Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel @ibnusultan38 Channel on Telegram

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

@ibnusultan38


( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ )
الأنفال (29)

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel (Arabic)

تعتبر قناة Muhammed Sultan (أبو عائشة) على تطبيق تليجرام واحدة من أفضل المصادر للحصول على المعرفة والتوجيه في الدين الإسلامي. يقوم محمد سلطان، المعروف أيضًا باسم أبو عائشة، بمشاركة مقتطفات من القرآن الكريم والحديث النبوي الشريف، ويقدم تفسيرات وتوجيهات دينية مفيدة للمتابعين لتعميق فهمهم للدين الإسلامي. إن قناة ibnusultan38 هي المكان المثالي للأشخاص الذين يبحثون عن الحكمة والتوجيه الروحي في حياتهم اليومية. من خلال متابعة هذه القناة، يمكنك الاستفادة من الموارد القيمة التي تقدمها لك المعلومات الدينية القيمة والمحتوى الملهم. إن القناة تستهدف الأشخاص الذين يسعون لتعزيز إيمانهم وزيادة فهمهم للتعاليم الدينية الإسلامية. بفضل المحتوى المميز الذي يقدمه أبو عائشة، ستجد نفسك في رحلة تعلم واستكشاف ديننا وثقافتنا بشكل أعمق. انضم إلى قناة Muhammed Sultan (أبو عائشة) اليوم لتجربة تجربة ملهمة وتحصل على الحكمة والتوجيه الروحي الذي تبحث عنه في حياتك اليومية. اكتشف معنى الإيمان والدعوة في عالمنا المعاصر من خلال هذه القناة الدينية الرائعة.

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

12 Jan, 05:05


تطبيق جامع الكتب التسعة
موسوعة شاملة للحديث مع ربطها بشروحها وغريبها والتخريج والأطراف والشواهد وصحتها..

حمل التطبيق الآن:
https://onelink.to/9books

يعمل على (الأيفون والأندرويد وهواوي)

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

11 Jan, 03:46


📌የዳዕዋ ፕሮግራም

☞ውድ የተከበራቹ ወንድም እና እህቶች በአሏህ ፍቃድ
ነገ ማለትም ቅዳሜ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ የዳዕዋ ፕሮግራም
በመርከዝ ኢማሙ አህመድ በአካል ተገኝታቹ እንድትታደሙ ስንጋብዛቹ በታላቅ ደስታ ነው

በአካል መገኘት ለማችሉ በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት  መከታተል ትችላላቹ

ተጋባዣ ዱዓቶች
↓↓↓↓↓↓
🎤ኡስታዝ ሳዳት ከማል

🎤ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🎤ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ


ዳዕዋው የሚተላለፍበት ቻናል
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

05 Jan, 17:58


ይሄ ሐሰን ታጁ የሚያስተዋውቀው ሰው ሙስሊሞችን "አላህ በቁርኣን እንደገለፀው ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም እያስወጣ የሚናገር ተክ - ፊሪይ ነው። ይሄ አቋም የ "ሙፍቲ" ዑመር አቋም ነው። እነ ሐሰን ታጁ በዚህ ቆ - ሻ ሻ አስተሳሰብ ላይ ሰዎችን ከተለያዩ ክፍላተ ሃገራት እያመጡ በህቡእ እያደራጁ በማጥመቅ ላይ በሰፊው ተሰማርተዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

29 Dec, 05:41


ከተማርናቸው የኡሱል ትምህርቶች ቢያንስ እነዚህን መያዝ ያስፈልጋል

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

24 Dec, 06:17


ደርስ ፡- ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
ክፍል፡- አምስት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

24 Dec, 03:47


ደርስ ፡- ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
ክፍል፡- አራት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

22 Dec, 14:56


ደርስ ፡- አልኡሱል ሚንዒልሚል ኡሱል
ክፍል፡- አራት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

18 Dec, 03:30


ለሃይቅ ከተማ ወንድሞች!
~
ሰሞኑን ከደዕዋ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ግርግር እንደነበረ ስለሰማሁ ለናንተም፣ ተመሳሳይ ሁኔታ ላላቸው ሌሎች አካባቢዎችም ከጠቀመ በሚል ትንሽ ለማለት ወደድኩ።

