AL-ikhlas @halalguys1 Channel on Telegram

AL-ikhlas

@halalguys1


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
تم افتتاح هذه القناة لبث كتب متنوعة لمختلف المعلمين

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
•••✿❒🌹❒✿•••┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

ይህ ቻናል የተከፈተው የተለያዩ እውቀቶችን በጥያቄና በንባብ ወደ እናንተ ለማቅረብ ነው

AL-ikhlas (Amharic)

ምንድን ነው AL-ikhlas ባሰብኩታል? ይህን ቻናሉ ለማንኛውም ህምቦቶችን ሲወያይ እና ለድግስት ሰለላውያን የተሰሎግነው መፅሃፍ ቅርበት ነው። በደምሽ ወቅታዊ መረጃዎችን ለመልኩትና በሰራዊት ያግኙልን። AL-ikhlas ቻናሉ በብርቱር እና በአማርኛ መፅሃፍዎችን በሚቆጠሩ እና በሚከባከቡ ክፍሎችን በቦክ ያግኙልን። ከዚህ በበገኗት ሆድ ሊሆን ይችላሉ። እናም በደምዋ በንባብ ማህበሩን ለሁሉም መፅሃፍ እና ማንቀሳቀሽ እንዲረሱ ማህበሩን በወጣያዊ ጥራት ላይ ያግኙልን። መፅሃፍ ማወቅ እና መረጃዎች ለሌሎች ምንጮች የተለየ መቆያን ነው። የAL-ikhlas ቻናል፣ ከበፍቃኞች እና ድግስት ሰለላውያን ዝናሎችን ድምፅ ገና የሚያንቀሳቀሱበት እና ወጣት ጥቆችን የተናገሩ አክሲቶችን ስለሚሞት ቻናሉን ይመልከቱ።

AL-ikhlas

10 Feb, 19:35


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
ባላቹ አቅም ተባበሩን ባረከላሁ ፊኩም

AL-ikhlas

12 Jan, 19:38


ሰላሙላሂ አለይኩም
       #ለማስታወስ ➳
ነገ ሰኞ የረጀብ ወር አያመል ቢድ የመጀመሪያ ቀን ነውና የቻለ ሰው ይፁም ያልቻለ ደግሞ ለሰዎች ያስታውስ።
✔️13- ሰኞ
✔️14-ማክሰኞ
✔️15- እሮብ
እነኚህን ቀናቶች በየወሩ መፆም አመቱን በሙሉ እንደ መፆም ነዉ ።


የአላህ መልእክተኛ ረሱል   ﷺ " ወደ  መልካም ነገር ያመላከተ ሰው፡ የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" (ﷺ)

ሼር💌

AL-ikhlas

09 Jan, 18:51


በአንድ ጊዜ ኢማሙ አህመድ እንዲህ ሚል ጥያቄ መጣላቸው
➡️እስከመች ነው ኢልምን ምትፈልገው? ተባሉ
እሳቸውም ከሚህበር ጋር(መፃፊያ ቀለማቸው)እስከ ምሞት ድረስ በማለት ተናገሩ

AL-ikhlas

08 Jan, 20:10


#ከባድ ነገሮችን ያልተሳፈረ የሆነ አካል ሚከጀሉ ነገሮችን አያገኝም(የሚፈልገው ነገር)

AL-ikhlas

06 Jan, 18:53


#ስራ ያለ ከኢኽላስ ያለ ምንም ጥቅም ከንቱ ሆኖ የሚሄድ መሆኑን እንወቅ

AL-ikhlas

06 Jan, 18:31


ማንኛውም ሸሪአዊ እውቀት እየተማርን/እያስተማርን ከሆነ 100%አላህ የመረጠን እና እድለኛ ሠዎች ነን

AL-ikhlas

28 Dec, 17:08


እስኪ ለቀቅ አርጉኝ ኒቃቤን አትኩት
ምን አቃጠላችሁ እኔ ለለበስኩት
ኒቃብ በመልበሴ ሞቀኝ የሚል ወጣኝ
ወይስ በመልበሴ ተክዤ አያችሁኝ
ነው እኔ ለለበስኩት እናንተን ሞቃችሁ
እድህ ይሄን ያህል ያገሸገሻችሁ


