የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ @lafto_qirat Channel on Telegram

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

@lafto_qirat


ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ

https://t.me/lafto_qirat

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ (Amharic)

ላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ በውስጥ ባለችው እና በሬሽያ የሚተውሉ የጥቂት የፊልሞች ኦዬንሽኑን ያገናኝ የሚጠቅም ታሪክዎችን እና የመጠቆላል የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሌሎች ለሆነ በሚቀንሱ መጠቀሚያዎች ለራሳችንም የሚጠቀሙ እና ለሚከተሉ የጨለማ ሰባት ጊዜም ፍላጎት እንዲሰጡ ለማደንዛት ቻናል ሙስሊሞችን የሚበላ እንዲሁም የሚፈልግ መረጃዎችን እንደዚሁም ከእነሱ ጨለማ ላይ ለሚጠየቁ ዓለም ትምህርት መድረክ። እንደኛ ቻናል የተከለለት ከባሐንገዞችን እና ከትምህርት ማህበረሰብ፣ የትምህርት ቤትታስቂን፣ ማንጠልጠል፣ ማበሉ፣ ማብላትና ማላገጫ መነሻቸውን ለማውረድ ይህ ቻናል ማግኘት የሆነ። በትምህርት መድረክ እና ደርሶች መሀዳችን ውስጥ ይገኛሉ።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

31 Jan, 05:42


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ አቡ ሀይደር(ሳዲቅ ሙሀመድ)

🗓 ነገ ቅዳሜ  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Jan, 18:49


በሻዕባን ወር ጾምን ማብዛት

ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ –አላህ ስራውን ይውደድለትና– እንዲህ ይላል:— «ለአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አልኳቸው " አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የትኛውንም ወር እንደ ሻዕባን ወር ሲጾሙ አይቼዎት አላውቅም (ለምን ይሆን?)። እሳቸውም ይህ ወር በረጀብ እና በረመዷን መካከል ያለ ወር ሲሆን ሰዎችም የሚዘናጉበት እዲሁም ሰራዎች ወደ አላህ የሚወጡበት ወር ነው፤  እኔም ጾመኛ ሆኜ ሰራዬ ወደ አላህ እንዲወጣ እፈልጋለሁ"አሉኝ።»
(ሀዲሱን ነሳኢ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል)

ይህ ሀዲስ በውስጡ ብዙ ቁም ነገሮችን ይዟል ከነዚያም መካከል:–

1️⃣ በሻዕባን ወር ጾምን ማብዛት የሚወደድ መሆኑን።

2️⃣ አላህ ሱብሃነሁ–ወተዓላ ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላይ መሆኑን ከሚያስረዱ አሰረጂዎች መካከል አንዱ የመልካም ንግግሮች እና ስራዎች ወደ አላህ መውጣት  መሆኑን።

3️⃣ አንድ ሰው ጾመኛ ሆኖ መልካም ስራዎቹ አላህ ዘንድ ሲቀርቡ የበለጠ ተቀባይነት ሊኖራቸው እንደሚችል  እንረዳለን።*

አላህ ይወፍቀን!

✍️ ጣሀ አህመድ (ሻዕባን 1/ 1442 )

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

29 Jan, 05:00


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በተወዳጁ ኡስታዝ አብዱል ካፊ

🗓 ነገ ሐሙስ  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Jan, 18:12


የሱብሒ አዛን!

• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡

እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡
እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡
እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡
ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡
እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡
የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡
በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡
ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡

የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!

☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡
በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።

ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?

©ስለቀልባችን

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Jan, 11:46


አላህ እንዳዘዛችሁ ሁኑ፤ ቃል እንደገባላችሁ ይሆንላችኋል። አላህ ሲጠራችሁ መልስ ስጡ፤ ለልመናችሁ ምላሽ ይሰጣችኋል።

(ኢማሙ ኢብኑል ጀውዚይ)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Jan, 03:27


ይህ የሐዲስ በጣም ግሩም እና አስደሳች አፅናኝ ሐዲስ ነው፣ ለማንኛውም ሰው በዚህ ዱንያ ውስጥ ያመለጠው ነገር ማንኛውም ነገር መጽናናትን ይሰጣል። እባክዎ ትኩረት ይስጡት እና ፅንሰ–ሀሳቡን ያሰላስሉ።

ሐዲሱን ዐብድላሂ ኢብኑ ዑመር (ረዲዬሏሁ አንሁማ) ያስተላለፉት ሲሆን ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡ 
"አራት ነገሮች በአንተ ውስጥ ካሉ፣ ከዚህ ዓለም ያመለጠህ ነገር ምንም አይጎዳህም፤ አማናን(አደራን) መጠበቅ፣ እውነትን መናገር፣ መልካም ምግባር እና በምግብ ላይ ቁጥብ መሆን ናቸው።" 
(አህመድ፣ ኢብኑ አቢ አድ–ዱንያ፣ አጥ–ጠበራኒ እና አልበይሃቂ በሐሠን በሚባለው የሐዲስ ደረጃ ሰንሰለቶች ዘግበውታል፣ አልባኒም ሰሒህ መሆኑን አረጋግጠዋል።) 

ይህ ሐዲስ በዚህ ውስጠ-ባለ ዓለም የምናጣው ነገር ምንም ቢሆን እነዚህ አራት ነገሮች በእኛ ውስጥ ካሉ በእውነቱ ከተቀማጠሉት ነገሮች የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው።  

እባክዎ ይህን ሐዲስ በልብዎ ውስጥ ያስቀምጡት እና በሕይወትዎ ውስጥ ለመተግበር ይሞክሩ።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Jan, 11:14


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ካሚል ጠሃ

🗓 ነገ ሰኞ ጥር 19 ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Jan, 18:15


አብሽር❗️

አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡(በበደላቸው ላይ ያለ ቅጣት) የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
[ኢብራሂም :42]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Jan, 06:32


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ኢብራሂም ሙሣ

🗓 ነገ ቅዳሜ ጥር 16 ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Jan, 18:44


🎯 ጀነት!

👌 መደመጥ ያለበት ገሳጭ ሙሐደራ❗️

🎙 በኡስታዝ ሳሊም ኡመር

🗓 ሐሙስ 15/05/2017 EC ከመግሪብ በኋላ

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ የተደረገ ልዩ ሙሀደራ

🔗 @lafto_qirat

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ❗️

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Jan, 17:05


ለፍቶ አዳሪ.....

በቅርብ ቀን

በሸይኽ አህመድ አደም

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Jan, 12:59


ሞት መንገድ ላይ ነው‼️

🔅ሞት በየተራ ወደ ሁላችንም እየመጣ መንገድ ላይ ነው ያለው፤ መች እኔ/አንተ/ አንቺ ጋር እንደሚደርስ አይታወቅምና ሁሌም ተዘጋጅተን እንጠብቀው!
መጃጃል እና በህይወት መቀለድ ኋላ ላይ ከባድ ጸጸት ውስጥ ይከታል።
ነገሩ ከተበላሸና ዕድሜን በከንቱ ከጨረሱ በኋላ ሞት ሲመጣ መጸጸት ምንም ዋጋ አይኖረውምና አሁኑኑ ሳይመሽ ወደ አላህ ተመለስ/ሺ።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል መዓድ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

22 Jan, 18:17


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ሳሊም ኡመር

🗓 ነገ ሐሙስ ጥር 15 ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

21 Jan, 18:33


አርአያዎቻችን እኚህ ናቸው❗️

ኹበይብ በመካ ጣዖታዊያን እጅ ከገባ በኃላ! ይህ ተከሰተ!

አቡ ሱፍያን (ከመስለሙ በፊት) እንዲህ አለው ፦

«ሙሐመድ ﷺ ባንተ ቦታ ሆኖ እሱን ብንገድለውና አንተ ከቤተሰቦችህ ጋር ብትሆን ትፈልጋለህን?» ብሎ ጠየቀው

ኹበይብም ፦

«በፍፁም በአላህ እምላለሁ እኔ ከቤተሰቦቼ ጋር  ሆኜ ሙሐመድ ﷺ አሁን ባለበት ቦታ እሾህ እንዲነካው እንኳ አልፈቅድም»  ሲል መለሰ! ከዚያም ሰቀሉት! ረዲየላሁ ዐንሁ!

ነፍስቻቸውን መስጠት ቢቀር ካላቸው ጊዜ እና ጉልበት ትንሽ እንኳን ለዲናቸው የሚሰጡ ጀግኖች የታሉ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

20 Jan, 18:59


ያለህበት መንገድ ትክክለኝነት እንጂ የመጨረሻው ውጤት አያስጨንቅህ❗️

ሙዕሚን በአላህ መንገድ ላይ በሚያደርገው ትግል ከግብ ቢደርስም በተቃራኒው ሆኖ ሳይሳካለት ቢቀርም ሁሌም አሸናፊ ነው።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

19 Jan, 18:42


አንተ ብቻ ታገስ ትናንት አይሳካም ብለህ ተስፋ ልትቆርጥበት የነበረው ነገር ፈልጎህ ይመጣል።

#ትዕግስት

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Jan, 19:04


ለሚመለከተው ሁሉ‼️

ረመዷን 42 ቀን አካባቢ ቀርቶታል

በሀይድ፣ በወሊድ ፣ በህመም፣ በጉዞ ምክንያቶች ያለፈዉ ረመዷን ቀዳ ያለባቹ ሙስሊም ወንድም እህቶች በቀሩት ቀናቶች ቀዳቹን አዉጡ!

ጊዜዉ ገና ነዉ በማለት ከመዘናጋት ከአሁኑ ዕዳችንን በግዜ እንክፈል ‼️

አላህ ያግዘን መጪውንም በሰላም አድርሶ በመልካም ከሚፆሙት ያድርገን!🤲

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Jan, 14:09


አላህ ወልዷል ማለት ክብሩን መንካትና በርሱ ላይም መዋሸት ነው

(وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ تَرَى الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى اللَّهِ وُجُوهُهُمْ مُسْوَدَّةٌ ۚ أَلَيْسَ فِي جَهَنَّمَ مَثْوًى لِلْمُتَكَبِّرِينَ)
[سورة الزمر 60]
📂የቂያማ ቀን እነዚያን አላህ ላይ የዋሹ ሰዎችን ፊቶቻቸው ጠቁረው ታያቸዋለህ! ጀሀነም ውስጥ ሃቅን አልቀበልም ብለው ለኩሩ ሰዎች መኖሪያ የለምን?/አለ!)