1ኛ፦ በቅድሚያ በተቻለ መጠን መስዋእትነት ከፍላችሁም ቢሆን ደዕዋችሁን ከግጭት አርቁ። በግርግር አትታወቁ። ለሁከት ፈጣሪዎች እድል አትስጡ። እናንተ ብትሸሹ እንኳ እምቢ ብለው ብጥብጥ ለማስነሳት የሚፈልጉ ስለሚኖሩ ነገሮችን በጥንቃቄና በሹራ (በመመካከር) ያዙ።
2ኛ፦ የሚቃረኑ አካላትን ጭምር ለመመለስ አልማችሁ ስሩ። አብዛኞቹ የሌሎች መጠቀሚያ እየሆኑ እንጂ በውል ለይተው አይደለም በተቃውሞ የሚሰለፉት።
3ኛ፦ ብልጥ ሁኑ። ሃላፊነት ላይ ካሉ አካላት ጋር ላለመጋጨት ሞክሩ። በለዘበ መልኩ እነሱንም ለመያዝ ሞክሩ። እነሱስ የኛው ወገኖች አይደሉ? መያዙ ቢቀር ለማለስለስ ጣሩ። ስማችሁን ለሚያጠፋ አካል ሰበብ ላለመስጠት የምትችሉትን ሁሉ ጥንቃቄ አድርጉ።
4ኛ፦ የጎንዮሽ ፍትጊያ ካለ አስወግዱ። የከፋ ተቀናቃኝ ኃይል ባለበት ሌሎች ውዝግቦችን አስወግዱ ወይም ቀንሱ። ተከባበሩ። ተደማመጡ። ተናበቡ።
5ኛ፦ ስጋት ከሌለ እስከ ገጠር እየወጣችሁ በርትታችሁ ስሩ። የሚያዳምጥ ወይም የሚቀበል ቀለለ ብላችሁ ሞራላችሁ እንዳይቀዘቅዝ። እንቅስቃሴያችሁ ሰሞንኛ አይሁን። ወረተኛ እንዳትሆኑ። ከየትኛውም አካል በሚመጣ ጫና አትታጠፉ ፣ እጅ አትስጡ። የነብያችንን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና የቀደምቶችን ታሪክ አስታውሱ።
6ኛ፦ ቁርኣን ማስተማር ላይ አድምታችሁ ስሩ። ከሌሎች የተሻለ ለውጥ የሚታይ ከሆነ ለሌላውም ደዕዋ ስንቅ ይሆናችኋል።
7ኛ፦ ተማሪዎች እና ሴቶች ላይ በሚገባ ስሩ። ቋሚ ፕሮግራም ይኑር።
8ኛ፦ ደዕዋችሁ ዘርፈ ብዙ ይሁን። ሁለት ሶስት ርእስ ላይ አትገደቡ። የሰዎችን ልብ በተለያየ አቅጣጫ አንኳኩ።
9ኛ፦ የሚቻላችሁ ከሆነ ማህበራዊ ስራዎች ላይ ለምሳሌ ደካማን አስተባብሮ መርዳት፣ ማቋቋም፣ ቤታቸውን ማደስ፣ ምስኪኖችን ማሳከም፣ ዘካተል ፊጥርና መሰል ሶደቃዎችን በተቀናጀ መልኩ በመሰብሰብ መስራት ለደዕዋውም እገዛ ይኖረዋል።

በተረፈ እኔ የሃይቅ ከተማን አንድ አመት ተምሬባታለሁ። ያኔ ከደዕዋ አንፃር የረባ እንቅስቃሴ የሌለባት በጣም የቀዘቀዘች ነበረች። ዛሬ የአላህ ፈቃድ ሆኖ በናንተ ጥረት ጥሩ ለውጥ አለ። በዚህ ለውጥ ላይ ትንሽም ብትሆን ድርሻ ያላችሁን ሁሉ አላህ ይመንዳችሁ። ከዚህም የበለጠ ለውጥ ይኖር ዘንድ በርትታችሁ፣ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ስሩ። ይሄ ኃላፊነት የከተማው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የተሁለደሬ ወረዳን ወንድም እህቶችን ይመለከታል። ማእከሉ ሲጠነክር ነውና ለገጠሩ የሚተርፈው ከአካባቢው ርቆ ያለውን ተወላጅ ጨምሮ ሁሉም በሚችለው በደዕዋው ስራ ላይ መረባረብ ይገባል።

