የሰለምቴዎች ቻናል @slmatawahi Channel on Telegram

የሰለምቴዎች ቻናል

@slmatawahi


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

የሰለምቴዎች ቻናል (Amharic)

የሰለምቴዎች ቻናል በእርስዎ እና በእናትህ ጋር ተቆማ፣ ተሻሽ፣ እንወዳለን! እስካሁንም አመሰግናለሁ በተጨማሪህ እና በግሩኝት ከሚሊኒ ላይ ወዳለብህ። የሰለምቴዎች ቻናል በአላህ በመምህር፣ እምነት፣ ለመስጠት፣ ልብን ማረጋገጥና ሌሎች የሰልፍ አባላት፣ ታሪኮች እንደካስ ላይ የሚሰሩበት አካባቢ ነው። የሰለምቴዎች ቻናል በዚህ ቻናል ሰነዶችን እየሰራ ብለኋል የተላችዋለበት ስትሰጥ ምርቃን የላከበትን ቪጋትን አሳዝኋለሁ።

የሰለምቴዎች ቻናል

19 Nov, 04:10


الْقُرْآن حَيَاة القلوب🍃

من يسمع القرآن بورك قلبهُ،
كيف الذي يتلو الكتاب المُنزلا.!

የሰለምቴዎች ቻናል

18 Nov, 18:54


https://t.me/path_of_the_prophets

መልሶቻችን ጀምረዋል ግቡ

የሰለምቴዎች ቻናል

18 Nov, 12:20


ርእስ ቁርአን እና ሳይንስ            ኡስታዝ አቡ ሙዓውያ    
https://youtube.com/watch?v=TvFIBtg0nUg&si=9xAFQA8EOatNNnbt

የሰለምቴዎች ቻናል

18 Nov, 11:13


ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል
https://t.me/path_of_the_prophets?livestream=8d2bc9ab657bbc866c

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 21:31


ቁርአን የልብ ብርሃን
የመንፈስ እርካታ
የህይወት መመርያ
የማንነታችን ፈውስ ብዙ ነገራችን ነው

Al-Qiyamah القيامة
: Islam Sobhi اسلام صبحي

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 21:19


◆▮ውይይት▮◆

"እስልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ"

◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ወንድም አሕመድ
◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ሌሎችም
         🅥🅢
◍ ከብዙ ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 20:39


ግቡ ሽሃዳ አለ

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 19:10


ቲላዋ🍂
በ Abu Yasir

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 19:08


የግብፅ ሥላሴ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

በሥነ ሥላሴ ጥናት"Triadology" ከክርስትናው ሥላሴ በፊት ሦስት የተለያየ ፊት ያላቸው "ሥሉስ አምላክ"Triple Deity" በተለያየ የዓለም ክፍሎች ይታምባቸው ነበር፥ ከእነዚያ አንዱ የግብፅ ሥላሴ ነበር። ግብፅ "እስክንድሪያ" ተብላ የተቆረቆረችው 331 ቅድመ ልደት በግሪክ ንጉሥ በታላቁ እስክንድር ሲሆን የግሪክ ቋንቋ በእስክንድሪያ ተጽዕኖ ስሳደረ አብዛኛውን የግብፅ ባህል በግሪክ ቋንቋ የተዘጋጁ ናቸው።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በኮይኔ ግሪክ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪያስ" τρῐᾰ́ς ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ በግዕዝ "ሥሉስ" ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ሥላሴ" ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው።

"ፕሮሶፓን" πρόσωπον ማለት "ፊት" "ገጽ" "መልክ" ማለት ሲሆን በግብፅ ከጥንት ጀምሮ ሦስት ፊቶች ያላቸው ነገር ግን አምላክነትን የሚጋሩ "ኦሲሪስ" Όσιρις አባት አምላክ፣ "አይሲስ" Ἶσῐς እናት አምላክ እና "ሆረስ" Ὧρος ልጅ አምላክ ይመለኩ ነበር።
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" Ο Θεός ο πατρὸς ማለት "አባት አምላክ"God the Father" ማለት ሲሆን እርሱም ኦሲሪስ ነው፣
፨ "ቴስ ቴያ ቴስ ሜትሮስ" τῆς θεά τῆς μητρὸς ማለት "እናት አምላክ"Goddess the Mother" ማለት ሲሆን አይሲስ ናት፣
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο υἱός ማለትም "ልጅ አምላክ"God the Son" ማለት ሲሆን ሆረስ ነው።
Strudwick, Helen (2006). The Encyclopedia of Ancient Egypt. New York: Page 118.

ኤጵፋኒዮስ ዘሳልሚስ"Epiphanius of Salamis" ከ 320 እስከ 403 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ የቆጵሮስ ኤጲስ ቆጶስ ሲሆን "The Panarion of Epiphanius of Salamis" የተባለ ዕውቅ የታሪክ መጽሐፉ ገጽ 637 ላይ "ኮሊሪዲያን"Collyridian" ብሎ የሚጠራቸው የክርስትና ጎጥ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ "ማርያማውያን"Mariamites" ናቸው፦
"ኮሊሪዲያን ድንግል ማርያምን እንደ አምላክ ያመልኩ ነበር፥ እነዚህ ጎጥ ድንግልን በማላቅ በግጻዌ መለኮት ውስጥ ስለሚያካትቱ ማርያማውያን ይባሉ ነበር"።
Readings in Biography: A Selection of the Lives of Eminent Men of All Nations <by William Cooke Taylor> Page 192.

የማርያማውያን ሥላሴ ከግብፅ ሥላሴ የተኮረጀ ሲሆን አባት፣ እናት ማርያም እና ልጅ ኢየሱስ የተባሉ ሦስት አካላት ናቸው። ፕሮፌሰር ጆን ሆልመስ"John Holmes" ማርያማውያን ማርያምን ከሥላሴ ሦስት አካላት አንዷ እንደሆነች አድርገው ያምኑ እንደነበር አበክረው ተናግረዋል፦
"ማርያማውያን በዚህ ስያሜ የተጠሩት ማርያም ስለሚያምልኩ እና ከአባት እና ከልጅ ጋር ከመለኮታዊ የሥላሴ አካላት አንዷ አርገው ስለሚያምኑ ነው"።
The Eclectic Magazine: Foreign Literature science and Art. By John Holmes Agnew, Walter Hilliard Bidwell, volume 21, page 40.

ሚሽነሪው የሥነ መለኮት ምሁር ጊልበርት ሪድ"Gilbert Reid" የማርያማውያን ሥሉስ አምላክ"Tritheism" አባትን፣ እናትን እና ልጅን እንደሚያቅፍ ተናግረዋል፦
"ክርስትናን በተመለከተ በዐረብ አገር የተወከለው ሥሉስ አምላክ እንጂ ግልጽ ያልተበከለ አምላካዊነት አልነበረም፥ ሰማያዊ አባት፣ የአምላክ እናት ማርያም እና ልጃቸው ኢየሱስ ሥሉስ አምላክ ሆነው ይመለኩ ነበር"።
Gilbert Reid – The Biblical World: Volume 48, Number 1, Page 12.

"ትራይቴይዝም"Tritheism" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "ትሪ" τρῐ እና "ቴዎስ" θεός ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ቴዎስ" θεός ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በላቲን "ትሪኒ" trīni ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪኒታስ" trīnitās ማለት ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ "ትሪኒቲይ"Trinity" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ሦስትነት"threeness" ማለት ነው።

የማርያማውያን ሥላሴ ልክ እንደ ዮሐንስ ተዐቃቢ"John Philoponus" ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ፈቃድ፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ ሕይወት አላቸው ስለሚሉ በዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ዘንድ "ሦሉስ አምላካውያን ወይም የሦስት ባሕርያት አማንያን" የሚል ነቀፌታ ይደርስባቸዋል፥ ዮሐንስ ተዐቃቢ ከ 490 እስከ 570 ድኅረ ልደት በእስክንድርያ ይኖር የነበረ ሲሆን "ሥላሴ በከዊን አይገናዘቡም" በማለቱ እና ፈቃድን ለባሕርይ ሳይሆን ለአካል ስለሚሰጥ "ሦስት ባሕርያት" ይላል በሚል የሐሰት ክስ በ 680 ድኅረ ልደት በ3ኛው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ተወግዟል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 85 ቁጥር 23
"ሐሰትን የያዙ ሌሎችም "ሥላሴ በባሕርይ እንደሆኑ ይናገራሉ"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 91 ቁጥር 11
"ሦስት አማልክት እና ሦስት ባሕርያት ከሚሉት መናፍቃን ጋር አንድ በሚሆን ድንቁርናው የሚመካ ተዐቃቢ የሚባል ዮሐንስ እንደ ተናገረ ይህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አነጋገር አይደለም"።

የዘመናችን የፕሮቴስታንት ሥላሴ ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው በሚል "ማኅበራዊ ሥላሴ"Social Trinity" እሳቤ የሚታወቁ ሲሆኑ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አካልን እንጂ ባሕርይን ታሳቢ ስለማያረጉ ከዮሐንስ ተዐቃቢ ጋር ያመሳስላቸዋል። እሩቅ ሳንሄድ ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ቀደም "የአስተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት" በሚል መጣጥፋቸው ላይ፦ "ሦስት አካል ናቸው" ስንል ደግሞ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት አላቸው" ማለታችን ነው፥ አካል የሚለውን ቃል የምንጠቀመው እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት እንዳለው ለማሳየት ብቻ ነው" በማለት እያንዳንዱ አካል የየራሱ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ እንዳለው ጦምረዋል።

ወደ ነጥባችን ስንመለስ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ማርያማውያን የክርስትና ጎጥ "ሦስት ነው" የሚሉትን ሆነ ዐበይት ክርስትና "ሦስት ነው" የሚሉትን አምላካችን አሏህ «ሦስት ነው» አትበሉ" በማለት ሁለቱንም ድንበር አላፊያን ይገስጻቸዋል፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 19:08


በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሦስቱን አካላት እነማን እነደሆኑ ቁርኣን ቢጠቅስ ኖሮ እያንዳንዱ አንጃ "የእኛን ሥላሴ በቅጡ አልተረዳውም፥ ቁልመማዊ ሕፀፅ አፅፆአል" ተብሎ ከሁለቱ ወገን በአንዱ ክስ ይቀርብ ነበር። ኢየሱስን የላከ አንድ አምላክ አሏህ ሆኖ ሳለ ያንን አንድ አምላክ ከሦስቱ ማንነቶች አንዱ ማንነት ነው" ማለት በእርግጥ ክህደት ነው፦
5፥73 እነዚያ «አላህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ ثَالِثُ ثَلَاثَةٍ
"Certainly they are unbelievers who say: "Allah is one of three". (Farook Malik Translation)
ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 5፥73 "የላቀው አሏህ ንግግር፦ "እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ" ማለት "ከሦስቱ አንዱ ነው" ማለታቸው ነው ። قوله تعالى: { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ }. أي أحد ثلاثة.

