ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ @abagiyorgismnale Channel on Telegram

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

@abagiyorgismnale


የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሕይወትና ትምህርት ይቀርብበታል።

https://t.me/abagiyorgismnale

ለሌሎች በማጋራት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ

ለጥያቄዎችና ለአስተያየት
@Dnmikii @feke17

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (Amharic)

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዚህ ቦታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በተመኘም ተመንግስት እና ተቝራማዕ እና መረጃ እንዲማለን። የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የዳበ መሰረትና ትምህርት እና ምዘና ስላለው ጸሎትን ከእኛ እናዘጋጃለን። በዚህ አድራጎት የተጠቃሚው ብቻ የሚዋጋ የሀሳቦችን መፍትሄ እና መንፈሳዊ ፍቅር እንያላችን ብቸኛው አሰርቫለን። ከዚህም ሁሉንም ሳምንት ቅኝታችን ውስጥ ትክክለኛና ተፈጥሯናል። እስከ ግድያና እከበርና ምዘናን የተላኩባቸውን ምርጥ ውጤቶች እና መፍትሄዎች እንዳለን ተለዋዋጭ እና በግብረ እናቶችን ለማገኘት መንካኤል እና ሰብሰቡንም በማህበረሰብ ሰንበት ፍቃድ እንዲበላን ለእኛ በመከታችሁ ሥሩ።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

30 Jan, 19:02


"በጥጃና በበሬ መካከል የክብደት እንጅ የዕውቀት ልዩነት የለም።"

[ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ]

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

29 Jan, 05:12


ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች

"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች ፡፡ በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ ፣ የጎኑን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች ። የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

28 Jan, 15:20


ኪዳን ዘሠርክ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

26 Jan, 22:30


#ሀገረ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተማ)

በኦሪት መጻሕፍት ላይ የሰፈረ ለእሥራኤላውያን የተሰጠ አንድ ልዩ ሀገር አለ እርሱም የመማጸኛ ሀገር "ሀገረ ምስካይ" ይባል ነበር።ሀገረ ምስካይ(የመማጸኛ ሀገር) ማለትም ሰው ለወፍ ለዛፍ ብሎ ድንጋይ ወርውሮ አንድም ባለማወቅ ነፍስ የገደለ እንደ ኾነ ያለ ፍርድ ባለማወቅ በሠራዊቱ በዳኛው ፊት ቆሞ እውነቱ እስኪመረመር ድረስ እንዳይሞት(እንዳይገደል) ይማጸንበት ዘንድ የሚጠጋበት አገር ማለት ነው።

በዮርዳኖስ ሦስት አገሮች በከነዓን ሦስት ሀገሮች በጠቅላላ ስድስት ሀገሮችን ለይተዉ ለመማጸኛ እና ለስደተኛ እንዲሰጡ በእስራኤላውያን ዘንድ ሕግ ነበር። ከእነዚህም ለነገደ ሮቤል መማጸኛ ባሶር ለነገደ ጋድ መማጸኛ አራሞት ለነገደ ምናሴ መማጸኛ ባሳን እንዲኾኑ ተለይተዉ ተሰጥተዋል፡፡

ሙሉ ቃሉ:-

"በስሕተት ነፍስ የገደለ ወደዚያ ይሸሽ ዘንድ የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑላችሁ ከተሞችን ለእናንት ለዩ።ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹም ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች ትሰጣላችሁ፥ በከነዓንም ምድር ሦስት ከተሞች ትሰጣላችሁ፤ የመማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ። በስሕተት ነፍስ የገደለ ይሸሽበት ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።"ዘኁልቅ 35:14

°°ከልቡ ወጥኖ ነፍስ ላጠፉው ለቃየል ያገኝው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት ያደረገለት ቅዱስ እግዚአብሔር ዳግመኛ ከልብ ላልሆነ ጥፋታቸው ባለማወቅ ለሠሩት ስህተታቸው በምድር ሕግ ምትን እንዳይሞቱ ደግሞ ከለላ የሚሆናቸውን ከልብ ስላልተደረገ በደላቸው የሚማጸኑበትን ከተማ ሠራላቸው።

°° ምሕረቱ ከመዓቱ፤ትእግስቱ ከቁጣው ይበልጣል ፍርዱ ልብን የሚያርድ፤መዓቱ መሸሻ የሌለው፤ቁጣው ሥጋን ምድርን የሚያንቀጠቅጥ አምላክ ሆኖ ሳለ አብዝቶ ይታገሳል። ምንማጸንበትን እድሜ ወደ ኋላ ዞረን የሰራነውን በደል የምንሽርበትን የመማጸኛ ጊዜ ይቸረናል።

°°የመማጸኛ ሀገር፤ፍዳ ማቅለያ ሀገር፤የንሰሐ እድሜን መጠቀምያ ሀገር ማግኝት መታደል ነው። ዓለም ባለማወቅ ለተሠራ ጥፋት ፍርድ አታቀልም በከሳሽ ቃል የጸና ቅጣት ታመጣለች። የመማጸኛ ጊዜ የላትም። ይህች እስራኤላውያን የሚጽናኑባት ከበደላቸው አርፈው የሚማጸኑባትን ከተማ ምነው በሰጠን? ብለን አናዝንም ይልቁንስ ቤተክርስቲያን ይህችን መማጸኛ ከተማ ትመስላለች እንገዶች መጻተኞች በደለኞች የሚጽናኑባት በምድር ያለች ሰማያዊት ሀገር እርሷ ናት። በእርሷ እቅፍ ውስጥ ስንት መዓቶች ያልፋሉ ስንት መገፋቶች ይቀላሉ ወደ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚደረገው ሩጫ በእርሷ ዘንድ ነው።

መጽናኛ መማጸኛ ሀገራችን ለኛስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት። ሰፊ የምሕረት በር የተተከለባት ስለ በደላችን ፈንታ ቸርነት የምታስገኝልን ከዓለም ሹማምንት ፍርድ አረፍ ብለን እግዚአብሔርን የምንማጸንባት በብዙ ጉድለታችን የምንኖርባት። በማውቅ አብዝተን ለበደልነው ባለማወቅ ላጠፋነው ሁሉ መጠጊያ መማጸኛ ሀገራችን እርሷ ናት።

ሀገረ ምስካይ፤ምስካየ ኅዙናን ቅድስት ቤተክርስቲያን

የተቸገሩ መጠግያ የመጸናኛ ሀገራችን ቤተክርስቲያን።

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
በዓለ ጥምቀት ቃና ዘገሊላ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

23 Jan, 19:28


https://youtu.be/I2Ew4MEESr8?si=HUJVgUYjzk3iq3aQ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

20 Jan, 04:28


ምንተ ኮንኪ ባሕር ዘጐየይኪ? ወአንተኒ ዮርዳኖስ ዘገባእከ ድኅሬከ?