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙነወር
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

15 Dec, 14:41


ደርስ ፡- አልኡሱል ሚንዒልሚል ኡሱል
ክፍል፡- ሶስት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

15 Dec, 14:28


ደርስ ፡- አልኡሱል ሚንዒልሚል ኡሱል
ክፍል፡- ሁለት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

13 Dec, 18:21


ልዩ የ ደዓዋ እና የኒያ ፕሮግራም ላይ

ሸይኽ አወል ገብተዋል
https://t.me/+lmLw2jJXwF45Zjdk

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

12 Dec, 18:26


💠 فهرس القناة:

1- بداية القناة

2- الشرائط من (1 _ 50)

3- الشرائط من (51 _ 100)

4- الشرائط من (101 _ 150)

5- الشرائط من (151 _ 200)

6- الشرائط من (201 _ 250)

7- الشرائط من (251 _ 300)

8- الشرائط من (301 _ 350)

9- الشرائط من (351 _ 400)

10- الشرائط من (401 _ 450)

11- الشرائط من (451 _ 500)

12- الشرائط من (501 _ 550)

13- الشرائط من (551 _ 600)

14- الشرائط من (601 _ 650)

15- الشرائط من (651 _ 700)

16- الشرائط من (701 _ 750)

17- الشرائط من (751 _ 800)

18- الشرائط من (801 _ 850)

19- الشرائط من (851 _ 901) .

💠 سلسلة الهدى والنور قناة تعنى بنشر جميع أشرطة سلسلة الهدى والنور ( 901شريطاً )،، لشيخنا المحدث محمد ناصر الدين الألباني رحمه الله وغفر له.

🔵 للإنضمام للقناة إضغط على الرابط:

t.me/alhoda_noor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

01 Dec, 04:37


እምቢ በይ እታለም!
(ከካ|ፊ- ር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
~
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ግን ብንንቃት?!!

እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬ ከመስመሩ ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩ -ሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህ -ደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡

ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡

ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ብቻ ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስኪወርድ ………. ከዱዓ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡

በሚታዩሽ ብልጭልጮች ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገ -ዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. በተኩላ እንዳትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. ኣኺራሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡

ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገ -ልቱ አተላ
ዛሬ እጅሽን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከአካልሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞቹ ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!
.
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 21/2008)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

23 Nov, 14:30


ወሕደተል አድያን - የሃይማኖቶች አንድነት ስብከት
~
በዚህ ዘመን ከሚታዩ አውዳሚ ስብከቶች ውስጥ አንዱ ሃይማኖቶችን በተለይም ኢስላም፣ አይሁድና ክርስትናን አንድ የማድረግ ወይም አንድ ናቸው የሚል ስብከት ነው። እንደ ኢስላም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው።

ሌሎቹ:-
* መፃህፍቶቻቸው የሰው እጅ የገባባቸውና የተበረዙ ናቸው።
* ሺርክ የሃይማኖቶቹ ቀኖና አካል ሆኗል።
* የሙሐመድን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነብይነት አይቀበሉም። ይህንን ያላረጋገጠ አካል ጋር የእምነት አንድነት የለም።
* አይሁድ መርየምንና ዒሳን ያወግዛሉ።

እነኚህና መሰል የማይታረቁ ልዩነቶች ባሉበት ሶስቱ ሃይማኖቶች አንድ የሚሆኑበት አግባብ የለም። ስለዚህ የሶስቱን እምነቶች ቤተ አምልኮት (መስጂድ፣ ቤተ ክርስቲያን እና ምኩራብ) አንድ ላይ በመስራት ወይም ቁርኣንና መፅሀፍ ቅዱስን አንድ ላይ በማተም ወይም የጋራ ድርጅት በማቋቋም ይህንን ስብከት ማሳካት አይቻልም።

በሌላ በኩል ሃይማኖቶችን እንዳጠቃላይ የሚያሰጉ ተግዳሮቶችን ወይም እንደ ግብረ ሰዶም ያሉ አፈን ጋጭ ልማዶችን፣ ወዘተ ለመጋፈጥ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች በጋራ ቢሰሩ ይሄ ከወሕደተል አድያን ጋር የሚገናኝ አይደለም። የማይገናኙ ነገሮችን ከወሕደተል አድያን ጋር እያገናኙ ሰዎችን በሌሉበት መክሰስ በጣም አደገኛ ጥፋት ነው። እንዲህ አይነት ውንጀላ ስለበዛ ሳያረጋግጡ ሰዎችን ከመክሰስ መጠንቀቅ ይገባል። ሌላው ቀርቶ ጤነኛ ያልሆነ ቅርርብ ቢኖር እንኳ በልኩ እርምት ከመስጠት ማለፍ አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

