

https://t.me/theideaofs