አንቺ ባሕር የሸሸሽ ፥ አንተም ዮርዳኖስ ወደ ኋላህ የተመለስህ ፥ ምን ሆናችኋል? መዝ ፻፲፫ ÷ ፫

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

19 Jan, 16:44


አለቃ ዘነብ
መጽሐፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

18 Jan, 03:25


መድኃኒት ነህና በስጋ በነፍስ
እንጠራሃለን ብለን ኢየሱስ
ጥዑመ ስም ያልነው ስለጣፈጠን ነው
ከስም ሁሉ በላይ ስምህስ ልዩ ነው

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

13 Jan, 19:44


"በምህረትሽ" - እጅግ ልብ የሚነካ የንስሐ ዝማሬ
ዘማሪ መላከ ሰላም ታደለ ፊጣ

አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ
የፈጣሪ እናት አስታውሽኝ
በምህረትሽ በምህረትሽ
በምህረትሽ ተማለጂኝ
አዝ.....
የመከራ ነፋስ አጠቃኝ
ህይወቴ ስላለች ደከመኝ
ከጥላሽ ስር ከጥላሽ ስር
ከጥላሽ ስር አሳርፊኝ
አዝ.....
ከጭንቀት ባህር ውስጥ አድኚኝ
ሰጥሜ እንዳልጠፋ አስጥይኝ
እመቤቴ እመቤቴ
እመቤቴ ተመልከችኝ
አዝ.....
አምላኬን ለማየት አልችልም
ሀጢያቴ ብዙ ነው አይሆንም
ካልደገፍሽኝ ካልደገፍሽኝ
ካልደገፍሽኝ እኔ አልድንም
አዝ.....
ድንግል እመቤቴ እባክሽ
ከፈጣሪዬ አስታርቂኝ ከልጅሽ
ያለ አንቺ ማን ያለ አንቺ ማን
ያለ አንቺ ማን አለኝ አስታዋሽ
---
አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ
የፈጣሪ እናት አስታውሽኝ
በምህረትሽ በምህረትሽ
በምህረትሽ ተማለጂኝ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

11 Jan, 16:05


አንተ ደጉ ሳምራዊ
አንተ ደጉ ሳምራዊ እለፍ በመንገዴ
በኢያሪኮ ላይ ጥሎኛል ወንበዴ (፪×)
ነፍሴ ወደ ፅኑ ሞት ተቃርባለችና
የአለም መድኃኒት ክርስቶስ ቶሎና ኢየሱስ ቶሎና

በሞትና ሕይወት መካከል ወደቅኩኝ
የሚያነሳኝ አጣሁ በብርቱ ቃተትኩኝ
ሰማሁኝ ከርቀት የአንድ ካህን ኮቴ
ያነሳኛል የሚል ነበረ ምኞቴ
       ደሜን ተመልክቶ እጅግ ተጸየፈ
ፈቀቅ ብሎ ሄደ ሳይረዳኝ አለፈ

አንድ ሌዋዊ ሰው በዚያ መንገድ መጣ
አንሳኝ ብላ ጮኸች ልቤ ሀዘን ተውጣ
ወደእኔ ሲጠጋ ኮቴውን ሰምቼ
አንሳኝ ብዬ ማለድኩ እጆቼን ዘርግቼ
         ፈቀቅ ብሎ ሄደ በሞት መኻል ሆኜ
         ነፍሴ ብላው ነበር መጣልኝ አዳኜ

አንድ ሳምራዊ ግን አየኝ ቀረበና
ከአህያው ወረደ በፍቅር በትህትና
ቁስሌንም ጠረገው በአህያው ላይ ጫነኝ
አነሳኝ ደግፎ በዘይቱ አጠበኝ
          ሁለት ዲናር ከፍሎ ለእንግዶች ጠባቂ
          ጌታዬ ታደጋት ነፍሴን ከነጣቂ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

10 Jan, 19:23


https://www.instagram.com/michael.eshetu4?utm_source=qr&igsh=MTVnOWRvYjExZWZ4Nw==

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

30 Dec, 19:12


ይህን ቪድዬ አዳምጡት በጣም ትጠቀሙበታላችሁ! ናብሊስ የተሰኘ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው። በጣም ጠቃሚ ጉዳዮች ነው የሚያነሱት። ከታች ያለውን ቪድዮ ሁላችንም እናዳምጠው ለሌሎችም እንዲያዳምጡት ሼር።

ያዩትን ሁሉ መመኘት፤ ከፍትወት እስራት ነፃ መዉጣት | ናብሊስ | ሀገሬ ቴቪ
https://youtube.com/watch?v=FxhCfRvmD54&si=gH0_cRFzhsG_ZMVF

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

28 Dec, 18:27


ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ

ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና
እንዳልጠፋ አምናለው ያንቺ ልጅ ነኝና 2

አዝ………………..

የፃድቃን እናቶች እጅግ ብዙ ናቸው
ከብሉይ ከሃዲስ ብንዘረዝራቸው
አንቺ ግን አንዲት ነሽ የለሽም ጭማሪ
ትኖሪያለሽ እንጂ ትውልድ ስታስምሪ

አዝ………………..

ያንቺን ስም ተማፅኖ ያንቺን ስም ቀድሶ
አንቺን አመስግኖ አንቺን አወድሶ
የተጠቀመ እንጂ በረከት አግኝቶ
አልታየም እስከ አሁን የተጎዳ ከቶ

አዝ………………..

ጎርጎርዮስና ሊቁ ዮሀንስ
አትናቴዎስ እና ሊቁ ባስልዮስ
አባ ኤፍሬምና አባ ጊዮርጊስ
ተጠቅመዋል ባንቺ በስጋም በነፍስ

አዝ………………..
https://t.me/abagiyorgismnale

አባትህን ጠይቅ ስለሚለን ቃሉ
ብንጠይቃቸው ቅዱሳኑን ሁሉ
ስላንቺ ነገሩን ክብር ታምራትሽን
ለሠው ዘር በሙሉ አማላጅ መሆንሽን

አዝ………………..

ገብርኤል ከሰማይ ኤልሳቤጥ ከምድር
በአንድ መሠከሩ ስለ ድንግል ክብር
ሰዓሊለነ ብሎ ተማፅኖ በአንቺ ሥም
የተጠቀመ እንጂ የተጎዳ የለም

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

27 Dec, 03:39


የጻፍከኝ በብራና አይደለም ፣ የጻፍከኝ በልብህ ነው ፤ ስለዚህ ሊሰርቅ የሚመጣው ሌባ አያገኘኝም ። የጻፍከኝ በቀለም አይደለም ፣ የጻፍከኝ በደምህ ነው ፤ ስለዚህ የጠላት ብዛት አያጠፋኝም ። የጻፍከኝ በአሸዋ ሰሌዳ አይደለም ፣ የቀረጽከኝ በዓለት ላይ ነው ፤ ስለዚህ የዘመን አቧራ አይሸፍነኝም ። የጻፍከኝ በወረቀት ላይ አይደለም ፣ የጻፍከኝ እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ላይ ነው፤ ስለዚህ በረከቴ ፈጣን ነው ። የጻፍከኝ ልትደመስሰኝ አይደለም ፣ የጻፍከኝ ለዘላለም ነው ፤ ስለዚህ ነገ አያሰጋኝም ። የጻፍከኝ ለገበታ ላይ አይደለም ፣ የጻፍከኝ ለበጉ ሰርግ ነው ፤ ስለዚህ የማያልፍ ዓለም አለኝ ። የጻፍከኝ በሞት መዝገብ አይደለም ፣ የጻፍከኝ በሕይወት መጽሐፍ ነው ፤ ስለዚህ የሞት ግርማ አያስደነግጠኝም ። የጻፍከኝ በአሳሳቢ አይደለም ፣ የጻፍከኝ በፍቅርህ ነው ፤ ስለዚህ በሰዎች ሐሜት አትጠላኝም ። የጻፍከኝ ለኮንትራት አይደለም ፣ የጻፍከኝ በማይፈርስ ውል ነው ፤ ስለዚህ ታምነህ አትከዳኝም ። የጻፍከኝ ዕዳ አለበት ብለህ አይደለም ፣ የጻፍከኝ ዕዳው ተከፍሎለታል ብለህ ነው ፤ ስለዚህ ወደ ቤትህ ስመጣ አታሳቅቀኝም ። የጻፍከኝ ለውግዘት አይደለም ፣ የጻፍከኝ ይቅር ለማለት ነው ፤ ስለዚህ አክብረህ አታዋርደኝም ።

የጻፍከው የትላንት ታሪኬን የዛሬ ድካሜን አይደለም ፣ የጻፍከው የነገ ተስፋዬን ነው  ። የጻፍከኝ ከአገር እንዳይወጣ ብለህ አይደለም ፣ የጻፍከኝ መንግሥቴን ሰጥቼዋለሁ ብለህ ነው ። የጻፍከኝ ከውርስ ይነቀል ብለህ አይደለም ፣ የጻፍከኝ የእኔ ሁሉ የእርሱ ነው ብለህ ነው ። የጻፍከኝ ለሞት አይደለም ፣ የጻፍከኝ ለሕይወት ነው ። የጻፍከው የሕይወቴ መጽሐፍ መግቢያው ፍቅርህ ፣ ማጠቃለያው መንግሥትህ ነው ።

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋና ይሁን ።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

26 Dec, 21:26


ከክርስቶስ ኢየሱስ ከሚለይ ከማንኛውም ንግግር ጆሯችሁን ድፈኑ፤ ከእርሱ ከተለየን ሕይወት የለንምና ::"ሥጋና ነፍስን የተወሐደ አንድ ሀኪም አለን፤ እርሱም በሰውነቱ ፍጹም ሰው የሆነ ፤በአምላክነቱ ፈጣሪ የሆነ በሥጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ፤በሞት ሕይወትን የገለጠ ከድንግል ማርያም እና ከእግዚአብሔር የተገኘ፤ በመጀመሪያ መከራን የተቀበለ፤ ከዚያ ቡሃላ ግን ሕማምና መከራ የማይደርስበት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ::

[ሰማዕት ወጳጳስ ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ወደ ኤፌሶን በላከው መልዕክቱ ምዕራፍ 7]

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

26 Dec, 04:00


ቅዳሴ ሰማያዊ ሕይወት ነው።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

25 Dec, 04:20


🌿🍂🌿🍂🌿

84 ዓመት

     መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሀና 84 ዓመት ቀንና ለሊት በፆምና በፀሎት፣ እለት እለት እያገለገለች ከቤተመቅደስ አትለይም ነበር ይላል። "እለት እለት" ሊያውም ቀንና ለሊት። ይሄ ሁሉ ዓመት ፈተና ሳይኖር ቀርቶ አይደለም።
   እኛ አንድ ግዜ እንመጣለን አንዴ እንቀራለን፣ ቀላል በሆኑ ምክንያቶች ወደኋላ እንቀራለን።
    ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በመኖሯ ምን አመጣላት እኛስ ብንኖር ምን እናገኛለን ለሚለው መልስ - እመቤታችን ጌታን ይዛው በ40 ቀኑ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ ሀና እሱን ለማየት በቃች። በዚያች ቅፅበት የሌለ ሰው እኮ አያገኘውም።
    ሚል 3 - የምትጠባበቁት ጌታ ድንገት በመቅደሱ ይገለጣል ይላል። መቅደሱ እኮ ሁሌም ቤቱ ነው ድንገት ይገለጣል ማለት ፀጋ የሚሰጥበት፣ ክብር፣ ኃይል የሚያድልበት፣ እለተ በረከት አለው።
ስንመኘው የነበረው፣ እግዚአብሔርን ስንለምነው የነበረውን ነገር ሊሰጠን ሲመጣ እኛ ደግሞ ከቤቱ እንዳንጠፋ።  በትጋታችን ልክ ዋጋ እንቀበላለን።
    በክርስትያን ህይወት ከሁሉ ከሁሉ ምን ይቀድማል? የሚቀድመው ቤ/ክ መምጣት ነው! ሳይመጡ መማር የለም፣ ሳይመጡ ማወቅ የለም፣ ሳይመጡ ንስሃ የለም፣ ሳይመጡ ቁርባን የለም፣ ሳይመጡ መለወጥ የለም። የአንድ ክርስቲያን የመጀመሪያው ስራው ወደ ቤ/ክ መምጣት ነው። ከመጡ ነው ማወቅ መሻሻል ያለው።

@KaleEgziabeher

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

23 Dec, 18:38


በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ሜሴጅ ይላኩ! ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን ይምረጡ!

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

22 Dec, 19:21


👉እንጨቶችን የፈጠረ ጌታ ካልተቸነከረ ዕፀ መስቀሉ በማን ደም ተቀደሰ?

👉ምድርን በውኃ ላይ ያጸናት ሞትን በሥጋ ካልቀመሰ ቤተክርስቲያን በማን ደም ዳነች?

👉የሕያዋን ጌታ የሙታንም ሕይወት ጎኑ በወታደር ጦር ካልተወጋ የሕይወት ውኃ ከማን ጎን ፈሰሰ?

👉የእግዚአብሔር በግ ካልታረደ የማን ሥጋ ለምእመናን የሕይወት ምግብ ይሆናል?

👉የእውነት ፀሐይ በመስቀል ጠፈር ላይ ካልኖረ ለዓለም ሁሉ ማን ያበራል?

👉የነቢያት እና የሐዋርያት አምላክ ካልተቀበረ የሙታንን መነሣት ተስፋ ማን ያሳያል?

👉የአዳም አምላክ ከአዳም ሴት ልጅ በነሣው ሥጋ ከሙታን ተለይቶ ካልተነሣ ማን በአብ ቀኝ ተቀመጠ?

👉የአዳም ልጅ የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ በአብ ቀኝ ካልተቀመጠ “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” ያለው የእግዚአብሔር ቃል በየት ይፈጸማል?

                       #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

19 Dec, 13:33


https://vm.tiktok.com/ZMkjmVR3Q/

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

19 Dec, 09:10


https://youtu.be/4HjMe7OWvO0?si=d4nhWklRkaYciJNh

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

18 Dec, 10:06


" ክፉ የሆነች ልማድ ሳበችኝ፣ በታዘዝኩላት ጊዜም በማይፈታ ማሰሪያ አሰረችኝ፡፡ ማሰሪያውም በእኔ ዘንድ የተወደደ ነው፤ ልማድ፣ በወጥመዷ ፈጽማ አሰረችኝ፡፡ በታሰርሁ ጊዜም ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ በማዕበሉም ያሰጥመኛል፤ በዚህም ደስ ይለኛል፡፡ ጠላት ሰይጣንም ዘወትር ማሰሪያዬን ያድስልኛል፤ በመታሰሬ ፈጽሞ ስደሰት አይቶኛልና፡፡ ኅፍረትና ጉስቁልኛ ሸፈነኝ፤ እኔ በፈቃዴ ታሰርሁ፤ ማሰሪያዬንም በቅጽበት በመበጣጠስ ከወጥመድ መውጣት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን አልሻም፤ እኔ በቸልተኝነትና በስንፍና የተያዝኩ ነኝና፡፡ ክፉ ለሆነች ልማድም የተገዛሁ ነኝና፡፡ እኔ ጎስቋላ በሆነ ስቃይ የታሰርሁና ለበጎ ነገር የማልጠቅም ሰነፍም ነኝ፡፡ እኔ አሁን ወደ አንተ ካልተመለስኩ እንደምትፈርድብኝ አውቃለሁና ወደ እኔ ትመለስ ዘንድም በእንባ እለምንሃለው፡፡ ስለዚህም ቁጣህን ከእኔ አዘግይ፤ ወደ አንተ መመለሴን፣ ንስሐ መግባቴንም ጠብቅ፤ አንተ ማንኛውም ሰው በእሳት እንዲቃጠል አትሻምና!! እንኪያውስ በምሕረትህ እታመናለው፣ በይቅርታህም እጸናለሁ፡፡ "

የሶርያው ሊቅ የቅዱስ ኤፍሬም ጸሎት

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

17 Dec, 05:30


[ታኅሣሥ 8 በዓሏ የሚከበረው ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ድንቅ ታሪኳ፤ በቀደምት ኢትዮጵያውያን የቀረበላት ውዳሴና ዓለም ዐቀፍ ክብሯ]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ከክርስቶስ የተቀበለችው ቃል ኪዳን ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው በመላው ዓለም ከጥንት ጀምሮ የምትታወቀው ከ273-306 ዓ.ም የነበረችው ሰማዕቷ ቅድስት በርባራ በሌሎች ሃገራት Αγία Βαρβάρα, Great Martyr Barbara በመባል ትታወቃለች።

💥 ከ305-311 በነገሠው በከሓዲው መክስምያኖስ (emperor Maximian) ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ ናት። እጅግ ውብ ስለነበረች ሰው እንዳያያት ጣዖት አምላኪ የነበረ አባቷ ለርሷም ለብቻዋ ሰገነት ያለው ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶላት አንድ አረማዊ መምህር ብቻ ወደርሷ እንዲገባ አደረገ።

ያሠራላት ሰገነት ከፍ ያለ ስለነበር አበባዎችን ይልቁኑ በምሽት የሚያበሩትን ከዋክብት የምሽቱ አስደናቂ ግርማ እየተመለከተች መደነቅ ጀመረች። በዚህ ጊዜ እነዚህ የአባቷ ጣዖታት አስደናቂ ዓለማትን እንደማይፈጥሩ ተረዳች። በሕይወቷ የዓለማት ፈጣሪን ለማወቅና በድንግልና ሕይወት ለመኖር ወሰነች። ብዙ የጋብቻ ጥያቄን ውድቅ አደረገች። በዚህ ምክንያት አባቷ ውጪውን እንድትለምደው ከግቢ እንድትወጣ ፈቀደላት።

በዚህ ጊዜ ከክርስቲያን ሴቶች ጋር በመገናኘቷ ስለ ምስጢረ ሥላሴ፣ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢርን አስረዷት። እውነተኛውን የድኅነት መንገድ በመረዳቷ ከእስክንድር ወደ ሄሊዎፓሊስ መጥቶ በነበረ ካህን በድብቅ ተጠመቀች።

በዚያ ወቅት አባቷ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት መስኮቶችና ቅንጡ የሆነ መታጠቢያ እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ምስጢረ ሥላሴን አስባ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም አዳኝ የኾውን የመስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡

አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም “ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ እስመ በሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ” ይላል ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም መስቀል ዓለሙ ኹሉ በርሱ በዳነበት በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት ተናገረችው፡፡

አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና “ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ ሰማች፤ ከዚያም ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡

በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤ ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የዳንኩት” አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡

በዚያም የሂሊኦፓሊስ ነዋሪ ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን ሲያሰቃይዋት አይታ ከርሷ ጋር በክርስቶስ ስም መከራን ለመቀበል በመወሰን አብራት መከራ መቀበል ጀመረች። ሁለቱም ሰማዕታትን በምስማር ሰውነታቸውን እየወጉ ያሰቃይዋቸው ነበር። ለመዘባበት ዕርቃናቸውን በአደባባይ ሊወስዷቸው ቢሞክሩም በቅድስት በርባራ ጸሎት ጌታ መልአኩን ልኮ በአስደናቂ መጎናጸፊያ ሰውነታቸውን ጋርዶታል።

በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ብዙ ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ።

ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤ በአባቷ ወደተዘጋጀው ወደመግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ (አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡

ከዚያም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት።

በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8, በ306 ዓ.ም. አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡ በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ ብልጭታ ይሣላል፡፡ ቅድስት በርባራም በዚህ ምክንያት በአማላጅነቷ ከጥንት ጀምሮ ባሉት ክርስቲያኖች ከመብረቅ አደጋና ከእሳት የምትጠብቅ እንደሆነች ይነገራል።

ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በመስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡

ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል ይዛ ይታያል፡፡ በዐዲስ አበባ በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ባሉት የግድግዳ ላይ ሥዕላት ላይ ቅድስት በርባራና ቅድስት ዮልያና ተሥለዋል። በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 8 በሚነበበው መዝገበ ቅዱሳን በሆነው ስንክሳር ላይ ቅድስት በርባራና ዮልያናን ታስባለች።

ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅድስት በርባራን አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር፤ ለምሳሌ ያኽል ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ቅዱስ አርከ ሥሉስ እንዴት እንዳመሰገኗት ብናይ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

17 Dec, 05:30


“ሰላም ለበርባራ ወዮልያና በፍኖተ ስምዕ እለ ቆማ፤
በድሮን እለ ፈጸማ
እለ ተጋደላ ከመ ሐራ
አርዑተ መስቀሉ ለክርስቶስ እለ ጾራ
መርዓዊሆን እስከ ረከባ
ድንግልናሆን እለ ዓቀባ”፡፡
(ሙሽራቸው ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ ድንግልናቸውን የጠበቁ፤ የክርስቶስ መከራ መስቀሉን የተሸከሙ፤ እንደ ጭፍሮች የተጋደሉ፤ ሩጫቸውንም የፈጸሙ፤ በምስክርነት ጐዳና የቆሙ ለኾኑ ለበርባራና ለዮልያና ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፡፡

ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ፡-
“ሰላም ለበርባራ እንተ አግሀደት ሃይማኖታ
እንዘ ታርኢ ሥላሴ በመስኮተ ቤታ
ኢያፍርሃ መጥባሕት ወሞሠርተ ሐጺን ኢያሕመመታ
ወሰላም ካዕበ ለዮልያና ካልዕታ
እንተ ሰቀልዋ በክልኤ አጥባታ”

(በቤቷ መስኮት የሥላሴን ምሳሌ እያሳየች ሃይማኖቷን የገለጠች ለኾነች ለበርባራ ሰላምታ ይገባል፤ ሰይፍም አላስፈራትም የብረት መጋዝም አላሳመመቻትም፤ ዳግመኛም በኹለት ጡቶቿ የሰቀሏት የርሷ ኹለተኛ ለምትኾን ለዮልያናም ሰላምታ ይገባል) በማለት የተቀበሉትን ጽኑ መከራ ጽፏል፡፡

ቅድስት በርበራ እመቤታችንን ለምና የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁት ላይ ያደረገችውን የመስከረም 25 ተአምሯን ደግሞ፦
"ሰላም ለበርባራ ወለዮልያና አምሳላ
በዛቲ ዕለት ዘአስተርአየት ኀይላ
በክልኤ ዕደው ዘሰረቁ መጽሐፈ ገድላ
ፈደየቶ ለአሐዱ እንባዜ እምኀበ ማርያም ስኢላ
ወለዐይነ ቢጹ ካልዕ አጽለመት ጸዳላ"

(የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁ በሁለት ወንዶች ላይ በዚህ ዕለት ኃይሏን ያሳየች ለሆነች ለበርባራና ርሷን በተጋድሎ ለምትመስል ለዮልያና ሰላምታ ይገባል። ከእመቤታችን ማርያም ለምና ለአንዱ መቅበዝበዝ የሁለተኛው ጓደኛውን ዐይን ብርሃኑን አጨለመች) በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ ተመሳሳይ ተአምርን እንደሠራች ይጽፋል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስ በመስከረም 25 ስንክሳር አርኬ።

💥 ❖የቅድስት በርባራ ዐለም ዐቀፍ ክብሯ❖💥

በእጅጉ የሚገርመው ከጥንት ጀምሮ በየክፍላተ ዘመናቱ እስከ ዛሬ ድረስ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በቅድስት በርባራ ከሚፈነዱ የጦር መሣሪያዎች፤ ከመብረቅ አደጋና ከድንገተኛ ሞት በቃል ኪዳኗ እንደምትጠብቅ ሲታመን፤ በጣሊያን የባሕር ኀይላችን ጠባቂ (the patron of the Italian Navy.) ይሏታል።

በቃል ኪዷና በእጅጉ ከመታመን የተነሣ በጊዜያችን ያሉ በርካቶች ኀያላን ሀገራት ብሪታኒያ (Royal Artillery, RAF Armoures, Royal Engineers) በካናዳ (Explosiv Ordance Technicaians) በአውስራሊያ (RNZAF Armourers) በኒውዝላንድ፤ በስፔን፣ በአሜሪካ፣ በግሪክ የቅድስት በርባራን በዓል በዐየር ኀይላቸው፣ በጦር ካምፓቸው፣ በባሕር ኀይላቸው ዲሴምበር 4 ላይ እንደሚያስቡ ጥናቶች በግልጽ ያሳያሉ::

