Revelation Center (apokálypsis) Angel @revelationcenter Channel on Telegram

Revelation Center (apokálypsis) Angel

@revelationcenter


ለህይወትህ የሚጠቅምህ የተፃፈልህ ሳይሆን ከተፃፈልህ ወስጥ የተገለጠልህ ነው። “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።”
— ኤፌሶን 1፥17
@Revelationcenter

Contact: My Telegram link: @Angelmiracle

Revelation Center (apokálypsis) Angel (Amharic)

ረቂቅ ቦታ (አፖካሊፕስ) አንጀልnnራሱ የህይወት ምንጭ ነው? ራሱ ምን ነው?nnረቂቅ ቦታ (apokálypsis) Angel በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠበቀህና ምንጭን ያረገለህ ተመልከት ይሆንልህ። በማወቅና በመገለጥ እንዴት ምን እርምባውን እንሰጥህ። እናመልከታለን።nnእንደሚገኙት ሴቶች ገለጹት እርምባና መገለጥ የሆኑትና የማምሁት ተስፋ የሚሆኑት ሕዝብ ሁሉ ይጠፋሉ።nnእባኮትህ በቶሎ መጀመር የሚለውን ታሪካዊ መረጃዎች ላሻሻያና ማሻሻያ ይሰጣል። የሰለባችሁን የጌታ ገንዘብ ስለማህበረሰብ መልስ እና ደራሽ እንገናኛለን።nnመልእክተኛ: የቴሌግራም ሊንክ: @Angelmiracle

Revelation Center (apokálypsis) Angel

09 Nov, 07:28


🔴ነገ እሁድ የማይቀርበት ድንቅ ጊዜ ስለሚሆን 8፡30 ጀምሮ በ ሀዋሳ Presence of God church እንገናኝ።

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

03 Nov, 19:46


🟥 Important Message📌

📣መልካም ዜና በሀዋሳ ለምትኖሩ ወጣቶች🎁🎁🎁ድንቅ የትንቢታዊ እና የትምህርት ጊዜ🇪🇹

➡️ለወጣቶች ድንቅ የሆነን መንፈሳዊ ምስጢርን የያዙ ትምህርቶችን እንዲሁም ልዩ እና ቀጣይነት ያለው ፕሮግራም አዘጋጅተን ጨርሰናል!!!

🟥በእለቱ ጥልቅ መገለጦችን እንከፋፈላለን፣በትንቢታዊ ቅባት እንገለገላለን እንዲሁም ለአይን መከፈት እና ለመንፈሳዊ ተሀድሶ በሀይል የምንፀልይ ይሆናል።

➡️ለወደፊት ህይወታችሁ የምታስቡ ከሆነ ይህ ፕሮግራም ያስፈልጋችኋል።ፕሮግራሙን ከአሁኑ ሳምንት ማለትም ህዳር 01/03/2017 የምንጀምር ሰለሚሆን በፀሎት አብራችሁን ተዘጋጁ እንዲሁም ላልሰሙ የሀዋሳ ልጆች share አድርጉላቸው።

ቦታውን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ 👇👇👇ያናግሩን

@Angelmiracle
@abinetvictor
@mintesnot_yosef

Revelation Center (apokálypsis) Angel

22 Oct, 05:30


🔴ወደ ህይወታችሁ እንዲገቡ የፈቀዳችሁላቸውን ሰዎች በማየት ለህይወታችሁ ያላችሁን ዋጋ ማወቅ ይችላል!

“ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።”
— ምሳሌ 13፥20

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

15 Oct, 15:23


🔴ራዕይ ጅማሬ እንዳለው ሁሉ መዳረሻም አለው፣ ስለዚህ ግባችሁን ካላወቃችሁ የትኛው ስፍራ ላይ ሩጫችሁ እንደሚያልቅ አታውቁም!!!

“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።”
— ሐዋርያት 20፥24

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

10 Oct, 16:57


🔴ሀሌም በአገልግሎት ህይወታችሁ ከሰዎች ጋር ፉክክር ውስጥ የምትገቡ ከሆነ ውስጣችሁ ያለውን አቅም እየገደባችሁ እንደሆነ እወቁ!!!

