CK Info Tube @radio_voa Channel on Telegram

CK Info Tube

@radio_voa


Listen Local and Global News

CK Info Tube (English)

Are you someone who is always eager to stay informed about the latest local and global news? Look no further than CK Info Tube, the Telegram channel where you can listen to a variety of news updates from around the world. With the username @radio_voa, this channel provides an easy and convenient way to access news content that matters to you. Who is CK Info Tube? It is a platform dedicated to bringing you the most relevant news stories, whether they are happening right in your neighborhood or across the globe. By tuning in to this channel, you can stay up-to-date on current events, politics, entertainment, and more. What is CK Info Tube? It is your go-to destination for curated news content that covers a wide range of topics. Whether you prefer to listen to news updates while on the go or want to catch up on the latest stories during your free time, this channel offers the flexibility to stay informed on your terms. Don't miss out on the opportunity to listen to local and global news updates conveniently through CK Info Tube. Join the channel today and start listening to the news that matters to you!

CK Info Tube

15 May, 04:44


አለማቀፍ ተቋማት ተቃውሞ እየደረሰባት ያለችው እስራኤል ግን በከተማዋ የመሸጉ ታጣቂዎችን ካልደመሰስኩ የጋዛ ጦርነት ድልን አላውጅም ብላለች።

CK Info Tube

15 May, 04:44


ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማቆም ሃማስን ከማጠናከር ውጭ ፋይዳ የለውም ካሜሮን
ብሪታንያ ከ2015 ጀምሮ ለእስራኤል 1 ቢሊየን ፓውንድ የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎችን መሸጧ ተገልጿል
ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማቆም “ትክክለኛው መንገድ አይደለም” አሉ የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን።
እርምጃው ሃማስን ከማጠናከር ውጭ ፋይዳ የለውም ማለታቸውም ተዘግቧል።
እስራኤል በራፋህ የእግረኛ ጦሯን አስገብታ ወረራ ከፈጸመች አሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለማቆም ማስጠንቀቋ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ብሪታንያ የአሜሪካን ፈለግ ልትከተል ትችላለች ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ካሜሮን፥ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ በመሸጥ ሁለቱ ሀገራት ለንጽጽር የሚቀርቡ አይደሉም ብለዋል።
አሜሪካ ለእስራኤል በሰጠቻቸው ቦምቦች ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን አመነች
እስራኤል ከውጭ ከምታስገባቸው የጦር መሳሪያዎች የብሪታንያ ድርሻ 1 በመቶ ብቻ ነው።
ይሁን እንጂ እስራኤል አለማቀፍ የሰብአዊ ህግን ከጣሰች ለንደን ሽያጯን ልታቋርጥ ትችላለች ብለዋል ሚኒስትሩ።
የተቃዋሚ ፓርቲው ሌበር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለንደን የዋሽንግተንን አቋም እንድትይዝ ግፊት እያደረጉ መሆኑን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ብሪታንያ ከፈረንጆቹ 2015 ወዲህ ለእስራኤል 1 ቢሊየን ፓውንድ የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎች እንደሸጠች መረጃዎች ያሳያሉ።
“ቢኤኢ” የተባለው የብሪታንያ ኩባንያ እስራኤል ለምትጠቀምባቸው ኤፍ-35 የጦር አውሮፕላኖች 15 በመቶ ግብአቶችን ያቀርባል።
የኔታንያሁ አስተዳደር እነዚህን የጦር ጄቶች በራፋህ ጥቃት ለመፈጸም እየተጠቀመባቸው ንጹሃን እየተገደሉ ነው የሚሉ የመብት ተሟጋቾች ኩባንያው ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን እንዲያቋርጥ እየጠየቁ ነው።
የራፋሁ ዘመቻ ከአጋሯ አሜሪካ ጀምሮ በተለያዩ ሀገራትና

CK Info Tube

15 May, 04:41


በራፋህ 450 ሺሕ ፍልስጤማውን ህፃናት በፈረንጆቹ ከግንቦት 6 ጀምሮ “በኃይል ተፈናቅለዋል“ ተባለ፡፡

የተ.መ.ድ የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ፣ የራፋህ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ከተነገራቸው ጀምሮ ህፃናት አማራጭ አጥተዋል ብሏል።

