ለሩህ°ቅመም @z_spicesoul Channel on Telegram

ለሩህ°ቅመም

@z_spicesoul


ስነ ልብ
ስነ ሩህ

ሰው-ነት





| ..የሩህ ቅመም..🤍 |

TT
http://tiktok.com/@abdlkadr_nuredin
Ig
https://instagram.com/ab_nure?igshid=YmMyMTA2M2Y=
FB
https://www.facebook.com/profile.php?id=100049014845688

ለሩህ°ቅመም (Amharic)

ለሩህ°ቅመም በኢንተርክተርም በምንወገድ ስለሚገኝ የሩህ ቅመም የወንድም እና ወንድሙ ድጋፍት እንዲሆን ነው። እናትና ህብረተኛም ተመሳሳይ ህብረቱ በባህልናቅም እንደተናዙበት የሚሆን ተራራም በምርምር ብለው ወንድ እና ወንድሙን አስኪያጅ ማህበረሰብ ይጀምራል። በተጨባው ትክበታ ከቀጣይ እና በሌሎች ሚሊዮን ምንም አመራሮች ላይ በመጠቀም ሩህ ቅመም በኛ ልብ ላይ እንደወቅታችሁ እንደገለጹ እና ከወንድም እና ከህብረተኛም እና ከህጋናም እንዲሁም ከአስተምህሩ የወንድ እና የህብረተኞ ቅመምን የሚልሰጥ ቅመም ነኝ። በተጨባው ትክበታ እና ተራራውን እንጋባ ስነ ልብ ላይ ይፈልጋሉ።

ለሩህ°ቅመም

31 Oct, 18:07


በምዕራፍ ሁለት በኩል አስተያየታችሁንም እይታችሁንም በውስጥም በውጭም ያደረሳችሁኝን ሁሉ ተቀብያለሁ🤝

እኔ ግን በዚሁ በመልካም ዱዐችሁ አስታውሱኝ እያልኩ ላልተወሰኑ ጊዜያት መልካም ቆዩኝ ማለት እፈልጋለሁ።

ፊ አማኒላህ🤍

ለሩህ°ቅመም

31 Oct, 18:06


መለያየትን ፍራቻ ሰው በማይቀርቡ እና የሚቀርባቸውንም ሰው በሚገፉ ሰዎች ላይ ምንም አይነት ፍርድ አይሰጥም። የመለያየትን የህመም ስሜት ኖረውበት ካልሆነ በቀር እንዲሁ በደፈናው አያገኙትም። ከባድ ነው ስላሉ ብቻ ሸክሙን አይደርሱበትም። ከዛ ህመም አንፃር በዚህ ውስጥ ላለፉ ምንም ማድረግ ለነሱ ኖርማል ነው። ስለሰው ስሜት አለመጨነቅ እንኳ ምንም ነው። ካገኛቸው ህመም አንፃር ምኑም ለነሱ ምንም ነው። ቀድሞስ መለየትን በሚወደው ያስተናገደ ማን መጣ ማን ሄደ ምን ግዱ ነው?