💥ከውሸት ሁሉ በጣም የከፋው አላህ ላይ መዋሸት ነው።
ይህም ይበልጥ የሚከፋው የአላህን ክብር የሚነካና እርሱ ላይም የጉድለት ባህሪን መለጠፍ የሚያስከትልን ውሸት መዋሸት ነው!
ይኸውም አላህ ወልዷል/ ልጅ አለው ብሎ ማመን ሲሆን ጌታችን አላህ ግን
ከዚህ እጅጉን የጠራ ነው
አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም
የሁሉ መመኪያና መጠጊያም ነው።
አቻና አምሳያም የለውም።
የወለደ በሙሉ ግን አቻና አምሳያ አለው!
🏷 ዒሳ የአላህ ልጅ ነው ብለው የሚያምኑና በዓሉንም የሚያከብሩ ሰዎችን ተግባር እንደቀላል ቆጥሮ በዓሉ ላይ መገኘት ከኩፍር የማይተናነስ ወንጀል ነው።

🔸ሰማይና ምድር "ለአላህ ልጅ አለው" የሚሉ ሰዎችን የኩፍር ቃል ሲሰሙ ሊሰነጣጠቁና ሊናዱ ይደርሳሉ!
እኛስ...?!

✍🏻 ዛዱልመዓድ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Jan, 09:37


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

🎙 በኡስታዝ ሙሀመድ ሳኒ

🗓 ዛሬ ቅዳሜ ጥር 10  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

17 Jan, 11:23


💥 የጁሙዓ ሰላት

🎙 ሸይኽ ሁሰይን በሽር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

17 Jan, 11:04


በሀሰት መናገር እና ሐቅን ከመግለፅ መለጎም ከተጋቡ የሚወለደው ሐቅን አለማወቅና ፍጡርን ማጥመም እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡”

ኢብኑልቀይም ረሒመሁላህ (አስሰዋዒቁል ሙርሰላህ፡ 1/315)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

17 Jan, 03:30


💡የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

🌴«የጁምዓ ዕለት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ፤ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ፤ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል።»

📚 (ቡኻሪ  ዘግበውታል)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

16 Jan, 12:51


ቁምነገሩ አላህን አንተ በምትወደው ነገር መገዛትህ ሳይሆን አላህን እሱ በሚወደው ነገር መገዛትህ ነው❗️

(ሸይኽ ሷሊስ አስሲንዲ)

#ቢድዓ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

15 Jan, 18:30


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ባህሩ አባስ

🗓 ነገ ሐሙስ ጥር 08  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

14 Jan, 12:01


ኢማምነት ሀላፍትና እንጂ ስልጣን አይደለም❗️

ኢማም ማለት ሰላት አሰጋጅ፣ መንገድ የሳተውን መካሪ፣ወደ ጌታው ለመቅረብ ጥረት እያደረገ የሚገኛውን በመንገዱ ላይ እንዲፀና አበረታች፣ የወጣቱ እና ታዳጊዎች አርአያ፣ የተጣላ አስታራቂ፣የማህበረሰቡ ዱንያዊም ሆነ አኺራዊ ጉዳዮች አማካሪ በአጠቃላይ ኢማም ማለት የማህበረሰቡ አባት ነው። እነዚህ እና ሌሎች ብዙ ሀላፍትናዎችን ወደ ጎን በመተው ልክ እንደ አንድ ባለስልጣን መስጂድ የሚገባባቸውን ቀናት ወስኖ ማህበረሱ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዳያገኝ ማድረግ በአኺራም በዱንያም የሚያስጠይቅ ትልቅ በደል ነው።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

13 Jan, 04:19


በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ውሳኔዎች ነገን አርቆ በማየት በጥንቃቄ ሊወሰኑ እንጂ በግዴለሽነት እና በችኮላ ሊወሰኑ አይገባም❗️

"ሁላችሁም የሀላፍትና ባለቤቶች ናችሁ፤ በሀላፊነት ስለተሰጣችሁ ነገርም ትጠየቁበታላችሁ።"(ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Jan, 19:06


ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?

አዎ ለቀብር ጨለማ !!
ለቂያማ ጭንቀት !!
በሲራጥ ለማለፍ !!
አላህ ፊት ቁመን ስንጠየቅ ላለው ጭንቀት !!
በጥቅሉ ከሞት በሗላ ላለው ሂወታችን  ምን አዘጋጅተናል?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዐላ) እንድህ ይላል:-

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ }

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ » [ሐሽር (18)]

በኡስታዝ ኢብኑ ሙሐመድዘይን

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Jan, 05:18


"ደክመው ሸሽተው ወዳንተ ለመጡ ባሮችህ ሁሉ እዘንላቸው ያ ረብ።"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

11 Jan, 12:15


የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ pinned «ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️ ⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም 🎙 በኡስታዝ አብዱረዛቅ ሙሰማ 🗓 ቅዳሜ ጥር 03  ከመግሪብ-ዒሻ ⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️ 🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ! ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!»

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

11 Jan, 12:09


ከሶስቱ መስጂዶች ውጭ መንፈሳዊ ጉዞዎችን ማድረግ በሸሪዓ ይፈቀዳልን?

ክፍል 1/2

በሀገራችን እና በብዙ ሀገራት በሚኖሩ የሌላ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከተለመዱ ተግባራት አንዱ መንፈሳዊ ጉዞ ነው።  ይህ አይነቱ ጉዞ ሰዎች  ቅዱስነቱን ወደሚያምኑበት ስፍራ ወይም ቅዱሳን መሆናቸው የሚታመንባቸው ሰዎች ወደተቀበሩበት ቦታ የሚደረግ ሲሆን፤  ከየሄዱበት ስፍራ በረከትንና ፈውስን የመሳሰሉ ጥቅሞችን ይከጅላሉ። መነሻው በጥቂት አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች ቅንጅት ይከወን የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ነጋዴዎች ስርአት እያስያዙትና የጉዞ ማህበራት በማቋቋም እያደራጁት ሄደዋል።

ይህንን ተሞክሮ ወደ ሙስሊሙ በማምጣት የታላላቅ ሰዎችን ቅዱስነት እና ወልይነት አጉልቶ መስበክ፣ ወደቀብራቸውም ጉዞ ማድረግ፣ የተለያዪ ፕሮግራሞችን በቀብራቸው ዙርያ ማዘጋጀት በተደራጀ መልኩ ቀጥሏል። 
ከዚህ ቀደም ባልተደራጀ መልኩ ጉዞዎችን የሚያስተናግዱ እንደ ነጃሺ፣ አናጂና፣ አብሬት፣ ቃጥባሬ እና መሰል ቦታዎች አሁን አሁን ሌሎች ጋር የተለመደውን የጉዞ አደረጃጀት በመከተል መጠናከረቸውን የሚያሳዩ ማስታወቂያዎችና እና እንቅስቃሴዎች በመስጂዶቻችን ላይ በስፋት እየታዩ ነው።

ባእድ አምልኮ የሚፈፀምባቸውን የቀብር ስፍራዎች፤ ቅርስን በመንከባከብ እና ባህላዊ እሴቶች በመጠበቅ ስም ለማነፅ በከፍተኛ በጀት የሚበጅቱት የአንዳንድ ሀገራት ኤምባሲዎች አላማ ከህዝበ ሙስሊሙ የተደበቀ አይደለም። በሌሎች እምነቶች ተፅእኖ ስር የወደቁትን የሱፊያ አስተሳሰብ መስመሮች ለሙስሊሙ ህብረተሰቡ በማስተዋወቅ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መገለጫ አድርገው በማቅረብ ሙስሊሙን እኛ እናውቅልሀለን የሚሉት ወገኖች አላማም አጠያያቂ ነው። ይህ አይነቱ ጉዞ በሸሪአ እንዴት ይታያል የሚለውን ለመቃኘት እንሞክራለን፤

1)  ነቢያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) {ወደ ሶስት ቦታዎች ካልሆነ ጓዝን ጠቅልሎ ጉዞ አይወጣም፤ መስጅድ አልሐረም (መካ) መስጂድ አነበዊ (መዲና) እና መስጂድ አልዓቅሷ} ማለታቸው በሰሒሕ ቡኻሪ እና ሌሎችም ድርሳናት ተዘግቧል

ይህ ሐዲስ እንደሚጠቁመው አምልኮትን ፍለጋ አንድን ቦታ በማላቅ የሚደረግ ጉዞ ወደ ሶስቱ መስጅዶች ካልሆነ ወደ ሌላ ቦታ መሄድን ይከለክላል። ይኸውም ሰዎች አንድን ቦታ በተለየ ቀድሰው በቦታው የሚገኝን ቀብር ወይም ሌላ ነገር በማላቅ ወደ ማምለክ(ሽርክ) እንዳይገቡና ከዲናቸው እንዳይወጡ ለመጠበቅ ሲባል ነው።

ከዚህም በመነሳት፤  አንድን ቦታ በማላቅ ወይም ከሌሎች ቦታዎች ይልቅ አምልኮት ተቀባይነት ያገኙበታል በሚል ግምት፤ ከሶስቱ መስጅዶች ውጭ መንፈሳዊ ጉዞ ማድረግ ሀራም ነው። ይህ አላህን በሰላት ዱአ እና መሰል ኢባዳዎች ለማምለክ ከሆነ ነው። ስለት በማስገባት፣ ድረሱልን ወይም አማልዱኝ በማለት  ቅዱሳንን መማፀን ከሆነ ግን ባእድ አምልኮ ነውና  በእጅጉ ከዚህ የከበደ የሽርክ ተግባር ነው። 

2) በአምልኮት ተግባራቸው እና ሌሎች  በሚለዩባቸው ባህልና ልማዶች አርአያ አድርጎ መመሳሰል ብሎም መከተል የማይፈቀድ ክልክል ተግባር ነው።
ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በአንድ ሐዲስ ... [ከናንተ በፊት የነበሩትን ፈለግ ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ፤ የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳ ትከተሏቸዋላችሁ] አሉ፤ ይህን የሚሰሙት ሶሐቦችም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ የየሁዳና ነሳራዎችን (ፈለግ ማለት ነው) ?] ብለው ሲጠይቋቸው እሳቸውም ]ታዲያስ?] ብለው መለሱላቸው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡

 የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤
[ከህዝቦች የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱ ነው] አቡ ዳውድ ዘግበውታል

  ቅዱሳንን በማላቅ አላማ የሚካሄዱ ጉዞዎች የሌሎችን  የአምልኮ ተግባራት በመኮረጅ ኢስላማዊ ቅብ መቀባት በመሆኑ መመሳሰል (ተሸቡህ) ነውና አይፈቀድም።

በዲናችን አንድን ቦታ በማላቅ ወይም ከፍ በማድረግ ወደዛ ስፍራ ሄዶ አምልኮትን መፈፀም የሚፈቀደው ወደ ሶስቱ መስጅዶች ብቻ ነው።

3) ሸሪዓችን ከተደነገጉት ሶስቱ መስጂዶች ውጭ አንድን ቦታ በማላቅ ወይም አንዳች ጥቅም በመፈለግ የሚደረግ የጀመዓ ጉዞ ነብያችንም ሆኑ ሶሐቦቻቸው በኖሩበት ጊዜ የማይታወቅ የቢድአ ተግባር ነው።  ወደ ተለያዩ ዶሪሆች እና መሳጂዶች የሚደረገው ጉዞ በእስልምናችን የማይታወቅ ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያላዘዙት መጤ የቢድአ ተግባር ነው። ነብያችንም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሸሪዓችንን በሚገባ አስተምረው እሳቸው ያላዘዙትን ከመፈፀም በብርቱ አስጠንቅቀው አልፈዋል። እናታችን አዒሻ ባስተላለፉት ሐዲስ ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል [የኛ ትእዛዝ የሌለበትን (የአምልኮ) ስራ የሰራ፤ (ስራው) ተመላሽ ነው] ሙስሊም ዘግበውታል፡፡

ስለሆነም ይህ በሸሪዓ እንዲጎበኝ ወዳልታዘዘ ቦታ በመጓዝ አጅር አገኛለሁ ብሎ መሳተፍ አላህም ሆነ መልእክተኛው ያላዘዙትን መስራት በመሆኑ አደገኛ የቢድዓ ወንጀል ነው!