ኢብኑ ዐባሥ ዐበይት የሥላሴ አማንያን የሚሉትን ታሳቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" እንደሆኑ ሲያስቀምጥልን ጀላለይን ደግሞ ማርያማውያንን የሚሉትን ዋቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ እናትን" እንደሆኑ አስቀምጦልናል፦
ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 5፥73 "እነዚያ «አሏህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፥ መርቁሢያህ፦ "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" አሉ"። { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ } وهي مقالة المرقوسية يقول أب وابن وروح قدس
ተፍሢር ጀላለይን 5፥73 «እነዚያ "አሏህ ሦስተኛ" ያሉ በእርግጥ ካዱ» አማልክት «ሦስት» አሉ፥ እርሱ(አሏህ) ከእነርሱ አንዱ ነው፥ ሁለቱ ኢየሱስ እና እናቱ ናቸው" ይህንን የሚሉት ከነሷሪይ ፊርቃህ ናቸው"።
{ لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ } آلهة { ثَلَٰثَةً } أي أحدها والآخران عيسى وأُمّه وهم فرقة من النصارى

"ፊርቃህ" فِرْقَة ማለት "ጎጥ" "አንጃ" ማለት ነው፥ ኮሊሪዲያን በአንድ ወቅት የነበረ አሁን ላይ የጠፋ የክርስትና ጎጥ"sect" ነው። ዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ሥላሴያቸው ከሂንዱ ሥላሴ የተቀዳ ሲሆን የኮሊሪዲያን ሥላሴያቸው ደግሞ ከግብፅ ሥላሴ የተቀዳ ነው፥ "ክርስቲያን ነን" የሚሉት ሁለቱም የየራሳቸውን ሥላሴ በጥቅሉ ቁርኣን በአንድ ድንጋይ "ሦስት ነው አትበሉ" በማለት ሁለቱንም አእዋፍ መቷቸዋል። ደግ አረገ! "ክርስትና የበቀለው ከዐረማዊነት ነው" የምንለው በምክንያት ነው። የክርስትና ታሪክ ምሁር ኤድዋርድ ጊቦን "History of christianity" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ ክርስትና ዐረማዊነት"paganism" እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"አረማዊነት በክርስትና ድል ቢነሳም ክርስትናም በዚያው መጠን በአረማዊነት ተበክሏል"።
History of christianity (Edward Gibbon) page XVI(16)

የሥላሴ አማንያን ክርስቲያኖች ሆይ! ነቢያት እና ሐዋርያት የማያውቁት እና ውስብስብ ከሆነው የክርስትና ሥላሴ ወጥታችሁ በተውሒድ እንድታምኑ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

17 Nov, 14:25


➧ኢብኑ ተይሚያ ~የሱንናዉ አንበሳ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

◉ክፍል 01

✍️ስም፣ዉልደትእና ተያያዥ ነጥቦች!


♦️ሙሉ ስማቸዉ፦አሕመድ ኢብን ዐብዲል ሐሊም ኢብን ዐብዲ ሰላም ኢብን ዐብዲላህ ኢብኒል ኸድር ኢብን ሙሐመድ ኢብን ተይሚያ ይባላል።

♦️የትዉልድ ቦታቸዉ፦ሐራን ትባላለች። ስለዚህ ''አልሐራኒ"ማለትም "ሐራናዊ"/የሐራን ሃገር ሰዉ/በመባል ይታወቃሉ።''ሐራን"በሚል መጠሪያ የሚታወቁ በርከት ያሉ አካባቢዎች አሉ። የሳቸዉ ትዉልድ ቦታ ሐራን ግን ዛሬ በሰሜን ምስራቅ ቱርክ ጫፍ ከሶሪያ ድንበር በጥቂት ርቀት ላይ ትገኛለች።

♦️የትዉልድ ዘመናቸዉ፦ ከእናታቸዉ ሸይኻ ሲቱ ኒዕም አልሐራንያ እና ከአባታቸዉ ዐብዱል ሐሊም ኢብን ተይሚያ በረቢዑል አወል 10/661ተወለዱ። ይህ ወደ ፈረንጂ አቆጣጠር ሲቀየር ጃንዋሪ 22/1263 ይሆናል።

♦️የኖሩበት ሃገር፦በ667ሂ.የስድስት አመት ልጂ ሳሉ የትዉልድ አካባቢያቸዉን ሐራንን ተታሮች ሰላጠቋት ወላጂ አባታቸዉ ቤተሰባቸዉንና ኪታቦቻቸዉን በመያዝ በፍጥነት በሌሊት ተጉዘኹ ደማስቆ ከመግባታቸዉ ለጥቂት ተርፈዋል።ከዚያ በኋላ ኑሯቸዉ በዚያዉ ሆነ።

♦️ኩንያቸዉ፦ አቡል ዐባስ ነዉ፣የዐባስ አባት።ግና ይሄ ኢስላም እዉቅና የሰጠዉ የዐረቦች ሱንና እንጂ ዐባስ የሚባል ልጂ አልነበራቸዉም።እንደዉም ከነጭራሹ እድሜ ልካቸዉ አላገቡም።

♦️ቅፀል መጠሪያቸዉ፦ በግዜ በነበረዉ ወግና ልማድ መሠረት በርካታ ታላላቅ ምሁራን"ሙሕዩዲን"ዒዘዲን" ''ጀላሉዲን" "አሣሩዲን" "ከማሉ ድን" "ፈኽሩዲን'" ፣የሚል ቅፀል ከስማቸዉ ይቀድም ነበር። ወይ ደግሞ በዚህ ቅፀል ይጠሩ ነበር። ታድያ ኢብኑ ተይሚያም"ተቅዩዲን" በሚል ቅፀል ይታወቁ ነበር።

♦️አካላዊ መገለጫዎች ሁኔታቸዉ፦ ቆዳቸዉ ነጭ ሲሆን የራሳቸዉ ፀጉር ጥቁር ሆኖ እስከ ጆሯቸዉ ድረስ ይወርዳል።ፂማቸዉ ጥቂት ሽበቶች አሉበት።ቁመታቸዉ መካከለኛ፣ትከሻቸዉ ሰፊ፣ሲናገሩ ድምፃቸዉ ከፍ ያለ፣ አንደበተ ርቱዕ ነበሩ። ሲያነቡ ፈጣን ናቸዉ። ሃይለኝነት ቢንፀባረቅባቸዉም ነፍሳቸዉን በመቆጣጠር በይቅር_ባይነት ያሸንፉታል። አይኖቻቸዉ ተናጋሪ ምላስ ይመስላሉ።ሲናገሩ ከአፍቸዉ ላይ ቃላት ይደራረባሉ።

♦️ጎሳቸዉ፦ የኑመይር ጎሳነዉ።"አንኑመይሪ"እየተባሉ የሚጠሩት በዚህ ሰበብነዉ። ይህ ጎሳ የዓሚር ኢብኑ ሶዕሶዐህ ጎሳ ንኡስ ክፍል ነዉ።

♦️ይህንን ሐቅ የኢብኑ ተይሚያህ የተማሪዎቻቸዉ ተማሪ የሆኑት ኢብኑ ናስሪዲን አድዲመሽቂ(842 ሂ)እና መሕሙድ ኢብኑ ሙሐመድ አልዐደዊ (1,032)ጠቅሰዉታል። እንድያዉም በአንዳንድ ኪታቦቻቸዉ ላይ ይሄዉ ኒስባ ተገኝቷል ። በክር አቡ ዘይድም ይህንኑ ሀሳብ አፀድቀዋል።(አልመዳኺል:16) ስለዚህ ኢብኑ ተይሚያህ አንዳንዶች እንደሚሉት ኩርድ ሳይሆኑ በቋንቋም በዘርም ዐረብ ናቸዉ ማለት ነዉ።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል .......................

የሰለምቴዎች ቻናል

16 Nov, 22:16


ኢስላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች መልሶቻችንነብያችንን ጅኒ ደፈሯቸው እያሉ ለሚዋሹት ውሸት መልስ*"የዓንሻ ጋብቻ"ሌሎች...
https://youtube.com/watch?v=YkfLDRgrCDE&si=kXRBD4OhA_F5yGao

የሰለምቴዎች ቻናል

16 Nov, 21:17


Abu Yasir

የሰለምቴዎች ቻናል

16 Nov, 11:07


የምስራች ከቁርአን ቀጥሎ ትልቁን ኪታብ ሶሂሁ አልቡኻሪን መቅራት ለምትፈልጉ ሁሉ

ለመመዝገብ


አኅት ዘሃራ ሙስጠፍን፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት ዝሃራ ኢማምን ፦ @Zehar678
ያናግሩ

የሰለምቴዎች ቻናል

15 Nov, 14:39


ከታዳሚያን ጋር ውይይት ጥያቄ  የካፊሮች ጥያቄ እና መልሶቻቸው ክፍል (3)   ደስ ይላል   ኢምራን     ዝሃራ ...
https://youtube.com/watch?v=5yFFotqPjRo&si=INXFHJjSdq21Nuf8

የሰለምቴዎች ቻናል

15 Nov, 08:56


سوره الكهف

«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡
ካህፍ 109

የሰለምቴዎች ቻናል

15 Nov, 08:51


የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል:–

የጁመዓህ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው በሁለቱ ጁመዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል

ዛሬ ጁመዓህ ነው ላስታውሳችሁ

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

(ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 9)
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡

የሰለምቴዎች ቻናል

14 Nov, 22:04


☀️አያሙል ቢድ ፆም ነገ ይጀመራል የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ።

⇛ አያሙል ቢድ _ጁምዓ 13
⇛ አያመል ቢድ _ ቅዳሜ 14
⇛ አያመል ቢድ _ እሁድ 15
ደስ ሲል ከዛ ሰኞ ነው
ዛሬ የጾማችሁ አምስት ቀን ተከታታይ ይሆንላችኃል ልጆችዬ ጹሙ እሺ ጾም ጋሻ ነው

🔸قال ﷺ : إذا صمت من الشهر ثلاثًا، فصم ثلاث عَشْرَةَ، وأربع عَشْرَةَ، وخمس عَشْرَةَ.