16 Nov, 10:19


Samira umu Ismail:
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ተቀርቶ የተጠናቀቀውን የሪያዱ ሷሊሒን ሙሉ ደርስ እነዚህን ሊንኮች በመጫን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ:- ⤵️
የኪታቡ ሶፍት ኮፒ  በpdf ለማግኘት :
https://t.me/IbnuMunewor/3505
ክፍል :--
❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3490
❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3508
❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3514
❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3536
❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3541
❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3572
❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3581
❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3620
❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3625
❿:
https://t.me/IbnuMunewor/3649
❶❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3656
❶❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3684
❶❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3691
❶❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3723
❶❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3731
❶❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3769
❶❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3775
❶❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3809
❶❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3813
❷⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/3837
❷❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3853
❷❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3870
❷❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3874
❷❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3931
❷❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3941
❷❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3944
❷❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3952
❷❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3968
❷❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3973
❸⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/3995
❸❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3999
❸❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4013
❸❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4018
❸❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4041
❸❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4047
❸❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4058
❸❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4064
❸❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4085
❸❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4091
❹⓪
https://t.me/IbnuMunewor/4103
❹❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4107
➍➋:
https://t.me/IbnuMunewor/4122
➍➌:
https://t.me/IbnuMunewor/4129
➍➍:
https://t.me/IbnuMunewor/4143
➍➎:
https://t.me/IbnuMunewor/4150
➍➏:
https://t.me/IbnuMunewor/4166
➍➐:
https://t.me/IbnuMunewor/4167
➍➑:
https://t.me/IbnuMunewor/4173
➍➒:
https://t.me/IbnuMunewor/4175
➎⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4194
❺❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4201
❺❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4216
❺❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4218
❺❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4254
❺❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4264
❺❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4486
❺❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4489
❺❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4511
❺❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4516
❻⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4534
❻❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4539
❻❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4547
❻❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4560
❻❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4566
❻❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4570
❻❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4577
❻❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4579
❻❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4588
❻❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4591
❼⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4639
➐❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4643
❼❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4660
❼❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4665
❼❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4675
❼❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4676
❼❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4709
❼❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4713
❼❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4722
❼❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4723
❽⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4730
❽❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4731
❽❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4746
❽❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4751
❽❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4771
❽❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4776
❽❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4798
❽❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4801
❽❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4821
❽❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4828
❾⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4857
❾❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4864
❾❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4874
❾❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4880
❾❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4904
❾❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4908
❾❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4922
❾❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4930
❾❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4947
❾❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4951
❶⓪⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4962
❶⓪❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4967
❶⓪❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4972
❶⓪❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4980
❶⓪❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4985
❶⓪❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4989

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

16 Nov, 10:19


❶⓪❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4999
❶⓪❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5004
❶⓪❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5012
❶⓪❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5017
❶❶⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5025
❶❶❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5029
❶❶❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5047
❶❶❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5063
❶❶❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5066
❶❶❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5072
❶❶❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5081
❶❶❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5087
❶❶❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5112
❶❶❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5120
❶❷⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5133
❶❷❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5147
❶❷❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5154
❶❷❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5159
❶❷❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5183
❶❷❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5189
❶❷❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5196
❶❷❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5221
❶❷❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5223
❶❷❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5243
❶❸⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5250
❶❸❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5259
❶❸❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5288
❶❸❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5295
❶❸❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5304
❶❸❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5315
❶❸❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5319
❶❸❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5332
❶❸❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5338
❶❸❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5354
❶❹⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5364
❶❹❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5365
❶❹❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5372
❶❹❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5400
❶❹❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5406
❶❹❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5431
❶❹❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5437
❶❹❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5452
❶❹❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5462
❶❹❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5664
❶❺⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5689
❶❺❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5693
❶❺❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5722
❶❺❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5740
❶❺❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5755
❶❺❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5796
❶❺❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5801
❶❺❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5818
❶❺❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5820