4)  አላህ ዲናችንን የተሟላ እና ምንም አይነት ጭማሪም ሆነ ማሻሻያ የማይሻ የማይፈልግ ለሁሉም ዘመንና ቦታ የሚሆን ሐይማኖት አድርጎታል። መንፈሳዊ ጉዞ ታላላቅ የዲን መሪዎች በኖሩባቸው የኢስላም ቀዳሚ ዘመናት ሙስሊሞች የማያውቁት ከሌሎች የተኮረጀ እንግዳ ስራ ነው።

اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم وَأَتمَمتُ عَلَيكُم نِعمَتي وَرَضيتُ لَكُمُ الإِسلامَ دينًا

«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ» ሱረቱ'ል-ማኢዳህ 3

በመሆኑም፤ መንፈሳዊ ጉዞ በሚል በተለያዩ መስጅዶች እየተዋወቀ ያለው ጥሪ ትኩረት አድርገን ካልተከላከልነው ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጥ ነው። በሸሪአችን በግልፅ የተከለከለ በመሆኑ  ሙስሊሙ እንዲጠነቀቅ፣ ራሱንና ቤተሰቡን በዲን ስም ከሚፈፀም ጥፋት እንዲጠብቅ እናሳስባለን። 

5) በብዙ አካባቢዎች፤ መቃብሮች ከአንድ ስንዝር በላይ ከፍ እንዳይሉ፣ እንዳይገነቡና እንዳይቀቡ እንዲሁም መቃብሮች መስጂድ ተደርገው እንዳይያዙ የሚከለክሉ ነብያዊ ትእዛዛትን የተቃረነ ተግባር በስፋት ይፈፀማል።
ጁንዱብ ኢብኑ አብደላህ ባስተላለፉት ሐዲስ  የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሁ ወሰለም) ከመሞታቸው ከአምስት ቀናት በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ብለዋል ‹‹ከእናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦች የነቢያቸውንና የደጋግ ባሮችን ቀብር መስገጃ ስፍራ አደረጉ፡፡ አደራ! ቀብሮችን መስገጃ እንዳታደርጉ ከልክያችኃለው››  ሙስሊም ዘግበውታል

በሌላ ዘገባም ጃቢር እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀብርን በጄሶ መመረግ፣ ላዩ ላይ መቀመጥ፣ ከላዩ መገንባት፣ ከአፈሩ ውጭ መጨመርና ቀብር ላይ መፃፍ ከልክለዋል›› 

ከላይ የተዘረዘሩት መረጃዎች በግልፅ እንደሚያሳዩት ከሶስቱ መስጂዶች ውጭ ወደ ወልዮች ሷሊሆችና ነብያት መቃብሮችም ይሁን መናገሻ ከተማዎች የሚደረጉ ጉዞዎች በሸሪዓ የተወገዙ ለሽርክ እና ባእድ አምልኮ የሚያጋልጡ መሆናቸው ግልፅ ነው። በአላህ ፈቃድ በቀጣይ ክፍል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማደናገርና ወደ ቀብር አምልኮ ለመምራት በዚህ ሀዲስ ዙርያ ለሚቀርቡ ማደናገሪያዎች ምላሽ እንሰጣለን።

አምልኮ ሁሉ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው። ስላሳወቀን የተውሂድ ብርሀን እናመሰግነዋለን። መንገድ ከመሳት በርሱ እንጠበቃለን።

ወልሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን!

አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Jan, 18:05


አያሳፍርም⁉️

ለዘላለም ኪሳራ ወደሚዳርግ ቦታ ማየት እንኳ የማይችሉ አዛውንቶች በዱላ በመታገዝ ነጠላ ለብሰው በሌሊት ሲጓዙ አንተ ምንም ሳይጎልህ እንዴት ለዘላለም ደስታ የሚያጎናፅፍህን የሱብሂ ሰላት በመተኛት ታሳልፋለህ?

#ፈጅር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Jan, 06:18


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ አብዱረዛቅ ሙሰማ

🗓 ቅዳሜ ጥር 03  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

08 Jan, 19:05


«ፈጅር ሰላትን በመተኛት ያሳለፈ፣እለቱን አውድሟል፤ ቀኑን ያለ ቢላዋ አርዷል።»

(ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር)

#ፈጅር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

08 Jan, 07:28


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ሳሊም ኡመር

🗓 ነገ ሐሙስ ጥር 01  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Jan, 18:56


💥 ትክክለኛው የሰላት አቋቋም(ሶፍ አሰራር)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Jan, 18:04


"አላህ ከተመለከባቸው ኢባዳዎች ሁሉ ትልቁ የሱን ባሮች መምከር ነው።"
[ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁላህ]

#ዳዕዋ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Jan, 11:43


"እደርሳለሁ የሚባለው መንገድ ጀምሮ ነው"

💯

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Jan, 08:01


በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን?

በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!!

በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!!

ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!!

(وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا *  تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا *  أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا *  وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا *  إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا *  لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا *  وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا)

[«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም]
Surah Maryam 88 - 95

ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...
ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና  የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ!

የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን?

እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ።  ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል»  አህካም አህሉዚማህ

የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44 

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!!

በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን።  ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ  የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)

አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
[Surah Al-Qalam 8 - 10]

ወላሁ አዕለም

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!

____
አቡጁነይድ ረጀብ 24/1437 ዓ.ሒ / ሜይ 1/ 2016 ከጥቂት ማሻሻያዎች ጋር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Jan, 18:51


"ትክክለኛ አማኝ አላህን ያመፀባቸው ወንጀሎችን ልክ ከላይ ሊወድቅበት የተቃረበን ተራራ እንደሚፈራው ይፈራቸዋል በተቃራኒው ሙናፊቅ ደግሞ የፈፀማቸውን ወንጀሎች ልክ ፊቱ ላይ አርፎበት በእጁ እንዳባረረው ዝንብ ቦታ አይሰጠውም።"

[አብደሏህ ኢብኑ መስኡድ ረዲየላሁ አንሁ]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Jan, 11:37


🔘 ወቅታዊ ሙሓደራ ❗️

🔊 በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

🌋በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መባልና መደረግ ያለባቸው ነገሮች

             ሰኞ 6/7/1446 ዓ.ሂ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Jan, 07:44


አላህ ወልዷል ማለት ክብሩን መንካትና   
  በርሱ ላይም መዋሸት ነው


وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ تَرَى الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى اللَّهِ وُجُوهُهُمْ مُسْوَدَّةٌ ۚ أَلَيْسَ فِي جَهَنَّمَ مَثْوًى لِلْمُتَكَبِّرِينَ)
[سورة الزمر 60]
📂የቂያማ ቀን እነዚያን አላህ ላይ የዋሹ ሰዎችን ፊቶቻቸው ጠቋቁረው ታያቸዋለህ! ጀሀነም ውስጥ ሃቅን አልቀበልም ብለው ለኩሩ ሰዎች መቀመጫ የለምን?/አለ!)

💥ከውሸት ሁሉ በጣም የከፋው አላህ ላይ መዋሸት ነው ይህም ይበልጥ የሚከፋው የአላህን ክብር የሚነካና እርሱ ላይም የጉድለት ባህሪን መለጠፍ የሚያስከትልን ውሸት መዋሸት ነው!
ይሄውም አላህ ወልዷል ልጅ አለው ብሎ ማመን ነው ጌታችን አላህ
ከዚህ የጠራ ነው

አልወለደም  አልተወለደምም
የሁሉ መመኪያና መደገፊያም ነው
አቻና አምሳያም የለውም
የወለደ በሙሉ ግን አቻና አምሳያ አለው!
  🏷ዒሳ የአላህ ልጅ ነው ብለው የሚያምኑና በዓሉንም የሚያከብሩ ሰዎችን ተግባር እንደቀላል ቆጥሮ በዓሉ ላይ መገኘት ከኩፍር የማይተናነስ ወንጀል ነው

🔸ሰማይና ምድር "ለአላህ ልጅ አለው" የሚሉ ሰዎችን የኩፍር ቃል ሲሰሙ ሊሰነጣጠቁና ሊናዱ ይደርሳሉ
ምነው እኛ አቀለልነውሳ?!

እሁድ 6/4/1439 ዓ.ሂ
✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
        @ ዛዱልመዓድ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Jan, 18:48


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በሸይኽ ኑረላህ ሐሚዲን

🗓 ነገ ሰኞ ታህሳስ 28  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Jan, 05:03


መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?

ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።”
📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Jan, 18:16


🌿 ሱናን አጥብቆ መያዝ

ማከክ እንኳን ብትፈልግ እንዴት እንደሚታከክ የሚሳይ ማስረጃ ካለ በዛ ማስረጃ መሰረት እንጂ እንዳታክ!!!