ድርጅቱ፣ ለአካባቢው “ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ብቸኛ ተስፋ መሆኑን“ ገልጿል።

እስራዔል በጋዛ ድንበር በምትገኘው ከተማ ጥቃት እንደምትከፍት በመግለጽ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡

CK Info Tube

15 May, 04:40


በኢንዶኔዥያ በጎርፍ አደጋ 47 ሰዎች ሲሞቱ፣ 17 ጠፉ።

የሀገሪቱ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣን፣ "በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 47 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ 17 ሰዎች ደግሞ ጠፍተዋል" ብሏል።

አስተዳደሩ፣ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነና የሞቱ ሰዎችን አስክሬን የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

CK Info Tube

15 May, 04:39


በሱዳን እንደ አዲስ ባገረሸው ግጭት #በአንድ ቀን ብቻ 27 ሰዎች ተገደሉ፡፡

ጦርነት ላይ በሚገኙት የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል በዳርፉር ፋሸር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በአንድ ቀን ብቻ 27 ሰዎች መገደላቸውን የተ.መ.ድ አስታውቋል፡፡

በከተማዋ ከዓርብ ጀምሮ በአየር ላይ ጥቃት የታገዘ ጦርነት እንደነበር የዓይን እማኞችን የገለጹ ሲሆን፤ በግጭት ከሞቱት ባለፈ 850 ሰዎች ተፈናቅለዋል።

CK Info Tube

15 May, 04:38


ፑቲን አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር ሾሙ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ለ6ኛው ዙር ሩሲያን ለመምራት ቃለመሀላ የፈጸሙት ፑቲን፣ አዲስ የካቢኔ ሽግሽግ እያደረጉ መሆናቸው ተገልጿል።

ፑቲን የመከላከያ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን #ሰርጌ ሾይጉን አንስተው የኢኮኖሚ አማካሪያቸው የነበሩትን #አንድሬይ ቤሌሶቭን አዲሱ የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል ተብሏል፡፡

የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ቲሙር ኢቫኖቭ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወሳል።

CK Info Tube

13 May, 09:34


CK Info Tube pinned «የአለርጂ መከላከያ መንገዶችና ህክምናው አለርጂ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በተለይም ለምግቦች፣ ለአበባ ብናኞች፣ ለአቧራ፣ለአየር ሁኔታ እና መሰል ነገሮች በሚሰጠው ምላሽ እንደሚፈጠር ይነገራል። ንጥረ ነገሩ ወይም ለሰውነትዎ የማይስማማ ነገሮች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓትዎ የሚሰጠው ምላሽ በሰውነትዎ ላይ አለርጂን ያስከትላል፡፡ በዚህም እብጠት፣ ማስነጠስ ወይም ሌሎች የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ…»

CK Info Tube

12 May, 19:53


"ኒታንያሁ የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ሆኖ ይወርዳል" - ፔትሮ

የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔድሮ የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኒታንያሁ "በዘር ማጥፋት ድርጊቱ በታሪክ ሲታወስ ይኖራል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ፣ "በሺዎች በሚቆጠሩ ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ ቦምብ ማዝነብ ጀግና አያስብልም" ብለዋል።

CK Info Tube

12 May, 17:33


ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህፃናት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆኑ
*****

ኢትዮጵያውያኑ ሶስት ሽልማቶችን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን የመጀመሪያው ከ 10 አመት በታች በተወዳደሩበት ሮቦ ፓሬድ የውድድር ዘርፍ ተሸልመዋል።

ሁለተኛው ደግሞ በሲንየር ኤግዚቢሽን ከ14 -16 አመት ስፔሻል አዋርድ ሽልማትንም ማግኘት ችለዋል።

በጁንየር ኤግዚብሽን ዘርፍ ደግሞ በአለም አቀፍ ውድድሩ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

እንዲሁም ከየውድድሩ ከ 1-3 ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አሜሪካ በሚገኘው የሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዮኒቨርሲቲ በተካሄደው ውድድር 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ወክለው በተለያዮ ዘርፎች ለውድድር መቅረባቸው ይታወሳል።

ተወዳዳሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ ፣ አብርሆት ላይብራሪ ከአቦጊዳ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በአለም አቀፍ መድረኮች ለማወዳደር በገቡት ስምምነት መሰረት የተካሄደ ነው።

የሮቦ ፌስት ውድድር በሎረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካን ሚችጋን ክፍለ ግዛት ውስጥ የሚሰጥ አለም አቀፍ ውድድር ሲሆን ዋነኛ አላማውም ሳይንስና ቴክኒወሎጂን በማበልፀግ ዝንባሌው ያላቸውን ታዳጊ ህፃናትን በዘርፉ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሸጋገር ነው።

CK Info Tube

12 May, 17:28


እስራኤል በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ካስተላለፈች በኋላ ወታደሮቿ ወደ ራፋህ ዘልቀው መግባታቸው ተገለፀ።  እንደ የዓይን እማኞች ገለፃ በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ የግብፅ ድንበር አቅራቢያ ከአየር ድብደባ ተፈፅሟል። እስራኤል ርምጃዋን "ውስን" እና "በስልታዊ መንገድ የተፈፀመ " ብላለች።  ጥቅጥቅ ያለ ህዝብ የሚኖርባቸው አካባቢዎችም እንደዚህ አይነት ርምጃ አልተወሰደም» ብሏል ጦሩ። እስራኤል ዛሬም በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ ውጊያዋን ቀጥላለች።  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ አስተላልፈዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ጫና ቢገጥማቸውም ራፋህ በምድር ጦር ለማጥቃት በያዙት እቅድ ጸንተው ገፍተዋል። እስራኤል ለሳምንቱ መጨረሻ ያስተላለፈችውን ትዕዛዝ ተከትለው 300 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ከራፋህ 10 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ወደምትገኘው አል ማዋሲ እንደሸሹ ተዘግቧል።
የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው እንደ ጎርጎሮሲያውያን አቆጣጠር ከጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም አንስቶ 35,034 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 78,755 ቆስለዋል።

CK Info Tube

12 May, 17:21


ደቡብ አፍሪቃ እስራኤልን «በጋዛ የህዝብ እልቂት እየፈፀመች ነዉ ስትል» የከፈተችውን ክስ ግብፅም እንደምትቀላቀል ዛሬ አስታወቀች።  የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው ግብፅ ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰችው እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን የጨመረ እና የተጠናከረ ጥቃት ተከትሎ ነው።  ግብፅ እስራኤል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የምታደርሰው ጥቃት እና የመሠረተ ልማት ውድመት ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ «የሰብአዊ ቀውስ» ውስጥ ከቷል ብላለች። ዋሽንግተን በበኩሏ እስራኤል ምናልባትም ከዩናይትድ ስቴትስ በቀረበላት የጦር መሣሪያ አለም አቀፍ ህግን ጥሳ ሊሆን ይችላል ብላለች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ምርመራ የሚሹ በርካታ ጥሰቶች እየተመረመሩ እንደሆነ ዛሬ አስታውቀዋል።

CK Info Tube

12 May, 17:20


የሩስያ ወታደሮች ከዩክሬን ኻርካይቭ ግዛት ሌሎች አራት መንደሮች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ትናንት ቅዳሜ የሩሲያ ወታደሮች በግዛቲቱ የሚገኙ አምስት የድንበር መንደሮችን መቆጣጠራቸውን አስታውቆ ነበር። ሩሲያ ካለፈው ዓርብ አንስቶ ከግዛቷ በሰሜን ዩክሬን በኩል አዲስ የምድር ውጊያ ከከፈተች ጊዜ አንስቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዩክሬን የጦር አዛዥ ኻርካይቭ ግዛት የሚዋጉ የዩክሬን ወታደሮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነውም የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ከዩክሬን በተሰነዘረ ጥቃት በሩሲያ ቤልጎሮድ ከተማ አንድ ባለ 10 ፎቅ  አፓርታማ በሮኬት ተመቶ  ህንፃው ሙሉ በሙሉ መውደሙን የከተማዋ ከንቲባ አስታውቀዋል። እንደ መገናኛ ብዙኃን ገለፃ በጥቃቱ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ 20 የሚሆኑ ሰዎች ፍርስራሹ ውስጥ ሊሆኑ እንደሚችል ተገምቷል።