➡️መሉ አቅማችሁን የምትጠቀሙት ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንት ማንነታችሁ ጋር መፎካከር ስትጀምሩ ነው።

“ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥”
— ፊልጵስዩስ 3፥13

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter
Join&share

Revelation Center (apokálypsis) Angel

08 Oct, 07:36


🔴ራዕይህ እንቅልፍ የማይነሳህ ከሆነ እና ማንነትህን እንድትቀይር ካላደረገህ የራዕይህን ትክክለኛነት አረጋግጥ!!!

2ኛ ቆሮ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።
²⁸ የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

04 Oct, 18:26


🟥የመጨረሻው ዘመን መልዕክት
መሉውን አድምጡት

➡️ይህ ትንቢታዊ መልእክት ከዛሬ 60 አመት በፊት በ ነብይ ዊሊያም ብራንሀም ስለመጨረሻው ዘመን የተተነበየ ነው!!!

🔴 Kamala Harris የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች ለሀሰተኛው መሲህ መገለጥ እና ለታላቁ ጥፋት ስለምትሰራ እግዚአብሔር ተጨማሪ ነብሳት እንዲድኑ ትንሽ ጊዜን እንዲጨምልን ፀልዩ!!!

ለዶናልድ ትራምፕ እና ለቤተክርስያን እግዚአብሔር ዳግም እድል እንዲሰጥ ፀልዩ🙏🙏🙏

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

25 Sep, 17:33


😷ህመምን ሳይሆን በሽታን ጥሉት!

🔴የህመም ዋና አላማ በሰውነታችሁ ውስጥ ለሚፈጠሩ በሽታዎች ማንቂያ ደውል ነው።

➡️ህመም የሌላቸው በሽታዎች ያለምልክት ሰውን የመግደል አቅም ስላላቸው እጅግ አደገኞች ናቸው!!!

🔴ነገር ግን አብዛኛው ሰው ከበሽታው ይልቅ ከህመም ስሜቱ ነው መገላገል የሚፈልገው ነገር ግን ህመም በሽታው የእኛ ሰውነት ውስጥ ገብቶ እንዳይገይለን እና መድሀኒትን እንድንጠቀም ማንቂያ ደውል ነው።

🙏ምልክት እና ህመም ከሌለው ጥፋት በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቃችሁ ሁኑ

“ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።”
— መዝሙር 19፥12

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

23 Sep, 05:29


🟥 የዕለቱ ቃል

ምሳሌ 3
³ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።
⁴ በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter
Join& share

Revelation Center (apokálypsis) Angel

21 Sep, 19:03


🟥አስቸኳይ መልዕክት🔥🔥🔥

🔴ሰላም የ Revelation center ቤተሰቦች እስካሁን በተለያዩ ማስታወቂያዎች ምክንያት መልዕክቶችን ለመልቀቅ አልቻልንም ነበር።
ነገር ግን ከአሁን ቦሀላ ማስታወቂያዎች እንደማይኖሩ እና መልዕክቶችን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ ለእናንተ የምናደርስ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን🙏🙏🙏

ስለዚህ በየጊዜው የሚለቀቁ መልዕክቶች እንዳያመልጧችሁ notification ማብራት እንዳትረሱ።እንዲሁም መልዕክቶችን ለምታውቋቸው ሰዎች share በማድረግ አብራችሁን የእግዚአብሔርን ስራ ስሩ🙏🙏🙏

➡️በመንፈሳዊ ህይወታችሁ ማደግ ከፈለጋችሁ ትክክለኛው ቻናል ላይ ናችሁ

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

24 Aug, 19:32


🟥መንፈሳዊ ህይወታችሁ ልክ እንደ COVID ጊዜ መሆን ያልቻለው ለምን ይመስላችኋል?

🔴የአብዛኛዎቻችን ህይወት እንደዚህ ስለሆነ እና ብዙ ሰዎችንም ስለተመለከትኩኝ ነው ይህን ሀሳብ ያነሳሁላችሁ።

➡️በ COVID ግዜ የነበረው መንፈሳዊ ረሀባችሁ፣የመፀለይ እና ቃሉን የማጥናት ጥማታችሁን ምን ወሰደው?