(ሱፊያን አስ ሰውሪ)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Jan, 14:56


ኡስታዝ ስላልተመቻቸው ለዛሬ የተፍሲር ደርስ እንደማይኖር ከይቅርታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Jan, 12:48


قال الله عزوجل: "واتقوا يوما ترجعون فيه إلى الله ثم توفى كل نفس ما كسبت وهم لا يظلمون"

"ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትመነዳበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡"
[ አል-በቀራህ - 281 ]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

02 Jan, 17:33


🌿 የሙሀደራ ፕሮግራም ግብዣ🌿

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ

💥ተጋባዥ ኡስታዞች

🎙ኢብኑ ሙነወር እና
🎙አቡል ዐባስ

🗓ቅዳሜ ታህሳስ 26

🕝ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

💡አይደለም መቅረት ማርፈድ እራሱ ያስቆጫል❗️

📍ሴቶችንም ወንዶችንም ተጋብዛቹሀል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

02 Jan, 04:09


ከዒልም አንራቅ፡ ልባችን እንዳይሞት
~
ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የሸሪዐ እውቀት ለልብ ምግቡ፣ መጠጡ እና መድሃኒቱ ነው። ህይወቱ በሱ ላይ ነው የቆመው። ልብ እውቀትን ካጣ ያኔ ሙት ሆኗል።"
[ሚፍታሑል ዳ ሪ ሰዓደህ፡ 1/344]
=
IbnuMunewor

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

01 Jan, 10:24


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ሙሀመድ አባተ

🗓 ነገ ሐሙስ ታህሳስ 24  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

31 Dec, 19:11


የምንችለውን እናስተምር
~
ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።

[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]
=
IbnuMunewor

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

31 Dec, 05:49


ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-
«እውነትን የሚፈልግ በምክር ደስ ይሰኛል፣ ስሕተቱን ሲነገረው ደስ ይለዋል( እንጂ አይከፋም)።"
📚ሸርሑ ኪታቢ አል – ዑቡዲያህ (252)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Dec, 19:17


🎯 "የኢልም መድረኮች ላይ መቀማመጥ ያለው ትሩፋት"

👌 መደመጥ ያለበት ገሳጭ ሙሐደራ❗️

🎙 በሸይኽ አሕመድ ሸይኽ አደም

🗓 ሰኞ 21/04/2017 EC ከመግሪብ በኋላ

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ የተደረገ ልዩ ሙሀደራ

🔗 @lafto_qirat

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ❗️

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Dec, 12:28


🌿የማይቀርበት ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ🌿


🎙በሸይኽ አሕመድ ሸይኽ አደም

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ!!!

🗓ዛሬ ማታ

🕝ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

💡አይደለም መቅረት ማርፈድ እራሱ ያስቆጫል❗️

📍ሴቶችንም ወንዶችንም ተጋብዛቹሀል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Dec, 06:42


"ምድር ላይ ዝቅ ያልክ ሁነህ እንጂ እንዳትራመድ
ካንተ በላይ ክብር ያላቸው ስንቶች ከምድር በታች ናቸው"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Dec, 18:21


🌿የማይቀርበት ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ🌿


🎙በሸይኽ አሕመድ ሸይኽ አደም

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ!!!

🗓ሰኞ,ታህሳስ 21/04/2017E.C

🕝ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

💡አይደለም መቅረት ማርፈድ እራሱ ያስቆጫል❗️

📍ሴቶችንም ወንዶችንም ተጋብዛቹሀል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Dec, 11:06


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ መንሱር ሑሰይን

🗓 #ዛሬ ቅዳሜ  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Dec, 17:50


ደስ የሚል እውነታ❗️


"ሐቅ እና ባጢል መሃል የሚደረገው ጦርነት: እስከ ትንሳኤው ቀን ድረስ አይቋረጥም። አላህ ሁሌም ኣማኝ ባሮቹን ይፈትናል። ከፈተና በኋላ ዱንያ ላይ አመቻችቶ የበላይ ያደርጋቸዋል አልያም ዱንያ ላይ ሕይወታቸውን መስዕዋት አርጎ ይቀበላቸውና አኼራ ላይ በጀነት ያከብራቸዋል። በዚህ ጦርነት አንዳንድ ጊዜ ባርነት ለአላህ ብቻ ያደረጉ ሙስሊሞች ድል አርገው ሲያሸንፉ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጠላታቸው እንዲፈተኑ ያደርግና ሸሂድ ያደርጋቸዋል።
  የኖረው በዕልቅና ይኖራል: የሞተው ሸሂድ ሆኖ ይከብራል!!

ከእኛ የሚፈለገው…………
   ሁልጊዜ ድል ማድረግ ሳይሆን: ሁል ጊዜ መንገዱ ላይ ፀንቶ መቆም ነው።

   👌ስለ ትግላችን እንጂ: ስለ ድላችን አንጠየቅም!!"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Dec, 14:19


ነብያችን ﷺ  የመጨረሻው ቀን ሲቃረብ ያለዉን ሁኔታ ሲገልፁ እንዲህ አሉ፦

    «ጊዜ ይቀራረባል ፣ እውቀት ይነሳል ፣ ፈተና ግልፅ ይወጣል ፣ ስግብግብነት (ስስት) ይስፋፋል ፣ "ሀርጅ"ም ይበዛል አሉ:: "ሀርጅ" ደግሞ ምንድን ነው ሲባሉ? ነብያችን  ﷺ  "ግድያ ነው" አሉ፡፡»

📚[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

                     ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Dec, 06:41


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Dec, 07:06


ሽማግሌ እንደ ሽማግሌ፣ወጣት እንደ ወጣት፣ ሴት እንደ ሴት...... ሲሆኑ ነው የሚያምርባቸው ከዚህ በተቃራኒ የፈለገ አላህ ያዋርደዋል።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Dec, 18:06


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በሸይኽ ጁነይድ ሁሴን

🗓 ነገ ሐሙስ  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Dec, 13:24


ገንዘብና ወለድ እውነታና ብዥታ መፅሀፍ

በገበያ ላይ ዋለ

በሸይኽ ኢልያስ አህመድ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

22 Dec, 19:12



  "ራስ ወዳድነት በሁለቱም አቅጣጫ እንደተሳለ ጦር ነው።

    አንደኛው ጫፍ አንተን ይገላል
ሌላኛው ጫፍ በዙርያህ ያሉ ወዳጆችህን ይገላል።
"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Dec, 17:22


ያለ አጫዋች ብቻህን ለምትገባበት አስፈሪው የቀብር ጨለማ ብርሀን የሚሆንልህን መልካም ስራ በመስራት እራስህን አዘጋጅ❗️

#ሞት_ቀጠሮ_የለውም

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Dec, 17:37


- قلتُ : يا رسولَ اللهِ أيُّ النَّاسِ أشدُّ بلاءً ؟ قال : الأنبياءُ ثمَّ الأمثلُ فالأمثلُ ، يُبتلَى الرَّجلُ على حسْبِ دِينِه ، فإن كان دِينُه صُلبًا اشتدَّ بلاؤُه ، وإن كان في دِينِه رِقَّةٌ ابتلاه اللهُ على حسْبِ دِينِه فما يبرَحُ البلاءُ بالعبدِ حتَّى يمشيَ على الأرضِ وما عليه خطيئةٌ

الراوي : سعد بن أبي وقاص | المحدث : المنذري | المصدر : الترغيب والترهيب
الصفحة أو الرقم: 4/221 | خلاصة حكم المحدث : [إسناده صحيح أو حسن أو ما قاربهما]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Dec, 13:31


🌾 🌿

አንድ ሷሊህ ሰው ጥሩ ጓደኛ እንዴት ነው ማገኘው ተብለው ተጠየቁ:


እሱም: አንተ ሷለህ ሁን ጥሩ ጓደኞች አንተን ለመጎዳኘት ይወዳደሩብሀል ብሎ መለሰለት ..

🌿 🌾

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

04 Dec, 19:01


ቀንህ ውብ ይሆንልህ ዘንድ የሱብሒን ሰላት መስጂድ መጥተህ በጀመዓ በመስገድ ጀምረው‼️

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

02 Dec, 18:18


🍂 ረሱል እንዲህ ብለዋል :

«ቁርኣንን አሳምሮ የሚያነብ ከተከበሩትና ከደጋጎቹ ልዑካን (መላኢካዎች) ጋር ነው። ያ እየተንተባተበና እያስቸገረውም ቁርኣንን የሚያነብ ሰው ሁለት አጅር አለው፡፡»

📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

29 Nov, 18:42


#ኢብኑ_ቁዳማህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«አብዛሃኛዎቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ወቀሳ በመፍራትና ሙገሳቸውን በመሻት መሆኑን አውቃለሁ። ሁሉም እንቅስቃሴያቸው የሰዎችን ውደታ በሚገጥም መልኩ ሆነ፤ ሙገሳቸውን መሻትና ወቀሳቸውን መፍራት! ይህ ከአጥፊ ነገሮች መካከል ነው። መታከም ይገባዋል
።»

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

29 Nov, 06:03


ታላቅ መሪ
እውነተኛ አፍቃሪ!

ብዙ ምላሶች ስለ ነብዩ ፍቅር አነብንበዋል ፤ እልፍ ብዕሮች ስለዚህ ታላቅ መሪ ውዴታ ከትበዋል! ገሚሱ በተግባር ውዴታውን ለመግለፅ ሲፍጨረጨር ገሚሱ ውዴታው ከተከሸኑ ቃላት ባለፈ ከላንቃው አልወርድ ብሎት ምላሱና ጣቶቹ ጫፍ ተንጠልጥሎ በተግባሩ እጅጉን ርቆ ይባስ ብሎ በተግባሩ አስተባብሏቸዋል!

ከተለያዩ የቃላት ጋጋዎች ይልቅ ግን የዚህ እውነተኛ አፍቃሪ ሰሐቢይ ውዴታውን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የገለፀበት አጋጣሚ እስከመጨረሻው ቀልቤን ገዝቶታል!

ኹበይብ በመካ ጣዖታዊያን እጅ ከገባ በኃላ! ይህ ተከሰተ!

አቡ ሱፍያን (ከመስለሙ በፊት) እንዲህ አለው ፦

«ሙሐመድ ﷺ ባንተ ቦታ ሆኖ እሱን ብንገድለውና አንተ ከቤተሰቦችህ ጋር ብትሆን ትፈልጋለህን?» ብሎ ጠየቀው

ኹበይብም ፦

«በፍፁም በአላህ እምላለሁ እኔ ከቤተሰቦቼ ጋር  ሆኜ ሙሐመድ ﷺ አሁን ባለበት ቦታ እሾህ እንዲነካው እንኳ አልፈቅድም»  ሲል መለሰ! ከዚያም ሰቀሉት! ረዲየላሁ ዐንሁ!

ማብራሪያ አይሻም!

ጁምዓ ነው እርሳቸውን ማውሳት እናብዛ !!!

ሁሌ የሚወሱ ድንቅ ነብይ!  እንዴታ ጌታቸውስ

"መወሳትህን ላንተ ከፍ አድርገንልሃል።" (95:4)

ብሏቸው የለ!

*اللــــــــهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد .اللـــــــهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد*

❁ ❁❁ ❁

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Nov, 18:47


ከሞትን በኋላ ሰዎች እንዴት በፍጥነት እንደሚረሱን ብናውቅ ኖሮ፤ አላህን አምፀን ፍጡራንን ለማስደሰት አንለፋም ነበር፡፡
አላማችን የአላህን ውዴታ ማግኘት ግባችን ጀነት ይሁን!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Nov, 19:15


ለርካሽ ጥቅም ዲንን፣ አቅልን እንዲሁም ክብርን ሽጦ ተላላኪ ሆኖ መኖር ምን የከፋ ነው!