የሰለምቴዎች ቻናል

09 Nov, 22:17


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

09 Nov, 21:02


አዲስ ቪድዮ You Tube ላይ ተለቋል። ግቡና ተመልከቱ። ክፍል ሁለት
https://youtu.be/8up1_xrX1rI?si=brv0xrMy5Hfjn5e6

የሰለምቴዎች ቻናል

09 Nov, 18:10


ኢስቲዋእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

"ኢስቲዋእ" اسْتَوَىٰ ማለት ምን ማለት ነው? የቋንቋ ምሁራን በተለየየ ዓይነት ትርጉም ይመጣል ይላሉ፤ ይህ ትርጉም ለሁለት ከፍለው ያዩታል፤ አንዱ "ሙቀየቅ" ሲሆን ሌላው "ሙጥለቅ" ነው፤ እነዚህን እስቲ ጥልልና ጥንፍፍ አድርገን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሙጥለቅ"
"ሙጥለቅ" مطلق ማለትም "ያልተገደበ" ሆኖ ሲመጣ ለምሳሌ "ኢስቲዋእ" ከሚለው ቃል በፊትና በኃላ ምንም መስተዋድድ ሳይመጣ ኢስተዋእ ሳይገደብ ሲቀር "በሰለ" "ተስተካከለ" "ሞላ" በሚል ቃል ይመጣል፦
28:14 ብርታቱንም በደረሰ እና *በተስተካከለ* ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَٱسْتَوَىٰٓ ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًۭا وَعِلْمًۭا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ

ነጥብ ሁለት
"ሙቀየድ"
"ሙቀየድ" مُقَيَّد ማለትም "የተገደበ" ማለት ሲሆን "ኢስቲዋእ" ከሚለው ቃል በፊትና በኃላ መስተዋድድ ሲመጣ ኢስተዋእ ሲገደብ የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል፤ ለምሳሌ ኢስተዋእ ከሚለው ቃል በኃላ "ኢላ" إِلَى ማለትም "ወደ" የሚለው መስተዋድድ ከመጣ "አሰበ" በሚል ይመጣል፦
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ *አሰበ*፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

ሌላው ለአላህ ዙፋን የዋለው “ኢስተዋእ” የሚለው ቃል “አላ” عَلَى በሚል መስተዋድድ መምጣቱ “ፈተአላ” فَتَعَالَى ማለትም “ከፍ አለ” የሚል ትርጉም ይኖረዋል፦
20፥5 እርሱ አር-ረሕማን ነው በዐርሹ ላይ *ተደላደለ*። ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَى ٱلْعَرْشِ ٱسْتَوَىٰ

አላህም እራሱን በሶስተኛ መደብ “አል-አዕላ” الْأَعْلَى ማለትም “ጸባዖት” መሆኑን ተናግሯል፤ ይህም የሚያሳየው አላህ አጠቃላይ ከፍጥረት ሁሉ በላይ መሆኑን ነው፦
87:1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን* ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى
16:49-50 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሻም በምድር ያለው ሁሉ መላክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም፤ ጌታቸውን *ከበላያቸው* ሲሆን ይፈሩታል፤ የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوْقِهِمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ ۩

“ፈውቅ” فَوْق ማለት “የበላይ” ማለት ሲሆን አላህ ከፍጡራን የተለየ መሆኑን ያሳያል፤ ለምሳሌ የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው ይላል፦
48፥10 እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ ከእጆቻቸው *በላይ* ነው፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ 

የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው ማለት የአላህ እጅ ከፍጡራን እጆች ተለይቶ የበላይ ነው ማለት እንደሆነ ሁሉ አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ማለት ከትልቁ ፍጥረት ተነጥሎ የበላይ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ አላህ በፈጠረው ፍጥረታት ላይ ሁሉ የበላይ ታላቅ ስለሆነ እራሱን “አል-ዓሊይ” العَلِيّ ብሏል፦
42:4 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፤ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ ።
22:62 አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ ።
2:255 እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

09 Nov, 13:01


አዲስ ቪድዮ You Tube ላይ ተለቋል። ግቡና ተመልከቱ።

https://youtu.be/jUxKc5RIb78?si=UZs12KJT4t2JxIzJ

የሰለምቴዎች ቻናል

09 Nov, 00:30


@slmatawahi

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 22:36


◆▮ውይይት▮◆

"ባይብል እንደት ነብያትን አዋረደ"
"ዳዊት ሰዎችን በመጋዝ ይሰነጥቅ ነበር" ሃሩን ጣኦት አመለከ"ዮናስ ሰዎችን አስገደለ"ሌሎችም"።

ክፍል 1
◍ ኡስታዝ ወሒድ
◍ ወንድም ዒምራን
◍ወንድም አቡ ሙዓዊያህ
◍ወንድም ሳለህ

         🅥🅢
◍ ከብዙ ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 21:00


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 14:51


የአላህ እጆች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት። ለምሳሌ "ጀንብ" جَنب ማለት "ጎን" በሚል ቃል መጥቷል፦
4፥103 ሶላትንም በፈጸማችሁ ጊዜ ቆማችሁም ተቀምጣችሁም *በጎኖቻችሁም* ላይ ተጋድማችሁ አላህን አውሱ፡፡ فَإِذَا قَضَيْتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ قِيَٰمًۭا وَقُعُودًۭا وَعَلَىٰ جُنُوبِكُمْ ۚ فَإِذَا ٱطْمَأْنَنتُمْ فَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ ۚ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتْ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ كِتَٰبًۭا مَّوْقُوتًۭا

"በጎኖቻችሁም" የሚለው "ጁኑቢኩም" جُنُوبِكُمْ ሲሆን "ጀንብ" جَنب የሚለው ቃል ሌላ ቦታ "በኩል"regard to" በሚል መጥቷል፦
39፥56 የካደች ነፍስ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስኾን በአላህ *በኩል* ባጓደልኩት ዋ ጸጸቴ» ማለቷን ለመፍራት፤ أَن تَقُولَ نَفْسٌۭ يَٰحَسْرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِى جَنۢبِ ٱللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ ٱلسَّٰخِرِينَ

የጀንብ ዝርያ "ጁኑብ" جُنُب ሲሆን "ሩቅ" በሚል ፍቺ መጥቷል፦
28፥11 ለእኅቱም ተከታተይው አለቻት፡፡ እርሱንም እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ *በሩቅ* ሆና አየችው፡፡ وَقَالَتْ لِأُخْتِهِۦ قُصِّيهِ ۖ فَبَصُرَتْ بِهِۦ عَن جُنُبٍۢ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 14:51


ስለዚህ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ ነው የምንለው ለዛ ነው፤ "Volume" በሥነ-ጽሑፍ "ቅጽ" ማለት ነው፤ በድምጽ ላይ ደግሞ ድምጽ መጨመሪያ እና መቀነሻ ሲሆን በቦታ ላይ "ይዘት" ይሆናል፤ ዐውዱ ይወስነዋል። ይህንን እሳቤ ይዘን ወደ አላህ እጆች ማየት እንችላለን፤ "የድ" يَد ማለት "አዪድ" أَيْيد ማለትም "ኃይል" በሚል መጥቷል፦
38፥45 ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ *የኅይል* እና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡ وَٱذْكُرْ عِبَٰدَنَآ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ أُو۟لِى ٱلْأَيْدِى وَٱلْأَبْصَٰرِ
38፥17 በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ *የኀይል* ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡ ٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلْأَيْدِ ۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
51፥47 ሰማይንም *በኀይል* ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ وَٱلسَّمَآءَ بَنَيْنَٰهَا بِأَيْي۟دٍۢ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ

"የድ" يَد የሚለው ቃል “ቀብል” قَبْل ማለትም "በፊት" የሚለውን ተክቶ ይመጣል ነው፦
3፥3 *”ከእርሱ በፊት”* ያሉትን የሚያረጋግጥ”* ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *”ከእርሱ በፊት”* ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ

"እጅ" የሚለው ቃል ልግስናን ለማመልከት መጥቷል፤ ለምሳሌ የእጅ መታሰር ስስትን መዘርጋት ለጋስነትን ለማመልከት መጥቷል፦
17፥29 *እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና*፡፡ وَلَا تَجْعَلْ يَدَكَ مَغْلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبْسُطْهَا كُلَّ الْبَسْطِ فَتَقْعُدَ مَلُومًا مَّحْسُورًا
5፥64 አይሁዶችም *የአላህ እጅ የታሰረች ናት» አሉ፡፡ እጆቻቸው ይታሰሩ ባሉትም ነገር ይረገሙ፡፡ አይደለም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው፡፡ እንደሚሻ ይለግሳል*፡፡ وَقَالَتِ الْيَهُودُ يَدُ اللَّهِ مَغْلُولَةٌ ۚ غُلَّتْ أَيْدِيهِمْ وَلُعِنُوا بِمَا قَالُوا ۘ بَلْ يَدَاهُ مَبْسُوطَتَانِ يُنفِقُ كَيْفَ يَشَاءُ

"እጅ" ሁሉን ተቆጣጣሪነት ያመለክታል፤ ሁሉ ነገር በእጁ ነው፤ መልካም ነገር፣ ንግሥና፣ ስልጣን፣ ግዛት፣ ችሮታ በእጁ ነው፦
3፥26 በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ *መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ* ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡» قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
67፥1 ያ *ንግሥና በእጁ የኾነው* አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
36፥1 ያ *የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የኾነው* ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ فَسُبْحَانَ الَّذِي بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُون
23፥88 *የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ* እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡ قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
57፥29 ይህም የመጽሐፉ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መኾናቸውን *ችሮታም በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል ማለትን እንዲያውቁ ነው፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው*፡፡ لِّئَلَّا يَعْلَمَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ أَلَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَىْءٍۢ مِّن فَضْلِ ٱللَّهِ ۙ وَأَنَّ ٱلْفَضْلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ ۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 14:51


እሩቅ ሳንሄድ "የእጁን አገኘ" ማለት የስራውን አገኘ ማለት ነው፤ ለዛ ነው "እጆቹ ያስቀደሙትን" የሚለን፦
78፥40 እኛ ሰው ሁሉ *እጆቹ ያስቀደሙትን* በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ إِنَّا أَنذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنتُ تُرَابًا
18፥57 በጌታውም አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ *እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር* ከረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِآيَاتِ رَبِّهِ فَأَعْرَضَ عَنْهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ ۚ إِنَّا جَعَلْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَن يَفْقَهُوهُ وَفِي آذَانِهِمْ وَقْرًا