❶❺❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5854
❶❻⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5859
❶❻❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5864
❶❻❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5868
❶❻❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5879
❶❻❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5886
❶❻❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5917
❶❻❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5927
❶❻❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5944
❶❻❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5949
❶❻❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5974
❶❼⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5984
❶❼❶;
https://t.me/IbnuMunewor/6015
❶❼❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6025
❶❼❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6057
❶❼❹;
https://t.me/IbnuMunewor/6073
❶❼❺:
https://t.me/IbnuMunewor/6095
❶❼❻:
https://t.me/IbnuMunewor/6103
❶❼❼:
https://t.me/IbnuMunewor/6136
❶❼❽:
https://t.me/IbnuMunewor/6158
❶❼❾:
https://t.me/IbnuMunewor/6182
❶❽⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/6191
❶❽❶:
https://t.me/IbnuMunewor/6217
❶❽❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6224
❶❽❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6265
❶❽❹:
https://t.me/IbnuMunewor/6266
❶❽❺:
https://t.me/IbnuMunewor/6303
❶❽❻:
https://t.me/IbnuMunewor/6304
❶❽❼:
https://t.me/IbnuMunewor/6315
❶❽❽:
https://t.me/IbnuMunewor/6320
❶❽❾:
https://t.me/IbnuMunewor/6366
❶❾⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/6367
❶❾❶:
https://t.me/IbnuMunewor/6396
❶❾❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6405
❶❾❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6439
❶❾❹:
https://t.me/IbnuMunewor/6445

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

10 Nov, 05:18


ሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይር እንዲህ ይላሉ፦
"ልብ ሳይገነዘብ እንዲሁ በምላስ ጫፍ የሚፈፀሙ ዚክሮች ይጠቅማሉ። ነገር ግን ምላስ ከልብ ጋር የተዋሀዱባቸው ዚክሮች የሚኖራቸውን ያክል ውጤትና ምንዳ አይኖራቸውም።" [አተዕሊቃቱ ሰኒያህ፡ 116]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

10 Nov, 05:18


ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ በሑዘይፋ መስጂድ የሚሰጠው ደርሳችን እንደተጠበቀ ነው።

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

01 Nov, 15:17


የደዕዋ ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ ጥቅምት 24/ 2017 ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሑዘይፋ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል። ቆይታችሁ ከኛ ጋር ይሁን

1- ኸዲር አሕመድ ከሚሴ
2- ዐብዱልፈታሕ ጀማል
3- ሙሐመድ ሲራጅ
4- አቡል ዐባስ
5- ሳዳት ከማል

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

16 Oct, 07:17


የመካ እና የመዲና ሱራዎች
ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 1)
~
ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል።
ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው።

በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ።

1 - የመካ ሱራዎች፦

ሀ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው።
ለ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
ሐ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
መ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት።
ሠ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው።
ረ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው።
ሰ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው።

2 - የመዲና ሱራዎች፦

ሀ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው።
ለ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው።
ሐ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው።

ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

11 Oct, 17:29


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዘወትር እሁድ በሁዘይፋህ መስጅድ የሚሰጠው ደርሰ ነገ በ03/02/2017 አይኖርም:: ላልሰሙት በማሰማት ተባባሩን