الله المستعان!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Nov, 18:58


ከብዛቱ ጥራቱ ❗️

ቀጥተኛውን መንገድ ተከተል ወደዛ መንገድ የሚገቡ ሰዎች ማነሳቸው አይጎዳህም❗️

አደራህን👇

የጥመት መንገዶችን ተጠንቀቅ ጠፊዎች በመብዛታቸው አትታለል❗️

(ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሂመሁላሁ ተዓላ)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Nov, 19:11


"ለወደፊቱ አስተካክል ያለፈው ይማርልሀል❗️"

{እናንተ በነፍሳቹ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ ከአላህ እዝነት በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ አላህ ወንጀሎችን በሙሉ ይቅር ይላል እነሆ እሱ መሀሪ እና አዛኝ ነው።} (ሱረቱ አዝ ዙመር:53)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Nov, 19:00



     ቀና በል ቀን አለ!!

መንገድ ሁሉ እንቅፋት  በሆነበት ዐለም
መነሳት ነው እንጂ   መውደቅ ብርቅ አይደለም።

ሰው ብታጣ ዛሬ   አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን   ያስተምራል እድሜ።

ሲኖርህ የኖረ   ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ   ከፊት ባታገኘው።


የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።

መሙላት ቢቸግርህ  ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ   ቀና በል ቀን አለ!!





منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Nov, 17:17


"እግርህ ጀነትን እሰከሚረግጥ እለት ድረስ ትፈተናለህ አሁንም ዳግም ትፈተናለህ! ከዚያም ጀነት ውስጥ ለአንዳፍታ ትነከርና "ወላሂ ችግር ፍፁም ቀምሼ አላውቅም" ትላለህ።
ይህንን እድል ከታጋሾች ሌላ ማንም አይጎናፀፈውም።
"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Nov, 18:03


እንዴት እንደሚኖሩ እንጂ ለምን እንደሚኖሩ ከማያውቁትን ሰዎች እንዳንሆን እንጠንቀቅ ፤ 
የተፈጠረልን ነገር የተፈጠርንለትን ዓላማ እንዳያስተን እናስተውል!

ለምንድን ነው የተፈጠርነው?

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

22 Nov, 18:45


"እውነተኛው የአላህ ባሪያ ማለት  የአካሉ ሞት ሳይሆን የልቡ ሞት የሚያስፈራው ነው፡፡  ሆኖም ብዙ ሰዎች የአካላቸውን ሞት ይፈራሉ ስለ ልባቸው ሞት ግን ግድ የላቸውም ፡፡"

(ኢማሙ ኢብኑል ቀይዩም)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

21 Nov, 18:54


ነጋዴ ወደ ማምሻ ላይ ሱቁን ይዘጋል ፣ ስለ ዕለት ውሎውም ሒሳብ ይሠራል ፤ መክሰር ማትረፉን ይገመግማል፣ ዕዳና ብድሩን ያወራርዳል …
እስኪ ሁላችንም ውሏችንን እናወራርድ ፣ ዛሬ ለአኼራችን ምን ሠርተን ዋልን?

ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

20 Nov, 18:56


☑️ እናታችን አኢሻ (رضي الله عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል።

«እናንተ ሰዎች ሆይ! (ከመልካም) ስራ የምትችሉትን ያክል ብቻ ያዙ። እናንተ እስካልተሰላቻችሁ አላህ አይሰለችም። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን ዘውታሪነት ያለውን ነው።»

[ 📖 صحيح البخاري (٥٨٦١) ]
==

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Nov, 19:00


«በአላህ ቁጣ የሰዎችን ውዴታ፣ እርካታ የሚፈልግ ሁሉ አላህ ይቆጣበታል። (ወደፊት)ሰዎችም  እንዲናደዱበት ያደርጋል።»

📚(ቲርሚዚ ዘግበውታል)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

16 Nov, 17:30


የሚያሳፍር⁉️

ብዙ ጀነት መግቢያ መንገዶች ተመቻችተውልን ይህን ማድረግ እንኳ ከበደን......አጂብ‼️

💫የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ከየግዴታ (ፈርድ) ሶላት በሗላ አየተል ኩርሲይን (ከሱረቱል በቀራ አንቀፅ 255-256) የቀራ የሆነ ሰው ጀነት ከመግባት ምንም አይከለክለውም ሞት እንጂ።» ነሳዒይ

©ዲናዊ መልዕክቶች

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

15 Nov, 11:13


ከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን።

ኢማኔ ደከመ፣ቀልቤ ደረቀ፣ከአላህ ራቅኩኝ፣
የቂኔ ከዳኝ፣ተወኩሌ ጠፋ፣ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣
ቁርአንን ዘነጋሁ፣አዘኔታ አጣሁኝ፣
ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣ሱና መስገድ ተውኩኝ፣ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣…

አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ  ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር።

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

13 Nov, 18:29


ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-

“አንድ ሙስሊም ከመናገሩ በፊት ቃላቱን መመዘን ይኖርበታል፣  ንግግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ  ውጤታቸውን ማጤን አለበት፣ ቃላቱን በትክክለኛ ሚዛን መዝኖ ሲያበቃ፣ ቃላቱ ለመልካም ሰበብ ከሆነ ይናገር፣ አሊያ ግን  ሸርን የሚያስከትል እና ለሸር ሰበብ ከሆነ ክፋቱን ከሰዎች ሊከላከል ይገባል።”

📚 ["ሸርሑ ኪታቢ አልፊተን ወል ሓዋዲስ" (ገጽ 239)]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Nov, 18:10


«የዘውትር ጭንቁ አኼራ የሆነ፤ አላህ ሀብትን በልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱንያ የግዷን ወደሱ ትመጣለች።

የዘውትር ጭንቁ ዱንያ የሆነ፤ ድህነትን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል። ጉዳዩንም ይበታተንበታል።»

ረሱል

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Nov, 13:15


ታላቁ ዐሊም ኢማሙ ኢብኑል ቀይዩም (አላህ ይዘንላቸውና) የምእመናን መሪ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረድየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ማለቱን አውስተዋል፦

«አንድ ሰው ከቤቱ ሲወጣ የቲሐማን ተራራ የሚያክል ወንጀል (ኃጢዓት) ተሸክሞ ይወጣል ሆኖም ግን (ሸሪዓዊ የሆነን) ዕውቀትን ሲሰማ ፍርሀት ያድርበትና ወደ ጌታው ይመለሳል ንስሀም ያደርጋል። በዚህም ምክንያት ወደ ቤቱ ሲመለስ ኃጢዓቱን አራግፎ ያለምንም ወንጀል ይመለሳል። ስለዚህም ከዓዋቂዎች ጋር መቀማመጥን እንዳትተዉ።»

📚[ሚፍታሑ ዳሩ አስሰዓዳህ (1/133)]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

11 Nov, 06:39


- يَـا نَفس أي شيء تتمنين؟.

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Nov, 17:52


አቢ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ ደካማና ስልቹ አትሁን፤ አንድ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ‘ይህን ነገር እንዲህ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል»

📚[ሙስሊም ዘግበዉታል]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Nov, 16:14


"የዘገየ ድርሻው አያመልጠውም። የፈጠነም ከተወሰነለት ውጭ አያገኝም።
መልካም ያገኘ አላህ ሰጠው። ከመጥፎ የተጠበቀም አላህ ጠበቀው። በመጥፎ ተግባር ከፊት ከመሆን፣ በመልካም ተግባር ከኋላ ሁን!"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

09 Nov, 19:23


በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ጊዜ በርካታ የሙስሊሞችን ጉዳይ ለማስፈፀም የተቀመጡ ሰዎች የያዙት ቦታ አላህ ፊት የሚጠየቁበት ሀላፍትና መሆኑን ዘንግተው ለግል ፍላጎታቸው ማስፈፀሚያ እና የፖለቲካ ተላላኪዎች ሆነዋል❗️

"ሁላችሁም የሀላፍትና ባለቤቶች ናችሁ፤ በሀላፊነት ስለተሰጣችሁ ነገርም ትጠየቁበታላችሁ።"(ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

08 Nov, 19:34


የሱብሒ አዛን❗️

• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡

እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡
እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡
እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡
ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡
እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡
የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡
በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡
ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡

የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!

☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡
በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።

ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Nov, 18:32


"አላህ ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ቀናቸውን በወንጀል ያሳለፉ ሰዎች ወደእርሱ እንዲመለሱ ምሽት ላይ እጁን ይዘረጋል እንዲሁም ምሽታቸውን በወንጀል ያሳለፉ ሰዎች ወደእርሱ እንዲመለሱ ቀን ላይ እጁን ይዘረጋል"

#ረሱል

"ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በወንጀል በድለናል ይቅር ካላልከን እና ካላዘንክልን ከከሳሪዎች እንሆናለን!"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Nov, 17:31


ብዙዎቻችን የማናውቀው ወሳኝ ጉዳይ‼️

ጠያቂ:- በእንቅልፍ ምክንያት የጀመአ ሰላት ያለፈው ሰው ጀመአ እንዳለፈው ቢያውቅ እንኳን መስጂድ መጥቶ መስገድ አለበት ወይስ ቤቱ ይሰግዳል?

ሸይኽ ሱለይማን አር ሩሀይሊ:- "ብቻው እንደሚሰግድ ቢያውቅ እንኳን መስጂድ መምጣት አለበት ምክንያቱም ይህንን ካደረገ የጀመዓ ሰላት አጅር ይፃፍለታል።

መስጂድ ሲገባ ሌላ ጀመዓ ካገኘ ከነሱ ጋር መስገድ ግዴታ አለበት"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Nov, 18:23


"ለአላህ ብለህ ማትሰራ ከሆነ አትልፋ❗️"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Nov, 17:31


"ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ❗️"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Nov, 15:47


ባለቤት የሌለው ክፍት ቤት የማንም መፈንጫ ይሆናል❗️

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Nov, 15:03


በኢልም ጥላ ስር ጥቂት ሰዓታትን መታገስ ያቃተዉ ሰዉ እድሜ ልኩን በጃሂልነት ጥላ ስር ይሶብራል።”

ኢማሙ ሻፊዕ[ረሒመሁሏህ]

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

04 Nov, 13:31


" لِلمَوتِ فينا سِهامٌ غَيرُ مُخطِئَةٍ
مَن فاتَهُ اليَومَ سَهمٌ لَم يَفُتهُ غَدا"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Nov, 18:30


🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ  🌾

             ቁ/286

🔆 የሒጃብ ጦርነት!


🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

01 Nov, 04:29


ስትንቅ ትናቃለህ!
~
"ኩራተኛ ልክ የተራራ ጫፍ ላይ እንዳለ ሰው ነው። ሰዎችን ቁልቁል ሲያይ ትንንሽ ሆነው ይታዩታል። ግና እሱም ለሰዎች ትንሽ ሆኖ ነው የሚታየው።"

የተተረጎመ
=
የቴሌግራም ቻናል
@IbnuMunewor

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

31 Oct, 18:55


አንተስ ማንን ነው የምትወደው⁉️

አነስ ኢብኑ ማሊክ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል:- "ከእስልምና ፀጋ ቀጥሎ መልዕክተኛችን ﷺ "የትኛውም ግለሰብ አኼራ ላይ ከሚወደው ጋር ነው" ከሚለው ንግግራቸው የበለጠ የተደሰትንበት  የለም እኔ አላህን፣መልዕክተኛውን ﷺ፣አቡበክርን እና ኡመርን እወዳለሁ የነሱን አምሳያ ስራ ባልሰራ እንኳን በውዴታዬ ከነሱ ጋር እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።"(ሙስሊም ዘግበውታል:2639)

አላህ ደጋጎችን የምንወድ ያድርገን!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Oct, 17:45


የአላህ መልእክተኛ ﷺ  እንዲህ ብለዋል:–

"ከመጥፎ ሰዎች አንዱ ባለ ሁለት ፊት ነው። ያ እነዚያን በሆነ ፊት፣ እነዚያኞቹን ደግሞ በሌላ ፊት የሚመጣ የሆነው።"

📚【ሙስሊም: 5422】

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

29 Oct, 18:21


መስጂዶች የግልም ይሁን የፓለቲካ አላማዎች ማስፈፀሚያ መድረኮች አይደሉም‼️

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

29 Oct, 08:35


🍃🌸🍃
🌸🌹
🍃

🌻ሒጃብን እንዴት እንረዳው?
            •┈•⊰✿🌺✿⊱•┈•

🌼ሂጃብ ማለት ቋንቋዊ ፍቺው መከለያ፣ መጋረጃ፣ መሸፈኛ እንደማለት ነው፡፡

🌺✿⊱•┈•
አማኝ የሆነች ሴት ባዕድ ሊያየው የማይገባውን የሰውነት ክፍሏን መሸፈን እንደሚገባት የሚያመላክት ቃል ነው፡፡

🌼 ሂጃብ አላህን በመውደድ አገልጋይ ባሪያው የሆኑ እንስቶች የሚደርቡት የክብር ዘውድ ነው፡፡ በዚህ ዘውድ የወጣትነት ትኩስ ስሜት ይረታል፣ የነፍስ ወከባ ይገታል፣ ጨዋነትና ቁጥብነት ይገለፁበታል፡፡

🌺✿⊱•┈•
ይህ የክብር ዘውድ ፈውስ ላጣው በሽታ መድሀኒት፣ ለተቅበጥባጭ ነፍስ ልጓም፣ ለአመፀኛ ልብ ሰንሰለት ነው።

🌺✿⊱•┈•
እህቴ_ሆይ! ሂጃብ አይን አፋርነት፣ ጨዋነት፣ ጥንቁቅነት የመሳሰሉ የፅድቅ ባህሪያትን ያካተተ ምጡቅ ስብዕና ነው፡፡

🌺✿⊱•┈•
ማህበራዊ ትሩፋቱ የጎላ ሰማያዊ እሴት ነው፡፡ ከጨርቅ በላይ ስም፣ ከመሸፈኛ በላይ ትርጉም ያለው የእምነት ሰንደቅ ነው፡፡

🌺✿⊱•┈•
በጊዜ ብዛት ማርጀት፣ በስልጣኔ ምጥቀት መቀየር፣ መከለስም ሆነ መሻሻል የሌለበት እንደ ማለዳ ፀሀይ ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ ዘመን የማይሽረው ልብስ ነው፡፡

🌺✿⊱•┈•
ትላንት በ"ድንጋይ ዘመን" ተለብሷል፣ ዛሬም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ወቅትም እየተለበሰ እንደሆነው ሁሉ፣ በአላህ ፈቃድ በማይታወቀው ነገም ሂጃብ እንደሚለበስ የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡

🌺✿⊱•┈•
ይሁን አፍሪካ፣ አውሮፓ ይሁን ኤሲያ ሂጃብ ሂጃብነቱን አይለቅም፡፡ ክረምት ብርድ ስለሆነ የሚለበስ፣ በጋ ስለሞቀ የሚወልቅ ሳይሆን ልባዊ እምነትን ዘወትር በገቢር ማሳያ፣ የኢስላማዊ ማንነት መገለጫ ነው፡፡

                 ┈•⊰✿🌺✿⊱•┈
#መልዕክት
#ሒጃብ
#ኒቃብ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Oct, 08:06


ጣፋጭ ኩርኩም
~
ህንዳዊ ሃኪም ነው። ፂሙ ከደረቱ ደርሷል። አንድ ፂሙን የላጨ በቁርኣንና ሱና ላይ የጠለቀ እውቀት ያለው የአዝሀር ሊቅ ጋር ተገናኘ። ህንዳዊው ስለ ፂም ጠየቀው።

የአዝሀሩ ሊቅ፡ "ፂም ማሳደግ የፈፀመው የሚመነዳበት፣ የተወው የማይቀጣበት ሱና ነው" ብሎ መለሰለት።

ህንዳዊው ሃኪም፡ "እኔ ምንም እንደምትል አላውቅም። ግን የአላህ መልእክተኛ እንደኔ ናቸው? ወይስ እንዳንተ? " አለው።

አዝሀሪዩ ፡ "አይ እንዳንተ ናቸው" ብሎ መለሰ።

[ሸርሑል ሙሐረር፡ 114]

* አንዳንዱ በእውቀት ካንተ ቢያንስ እንኳ አሻራው እድሜ ልክህን የማይጠፋ ቁንጥጫ ይሰጥሃል።
እይታህ ቢለይ እንኳ ከፍ ያለውን መምረጥ ላይ አይንህን አትሽ።
{ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِی هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِی هُوَ خَیۡرٌۚ }
"ያንን እርሱ ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ እርሱ በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን?" [አልበቀረህ፡ 61]
=
© ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Oct, 19:05


ለልብ ባለቤቶች ሁሉ‼️

"ለሰዎች ያላቹ ጥላቻ ፍትህን እንድታጓድሉ አያድርጋቹ"(ማኢዳህ :8)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Oct, 07:31


ተጠንቀቅ! ደካማ አያልቅስብህ
~
በጉልበትህ፣ በስልጣንህ፣ በወገንህ፣ በሃብትህ፣ ... ተማምነህ ሰዎችን አትግፋ። "ጌታዬ! እኔ አቅም የለኝም፣ አንተ ፍረደኝ!" ብሎ ሰው ካለቀሰብህ ወላሂ ወዮልህ! ያኔ እርቃንህን ብቻህን ከአላህ ፊት ለምርመራ ስትቀርብ ምን ይውጥሀል?! ያኔ ዛሬ የተመካህበት ጉልበት ይከዳሀል። ያኔ ዛሬ የጠገብክበት ስልጣን ያዋርድሃል። "ምነው በቀረብኝ?!" ትላለህ። ያኔ ዛሬ የተመካህበት ዘመድና ወገን ጥሎህ ይሸሻል።
{ فَإِذَا جَاۤءَتِ ٱلصَّاۤخَّةُ (33) یَوۡمَ یَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِیهِ (34) وَأُمِّهِۦ وَأَبِیهِ (35) وَصَـٰحِبَتِهِۦ وَبَنِیهِ (36) لِكُلِّ ٱمۡرِئࣲ مِّنۡهُمۡ یَوۡمَىِٕذࣲ شَأۡنࣱ یُغۡنِیهِ (37) }
"አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ ከእናቱም ከአባቱም፤ ከሚስቱም ከልጁም እንዲሁ። ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁነታ አልለው።" [0በሰ፡ 33-37]
=
© ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Oct, 18:48


💦የሩቅ መንገደኛ💦‼️

ገና  ሳትፈጠር ዱኒያን ሳታስበው፣
ሁሉም ነገር አልቆ ተላልፎ ውሳኔው፣
ምን ያዘናጋሃል  ለዛ ለወዳኛው።⁉️
💦💦💦💦💦💦💦💦💦
የሩቅ መንገደኛ  ስንቁን ይሰንቃል፣
ከመጥፎው እርቆ  በመልካም ይኖራል፣
ስንቁ እንዳይበላሽ ይወጣል ይወርዳል፣
ደሞ እንዳያልቅበት በጣም ይሰስታል፣
ሌላም ለማገኘት  እጅጉን ይለፋል፣
              🛍🛍
እኛግን እረሳን  ያንን የሩቅ ጉዞ፣
ወደ ዱኒያ ህይወት አይናችን አማትሮ፣
ምኑንም ሳናውቀው ሁሉም ተቀይሮ፣
ሀይ የነበረው ሰው  ሙታን ሲሆን ዙሮ፣
አይናችን እያዬ ልባችን ታውሮ፣
ህይወት መግፋት ሆነ በጨለማ ኑሮ፣
በደመነፍስ ሆነ  የጭቃላይ ኑሮ።

የሩቅ መንገደኛ በጊዜ ተነስቶ፣
ሰአቱን በአግባብ ከፋፍሎ ከፋፍሎ፣
መዋያ ማደሪያ ስፍራውን አስቦ፣
ይጓዛል በጊዜ ህይወቱን አስውቦ፣
ምን ያስተክዘዋል ስንቁን  አስቀድሞ።
የሩቅ መንገደኛ መሆኑን ተረድቶ።

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Oct, 17:38


"ወደ አላህ ተመልሳቹ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ያለ ምንም በደል የምትመነዳበትን ቀን ፍሩ።"
(አል በቀራህ : 281)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Oct, 18:06


"እስልምና ልቡ ውስጥ ያለውን ቦታ ማወቅ የፈለገ ለሰላት ያለውን ቦታ ይመልከት!"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

22 Oct, 18:44


የመልዕክተኛው ﷺ ሱና ላይ ባለህ ጥንካሬ ልክ አላህ ይወድሀል‼️

"አላህ አንድን ባሪያ ሲወደው ጅብሪልን እከሌን ወድጄዋለሁ እና ውደደው ይለዋል ጅብሪልም ይወደዋል ከዛም ጅብሪል ሰማይ ውስጥ  "አላህ እከሌን ወዶታልና ውደዱት" ብሎ ይጣራል ሰማይ ላይ ያሉ መላኢካዎች በሙሉ ይወዱታል በምድርም ላይ ተቀባይነት እንዲያገኝ አላህ ያደርገዋል።"

ረሱል ﷺ

አላህ ከተወዳጅ ባሮቹ ያድርገን

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

20 Oct, 18:33


አላህ በወንድነታቸው የመሰከረላቸውን እውነተኛ ወንዶች ማየት ከፈለግክ ከአዛን በኋላ ብቅ በል!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

20 Oct, 10:47


ለሀቅ እንቅፋት ለመሆን አይደለም መውጣቱ አጠገቡ መቆሙ እራሱ የሚከብድ ተራራ የሆኑ ለባጢል ጊዜ ግን ተስተካክሎ የተነጠፈ ምንጣፍ የሆኑ፤ የፍትሐዊነትን ጭምብል ያጠለቁ ዳሩ ግን ፍትሀዊነት ምን እንደሆነ ያልተማሩ ስንት እና ስንት ጉዶች አሉ