በስፓኒሽና በጣሊያን ይታተም የነበረው መጽሔት መርከበኞች ከድንገተኛ አደጋ መርከባቸው ይጠበቅ ዘንድ ሥዕሏን ይይዙ እንደነበር ይጽፋል።

በሰሜን አሜሪካ የጦር ኃይልም ቅድስት በርባራ የምትታሰብ ሲሆን በጦር ኃይሉ ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ለሠሩ ምርጥ ወታደሮች በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ የቅድስት በርባራ ሥዕል ያለበት ሜዳልያ (ANCIENT ORDER OF SAINT BARBARA) ይበረከትላቸዋል። (https://www.fieldartillery.org/awards)
💥 (United States Field Artillery Association, fieldartillery.org. retrieved 23 January 2010,) (Cyprus Army notes on Saint Barbara, Army)

በሰሜን አሜሪካ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ 100 ማይልስ በሚገመት አግጣጫ ያለችው በቅድስተ በርባራ ስም ሳንታ ባርባራ Santa Barbara በመካከለኛው ካሊፎርንያ ከተማ ተሠይሞላታል፤ በተመሳሳይ መልኩ በስፔንና ፖርቱጋል ቦታ ላይ በብራዚል፣ በቺሊ፣ በኮሎምቢያ፣ በሆንዱራስ፣ በሜክሲኮ፣ በቬንዝዌላ፣ በፊሊፒንስ በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ አለ። በሊባኖስ ክርስቲያኖችም በጣም ትታሰባለች (Hammond Atlas of the World.1997.)፡፡

ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ሊቁ አርከ ሥሉስ ያወደሷት፤ ክብሯ በስንክሳር ላይ የተጻፈላት በርካቶች ቃል ኪዳናትን የተቀበለች ቃል ኪዳኗም ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ጥንታዊ ሥዕላት በብራና ላይ እንዳሉ ባውቅም በስሟ የተሰየመ ታቦት እንዳለ ግን ጥናቱ የለኝም።

💥 እኔ ከክብሯ በዐጭሩ በረከቷን ለመሳተፍ ያህል እንደጻፍኩ እናንተም ታኅሣሥ 8 በስሟ ለነዳያን በመመጽወት በቃል ኪዳኗ በመማጸን በረከቷን ተሳተፉ።

💥 ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።”
— (ሮሜ 13፥7) እንዳለ

ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ ፓስት ያደረኩት)

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

10 Dec, 03:54


አሐቲ ድንግል
#ማርያም ማለት ምን ማለት ነው?

ማርያም ማለት፦
እግዝእት:- እመቤት ማለት ነው የዓለሙን ንጉስ በመውለዷ ከፈጣሪ በታች የፍጥረት ንግስት ሆናለችና፤

ጸጋ ዘተውኅበት ለኩሉ ዓለም፦ ለዓለሙ ሁሉ የተሰጠች ጸጋ ማለት ነው። ለአበው በተስፋ የሰጣቸው ሲሆን ለእኛ ደግሞ ከመስቀሉ ሥር እናት ትሁናችሁ ብሎ ሰጥቶናልና። (ዮሐ ፲፱፤፳፮) ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ንግሲቲቱ በቀኝህ ትቆማለች የሚለውን የዳዊት መዝሙር ሲተረጉም In becoming the mother of creator she become the Mistress of all creation (የፈጣሪ እናት በሆነች ጊዜ የፍጥረታት ሁሉ ንግስት እመቤት ሆናለችና በማለት ተርጉሞታል። (መዝ 44፤9)

ተስፋ ማለት ነው፦ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ካለው ጀምሮ መድኃኒቴን የምትወልጅልኝ ልጄ እያለ ተስፋ አድርጓት በልቦናው መዝገብነት ይዟት የኖረ ስንቁ ናት። አበውም ድንግል ማርያምን መቼ ፀሐይ ክርስቶስን ወልዳልን ከቁረ መርገም ድነን አይተነው እያሉ ተስፋ አድርገዋት ነበር። ተስፋቸው ክርስቶስም ከእርስዋ ተወልዶ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ገብተዋል። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አረጋዊ ስምዖን "ጌታ ሆይ አገልጋይህን ዛሬ ታሰናብተዋለህ፥ አቤቱ በሰላም እንዳዘዝክ አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና በህዝብ ፊት ሁሉ ያዘጋጀኸውን ለአሕዛብ ብርሃንን ትገልጽ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ክብርን" በማለት ተስፋውን አይቶ አርፏል። (ሉቃ 2፥29)

የባሕር ከርቤ (Myrrh of the sea) ማለት ነው። ይህ ከርቤ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ከዘይት ጋር ተጨምሮ  በጠበብተ ኦሪት ተቀምሞ ለንዋያተ ቅድሳት ማክበሪያ የታዘዘ ሽቱ ነው። ሙሴ ደብተራ ኦሪቱን በኦሪት መቅደሱ ያሉትን ሁሉ በዚህ ሽቱ እንዲቀባ ታዟል። ሽቱ ያረፈባቸውን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮታል። ባሕር የተባለ ይህ ዓለም ሲሆን እመቤታችንም ከእርስዋ ስጋን ነስቶ ክርስቶስ ተብሎ ስሙ እንደ ዘይት ተዋህዶን ክርስቲያን ተብለን እንድንጣፍጥ የድኅነት መሳሪያ የመዓዛ መንፈሳዊ ምንጭ ናትና የባህር ሽቱ ትባላለች።

ሽቱ ያረፈበትን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ በልጇ ስም አምነው ተጠምቀው በእምነት የሚቀርብ ሁሉ ይጣፍጣልና ይላሉ አበው!

የባሕር ኮከብ (Star of the seas) ማለት ነው። ባሕር የተባለ ይህ ዓለም ነው፥ በባሕር የሚበላም የማይበላም ደግሞ ክፉም ፍጥረት እንዳለ በዚህ ዓለምም አማኒም ከሓዲም መናፍቅም ጻድቅም ኃጥእም ይኖራልና፥ ዳግመኛም ባሕር ከሁከት አይርቅም ይች ዓለምም ከሁከት አትርቅምና፥ በባህር ላይ ሲጓዙ በመርከብ ላይ ሆነው የንጋት ኮከብን አብነት አድርገው ከተጓዙ ካሰቡት ይደረሳል። ሰብአ ሰገልን ኮከብ እየመራ ቤተልሔም እንዳደረሳቸው ማለት ነው። እንዲሁም ሁሉ እመቤታችን በዚህ ዓለም የክህደት የኃጢአት  ሞገድ እንዳያጠፋን የተረፍንባት መርከባችን ናት።

ብርህት (Illuminated) ማለት ነው። ብርሃኗ ከፀሐይ ይበልጣል፤ መለወጥ የሌለባት የድኅነት በር ናት ውበቷም በፍፁም ክብርና ሞገስ የተሸለመ ነው፤ እውነት በእውነት የመና መሶብ ነች። ጽድልት መባሏ ነውርና ነቀፋ የሌለበት የእግዚአብሔር እናት በመሆኗ ነው።

አሐቲ ፍቅርት፦ ብቻዋን የምትወደድ (Beloved One) ማለት ነው። ንጉስ ውበትሽን ወዷልና ተብሎ የተዘመረላት እግዚአብሔር መዓዛ ድንግልናዋን ወዶ ከእርሷ ሰው እስኪሆን ድረስ፥ ፍጥረትን ሁሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብቅሎ የሚመግብ ጌታ ጡቶቿን ጠብቶ እስከማደግ ድረስ ደርሶ ብቻዋን በእግዚአብሔር የተወደደች ናትና።

የባሕር ምንጭ (Drop of the sea) ማለት ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም በሦስት ዋና ዋና የድኅነት ምንጭ ሆናለችና። የጥምቀት፥ የቁርባን፥ የቅዳሴ ናቸው። ይህም ማለት ከጎኑ የፈሰሰው ውሃ፥ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ከእርሷ ባህሪ የተገኘ ነውና ጌታ የተጠመቀውም ከእርሷ በነሳው ስጋ ነው የምንበላው ቅዱስ ስጋው የምንጠጣው ክቡር ደሙ ከእርሷ የነሳው ነውና የቁርባን ምንጭ ትባላለች።

ዳግመኛም ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው።.... (ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው አንብቡ)

አሐቲ ድንግል በአባ ገብረኪዳን ግርማ ገጽ 257 የተወሰደ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

08 Dec, 09:39


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ✧  ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ ✦
 
ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ
ፅድቄ ነው ፍቅርህን መመስከሬ
ጌታዬ አምላኬ እልሃለው/2/
ስጠራህ ሳመልክህ እኖራለሁ/2/

አይቼ የእጅህን ተአምራት
ሰምቼ የቃልህን ትምህርት
ሆኛለሁ ምስክር ለአዳኝነትህ
ሥጋን ተዋሕደህ ለኛ መገለጥህ/2/

አዝ--------------

ተከተልኩ ሁሉን ነገር ንቄ
መድሃኒት መሆንክን አወቄ
ከመልካሟ ቤትህ ተጠልያለሁ
የእጅህን በረከት ካንተ እጠግባለሁ/2/

አዝ--------------

እርፍ ይዤ ላላርስ ወደ ኃላ
እያየሁ መረቤን ስትሞላ
እመካብሃለሁ ባንተ መድኅኜ
አምላኬ ነህና የምትራራ ለኔ
አባቴ ነህና የምታስብ ለእኔ

አዝ--------------

ቸርነት ምህረት ከበዛልኝ
ለስምህ ውዳሴ ቅኔ አለኝ
ክብሬና ሞገሴ አንተ ነህ ጌታ
ተመስገን ተመስገን ጠዋትና ማታ /2/  

        ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

 

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

07 Dec, 16:45


‹ኢየሱስ ሰርግ ቢጠሩት በቃና ዘገሊላ ውኃውን ጠጅ አድርጎ አጠጣ፡፡
በሰው ሰርግ እንደዚህ የሆነ በራሱ ሰርግ እንዴት ይሆን?
የእግዚአብሔርን ልጅ ሰርግ አይቼ ከድግሱም በልቼ ጠጥቼ ከዚያ ወዲያ ምነው በሞትሁ›

/አለቃ ዘነብ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም./

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

18 Nov, 19:58


«#ሁሉን_የፈጠረ፥ ሁሉን የፈጸመ፥ ሁሉንም የጀመረ፥ ሁሉን የያዘ፥ ሁሉንም የጨበጠ እግዚአብሔር። መላእክትና የመላእክት አለቆች፥ መናብርትና ሥልጣናት፥ አጋዕዝትና ኃይላት፥ ፀሐይና ጨረቃ፥ ከዋክብትም ድርገታትም የሚሰግዱለት፤ ተገዦቹና ጉልቱም ናቸውና። በሁሉ ባለጠጋ ሲሆን ራሱን ከሁሉ ደሀ አደረገ። ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው፥ እስከ ሞትም አደረሰው።»
#ቅዳሴ_ማርያም (ቊ. ፩፻፳፮–፩፻፳፯)።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

15 Nov, 04:46


እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም (እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ) ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፡፡
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፡፡
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፡፡
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ፡፡
እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡
ወተመይጠት ማርያም ሀገረ እስራኤል አቡሃ።
ነቢራ በግብፅ ኣርብዓ ወክልኤተ አውራኀ፡፡
ይሰግዳ ላቲ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ።
እምይእዜሰ ነገፍኩ ላሀ ፡፡
ለእምየ በእትወታ ረኪብየ ፍሥሓ፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ትርጉም
እመቤቴ ማርያም ሆይ እስከመቼ ድረስ በባዕዳን አገር ትኖሪያለሽ?
ወደ አገርሽ ገሊላ አሁን ተመለሺ እንጂ
ናዝራዊ ከሚሰኝ ሕፃን ልጅሽ ጋር ተመለሺ
ዖዝያን ንጉሥ ስለ ቅዱሳን ክብር እንደተናገረው፥ አንድም በንጉሥ ዖዝያን ዘመን ስለ ቅዱሳን ክብር እንደተነገረው
የልጅሽ የብቻ አባቱ ከሰማይ ሆኖ ከግብፅ ምድር እንደሚጠራው፥ እንደጠራው እንድትኖር
ማርያም ወደ አባቷ አገር ወደ እሥራኤል ተመለሰች
በምድረ ግብፅ በስደት አርባ ሁለት ወራትን ከኖረች በኋላ፥ ኖራ
የጢሮስ ልጆች ስጦታውን አቅርበው ይሰግዱላታል፥ ይስገዱላት፥ እንደሰገዱላት
እኛም እንዲሁ ስጦታዋ የሆነ ምስጋናዋን አቀረብንላት
በእመቤታችን ከግብፅ ምድር መመለስም ልቦናችን ሐሴት አደረገች።

🌹@weldwahid🌹

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

14 Nov, 05:21


ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15

ጢሞቴዎስ በሕጻንነቱ ያነባቸው የነበሩት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው ካልን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው በዚያን ሰዓት ገና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አልተጻፉም ነበርና።

ብሉይ ኪዳን በሐዲሰ ኪዳን የተብራራ ስለ ክርስቶስ የሚናገር በውስጡ ሐዲስ ኪዳን የተሰወረበት መጽሐፍ ነው ሊቁ አውግስጢኖስ ይህንን በግልጥ ነግሮናል።


ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ “ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል፡” እንዳለው እኛ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በሙሴ ሕግና በነቢያት መጻሕፍት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገሩትን ከመማር ብሉይና ሐዲስን አስተባብሮ ከመያዝ ወደ ኋላ እንል ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍት አያሰናብቱንም ።የዮሐንስ ወንጌል 1፥45

ዲ/ን ዘሚካኤል እሸቱ
ህዳር 5/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ /ኢትዮጵያ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

14 Nov, 04:23


በሰማዕቱ የእስጢፋኖስ ወዳጆች ፤ ሰማዕቱ አለሁ ይበላችሁ።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

06 Nov, 08:31


((((. ጥቅምት 27. ))))

+++ አባ ጽጌ ድንግል +++

#የማኅሌተ_ጽጌ ደራሲ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡

በዕለታት በአንዱ ቀን በጻዲቁ በአቡነ ዜና ማርቆስ በተገደመው ደብረ ብስራት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሄዶ ሳለ ጻዲቁ አቡነ ዜና ማርቆስ በትንቢተ ኢሣይያስ የተነገረውን በኅብረ አምሳል ያጌጠውን ‟ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ ፤ ከእሴይ ግንድ በትር ትወጣለች ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል" የሚለውን ሲያነብ ቢሰማ ቀድሞውንም ቃሉን የሚያውቀው ይሁንና ትርጓሜውን ያልተረዳ መሆኑን ጠይቆ እንዲተረጉሙለት ቢጠይቅ ጻዲቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ንባቡን ከትርጓሜ ትርጓሜውን ከምስጢር አስማምቶ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡

+ በእንተ ማኅሌተ ጽጌ +

ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ #ማኅሌት ማለት ኀለየ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውን ምስጋና፣ መወድስ ማወድስ ማለት ነው፤ #ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው፡፡

🌹🌹🌹🌹

#ማኅሌተ_ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ የፍሬ ምስጋና መዝሙር መወድስ ማለት ነው፡፡ ይህም አበባ ተብላ የተጠራች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ፍሬ የተባለው ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎች እና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡

የአባ ጽጌ ድንግል በረከታቸው ይደርብን🙏🙏🙏

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

06 Nov, 05:16


"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

31 Oct, 19:29


በረከታቸው ይደርብን 🙏🙏
የህንድ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤ/ክ ፓትርያርክ ማር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

26 Oct, 08:11


ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት ፲፯
በዓለ ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

25 Oct, 11:06


https://youtu.be/OncVfFPScXg

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

23 Oct, 05:19


#ድንግል ሆይ የኔን አመንዝራነቴን እናገራለሁ ያነቺን ንጽሕና የልጅሽን ቸርነት አወራለሁ፡፡
#ድንግል ሆይ የኔን ስሕተት ያንቺን ማማለድ የልጅሽንም መታገስ እናገራለሁ፡፡
#ድንግል ሆይ የኔን ስንፍና ያንቺን ምክር የልጅሽንም ይቅርታ እናገራለሁ፡፡

መጽሐፈ አርጋኖን

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

21 Oct, 12:07


የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይጻፍብኝ በልዩ ኅብር በልዩ ኅብር

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

18 Oct, 15:31


https://www.instagram.com/michael.eshetu4/profilecard/?igsh=MTVnOWRvYjExZWZ4Nw==

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

11 Oct, 20:47


አሐቲ ድንግል - በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የሚያረካ የመጻሕፍት ፊት አውራሪ ፤ የነገረ ማርያም ጥም ቆራጭ ፤ የትርጓሜ ድግስ ፤ የምሥጢራት ዝናም ፣ ያለ ስስት በፍቅር የተጻፈ ቅኔ መወድስ ፤ እንደ ሊቅ በምሥጢር እየተራቀቁ እንደ መናኝ በፍቅር እሳት እየተማወቁ የጻፉት በጸዳለ ምሥጢር የተጽደለደለ መጽሐፍ ተከስቶአል:: እመቤታችንን የሚወድ ሁሉ በፍቅርዋ ባሕር ለመዋኘት የሚችልበት እጅግ እጅግ እጅግ ውብ መጽሐፍ ፤ በጸሎት መንፈስ ለብቻ ተኾኖ ካልሆነ ሊነበብ የማይችል በዕንባ የሚያሰጥም መጽሐፍ ፤ ሌላ ነገር አንብበህ በዚያው ዓይንህ ልታነበው የማይገባ ዓይኖች ጾመው ሌላ ከማየት አክፍለው ሊያነቡት የሚገባ የወላዲተ አምላክ የቀሚስዋን ዘርፍ በፍቅር የሚያስነካ መጽሐፍ እነሆ ከደጃችን ነው::

እንደ ቃና ሊቀ ምርፋቅ መልካም የወይን ጠጅ “አሐቲ ድንግል" እያለች በመናኛ መጻሕፍት ለምን ሰከርን የሚያሰኝ የመጽሐፍ ወይን ታዩ ዘንድ ኑ! !

ሥዕል :- ሠዓሊ ዲ/ን ዮርዳኖስ ዘሪሁን (ገብረ ኪዳን) እንደሣለው

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

11 Oct, 11:49


https://vm.tiktok.com/ZMhDGCq3L/

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

11 Oct, 04:31


https://vm.tiktok.com/ZMhASQtxV/

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

10 Oct, 05:22


ቃለ ዓዋዲ(ቅዱስ ዮሐንስ)

➽ዮሐንስ የሚለብሰው የግመል ጸጉር ነበር። የግመልፀጉር የመልበሱ ምክንያትና ምሳሌ :-

🔵፩:-ግመል ምን ፀጉር አላትና የግመል ፀጉር ይለብሳል ቢሉ ከጅራቷ ቢፈልጉ ፀጉር አያጡም እናቱ ያንን አስማምታ አልብሳዋለች።

🔵፪:-ለጊዜው ኑሮው ገዳም ነውና ለልብሱ ሲሉ ወንበዴዎች እንዳይጣሉት የግመል ፀጉር ተርታ ልብስ አለበሰችው።

🔵፫:-አንድም ደግሞ ምታለብሰው ብታጣ የግመል ፀጉር አትታ አለበሰችው።

🔵፬:-አንድም ትእምርተ ምናኔ ነው። ለምናኔ በሄዳችሁ ጊዜ ተርታ ልብስ ለብሳችሁ አልባሌ መስላችሁ ኑሩ ለማለት የግመል ፀጉር ልብስ ለበሰ።

🔵፭:- አንድም ግመል በቀለኛ ናት አንድ ቀን አጥብቆ የመታትን እስከ ስድስት እስከ ሰባት ዓመት ኖራ አትረሳውም። ስፍራ ሲመቻት ደብዳቢዋን ትረግጠዋለች ገደል ገፍታ ትጥለዋለች እርሱም "ወይወድይዎሙ ውስተ እቶነ እሳት" የምትል ሕገ በቀል ወንጌልን አስተምራለሁ ሲል የግመል ፀጉር ለበሰ።

🔵፮:- አንድም ግመል ሁለት ግብር አላት። የሚበላና የማይበላ "እስመ ግመል ያመሰኩዕ ወኢኮነ ንፉቀ ሰኮናሁ" እንዲል ዘሌ 11:4 እንደ ላም እንደ በሬ ምንዝሃ ታወጣለች እንደፈረስ እንደበቅሎ ሰኮናው ጽፉቅ ነው። እርሱም ሕገ ሕዝብ ወለአሕዛብ ወንጌልን አስተምራለሁ ሲል የግመልስ ፀጉር ለበሰ።

🔵፯:-አንድም "ገመሎ" የሚባል እንጨት አለ አድርቀው ከውኃ ይነክሩታል ቆይቶ ጭረት ይወጣዋል ኤልሳቤጥ እናቱ ያንን ታትታ አልብሳዋለች።

====

➽መጥምቁ ዮሐንስ ምን ይመገብ ነበር?

🌿ዮሐንስ የሚበላው እንቦጣ የሚባል ቅጠል ነበር በልሳነ አቴን ቀምሲስ ይለዋል።

🌿ወመዓረ ገዳም አለ የማጎ ማር ሲል ነው ይህንንም ማር ይመገብ ነበር።

🌿 አንድም በቁሙ አንበጣውን ይበላው ነበር። በዐረቡ "አልጅራድ" ይለዋል አንበጣ ሲል ነው።

🌿 ሶምሶንም ከአፈ አንበሳ ማር አግኝቶ በልቷል ኤልያስም ምግብ በአፈ ቋዐ እየመጣለት ተመግቧል ዮሐንስም በቁሙ አንበጣውን ይበላው ነበር።

🌿ወመዓረ ገዳም ባለው "ወመዓረ ጸደና" ይለዋል የጣዝማ ማር ነበር።

🌿 መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ አንበጣና ማር መመገቡን ሊቃውንት እንዲህ ይፈቱታል። "አንበጣ ዘይቤ ልዕልና ስብከቱ ወመዓር ዘይቤ ጣዕመ ስብከቱ ይእቲ" ብለዎ ተርጉመውታል። አንበጣ የስብከቱ ልዕልና ማር ደግሞ የስብከቱ ጠዓም ምሳሌ።

የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

09 Oct, 07:48


+ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማን(The Martyrdom of St. Arbsima (Repsima) the Virgin) በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይሉናል?

የተሐድሶ የስሕተት አዘቅት አቀንቃኞች 'አሁን በቅርብ የመጣች....' በሚል ጸያፍ አነጋገር ሲዘልፉ ይደመጣሉ፡፡

➾ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ Hripsime (Armenian: Հռիփսիմէ), በሦስተኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ጣልያን የተወለደች ሲኾን በሰማዕትነት ያረፈችውም በ 290 ዓ.ም(died c. 290) መኾኑ መገንዘብ ተገቢ ነው።

➲ በውኑ ስለ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በትርጓሜ መጻሕፍት አልተነገረምን?!