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

05 Oct, 05:54


አንዱ ለመስቀልና ለገና በዓላት "እንኳን አደረሳችሁ" እያለ ከዚያ ግን "ኢሬቻ ሺርክ ነው" ብሎ እያስጠነቀቀ ነው። አዎ ኢሬቻ ሺርክ ነው። ግን መስቀልና ገናውም እኮ የሺርክ በዓላት ናቸው። እና ከመለያየቱ ጀርባ ያለው ምክንያት ምንድነው?
ሌላኛው "መውሊድ ቢድዐ ነው" ሲባል ደግፎ "ኢሬቻ የምስጋና ቀን ነው። ምንድነው ችግሩ?" ይላል፤ ወይም እንደዚያ የሚሉትን ይደግፋል። መውሊድ የሚወገዝበት ምክንያት በሙሉ በባሰ መልኩ ኢሬቻ ላይ አለ። ኢሬቻ ሌላ ምንም ችግር ባይኖርበት እንኳ በኢስላም "የምስጋና ቀን" ብሎ በአመት አንድ ቀን በዓል መያዝ ቢድዐ ነው። ከዚያ ባለፈ ግን በዓሉ የሙስሊም ሳይሆን የዋቄፈና እምነት በዓል ነው። ሌላ ሃይማኖት።
ሺርክን ወይም ቢድዐን ስንቃወም በፖለቲካ ወይም በዘር መነሻ ሊሆን አይገባም። እነዚህ ዝንባሌዎች ጣልቃ ሲገቡ ነው የሚጣረሱ አቋሞች የሚንፀባረቁት። ጉዳዩ አላህን በማሰብ፣ በተቆርቋሪነት እንጂ የትኛውንም ህዝብ ከመውደድና ከመጥላት ጋር ሊያያዝ አይገባም።
ስንቃወምም ስንደግፍም ከብሄር ቀረጢት ልንወጣ ይገባል። ስለ ሃይማኖት ስናወራ በሸሪዐ ሚዛን ብቻ ነው መመዘን ያለብን። ከኢሬቻ ስናስጠነቅቅ
የኦሮሞን ህዝብ ለመንካት አይደለም፣ መሆንም የለበትም። አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብኮ ሙስሊም እንጂ ዋቄ ፈታ አይደለም። ይልቅ ይበልጥ መልእክቱ ተደራሽና ፍሬያማ እንዲሆን በኦሮሞ መሻይኽ/ዱዓቶች የተዘጋጁ ትምህርቶችን ማሰራጨት ላይ ብናተኩር መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

05 Oct, 04:09


ደርስ ፡- ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
ክፍል፡- ክፍል ሶስት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

04 Oct, 08:59


የኔዎች
~
ዘር ያላጎራበተን … በደም ያልተዛመድን
ኢስላም ብቻ ያገናኘን … በሱና፞ የተጋመድን
የልቦቻችን ስስቶች … የፍቅራችን አሻራ
ከስልጤ፣ ከጉራጌ … ከኦሮሞ፣ ከአማራ
ከትግሬ፣ ከሱማሌ … ከአፋር፣ ከአርጎባ
ከበርታ፣ ከወለኔ … ከአደሬ፣ ከሀላባ



በዘር ነውጥ ያልተናጡ … ለኢስላም እጅ የሰጡ
በሱና፞ የሚለኩ … በሱና፞ የሚቆርጡ
ለልባችን የቀረቡ … አእላፍ ወዳጆች አሉ
ለአላህ ሲሉ የሚወዱ … ለአላህ ሲሉ የሚጠሉ።
አሉኝ "የኔ" የምላቸው … በምስራቅ በምእራብ
ከወንድም፣ ከእህቶቼ … በሰሜኑም በደቡብ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

02 Oct, 03:14


🔴 አሁን ቀጥታ ስርጭት

📚 رياض الصالحين
ክፍል - 84

(33) باب حق الزوج على المرأة

رقم الحديث 288

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

ሼር በማድረግ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያድርጉ

የላይቩ ሊንክ
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

27 Sep, 07:15


" إريتشا في عشر دقائق "

"Irreecha daqiiqaa 10 kessatti "


Fuad mohammed
https://t.me/fuadorodurus

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

27 Sep, 05:11


ደርስ ፡- ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
ክፍል፡- ክፍል ሁለት
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

27 Sep, 04:01


ደርስ ፡- ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
ክፍል፡- ክፍል አንድ
የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር እሁድ
የሚሰጥበት ቦታ፡- አዲስ አበባ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሁዘይፋህ መስጂድ
https://t.me/ibnusultan38

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

23 Sep, 18:35


(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"

(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"
(15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አሰተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት።
ሰላም!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

23 Sep, 18:34


ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል።
ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል።

① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ ራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ። አንተ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"ራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሃብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮችን ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ ራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ ራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ ቴኳንዶ፣ የእጅ ሙያዎች፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