ወይ ሀቅን የበላይ ያላደረጉ ወይም ደግሞ ባጢልን ያልሰበሩ መኖራቸውም አለመኖራቸውም ያው የሆኑ ገራሚ ፍጥረቶች ❗️

አላህ ሂዳያ ይስጣቸው

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

19 Oct, 18:23


«ደህና እደሩ» ብሉ የተኛ ሁሉ በርግጥ የተኛ ይመስላችኋልን?! ዉሸት ነው።ዱንያ ስንቱን አድክማለች መሰላችሁ።

አንዳንዱ ዓፊያ ርቆት ይገላበጣል፣ሌላዉን ትዝታ ወስዶት ያንገላተዋል፣አንዳንዱን ናፍቆት ወጥሮ ትያስከንፈዋል፣ሌላው ብቸኝነት ወስዶ ያስባንነዋል፣ትራስ ላይ ያረፈ ጭንቅላት ሁሉ አይተኛም፣ያረፈ ገላ ሁሉ አያርፍም፣የነገ ዉሎው የሚያሳስበው አለ፣የወደፊት ዕጣወ የሚያስጨንቀው ብዙ ነው፣የሁኔታዉን መጨረሻ የሚያሰላስል በርካታ ነው፣የዕዳ መዓት የሚያስተክዘው መዓት ነው፣የተጋደመ ሁሉ አይተኛም።

ጨለማ ብርድልብስ ነው። በዉስጡም  የሚወራ ነገር ጉድ ነው።ምሽት ፀጥታ ነው፣ የናፍቆት ጓዙ በርካታ ነው።

ወዳጄ ሁሉን ነገር ነፍስህን ለፈጠራት ጌታ አስረክበህ ተኛ።ከተሸከምነው ይከብደናል፣ ለሱ ስንሰጥ ግን ይቀለናል።

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

19 Oct, 05:56


ለዱኒያ ከልክ በላይ የሚጨነቅ ሰው ለአኺራህ ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖረውም።

قال مالك بن دينار رحمه الله :

بِقَدْرِ مَا تَحْزَنُ لِلدُّنْيَا فَكَذَلِكَ يَخْرُجُ هَمُّ الْآخِرَةِ مِنْ قَلْبِكَ، وَبِقَدْرِ مَا تَحْزَنُ لِلْآخِرَةِ فَكَذَلِكَ يَخْرُجُ هَمُّ الدُّنْيَا مِنْ قَلْبِكَ ".

📖[الزهد لابن أبي الدنيا(٥٠)].

¶ ማሊክ ኢብኑ ዲናር አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ:-

ለዱኒያ በምታስበው በምትጨነቀው ልክ  ለአኺራህ የምትጨነቀው እና የምታስበው ከልብህ ይወጣል። 
ለአኺራህ በምትጨነቀው እና በምታስበው ልክ ደግሞ የዱኒያ ሀሳብና ጨንቀት ከልብህ ይወጣል

📖[አዝሁድ ሊኢብኒ አቢ አል-ዱንያ (50)]።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Oct, 19:06


መስገድ እኮ አልቻልንም!
.
አሰላምተን ሳንጨርስ ሁለት ሶስት ሰዎች ተነስተው ይጮኻሉ ... እንደየመስጅዱ የሰው ብዛት በየሰላት ወቅቱ ተነስተው የሚለምኑትም መጠን ይለያያል ... መዘከርና ኢስቲግፋር ቀርቶ በየሰላቱ የነሱን የውሸት የመከራ መአት መስማት ግድ ነው ... አንድ ወይ ሁለት ረከአ ያመለጠውማ ምንም ኹሹዕ ሳይኖረው ውሸት ነው እውነት እያለ የሚሰማውን ያጠነጠናል ...
.
ልፍለፋቸውን ሳይጨረሱ ሰው እንዳያመልጣቸው በየሰው ትከሻ እየተረማመዱ እየጮኹ ይወጣሉ ... በሩን እንቅ አርገው ይዘው በየቆሙበት ይቀጥላሉ ... ይሄ የየቀን የየሰላት ሰአቱ ትርኢት ነው ... በየመስጅዱ ስንሄድ ሌላ መስጅድ ያየናቸው አጭበርባሪዎች በተመሳሳይ ወይ ሌላ ታሪክ ሲያጭበረብሩ እናያለን ...
.
ሲበዛብንና ይዘን ስንጠይቃቸው ገና በቀዳሚ ንግግራቸው ውሸታም መሆናቸው ይረጋገጣል ... ግማሾቹ አጫሽ ከፊሎቹ ቃሚ አንዶንዶቹ ደሞ ጠጪም ናቸው ... የሌለባቸውን በሽታ የሚያስመስሉ ... ያልኖረባቸውን አካል ጉዳት ወይም ያለውን የሚያጋንኑ ይዘናል ... መስጅድ ውስጥ ሰክረው ከሚለምኑ እስከንሙተነቂብ ክርስቲያኖች አግኝተናል
.
ይህ መስጅድ በአጭበርባሪዎች እንዲረበሽ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ኑሮ ያደከማቸው ለፍቶ አዳሪዎችም በቀላሉ ገንዘብን በዚህ መልክ ማግኘት እንዲመኙ የሚያደርግ ... ትውልዱ በሚቀርቡት የውሸት ታሪኮች ተስፋ እንዲያጣ የሚገፋና ... ትክክለኛ ችግረኞች እንዳይረዱ የሚጋርድም ጭምር ነው ...
.
ችግሩ አንድ መስጅድ ላይ ተይዘው ሲለቀቁ በነፃነት ሌላው ጋር ሂደው በተመሳሳይ መንገድ ይቀጥላሉ ... እነዚህን ማጋለጥ ግድ ነው ... ቸግሮት ይሆናል ለምን ፊቱ ይታያል የሚሉ ቅቤ አንጓቾች ግን አደብ ሊይዙ ይገባል ... አስደፋሪዎቻችን እነዚህ ናቸው

© Bin Ali

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Oct, 14:01


የተፍሲር ደርስ አለ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

18 Oct, 06:17


💡የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

🌴«የጁምዓ ዕለት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ፤ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ፤ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል።»

📚 (ቡኻሪ  ዘግበውታል)

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

17 Oct, 17:31


"የዘነጋነው ቀን❗️
~
ከየትኛውም አካል ጋር በየትኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ቢኖር "መረጃ አይቀርብም፣ ሰው አያውቅብንም" ብለን በደል ከመዳፈር ልጠነቀቅ ይገባል። ዛሬ ላይ የጠላነውን ሰው በሃሰት ጭምር ከሰን ብናሸማቅቅ፣ ውንጀላችንን እውነት አስመስለን ሰዎችን ብናሳምን፣ ተበዳይን በዳይ አስመስለን ብናቀርብ፣ ክብር ብናጎድፍ፣ ንብረት ብንወስድ፣ ... ነገ በቂያማ ቀን ሁሉን አዋቂው ጌታ ዘንድ እንቀርባለን። ወዮ ለኛ ያኔ! ያኔ የገዛ አካላችን በኛ ላይ ይመሰክራል። ያኔ ቅጥፈት ያዋርዳል። ያኔ
{وَقَدۡ خَابَ مَنِ ٱفۡتَرَىٰ}
"የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ።" [ጣሀ፡ 61]
ያኔ የዱንያ በደል ኸይር ስራዎችን እንደ እሳት በልቶ ለፀፀትና ለኪሳራ ይዳርጋል።
{وَقَدۡ خَابَ مَنۡ حَمَلَ ظُلۡمࣰا}
"በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" [ጣሀ፡ 111]

የዛሬ ክፋት የነገ ውርደት እንደሚያስከትል አውቀን በጊዜ እንወቅበት። ዱንያ ላይ ምስክር ያጣ ስንት ባለ ሐቅ አለ?! እንባውን አዝርቶ፣ ውስጡ እሳት ተዳፍኖ በደሉን ለአላህ የሰጠ፣ ፋይሉን ወደ ኣኺራ ያሻገረ ስንት ምስኪን አለ?! በዳይ እንደ ተበዳይ እየጮኸ ዝምታን የመረጠ ስንት ተበዳይ አለ?! ግና በከፋ መልኩ ሂሳብ ሳይወራረድ በከንቱ የሚቀር ሐቅ የለም። ያኔ ዳኛው ውስጥ አዋቂው አላህ ነው። አገሩ ተቅዋ እንጂ ብልጠት የማያዛልቀበት አገር! ጊዜው ደግሞ የዱንያ ብልጠትና ሴራ የማያዋጣበት አስፈሪ ጊዜ! ይህን ቀን መዘንጋታችን ነው በበደል ባህር ውስጥ እንድንዋኝ የሚያደርገን።
አልአስመዒይ - ረሒመሁላህ - አንዲት አዕራቢያህ ከሆነ ሰው ጋር እየተሟገተች እንዲህ ስትለው ሰማኋት ይላሉ፦
"አላህን ፍራ! እወቅ! ከኋላህ ከሳሽ ማስረጃ እንዲያቀርብ የማያስፈልገው ዳኛ አለ።" [ዘህሩል ኣዳብ ወሰመሩል አልባብ፡ 4/913]"

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

14 Oct, 18:43


የተፈቀደ ተግባር ቢሆን እንኳን ሰዎች ጋር ካለህ ቦታ ጋር አብሮ የማይሄድ ከሆነ መተዉ ኢስላማዊ አደብ ነው።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

14 Oct, 10:57


ሙእሚን እንደወፍ ነው ይላሉ። ቀልቡ ንቁ ነው፡፡ ልቡ ደንዳና አይደለም ስስ ነው። ተዘናግቶ ብዙ አይቆይም።ጠፍቶ አይቀርም ይባንናል። ከአላህ አንፃር ሁሌም ሁኔታዉን ይገመግማል። አጥፍቼ፣ ተሳስቼ፣ መንገድ ስቼ ... ይሆን ይላል። ያጠፋዉን ቶሎ ያርማል። ያበላሸዉን ያስተካክላል። የበደለዉን ይክሳል።

ሙእሚን፤ አካሉ ዱንያ ላይ ቢሆንም ሀሳቡ ኣኺራ ነው። ሌቱን በሁለት ዐይኖቹ አይተኛም። ምሽቱን ራሱን ጥሎ እንደግንድ ተጋድሞ አያድርም። ቀኑን፤ በግርግር መሀልም ቢሆን ንቁ ነው። የሆነ ቀን ላይ ዱንያን እንደሚሠናበት ያውቃል። ወዴት እየሄደ እንደሆነ አይጠፋዉም። ለዚያ ረጅም ጉዞው በቂ ስንቅ የያዘ ስለመሆኑ ይፈትሻል።