እስቲ ለጥቂት ጊዜ አስቡት እና ራሳችሁን ጠይቁት...ከዛም ቦሀላ የድምፅ መልዕክት እልክላችኋለው🙏

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

12 Aug, 08:31


ትንቢታዊ ቃል
ሰኞ ነሐሴ 12

በዘመን የሸመገለው

ዳንኤል 7:9
፣ ዙፋኖችም እስኪወድቁ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፥ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጠጕር ነበረ፥ ዙፋኑም እንደ እሳት ነበልባል ነበረ። መንኮራኩሮቹም የሚነድድ እሳት ናቸው።

የሚያጋጥሙህ ችግሮች ሁሉ ከእግዚአብሔርን ኃይል የሚበልጡ ለመምሰል እየሞከሩ ነው።ነገር ግን አሁንም ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ሁኔታ የለም። እግዚአብሔር የነበረው ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ነበር፣ እና ከጌታ ኢየሱስ በፊት ምንም አዲስ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ነገር የለም።ያላችሁበት ሁኔታ ምንም ያህል የተወሳሰበ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር አሁንም የበላይ ቢሮ ሆኖ ይኖራል።

ዳንኤልም በዘመናት የሸመገለው ብሎ ጠራው።ይህ ማለት ዘመኑ እንኳን እንደሸመገለ ያውቃል ማለት ነው። እሱን ስታመልኩት ትላንት የተቀረጸውን ጣኣት ሳይሆን ከጥንት ዘመን በፊት የነበረውን አምላክ እያመለካችሁ ነው። ከውስጥም ከውጭም ያውቃችኋል; ሁኔታቹ ለእርሱ አዲስ ነገር አይደለም።

እግዚአብሔር በራሱ ዙሪያ ተቀምጧል። ያ በሰውነታችሁ ውስጥ ያለው ህመም፣ ወይም በስራ ቦታችሁ ወይም በትምህርት ቤታችሁ ያለው ሁኔታ፣ ከስልጣኑ ጋር ሊወዳደር አይችልም። የጌታ እጅ በአናንተ ላይ ነውና በሁሉም የሕይወታችሁ ዘርፍ ላይ ለውጥን ተመልከቱ። ክብር!!!

ትንቢታዊ አዋጅ

አምላኬ በዘመናት የሸመገለ ነው። እሱ ከእኔ ሁኔታ በፊት ነበረ። ታላቁን እኔ ነኝ ያለውን አምላክ አመልካለሁ። በህይወቴ ያለው ነገር ሁሉ በኢየሱስ ስም ለጥቅሜ ይሰራል። ኣሜን!!!

ተጨማሪ ጥናት ራእይ 22:13 የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ ጥቅስ፡ ኤርምያስ 18-22


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

11 Aug, 05:08


🔴 Before the double portion anointing there's always a rejection and separation.

🟥ሁለት እጥፍ ቅባት ከመምጣቱ በፊት ሁልጊዜ መገፋት እና ከግርግር መሀል መለየት ይኖራል።

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter
Join&share

Revelation Center (apokálypsis) Angel

10 Aug, 06:14


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
ቅዳሜ

በቃሉ ውስጥ የሚያሸንፍ ኃይል

“እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።”
  — ሐዋርያት 19፥20

ቀንና ሌሊት ሰዎች በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ውስጥ ድልን ይፈልጋሉ። ለዛ ሁኔታ በሙያህ፣በቢዝነስህ ወይም በትዳርህ ውስጥ እንቅልፍ አልባ ምሽቶች እየሰጠህ ላለው ሁኔታ መልስ ወይም መፍትሄ እየፈለግህ ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን ድሉ ከየት ይመጣል? ዛሬ መልሱን ታገኛለህ።
የዛሬው መጽሃፋችን በጣም ጥልቅ የሆነ ነገር ይናገራል። ያደገውና ያሸነፈው ሐዋርያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አስተውል:: በቃሉ ውስጥ የበላይ ኃይል አለ! በቃሉ ራስህን ሙላ፣ እና በአንተ ያለው ቃል ሲያሸንፍ ትመለከታለህ። ዛሬ እግዚአብሔር በቃሉ ድልን እየሰጣችሁ ነው። በመንፈሳችሁ ውስጥ የሰማችሁት እና የያዛችሁት የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የድል ኃይል ሆኖ ይበቅላል!