23 Sep, 03:38


ሸይጧናዊ ከራማዎች
~
የሸይጧን ወሊዮች የተለያዩ ወጣ ያሉ ነገሮችን ሊሰሩ፣ አንዳንድ ለሰው የተደበቁ ነገሮችን ሊያውቁ ይችላሉ። ይሄ ሸይጧን ለወዳጆቹ የሚያደርገው እንክብካቤ እንጂ የሩቅ አዋቂ ሆነው አይደለም። ነብይነትን ሲሞግቱ የነበሩት ቀጣ.ፊው ሙሰይሊማ እና አስወድ አልዐንሲ በሸይጧን እየታገዙ ድብቅ ሚስጥራትን ይናገሩ፣ አነጋጋሪ ነገሮችን ይፈፅሙ ነበር። በጥፋት ላይ እየተጓዙ ወይም ከሸሪዐ ጋር የሚፃረር ነገር እየፈፀሙ ወጣ ያሉ ነገሮችን መናገራቸው ወይም መፈፀማቸው የተከበሩ ወሊዮች ሆነው ሳይሆን ከጀርባቸው ሌላ አካል ስለነበር ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡

“በወሊዮች ከራማዎችና እነሱን በሚመስሉ ሸይጧናዊ ሁኔታዎች መካከል በርካታ ልዩነቶች አሉ። ከነዚህ ውስጥ የወሊዮች ከራማዎች ሰበባቸው ኢማንና ተቅዋ ሲሆን የሸይጧናዊ ሁኔታዎቹ ሰበብ ደግሞ አላህና መልእክተኛው የከለከሉት ነገር ነው። በእርግጥ አላህ እንዲህ ብሏል፡- { 'ጌታዬ የከለከለው፡ ግልፅም ይሁን ስውር የሆኑ አስቀያሚ ጥፋቶችን፣ ሃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ ማስረጃ ባላወረደበት በአላህ ላይ ማጋራታችሁንም፣ በአላህ ላይ የማታውቁትን መናገራችሁንም ነው' በላቸው።} [አልአዕራፍ፡ 33]

በአላህ ላይ ያለ እውቀት መናገር፣ ማጋራት፣ በደልና አስቀያሚ ወንጀሎች አላህና መልእክተኛው የከለከሏቸው ናቸው። እናም እነኚህ ጥፋቶች በከራማ በመታጀብ በአላህ ለመከበር ሰበብ ሊሆኑ አይችሉም። በሶላት፣ በዚክርና ቁርኣንን በመቅራት ያልተገኙ ከራማዎች፣ ሸይጧን በሚወደው፣ ከፍጡር እርዳታ በመጠየቅ አይነት ባሉ በሺርክ ነገሮች ወይም ለበደል በሚታገዙባቸው ነገሮች፣ አስቀያሚ ወንጀሎችን በመፈፀም የሚገኙ ከሆነ እነሱ ያለጥርጥር ከሸይጧናዊ ሁኔታዎች እንጂ ከአረሕማን ከራማዎች አይደሉም። ከነዚህም ውስጥ ፉጨትና ጭብጨባ ያለበት ጭፈራ ላይ ሲገኝ ሸይጧኑ ወርዶለት ባየር ላይ ተሸክሞት ካለበት ሀገር የሚያስወጣው አለ። ከአላህ ወሊዮች አንዱ ተገኝቶ ሸይጧኑን ካባረረው ግን ጥሎት የሚጠፋ አለ፣ ብዙዎች ላይ እንዳጋጠመው።