👉 የመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ይናገራ!! መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶቾ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባቡና ትርጓሜው አዳኝተን(ዳኛ አድርገን) እንዲህ እንላቸዋለን፡፡

❖ ጸሎት ዘጎርጎርዮስ ቅድመ ግብዓተ መንጦላዕት(ወደ መቅደስ ከመግባት አስቀድሞ ጎርጎርዮስ የጸለየው ጸሎትን) ሲተረጉም:-

➨ ዲዮቅልጥያኖስ(Emperor Diocletian) መልከ መልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኝአላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በያገሩ ሰደደ፤ ይህች አርሴማ ፸፪ (72) ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣለች፤ ኸያ ዓራቱ ደናግል፤ የቀሩት መዓስባን(ያገቡ) ናቸው፡፡ እመ ምኔቲቱ አጋታ(Agatha(Ghana)) ትባላለች። እየፈለጉ ካለችበት ደረሱ፡፡

➦ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት፡፡ መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል፤ እስዋን አምጡልኝ አላቸው፡፡ እስዋም እንዳስፈለጋት አውቃ አርማንያ ወረደች፡፡ እሱም ከዚያ እንደ ወረደች አውቆ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፤ እንዲህ ያለች ብላቴና ወዳገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ ላከበት፡፡ ቢያስፈልግ አገኛት፤ ቢያያት እንደ ፀሐይ ስታበራ አያት፤ ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ ለሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን ይህችን ብላቴና ለምኝልኝ አላት፡፡ አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ ይሁን አለችው፡፡

➦ ኋላ ግን ለሰማያዊ መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቸሻለሁና ይህ ርኩስ እዳያረክስሽ እወቂ አለቻት(told her that she must not forsake her true Bridegroom, the Lord Jesus Christ)፡፡ ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት፤ ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው፡፡

➥ ንጉሥ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት፡፡ ከዚያ አያይዞ መላውን አስፈጅቷቸዋል፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ስራ ማሰራት ኋላ ማጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውሃ የማይቀምስ ሆነ፡፡ ብላቴኖቹ ሲሞት እናያለን? አደን እንጂ ኃዘን ያስረሳል፤ አደን ይዘነው እንሂድ ብለው ይዘውት ሄዱ፡፡ በዚያ ባለበት ዕሪያ ሁኖ ቀርቷል፡፡

➦ ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መልአክ ለእኅቱ ከጎርጎርዮስ (Saint Gregory, Bishop of Armenia) በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት። በሃይማኖት ምክንያት ተጻልቶት ከአዘቅተ ኲስሕ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ፡፡ መልአክ ላንዲት መበለት ነግሮለት አንድ ፥ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት ፲፭ (15) ዓመት ያህል ኑሯል፡፡

➦ የኒህ ክርስቲያን አምላክ ጽኑ እንጂ ነው እንዳለ ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው ሐብሉን ቢስቡት ከሰል መስሎ ወጥቷል፡፡ ወንድሜን አድንልኝ አለችው፡፡ ያለበትን ታውቂውአለሽን አላት፡፡ አዎን አለችው፡፡ አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን አሳይኝ ብሏት አሳየችው፡፡

➦ ዓፅመ ሰማዕታትን አስቀብሮ በዪ ውሰጂኝ አላት፡፡ ይዛው ሄደች፡፡ አንተ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው፡፡ ወአድነነ ርእሶ ወአንገሥገሠ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል ይላል፡፡ ግዕዛኑን (አዕምሮውን) አልነሣውም ነበርና ይሁን አለው። እንዳይታበይ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል፡፡

➦አስተማረው አሳመነው አጥምቀኝ አለው፡፡ ማጥመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ፤ ለኔ ስልጣን የለኝም አለው፡፡ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል፡፡ {መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው፤ ሥርዓተ ቅዳሴ፤ ምዕራፍ ፪፤ ገጽ. 20 -21፤ Coptic Synaxarium, Tout 29}

✞ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ Their intercession be for us, and Glory be to Our God, forever, Amen.✞✞✞

ዘማርያም ዘለቀ

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

08 Oct, 05:00


አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቁርጥ ልመናችንን ስማን፡፡ድዳ ለነበሩት ቃል፡ ለተሰበሩት ምርኩዝ፡ ለእውራን ብርሃን፡ ለአንካሶች መሄጃ፡ ለምጻሞችን የምታነፃ ሆንካቸው፡፡ በደዌ የተያዙትን አቤቱ አዳንህ፡፡ ደንቆሮዎችን ፈወስህ፡፡

ሞትን ዘለፍከው፡፡ ጨለማን አስወገድከው፡፡ ብርሃንን የፈጠርክ ሕልፈት የሌለብህ ፀሐይ፡ የማትጠፋ ፋኖስ፡ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የምታበራ ፀሐይ፡ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠርክ ሆይ ቁርጥ ልመናችንን ስማን፡፡

ሰውን ለማዳን ለሁሉ ተገለፅህ፡፡ ነፍስን የመለስካት አንተ ነህ፡፡ ሁሉን እንደሚገባ ማሰብን አስቀደምህ፡፡ መላእክትን የፈጠርህ፡ የሁሉ አባት፡ የሁሉ ጌታ፡ የዓለም ጌጥ፡ ምድርን የፈጠርካት አንተ ነህ፡፡ እንደ ፈቃድህ የሆነውን ልመና ስማን፡፡

ዓለም ሳይፈጠር የነበርህ ጥበብና እውቀት፡ ከአብ ወደዚህ ዓለም ተላክህ፡ ይህ አኗኗር የማይለወጥ፡ የማይፈርስ፡ የማይመረመር ነው፡፡ የማይታይ መንፈስ ነው፡፡ ይህን የተናገርህ አንተ ምስጉን ነህ፡፡ ስምህም፡ ምስክርነትህም የተደነቀ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ አገልጋዮችህ እናመሰግንሃለን፡፡

ጸሎተ ኪዳን

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

07 Oct, 18:14


የማትለወጥ ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኛ ዘንድ የነበረውን ጨለማ በአባትህ ፈቃድ አራቅክልን፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን አወጣኽን፤ ከሞት አድነህ ሕይወትን ሰጠኽን፤ ከመገዛት ነጻ አወጣኸን፤ በመስቀልህ በሰማይ ወዳለው ወደ አባትህ ያቀረብከን አቤቱ በወንጌል መራኽን፤ በነቢያትም አረጋጋህን፤ ያቀረብከን አምላክ አንተ ነህ፤ ጌታ ሆይ ያንተን ስም ሰምቶ ሞት ይደንግጥ፣ ቀላያት ይሰንጠቁ፣ አለማመን ይራቅ፣ ወንጀለኛ ይቸገር ፣ ቁጣ ጸጥ ይበል፣ ቅናት ጥቅም አያግኝ፣ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ፣ መርዝ ያላቸው የፍጥረት ወገን ይጣል፣  የእግዚአብሔር ልጅ  ኢየሱስ ሆይ በልቡናችን ለዘለዓለም ንገሥ ። አሜን !

ጸሎተ ኪዳን

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

07 Oct, 12:30


ዝክረ ዮሐንስ

የልጃችንን ዮሐንስ ዳንኤል 12ኛ ቀን መታሰቢያ በደብራችን ዐውደ ምሕረት በጸሎት እና በማጽናኛ መርሐግብራት ስለሚደረግ ሁላችሁም እንድትገኙ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

🗓 መስከረም 29/2017
⌚️ 11:00
📍 ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ

አድራሻ ፦ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፊት ለፊት

አዘጋጅ ስምዓ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት

1,673

subscribers

565

photos

44

videos