CK Info Tube

12 May, 16:44


አሜሪካ ከ80 ዓመት በፊት ለሞቱ ወታደሮች የጀግና ሽልማት ሰጠች
ተሸላሚዎቹ በ1945 በጃፓኗ ኦኪናዋ 31 ወታደሮችን የጫነ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሶ ህይወታቸው ያለፉ ናቸው
አሜሪካ ከ80 ዓመት በፊት ለሞቱ ወታደሮች የጀግና ሽልማት ሰጠች፡፡
ሁለተኛው ዓለም ጦርነትን ዘግይታ የተቀላቀለችው አሜሪካ ጦርነቱን በበላይነት ካጠናቀቁ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ናት፡፡
በዚህ ጦርነት አሜሪካ እና አጋሮቿ አሸናፊ እንዲሆኑ የጃፓን ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊያን ድርሻ ቀላል አልነበረም፡፡
እነዚህ ወታደሮች በተለይም ጃፓንኛ ቋንቋን በመተርጎም፣ ጃፓንን በመሰለል እና ሌሎች ወታደራዊ ግዳጆችን እንደፈጸሙ ገለጻል፡፡
ጃፓን በዚህ ጦርነት ከተሸነፈች በኋላ ለተጨማሪ ወታደራዊ ስራዎች ወደ ጃፓኗ ኦኪናዋ በአውሮፕላን ያመሩ 31 ወታደሮች በገጠማቸው አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡
አሜሪካ በዚህ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለተሳተፉ ወታደሮች የጀግና ሜዳሊያ የሸለመች ቢሆንም በኦኪናዋ ወታደራዊ አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈሩ እና በአደጋ ምክንያት ከሞቱ 31 ወታደሮች መካከል ሁለቱን ብቻ ሸልማም ነበር፡፡
አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል ገድየዋለሁ ያለችው ሰው ድሃ ገበሬ ሆኖ ተገኘ
ይህ ክስተት ከተፈጠረ 80 ዓመት በኋላም ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና መስጠቷን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ለእነዚህ ወታደሮች የጀግና ሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱም የሟች ወታደሮች ቤተሰቦች ተሰጥቷል፡፡
ይህን የጀግና ሽልማት የወሰዱት የአራት ወታደሮች ቤተሰቦች ሲሆኑ የቀሪ ወታደሮች ቤተሰቦች እየተፈለጉ እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ክስተቱ ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ማስቆጠሩን ተከትሎ በአደጋው የሞቱ ወታደሮች ቤተሰቦችን በቀላሉ ማግኘት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን የሟች ቤተሰቦች ሲመጡ ሜዳሊውን መውሰድ ይችላሉም ተብሏል፡፡

CK Info Tube

12 May, 15:13


ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች

ሰሜን ምዕራብ ቻይና ሞቃታማ እና አሸዋማ አካባቢ ነው
ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች፡፡
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተክላላች፡፡
ሀገሪቱ የግመል ትራንስፖርት መጨናነቅ በሚታይበት ሰሜን ምዕራባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች ነው፡፡
ጋንሹ ተብሎ የሚጠራው ይህ ግዛት አሸዋማ እና ደረቃማ አካባቢ ሲሆን በዚህ ወቅት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት ቦታ ነው፡፡
አካባቢው አሸዋማ በመሆኑ ምክንያትም የግመል ትራንስፖርት ዋነኛ አማራጭ ሲሆን በዚህ ጊዜ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠር የትራፊክ መብራት ተክላለች፡፡
በዚህ አሸዋማ ስፍራ ከ2 ሺህ 400 በላይ ግመሎች ለትራንስፖርት የተዘጋጁ ሲሆን በየዕለቱ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ወደ ስፍራው እያቀኑ ነውም ተብሏል፡፡
በተለይም ሚንግሻ የሚባለውን ተራራ ለመጎብኘት ጎብኚዎች ይህን አሸዋማ ስፍራ ለማለፍ የግድ ግመልን መጠቀም ግዴታ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የትራፊክ ፖሊስ መስሎ ለወራት በጎዳናዎች ላይ ሲሰራ የቆየው ግለሰብ ታሰረ
አሁን ላይ ሚንግሻ ተራራ በየቀኑ በ20 ሺህ እና ከዛ በላይ ጎብኚዎች እየገበኙት ነው የተባለ ሲሆን ለግመል ትራንስፖርት አቅራቢ ቻይናዊያን ወቅቱ ትልቅ እድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል፡፡
በትራፊክ መብራቱ መሰረትም አረንጓዴ ሲበራ ግመሎቹ የሚጓዙ ሲሆን ቀይ ሲበራ ደግሞ እግረኛ ሰዎች እንዲጓዙ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ቻይናዊያን ሀገራቸውን በመጎብኘት ከሌላው ዓለም የተሻለ ልምድ አላቸው የተባለ ሲሆን በዓለም የሰራተኞች ቀን ብቻ 240 ቻይናዊያን ወደ ሚንግሻ ተራራ ለጉብኝት አምርተዋል ተብሏል፡፡

CK Info Tube

12 May, 07:01


የአለርጂ መከላከያ መንገዶችና ህክምናው

አለርጂ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በተለይም ለምግቦች፣ ለአበባ ብናኞች፣ ለአቧራ፣ለአየር ሁኔታ እና መሰል ነገሮች በሚሰጠው ምላሽ እንደሚፈጠር ይነገራል።
ንጥረ ነገሩ ወይም ለሰውነትዎ የማይስማማ ነገሮች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓትዎ የሚሰጠው ምላሽ በሰውነትዎ ላይ አለርጂን ያስከትላል፡፡
በዚህም እብጠት፣ ማስነጠስ ወይም ሌሎች የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን ፥ እንደግለሰቡ የአለርጂ ዓይነትና ሁኔታም ምላሹ የተለያየ እንደሚሆን ነው የሚገለጸው፡፡

አለርጂ እንዴት ይታከማል?
አለርጂን ጨርሶ ማጥፋት እንደማይቻል ይነገራል፤ ሆኖም መከላከል ግን ይቻላል፤ በብዙ የህክምና ባለሙያዎች የሚመከረው አለርጂ ከሚያስከትሉብዎ ነገሮች መራቅ ለነገ የማይባል መፍትሄ ነው፡፡
ሆኖም ይህን አማራጭ መውሰድ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ የህክምና አማራጮችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ይህም ከህክምና ባለሙያ ጋር በመነጋገር የመድኃኒት አማራጭን መጠቀም የሚቻል ሲሆን ÷የህክምና ባለሙያን ሳያማክሩ መድኃኒት መውሰድ ግን አይመከርም፡፡
በተጨማሪም ከሃኪምዎ ጋር በመመካከር አለርጂ በቤት ውስጥ ሊታከም የሚችልበትን መንገድ መፈለግ ሌላው አማራጭ ነው፡፡
ይህን የቤት ውስጥ ህክምና ከማድረግዎ በፊት ግን በቤትዎ ውስጥ የሚያዘጋጁት ንጥረ ነገሮች ሌላ አለርጂ ላለመሆናቸው እርግጠኛ መሆን አለብዎ፡፡
አለርጂ ጉንፋን ከሚመስል ማስነጠስ፣ የቆዳ ችግርና ሌሎች ለከፋ ጉዳት የማያስከትሉ ጉዳቶች ቢኖሩትም ለአንዳንድ ሰዎች ለህይወት አስጊ ሊሆንም ይችላል፡፡
እንደአብነትም የምላስ እና የአፍ እብጠት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የመተንፈስ ችግር፣ ራስን መሳትና ሌሎች ከፍ ያሉ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
በዚህም አለርጂው ከፍ ያሉ ጉዳቶችን የሚያስከትልብዎ ከሆነ ምንጊዜም ጥንቃቄ ሊለይዎት አይገባም፡፡
ከዚህ ካለፈም የድንገተኛ ህክምና ዘዴዎችን ከሃኪምዎ ጋር ቢወያዩበት ሲል ኽልዝላይን ይመክራል ፡፡

CK Info Tube

11 May, 22:02


🚺🚺 #አራቱ_ሚስቶች 🚺🚺

አራት ሚስቶች የነበሩት አንድ ሀብታም ነጋዴ ነበር፡፡ አራተኛ ሚስቱን
ከሌሎች አብልጦ በእጅጉ ይወዳታል፡፡ ስለሚወዳትም ጥሩውን ሁሉ ለእርሷ በመስጠት ይንከባከባታል ያስደስታታል፡፡

ሦስተኛ ሚስቱን መውደድም ብቻ አደለም ይኮራባታል፣ ይመካባታልም ጭምር ይዟት በአደባባይም ለመታየት ይፈልጋል ነገር ግን ጥላው እንዳትሄድ በጣሙን ይሰጋል፡፡

ሁለተኛ ሚስቱንም እንዲሁ ይወዳታል ይች ሁለተኛ ሚስቱ በነገሮች አስተዋይና ብልህ ታጋሽም በመሆኗ ይመካባታል፡፡ ነጋዴው አንዳች እክል ከገጠመው እንዲሁ ችግሩን ታቅፎ እሚያመራው ወደ ሁለተኛ ሚስቱ ነው እሷም በአስቸጋሪው ሰዓት ከጭንቀቱ ትገላግለዋለች፡፡

የመጀመሪያ ሚስቱ በጣም ታማኝ አጋሩ ናት ቤቱንና ንግዱን
የምትመራለትና የምታስተዳድርለት እሷው ነች እሷ በጣም የምታፍቅረውዐቢሆንም እሱ ግን ስለማያፈቅራት አንድም ቀን በትውስታው ውስጥ ቦታ ሰጥቷት አያውቅም ነበር፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ህመም ተሰማውና ማለፉን ባሰበ ጊዜ የተድላ ዓለሙን እያስታወሰ እንዲህ አሰበ “አራት ሚስቶችና የተትረፈረፈ ሀብት አለኝ ነግር ግን በሞት ጊዜ ብቻዬን እሆናለሁ፡፡ እንዴት ብቻዬን እሆናለሁ?” በማለት አራቱንም ሚስቶች በማስጠራት ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡

ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ የሚያምሩ አልባሳትንም እያለበስኩ ሳስጌጣችሁ ኖርኩ አሁን ግን ልሞትናውና ከብቸኝነቴ ታድኑኝ ዘንድ ተከተሉኝ አላቸው፡፡

አራተኛው ሚስቱ “በፍጹም አይሆንም” ስትል መልሱን ሰጥታው
ከአካባቢው ተሰወረች፡፡ ነጋዴው በሰማው ምላሽ ልቡ ተነካ፡፡

ለሦስተኛዋ ሚስቱ “በሕይዎቴ ሙሉ ስወድሽ ኑሪያለሁ አሁን አብረሽኝ ልትሆኝና ወደምሄድበት ልትከተይኝ ትፈቅጃለሽ?” አላት በአዘኔታ ሆኖ መልስ ሲጠባበቅ “አይሆንም ሕይወት አትጠገብም፡፡ እዚህ መኖር መልካም ነው እናም ከአንተ ሞት በኋላ አግብቼ መኖር እሻለሁ” አለችው፡፡ ይህ ሀብታም ነጋዴ ልቡ ዝቅ ሲልና ወደ ቀዝቃዛነት ሲለወጥ ተሰማው፡፡

አሁንም በተስፋ መቁረጥ ሁኖ “በሕይዎቴ ሙሉ እርዳታን ስፈልግ ወደ አንች ስመላለስ ኖሪያለሁ ስትረጅኝም ነበር አሁንም እርዳታሽን ፈልጊያለሁና እርጅኝ” ሲል ሁለተኛ ሚስቱን ጠየቃት፡፡

“በዚህ ሰዓት ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ ማድረግ የምችለው አንተን ወደ መቃብርህ መሸኘት ብቻ ነው” ስትለው መብርቅ የመታው ያህል ክው አለ፡፡