ከላይ ለመንደርደሪያነት "የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ ነው" ብለን ነበር፤ "የድ" يَد የሚለው የአላህን ህላዌ ባህርይ ለማመልከት መጥቷል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

"የደይየ" ِيَدَىَّ ማለት ሙተና"dual" ነው፤ ይህንን ቃል "ብርታት" "ሃይል" "ችሎታ" ልግስና" ብለን እንዳንተረጎግም ቋንቋው አይፈቅድልንም፤ ምክንያቱም ሁለት "ብርታት" "ሃይል" "ችሎታ" ልግስና" የሚባል ቃላት ትርጉም አልባ ነው፤ ሁለቱ እጆቹ ታዲያ እንደ ሰው ሁለት እጅ ነውን? በፍጹም። ምክንያቱም የሰው ሁለት እጅ ቀኝና ግራ ናቸው፤ የአላህ ሁለት እጆች ግን ቀኝ ናቸው፦
ኢማም ሙስሊም 33, ሐዲስ 21
"ፍትኸኞች አላህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር-ረህማን በስ-ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፤ *ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው*። " ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻘْﺴِﻄِﻴﻦَ ﻋِﻨْﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻨَﺎﺑِﺮَ ﻣِﻦْ ﻧُﻮﺭٍ ﻋَﻦْ ﻳَﻤِﻴﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻭَﻛِﻠْﺘَﺎ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻤِﻴﻦٌ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﺪِﻟُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺣُﻜْﻤِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﻟُﻮﺍ "

የአላህ ዛት የራሱ ሲፋህ አለው ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ እና እጅ ግን ከፍጡራን ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ፣ መናገር እና እጅ ጋር አይመሳሰልም። ይህንን ለማስረዳት አንድ ናሙና ማየት ነው፤ ለምሳሌ አላህ "የሚመስለው ምንም ነገር የለም" አላህ ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው፦
42:11*"የሚመስለው" ምንም ነገር የለም፤ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ"* ነው። لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

አላህ "ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው እንደተባለ ሁሉ ሰውም "ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው ተብሏል፦
76:2 እኛ ሰዉን፥ በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ *"ሰሚ" "ተመልካችም"* አደረግነዉ። إِنَّا خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍۢ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَٰهُ سَمِيعًۢا بَصِيرًا

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 14:51


ነገር ግን አላህ "ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው የተባለው ሰው "ሰሚ" እና "ተመልካች" በተባለበት ሒሳብ እንዳልሆነ ሁሉ አላህ ሁለት እጆች አሉት ማለት ሰው ሁለት እጅ አለው በተባለበት ስሌትና ቀመር አይደለም። የሰው ሁለት እጆች ፍጥረታዊ ሲሆኑ የአላህ ሁለት እጆች ግን መለኮታዊ ናቸው። ምክንያቱም አላህን የሚመስለው ምንም ነገር ከሌለ ፍጥረታዊ ባህርያትን ከመለኮታዊ ባህርያት ጋር ማመሳሰል እራሱ በተውሒደል አስማ ወሲፋት ላይ ማሻረክ ነው። እኛ አላህ እንደ ኢየሱስ ፍጥረታዊ የሆነ የሰውነት እጆች የሉትም ብለን እናምናለን፤ ኢየሱስ ሰውነቱ ከመፈጠሩ በፊት እኮ የፈጠረው ፈጣሪው መለኮት ሆኖ ሳለ ሁለት እጆች አሉት፦
መዝሙር 119፥73 *እጆችህ* ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ። עג יָדֶיךָ עָשׂוּנִי, וַיְכוֹנְנוּנִי; הֲבִינֵנִי, וְאֶלְמְדָה מִצְו‍ֹתֶיךָ.

ታዲያ እነዚህ የፈጣሪ እጆች ምን አይነት ናቸው? መለኮታዊ ወይስ ፍጥረታዊ? ምነው አምላክ መንፈስ ነው ትሉ የለ እንዴ? መንፈስ አካላዊ እጆች ወይስ መንፈሳዊ እጆች ነው ያሉት? ፈጣሪ የስጋ ዓይን የለውም። ሰው እንደሚመለከተው አይመለከትም ካላችሁን እንግዲያውስ የአላህንም ባህርያት በዚህ ስሌት ተረዱት፦
ኢዮብ10፥4 *በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን? 
ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን?*


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

08 Nov, 13:20


አዲስ ቪድዮ You Tube ላይ ተለቋል። ግቡና ተመልከቱ።

https://youtu.be/8V1oc_J3U6U?si=FzPZKNYyNNjfwfYo

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 18:34


ግቡ ዒምራን ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 18:30


የአላህ ንግግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው? اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

አላህ "ሲፋቱል ከላም" صفات الكلام ማለትም "የመናገር ባህርይ" አለው፤ እምላካችን አላህ "ሙተከለም" مُتَكَلِّم ማለትም "ተናጋሪ"speaker" ነው፤ የራሱ "ከላም" كَلَٰم ማለትም "ንግግር"speech" የራሱ ባህርይ ነው፤ "ከላም" ሁለት ይዘት ያቅፋል፤ አንዱ "ሐርፍ" حَرْف ማለትም "ሆሄ" ሲሆን ሌላው "ሰውት" صَوْت ማለትም "ድምፅ" ነው፤ የአላህ ንግግር ወደ ነብያችን"ﷺ" የተወረደ ሆሄሃት ናቸው፦
11፥1 *አሊፍ ላም ራ*፤ ይህ አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ *መጽሐፍ* ነው፡፡ *ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው*፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
13፥1 አሊፍ ላም ሚም ራ ይህች ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ المر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ ۗ وَالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ الْحَقُّ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 45, ሐዲስ 3158
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥኡድ ሲናገር እደሰማሁት የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ ማንም ከአላህ መጽሐፍ አንዲት ሐርፍ የቀራእ አንዱን ሐሠናህ በአስር ሐሠናት ይቀበላል፤ አሊፍ፣ ላም፣ ሚም አንድ ሐርፍ ነው አላልኩኝም፤ ነገር ግን አሊፍ አንድ ሐርፍ ነው፤ ላም አንድ ሐርፍ ነው፤ ሚም አንድ ሐርፍ ነው። قَالَ سَمِعْتُ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ مَسْعُودٍ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ قَرَأَ حَرْفًا مِنْ كِتَابِ اللَّهِ فَلَهُ بِهِ حَسَنَةٌ وَالْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا لاَ أَقُولُ الم حَرْفٌ وَلَكِنْ أَلِفٌ حَرْفٌ وَلاَمٌ حَرْفٌ وَمِيمٌ حَرْفٌ ‏"‏

እስቲ ይህንን አንዳንድ ማሳያዎች ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ቁርኣን"
ለምሳሌ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው፦
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር* ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይሰማ ዘንድ" ተብሎ የተቀመጠው የአላህን ንግግር ቁርኣን ነው፤ ቁርኣን አላህ በጂብሪል በነብያችን"ﷺ" ላይ ያነበባላቸው የራሱ ንግግር ነው፦
45፥6 እነዚህ በአንተ ላይ በእውነት *የምናነባቸው* ሲኾኑ *የአላህ ማስረጃዎች* ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ *በየትኛው ንግግር* ያምናሉ? تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَ اللَّهِ وَآيَاتِهِ يُؤْمِنُونَ

አምላካችን አላህ ለነብያችን"ﷺ" "ቁል" قُلْ ማለትም "በል" በሚል ትእዛዛዊ ግስ እውነትን ይናገራል፤ "አላህ እውነትን ተናገረ" የሚለው ይሰመርበት፤ ይህም እውነት ከአላህ ወደ ነብያችን"ﷺ" የወረደው ነው፦
3፥95 *አላህ እውነትን ተናገረ*፡፡ የኢብራሂምንም መንገድ ወደ እውነት ያዘነበለ ሲኾን ተከተሉ፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» *በላቸው*፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
78፥48 *ጌታዬ እውነትን ያወርዳል*፡፡ ሩቅ የኾኑትን ምስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّ رَبِّي يَقْذِفُ بِالْحَقِّ عَلَّامُ الْغُيُوبِ
3፥60 *ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው*፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 18:30


ነጥብ ሁለት
"ሲፈቱል ከላም"
ይህንን ካየን ዘንዳ ስለ አላህ ንግግር እሳቤ በሙላት ባይሆንም በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል እናያለን፤ በንግግር ከአላህ የበለጠ እውነተኛ ማን ነው? ማንም የለም፤ አላህ በእውነት ይናገራል፦
4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ *በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?* اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም፤ በትንሳኤ ቀንም ሁሉን ይሰበስባል፤ እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በእርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም፡፡ አላህም በትንሣኤ ቀን አያናግራቸውም፦
2፥174 እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በእርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም፡፡ *አላህም በትንሣኤ ቀን አያናግራቸውም*፤ ከኃጢኣት አያጠራቸውምም፡፡ ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنزَلَ اللَّهُ مِنَ الْكِتَابِ وَيَشْتَرُونَ بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۙ أُولَـٰئِكَ مَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ إِلَّا النَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

"አያናግራቸውም" ለሚለው ቃል የገባው "ላ ቱከለሙሁም" َلَا يُكَلِّمُهُمُ ሲሆን "ላ" َلَا የሚለው አፍራሽ ቃል ሲወጣ "ያናግራቸዋል" ቱከለሙሁም" يُكَلِّمُهُمُ የሚል ቃል ይመጣል፤ አላህ አማንያንን ሲያናግር ከሃድያንን ግን አያናግራቸውም፤ ነገር ግን በተቃራኒው አላህ ከሃድያንን አፋቸውን ያትምና እጆቻቸው፣ እግሮቻቸው፣ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸው እና ቆዳዎቻቸውም እንዲናገሩ ያደርጋል፤ አላህም ያናግራቸዋል፦
36፥65 ዛሬ *በአፎቻቸው ላይ እናትም እና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ*፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ
40፥20 በመጧትም ጊዜ *ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸው እና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
40፥21 *ለቆዳዎቻቸውም* «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» *ይላሉ*፡፡ «ያ አንዳቹን ነገር ሁሉ *ያናገረው አላህ አናገረን*፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ጊዜ ፈጠራችሁ፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ» *ይሏቸዋል*፡፡ وَقَالُوا لِجُلُودِهِمْ لِمَ شَهِدتُّمْ عَلَيْنَا ۖ قَالُوا أَنطَقَنَا اللَّهُ الَّذِي أَنطَقَ كُلَّ شَيْءٍ وَهُوَ خَلَقَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

