ከማትወጅው ጋር ባለሽ ግንኙነት
✍ የሚስማሙሽ ጋር ሳይሆና የማይስማሙሽ
ሰዎች ጋር የምታደርጊው ግንኙነት
✍ በሀሳብ ከምትግባቡት
ሳይሆን ከማትግባቡት
✍ አንች ከምታምኒባቸው ጋር ሳይሆን
ከማያምኑብሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት
💎🔝 በአስደናቂ ሁኔታሽ በምቾት ውስጥ
ሳይሆን በአስቸጋሪ ሁኔታዎችሽ ውስጥ ውሳኔ
አወሳሰድሽ በደህና ጊዜማ ሁሉም ሰው
ደግ ነው ለሚወደው ሁሉም ሰው ጥሩ ነው
ግን ሁኔታዎች ሲቀየሩ 👍
ሀሳቦች እና አስተያየቶች ሲለያዩ🔝
እውነተኛው ገጸ ባህሪ ይገለጣል!🔝
.
#ነፋሳችን ትመከር!
ምሳሌ እኔ ልጄን ወደዋለሁ ምናገረውን
ሲሰማኝ ሲታዘዘኝም ሳይረብሽ ሲቀር
ቤት ሳያቆሽሽ ሳይጮህ ብቻ በጥቅሉ
እኔ እምፈልገውን ሲያረግልኝ ጥሩ ጥሩ
ነገር አረግለታለሁ ለየት ብሎ
ማልፈልገውን ሲያረግ እቆጣዋለሁ
ምናልባትም አስለቅሰዋለሁ!
በመጠኑ የማረገው ቀርቶ ያለውን
እቀማዋለሁ እሱም በተናደደበት
ስአት ጥሩ አደለሽም ይለኛል ሲረጋጋ
ጥሩነሽ ይለኛል ልጅ ያው ልጅ ነው ካልተኮተኮተ
አይሆንም ይህ ህይወት ግን በዙሪያችን ባሉ
ሰዎችም ላይ አለ!!
ጥሩ ስነ ምግባር ያለው ሰው በክፍው
ጊዜም ጥሩ ነው!
~ በሁላችንም ሀያት ያለ ነው እስከ ወደድናቸው
እስከተስማሙን ድረስ ሁሉም ለሁሉም ጥሩ ነው!
ለየት ስንባባል ትክክለኛ ማንነት ይወጣል!
~ የትክክለኛ ስነ ምግባር ባለቤትነት
ራሳችንን የምንፈትሸው በፈተናዋ ስአት
ነው ወዳጅ ጠላት ሲሆን ያመንሽው
ሲከዳ ሀሳብሽ ሲለያይ ባንች ላይ ሲዶልቱ
ሲያስመስሉብሽ ሲዋሹብሽ
ሲቀጥፉውብሽ በምትሰጭው
ምላሽ ይወሰናል!!
~ አስተውይ ሰዎች የራሳቸው ጉዳይ
ልብሽ እንዳይቆሽሽ ህሊናሽ እንዳይሞት
ሚሊየን ጊዜ ራስሽን ወደሽ ስነ ምግባርሽን
ለማነፅ ሞክሪ ራስሽን ለመሆን ያለሽ
አማራጭ ይህው ነው ።።
ከፍ እንድትይ ካንች በታች እና የወረደ
አመላካከት ያላቸው አንችን ከማናናቅ
ስህተትሽን ከመፈለግ ሀሳብሽን ከማርከስ
ውጭ ሊያረካቸው የሚችል የራሳቸው የሚሉት
ነገር የላቸውም!!!
የሚመጣውን በጥሩ መመለስሽ
ደረጃቸው ሁሉ ላቅ ያለውን የሀቢብሽን ሱና
ሀይ ማረግሽ ደረጃሽን በጀሊሉ ላቅ ማረግሽ
ነው አበደን እንዲያደፈሩስሽ እድል አትስጫቸው!!!