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

31 Oct, 17:47


የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ልብ የቱንም ያህል ስስ ቢሆን ብዙ ነገሮችን የመተዉ ሀይል አለው። ምን ቆራጥ መሆን ላይ ነፍስ ፈሪ ብትሆንም ልባችን ጋር ግን የመቁረጥ አቅም አለ። ለልብ ይከብድ የነበረው ሁሉ በልብ ጉልበት በጊዜ ውስጥ ምንምነትን ተስተካክሎ ይገኛል። አልችለውም ብለን ስናስብ የቆየንበት ላይ ሁሉ ችለን የመቆም ብቃትን በልብ ሐይል እናገኛለን። በልብ ጥንካሬ ከባዱን መለያየት እንኳ መልመድ እንችላለን። መተዉንም መሔድንም ጨምሮ የመቋቋም አቅሙ አለን። በሰአቱ ፊል የምናደርገው ስሜት ብቻ ከዚህ አቅቦ የያዘን ሊመስለን ይቻል እንጂ ከልብ ጋር በጊዜ የማይሻር አንድም ሁነት የለም።
አንዳንድ ሰዎችም እንዲሁ ናቸው መተዉ የማትችሉ አድርገው ያስቧችሁና በስራቸው አኑረው ሊጫወቱባችሁ ይፈልጋሉ። የልባችሁን ጊዜያዊ መልክ እያዩ መሔድ የማትችሉ አድርገው በማሰብ ባሪያቸው ሆናችሁ ሊገዟችሁ  ይፈልጋሉ። ሁሉም ነገር የጊዜ ጉዳይ መሆኑን አያስቡምና ሊረቷችሁ ይጋጋጣሉ። ሰአቱ የደረሰ ጊዜ ግን ትክክለኛውን ገፅታ በራሳችሁ ተግባር ይመለከታሉ። እውነታውን በትክክለኛው ሰአት ይረዳሉ። እስከዛው ግን ባይተዋር ናችሁ። እስከዛው ታዳ የምትገፉ ናችሁ። በገዛ እጃችሁ ተገፊ ናቹ። የሆነን ታሪክ ፈጥራችሁ ለማለፍ ስትሉ ብቻ የሚሆንባችሁን ሁሉ የምትታገሱ ናቹ። አስፈላጊነታችሁን በትክክለኛው ሰአት ለማሳየት ስትሉ ብቻ ጠንከር ለማለት ትሞክራላችሁ። የመተዉ አቅም የላቸውም ብለው እንዳሰቧችሁ ሳይሆን ልባችሁ መተዉንም መሔድንም እንደሚችል ለማሳየት ስትሉ ብቻ ደስ በማይሉ ነገሮች መሀል ታልፋላቹ። የጊዜን ርቱዕነት ለማሳየት ብቻ ቻይ ትሆናላችሁ። የጊዜ ጉዳይ መሆኑን ለማስመሰከር ብቻ!

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

31 Oct, 17:42


አልሀምዱሊላህ ማለት ሁሉም ነገር ደህና ነው ማለት አይደለም።  ይልቅ አላ ኩሊ ሀል ለአላህ ምስጋና ይገባው ማለት ነው።

©ለሩህ ቅመም

ለሩህ°ቅመም

29 Oct, 17:50


አንዳንድ ነገር ስለ °የሩህ ቅመም ቡክ ካፌ°

ወደሶስት ወር ገደማ በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ምሽት ወደናንተ ሲደርስ የነበረው °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° የተሰኘው ልዩ የአንባቢያን ፕሮግራም የመጨረሻው ክፍል 11ን ከመጨረሻዋ እንግዳ ጋር ቆይታ አድርገን ምዕራፉን ዘግተናል። በዚህ ምዕራፍ ላይ ከተለያዩ ጎበዝና ጠንካራ አንባቢያንም ጋር ቆይታ አድርገናል። በቆይታችንም መሐል የተለያዩ ሐሳቦችን ስናነሳ እንዲሁም ስንጥል ቆይተናል። ስለንባብ ብዙ አውጥተናል አውርደናልም። የአንብብ ትውልድ በሚለው ሰፊ ውቅያኖስ ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ቀዝፈናል። ይህንን ትልቅ ራዕይ ከጣልንበት ስለማንሳት በብዙ ተወሳስተናል። ተጋባዥ እንግዶች ውብና ማራኪ፣ጥልቅና ገንቢ የሆኑ ምክሮችን እንዲሁም መንገዶችን አመላክተውናል። ለዚህም በመንገዱ ላይ የመመላለስ ሀላፊነቱ ደግሞ የኛው ሆኖ አልፏል።

ይህ ምእራፍ ብዙ ማለት እንዲቻል ተደርጎ የተሰናዳ ወጣ ያለ ፕሮግራም ቢሆንም ስለነበረው ቆይታ ግን ጥቂት አንዳንድ ነገሮችን እንበል።
ፕሮግራሙን ቀድሜ ሳስበው ከአንዳንድ የቅርብ ሰዎች ጋር (ከተጋባዥ እንግዶችም መሀል) ስለፕሮግራሙ አንዳንድ ነገሮችን አውርተንበታል። ተሰርቶበት የማያውቅ ወጣ ያለ ይዘትም ስለነበር ቆንጆ የሆነ ምልከታንና ይሁንታን ነበር ያገኘሁት። በምን መንገድ ይሁን በሚለው ላይም የፕሮግራሙ ዘውግ በፅሁፍ እንዲሆን ወስነን ወደተግባር አውርደነዋል። ከዚህ በኋላም ከንባብ ጋር አሪፍ ግንኙነት አላቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ሰዎች በራሴም በኩል በሰውም ጥቆማ በማግኘት ፕሮግራሙ ላይ ማሳተፍ ተችሏል። ከጥቂት እንግዶች በቀር ከሁሉም ጋር ቆንጆ የሆነ ቅርበትም ስለነበረን ፖዝቲቭ በመሆንና በማበረታታት ያቀረብኩላቸውን ጥያቄ ተቀብለውኛል። አንዳንድ ከታሰቡ እንግዶች በቀር 95% ለፕሮግራሙ የያዝኳቸው ሰዎች በቦታቸው ተገኝተው ፕሮግራሙን መታደም ችለዋል። ነገር ግን ይቀርባሉ ተብለው ስማቸው ተጠቅሶ መሳተፍ ያልቻሉም አንዳንድ ሰዎች አሉ። ለዚህም የተለያዩ ሐጃዎች መብዛትና የግል ጉዳዮች መኖር ሐላፊነቱን ይወስዳል። ፕሮግራሙ በትንሹ ሁለትም ሶስትም ሰአትና ከዛ በላይ የሚወስድም ነበርና ተጀምረው ያልተጨረሱ እንዲሁም ሐሳባቸው ያልተቋጩ ቆይታዎችም እንደፕሮግራም ሳይካተቱ ቀርተዋል።

እዚህ ምዕራፍ ላይ ተጋባዥ የሆኑ እንግዶች በብዛት ከንባብም በዘለለ በስነ-ፅሁፍ ውስጥ ያሉ ነበሩ። ከሚዲያ ጋዜጠኛ እስከ ገጣሚያን የተካተቱበት ነበር። ከንባብና ስነፅሁፍ ልምዳቸውም መካፈል የቻልንበት ነው።

ይህ ፕሮግራምም ሆነ ምዕራፍ አንድ ላይ የነበረው ፕሮግራም በብዛት ያልተለመዱና ለየት ያሉ መሆናቸው ግልፅ ነው። ለዚህም ዋና አላማ የተሰጠንን ማዕረግ ከጣልንበት እናንሳ የሚለውን ጭብጥ የሚያስይዘን ነው። የናንተ ነው ተብሎ የተሰጠንን መጠሪያ እንዴት መያዝ አለብን የሚለውን በተለየ የፕሮግራም መንገድ ያቀረብንበት ነው። አላማው ይህ ሆኖ ሳለ ይህ ምዕራፍ ላይ ፖስት ሲደረግበት ከነበረው መንገድ አንፃር ሊሆን ይችላል ያን ያህል አጥጋቢ ታዳሚ ነበር ለማለት አያስደፍርም። ያ ማለት አሁንም ለንባብ እየሰጠን ያለነው እይታ ጠባብ መሆኑን ያሳያል። መንገድ ነው ተብሎ ከተሰጠን በኋላ በዛ መንገድ ላይ መረማመድ የኛው ሐላፊነት ነውና አማራጩ የግላችን ይሆናል።

ይህ ፕሮግራም ከመነሻው አንስቶ በሐሳብ ደረጃ እንዲህ ቢሆን ሲሉኝ  የነበሩትን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ። በተጨማሪም ይህን ፕሮግራም እንዲታደሙ ስጠይቃቸው ምላሻቸውን በአዎንታ ለሰጡ እንግዶች ሁሉ  አመሰግናለሁ። የአላህ ፍቃድ ከሆነ ምዕራፍ ሶስትም በተለየ መንገድ ይመጣል የሚል ተስፋ ካለ የምንገናኝ ይሆናል። ካልሆነም በሁለት ምዕራፎች ስናደርግ የነበረውን የመፅሐፍና አንባቢያን ፕሮግራማችንን እዚሁ ዘግተነዋል።

ስለዚህ ምዕራፍ ስለይዘቱና ስለአቀራረቡ እንዲሁም ስላገኛችሁበት፣ስለሀሳባችሁ ሁሉ ልትሉ ያሰባችሁትን ከዚህ ሰአት አንስቶ ብታደርሱን መልካም ብለን እንቀበላለን ና ከስር ባለው አድራሻ ወይንም ኮሜንት ሴክሽን ላይ አስቀምጡልን።

ስለዚህኛው ምዕራፍ ምን አሉ?
( @zspicesoul_bot )

#ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ
#episode_2
#በአብድልቃድር_ኑር
#ٱقۡرَأۡ_Generation

ለሩህ°ቅመም

26 Oct, 18:05


#ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ
#episode_2
#በአብድልቃድር_ኑር
#ክፍል_11
#የመጨረሻው_ክፍል
#ٱقۡرَأۡ_Generation

የምዕራፍ ሁለት በክፍል አስራ አንድ (በመጨረሻው ክፍል) መሰናዶአችን ላይ ከ ያስሚን ዚያድ ጋር ያደረግነውን ቆንጆ ቆይታ ከስር በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://telegra.ph/%E1%88%88%E1%88%A9%E1%88%85-%E1%89%85%E1%88%98%E1%88%9D-%E1%89%A1%E1%8A%AD-%E1%8A%AB%E1%8D%8C-10-26

ለማንኛውም ሐሳብና አስተያየት ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።

@Zspicesoul_bot

ለሩህ°ቅመም

21 Oct, 18:24


አላህ ሁን ብሎት አሁን ሀፕን እያደረገ ባለ አስቸጋሪ ከረንት ውስጥ ዱዐችሁን አጥብቃችሁ ያዙት፣ከአላህ ጋር መሆናችሁን መልክ ስጡት፣እጣፈንታችሁ እየሆነባችሁ እንደሆነ በማመን ከተስፋ ርቆ መገኘት ውስጥ አትግቡ። ከአላህ በቀር እሱን ስሜታቹ የሚጋራ አንድም አካል የለምና ለነፍሳችሁ ስትሉ ጠንካራ ለመሆን ሞክሩ። የአላህ ነገሮችን በመቀያየር ችሎታ ላይ እምነታችሁ ሙሉ ይሁን። ያኔ ወደተሻለው መዳረሻ እንደሚወስዳችሁ ጥርጥር አይገባችሁም። ግድየለም አብሽሩ🤍

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

21 Oct, 18:19


መኖራችሁ ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ዘንድ ያለመኖራችሁስ ዋጋ ምን ያህል ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
ከልቡ ሰው የሆነን ስትፈልጉ አላህን ከቀድራችሁ ጋር የገጠመውን እንጂ ከዛ ሌላ አትለምኑት።

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

19 Oct, 18:08


#ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ
#episode_2
#በአብድልቃድር_ኑር
#ክፍል_11
#ٱقۡرَأۡ_Generation

የምዕራፍ ሁለት በክፍል አስራ አንድ መሰናዶአችን ላይ ከ አፍደል ከድር ጋር ያደረግነውን ቆንጆ ቆይታ ከስር በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://telegra.ph/%E1%88%88%E1%88%A9%E1%88%85-%E1%89%85%E1%88%98%E1%88%9D-%E1%89%A1%E1%8A%AD-%E1%8A%AB%E1%8D%8C-10-19

ለማንኛውም ሐሳብና አስተያየት ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።

@Zspicesoul_bot

ለሩህ°ቅመም

18 Oct, 17:27


የአንብብ ትውልድ ስለመሆናችን እንዲህ በማለት ይጀምራሉ፦

አላህ በቃሉ ለረሱል ሰ ዐ ወ መጀመሪያ የእስልምናን መልዕክት ለሰው ልጆች እንዲያደርሱ ሲመርጣቸው የወረደው የቁርዓን አያ "አንብብ" የሚለው በመሆኑ ከሁሉም በፊት ማንበብ እንደሚቀድም ያስገነዝበናል። በዚህም አሁንም ሆነ ቀደምት የነበሩ ህዝቦች  የአንብብ ህዝብ/ ትውልድ ከመሆን ውጪ አማራጭ ሊኖራቸው አይችልም።
ማንበብ አሁን ላለንበት ሁኔታዎች ሁሉ መቅረፊያ ሊሆንም ይችላል።

በቴሌግራም ቻናሉ
( https://t.me/afikedir) ላይ በሚፅፋቸው የተለያዩ ውብ ፅሁፎቹ እናውቀዋለን። በቲክቶክ ፕላትፎርም ላይም እንዲሁ ኢስላማዊ ኮንተንት ያላቸውን ስራዎች ያደርሰናል።

#አፍደል_ከድር የዚህ ሳምንት የ °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ°  መሰናዶአችን ላይ ተጋባዥ እንግዳችን ነው።

ሙሉ ቆይታችንን የፊታችን ቅዳሜ ምሽት (09/02/2017) በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 03:00 ላይ የምናደርግ ይሆናል።

መልካም ቆይታ!