ተውልኝ ኒቃቤን ለኔ ክብሬ እሱ ነው
በማታቁት ነገር መሞገት አግባብ ነው?
ስለዚህ ተውልኝ ጥቅሜን እኔ አቃለሁ
ከአራህማኑ በታች ከለላ አግቻለሁ
ሀይ ብሎ የሚይዝ ሀጅ ነብይ ዱርየ
ከኔ ጣገብ ሲዴርስ ምን እዴሚል ላየ
አሰለሙአለይኩም ብሎ ሲያገል ላየ
ትተአጄብ ነበር እንኳንስ ልጠላው
የምን ኒቃብ ብለህ እኳን ልታጥላላ



Copy

AL-ikhlas

20 Dec, 04:49


የጁመዐ ቀን ሱናዎች

❶ገላን መታጠብ (ከፈጅር በኋላ ጀምሮ )

❷ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)

❸ጥሩ ልብሱን መልበስ ነጭ ቢሆን ይመረጣል

❹በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ

❺ሲዋክን መጠቀም

❻ሱረቱል-ከህፍን መቅራት

❼ዱዐን ማብዛት በተለይ በ2 ኹጥባ መካከል እና ከዐሱር በኋላ ያሉ ጊዜያቶች በዱዐእ መጠባበቅ

❽ሶለዋት ማለትን ማብዛት

يقول الله جل وعز في كتابه الكريم

👇

(إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا)
سورة الأحزاب ٥٦
አሏህና መላእክቶች በነቢዩ ላይ ውዳሴን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ ሶለዋት አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

ويقول النبي صلى الله عليه وعلى اله وسلم فيما رواه مسلم من حديث ابي هريرة رضي الله عنه

👇

" مَنْ صَلَّى عَلَيَّ وَاحِدَةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ عَشْرًا ".
በኔ ላይ 1️⃣ ሶላት ያወረደ በሱ ላይ አሏህ 🔟 ሶላት ያወርድለታል።


👌اللَّهُمَّ صَلِّ وَ سَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ

AL-ikhlas

31 Aug, 09:28


⚠️መውሊድ በዲን ላይ የተጨመረ የፈጠራ ተግባር ነው❗️

ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن أَحْدَثَ في أَمْرِنا هذا ما ليسَ فِيهِ، فَهو رَدٌّ﴾

“በዚህ ዲናችን ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ስራው ተቀባይነት የለውም ወደራሱ ተመላሽ ይሆናል።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 2697

AL-ikhlas

22 Aug, 14:06


እኔ ብቻ ነኝ ግን እናቴ ዝም ብላ ስቶጣ ደውዬ
.
.
.
.
.
.
ኡሚ ምሳ ምንድነው ሚሰራው ምላት ግራ እኮ ነው ሚገባኝ

AL-ikhlas

20 Aug, 17:24


🌺🌺👇

ነሲሀ ላንቺ ለውዷ እህቴ

قال الشيخ مقبل الوادعي رحمه الله تعالى :  أنصح المرأة الصالحة أن تحرص على مجالسة النساء الصالحات فإنها تزداد إيمانا وتزداد علما وتزداد بصيرة.


ሸይኽ ሙቅቢል رحمه الله تعالى እንዲህ አለ ፡ መልካሟን ሴት እመክራታለሁ ከመልካም ሴቶች ጋር መቀማመጥን እንድትጓጓ ፤ በዚህ ነገር ዒማኗን ትጨምራለች ዒልምን በሲራንም ትጨምራለች።

       📚 غارة الأشرطة

ኡኸየቲ...በዙሪያሽ ብዙ ጀግና እህቶች ይኖሩሻል ልትቀማመጫቸው ከጅይ...ኡኽታ እነሱ ጋር መቀማመጥሽ ብዙ ልምዶችን እንድትወስጂ ያደርግሻል።

ዓዚዘቲ...የዒልም ነሻጧ ያላቸው እህቶች ጋር ስትቀማመጪ ነሻጣሽ እንዲጨምር ሰበብ ይሆንሻል....ዒባዳ ላይ የነሸጡት ጋር ስትውይ በዒባዳ ላይ እንድትነሽጪ ያደርግሻል...በሒጃባቸው ላይ ጥንቁቅ ከሆኑት ጋር ስትውይ በሒጃብሽ ጥንቁቅ ትሆኚያለሽ.

ታውቂያለሽ ፡ ሰው አዋዋሉን ይመስላል...ጓደኛውን ይመስላል...አዎ ከሰለፍዮች ጋር መቀማመጥ..ከእነሱ ጋር መዋል የቀልብ ውስጥ ብርሀን...የነፍስ ውስጥ ቀለብ...የበሽታዎችም መድሀኒት ነዉ።

አዎ እህቴ ከሸር ሰዎች ጋር የምትውይው ውሎ እና ከጧሊባ ጋር የምትውይው ውሎ ጭራሽ አይመጣጣንም...ከሽሪር ጋር የዋለ ቀልቡ ከድንጋይ ብሶ ደርቆ ታገኝዋለሽ (الله ይጠብቀን)..ከጧሊበል ዒልም ጋር የዋለ ደግሞ ቀልቡ ራሀን የተሸከመች ሆና ይውላል..

AL-ikhlas

11 Aug, 07:00


እውነተኛ ፍቅር መገለጫው ኒካህ እንጂ በየጥጋጥጉ የሚፈፀም ዝሙት አይደለም!!
የእውነት ከወደደሽ ያግባሽ በትክክለኛው በር ይግባ


ቀድመሽ ከሰጠሽው ሰርጉን እርሽው ነው ነገሩ ጠንቀቅ ቆፍጠን በሉ

AL-ikhlas

07 Aug, 17:08


واذكروا الله كثيرًا لعلكم تُفلحون 🌺🌺.

سبحان الله.. والحمد لله.. ولا إله إلا الله ..والله أكبر🦋.

لا حول ولا قوة إلا بالله العلي العظيم🦋.

سبحان الله وبحمده سبحان الله العظيم 🦋.

لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير 🦋.

لا إله إلا أنت سبحانك إني كنت من الظالمين 🦋.

استغفر الله العظيم الذي لا إله إلا هو الحي القيوم وأتوب إليه 🦋.

AL-ikhlas

05 Aug, 16:58


አ ዳ ማ ዬ!

AL-ikhlas

03 Aug, 17:07


Aselamu aleykum werahmetulahi weberekatu

AL-ikhlas

02 Aug, 04:27


Happy jumea yaa family

AL-ikhlas

02 Aug, 04:26


☀️ፀሀይ ከወጣችበት ቀናቶች ሁሉ ዉብ ቀን የጁምአ ቀን ነዉ። 
ውብ ጁመአ ተመኘሁላቹ

ሰብሀል ኸይር

AL-ikhlas

01 Aug, 11:41


8ቱ የጀነት በሮች

ነቢዩ (ﷺ) ስለ ጀነት በሮች ብዛት ሲናገሩ

«ጀነት ስምንት በሮች አሏት። አንደኛው አር-ረያን ሲሆን ከጿሚዎች በቀር የሚገባበት የለም።» ብለዋል።
(ቡኻሪይ 3257/ ሙስሊም 1152)

በሌላ ሐዲሳቸው ደግሞ፦

«አንድ ሰው ለአላህ ብሎ ሁለት ነገሮችን ሰደቃ ቢሰጥ አላህ ጀነትን ግባ ይለዋል። እንዲሁ ሶላትን የሚሰግዱ በሶላት በር ግቡ ይባላሉ። በጂሐድ የተሳተፉ በጂሐድ በር ግቡ ይባላሉ። ሰደቃ የሰጡ በሰደቃ በር ግቡ ይባላሉ። ፆም የፆሙ በአር-ረያን በር ግቡ ይባላሉ።» አሉ። አቡበክር ሲዲቅም «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በሁሉም በር እንዲገባ የሚጠራ ይኖራልን?» አሏቸው። ነቢዩም (ﷺ) «አወ! አንዱ አንተ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ።» አሉ።»
(ቡኻሪይ 1897/ ሙስሊም 1027)

ዑለማዎች ከእነዚህና ሌሎች ሰነዶች በመነሳት የስምንቱን በር ስሞች ያስቀመጡ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦

❶ ባብ አስ-ሶላት
♦️ ሰጋጆች የሚገቡበት

❷ ባብ አል-ጂሐድ
♦️ በጂሐድ የተሳተፉ የሚገቡበት

❸ ባብ አስ-ሰደቃህ
♦️ ሰደቃ የሰጡ የሚገቡበት

❹ ባብ አር-ረያን
♦️ ጿሚዎች የሚገቡበት

❺ ባብ አል-ሐጅ
♦️ ሐጂ ያደረጉ የሚገቡበት

❻ ባብ አል-ኢማን
♦️ ፅኑ ኢማን ያላቸው የሚገቡበት

❼ ባብ አል-ካዚሚን አል-ገይዝ
♦️ ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩና ይቅር ባዮች የሚገቡበት

❽ ባብ አዝ-ዚክር
♦️ ዚክር የሚያበዙ የሚገቡበት

1,613

subscribers

150

photos

64

videos