ሱናህ(السنة)

@hassendawd


ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል
1,አቂዳ
2, ፊቂህ
3, ሀዲስ
4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ)
5, ሙስጠላህ
6,ኡሱል
ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

ሱናህ(السنة)

19 Oct, 13:04


ቀልባችን አላህን እንድፈራ ሊያግዙን ከሚችሉ ጉዳዮች ዉስጥ፦
1) የአላህን ዉለታዎች ማስታወስ
2) የአላህን ስሞችን እና ባህርያቶች ማወቅ
3) ሰለፎችን አላህን እንዴት እንደሚፈሩት ታሪካቸውን ማንበብ
4) ሞትን ማስታወስ
5) ምክሮችን ማዳመጥ
6) ሀላልን መመገብ
7) የቲሞችን መንከባከብ
8) ስለቂያማ ማስታወስ
9) ወንጀሎችን መራቅ
10) ጥሩ ጓደኞችን መጎዳኘት
11) መቃብርን መዘየር
12) ዱዓእ ማድረግ
13) ማለቃቀስ ( አላህን ብቻ በማስታወስ እምባ ባይመጣም ለማልቀስ መታገል )
14) ቁርአንን መቆራኘት
15) ዚክርን ማብዛት
.
ይገኙበታል::
=
ከአላህ ርቃችሁ ደስታ አጣን አትበሉ።
=
እሱ በሱ ላይ መልካም ያሰቡትን ፣ በሱ የተመኩትን፣ በሱ ላይ ተሰፋ የጣሉትን ሁሉ አያሳፍራቸውም።
منقول

ሱናህ(السنة)

18 Oct, 15:09


ይህ የደዕዋ ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

★★★★★
📡 የ ዳዕዋ ቲቪ ስርጭትን በ ናይል ሳት
ለመከታተል:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11636
ሲምቦልሬት:- 27500
ፖላራይዜሽን:- vertical
★★★★★

Youtube
https://www.youtube.com/@daewa_tv

Facebook
https://www.facebook.com/daewatv/

Telegram
https://t.me/daewa_tv

ሱናህ(السنة)

06 Oct, 06:00


ራ*ፊ*ዳ* ሺዓዎች!

“እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ ስም ማጥፋት ፈልገው ነበር፣ ነገር ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው የሰሓቦቻቸውን ስም አጠፉ። እርሱ መጥፎ ሰው ነው እንጂ እርሱ ጥሩ ሰው ቢሆን ኖሮ ባልንጀሮቹም ጥሩ ይሆኑ ነበር፤ እንዲባል የነቢዩ ﷺ ባልደረቦቻቸውን ሰደቡ።”

| ኢማሙ ማሊክ/አስ – ሷሪም አል– በት–ታር (580)

ሱናህ(السنة)

04 Oct, 16:35


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ትልቅ የስራ እድል!!!


ሐላል ብሪጅ ሰሉጅንስ ከዚህ በታች በሚቀርቡ ስራዎች ላይ መስራት የምትፈልጉ ሰዎችን ይፈልጋል።
1) ቁርአን/ኪታብ ቂርአት ማቅራት
2) ቁርአን/ኪታብ ቂርአት ማቅራት ዘመናዊ ትምህርት ከማስጠናት ጋር
3) የዘመናዊ ትምህርት የማስጠናት ስራ
በእነዚህ ዘርፎች ላይ መስራት የምትፈልጉ በአስቸኳይ በቴሌግራም ቻነል t.me/HalalBridgeSolutions ወይም በስልክ ቁጥር 0973103819 ወይም በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ለማሳወቅ እንወዳለን። ወንዶችም ሴቶችም ይፈለጋሉ።

ሱናህ(السنة)

03 Oct, 12:24


ኢሬቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?

እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።

ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።

መውሊድ፣ ገና፣ ፋሲካ በዓል "ቢድዓህ" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ ነው "ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ሱናህ(السنة)

03 Oct, 06:14


#አብሽሩ
የትኛውም ውስብስብ ጉዳይ ቢገጥማችሁ ለአላህ ቀላል ነውና ትእግስት በማድረግ
ሰላትና ዱዓ በማብዛት ወደ አላህ ተመለሱ ውጤቱንም በትእግስት ጠብቁ ይሳካል አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና አብሽሩ ! ! !
((يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ))
((እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡))(አል-በቀራህ - 153)
★ ያ አላህ ላንተ መስገድን አንተን መማፀንን አግራልን
★ ያ አላህ የሚገጥሙንን ፈተናዎች ምናልፍበት ጠንካራ ትእግስትን ስጠን
★ ያ አላህ በእምነታችን ከሚያሳንፈን ፈተና ጠብቀን

ሱናህ(السنة)

02 Oct, 16:07


#ምላስ
የሰው ምላስ በአጉሊ መነጽር ሲታይ ይህን ይመስላል ወጣ ብለው ሚታዩት ነገሮች(taste bud) ጣእም ሚለዩልን ህዋሶች ናቸው👅
የሰው ምላስ ጣፋጭ፣ጎምዛዛ ፣ ጨዋማ እና መራራ ምግቦችን የመለየት ኃላፊነት ያላቸው ከ2,000 እስከ 8,000 የሚደርሱ የጣዕም መለያ taste bud ይዟል።
እያንዳንዱ ሰው ከሌላው የሚለይ #ልዩ የምላስ #አሻራ አለው
የምላስ የላይኛው ክፍል ልዩ የሆነው ክፍል ሲሆን
ሁለት ሰዎች አንድ አይነት የምላስ ቅርፅ ፈፅሞ አይኖራቸውም። #ሱብሃን_አላህ
وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?›

ሱናህ(السنة)

