~
የሌሎች ሃይማኖቶች የእምነት መገለጫ ምልክቶችን መጠቀም፣ የመስቀል ጥልፍ ያለበት ባህላዊ ልብስ መልበስ፣ መሸጥ፣ መስቀል ያለባቸው የሬሳ ሳጥን መሸጥ አይፈቀድም። እናታችን ዓኢሻ – ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ – እንዲህ ትላለች: –
لم يكن رسول الله صلى الله وسلم يترك في بيته شيئا فيه تصاليب إلا نقضه
"የአላህ መልእክተኛ – ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለም – ቤታቸው ውስጥ መስቀሎች ኖረውበት ሳያበላሹት የሚተውት ነገር አልነበረም።" [ቡኻሪ]
እዚህ ላይ አንዳንድ በባህል ሽፋን ወደ እምነታቸው የሚጣሩ ብልጦች ይህንና መሰል ትምህርቶችን እንደ ማክረር ሊቆጥሩ ይችላሉ። አክራሪዎቹ ግን እነሱ ናቸው። በሌሎች እምነት ውስጥ ገብቶ ብይን ለመስጠት ማንጋጠጥ ፅንፈኝነት ብቻ ሳይሆን ብል -ግናም ጭምር ነው። እኛ "ኮፍያ ወይም ጂልባብ ልበሱ" አላልንም። "እንደኛ ካልለበሳችሁ አካራሪዎች ናችሁ" የምንል አጉል ደፋሮችም አይደለንም። ያወራነው ስለራሳችን እምነት ብይን ብቻ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor