ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services @sebeztraining Channel on Telegram

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

@sebeztraining


የአለም አቀፍ ( የአስመጪና ላኪነት) ንግድ Import Export
📝ሥልጠና 🖍Training
💼ማማከር 📒Consultancy
👷‍♀️ሙሉ ስራ 👷‍♂️Outsource
ስለ ስልጠናችን ለማወቅ @sebeztrainingbot
www.sebeztraining.com/courses
www.sebeztraining.com

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services (Amharic)

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services የሚገኝን ባቡሯነት ላይ ሰብስክዎችን ለመጠቀም ፣ ላስከተለያይ እና ለመቆጣጠር በሚያመነዝሩበት ቦታ ነጻ ነን። እኛ ይህንን የሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት በመጠቀም ምንድን ነው ፡፡nnሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services ከዚህ በታች የሚቀጥልን እና በአለም አቀፍ (የአስመጪና ላኪነት) ንግድ (Import Export) ሥልጠናን እና ማማከርን በማስመጣጠብ ጥቅምት ለሚቀርብ ነው። በምላሹ በአለም አቀፍ ከፍተኛ የንግድ ቡድን ውስጥ በመኖር ለሚከበሩ እና የሥልጠና እንስሳት በተለያዩ ክፍሎች በመሠረት የሚያረግፉን እና ማከር አገልግሎት በመመልከት ለሚቀጥሉበት መስሪያ ነው።nnየሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services ስለ እኛ ለማወቅ @sebeztrainingbot ድረገው እናመሰግናለን። የተጨማሪ በመሆን ተጨባጭ ማግኘት እና ግንባታዎችን በተግባር ለማቅረብ እና በመድገም የሚያስተላለፍ እንዲሆኑ ማስታወቅ እና ለመረዳት የሚጠፋ እና ነገር እንጠቀማለን። በዚህ ቦታ ላይ በእኛ ላይ ሰብስክ ለሚቀጥል ለማወቅ እና መገናኛ አገልግሎት ለሚጽፋ እንችላለን።nnምንጊዜ እና እንደምንጠበቅበት የሚያዘንብበት እንቅስቃሴ ለመረዳት እና ለስለስ ለመጠን እና ለሥልጠና ማማከር አገልግሎት በመዘጋጀት እንለቅጣለን። እናትና ጓደኞች ለስልጠና እና ማማከር አገልግሎት እና ብዙዎች ለተጠቃሚዎች እንዲሁም እናቶች ለሚጋገሩ ወይም ተጠቃሚዎች ለሚቀጥሉ እርምጃ ለሚሰራ። እኛ የሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services እናመሰግናለን።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

13 Feb, 16:01


" ከታክስ በፊት 34.4 ቢሊዮን ብር አትርፊያለሁ " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች በማፍራት አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቹን ብዛት 80.5 ሚሊዮን ማድረሱን አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ሪፖርት ያቀረቡት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ምን አሉ ?

➡️ 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች አፍርተናል።

➡️ 9.3 ሚሊዮን የአዳዲስ ሲም ካርድ ሽያጭ የተከናወነ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ8% ጭማሪ እንዲሁም ከእቅድ ጋር ሲነጻጸር የ113% አፈጻጸም አለው።

➡️ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 7.5 % እድገት በማሳየት የተጠቃሚዎች ቁጥር 43.5 ሚሊዮን ደርሷል።

➡️ የሞባይል ኢንተርኔት ትራፊክ ማለትም (በሞባይል ኔትወርክ የተላከ እና የተቀበለው የዲጂታል መረጃ መጠን) በተመለከተ በበጀት አመቱ እስከ ህዳር ወር ድረስ 642.2 ቢሊዮን ሜጋ ባይት ትራፊክ ተመዝግቧል። ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ48.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

➡️ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት 5% ጭማሪ በማሳየት የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 784.1 ሺ ደርሷል።

➡️ በአጠቃላይ ከባለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የደንበኞች እድገቱ በ7.9 በመቶ አድጓል።

ኩባንያው ምን ያህል አተረፈ ?

➡️ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 61.9 ቢሊዮን ገቢ አግኝተናል። ይህም የዕቅዳችን 90.7 በመቶ ያሳካ ነው።

➡️ ከታክስ መሰል ወጪዎች በፊት ያለው ምጣኔ (EBITDA) 55.5 በመቶ ነው። ከታክስ በፊት 34.4 ቢሊዮን ትርፍ ተመዝግቧል።

➡️ ከአጠቃላይ ከገቢ ውስጥ 72.61 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን በውጭ ምንዛሬ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

06 Feb, 11:50


#ሰበር_መረጃ

⭐️ አስመጪዎች መክፈል የሚችሉት ቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው።
***
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስመጪዎች ያለባንክ ዋስትና መላክ የሚችሉት ቅድመ ክፍያ/advance payment መጠን ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው።
ላለፉት 27 አመታት ሲተገበር በቆየው አሰራር መሰረት አስመጪዎች ያለባንክ ዋስትና ለሚያስገቡት እቃ በቅድሚያ መላክ/መክፈል የሚችሉት የውጭ ምንዛሬ መጠን ከ5 ሺ ዶላር መብለጥ እንደማይችል የማእከላዊ ባንኩ መመሪያ ይደነግጋል።
ሆኖም ከ5ሺ ዶላር በላይ ቅድመ ክፍያ መፈፀም ከፈለጉ ከአገር ውስጥ ባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበር።
የቅዳሜ ገበያ ምንጮች እንደገለፁት አሁን ማእከላዊ ባንኩ ያለዋስትና መላክ በሚቻለው ቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ጭማሪ ለማድረግ መመሪያውን እየከለሰ ይገኛል።
ምንጮች የጭማሪ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ከመግለጥ ቢቆጠቡም አዲሱ መመሪያው ግን በቀጣይ መጋቢት ወር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

05 Feb, 05:18


የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያን ለማሻሻል በወጣ መመሪያ ቁጥር 188/2017  መሠረት ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ መለያ ኮድ (Unique QR code) የሌለው ደረሰኝ መጠቀም የማይቻል መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ልዩ መለያ ኮድ (Unique QR code) ያለበት የደረሰኝ ህትመት ለማሳተም  ወደ ገብረ ሰብሳቤ ቅርንጫፋችሁ ስትሄዱ ልታሟሉት የሚገባቸው ሁኔታዎች
ሀ ለአዲስ/ለመጀመሪያ ጊዜ አመልካቾች

1.ፎርም ተሞልቶ ማህተም ይደረግበታል፣ ፎርሙን የሚሞላው ስራ አስኪያጅ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ብቻ ነው፣
2. ንግድ ፈቃድ  ኦርጅናል እና ኮፒ
3. ንግድ ምዝገባ  ኦርጅናል እና ኮፒ .
4. ቲን  ኦርጅናል እና ኮፒ  
5. ቫት  ተመዝጋቢ ከሆኑ ኦርጅናል እና ኮፒ 
6. የተለያዩ የሥራ ዘርፎችና ቅርንጫፎች ካሉት በናሙናው ላይ መመዝገብ አለበት፣
7. ሥራ አስኪያጅ ወይም በድርጅቱ ስም የተሰጠ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ያለው እና የሥራ አስኪያጅ 1 ጉረድ ፎቶ  ፣  
8. ድርጅቱ የንግድ ምልክት /logo/ ካለው ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የእውቅና  ፍቃድ፣
9.. የደረሰኝ ህትመት አጠቃቀም መከታተያ ካርድ ካለዎት አዲስም ሆነ ቀጣይ ለማሳተም ሲመጡ ካርዱን ይዘው ይምጡ
ለ ለነባር /ቀጣይ አሳታሚዎች
1.ፎርም ተሞልቶ ማህተም ይደረግበታል ፎርሙን የሚሞላው ስራአስኪያጅ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ብቻ
2. የደረሰኙ የታተመዉ  የመጨረሻ ቁጥር ኮፒ ከጀርባው ማህተም ይደረጋል፣
3.ቲን  ኦርጅናል፣ ቫት  ኦርጅናል፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ  ኦርጅናል እና ንግድ ምዝገባ  ኦርጅናል
4.  ሥራ አስኪያጅ ወይም በድርጅቱ ስም የተሰጠ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ያለው፣
5.  የደረሰኝ ህትመት አጠቃቀም መከታተያ ካላችሁ ካርዱን ከሌላችሁ የስራ አስኪያጅ1ጉርድ ፎቶ ይዘው ይምጡ፣
ሐ  መንግስታዊ ላልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የመሳሰሉት
1.  ፎርም ይሞላል፣ ፎርሙን የሚሞላው ስራአስኪያጅ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ብቻ  ሰርተፍኬት ኦርጅናል፣ ቲን ኦርጅናል፣

2. ሥራ አስኪያጅ ወይም በድርጅቱ ስም የተሰጠ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ያለው፣
    የሚታተሙ  ዋና ዋና የደረሰኝ አይነቶች
1. Cash Sales /VAT,TOT, Exempt
2. Credit Sales/VAT,TOT, Exempt
3. Cash Receipt Voucher
4. Purchase Voucher
5. Withholding tax on payment
6. Employers tax deduction reciept
ሙሉ ፎርሙን ከታች ያገኙታል ።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

29 Jan, 06:50


የቤቶችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ሥርዓት እንደ ሀገር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ
January 28, 2025
የቤት ችግርን ለመቅረፍ ይቋቋማል ለተባለዉ ስርዓት ጥናት መደረጉ እና የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። 35 በመቶ በሀገሪቱ የሚገነባው የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበራት መገንባት አለበት ተብሏል። ይህን ለመገንባት ሁለት መሰረታዊ ችግሮች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን እነርሱም የመሬት አቅርቦት እና የፋይናንስ ችግሮች መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ አቶ ፀጋዬ ሞሼ እንደተናገሩት አዲስ በሚወጣው የመሬት ሊዝ አዋጅ 30 በመቶ የሚሆነው መሬት ከተሞች በምደባ ከሚያቀርቡት አስገዳጅ ሆኖ ለመኖሪያ ቤት መዋል እንዳለበት እና ይህም የቤት ችግርን እንደሚቀርፍ ታስቧል። ይህን ተከትሎ የፋይናንስ ችግርይ ለመቅረፍ " Housing Finance System" እንደሀገር ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱንና ስርዓቱን ለማቋቋም ጥናት መጠቱና የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸው አስረድቷል። ከ 1999 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ የተገነባው ቤት 62 ሺህ አይበልጥም አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ግን ባለፉት ስድስት ወራት 20 ሺህ 754 ቤቶች መገንባት መቻሉን ካፒታል ለመረዳት ችላለች።
ምንጭ፡ ካፒታል

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

14 Jan, 12:11


የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ እና መመሪያ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Jan, 09:19


በአምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ።

መደበኛውን ነጋዴ መደገፍና ማበረታታት የሚያስፈልገውን ያህል በሕገወጥና ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚሳተፍ ነጋዴ እንዳይኖር በየዕለቱ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

በሕገወጥና በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚደረገው የቁጥጥር ስራም ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አስታውቀዋል።

የወርቅ ወጪ ንግድን ለአብነት ያነሱት ሚኒስትሩ፣ ባለፈው በሙሉ ዓመት ከወርቅ ወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 350 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ተናግረዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አመላክተዋል።

ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው በፖሊሲ በመመራት የንግድ ስርዓቱን ማስተዳደር በመቻሉ በመሆኑ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዘበዋል። Source:- ኢ ፕ ድ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Jan, 09:17


በአምስት ወራት ከቁም እንስሳት ወጪ ንግድ 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ
በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከቁም እንስሳት ወጪ ንግድ 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የቁም እንሰሳት የወጪ ንግድ ለኮንትሮባንድ ከተጋለጡት ዘርፎች መካከል እንደነበር አስታውሰው የዘርፉን ሕገወጥ ንግድ ለመከላከል በተሰራው ስራ በ2016 በጀት በዓመት ከተገኘው ገቢ በላይ በ2017 በአምስት ወራት ማግኘት ተችሏል።

በ2016 የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ዓመታዊ ገቢ 18 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፤ በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከቁም እንስሳት ወጪ ንግድ 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡ Source:- ኢ ፕ ድ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

30 Dec, 18:52


News Alert Dec-02/2024

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

28 Dec, 15:32


በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት የሚያጋጥምን ብክነት እንደ ወጪ ስለመያዝ
ወደ ዉጭ የሚላኩም ሆነ በሀገር ዉስጥ የሚሸጡ ምርቶች በጊዜ ቆይታ፤በማምረት እና በማከፋፈል ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ሊባክኑ ስለሚችሉ ቀድሞ የነበራቸዉን ክብደት እና ጥራት ሊያጡ ይችላሉ ፤
ለምሳሌ ፤-ዕሴት የተጨመረበት ቡና ማለትም ተቆልቶ የተፈጨ እና የታሸገ ቡና ቡናዉ በሚቆለበት ጊዜ በሚፈጠረዉ ሙቀት ቀድሞ የነበረዉን ክብደቱን የሚያጣ ሲሆን ተፈጭቶ በሚታሸግበትም ጊዜ በሚፈጠረዉ ብክነት የነበረዉን ክብደት መጠን ሊቀንሰዉ ስለሚችል የገቢዎች ሚኒስቴር ለታክስ ስሌት የሚዉል ተቆል ቶየተፈጨ ቡና የብክነት መጣኔ ተጠንቶ እንዲገለጽለት ለምግብ፤ለመጠጥ እነ ለፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲዩት በጻፈዉ ደብዳቤ ኢኒስቲቲዩቱ ቡናን ቆልቶ በመፍጨት እና ለዉጭ ገበያ ሲቀርብ የሚኖረዉ የብክነት መጠን 20.54 በመቶ እንደሆነ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ አሳዉቋል ስለሆነም ተቆልቶ የተፈጨ ቡና ለዉጭ ገበያ ሲቀርብ 20.54 በመቶ ይባክናል ተብሎ ስለተጠና ይህንኑ ፐርሰንት በወጪነት እንዲያዝ   ይደረጋል፤፤
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሌሎች ምርቶችም በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት የሚያጋጥም ብክነት (ሰሊጥ እና ኑግ  በብጣሪ ፤በትነት ነዳጅ ፤ብረት በማቅለጥ ፤በሽርፋራፊ፤ቡና በቆይታ ጊዜ ፤ዕጣን ፤መዉጫ ወዘተ) የሚባክን ምርትን በሚመለከተዉ የመንግስት አካል በቀረበ ጥናት መሠረት እንደ ወጪ ሊያዝ ይችላል ፤ የተሟለ ጥናት ማግኘት ካልተቻለ ባለስልጣኑ ከግል ተቋማት ከግብር ከፋዮች አግባብነት ያለዉ አካል ወይም ባለስልጣኑ በሚያደርገዉ ጥናት መሠረት ወጪ የሚያዝበትን መጠን ሊወስን ይችላል ፤ለእያንዳንዱ ምርት መረጀ ሊሰጥ source MOR West Addis Ababa

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

20 Dec, 17:08


ሰላም ውድ የሰበዝ ቤተሰቦች። የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታውን ለማሻሻል የsimple English with Gere ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/TDallasLanguages

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

16 Dec, 10:35


https://vm.tiktok.com/ZMk2RhXLV/

አዲስ ቢዝነስ ጀማሪዎች የሚሰሯቸው ሰህተቶች

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

16 Dec, 07:50


የኢትዮጲያን በጀት አመት የሚጠቀሙ ንግዶች የንግድ ፍቃድ እድሳት ጊዜ ማብቃትን ተከትሎ የሚከፈለውን ቅጣት መጠን ያውቃሉ?

      ከ ጥር 1 እስከ ጥር 30 ብር 2,500.00
      ከ የካቲት 1 እስከ የካቲት 30 ብር 4,000.00
      ከ መጋቢት 1 እስከ መጋቢት 30 ብር 5,500.00
      ከ ሚያዚያ 1 እስከ ሚያዚያ 30 ብር 7,000.00
      ከ ግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30 ብር 8,500.00
      ከ ሰኔ 1 እስከ ሰኔ 30 ብር 10,000.00
      ከሃምሌ 1 ጀምሮ ለሚመጣው 1 አመት 20,000.00
ከ 1 ዓመት በኋላ ፍቃዱን በአዋጅ ይታገዳል በተጨማሪም ነጋዴው ለ 1 አመት በታገደው የፍቃድ መስጫ መደብ ፍቃድ ማውጣት እንዳይችል ይታገዳል።
ማሳሰቢያ
አብዛኛው ጊዜ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ ለማደስ ወሩ መጨረሻ ላይ ስለሚመጡ ቀድመው በማደስ ፈጣን አገልግሎት ያግኙ!!!
source:- etrade

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

13 Dec, 12:24


https://vm.tiktok.com/ZMkFhnAvD/

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

12 Dec, 03:40


#ለመረጃ፡ የኢትዮጵያ የቀረጥና ታክስ ሕጎች በቀላሉ የሚገኙበት የኦንላይን ድረ ገጽ ይፋ ሆኗል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ድረ ገጽ፡ ከ300 በላይ የታክስ ሕጎች በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተቀመጡበት ነው።

ድህረገጹን ለምትፈልጉ https://ethiopia.mylexisnexis.co.za/#/navigation-view;listCode=LNSA

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

11 Dec, 12:17


የእጅ በእጅ ደረሰኝ Manual Receipt ማሳተም የሚቻለው በብረሀን እና ሰላም ብቻ ነው ተባለ። ደረሰኙም Qr  code  ያካትታል

https://vm.tiktok.com/ZMkLoPPwq/

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

11 Dec, 06:15


#Berbera

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ መጀመሩን ገልጿል።

የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ  " የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ አስጀምሯል " ሲሉ ይፋ አድርገዋል።

" ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝንተ ያሳያል ሲሉ አክለዋል።

ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በይፋዊ ማስጀመሪያ ስርዓቱ ላይ ወደቡን የሚያስተዳድረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World በርበራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው እንደነበር ገልጿል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ " ይህ ቢሮ ወደቡ ላይ የሚራገፉ የተለያዩ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው " ብለዋል።

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስትሩ ሳድ (ዶ/ር) " ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ግንኙነታቸው የተጠናከረ ነው ፤ 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን መጠቀም ትችላለች " ማለታቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Photo Credit : #SomalilandFinanceDevelopment

@tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

10 Dec, 15:43


ታህሣስ 1፣2017

ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ የእቃ መያዣ ቀረጢት ይዞ ከተገኘ ከ5,000 እስከ 10,000 የሚያስቀጣው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውሃ መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል፡፡

ይህ በመላው hገሪቱ በ #ደረቅ_ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው ረቂቅ አዋጅ 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከምንጩ ደረቅ ቆሻሻን መቀነስ መልሶ መጠቀም እና በአግባቡ ማስወገድ መሰረታዊ መርሆቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ ምርት አምራቾች ላይ የሚከተሉትን ሀላፊነቶች ደንግጓል፡፡

በዚህም የ #ፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ እንዲሰበሰብ ለዳግም ጥቅም ወይንም መልሶ ሁደት ላይ ሊውል የሚችልበትን ሥርዓት መፍጠር የፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎቱ ዘመን እንዳበቃ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ በአምራቹ ላይ ጥሏል፡፡

የደረቅ ቆሻሻን ስለመሰብሰብ በተመለከተም ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፈቃድ ለጥሬ ምርትነት ካልሆነ በስተቀር ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትም የሚከለክል ነው፡፡

ረቂቅ አዋጁ የደረቅ ቆሻሻን አወጋገድን በተመለከተም ማንኛውም ሰው ለዚህ ዓላማ ተብሎ ከተለየ ቦታ ውጪ ደረቅ ቆሻሻን ማስወገድ እንደማይቻል ጠቁሟል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ልዩ ልዩ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በተመለከተም ማንኛውም ሰው ከ #መኖሪያ_ቤት ይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 20 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማፅዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ወይንም የንግድ ተቋም ከይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ጠርሙስ፣ ጣሳ፣ የታሸገ ውሃ መያዣ ፕላስቲክን በተመለከተም ረቂቁ የምግብ፣ የመጠጥ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የመዋቢያ ምርቶችን በጠርሙስ፣ በጣሳም ወይም በፕላስቲክ መያዣ የሚያመርቱ፣ የሚያስመጡ፣ የሚያከፋፍሉ ሰዎች ጠርሙስ ወይንም የቆርቆሮ ጣሳ የአገልግሎት ዘመኑ እንዳበቃ መልሶ የሚወገድበትን ዘዴ የመዘርጋት ግዴታ አለበት ይላል፡፡ 

ረቂቅ አዋጁ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የላስቲክ የእቃ መያዣዎችን ወደ ሀገር ማስገባት፣ ማምረት፣ መሸጥና ማከፋፈልን ይከለክላል፡፡

ይህን አድርጎ የተገኘም ከ50,000 ብር እስከ 200,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እና ከ5 ዓመት ያልበለጠ ፅኑ እስራት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

Source Sheger Radio

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

10 Dec, 11:59


የማንዋል ደረሰኝ ህትመት አገልግሎትን አንድ ማተሚያ ድርጅት ብቻ እንዲያሳትም ተወሰነ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭትና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ደረሰኝ እንዲታተም ፍቃድ ከመስጠት ጀምሮ ያሉ አገልግሎቶችን ማስተናገድ እንዲቻል የራሱ የሆነ ዲጂታል ፕላትፎርም የተዘጋጀ ሲሆን ማንኛውም ግብር ከፋይ በዚሁ መንገድ መስተናገድ ይችላል ተብሏል።

ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ ፕላትፎርም የማንዋል ደረሰኝ የማሳተም ጥያቄ ማቅረብ ይቻላልም ተብሏል።

በአንጻሩ ከየካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ  ጥቅም ላይ የሚውለው የማንዋል ደረሰኝ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ መሆን ይጠበቅበታል።

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት የማይቻል የህትመት ሥራ ለማከናወን መዘጋጀቱን በስምምነቱ ወቅት ገልጿል።

@TikvahethMagazine

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

10 Dec, 09:44


አማራ ባንክ አጠቃላይ የሃብት መጠኑ ከ35 ቢሊዮን ብር መብለጡን አስታወቀ

👉 ባንኩ በዛሬዉ ዕለት ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው

ታሕሳስ 1/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አማራ ባንክ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በጉባዔው ላይም አጠቃላይ የሃብት መጠኑ 35 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል።

ባንኩ የብድር የቅድሚያ ክፍያውን በ33 በመቶ በማሳደግ 20 ቢሊዮን ብር አካባቢ ማድረሱን የገለጸ ሲሆን፤ የመደበኛ እና የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አጠቃላይ ተቀማጭ በ26 በመቶ ጨምሮ ወደ 25 ቢሊዮን ብር ማደጉንም ገልጿል።

በተጨማሪም የዓመቱ አጠቃላይ ገቢ 146 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን የገለጸው ባንኩ፤ በዚህም 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

ባንኩ ሰፊውን የማህብረሰብ ክፍል ለማገልገል አልሞበት የተነሳበትን ራዕይና 'ከባንክ ባሻገር' የሚለውን መሪ ቃሉን እውን ለማድረግ፤ ከፍተኛ የሃብት መጠን ለማካበት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የቦርዱ ሰብሳቢዎች በጉባዔው ተናግረዋል።

ከተደራሽነት አንፃር ባደረገው ጥረት በበጀት ዓመቱ 143 ተጨማሪ ቅርጫፎችን በመላ ሀገሪቱ በመክፈት፤ በአሁኑ ወቅት የቅርጫፎቹን ብዛት 310 ማድረሱንም አስታዉቋል።

በተጨማሪ የባንኩ የደንበኞች ብዛት ከ1 ነጥብ 8ሚሊዮን በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ 600 ሺሕ የሚጠጋ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ገልጿል።

ባንኩ "በባለፉት ዓመት የገጠመዉን ኪሳራ በፍጥነት በማካካስ ካለፈዉ ዓመት ካገኘዉ ትርፍ ጋር ሲነፃፀር፤ የዘንድሮው ከ669 ሚሊዮን ብር ልዩነት አሳይቷል" ብሏል።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_Radio

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

05 Dec, 16:14


የኢምፖርት ኤክስፖርት ስራ ስልጠና
Export Import Trainin
g
* የኢምፖርት ኤክስፖርት ንግድ አሰራር
* ሰነድ አይነቶችና አዘገጃጀት
* የአለም አቀፍ ንግድ የክፍያ ዘዴዎች እና አጠቃቀም
* የጉሙሩክ አሰራር እና ደንብ
* የአንድ መስኮት( ESW System) አጠቃቀም
* የአለም አቀፍ ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አጠቃቀም
እና ሌሎችም
Online ሰኞ በ 30 Weekend ቅዳሜ በ 28 ይጀመራል
ለበለጠ መረጃ 0923 75 35 35

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

04 Dec, 17:05


#EthiopianInvestmentHoldings

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ጨምሮ 8 ተቋማት ከአሁን በኃላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሚተዳደሩ ተነገር።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 8 ተጨማሪ የመንግስት ድርጅቶችን በስሩ በማካተት ፖርትፎሊዮውን ማስፋቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በስሩ ከሚገኘትና ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተጨማሪ 8 አዳዲስ ቁልፍ ተቋማትን በስሩ በማካተት የድርጅቶቹን ቁጥር ጨምሯል።

8ቱ ተቋማት እነማን ናቸው ?

- ኢትዮ ፖስት፣
- ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ
- የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፣
- የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣
- የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣
- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዮ ፋርማ ግሩT ተጠሪ የሆኑት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥቢታ ተቋምና ሺልድ ቫክስ ናቸው።

እነዚህ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ተጠሪ የነበሩት የልማት ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የሚመሩት በኢኢሆ ስር ሆኗል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

03 Dec, 14:40


ንግድ እና ቀጣናዊ ትስድር ሚኒስቴር "የምርት ነፃ ዝውውርን የሚገድቡ" ያላቸው 283 ሕገ ወጥ የከተማ በር ወይም መቅረጫ ኬላዎች በመላው ሀገሪቱ መኖራቸውን ገለፀ።
ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንዳሉት ይህ ለምርቶች ዋጋ መጋነን እና የሸቀጦች ዋጋ መናር ምክንያት ሆኗል።
ሚኒስትሩ መሥሪያ ቤታቸው ባለፉት አምስት ወራት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ቢሉም ከምክር ቤት አባላት እርምጃ ለምን እንደተወሰደ? ያ በመሆኑ ምን ውጤት እንደተገኘ እንደማይገለጽ ተጠቅሶ ሚኒስቴሩ ከደላላ ዕጅ አስወጥቶ የሀገሪቱን ንግድ በአግባቡ እየመራ ስለመሆኑ አለመሆኑ ጥያቄ ተነስቶበታል።
የሀገሪቱ ንግድ በደላላ እየተመራ ነው በሚል የቀረበባቸውን ትችት ያጣጣሉት ሚኒስትሩ እውነታው በዚያ ደረጃ የሚገለጽ እንዳልሆነ፣ ሆኖም ግን የደላላ ጣልቃ ገብነት አሁንም የሚቀር እንዳልሆነ ጠቅሰዋል። በየክልሉ በከተሞች መግቢያ እና መመውጫ በር ላይ ገመድ ወጥረው ነጋዴውን ለድርብርብ ክፍያ እና ወጪ የሚዳርጉ ሕገ-ወጥ አሠራሮች በቀላል የማይታይ አደጋ መደቀናቸውን ግን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰዋል ሲል ስብሰባውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ዘግቧል።

Source VOA

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

03 Dec, 08:55


Urgent Notice from Ministry of trade‼️ ማሳሰቢያ ‼️
በኢትዮጵያ በጀት ዓመት የምትጠቀሙ ውድ ደንበኞቻችን፣   የንግድ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ጠይቃችሁ እና አገልግሎት ክፍያ የደረሳችሁ ከታህሳስ 30 በፊት እንደድትከፍሉ በጥብቅ እያሳሰብን ከታሕሳስ 30 በኋላ ክፍያ የምትፈፅሙ ከሆነ በደረሳችሁ መክፈያ ኮድ በቅጣት የምታድሱ መሆኑን እንገልፃለን።
Source etrade.gov.et

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Dec, 17:05


የጉምሩክ ኮሚሽን ከ ከጥቅም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በፊት የንግድ ሸቀጦች በፍራንኮቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸውን ሰነዶች በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስመዘገቡ እና በዋና መስሪያቤት በኩል የተረጋገጡ አስመጪዎች በአንድ ወር ዉስጥ የንግድ ሸቀጣቸዉን አጠቃለዉ ወደ አገር ዉስጥ እንዲያስገቡ ነዉ ማሳሰቢያ የሰጠዉ።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Dec, 17:04


#ፍራንኮቫሉታ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሽቀጦች ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ወደ ሃገር እንዲገቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ /LC/ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ማስታወቁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈዉ ደብዳቤ በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሸቀጦች በአንድ ወራት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ብቻ ወደ ሃገር ዉስጥ መግባት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ኮሚሽኑ ይህን ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴርን ዉሳኔ ተከትሎ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንዲያዉቁት አድርጓል።

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ አድርጓል፡፡

ይሁን እንጂ የፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉንም የገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ " በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም " ተናግረው ነበር።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Dec, 17:03


ብሔራዊ ባንክ በመደበኛው ገበያና በጥቁር ገበያ መካከል ያለው የውጭ ምንዛሪ ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን ገለጸ
November 29, 2024
ማሻሻያው በተተገበረባቸው በእነዚህ ጊዜያት በተለይ የፋይናንስ ዘርፉ ምን ለውጥ መጣ? በሚል በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመደበኛው ገበያና በጥቁር ገበያ መካከል ያለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ልዩነት እየጠበበ መጥቶ 7.8 በመቶ መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ካካሄደች ከ3 ወራት በላይ የሆናት ሲሆን ማሻሻያው ሲደረግ ለማሳካት እንደግብ ከተቀመጡ በርካታ ጉዳዮች መካከል የፋይናንስ ዘርፍ ፓሊሲ ማሻሻያ አንዱ እንደሆነ ተነስቷል፡፡
በዚህም ውስጥ የፋይናንስ ተደራሽነትና አካታችነትን ማረጋገጥ እንደሚገኝበት እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያም ሌላው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህም ሲደረግ ገበያ መር የሆነ የውጭ ምንዛሪ እንዲኖር ማስቻልን፣ በፋይናንስ ሴክተሩ በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲኖር ለማድረግ በማሰብ እንደተደረገ ለምክክሩ መነሻ ሚሆን ገለፃ ያደረጉት በብሔራዊ ባንክ የውጭ ኢኮኖሚ ትንተናና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡ በገለፃቸውም ባለፉት 3 ወራት በጉልህ ከታዩ ለውጦች መካከል በመደበኛና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደተቻለ አንስተው ማሻሻያው ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት ሐምሌ 21 ቀን 2016 በፊት በመደበኛና በጥቁር ገበያ መካከል የነበረው ልዩነት 97 በመቶ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ሪፎርሙ ካሳካቸው ለውጦች መካከል ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ግኝት መጨመሩ ተነስቷል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሪፎርሙ በፊት በዚህ ዘርፍ ባለፉት 3 ወራት 793 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን ከማሻሻያው በኋላ ባሉት 3 ወራት ግን ከኤክስፖርት የተገኘው 1.7 ቢሊየን ዶላር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

17 Nov, 08:40


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ላኪዎች የያዙትን ምርት እንዲሸጡ ማሳሰበያ ሰጠ
ሙሉ መረጃዎ
https://www.ethiopianreporter.com/135482/
በፌስቡክ @sebeztraining
በቴሌግራም፡- https://t.me/sebeztraining
በድረገጽ፡- https://Www.sebeztraining.com
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

17 Nov, 08:29


ፕሬስ ሪሊዝ
እንደደረሰ በጥቅም ላይ የሚውል
ህዳር 07/2017
ኢ/ቡ/ሻ/ ባለስልጣን
የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወጪ ንግድ አፈጻጸም
በ2017 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር 21,251.98 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 109.53 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 38,406.21 ቶን (ከዕቅዱ 180.72%) በመላክ 156.35 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 142.74%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን 17,492.55 ቶን (83.64%) እና በገቢ 61.91 ሚሊየን ዶላር (65.55%) ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡
በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ደግሞ 104,546.23 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 536.63 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 157,257.98 ቶን (ከዕቅዱ 150%) በመላክ 678.33 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 126%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን 65,863.67 ቶን (72%) እና በገቢ 226.97 ሚሊዬን ዶላር (50%) ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡
የቡና ወጪ ንግድ አፈጻጸም
በ2017 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ብቻ 20,009.48 ቶን ቡና በመላክ 108.05 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 35,171.82 ቶን (ከዕቅዱ 176%) በመላክ 155.53 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 144%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በመጠን 15,078.03 ቶን (75%) እና በገቢ 62.08 ሚሊየን ዶላር (66%) ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡
በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ደግሞ 98,999.38 ቶን ቡና በመላክ 531.04 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 150,346.57 ቶን (ከዕቅዱ 152%) በመላክ 674.55 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 127%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 62,587.58 ቶን (71%) እና በገቢ 226.89 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር (51%) ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡
  የቡና ወጪ ንግድ በመዳረሻ ሀገራት
በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት የተላከዉ ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ጀርመን በመጠን 32,666.48 ቶን (22%) እና በገቢ 132.40 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (20%) ድርሻ፣ ሳዉድ አረቢያ በመጠን 26,579.49 ቶን (18%) እና በገቢ ደግሞ 113.83 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (17%) ድርሻ እንዲሁም ቤልጅዬም በመጠን 15,325.09 ቶን (10%) እና በገቢ 71.59 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (11%) አፈፃፀም በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ የቀሩ መዳረሻዎች በ2017 በገቢ ቅደም ተከተል 4ኛ አሜሪካ፣ 5ኛ ደ.ኮሪያ ፣ 6ኛ ጃፓን፣ 7ኛ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ 8ኛ ጆርዳን  ፣ 9ኛ ጣልያን እና 10ኛ አዉስተራልያ ሲሆኑ ከ1 እስከ 10 ያሉት በአጠቃላይ በመጠን 77% እና በገቢ 78% የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ይሸፍናሉ፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ዋና 10 መዳረሻ ሀገራት ከ2016 አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር በመጠን 84% እና በገቢ ስታይ የ60% ጭማሪ አለው፡፡
Source:- ETCA
በፌስቡክ @sebeztraining
በቴሌግራም፡- https://t.me/sebeztraining
በድረገጽ፡- https://Www.sebeztraining.com
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

17 Nov, 08:28


የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወጪ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

14 Nov, 16:42


https://vm.tiktok.com/ZMhsP4fxh/

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

14 Nov, 14:36


Price Inflation Shows Moderate Decline Last Month
November 13, 2024
According to the report released by the Ethiopian Statistics Service report, the inflation of consumer goods in October recorded as 16.1 percent, and the inflation showed a slight decrease compared to the previous month. Food items accounted for a 19.2 percent in recorded monthly price inflation, while non-food items registered 11.6 percent increase.
The institution reminds that last September consumer goods price inflation reached 17.5 percent, and food price inflation alone decreased from 19.6 percent to 19.2 percent. The report shows that overall price inflation has moderately declined, dropping from 17.5 percent in September to 16.1 percent in October.
The report also indicated the Major division of food and non-food commodities, which holds large share in the commodity basket, the magnitude of inflation rate at September EFY2017 showed a fall as compared to the previous month. From Food and Non-Alcoholic Beverage aspect, the highest wei

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

14 Nov, 07:14


#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡
የማኑዋል ደረሰኝ አጠቃቀምን በተመለከተ QR code እንዲያካትት የወጣ መመሪያ። የሽግግር ጊዜው ሶስት ወር ስለሆነ ተጨማሪ ደረሰኝ ከማሳተማችሁ በፊት ጥንቃቄ እንድታደርጉ።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

14 Nov, 06:19


ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ
-ብሔራዊ ባንክ
****
(ኢ ፕ ድ)

ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለአካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት፣ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።

በወቅቱ አሰራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበር አቶ ማሞ አስታውሰዋል።

ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ብለዋል።

ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ህዳር 4 ቀን 2017 ዓም

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

13 Nov, 12:15


ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር  ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ተባለ

ዕረቡ ህዳር 04 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር  ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ  ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ አዲስ ማለዳ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

13 Nov, 11:56


የጉሙሩክ ዝቅተኛ የህግ ተገዢነት ደረጃ ያላቸው አስመጪና እና የጉሙሩክ አሰተላላፊዎች ዝርዝር

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

11 Nov, 13:28


የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግመው መውጣታቸው እና መቀያየራቸው ለስራ አስጊ እየሆነብን ነው ሲሉ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰሙ

ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግሞ መውጣት የንግድ ዘርፉን ስጋት ውስጥ እየጣለው ነው ሲሉ በአስመጪና ላኪ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በቅርቡ ክልከላ የተጣለበት የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ እንኳን ብዙ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ችግር ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ደጋግመው ሲገልጹ ይደመጣል፡፡

እንደነዚህ ያሉት ማሻሻያዎች ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ዓላማ ቢኖራቸውም ፣ ድንገተኛ ትግበራቸው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበሳቸው ብዙውን ጊዜ የንግድ ሥራዎችን በአግባቡ እንዳይካሄዱ እየዳረገ ነው ሲሉም ነው ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ያሰሙት ።

ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ  እንዳሉት  በተደጋጋሚ የፖሊሲ ለውጦችን በኢኮኖሚው ላይ መተግበራቸው ለንግድ ድርጅቶች ቀጣይ እርምጃ ከፍተኛ ጥርጣሬን እየፈጠረ ነው ብለዋል።

“ኢኮኖሚው ከመንግስት የፖሊሲ መረጋጋትን ይፈልጋል ምክንያቱም ብዙ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች መወሰን ሚቻለው ያኔ ነው” ያሉት ቅሬታ አቅራቢው ፖሊሲዎች ከመተግበራቸው በፊት በደንብ ሊጠኑ እንደሚገባ አስምረው መንግስትም ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር እንዲወያይ ጠይቀዋል፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አጥላው ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚቀያየሩት ፖሊሲዎች የንግድ ባለቤቶች ረጅም ለማቀድ እንዳይችሉና ጥርጣሬ እንዲፈጥርባቸው እንደሚያደርጋቸው ጠቁመዋል፡፡

አክለውም ድርጅቶች በፖሊሲዎች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን በመገመት አሳሳቢ ጉዳዮቻቸውን እና ስራዎቻቸውን በረጅም እቅድ  ላይ ከማተኮር ይልቅ በአጭር ጊዜ እቅድና የንግድ እንስቃሴ እንዲገደቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የቢዝነስ ተቋማት ፈጣን የፖሊሲ ሽግሽግ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመዳሰስ ፈታኝ እየሆነባቸው እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።

ምንጭ አዲስ ማለዳ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

09 Nov, 05:22


ሞኤንኮ ፥ በኢትዮጵያ የቢዋይዲ (BYD) ኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ይፋዊ አከፋፋይ መሆኑን ገለጸ።

በኢንችኬፕ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ሞኤንኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ መሪ ከሆነው ቢዋይዲ (BYD) ጋር በኢትዮጵያ የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ዋና አከፋፋይ ለመሆን የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን ገልጿክ።

በስምምነቱ ሞኤንኮ በኢትዮጵያ በዋናነት የቢዋይዲ (BYD) ተሽከርካሪዎችን የሚያከፋፍል ይሆናል።

ሞኤንኮ ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ለአካባቢ አየር ተሰማሚ እና በቴክኖሎጂ የተራቀቁ የቢዋይዲ ተሸከርካሪዎችን ከአስተማማኝ ጥገና ፣ መለዋወጫ እና ዋስትና ጋር እንደሚያቀርብም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

" ይህ ስምምነት ዘላቂና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን የማስተዋወቅ እና ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ' ብሏል።

የኢንችኬፕ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍራንሲስ አግቦንላሆር ፥ " ይህ አጋርነት ለኢትዮጵያ የተሸከርካሪ ኢንዱስትሪ ወሳኝ አስተዋጽዖ ያበረክታል ፤ ይህም የአዳዲስ ፈጠራ መስፋፋት እና ታዳሽ ሀይልን በመጠቀም ዘላቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎትን ያፋጥናል " ብለዋል።

@tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

09 Nov, 05:22


ሞኤንኮ ፥ በኢትዮጵያ የቢዋይዲ (BYD) ኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ይፋዊ አከፋፋይ መሆኑን ገለጸ።

በኢንችኬፕ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ሞኤንኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ መሪ ከሆነው ቢዋይዲ (BYD) ጋር በኢትዮጵያ የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ዋና አከፋፋይ ለመሆን የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን ገልጿክ።

በስምምነቱ ሞኤንኮ በኢትዮጵያ በዋናነት የቢዋይዲ (BYD) ተሽከርካሪዎችን የሚያከፋፍል ይሆናል።

ሞኤንኮ ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ለአካባቢ አየር ተሰማሚ እና በቴክኖሎጂ የተራቀቁ የቢዋይዲ ተሸከርካሪዎችን ከአስተማማኝ ጥገና ፣ መለዋወጫ እና ዋስትና ጋር እንደሚያቀርብም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

" ይህ ስምምነት ዘላቂና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን የማስተዋወቅ እና ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ' ብሏል።

የኢንችኬፕ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍራንሲስ አግቦንላሆር ፥ " ይህ አጋርነት ለኢትዮጵያ የተሸከርካሪ ኢንዱስትሪ ወሳኝ አስተዋጽዖ ያበረክታል ፤ ይህም የአዳዲስ ፈጠራ መስፋፋት እና ታዳሽ ሀይልን በመጠቀም ዘላቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎትን ያፋጥናል " ብለዋል።

Source:- tikvahethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

08 Nov, 14:20


በፍራንኮ ባሎታ ግዥ ፈጽማችሁ በሂደት ላይ ያላችሁ ከጥቅምት  28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 የሥራ ሳምንታት ውስጥ ብቻ አስፈላጊውን ዶክመንት በማቅረብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

07 Nov, 10:56


ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ገለጸ

ሐሙስ ጥቅምት 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ ከህዳር 22 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አዲሱ መመሪያ ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማጎልበት እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር እንደሚያግዝ እና የዲጂታል ግብይትን እየለመደ ያለውን ማህበረሰብ በይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ይህ ኢት ኪውአር ኮድ (EthQR Code) የሚል ሥያሜ የሚኖረው አሠራር ዓለምአቀፍ የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ፣ የክፍያም ሆነ የግብይት ተዋናያንን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ነገር ግን ከተወሰኑ አስፈላጊ መረጃዎች በቀር ሌሎቹን በምሥጢር የሚጠብቅ  ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትና ግብይት የጥሬ ገንዘብን ዝውውር የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ሕብረተሰቡ ለሥርቆት፣ በእጁ ያለው ገንዘቡም ለእርጅና እንዳይጋለጥ፤ ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ፣ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ገንዘቡን ለማሳተም የሚወጣ ወጪን እንዳይጨምር ለማድረግ ይረዳል ብሏል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

30 Oct, 08:26


#ለመረጃ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ ኩባንያዎች የሚያቀርቧቸው የኤሌክትሮኒክ የማጓጓዣ ሰነዶች ተቀባይነት አግኝተው እንዲገለገሉ ፈቀደ፡፡

ሪፖርተር የተመለከተውና በጉምሩክ ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ ተፈርሞ ለሁሉም የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለሚፈጸምባቸው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተመራው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ሌሎች በሕግ የተገለጹ ደጋፊ ሰነዶች መሟላታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ሥርዓት ጥሬ ዕቃ ወደ አገር የሚያስገቡ ኩባንያዎች ብቻ የሚያቀርቡት የቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release)፣ ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) ሰነዶች እንደ መጓጓዣ ሰነድ ተቀባይነት አግኝተው ተገቢው አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

ቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release) ግዥ ለተፈጸመበት ዕቃ መርከብ ላይ መጫኑ ሲረጋገጥ አጓጓዡ ወይም የአጓጓዡ ወኪል (Agent) በየትኛውም ቅርንጫፍ ዋናውን ቅጂ በማስገባት (Surrendered)፣ ሰነዶቹን የተቀበለው አጓጓዥ ድርጅትም ሆነ የአጓጓዡ ወኪል ዋናውን ቅጂ መቀበሉን በማረጋገጥ ለመዳረሻ ወደብ (Destination Port) ዕቃው እንዲለቀቅ በኤሌክትሮኒክ መልዕክት የሚያስተላልፍበት ሥርዓት ነው፡፡

ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) ደግሞ አጓጓዡ ድርጅት (Carrier/Shipping Line) ዕቃውን ስለመቀበሉ የሚረጋገጥበትና የመጓጓዣ ውል ማስረጃ ሆኖ የሚያገለግል ሰነድ ሲሆን፣ መዳረሻ ወደብ ደርሶ ክሊራንስ ከመጠናቀቁ በፊት ባለቤትነት ማስተላለፍ የማይቻልበት ነው፡፡

በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጪ የሚገኙ አምራቾች ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ ቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release) እንዲሁም ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) የማጓጓዣ ሰነድ እንደሚጠቀሙ በመግለጽ፣ በእነዚህ ሰነዶች አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ታውቋል፡፡

የዕቃ ዲክላራሲዮን በኤሌክትሮኒክ ሰነድ መቅረብ እንደሚችልና ወደ አገር ለሚገቡና ለሚወጡ ዕቃዎች ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለመፈጸም የሚቀርቡ ደጋፊ ሰነዶችን ለመወሰን ሥልጣን የተሰጠው ኮሚሽኑ፣ የተሻሻለውን የጉምሩክ አዋጅ 859/2014 መሠረት በማድረግ ኩባንያዎች ውጭ አገር ከሚገኝ ላኪ ድርጅት ጋር ባላቸው ስምምነት መሠረት የሚላኩላቸውን ጥሬ ዕቃዎች ለመቀበል የሚጠቀሙበት ሥርዓት በመሆኑ ውሳኔውን ተግባራዊ ማድረግ እንዳስፈለገ አስታውቋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ቴሌክስ ሪሊዝና ሲ ዌይቢል ሥርዓት በሌሎች አገሮችም ንግድን ለማቀላጠፍ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የጉምሩክ ኮሚሽን ቴሌክስ ሪሊዝና ሲ ዌይቢል እንደ ሕጋዊ የማጓጓዣ ሰነድ አድርጎ መቀበሉ፣ ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ ዕቃዎች የማጓጓዝ ስታንዳርድ ጋር የሚያስተሳስር ነው ብለዋል፡፡

ባለሙያዎቹ በተጨማሪም ኮሚሽኑ የፈቀደው ይህ ሥርዓት የሎጂስቲክስና የጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት አሠራርን ከማስተካከል ባሻገር፣ ፍጥነትና ቅልጥፍናን እንደሚጨምር አስረድተዋል፡፡
መረጃው የሪፖርተር ነው!

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

24 Oct, 05:50


ጅቡቲ የደረሰው ስንዴ ያለ ተጨማሪ ታክስ ክፍያ ወደ ሀገር እንዲገባ መንግስት ፈቀደ

ኢትዮጵያበ2015 ዓ.ም 30 ሚሊየን ኩንታል ወደ ውጪ የመላክ እቅድ የነበራት ቢሆንም በአመት ከ20 ሚሊየን ኩንታል በላይ ወደ ሀገር እየገባ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ-
ዝርዝሩን ያንብቡት-
https://cutt.ly/AeSJ5XIo

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

21 Oct, 13:26


የቅባትና ጥራጥሬ እህሎችን በ60 ቀናት ውስጥ ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ የሚያስገድድ ሕግ ፀደቀ

ላኪዎች በቀጥታ የግብይት ሥርዓት የገዙትን የቅባትና ጥራጥሬ እህሎች በአንድ የምርት ዘመን ወይም የምርት ዘመን ባለቀ በ60 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ መመርያ ቁጥር 1026/2017 የቅባት እህሎችንና የጥራጥሬ ምርቶችን የቀጥታ ግብይት ለመወሰን የወጣው መመርያ ክፍል አንድ በተራ ቁጥር ስምንት ያስገድዳል።

ዘርፉን ከሕገወጥ ንግድ ለመታደግ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል አማራጭ ግብይት ለመዘርጋት በማስፈለጉ መመሪያው እንደወጣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለጥራጥሬና ቅባት እህል ላኪዎች ማኅበር ስለመመርያው በላከው የማብራሪያ ደብዳቤ ይገልጻል፡፡ የቀጥታ ግብይት ሥርዓት ያስፈለገበት ምክንያት የረዥም የግብይት ሰንሰለት ለምርት ብክነትና የጥራት መጓደል፣ ሕገወጥ ግብይትና የኮንትሮባንድ መስፋፋት፣ የምርት ክምችትን የመደበቅ ችግሮች በተሞክሮ በመስተዋሉ መሆኑን የተላከው ደብዳቤ ያስረዳል፡፡
ይህም በውጭ የንግድ አፈጻጸም ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ምርቶችን የቀጥታ ግብይት አሠራር በመዘርጋት እንደ አንድ መፍትሔ እንደተወሰደ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ሪፖርተር
@sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

15 Oct, 17:50


አዲሱን የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ተከትሎ ባንኮች በውጭ ምንዛሬ ላይ እስከ አስራ አንድ ብር የሚደርስ ቅናሽ ማሳየታቸው ተገለጸ

ማክሰኞ ጥቅምት 05 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ብሄራዊ ባንክ አዲስ ባወጣው መመሪያ ባንኮች በየቀኑ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የመሸጫና የመግዣ መጠን ላይ ልዩነቱ ከሁለት በመቶ በላይ እንዳይሆን ማስታወቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋቸው ላይ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡

በዚህ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የመሸጫ እና የመግዣ ዋጋቸውን በየዕለቱ እየወሰኑ ይፋ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ በአብዛኛዎቹ ባንኮች በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸው መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በላይ መድረሱ ተጠቁሟል።

በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ባስተዋወቀው አዲስ ፖሊሲ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የመግዣ እና የመሸጫ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ወስኗል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ባወጣው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት የዋጋ ዝርዝር ላይ የዶላር የመሸጫ ዋጋው ከትናንቱ ጋር ሲነጻጸር የስምንት ብር ቅናሽ ያሳየ ሲሆን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ደግሞ የአስራ አንድ ብር ቅናሽ አድርጓል፡፡

ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ በተመለከተ ለሁሉም ባንኮች በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን እስከ ረቡዕ ድረስ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አዟል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

15 Oct, 17:16


መንግሥታዊው ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋ ቀነሰ።

በመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዶላር ከብር አንጻር ያለው ምንዛሬ በመሸጫው ቅናሽ አስመዝግቧል። ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ሲያደርግ በመግዣው ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጓል።
ባንኩ የባለፈውን ሳምንት ቀናት እንዲሁም ትናንት ጥቅምት 4/2017 ድረስ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ112.39 ሲገዛ የነበረ ሲሆን፣ መሸጫው 123.63 ነበር።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 5/2017 ባወጣው አዲስ ዋጋ የመግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ አንድ ዶላር 113.13 እንደሚገዛ አሳውቋል። በአንጻሩ ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ በማድረግ ለአንድ ዶላር 115.39 ዋጋ አስቀምጧል። በመሸጫ ዋጋ ላይ የተመዘገበው ቅናሽ 8.24 ብር ነው።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

12 Oct, 09:24


Vacancy
Job Description
Nebil Trading is seeking a highly organized and detail-oriented Secretary to provide administrative support to our company.
Key Responsibilities:
●      Provide administrative support to the team, including scheduling appointments, preparing meeting materials, and assisting in office documentation
●      Manage the day-to-day operations of the office, ensuring a smooth and efficient workflow
●      Respond to phone calls, emails, and letters in a timely and professional manner
●      Maintain confidentiality and handle sensitive information with discretion
●      Perform other administrative tasks as needed
Tax Compliance:
●      Prepare and submit tax returns (e.g. VAT, WHT, income tax, pension etc) on behalf of the company
●      Maintain accurate records of expenses, invoices, and receipts
●      Ensure compliance with all tax laws and regulations
Office Maintenance:
●      Ensure the office is clean, organized, and well-maintained at all times
●      Restock supplies, maintain inventory levels, and perform other tasks as needed to keep the office running smoothly
●      Maintain a professional appearance of the office space
●      Follow up on office mail, including incoming correspondence, packages, and deliveries
●      Receive guests and visitors in a professional manner
●      Forward messages to concerned staff in a timely manner
Additional Responsibilities:
●      Perform other administrative tasks as needed, such as data entry, filing, and record-keeping
●      Develop and maintain relationships with vendors, suppliers, and other stakeholders
Job Requirements
●      BA Degree in Office Management, Business Administration  accounting
●      Proficiency in Microsoft Office Suite (Word, Excel, PowerPoint, Outlook)
●      Strong communication and organizational skills
●      Ability to maintain confidentiality and handle sensitive information with discretion
●      Strong attention to detail and accuracy
●      Ability to work independently and as part of a team
●      Proficiency in English communication is required
Place of Work
·       Around Sumit 72 ,
How to Apply
Applicants who fulfill the above-mentioned criteria could submit detailed CV along with supporting documents/credentials and Cover Letter to the following email: [email protected]

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

11 Oct, 05:26


#ሪልስቴት

ያልተገነባ ቤት / ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።

ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን #እንዳይመዘግቡ እና #ቅድመ_ክፍያ እንዳይሰበስቡ ይከለክላል።

በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ " የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ " የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን አለባቸው።

የአገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች ግንባታውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን " የፋይናንስ አቅርቦት ምንጭ " የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦባቸዋል። ይሁንና ረቂቁ፤ " የቅድሚያ ቤት ሽያጭ ተጠቃሚነት " መብትን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰጥቷል።

ይህ አሠራር የሪል ስቴት አልሚዎች የቤት ግንባታውን ሳያከናውኑ ወይም በሂደት ላይ እያለ ለግንባታው የሚውልን ፋይናንስ የሚያሰባስቡበት እና ገንዘቡብ ለግንባታው የሚያውሉበት መንገድ ነው።

የቤት ግንባታው ሳይከናወን በፊት ከገዢዎች ጋር ውል ማሰር እና ክፍያ መፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በሪል ስቴት ልማት ላይ በተሰማሩ አልሚዎች በኩል የተለመደ አሰራር ነው።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ በዚህ ዓይነት መልኩ ለግንባታ የሚውለውን ሀብት ማሰባሰብ የሚፈልጉ አልሚዎች " አግባብ ካለዉ አካል ፈቃድ ማቅረብ " ይጠበቅባቸዋል። ይህም ግዴታ ነው።

የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።

አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ " የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ " እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።

አዲሱ ሕግ፤ ገንዘቡ የሚቀመጥበት ዝግ የባንክ አካውንት የሚከፈተው " አግባብ ባለው አካል ፈቃድ መሠረት " እንደሆነም ያስረዳል።

በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚወጣ ደንብ ይወሠናል።

ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ " በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ " እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።

ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት " ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ " እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።

ረቂቅ አዋጁ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ሌሎችንም ግዴታዎች ጥሏል።

በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።

" ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም " ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።

ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።

አልሚዎች ምዝገባ ማድረግ እና ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉት " የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከተረከቡ " በኋላ ነው።

" በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም " የሚለውም ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች መካከል ነው።

ለሪል ስቴት ልማት አሠራር የሚዘረጋው አዲሱ አዋጅ፤ ከግዴታዎች ባሻገር አልሚዎች ከመንግሥት  " መሬት በስፋት " ማግኘት የሚችሉበትን ሂደትም ያስቀመጠ ነው።

ከመንግሥት መሬት " በስፋት " የሚቀርብላቸው አልሚዎች ረቂቁ ላይ ከተጠቀሱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በብዛት ቤቶችን መገንባት እና ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ " 40 በመቶውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ " ማድረግ የሚለው አንዱ ነው።

ይህንን ቅድመ ሁኔታ የሚከተሉ አልሚዎች የሚገነቡበት ቤት ብዛት " እንደ ከተሞች ደረጃ በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 5 ሺህ " ሊሆን እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተጠቅሷል።

መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት " በስፋት " የሚያቀርበው " በአዲስ አበባ ከ5 ሺ በላይ ቤት ለሚገነባ እና ለሚያስተላልፍ " አልሚ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

በሌሎች ከተሞች መሬት " በስፋት " የሚቀርበው እደሚኖራቸው " ተጨባጭ የቤት ፍላጎት " ሲሆን፣ " ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባሉ ከተሞች " ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች እንደሚቀርብላቸው ረቂቁ ያስረዳል።

ከመንግሥት መሬት " በስፋት " ማግኘት የሚፈልጉ አልሚዎች የተቀመጠባቸው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተገናኙ ናቸው።

በአገር ውስጥ " በጥራት እና በብዛት የማይገኙ " ግብአቶችን በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (ፍራንኮ ቫሉታ) የሚያስገቡ እንዲሁም የሚያገኙትን ትርፍ እስከ አስር ዓመት ከአገር ሳያወጡ አገር ውስጥ መልሰው የሚጠቀሙ አልሚዎች የዚህ አሠራር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

" የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ " የተሰኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተጨማሪ ዕይታ ወደ ከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል።

መረጃው ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ ነው።

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

10 Oct, 05:04


የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።

በዚህ መሰረት፦
➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር 
➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
@sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

10 Oct, 05:04


ለቻይና የሚቀርቡ ምርቶች በንግድ ባንክ በኩል እንዲሆኑ የሚያስገድደው መመርያ እንዲሻር ተጠየቀ

ለቻይና ገበያ የሚቀርቡ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በመደረጋቸውና ከሌሎች የግል ባንኮች ተበድረው የሚሠሩ ነጋዴዎች በመጎዳታቸው፣ አስገዳጅ መመርያው እንዲሻር የጥራጥሬና የቅባት እህል ላኪዎች ማኅበር ጥያቄ አቀረበ፡፡ ማኅበሩ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ለአቶ ማሞ ምሕረቱ ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ፣ ለቻይና ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች በአስገዳጅ በንግድ ባንክ ብቻ መደረጋቸው፣ ከግል ባንኮች ብድር ወስደው ኤክስፖርት የሚያደርጉ ላኪዎች ለኪሳራ ተጋልጠዋል ብሏል፡፡ ቻይና ለታዳጊ አገሮች የሰጠችውን ከቀረጥና ከኮታ ነፃ ዕድል በአግባቡ የኢትዮጵያ ላኪዎች እንዲጠቀሙ ታሳቢ ያደረገ ዕገዛ እንዲያደርግ ብሔራዊ ባንክን የጠየቀው ማኅበሩ፣ በቀጣይም ከብሪክስ አገሮች ጋር የሚኖረውን የንግድ ግንኙነት ለማቀላጠፍ መመርያው እንዲሻር ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

Source: Financial Ethiopia

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

06 Oct, 18:20


በአዲስ አበባና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ  ተሰምቷል

ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 2:10 ሰዓት አካባቢ፣ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ።

የመሬት መንቀጥቀጡ የደረሰው ለተወሰኑ ሰከንዶች ሲሆን ፤ጦር ሃይሎች፣ የካ አባዶ፣ ሰሜን ሆቴል፣ አያት ሲኤም ሲ፣ አራብሳ፣ ጀሞ፣ ጉለሌ፣ ኮዬ፣ ቤቴል  ኮንዶሚኒየምና አፓርትመንቶች  መንቀጥቀጡ ካጋጠመባቸው አካባቢዎች የተወሰኑት  መሆናቸው ተረድተናል ።

ህንፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎች በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን፤ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች ቦታዎች መሰል ሁኔታ መከሰቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ: አዲስ አድማስ

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

02 Oct, 15:21


#መረጃ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureau) የስራ ፈቃድ ሰጠ!
የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎቹ…

ዶላር #መግዛት የሚችሉት (ብር ሰጥተው ዶላር የሚቀበሉት)….
ከማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት እስከ 10ሺ ዶላር!

የጉምሩክ ዲክላራሲዮን (ማረጋገጫ ከሚያቀርቡ) የቻሉትን ያህል ዶላር መግዛት ይችላሉ!

ዶላር #መሸጥ የሚችሉት (ብር ተቀብለው ዶላር የሚሰጡት)

ወደውጪ ለመሄድ አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ለሚያቀርቡ የግል ተጓዦች (ለምሳሌ ቪዛ) እስከ 5ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

ለንግድ ስራ ተጓዦች (አስመጪ ሊሆን ይችላል) እስከ 10ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

ለንግድ ስራ ተጓዦች (አስመጪ ሊሆን ይችላል) እስከ 10ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

source The economics view
t.me/sebeztraining
www.sebeztraining.com

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

02 Oct, 15:20


#ኢትዮጵያ

ባንኮች በአገልግሎት ክፍያ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው  አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ታውጇል፡፡

በዚህም የመንግሥት እና የግል ባንኮች ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንክ አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

@tikvahethiopia
www.sebeztraining.com
t.me/sebeztraining

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

01 Oct, 05:23


ኢትዮቴሌኮም የታሪፍ ጭማሪውን ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን አስታወቀ

ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም ከነገ መስከረም 21፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ ጭማሪ የሚያደርግ መሆኑን አስታዉቋል።

ተቋሙ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንደማይነካ የገለፀ ሲሆን ተመጣጣኝ እና የዲጅታል አካታችነትን መርህ በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ብለሏል።

ተቋሙ የሚደረገዉ ማሻሻያዉ 22 ፓኬጆችን የማይነካ እንደሆነ ቢገልፅም በምን ያህል ፐርሰንት የሚለዉን እና በየትኞቹ አገልግሎቶቹ ላይ  ተግባራዊ እንደሚደረግ አላሳወቀም።

ካፒታል የዉጪ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲመራ መደረጉን ተከትሎ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን መዘገቧ ይታወቃል ።
t.me/sebeztraining

1,802

subscribers

157

photos

4

videos