እጆቻቸው "ያነጋግሩናል" ለሚለው ቃል የመጣው "ቱከለሙና" تُكَلِّمُنَا ሲሆን እንግዲህ “መኻሪጁል ሑሩፍ” مخارج الحروف ማለት “የፊደላት መውጫዎች” ሳይኖሩ እጆቻቸው ይናገራሉ፤ መሃሪጀል ሁሩፍ በሥስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላሉ፣ እነርሱም፦
1ኛ. “ኸልቅያ” الحلقية የሚባሉት ሃርፎች የጉሮሮ ክፍል”the throat Letters”
2ኛ. “ሊሳንያ” السان የሚባሉት ሃርፎች የምላስና ትናግ ክፍል”the tongue Letters”
3ኛ. “ሰፈውያ” الشفتان የሚባሉት ሃርፎች የከንፈር ክፍል”the Lip Letters” 4 ናቸው።

አንድ ማንነት ወይም ምንነት ለመናገር “የፊደላት መውጫዎች” ሸርጥ ነው ብሎ የሚፈላሰፍ እነዚህ አንቀጾች ውድቅ ያደርጉታል፤ የትንሳኤ ቀን እጅ፣ እግር፣ ቆዳ ወዘተ ያለ "መኻሪጅ" مخارج መናገራቸው እንዴት እንደሆነ “ገይብ” غَيْب ከሆነ አላህ እንዴት እንደሚናገርም ገይብ ነው፤ አላህ ያውቃል፣ ያያል እና ይሰማል ሲባል እንደ ፍጡር ለማወቅ አንጎል፣ ለማየት ሌንስ፣ ለመስማት ሃመር ብላችሁ ከፍጡር ጋር እንደማታመሳስሉት ሁሉ ለመናገሩም እንደ ፍጡር ጉሮሮ ብላችሁ አትፈላሰፉ፤ እርሱ ማንንም ፍጡር አይመስልም። ፍጡር ጋር የሚታወቅ ክስተት ሳይኖር ዕውቀት፣ የሚታይ ነገር ሳይኖር ማየት፣ የሚንኮሻኮች ነገር ሳይኖር መስማት፣ ትናጋ ሳይኖር መናገር የለም፤ መንስኤ እና ውጤት ለፍጡር አይነጣጠሉም፤ ያለ ውጤት መንስኤ የለም። ነገር ግን የአላህ ዕውቀት፣ ማየት፣ መስማት እና መናገር ያለ ውጤት የህላዌ ባህርያት ናቸው።

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 18:30


የአላህ ንግግር እንደ ፍጡራን ንግግር አያልቅም፤ ለምሳሌ እኔ አሁን የምናገረው የእኔ ንግርር ትላንት አልነበረም ነገ አይኖርም፤ እኔ መጀመሪያ ስላለኝ ጅማሬ አለው፤ ፍጻሜ ስላለኝ መጨረሻ አለው፤ የአላህ ንግግር ግን ባሕሩ ሁሉ ቀለም በጥብጠው እና ዛፉ ሁሉ ቅጠል ዳምጠው ቢጽፉት የአላህ ንግግር አያልቅም፦
18፥109 *«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት መጻፊያ ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር*» በላቸው፡፡ قُل لَّوْ كَانَ الْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَاتِ رَبِّي لَنَفِدَ الْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَاتُ رَبِّي وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِ مَدَدًا
31፥27 *ከዛፍም በምድር ያለው ሁሉ ብእሮች ቢሆኑ ኖሮ ባሕሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር*፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَلَوْ أَنَّمَا فِي الْأَرْضِ مِن شَجَرَةٍ أَقْلَامٌ وَالْبَحْرُ يَمُدُّهُ مِن بَعْدِهِ سَبْعَةُ أَبْحُرٍ مَّا نَفِدَتْ كَلِمَاتُ اللَّهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

ነጥብ ሦስት
“ወሕይ”
ይህ የአላህ ንግግር የአላህ ዕውቀት ነው፤ ይህ ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ተከትቧል፤ ከዚህ ሰሌዳ ላይ ጊዜው ሲደርስ በሦስት አይነት መንገድ ንግግሩን ያወርደዋል፦
“ሩዕያ”
አንደኛ መንገድ በሩዕያ ማናገር ነው፤ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ በሪዕይ ውስጥ ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ሪዕይ” رِءْي ማለት “እይታ” ማለት ሲሆን እውን ላይ ሆኖ ሳይተኛ በሰመመን ወይም በተመስጦ”contemplation” ላይ ሆነው ሲሆን ነው፤ የራዕይ አንዱ ገፅታ “መናም” مَنَام ማለት “ህልም” ሲሆን ይህም በነውም ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ነውም” نَوْم ማለት “እንቅልፍ” ማለት ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል የኢማን አባት የሆነው ኢብራሂም”አ.ሰ.” ነው።

“ተክሊም”
ሁለተኛ መንገድ በተክሊም ማናገር ነው፤ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይና ህልም ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆና የሚያናግርበት መንገድ ነው፤ በዚህ መልኩ አላህ ያናገረው ነብይ ለናሙና ያክል ሙሳ”አ.ሰ.” ተጠቃሽ ነው።

“ረሱል”
ሶስተኛ መንገድ በመልአክ ማናገር ነው፤ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል”አ.ሰ.” ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል ነብያችን”ﷺ” ናቸው፦
42:51/ለሰው” አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ ሰው የተባለው ነቢይነት የተሰጠው ነብይ ነው፦
3:79 *ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን “ነቢይነትንም” ሊሰጠዉና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም*፤ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ ٱللَّهُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا۟ عِبَادًۭا لِّى مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن كُونُوا۟ رَبَّٰنِيِّـۧنَ بِمَا كُنتُمْ تُعَلِّمُونَ ٱلْكِتَٰبَ وَبِمَا كُنتُمْ تَدْرُسُونَ

ለናሙና ያክል የሙሳ”አ.ሰ.” እንይ፤ አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት «ሙሳ ሆይ» በማለት ጠርቶታል፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት *”ተጠራ*፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ

ይህንን ጥሪ ጠርቶ ያነጋገረው እራሱ እንደሆነ በመጀመሪያ መደብ ለነብያችን”ﷺ”፦ “ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው” በማለት ሙሴን የጠራው እርሱ እንደሆነ ይናገራል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ *ሙሳንም አውሳ*፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًۭا وَكَانَ رَسُولًۭا نَّبِيًّۭا
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም *ጠራነው፤ ያነጋገርነውም* ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

አላህ ሙሳን፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት “የሚወረድልህንም አዳምጥ” ብሎታል፤ ይህ የሚያሳየው የሚወርደው ንግግር መነሻ የሌለው መዳረሻ የሌለው የአላህ ንግግር ነው፦
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ *”የሚወረድልህንም”* አዳምጥ፡፡ وَأَنَا ٱخْتَرْتُكَ فَٱسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰٓ

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 18:30


ነጥብ አራት
“የትንሳኤ ቀን”
የአላህ ንግግር ከፍጡራን ጋር በማይመሳሰል የራሱ “ሰውት” صَوْت ማለትም “ድምፅ” አለው፤ አላህ አማንያንን በትንሳኤ ቀን ያለምንም መካከለኛ ጣልቃ ገብነት በድምጽ ያናግራል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 97, ሐዲስ 69
ዐዲይ ኢብኑ ኻቲም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ከእናንተ መካከል አንድም የለም ጌታው የሚያናግረው ቢሆን እንጂ፤ በጌታውና በእርሱ መካከል ተርጓሚ(መካከለኛ) አሊያም የሚጋርድ ግርዶሽ የለም። حَدَّثَنَا يُوسُفُ بْنُ مُوسَى، حَدَّثَنَا أَبُو أُسَامَةَ، حَدَّثَنِي الأَعْمَشُ، عَنْ خَيْثَمَةَ، عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ سَيُكَلِّمُهُ رَبُّهُ، لَيْسَ بَيْنَهُ وَبَيْنَهُ تُرْجُمَانٌ وَلاَ حِجَابٌ يَحْجُبُهُ ‏”‌‏.‏
ሰሒሁል አንባኒህ መጽሐፍ 7 ሐዲስ 757
ዐብደላህ ኢብኑ አኒሥ እንደተረከው ነብዩ”ﷺ” አሉ፦ ሰዎች በትንሳኤ ቀን እርቃናቸውን፣ ያልተጫሙና ምንም ነገር የሌላቸው ሆነው ይቀስቀሳሉ። አላህ በድምጽ ይጠራቸዋል፤ ልክ ከቅርበት ርቀት እንደሚስሙት ሆኖ ይስሙታል። ፦ “እኔ ንጉስ ነኝ፤ እኔ የስራችሁን ውጤት ከፋይ ነኝ” ይላል። وعن عبد الله بن أنيس عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه قال : (يُحْشَرُ النَّاسُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عُرَاةً حُفَاةً بُهْمًا فَيُنَادِيهِمْ بِصَوْتٍ يَسْمَعُهُ مِنْ بُعْدٍ كَمَا يَسْمَعُهُ مِنْ قُرْبٍ : أَنَا الْمَلِكُ، أَنَا الدَّيَّانُ) أخرجه أحمد ، وصححه الألباني في ” الصحيحة ”

በተቃራኒው ከሃድያንን ግን አያናግራቸው፤ ከዛ ይልቅ ፦”ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም” ይላቸዋል፤ ለእነዚያ ለካዱት ከእርሱ ንግግር አይፈቀድላቸውም፦
23፥108 አላህም «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ *አታናግሩኝም*» ይላቸዋል፡፡ قَالَ ٱخْسَـُٔوا۟ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ
16:84 ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ፤ ከዚያም *ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸውም*፤ እነሱም በወቀሳ አይታለፉም። وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍۢ شَهِيدًۭا ثُمَّ لَا يُؤْذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ

አላህ በትንሳኤ ቀን ከሚያናግራቸው ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 17:58


Maqaan #Yesuus jedhu uumama dha.

بسم الله الرحمن الرحيم

Jalqaba wanti nuti hubachuu qabnu, maqaan uumamaa maqaa Waaqayyoof tajaajiluu hin dandeenye akkasumas maqaan Waaqayyo uumamaaf akka hin tajaajilleedha.

Kana irraa kaanee maqaan Yesuus uumama moo miti kan jedhu ni ilaalla.

Maqaan Yesuus jedhu; bara kitaaba kakuu moofaa keessatti nama baay'eef ooleera. Namni uumama.