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

14 Oct, 08:14


እጅግ አስደናቂ ታሪክ!
"ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ የግብረ ገብ ኪታብ ውስጥ መፃፍ አለበት!"
አቡ ዐብደላህ ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሙሳ አል– ቃዲ "- በአር-ረይ - ከተማ በሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት አ/ሂ ምክር ቤት ተገኘሁ።" ይላሉ። የሰሙት እና ያዩት አሰደናቂ ክስተት እንዲህ ሲሉ ያጫውቱናል።

"አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ለክስ ቀረበች፣ ቅርብ ሀላፊዋ (ወሊዯ) ባሏ ላይ አምስት መቶ ዲናር መህር እዳ እንዳለበት ክስ መሰረተ፣ ባልየው ግን የተባለው ብር እዳ የለብኝም በማለት ክሱን አልተቀበለም።

ዳኛውም፦ “ምስክሮችህ የት አሉ?” ሲል ጥያቄ አቀረበ።
ባልም፦ “ሁሉም እዚህ ተገኝተዋል” በማለት መለሰ።
ዳኛውም፦ ከምስክሮች መካከል አንዱን ጠርቶ፤ " "ሴትየዋ እሷ መሆኗን እንዲመለከትና ምስክርነቱ እንዲሰጥ አዘዘ።
ምስክሩም ተነስቶ፣ ሴቲቱን፦ “ተነሺ” አላት።

ባልየውም(በቅናት መንፈስ)፦ "ምን እየሰራህ ነው?" ምን ልታደርጋት ነው?! ሲል ጥያቄ አቀረበ።

የሴቲቱ ወኪል፡- "ሚስትህን በትክክል ለይቶ ያውቃት ዘንድ ኒቃቧን ከፍታ ሊመለከታት ነዋ።"

ባልየውም ለዳኛዋ ፦ " ፊቷን በፍፁም እንዳትገልጥለት! የምትለውን ጥሎሽ የማግኘት መብት እንዳላት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለ።

ሴቲቷም ክሷን ወዲያውኑ ሰርዛ፡- "ጥሎሽን አውፍ ብየዋለሁ! በዱንያም ሆነ በአኼራ ነፃ እንዳደረግኩት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለች።

ዳኛውም፡- "ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ በመልካም ሥነ ምግባር ኪታብ ውስጥ ይስፈር!" ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ።

📚ኸጢብ አልበግዳዲይ "ታሪኽ አልበግዳድ" በተሰኘው ኪታባቸው (13/55) ላይ ኢብኑል ጀውዚይ ደግሞ " አልሙንተዘም ፊ ታሪኽ አል ኡመም ወል ሙሉክ (12/403) ላይ አስፍረውታል።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Oct, 18:08


«አኼራ እየመጣች ነው፣ዱንያ ላትመለስ እየሄደች ነው።የአኼራ ልጆች ሁኑ። የዱንያ ልጆች አትሁኑ። ዛሬ ሥራ እንጂ ሂሳብ የለም። ነገ ሂሳብ እንጂ ሥራ የለም።»

ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

12 Oct, 07:50



      እኛ የት ነበርን??

  ሁለት ጓደኛሞች አብረው ከተማ ውስጥ እየዞሩ ናቸው። እና አንደኛው ወደ ትላልቅ ህንፃዎች ተመለከተና ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ጠየቀው

"ይህንን ሁሉ ሀብት ሲታደል እኛ የት ነበርን?" አለው

  ጓደኛውም "ና" ብሎ እጁን ይዞ ወደ ሆስፒታል አስገባውና
  "ይህንን ሁሉ በሽታ ሲታደል እኛ የት ነበርን?" ብሎ ጠየቀው።


👌የተሰጠን ብናውቅ የተከለከልነው የለም!!


منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

11 Oct, 14:19


ማስታወሻ❗️

ባማረ አቀራረብ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ እየተሰጠ የሚገኘው የተፍሲር ደርስ በአላህ ፍቃድ ዛሬም የሚቀጥል ይሆናል❗️

🔖 🔖"ለዓይን ብርሃን እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ለልብም ቁርኣንና የቁርኣን እውቀት ያስፈልገዋል"።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Oct, 18:52


ማንነትህን ከአላህ ቀጥሎ አንተ ነህና የምታውቀው የሰዎች ሙገሳ አያታልህ!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

10 Oct, 10:31


“ሀያል የሆነው አላህ፤ ሰለ መጨረሻው ዓለም(አኼራ) የማያውቅና ስለ ዱንያ ብቻ ምሁር የሆነን ሁሉ ይጠላል።˝
(ረሱላችን ﷺ )

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Oct, 18:29


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ

በላፍቶ ቢላል መስጂድ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ሲሰጥ ከነበረው የወንዶች የበጋ ቂርአት በተጨማሪ #ለአዲስ ተማሪዎች ከአሱር እስከ መግሪብ አላህ ካለ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚጀመር ሲሆን በዚህ ሳምንት ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል። ስለሆነም በመደበኛው(ከመግሪብ-ኢሻ) በሚሰጠው ደርስ ላይ ልጆቻቹ የማይሳተፉ ወላጆች እድሉን እንድትጠቀሙ ለማለት እንወዳለን።

⚠️ ይህ ፕሮግራም ነባር ተማሪዎችን አይመለከትም!

⚠️ የሴቶች ቂርአት እንደነበረው ከአሱር እስከ መግሪብ የሚቀጥል ይሆናል

🔗ለበለጠ መረጃ:-0967938642 ላይ ይደውሉ።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Oct, 18:40



   ልትተኛ ነው??

እንግዲያውስ………
  ጠዋት ፍራሽህ ላይ ሆነህ የፈጅር አላርም ይቀሰቅስሃል??
ወይስ ቀብርህ ውስጥ ሆነህ ነኪርና ሙንከር ይቀሰቅሱሃል? አታውቅም።

እናም፦
  ከስህተቶችህ ሁሉ ተውበት አድርገህ ተኛ!!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

06 Oct, 17:39


አንድ ቀን በድንገት (በቅፅበት) ሁሉም የዚህ ዓለም ህውከት፣ ጫጫታ፣ ረብሻ፣ ንትርክ፣ ጭቅጭቅ ብሎም ቅሬታ ቀርቶ ወደ ሌላ ዓለም የምንሻገርበት አጋጣሚ ይመጣና ይህ ሁሉ ነገር ከንቱ መሆኑ ይገለጣል። ለእዛ እለት እንስራ!!!

አቡ ዐብደላህ መሐመድ ሐሰን ማሜ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Oct, 18:55


ያልተነቃበት ጠላፊ!

የስልክ ሱስ በዚህ ዘመን ስንትና ስንት መስራት የሚችሉ ወጣቶችን ያደነዘዘ እና መስመራቸውን ያሳተ ያልተነቃበት አደገኛ ጠላፊ ነው።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

04 Oct, 08:21


ማስታወሻ❗️

ባማረ አቀራረብ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ እየተሰጠ የሚገኘው የተፍሲር ደርስ በአላህ ፍቃድ ዛሬም የሚቀጥል ይሆናል❗️

🔖 🔖"ለዓይን ብርሃን እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ለልብም ቁርኣንና የቁርኣን እውቀት ያስፈልገዋል"።

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

04 Oct, 07:33


ሙእሚን ለዘመናት በተቅዋና ደግነት የገነባው ቤቱ በኀጢአት ወረራ ሲፈርስበት አይቶ በቁጭት ቢያለቅስ ምኑ ይገርማል ።

አይገርምም ወላሂ።

እየወደቃችሁ እየተነሳችሁ ኑሩ እንጂ አደራችሁን የኃጢአትን ምቾትና ሙቀት አትላመዱ።

منقول

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Oct, 18:07


Irraa if-eegaa   ይጠንቀቁ! ያስጠንቅቁ!

የኦሮሚያ ታላቁ ዐሊም እና ሙፍቲ የሆኑት ሸይኽ አደም ቱላ ኢሬቻን አስመልክቶ የሰጡትን ምላሽ ......

«ሙስሊም ሆኖ ኢሬቻን ማክበር አይቻልም የሰይጣን ስራ ነው። የሙስሊም ባህሉ ሃይማኖቱ ነው። ኢሬቻ ነፃ ያወጣኛል የሚል ሙስሊም እምነቱ አደጋ ላይ ነው።»
[ሸይኽ አደም ቱላ ከተናገሩት]

Namni muslima tahe Ayyaana Irreechaa akka hin dhayne.

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Oct, 10:39


ታመናል በጠና!

ውጫችን ተውቦ በሱና አሸብርቆ
የሚያስደምም ሆኖ ዟሂራችን ደምቆ

ቀልብ ካልረባማ ከተቆራመደ
የድብቅን ወንጀል ከተለማመደ

ከባድ አደጋ ነው ታመናል በጠና
ፈውሱን እንፈልገው ከቁርአን ከሱና

ጀግና መስለን ውለን በቀን በጠራራ
ሌቱን ከገፋንው ከኢብሊሱ ጋራ
ምኑን ተከተልንው የነብዩን ስራ?!
ልባችን ደካክሞ ባጋንነቶች ጭፍራ!

ይብቃን አረ ይብቃ እንዲህ መዳከሩ
በድብቅ ወንጀሎች ሌት ቀን መነከሩ
መንገዱን እንጀምር በዲን በመስመሩ!!

✏️ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጁ―

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

02 Oct, 17:45


ታሪክን የማወቅ ዋና ቁምነገር ከታሪኩ ለሂወት ጠቃሚ የሆኑ ቁምነገሮችን ወስዶ መጠቀም ነው እንጂ ታሪኩን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው መሸምደድ አይደለም።

ስንት ታሪኮችን አንብበናል ወይም ሰምተናል ሳይሆን ቁምነገሩ ከታሪኩ ለህይወታችን ስንት ቁምነገር ወስደናል ነው!

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

01 Oct, 18:40


"የሚደንቀው ጥፋት ላይ የወደቁ ሰዎች እንዴት ወደቁ የሚለው ሳይሆን ከጥፋት የዳኑት እንዴት ዳኑ የሚለው ነው!"

#ያለንበት_ተጨባጭ

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

01 Oct, 11:22


📢ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም በፈዲለቱ ሸይኽ ዶ / ፈህድ ሙሐመድ አስ-ሱለይም

🕒 ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

🗓 ዛሬ መስከረም 21/2017

🕌 ሳሪስ አዲሱ ሰፈር ሒክማ መስጂድ

©: Hanif Multimedia

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

30 Sep, 18:42


#ግጥም
ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ፣
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ።

ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ፣
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ

ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥህ፣
ከቀብር ስትገባ ይታያል ጉድህ።

ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥሽ፣
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ።

#ሸይኽ #ሙሐመድ #ወሌ አሕመድ ረሒመሁላህ
  

1,724

subscribers

192

photos

64

videos