በድንጋጤ ስሜት ተውጦ እያለ “የትም ብትሄድ እከተልሃለሁ፤ አንተጋ እሆናለሁ!” የሚል ድምጽ ሲያስተጋባ ተሰማው ዓይኑን ሲያነሳ የተጎሳቆለ እይታ ያላት የመጀመሪያ ሚስቱ ነበረች ነጋዴው እየተናነቀው “ሲኖረኝና ስችል ልንከባከብሽ ይገባኝ ነበረ” በማለት እቅፍ አድርጎ ወደሰውነቱ አስጠጋት፡፡

በመሠረቱ ሁላችንም በሕይዎታችን አራት ሚስቶችን አኑረን ይሆናልና የእኛም ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡

አራተኛው ሚስታችን ፈራሹ ስጋችን ነው ለምቾቱና ለውበቱ
ተጨንቀን ብንደክምም ቀሪ እንጅ ተከትሎን አይሄድም፡፡

ሦስተኛው ሚስታችን አለን የምንለው ነገር ንብረት ሀብትና ክብራችን ነው ይሄም እኛ ስንሞት ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው፡፡

ሁለተኛው ሚስታችን ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን የቱንም ያህል ቀረቤታና ቁርኝት ቢኖረንም ማድረግ የሚችሉት እስከ መቃብር መሸኘት ብቻ ነው፡፡

የመጀመሪያዎ ሚስታችን ሕያው ነፍሳችን ናት፡፡ በመልካም ስራ እናድሳት ነገ አብራን ትኖራለች ቁስና ሀብት ስናሳድድ ወደ ጎን ገፍተናት ቢሆንም አብራን የምትሆነው እሷው ነችና በመጨረሻው ሰዓት
ሳይሆን #አሁኑኑ_እንድናለመልማት_ያስፈልጋል ፡፡

CK Info Tube

11 May, 21:53


ይህ የሆነው ሩቅ ሀገር አይደለም። እዚህ ጎረቤታችን ኬንያ ነው ።
......
ይህች በስልክ እንጨቱ ላይ ያለችው ወፍ ግንደ ቆርቁር ( woodpecker ) ትባላለች ። ግንድ ቆርቁራ ጎጆዋን ትቀልስና ፡ በዛ ለአመታት ትኖራለች ። ቤተሰብ መስርታ ልጆቿንም በዛው ታሳድጋለች ።
.......
በፎቶው የምታዩዋት woodpecker በዚህ የመብራት ፖል ላይ ቆርቁራ መኖር ከጀመረች ቆይታለች ። እና የኬንያ መብራት ሀይል መስሪያ ቤት ይህን ያረጀ ፖል ፡ በኮንክሪት ሊቀይረው ይመጣል ። እና ልክ ፖሉን ለመጣል አስረው ማዝመም ሲጀምር ፡ ከተቆረቆረው ግንድ ውስጥ አንድ woodpecker ወፍ ትወጣለች ።
ነገር ግን ከዛ መራቅ አልቻለችም ፡ ትወጣና መልሳ ለመግባት ትሞክራለች ፡
ሰራተኞቹ ፖሉን ነቅለው አስቀመጡት በዚህ ጊዜ ወጥታ የነበረችው ወፍ መጥታ ተቀመጠች ፡ ሰራተኞች ቀርበው አዩ ። ተቆርቁሮ በተሰራው የወፍ ቤት ውስጥ ጫጩቶች ነበሩ ።
...........
ልክ ይህን እንዳዩ መልካም ልብ ያላቸው የመብራት ሀይል ሰራተኞች ይህችን ወፍ ከነልጆቿ ቤት ማሳጣት ጭካኔ እንደሆነ ተሰማቸውና ቤቷ ያለበትን አካባቢ ሳይነኩ ፡ ከረዥሙ የመብራት ፖል ላይ የተወሰነውን ትንሽ ክፍል ቆርጠው ፡ ከአዲሱ የኮንክሪት ፖል ጋር በዚህ መልኩ አያያዙት ። አውጥተው ሊጥሏት ሲችሉ ፡ አዘኑላት ፡ ለልጆቿ ልባቸው ራራ ።