#1. “Ilma Naawe Iyyaasuu”
👉 Seera Lakkoobsaa 11:28
"Kana irratti Iyaasuun ilmi Nun inni ijoollummaa isaatii jalqabee gargaartuu Musee ture, "Yaa Musee gooftaa ko! Jara kana dhowwi!" jedheen."

Ati maal taate, kun #Iyyaasuu jedha jechuun Keessan hin oolu.

Maqaan #Yesuus jedhu kun maqaa uumama akka hin taane gochuuf baay'ee itti dhama'ani. Bakka #Iyyesuus jedhu hunda #Iyyaasuu jechuun jijjiiranii bakka buusani. Kan afaan #Gee'izii #Yesuus jedha malee #Iyyaasuu hin jedhu. 👇

ዘኍልቍ 11፥28 ወይቤሎ #ኢየሱስ ዘነዌ ዘይቀውም ቅድሜሁ ለሙሴ ዘውእቱ ኅሩዩ ይቤሎ #እግዚእየ ሙሴ ክልኦሙ ።
#Hiikkaan፦
“ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ #ኢየሱስ፦ #ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።”
"Kana irratti Iyyesuus ilmi Nawe inni ijoollummaa isaatii jalqabee gargaartuu Musee ture, "Yaa Musee gooftaa ko! Jara kana dhowwi!" jedheen."

Akkuma argitan; maaliif isa Iyyaasuu jedhu gara Yesuusitti jijjiirani kan jedhuuf deebiin sammuu keessaniif haa taa’u!
Dhugaa jiru adda baasuuf link armaan gadiin lakk 28 irraa hubachuu dandeessu. 👇
https://www.tau.ac.il/~hacohen/Octateuch/Numeri%2011.html

Kanaafuu maqaan Yesuus maqaa uumamaa ta'uu kan ittiin adda baasnu keyyata kana jechuudha.

Mee itti aansuun kakuu moofaa keessatti waan argine kana akkuma jirutti qabannee, gara kakuu haaraa haa dhufnu. Akkuma kana maqaan Iyyaasuu jedhu gara Yesuus akka jijjiirame hubanna. Ammas Ilma Naawee kan ta'e Yesuus gara Iyyaasuutti jijjiirame. 👇

"Abbooni keenya warri isaan booddees godicha fudhatanii, Iyaasuudhaa wajjin biyya saba warra Waaqayyo isaan duraa oofee baaseetti galan; godichis hamma bara Daawititti isaan gidduu ture." (Hojii Ergamootaa 7:45)

Afaan Amaaraatiin Iyyaasuu jedhanii dhoksuuf yaalanis, Afaan ingiliffaa irratti #Jesus jechuun ifaan ifatti kaa’eera.
👉 Acts (KJV) 7:45
"Which also our fathers that came after brought in with #Jesus into the possession of the Gentiles, whom God drave out before the face of our fathers, unto the days of David;

Ammas dabalataanis 👇
Ibroota 4:8
#Iyaasuun iddoo boqonnaa sanatti utuu isaan galcheera ta'ee, Waaqayyo ergasii waa'ee guyyaa kan biraa hin dubbatu ture."

Hebrews 4:8 (KJV) -
"For if #Jesus had given them rest, then would he not afterward have spoken of another day."

Egaa; akka itti jachi Yesuus jedhu gara Iyyaasuutti jijjiirame sirriitti hubachuu dandeessu.

Namni #Yusxos jedhamu maqaan isaa #Yesuus akka ta'e dabalataanis haa ilaallu.
ኢዮስጦስ ኢየሱስ”

Qolasiyaas:- 4:10-11.
"Arisxaarkos inni anaa wajjin hidhamee jiru nagaa isiniif in dhaama. Maarqos inni durbiin Baarnaabaas akkasuma nagaa isiniif in dhaama. Waa'ee Maarqos kanaan dura dhaamsi isin ga'eera; inni gara keessan yommuu dhufu simadhaa! #Yoshu'aan inni Yusxos jedhamus nagaa isiniif in erga; warra seera dhagna-qabaa eegan keessaa isaan kana kophaatu mootummaa Waaqayyootiif anaa wajjin hojjeta; isaan immoo guddaa na jajjabeessan."

Colasians:- 4:10-11. (KJV)
"Aristarchus my fellowprisoner saluteth you, and Marcus, sister's son to Barnabas, (touching whom ye received commandments: if he come unto you, receive him;) And #Jesus, which is called Justus, who are of the circumcision. These only are my fellow workers unto the kingdom of God, which have been a comfort unto me."

Wanti baay'ee na dhibu, Yesuusiif maqaa kan moggaase Maleeykaa dha. Maleeykaan uumama.
👉 Luqaas 2:21
"Guyyaan saddeettaffaan erga darbee mucicha dhagna qabuun in ga'e; akkuma ergamaan Waaqayyoo utuu isheen hin ulfaa'in dura, haadha isaatti #himee turetti maqaa isaa #Yesus" jedhan."

Yesuus Waaqayyo yoo ta'e, maqaa uumama garaa garaatu itti moggaase jechuudha. Kana jechuun #Abbaan_koo isa #booda_koo dhalatuuf #ani maqaa itti moggaasuu jechuudha.

የሰለምቴዎች ቻናል

07 Nov, 17:58


Nama dhugaa barbaaduuf ragaan xiqqoon gahaadha. Maqaan Yesuus jedhu uumama. Maqaan uumamaa immoo Waaqayyoof hin fayyadamamu. Maqaa Yesuus jedhu kan moggaase uumama. Uumamni Uumaaf maqaa hin moggaasu. Kanaafuu Yesuus maqaa isaa irraa ka'ee uumama akka ta'e hubanna.

Yesuus uumama ta'ee osoo jiruu, Waaqayyoodha jedhanii gabbaruun karaa #jennataa namatti cufuun, #jaannama nama geessa.

لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ ٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُۥ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًاۗ وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَاۚ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
"Warri “Rabbiin isumatu Masiih ilma Maryami” jedhan dhugumatti kafaraniiru. Jedhi: "sila yoo Inni Masiih ilma Maryam, haadha isaatiifi namoota dachii irra jiran hunda balleesuu fedhe eenyutu Rabbi irraa isin tiksa?" Mootummaan samii, dachiifi wantoota gidduu isaan lamaanii jiran hundaatuu kan Rabbiiti. Waan fedhe uuma. Rabbiin waan hunda irratti danda’aadha." [5:17]

Rabbiin qajeeluma isaaniif haa kennu! Nuuf immoo Obsa gaarii haa kennu!

https://t.me/Know_to_Islamic

የሰለምቴዎች ቻናል

23 Oct, 00:08


ሱረቱል ዋቂዓ📖🎧
فَأَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ

የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡

◍ ወንድም ቶፊቅ

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 23:43


የፕሮቴስታንት ሊቅ አስተማሪ ተብሎ የሚታወቀው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ስለ ኡሥታዝ ወሒድ የሰጡት ምስክርነት

አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው መምህራችን።

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 23:11


「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┄┈┈⟢
│❏ አል ቀዋዒዱል ሒሳን القواعد الحِسان

│አል ሙተዐሊቀቲ ቢተፍሲሪል ቁርኣን
╰─────────────────╯    
🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
🎧 ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
╰──────────────
╭⧿⧿⛉
├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ
│ይጠቀሙ!

┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ
│ተቋዳሽ ይሁኑ!
╰───────────
╭╼──────────────
┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

🖇 t.me/SheikhMuhammedZainadam
╰╼───────────────────────╯

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:29


◆▮ውይይት▮◆

"የኢየሱስ ስም ወሎ ነው"እየሱስ እጃችሁን ሳትታጠቡ ብሉ ይላል? ኢየሱስ እጁን ሳይታጠብ በላ ? "


◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም አቡ ሳለህ
         🅥🅢
◍ወገናችን ኪንግ
◍ወገናችን ኢስጢፍኖስ
ሌሎችም  ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


መደምደሚያ
አላህ ሰዎች ሳያውቁ በሚሰሩት መጥፎ ሥራ አይጠይቃቸውም፤ የራሱን መልእክተኛ እስከሚልክ ድረስ ማንንም ያለ ፍትሕ አይቀጣም፦
33:5 *በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ሐጢያት የለባችሁም፤ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ሐጢያት አለባችሁ* አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا
17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًۭا

ከመልክተኞቹ መላክ በኋላ ሰዎች አልሰማንም ብለው በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎች እና አስጠንቃቂዎች የኾኑን መልክተኞች ልኳል፦
4፥165 *ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎች እና አስጠንቃቂዎች የኾኑን መልክተኞች ላክን*፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ رُّسُلًا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى اللَّهِ حُجَّةٌ بَعْدَ الرُّسُلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

አላህ ባለማወቅ ለሠራነው መጥፎ ሥራ በዱንያ ተውበት ማድረግ ነው፤ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፦
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥54 እነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ *እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ አላህ መሓሪ አዛኝ ነው»* በላቸው፡፡ وَإِذَا جَاءَكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِنَا فَقُلْ سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۖ كَتَبَ رَبُّكُمْ عَلَىٰ نَفْسِهِ الرَّحْمَةَ ۖ أَنَّهُ مَنْ عَمِلَ مِنكُمْ سُوءًا بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابَ مِن بَعْدِهِ وَأَصْلَحَ فَأَنَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

እንግዲህ ኢሕሳን የዲን ሦስተኛው ደረጃ ሲሆን መልካም ሥራ በኢማንና በተውሒድ ከተሰራ አላህ "ሙሒሢን" የሚላቸው ባሮቹ እንሆናለን፦
2፥195 በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም እራሳችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ *በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና*፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

አላህ ሙሕሢኒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


ነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
27፥11 «ግን *የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ አዛኝ ነኝ*፡፡ إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًا بَعْدَ سُوءٍ فَإِنِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
4፥40 *አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ መልካም ሥራ ብትኾንም ይደራርባታል፡፡ ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ ۖ وَإِن تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِن لَّدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا
29፥7 *እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነሱ ላይ እናብስላቸዋለን፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን*፡፡وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَحْسَنَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ
6፥160 *በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ነገር ግን "ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" ይዘው በሚሠሩት መጥፎ ሥራ ተውበት ካላደረጉ ብጤዋን እንጅ አይመነዱም፤ በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፤ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፤ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፦
27፥90 *በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም?»* ይባላሉ፡፡ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥4 *ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን?* ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ፡፡ أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ أَن يَسْبِقُونَا ۚ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ
28፥84 *በደግ ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው፡፡ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም*፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ خَيْرٌ مِّنْهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَى الَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ إِلَّا مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
74፥38 *ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት*፡፡ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَة

ለአማንያን ሥራዎቻቸው የሚመዘንበት ሚዛን ያላቸው ለዛ ነው፤ ከሃድያን ግን የጀነት ስላልሆኑ ሥራዎቻቸው የሚመዘንበት ሚዛን የላቸውም። አማንያን "ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" በመያዛቸው በሠሩት መጥፎ ሥራ ልክ ተቀጥተው የጀነት ናቸው፤ ከሃድያን ደግሞ በመካዳቸው ጀሃነም ሲዘወትሩ በሚሠሩት መጥፎ ሥራ እንደሥራቸው ያገኛሉ፦
41፥27 *እነዚያንም የካዱትን ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡ የእዚያነም ይሠሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን*፡፡ فَلَنُذِيقَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا عَذَابًا شَدِيدًا وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَسْوَأَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


መልካምና መጥፎ ሥራ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥39 *ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም*፡፡ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

ነጥብ ሁለት
"አኺራህ"
"አኺራህ" آخِرة ማለት "መጨረሻይቱ" ማለት ሲሆን የሚቀጥለውን ዓለም ያመለክታል፤ አምላካችን አላህ በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን ያቆማል፤ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፤ ሥራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም አላህ ያመጣዋል፦
21፥47 *በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ ሥራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን*፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ፡፡ وَنَضَعُ الْمَوَازِينَ الْقِسْطَ لِيَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا ۖ وَإِن كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا ۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَاسِبِينَ

እነዚያም ያመኑት መልካም ሥራዎችንም የሠሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ይገባሉ፤ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው፦
22፥56 በዚያ ቀን ንግሥናው የአላህ ብቻ ነው፡፡ በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ *እነዚያም ያመኑት መልካም ሥራዎችንም የሠሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው*፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ
12፥57 *የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው*፡፡ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ

አማንያን በዚያ ቀን ለሁሉም ከሠሩት መልካም ሥራ የተለያየ የምንዳ ደረጃዎች አሏቸው፦
46፥19 *ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አሏቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው እነርሱም አይበደሉም*፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
6፥132 *ለሁሉም ከሠሩት ሥራ የተበላለጡ ደረጃዎች አሏቸው*፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ

"መልካም ሥራ" ሁሉ አምልኮ ነው፤ “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው።
“ኢማን” إِيمَٰن ማለት “እምነት” ሲሆን ያለ ኢማን ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
“ኢኽላስ” إخلاص ማለት ደግሞ ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ሲሆን ያለ ኢኽላስ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
ሦስተኛው “ኢቲባዕ” إتباع ነው፤ “ኢቲባዕ” የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ቁርኣንና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ሑክም ማምለክ ነው፤ ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።

የከሃድያን መልካም ሥራ ያለ እነዚህ ሦስት መስፈርት በዲንያ የሚያከትም ሲሆን በትንሣኤ ቀን መልካም ሥራቸው የሚመዘንበት ሚዛንን አይቆምላቸውም፤ ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፤ አይጠቅማቸውም፦
18፥104 *እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው*፡፡ الَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا
18፥105 *እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ማስረጃዎችና በመገናኘቱ የካዱት ናቸው፡፡ ሥራዎቻቸውም ተበላሹ፡፡ ለእነሱም በትንሣኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸውም*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ وَلِقَائِهِ فَحَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فَلَا نُقِيمُ لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَزْنًا
11፥16 *እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ፤ ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ

የእነርሱ መልካም ሥራ ያለ እምነት ስለሆነ በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህ የተበተነ ትቢያም ያደርገዋል፤ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፦
24፥39 *እነዚያም የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው*፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِندَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
25፥23 *ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን*፡፡ وَقَدِمْنَا إِلَىٰ مَا عَمِلُوا مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَاهُ هَبَاءً مَّنثُورًا
14፥18 *የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ምሳሌ መልካም ሥራዎቻቸው በነፋሻ ቀን ነፋስ በእርሱ እንደ በረታችበት አመድ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው*፡፡ مَّثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ أَعْمَالُهُمْ كَرَمَادٍ اشْتَدَّتْ بِهِ الرِّيحُ فِي يَوْمٍ عَاصِفٍ ۖ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ

"ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ማለትም "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ ጣዖታትን ውድቅ አድርጎ እና አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት ያመለከ ሰው ለሠራው መጥፎ ሥራ ተውበት ከገባ አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጥለታል፤ ተጸጽቶ በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ ይደራረብለታል፦
25፥70 *ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእ

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 18:49


መልካምና መጥፎ ሥራ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥39 *ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም*፡፡ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

መግቢያ
በኢስላም “ነገረ-ደህንነት”Soteriology” እራሱን የቻለ ትልቅ ነጥብ ሲሆን “ፈላህ” فلاح ይባላል፤ አምላካችን አላህ አንድ ሰው ከጀሃነም ለመዳን ከፈለገ አራት መስፈርቶችን አስቀምጦልናል፤ እነርሱም፦ 1ኛ “ተውበት” تَوْبَة ማለትም “ንስሃ” 2ኛ “ኢማን” إِيمَٰن ማለትም “እምነት” 3ኛ “ዐሚሉስ ሷሊሐት” عَمِلُوا الصَّالِحَات ማለትም “መልካም ስራ” 4ኛ “ኢስቲቃማ” استقامة ሰው በንስሃ ቃል በገባበት፣ ባመነበትና በሚሰራው መልካም ስራ “መፅናት” ናቸው።

ዲን የፈላህ ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና ነው፤ “ዲን” دِين ማለት ደግሞ “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርህ” ማለት ነው፤ “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፦ “ኢሥላም” إِسْلَٰم ፣ “ኢማን” إِيمَٰن እና “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው፤ “ኢሥላም” ማለት “አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ” ሲሆን “ኢማን” ማለት ግን “እምነት” ማለት ነው፤ “ኢሕሣን” ማለት “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፤ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው።

“ኢሕሣን” إِحْسَٰن ማለት ቋንቋዊ ፍቺው “መዋብ” “ማማር” “መልካም” “በጎ” “ጥሩ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “መልካም” “ውብ” ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “የተዋበ” “መልካም” “ያማረ” ማለት ነው፤ አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ሲባል፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ሲባል፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይባላል፤ “ሙሕሢን” مُحْسِن ማለት “ጥሩ ሠሪዎች” “መልካም ሠሪዎች” “በጎ ሠሪዎች” ማለት ነው፤ የዲን መዋቢያውና ማሳመሪያው “መልካም ሥራ” ነው፤ አንድ ሥራ መልካም ወይም መጥፎ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ነፍስያህ ለእኛ መልካም የሆነን ነገር ትጠላለች መጥፎ የሆነን ነገር ትወዳለች፤ የሚሻለውን ነገር አላህ ያውቃል እኛ ዐናውቅም፤ ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ፤ መጥፎንም ነገር ይለምናል፦
2፥126 *አንዳች ነገርን እርሱ ለእናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለእናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም የሚሻላችሁን ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም*፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
17፥11 *ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ፤ መጥፎንም ነገር ይለምናል፡፡ ሰውም ቸኳላ ነው*፡፡ وَيَدْعُ الْإِنسَانُ بِالشَّرِّ دُعَاءَهُ بِالْخَيْرِ ۖ وَكَانَ الْإِنسَانُ عَجُولًا

ለምሳሌ አንድ ሰው ቢገድል ያ ገዳዩ መገደሉ ፍትሕ ቢሆንም ለሰው የተጠላ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ መሆኗ ፍትሕ ነው፦
42፥40 *የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም*፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

የሥነ-ምግባር መርህ ላይ፦ “ይህ ነገር እኩይ ነው፤ ይህ ነገር ሰናይ ነው” ማለት የሚችለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፤ ያ ካልሆነ ነፍስ ሁሉ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

አላህ በነቢያቱ መልካም ነገር ያዛል፤ በተቃራኒው ሸይጧን በውስዋስ መጥፎ ነገር ያዛል፦
7፥28 መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ *«አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም*፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡ وَإِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً قَالُوا وَجَدْنَا عَلَيْهَا آبَاءَنَا وَاللَّهُ أَمَرَنَا بِهَا ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ ۖ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
23፥51 እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ *በጎ ሥራንም ሥሩ፤ እኔ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ*፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
2፥268 *ሰይጣን እንዳትለግሱ ድኽነትን ያስፈራራችኋል፡፡ በመጥፎም ያዛችኋል*፡፡ الشَّيْطَانُ يَعِدُكُمُ الْفَقْرَ وَيَأْمُرُكُم بِالْفَحْشَاءِ
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ

እዚህ ድረስ ከተግባባን መልካም ሥራ እና መጥፎ ሥራ በዱንያ ሆነ በአኺራህ የሚኖረውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ምንዳ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እንመለከታለን፦

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 18:49


ነጥብ አንድ
“ዱንያ”
“ዱንያ” دُّنْيَا ማለት “ቅርቢቱ” ማለት ሲሆን የምንኖርበት ይህንን ዓለም ያመለክታል፤ አምላካችን አላህ የትኛችን ሥራችን ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊፈትነንና ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትመነዳ ዘንድ ሞትንና ሕይወትን በዱንያ የፈጠረ ነው፦
67፥2 *ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ
45፥22 አላህም ሰማያትንና ምድርን ለችሎታው እንደሚያመለክትባቸውና *ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳ ዘንድ በትክክል ፈጠረ፡፡ እነርሱም አይበደሉም*፡፡ وَخَلَقَ اللَّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَلِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

አንድ አማኝ በእምነት የሚሰራው መልካም ሥራ አላህ በዱንያ መልካም ኑሮን ይመነዳዋል፤ መልካምም ያደርግለታል፦
16፥97 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን*፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
28፥77 «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ *ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ*፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» አሉት፡፡ وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ
3፥145 ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢኾን እንጅ ልትሞት አይገባትም፡፡ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ *የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፡፡ የመጨረሻይቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን*፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا ۗ وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ الْآخِرَةِ نُؤْتِهِ مِنْهَا ۚ وَسَنَجْزِي الشَّاكِرِينَ
16፥30 ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ *ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው*፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር! وَقِيلَ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا مَاذَا أَنزَلَ رَبُّكُمْ ۚ قَالُوا خَيْرًا ۗ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَـٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۚ وَلَدَارُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ ۚ وَلَنِعْمَ دَارُ الْمُتَّقِينَ
39፥10 «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለእነዚያ *በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው*፡፡ قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَـٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