ትንቢታዊ አዋጅ
የእግዚአብሔር ቃል በእኔ በኩል ያሸንፋል። እኔ የእርሱ ሞገስ እና ክብር ነኝ፣ በኢየሱስ ስም።
ተጨማሪ ጥናት ዕብራውያን 4፡12
የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ ጥቅስ፡ ኤርምያስ 10-13

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

09 Aug, 08:28


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
አርብ

እውነተኛ ነፃነት

“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።”
  — ዮሐንስ 8፥32

የአምላክን ቃል እውነት አለማወቅህ በባርነት እንድትቆይ እና የዓለም ሰዎች የሚሰቃዩትን ተመሳሳይ መከራ እንድትቀበል ያደርግሃል። መፅሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እውነት ነፃ ያወጣችኋል ይላል። ያወጣችዃል!በዓይነ ህሊናህ የተዘጋ ጠርሙስ ውስጥ ያለች ዝንብን ሳል; የጠርሙሱን ክዳን ከከፈትከው ነፃ ታወጣዋለህ, ጠርሙሱን ግን ገልብጠህ ካስቀመጥከው በራሱ ገፍተህ ነጻ እያደረግከው ነው ማለት ነው ይህ ማለት በቀደመው ስፍራ ብትፈልገውም አታገኘውም።
-የእግዚአብሄርን እውነት ማወቅ ከጠላት መዓት እና መጨናነቅ ወደ ውጭ እንደሚያወጣህ ኃይል ገፍቶ ያወጣሀል።
ይህ የምታነበው ቃል ሙሉ በሙሉ ነፃ ያወጣሃል። በህይወታችሁ ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች ለዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ምላሽ እየሰጡ ነው። ሕይወታችሁ እንደ ወተትና ማር በነፃ ይፈስሳል። በኢየሱስ ስም ገደብ በሌለው የአጋጣሚዎች ግዛት ውስጥ ተገፍታችዃል።

ትንቢታዊ አዋጅ
እኔ የጌታ የተባረኩ ልጅ ነኝ። እግዚአብሔር የራሴ ጋሻና መከታ ነው። በኢየሱስ ስም ሰማያዊ ጥበቃ እና ከለላ አለኝ። ኣሜን።
ተጨማሪ ጥናት:- የዮሐንስ ወንጌል 8፡36
የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ ጥቅስ፡ ኤርምያስ 7-9


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

08 Aug, 08:06


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
ሐሙስ

ጠንካራ እና ተጣጣፊ

መዝሙር 92
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
¹³ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።

የአየር ንብረትን በተመለከተ የሊባኖስ ዝግባ አስገራሚ ነው። ከባድ እና ሀይለኛ አውሎ ንፋሶች አንድን ሀገር ሲያቋርጡ በህንፃዎች እና በዛፎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ያስከትላል። በዚህ ሁሉ ግን አንድ የተለየ ዛፍ አለ የሊባኖስ ዝግባ የሚባል, ይህ ዛፍ ከአውሎ ንፋሱ በጣም ከባድ ከተባለው እንኳን ሳይቀር ይተርፋል።
➡️የሊባኖስ ዝግባ በነፋሱ ጊዜ አጎንብሶ ነፋሱ ባለፈ ጊዜ ወደ መጀመሪያ ስፍራው ይመልሳል። ነገር ግን የሚያጎነብሰው ደካማ ስለሆነ ሳይሆን ተጣጣፊ ስለሆነ ነው። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጻድቅ አድርጎሃል ጻድቃንም እንደ ሊባኖስ ዘንባባ ናቸው። ስለ አንተ ክፉ ቢናገሩም ሆነ ቢጽፉ በቀላሉ ጎንበስ ብለህ ወደ ነበርክበት ቦታህ ትመለሳለህ። ልክ እንደ ሊባኖስ የዘንባባ ዛፍ ጠንካራ እና ተጣጣፊ ነህ።

ትንቢታዊ አዋጅ
ክርስቶስ ጽኑ መሠረቴ ነው፥ እኔም አልናወጥም! ንግዴን፣ ትዳሬን፣ አገልግሎቴን ወይም የእኔን የሚመለከት ማንኛውንም ማዕበል ወይም ንፋስ አያናውጠውም፣ በኢየሱስ ስም!