©ለሩህ ቅመም

ለሩህ°ቅመም

15 Oct, 18:03


indeed some days ከአላህ በታች የሰውም እገዛ እንደሚያስፈልገን ማመን አለብን። ይህም በጉዳያችን ላይ አላህ ሰበብ አድርጎ ለሚልክልን ሰዎች ክፍት ከመሆን ይጀምራል። የአላህ እርዳታ በባሮቹም በኩል ሊመጣ እንደሚችል ማወቅ አለብን። መቼስ አላህ እያገዘን መሆኑን ለማረጋገጥ ወህይ ይውረድልኝ አይባልም አይደል?
አንዳንድ ጉዳዮች ልክ እንደ አንድ ሙዕሚን ንቁ መሆንን ይፈልጋሉ።

ለሩህ°ቅመም

15 Oct, 14:35


ደሞ ፈፅሞ ስሜታችንን ልንደብቃቸው የማይቻለን አንዳንድ ሰዎች አሉ። ምን ያህል ስሜት መደበቅ ላይ ጠንካራ ብንባል እንኳ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ግን ይህ ጥንካሬ ዋጋ ያጣል። ያነቡናል።ከማንበብም በላይ ግልጥልጥ አድርገው ያነቡናል።ከዛም በላይ ለነሱ ብቻ የከፈትነው ማንነታችን ስላለ ማግኘትን ያገኙናል። የሩሀቸውን ሰአዳ እና የልባቸውን ሰላም ከመመኘት በቀር ምን ልንሰጣቸው እንችላለን?

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

15 Oct, 14:24


የአንዳንድ ቶሎ አኩራፊ ስስ ልቦችን የልብ ንፅህና የሚረዱ ሰዎች በአለም ላይ እምብዛም ጥቂት ናቸው። ከመናገራቸው በፊት እንባ የሚቀድማቸው፣በትንንሽ ነገር ሆድ የሚብሳቸው ለሆኑ ሰዎች የተፈጠሩ ፍጡሮች ብዙ የሉም።
ስሜታቸውን የሚረዳና አይናቸውን የሚያነብላቸው ብዙ አካል የለም። ልባቸው ስስ መሆኑ ያልገባቸው ሁሉ ሲያኮርፉ ደሞ ጀመራት፣ይኸው ተነሳበት ከማለት በቀር አይረዷቸውም። ንግግራቸውን ከመጀመራቸው እንባ ሲተናነቃቸው ያዩ ሁሉ ከእውነታው እየሸሹ አድርገው ያስቧቸዋል። መነፋረቅ ብቻ የሚሏቸውም ብዙ ናቸው። ዝምታቸው አንደበታቸው መሆኑን ያልተረዱ ሁሉ የተሸነፉ አድርገው በማሰብ ራሳቸውን በነሱ ላይ የበላይ ለማድረግ ይሞክራሉ።
ብዙ ጊዜ የልብ ንፅህና እነዚህ ሰዎች ጋር መኖሩ ስለማይገባቸው ለነሱ ያላቸው ግምት አናሳ ነው። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ጋር ከልብ የሆነ መውደድ አለ፣ከልብ የሆነ ርህራሄና ፍቅር አለ። ሰዎች ሊያዩት የማይችሉት ውብ ልብ አላቸው። ከአንዳንድ ሰዎች በቀር ማንም ሊደርስበት የማይችል ስብዕና አላቸው።
እነዚህን ሰዎች ለማንበብ የተሰጡ ሰዎች ባህሪያቸውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አያያዛቸውን ያሳምራሉ። ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለሚረዱ ቅርበታቸው ላይ ጥንቁቅ ናቸው። እንዲሆን የሚፈልጉትና የማይፈልጉት ሁሉ ስለሚገባቸው ማድረግ ያለባቸውን ማድረግ ከሌለባቸው ይለያሉ። ልክ ነው ለእንደነዚህ አይነት ስስ ልቦች አምሳያ ልብ ወይንም መልካም የሆነ ልብ ያስፈልጋቸዋል። ከቻልን እስቲ ለመረዳትና ለማንበብ እንዲሁም ከአጠገባቸው ለመሆን እንሞክር።

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

12 Oct, 18:03


#ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ
#episode_2
#በአብድልቃድር_ኑር
#ክፍል_10
#ٱقۡرَأۡ_Generation