በተመሳሳይ አንድ ካሃዲ ያለ እምነት የሚሰራው መልካም ሥራ አላህ በዱንያ ይሞላለታል፤ ምክንያቱም የመልካም ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ አይደለም፤ የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፦
11፥15 *ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም*። مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَٰلَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ
55፥60 *የመልካም ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?* هَلْ جَزَاءُ الْإِحْسَانِ إِلَّا الْإِحْسَانُ
99፥7 *የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ አማኝም ይሁን ከሃዲ በዱንያ ያገኘዋል፦
99፥8 *የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

ነገር ግን ሁልጊዜ አማኝ በሚሰራው መልካም ሥራ በዱንያ አሊያም ከሃዲ በሚሰራው መጥፎ ሥራ በዱንያ ያገኛል ማለት ላይሆን ይችላል፤ ፍትሕ የሚዳኝበት እውነተኛ ምንዳ በመጨረሻይቱ ዓለም ነው። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ አኺራህ እንቀጥላልን……..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 17:59


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 08:50


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


ነገ ሰኞ ነው ጹሙ ቤተሰብ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


ሱረቱል ዩውሱፍ📖🎧

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

እኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡

◍ ወንድም ጧሪቅ
◍ ወንድም ቶፊቅ
◍ ወንድም ሙዓዝ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


◆▮ውይይት▮◆

"አምላኩን የማያውቅ ነብይ?እራሱ ነብይ እንደሆነ የማያውቅ ነብይ  ?ገነት በባይብል እና በቁርአን ? ሌሎችም ጥያቄች የተካተቱበት ውይይት"

◍ ኡስታዝ ወሒድ
◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም አሕመድ
         🅥🅢
◍ወገናችን ሚስተር
◍ወገናችን ኤቢ
ሌሎችም  ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 19:40


በተጨማሪም ኢብኑ ከሲር ነብዩላህ ዩኑስ የተላከው ለነነዌ ሰዎች እንደሆነ የነነዌ ሰዎች ደግሞ መውሲል እንደሆኑ ይናገራል፤ መውሲል ያሁኑ ሰሜናዊ ኢራቅ እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ፤ ኢብኑ ሳድ በኪታቡ ዩኑስ ከቤተ-እስራኤል እንደሆነ ይተርካል፣ ታዲያ ህዝብ ማለት የትውልድ የዘር ሃረግ ቢሆን ኖሮ አላህ የነነዌ ሰዎችን የዩኑስ ህዝብ ብሎ ባልተናገረ ነበር፦
10:98 *”የዩኑስ ሕዝቦች” َ “ባመኑ ጊዜ” በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ “እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው”*፡፡ فَلَوْلَا كَانَتْ قَرْيَةٌ ءَامَنَتْ فَنَفَعَهَآ إِيمَٰنُهَآ إِلَّا قَوْمَ يُونُسَ لَمَّآ ءَامَنُوا۟ كَشَفْنَا عَنْهُمْ عَذَابَ ٱلْخِزْىِ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍۢ
37:147 *ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም “ላክነው”፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ “አመኑም”፡፡ “እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው”*፡፡ وَأَرْسَلْنَٰهُ إِلَىٰ مِا۟ئَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ فَـَٔامَنُوا۟ فَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 19:40


ቋንቋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

55፥3-4 ሰውን ፈጠረ፡፡ *መናገርን አስተማረው*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ عَلَّمَهُ ٱلْبَيَانَ

መወለድ፣”መሞት፣መብላት፣ መጠጣት፣ ያ የተበላውንና የተጠጣውን ነገር በሌላ መልኩ ከሰውነት ማስወገድ፣ መተኛት፣ ከተቃራኒ ጥንድ ጋር ተራክቦ ማድረግ ሰው ከእንስሳ የሚጋራበት ተፈጥሮ ነው፤ ነገር ግን ሰው ከእንስሳ፣ ከእጽዋት፣ ከማዕድናት በተፈጥሮ ይልቃል፤ አላህ ሰውን ከሌላው ፍጡር አክብሮታል፤ ከፈጠረውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አብልጦታል፦
17፥70 *የአደምንም ልጆች በእርግጥ ከሌላው ፍጡር አከበርናቸው*፡፡ በየብስ እና በባህርም አሳፈርናቸው፡፡ ከመልካሞችም ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ *ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው*፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِىٓ ءَادَمَ وَحَمَلْنَٰهُمْ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ وَرَزَقْنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلْنَٰهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍۢ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًۭا

አላህ የአደምንም ልጆች ከሌላው ፍጡር ያከበረበት እና ያበለጠበት በሁለት ነገር ነው፤ አንደኛው ዐቅል በመስጠት ነው፤ ዐቅል” عَقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ነው፤ የሰው ልጅ “አዕምሮ” እራሱ “ዐቅል” ይባላል፤ ዐቅል የጥበብ ተውህቦ”faculty” ነው፤ አላህ አደምን ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፤ ሰው ያላወቀውን ሁሉ አሳውቆታል፦
2፥31 *አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው*፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ ተጠሪዎቹን አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የእነዚህን ተጠሪዎች ስሞች ንገሩኝ» አላቸው፡፡ وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمْ عَلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ فَقَالَ أَنۢبِـُٔونِى بِأَسْمَآءِ هَٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
96፥4-5 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ሁለተኛው ቀውል በመስጠት ነው፤ “ቀውል” قَوْل ማለት “አንደበት”articulate speech” ማለት ነው፤ ሰው ስሜቱንና ሃሳቡን የሚገልፅበት ቋንቋ ነው፤ ሰውን መናገር ያስተማረው አላህ ነው፦
55፥3-4 ሰውን ፈጠረ፡፡ *መናገርን አስተማረው*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ عَلَّمَهُ ٱلْبَيَانَ

የሥነ-ቋንቋ ጥናት”Linguistics” ምሁራን እንደሚያትቱት የሰው ልጆች የጋራ የሆነ ሰዋስው”grammar” አላቸው፤ በዚህ አንዱ የሌላውን ቋንቋን በመልመድ ይግባባል፤ ሁሉም ቋንቋ ውስጥ ጋር ስም፣ ተውላጠ-ስም፣ ግስ፣ ተውሳከ-ግስ፣ ገላጭ፣ መስተጻምር፣ መስተዋድድ እና ቃል-አጋኖ አለ።
በዓለማችን ላይ ከአምስት ሺ እስከ ስምንት ሺ ቋንቋዎች አሉ፤ እነዚህ ቋንቋዎች የመጡበት የራሳቸው ቤተሰብ አላቸው፤ አፍሮ-አሲያቲክ፣ ኢንዶ-ኢሮፒያን፣ ናይሎ-ሰሃራን፣ አዩስትሮ-አሲያቲክ ወዘተ ይባላሉ። አፍሮ-አሲያቲክ ቤተሰብ ውስጥ ሴሚቲክ፣ ኦሞቲክ፣ ኩሸቲክ፣ ቻዲክ ወዘተ ናቸው። የሴሜቲክ ዝርያ ውስጥ ዐረማይክ፣ ዕብራይስጥ፣ ዐረቢኛ፣ ግዕዝ፣ ዓካድ ወዘተ ናቸው። ወደድንም ጠላን እነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች መሰረታቸው አንድ ቋንቋ ነው፤ ለምሳሌ በዐረቢኛ “አሊፍ” ا በዐረማይክ “አሊፍ” ܐ በዕብራይስጥ “አሌፍ” א በግሪክ “አልፋ” Άλφα ነው፤ በዐረቢኛ “ባ” ب በዐረማይክ “ባ” ܒ በዕብራይስጥ “ቤት” ב በግሪክ “ቤታ” βῆτα ነው፤ ይህ መመሳሰል ቋንቋዎች መሰረታቸው አንድ ቋንቋ መሆኑን ያሳያል፤ እያንዳንዱ ፊደላት ትርጉሙ በሁሉም አንድ ነው፤ ለምሳሌ “አሌፍ” ማለት “መጀመሪያ” ወይም “በሬ” ማለት ነው፤ “ባ” ማለት “ቤት” ማለት ነው፤ “ጂም” ማለት “ግመል” ማለት ነው። ይህንን በሌሎች ቋንቋዎች ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

ይህ የመጀመሪያው የአደም ቋንቋ ማን ነው? የሚለው ብዙ መላምት ቢኖርም፤ አብላጫውን የቋንቋ ምሁራን መላምት ዐረማይክ የሚል መረጃ ነው ያለው፤ ለማንኛውም የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአላህ አስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ በዚህ ውስጥ *ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

አላህ ነብያትን ሲልክ በወቅቱ የተወለዱበት ማህበረሰብ ሊግባቡበት በሚችል ቋንቋ ነው፦
14፥4 ከመልክተኛ ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ *በህዝቦቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም*፡፡ ﻭَﻣَﺂ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﻣِﻦ ﺭَّﺳُﻮﻝٍ ﺇِﻟَّﺎ ﺑِﻠِﺴَﺎﻥِ ﻗَﻮْﻣِﻪِۦ ﻟِﻴُﺒَﻴِّﻦَ ﻟَﻬُﻢْ ۖ ﻓَﻴُﻀِﻞُّ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ﻭَﻳَﻬْﺪِﻯ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ۚ ﻭَﻫُﻮَ ﭐﻟْﻌَﺰِﻳﺰُ ﭐﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ

“ቀውም” قَوْم “ህዝብ” በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋ፣ አኗኗር፣ ታሪክ፣ መንግሥት እና ቦታ ያለው ማህበረሰብን ያመለክታል፣ ሙሳ ነብይ ሆኖ በተነሳበት ዘመን አላህ ሙሳን ወደ ህዝቦቹ “በታምራታት” እንደላከው እነዚያም ህዝቦች “ፈሮዖንና ሹማምንቶቹ” የሚጠቀልል መሆኑን ለማመልከት “ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን” በማለት ይናገራል፦
14:5 ሙሳንም፤ “ሕዝቦችሀን” ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ፤ የአላህንም ቀኖች አስገንዝባቸው፤ በማለት *”በታምራታችን” በእርግጥ “ላክነው”*፤ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِ
43:46 ሙሳንም *”በታምራቶቻችን” ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ “ላክን”*፤ እኔ የአለማት ጌታ መልክተኛ ነኝ አላቸውም። وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَقَالَ إِنِّى رَسُولُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 13:54


ሁላችሁም እንዳትቀሩ አብዱል ከሪም ቤት ፕሮግራም አለ

https://www.tiktok.com/@abdulkerim1100?_t=8qhcDJjyC8O&_r=1

3,960

subscribers

983

photos

1,344

videos