ተጨማሪ ጥናት:- 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16-18 የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ ጥቅስ፡ ኤርምያስ 4-6


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

07 Aug, 16:19


🔴ያለ ምክንያት ጥለዋችሁ ከሄዱ በምክንያት ተመልሰው እንዲመጡ አትፍቀዱ!!!

➡️ለራሳችሁ እና ለህይወታችሁ ክብር ይኑራችሁ።

#Ambassador Uebert Angel

Revelation Center (apokálypsis) Angel

07 Aug, 09:51


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
ረቡዕ

የማንነት ቀውስ

“እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።”
  — ዮሐንስ 1፥13

እየኖርን ያለነው ትልልቅ ወንዶች እና ሴቶች እንኳን ምንም ነገር ማስተናገድ በማይችሉበት ዓለም ውስጥ ነው ምክንያቱም ገና ሳይወለዱ የጠፉ ሥጋዊ አባቶቻቸውን በመፈለግ ላይ ናቸው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ወንዶች እና ሴቶች በዚህ ምክንያት ብዙ የስሜት ጭንቀት ይሰቃያሉ! የዘር ሐረግህን የማወቅ ፍላጎት ለሕይወት አስጊ ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አስፈላጊ ነው። ጥቂቶች የተጠሙት ለሆነ አካል የመሆንን(belongingness)ብቻ ነው፣ ቢያንስ የአንድ የተወሰነ ክፍል ወይም ቡድን አባል ለመሆን ይፈልጋሉ።
ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ከላይ የተወለድን የእግዚአብሔር ዘር ነን ይላል። ትክክለኛው ማንነታችን ይህ ነው። አስታውስ፣ ኤርምያስ እንኳ በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ከመፈጠሩ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚታወቅ በእግዚአብሔር እንደተነገረው አስታውስ፣ ይህም ማለት ወደ ሥጋ ቤተሰቡ ከመድረሱ በፊት በሌላ ግዛት ውስጥ አስቀድሞ ይኖር ነበር።
➡️እናንተ የእግዚአብሔር ዘር ናችሁ እና የእሱ DNA በእናንተ ላይ ታትሟል። አንተ የልዑል ዘር ስለሆንክ ምንም እና ማንም ሊያግድህ አይችልም. ውጣና አሸንፍ። በኢየሱስ ስም ወተትና ማር ያንተ ናቸው!

ትንቢታዊ አዋጅ
እኔ ከላይ የተወለድኩ የኢየሱስ ክርስቶስ አምባሳደር ነኝ። ምንም እና ማንም አያግደኝም! ማር እና ወተት በኢየሱስ ስም የእኔ ናቸው። ኣሜን።

ተጨማሪ ጥናት:- ኤርምያስ 1:5 የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ መፅሐፍህ፡ ኤርምያስ 1-3


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

06 Aug, 07:18


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
ማክሰኞ

ማታለል(Deception)

“ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”
  — ማቴዎስ 24፥24
ማታለል ከአንድ ሰው ለመጠቀም ሲባል እውነትን መደበቅ ነው። ኢየሱስ በመጨረሻው ቀን፣ በፍጻሜው መጨረሻ ማለት ነው፣ ማታለል ይስፋፋል ብሏል። ስለዚህ ጠላት የሚጠቀምበትን ትልቁን የማታለያ መግቢያ በር ማወቅ አለብን።
ኢየሱስ ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ተጠበቁ ሲል ተናግሯል፣ ይህ ማለት የማስተማር አገልግሎት ዲያብሎስ ብዙዎችን ለማታለል የሚጠቀምበት በር ስለሆነ ነው። የምታዳምጡት የትምህርት አይነት ወይ ለማታለል ታቅቀደው የተዘጋጁ አልያም ከማታለል ማምለጫ የሆኑ ናቸው።
-ማንንና ምንን በጥሞና ማዳመጥ እንዳለባችሁ ምረጡ ምክንያቱም መታለል ወይም አለመታለል የሚወስነው በዚህ ነው። ከመታለል የማምለጥ መድሀኒቱ ደግሞ እውቀት ነው። ቃሉን በማንበብ እና በትክክለኛው ትምህርት ስር በመቀመጥ እውቀትን አግኙ። ይህን ትንቢታዊ መልእክት ስታነቡ ብርሃን ወደ መንፈሳችሁ እየመጣ ነው ስለዚህም ደግሞ ዲያብሎስ ሊያታልላችሁ ከቶ ቀላል አይሆንለትም። እራሳችሁንን ለቃሉ አደራ ስጡ እና ለራሳችሁ ለማወቅ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።
ሰባኪውን ብቻ አትጠብቁ; በራሳችሁ አንብቡት እና ከተሰበከ በኋላም እንደ ቤርያዎች ሁኑ እናም እውነት ስለመሆኑ በራሳችሁ አረጋግጡ።