የምዕራፍ ሁለት በክፍል አስር መሰናዶአችን ላይ ከ ናዲያ ቢያ ጋር ያደረግነውን ቆንጆ ቆይታ ከስር በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://telegra.ph/%E1%88%88%E1%88%A9%E1%88%85-%E1%89%85%E1%88%98%E1%88%9D-%E1%89%A1%E1%8A%AD-%E1%8A%AB%E1%8D%8C-10-12

ለማንኛውም ሐሳብና አስተያየት ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።

@Zspicesoul_bot

ለሩህ°ቅመም

12 Oct, 08:24


በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ላይ በምታዘጋጃቸው ውብ ፅሁፎቿና ፕሮግራሞቿ እናውቃታለን። በተለይም በፌስቡክና ዩቲዩብ እንዲሁም ቴሌግራም ፕላትፎርም ላይ እናገኛታለን። በቲክቶክ እና ኢንስታግራም ገጿም ላይ ፕሮግራሞቿን ታደርሰናለች። በፌስቡክ እንዲሁም በቴሌግራም ፕላትፎርም ላይ የተለያዩ ፅሁፎችን ታዘጋጃለች። ፅሁፎቿም በብዛት መልዕክተኛውን (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) የሚያወሱ  ናቸው። ሲራቸውን በራሷ ቀለም እያዘጋጀች ወደሚጠብቋት አንባቢዎቿ ታደርሳለች።
ከዛ በተጨማሪ one tube በተሰኘ የዩቲዩብ መስኮት  ላይ አብረዋት ከሚሰሩ ሁለት ልጆች ጋር በመሆን የተለያዩ ኢስላማዊ ይዘት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ስራዎችን በመስራት ብዙ ምእራፎችን ማዘጋጀት ችለዋል።

በቴሌግራም ቻናሏ (@Loverofthemessenger ) እናውቃታለን። #ናዲያ_ቢያ የዚህ ሳምንት የ °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ°  መሰናዶአችን ላይ ተጋባዥ እንግዳችን ናት።

ሙሉ ቆይታችንን ዛሬ ምሽት (02/02/2017) በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 03:00 ላይ የምናደርግ ይሆናል።

መልካም ቆይታ!

©ለሩህ ቅመም

ለሩህ°ቅመም

10 Oct, 18:11


በልብ መስፋት ዙሪያ ረሱሊ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም ልባቸው የሰፋ እንደነበር በራሱ በጌታችን ከላም የሰማነው ሐቅ ነው። ልብህን ላንተ አላሰፋንልህምን? እያለ ሱራ ሸርህ መባቻውን በዚህ ጥያቄ ያደርግና ፥ አስፍተንልሀል ብሎ ደሞ አላህ ራሱ ምላሽ ይሰጥበታል። ነብየላህ ሙሳ የልብ መስፋትን ከአላህ ተማፅነው ሲሰጡ የኛ ነብይ ሙሐመድ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም ግን ገና ሲወለዱ የተሰጡት ስጦታ ነው። ይህም የአላህን ችሮታና ጥበብን ያሳየናል። የነብያችን የልብ መስፋት ይዞ የመጣውን ኸበር ሁሌም የምናውቀው ነው። ይበልጥ ደግሞ ለኛ ይዞልን የመጣው ብዙ ነው። የረሱሊ የልብ መስፋት የፈጠረውን ተፅዕኖ ስናስተውል እና ነብየላህ ሙሳ በዚህ ዱዐ ጌታቸውን እንደተማፀኑ ስናይ ታዳ ይህ ነገር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንመለከታለን። የልብ መስፋት ከአላህ እንደሆነ ካመንን እና ይህም ለምርጥ ባሮቹ ብቻ መሆኑን ከተረዳንም አላህን በዚህ ዱዐ ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም።
(ጌታችን ሆይ ልባችንን አስፋልን)

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመድ ወአላ አሊ ነብይና ሙሀመድ

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

08 Oct, 17:56


ከምዕራፍ አንድ በመቀጠል በምዕራፍ ሁለት ላይ ከአንባቢያን ጋር ስናደርግ የነበረው ልዩ ቆይታችን (ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ) መገባደጃው ደርሷል። ይኸውም መጪዎቹን ሶስት ቅዳሜዎች ማለትም (02-02-17 ፣ 09-02-17 ፣ 16-02-17( ) ከሶስት የመጨረሻ እንግዶች ጋር ቆይታችንን አድርገን ይህን ምዕራፍ የምንዘጋው ይሆናል።

ስለዚህ የምዕራፍ ሁለት ፕሮግራም ልትሉ ያሰባችሁትን እንዲሁም ለማለት የምትፈልጉትን ሁሉ እያዘጋጃችሁ ቆዩ።

መልካም ቆይታ!