ከነዚህም ውስጥ በህይወት ባለ ወይም በሞተ ፍጡር እርዳታ የሚጠይቅ አለ። የሚጠራው አካል ሙስሊም ሊሆን ይችላል፣ ክርስቲያን ሊሆን ይችላል፣ አጋሪ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ሸይጧኑ በዚያ እርዳታ በተጠየቀው ሰው ተመስሎ የእርዳታ ጠያቂውን አንዳንድ ጉዳዮች ይፈፅማል። ሰውየው ራሱ ወልዩ ወይም በለመነው ሰው ተመስሎ የመጣ መልአክ ይመስለዋል። እሱ ግን በአላህ ላይ በማጋራቱ እያጠመመው ያለ ሸይጧን ነው። ልክ ሸይጧኖች ጣኦቶች ውስጥ እየገቡ አጋሪዎችን ሲያናግሩ እንደነበረው። ከነዚህ ውስጥ ሸይጧን ተመስሎለት ‘ኸዲር ነኝ’ የሚለው አለ። አንዳንድ ነገሮችን ሊነግረው፣ አንዳንድ ጉዳዮቹን ሊፈፅምለትም ይችላል፣ ለብዙ ሙስሊሞች፣ አይሁዳውያን፣ ክርስቲያኖችና ሌሎችም ከሃዲዎች በምስራቅም በምእራብም እንዳጋጠመው። አንድ ሰው ከሞተባቸው በኋላ ሸይጧን በሱ ተመስሎ ይመጣል። እነሱ ሟቹ ነው ብለው ያምናሉ። እዳዎቹን ይከፍላል። አደራዎችን ይመልሳል። ከሟቹ ጋር የሚያያዙ ነገሮችን ይፈፅማል። ከሚስቱ ዘንድ ይገባል። ከዚያም ተመልሶ ይሄዳል። ምናልባት እነሱ የሟቹን አስከሬን አቃጥለውም ይሆናል፣ ልክ የህንድ ከሃ .ዲዎች እንደሚያደርጉት። ከዚያም እነሱ ከሞት በኋላ ኖረ ብለው ያስባሉ። ከነዚህ ውስጥ አንድ ግብፅ ውስጥ የነበረ ሸይኽ ክስተት የሚጠቀስ ነው። ለአገልጋዩ፡ ‘ስሞት አንድም የሚያጥበኝ ሰው እንዳትጠራ። እኔ ራሴ መጥቼ ራሴን አጥባለሁ’ ይለዋል። ሸይኹ ሲሞት አገልጋዩ እሱን የመሰለ ሰው ያያል። ሸይኹ እንደተናገረው መጥቶ ራሱን አጠበ ብሎ አመነ። አጥቦ እንደ ጨረሰ ተሰወረ። ሟቹን በህይወት ሳለ ከእምነት ያስወጣው ሸይጧን ነበር። ‘ስትሞት ራስህን ተመልሰህ ታጥባለህ’ ብሎ ነግሮታል። ሲሞት ደግሞ በህይወት ያሉትን ሊያሳስት ነው ሰውየውን ተመስሎ የመጣው።

ከነሱም ውስጥ ከበላዩ ብርሃን ያለበት ዙፋን ባየር ላይ የሚመለከት አለ። ‘እኔ ጌታህ ነኝ’ በማለት የሚያናግረው ይሰማል። እውቀት ካለው ሸይጧን እንደሆነ አውቆ ይገስፀዋል። ከሱም በአላህ ሲጠበቅ ይወገዳል። ... እነዚህ ሸይጣናዊ ክስተቶች የሚከሰቱት ከቁርኣንና ከሱና ለወጣ ነው። እነሱም የተለያዩ ደረጃዎች አሏቸው። ከነሱ ጋር የሚቆራኙትም ጂኖች የነሱው ብጤ አፈንጋጮች በነሱው መንገድ ላይ ያሉ ናቸው። ጂኖች፡ ከሃዲ፣ አመፀኛና ስህተተኛ አላቸው። ሰውየው ከሃዲ ወይም አመፀኛ ወይም መሀይም ከሆነ ጂኖቹ ከሱ ጋር ወደ ክህደት፣ አመፅና ጥመት ውስጥ ይገባሉ። በሚመርጡለት ክህደት ላይ ከተስማማ ሊያግዙት ይችላሉ። ለምሳሌ በሚያከብሩት ጂን ስሞች ወይም በሌላ እንዲምል ሊሆን ይችላል። የአላህን ስሞች ወይም ንግግሮቹን በቆሻሻ ነገር እንዲፅፍ ሊሆን ይችላል። ወይም ፋቲሐን ወይም ሱረቱል ኢኽላስን ወይም ኣየተል ኩርሲይን ወይም ሌላ ገልብጦ ከመጨረሻ ወደ መጀመሪያ በቆሻሻ እንዲፅፍ ሊሆን ይችላል። ክህደት እየፈፀመ ሲያስደስታቸው ውሃን ሊያሰርጉለት፣ ይዘውት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ። የሚፈልገውን ሴት ወይም ህፃን በአየር ላይ ወይም ባለበት ገፍተው ሊያስጠጉለት ይችላሉ። ይህን የሚመሳስሉ ተተርከው የማያልቁ ነገሮች አሉ። በነዚህ ነገሮች ማመን በድግምትና በጣኦት ማመን ነው። [አልፉርቃን፡ 171-175]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel

22 Sep, 13:47


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

3,362

subscribers

114

photos

3

videos