ትንቢታዊ አዋጅ
በውስጤ ያለው የጌታ ቃል ብርሃኔ ነው። በማታለል ወይም በሽብር አልሰናከልም። በኢየሱስ ስም በመንፈስ ተመርቻለሁ። ኣሜን።

ተጨማሪ ጥናት :-መዝሙረ ዳዊት 119:130
የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ መፅሐፍህ፡- ሶፎንያስ


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

05 Aug, 10:17


ይህ ለእናንተ ትንቢታዊ ቃል ነው።
ሰኞ ነሐሴ 5

ማን ነገረህ?

“እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?”
  — ዘፍጥረት 3፥11

የስብዕና፣ የባህሪ ወይም የእምነት መሰረት መረጃ ነው። ይህ መረጃ እናንተን ለውድቀት ወይም ለስኬት የማዘጋጀት ኃይል አለው። ዲያብሎስ ሲመጣ እናንተን ለመያዝ መረጃን ይጠቀማል እና እሱን የሚያባርረው በመረጃ ማግኛ የተገኘ ብርሃን ነው።
ጠላት አዳምና ሔዋንን በጎበኘ ጊዜ ፍሬውን እንዲበሉ በመረጃ በማሳመን እርቃናቸውን አጋልጧል። እግዚአብሔር በወረደ ጊዜ እንዴት እርቃናቸውን እንደ ሆኑ ሳይሆን ማን ያንን እንደነገራቸው ነው የጠየቃቸው።
የትኛውም መረጃ ወይንም እውቀት ወደ እናንተ ለሚደርስበት አስተማማኝ ስፍራ ይኑራችሁ። ይህ ማለት እርቃንን ለማጋለጥ ታስበው የተዘጋጁ አንዳንድ ስብከቶች እና መጽሃፎች አሉ።
እግዚአብሔር ተቤዥቶሃልና ከእንግዲህ በአንተ ላይ ነውር የለም። ኃጢአተኛ ወይም ደካማ መሆንህን ማን ነገረህ?  ይህ ከዲያብሎስ የመጣ መረጃ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ የተመረጠ ትውልድና አዲስ ፍጥረት ናችሁ። ስለእናንተ ያሉ ነገሮች ሁሉ አዲስ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫዎች እንደሆናችሁ በዚህ አዲስ ግንዛቤ ዛሬ ውጡ። ምርጥ የተመረጠ ትውልድና የንጉስ ካህናት ናችሁ። በእናንተ ውስጥ ምንም አይነት ሁኔታ እና ጉድለት ቢኖርባችሁ ስልጣን ግን አላችሁ።

  ትንቢታዊ አዋጅ
አእምሮዬ የሚለወጠው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ነው። በእግዚአብሔር ቃል እውነት ከፍ ከፍ ብያለሁ፣ እና አሁን እኔ ማን እንደሆንኩ በኢየሱስ ስም አውቅያለሁ።

ተጨማሪ ጥናት:- ሮሜ 12፡2
የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና የዛሬ መጽሐፋችሁ፡- 2ኛ ነገ 22-23፣ 2ኛ ዜና 34-35

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

27 Jul, 12:08


🔴 በአገልግሎት ዘመናችሁ 3 አይነት ሰዎች ያጋጥማችኋል...