©ለሩህ ቅመም

ለሩህ°ቅመም

03 Oct, 18:24


ልቤን ሞቅ የሚያደርግ አንድ ሩህ ያለው የነብየላህ ሙሳ ዱዐ አለ።
ይኸውም፥ጌታዬ ሆይ ልቤን አስፋልኝ፣ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ እያለ የሚቀጥለው ዱዐ ነው። ያሰላምም በርግጥም ነብየና ሙሳ ለጌታቸው ከሩህም ሩህ ያለውን ሸጋ ተማፅኖን ተማፅነዋል። ምክንያቱም የልብ መስፋት ጥቅማ ጥቅሙ ብዙ ነውና። ከሁሉ ቀዳሚው ከአላህ ጋር ያለንን ሪሌሽን ፀአዳ የተሞላበት እንዲሆን ማድረግ ነው። የልብ መስፋት በአላህ ላይ ያለን እምነት ኢህሳን እንዲኖረው፣ለአላህ ያለን ታዛዥነት ግሬስ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው። የማስተዋልና የመረጋጋት ጥበብንም የሚያላብስ ነው። ምንጊዜም የልብ መስፋትን ተከትለው የሚመጡ ነገሮች ሁሉ ሸጋ ናቸው። ለዚህም አላህ ለመረጣቸው ባሮቹ ካልሆነ በቀር የልብ መስፋትን ለሁሉም አይሰጥም።ለምን ከተባለ አንዳንድ ውድ ነገሮች ያለቦታቸው ርካሽ ናቸው እንላለን። አላህ ልባችንን እንዲያሰፋልን ቀድመን ከሱ ጋር ያለንን ኑረት ውብ ማድረግ አለብን። ልባችንን እንዲያሰፋልን ወደአላህ ዱዐ ማድረግ ይጠበቅብናል። ያ ማለት ከአላህ ጋር መሆናችን ሌላ ውብ ነገር ሆኖ ሳለ የልብ መስፋትን መሰጠት ደግሞ ሌላ ከውብም ውብ የሆነ ሽልማት ነው። ሙሳም ከጌታቸው ጋር ነበሩ እንዲሁም በጌታቸው ላይ የነበራቸው እምነት ውብ ነበር። ታዲያ አላህም አብረዉት ያሉ፣ ሙሉ እምነታቸውን የሰጡት ባሮቹን መሻት አይቶ ዝም አይልምና ሙሳ የጠየቁትን ነገር «ሙሳ ሆይ ልመናህን በእርግጥ ተሰጠህ» በማለት የጠየቁትን ተፈፃሚ እንዳደረገላቸው ይነግረናል። ነብየላህ ሙሳም የልባቸውን መስፋት ፈልገዋልና የፈለጉትን ማግኘት ችለዋል።
አላህ የኛንም ልብ ያሰፋልን ዘንድ ታዳ ከሱ ጋር ያለንን ሐያት ማሳመር አለብን።

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

28 Sep, 18:05


#ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ
#episode_2
#በአብድልቃድር_ኑር
#ክፍል_9
#ٱقۡرَأۡ_Generation

የምዕራፍ ሁለት በክፍል ዘጠኝ መሰናዶአችን ላይ ከ ሂክማ ወለላው ጋር ያደረግነውን ቆንጆ ቆይታ ከስር በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://telegra.ph/%E1%88%88%E1%88%A9%E1%88%85-%E1%89%85%E1%88%98%E1%88%9D-%E1%89%A1%E1%8A%AD-%E1%8A%AB%E1%8D%8C-09-28

ለማንኛውም ሐሳብና አስተያየት ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።

@Zspicesoul_bot

ለሩህ°ቅመም

26 Sep, 18:52


#የጥበብ_ቤት በተሰኘ የስነ-ፅሁፍ ማህበር ውስጥ ከአባላቶች መሐል ትገኛለች። በስነ-ፅሁፍ ውስጥ ከግጥም አንስቶ የተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ይዘቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ታጋራናለች። በዩቲዩብ ፕላትፎርም ላይ የኢንተርቪው እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ 5 ክፍል የሚጠጋ በኑረታችን ላይ ያጠነጠነ ፖድካስት ሰርታለች።

#ሂክማ_ወለላው የዚህ ሳምንት የ °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ°  መሰናዶአችን ላይ ተጋባዥ እንግዳችን ናት።

ሙሉ ቆይታችንን የፊታችን ቅዳሜ ምሽት (18/01/2017) በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 03:00 ላይ የምናደርግ ይሆናል።

መልካም ቆይታ!