1, እናንተ ላይ ባለው ቅባት የማያምኑ ወይም የማይቀበሉ ነገር ግን እናንተን ላለማስከፋት እንደሚያምኑ የሚያስመስሉ።

2,እናንተ ላይ ያለውን ቅባት የሚጠራጠሩ ወይም ተደጋጋሚ ማረጋገጫን የሚሹ።

3,እናንተ ውስጥ ባለው ቅባት በሙሉ ልባቸው እርግጠኛ የሆኑ፣በሰው ፊት ስለእናንተ በድፍረት መናገር የሚችሉ እና ስለእናንተ ዘወትር የሚፀልዩ ናቸው።

➡️ አንድ እና ሁለት ኖሩ ወይም ሄዱ ምንም አይቀንስባችሁም...ሶስተኛዎች ግን ከእግዚአብሔር የተሰጧችሁ ስጦታ ስለሆኑ በቁጥርም በጣም ትንሽ ስለሆኑ በደንብ ጠብቋቸው፣ፀልዩላቸው እናም በእናንተ ላይ ያላቸውን እምነት በተግባር አሳዩላቸው!!!

ሉቃስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ኢየሱስም ይህን ሰምቶ በእርሱ ተደነቀ፥ ዘወርም ብሎ ለተከተሉት ሕዝብ፦ እላችኋለሁ፥ በእስራኤልስ እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም አላቸው።
¹⁰ የተላኩትም ወደ ቤት ተመልሰው ባሪያውን ባለ ጤና ሆኖ አገኙት።

@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

Revelation Center (apokálypsis) Angel

29 Jun, 11:09


መልካም ዜና
ቅዳሜ ሰኔ 22 ||

ከሰው ጥበብ ባሻገር

1ኛ ቆሮንቶስ 3:19፣ የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል ተብሎ ተጽፎአልና።

ጥበብ ልምድ፣ እውቀት እና ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ነው። ዓለም የአንድን ሰው የጥበብ ደረጃ ለመለካት የራሷ የሆኑ ደረጃዎች አሏት። አንዳንድ ጊዜ ጥበብ የሚለካው በገንዘብ፣ በትምህርታዊ ብቃቶች ወይም በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ላይ ባለው ተጽእኖ ነው። የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላችን ከሰው ልጅ አለም በላይ የሆነ የላቀ ጥበብ እንዳለ ይገልፃል። በዚህች ፕላኔት ላይ ያሉትን ሁሉንም ፈጠራዎች እየተመለከትን እንኳን አሁንም እጅግ የላቀ እንደሆነ ተደርጎ የሚቆጠር ጥበብ አለ።

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ የዚህ ዓለም ጥበብ በእርግጥ ሞኝነት ነው ብሏል። በዚህ ዓለም ስርዓቶች ላይ መተማመን ወይም መደገፍ አያስፈጋችሁም ምክንያቱም ሁልጊዜ ድክመቶች አሏቸው!!! የከፍተኛ ጥበብ መገለጫ የሆነው እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ብቻ ነው። በጥበቡ፣ የምድርን መሰረት አዘጋጀ እና ሁሉም ነገር በቦታ ላይ እንዲሆን አዘዘ። በዚህ ቃል ላይ ስታሰላስሉ እና ስትጸልዩ ያው ጥበብ ወደ መንፈሳችሁ እየገባ ነው። ሊወድቅ እና ሊሳሳት በማይችል በላቀ ጥበብ ትንቀሳቀሳላችሁ፣ በኢየሱስ ስም!!!

ትንቢታዊ አዋጅ

ከላይ የሆነችን ጥበብ ተቀብያልው። በዓለም ካለው ይልቅ በእኔ ያለው ታላቅ ነው። የድካሜ ፍሬዎች በኢየሱስ ስም የተባረኩ ናቸው። ኣሜን!!!

ተጨማሪ ጥናት ያዕቆብ 1፡5 የ365 ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈተና ይዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፡- 1ኛ ነገ 22፣2ኛ ዜና 18


@Revelationcenter
@Revelationcenter
@Revelationcenter

1,999

subscribers

6

photos

2

videos