©ለሩህ ቅመም

ለሩህ°ቅመም

23 Sep, 18:15


ደሞ አንዳንዴም ለኛ የተግራራው ሁሉ ለሌላውም ይግራራል ከሚል እሳቤ መውጣት አለብን።ገጠመኝ የሆነልንን ጉዳይ ለሌላውም ይሆናል የሚል እሳቤ ሊኖረን አይገባም።ለኔ ሆኖ ያየሁት የምርም ለዛ ሰው ይሆናል ወይ የሚል ጥያቄ ውስጣችን ሊፈጠር ይገባል።ለኔ የተቻለኝ ለዛ ሰውስ ይቻል ይሆናል ወይ ብለን ማሰብ አለብን።ግድየለም አንዳንድ ነገሮችን ሳናጠና በችኮላ የሰው ሰውን ተስፋ አንግደል።ኸይሩን አደረግን ብለን ባለማወቅ መጥፎውን አናስቀር። አንዳንድ ውለታዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናልና እስቲ ስለሁሉም እያስተዋልን።

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

23 Sep, 18:02


ብዙ የፈተነን መንገድ ውስጥ ማንም እንዲገባ አናደርግም። ቀድመን ያለፍንበትን አስቸጋሪ ጉዞ ሌላውም እንዲያልፍበት አንፈቅድም። ሰዉ ነንና ማንም ወደአዘቅት ሲራመድ እያየን ዝም አንልም። መንገዱን ሳያውቁ ጉዞ ለጀመሩ በጉዞው መሀል እንቅፋቱ የት ጋር እንዳለ ከመናገር ወደኋላ አንልም። በስህተት የጀመርነውን መንገድ ሌላ አካል ሲጀምረው አይተን ባላየ አናልፍም።የኛኑ ስህተት ሌላ ሰው እንዲደግመው አንፈቅድም።እኛ ተሳስተናል ብለን ሌላውም እንዲሳሳት አናደርግም።ለሰው የምንመኘው ሁሉ ለራሳችን የተመኘነውን ያህል ሊሆን የግድ ነው። ሰዉ መሆን መልኩ ይህንንም ይመስላል።

(አብድልቃድር ኑር)

ለሩህ°ቅመም

23 Sep, 15:00


አንዳንድ ያለምንም ዱዐ የተወሰኑ ውሳኔዎች የእድሜ ልክ ፀፀትን ያስቀራሉ። አላህ ሆይ መንገዱን አንተ ምራኝ ያልተባለለት መንገድ አባጣ ጎርባጣው ብዙ ነው። በነገሮች ውስጥ አላህን ያለመያዝ እና እሱን ያለማስገባት መዳረሻው ከዚህ ሊያልፍ አይችልም።
አንዳንድ ውሳኔዎች ግብራቸው ምን መልካም የሆነ ቢሆን እንኳ አላህ ካልኖረባቸው አያምሩም።
በአንዳንድ ውሳኔዎቻችን ውስጥ ከልባችን ና ከአላህ ውጪ ማንም ሊገባባቸው አይገባም። ውሳኔያችን ውስጥ አላህ እስካለና ልባችን እስካመነበት ማንም ጣልቃ እንዲገባ መፍቀድ የለብንም።የአንዳንድ ውሳኔዎች መበላሸት ከሌላ አካል የመጡ እንደሆን ነው።በማንነታችን ላይ፣በሕይወታችን ላይ የውሳኔውን መንገድ ሌላ ሰው ሲወስን ነው። ከአላህ ቀጥሎ ልባችን ወደመራን ከዛ አለፍ ካለ ግን አንዳንዴም የሩህ ሰዎቻችንን ምልከታ መቀበል የተሻለ ነው። ማንም መጥቶ ይህ ነው የሚሻለው ስላለ ብቻ ልባችን ክፍት ሊሆን አይገባም።ምናልባት ያ ውሳኔ ለዛ ሰው የተሻለ ሆኖ ብናይ እንኳ የኛም እጣፈንታ እንዲያ ይሆናል ብለን አናስብ።

(አብድልቃድር ኑር)