02 Oct, 14:04


ከአላህ ውጪ ሌላን አታምልኩ ማለት ወሀብይነት ነው ?
---------------------------------
#ሸይኽ_ሙሓመድ_ዘኪ
#አቂደቱል_ዋሲጢያ

ሱናህ(السنة)

01 Oct, 07:15


ወላሂ! ... ከአርሽ በላይ ከፍ ባለው ጌታዬ እምላለው ፤ ቢዒዝኒል ዋሂደል አሀድ ከአላህ ጋር ያለህ ግንኙነት ሲያምርና ሲስተካከል ልብህ አዛንን መናፈቅ ትጀምራለች። ይህኔ አንተም መች ነው ሙዐዚኑ حي على الصلاة (ኑ ወደ ሰላት) ብሎ የሚጠራኝ ብለህ በጉጉት ጥሪውን መጠባበቅ ትጀምራለህ። ሱጁድም ከሁሉ ነገር ማረፊያህ እና መደሰቻህ ትሆናለች።

የረሱል ተወዳጅ ባልደረቦች ሰላታቸውን አሰላሙዐለይኩም ወራመቱላህ ብለው ሲጨርሱ ያለቅሱ ነበር። ምነው ለምን ነው ምታለቅሱት ሲባሉ መልሳቸው ጌታዬን እኮነው የተለያየሁት፣ አላህን እኮ ነው ማናገር ያቆምከት ነበር።

ነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) የሰላት ወቅት ሲደርስ ቢላልን፦

ارحنا بالصلاة يابلال

ይሉት ነበር። "ቢላል ሆይ በሰላት አሳርፈን"። ምን ያማረ ንግግር ነበር ፤ ሁሌም ንግግሩ ጣፋጭ ከሆነው ነብይ ዘንድ ይወጣ የነበረው።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

ሱናህ(السنة)

29 Sep, 05:22


ኢማም አሕመድ ኢቢኑ ሐንበል - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ተባሉ።፦
🍃ሰውየው የኢብኑ አቢ ዳውድ ባልደረቦች(የቢድዓ ሰዎች) በሚያጋጥማቸው ነገር ይደሰታል፣ ይህን ማድረጉ ኃጢአት ነውን?
እርሳቸውም ፦"በዚህ የማይደሰት እርሱ ማነው!?"

🌷 አስ–ሱና ሊልኸላል (1769)

ሱናህ(السنة)

28 Sep, 09:06


እጅግ ከሚያስደንቀኝ ነገር መካከል ሱናን በተወሰኑ ተቃርኗል ብለህ ምታስበውን ሰው መዘርጠጥ፣ መሳደብ ምን ይባላል??

ከየትኛውም ሂዝብ ሁን ከፈለክ ከዐብዱልሀሚድ፣ ከኢልያስ፣  ከኢብኑ ሙነወር፣ ከአቡቀታዳ ከማንኛውም ሀቅ ላይ ነው ብለህ ከምታስበው ዘንድ ተጠግተህ ቢሆን በተወሰነ መልኩ ሱናን ተቃርኗል ብለህ ምታስበውን ኡስታዝ እንዴት ዝቅ አድርገህ ትዘረጥጣለህ??

የእውነት የአላህን ፊት ፈልገህበት ነው ምትሰድባቸው ምታንቋሽሻቸው?? ነፍስህን ጠይቅ የእውነት ከአላህ አጅር ትፈልግበታለህ??

እንዴት ሙናፊቆቹ ዑመር ገነቴና ዑመር ኮምቦልቻና ማትናገረውን ንግግር በእምነት ሚቀርብህን ግለሰብ ትናገራለህ?? ያውም የእድሜ ታላላቆችህን

አላሁ ሙስተአን

ሱናህ(السنة)

28 Sep, 09:06


በጀመአ የሰገደ ብቻውን ከሰገደ 27 እጥፍ ይበልጣል
በመስጂድ የሰገደ ቤቱ(በጀመአም ቢሆን) ከሰገደ 25 ይበልጣል

ሼኽ ዐብዱሰላም ሀፊዘሁላህ

ሱናህ(السنة)

27 Sep, 14:04


ብዙዎቻችን አሟሟታቹ እንዴት ቢሆን ትመርጣላቹ? ተብለን ብንጠየቅ----- ከፊሉ መስጂድ የጀመአ ሰላት እየሰገደ በሱጁድ ላይ ይላል። ከፊሉ ደግሞ በአላህ መንገድ ላይ ስዋደቅ ፤ ሸሂድ ሆኜ መሞትን ነው ምፈልገው ይላል። የአላህ ቃል የሆነውን ቁርአን  እየቀራ መሞት የሚመኝም ከመሀከላችን አይጠፋም። ቅሉ ግን ወዲ ነው--------

አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ ሱጁድ ላይ መሞት የሚመኘውም በሰላቱ ደካማ ሆኖ እናገኘዋለን። ሸሂድ መሆን የሚመኘውም ፤ ውሎው ሸሂዶች ከሚውሉበት ቦታ ፈፅሞ የራቀ ሆኖ እንመለከተዋለን። ቁርአን እየቀራ መሞት የሚፈልገውም ቢሆን ቁርአኑን ከፍቶ ካየው ወራቶች አስቆጥረዋል። ታዲያ ፍየል ወዲ ቅዝምዝም ወዲያ ሆንን አሟሟታችን እኛ እንደምንመኘው ይሆናልን-----?

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
https://t.me/Hassendawd

ሱናህ(السنة)

27 Sep, 12:47


ኢስሀቅ ኢብኑ ረሀወይ

أبو يعقوب إسحاق بن إبراهيم بن مخلد بن إبراهيم بن عبد الله بن مطر بن عبيد الله

አቡ የዕቁብ ኢስሀቅ ቢን ኢብራሂም ቢን ሙኸለድ ቢን ኢብራሂም ቢን ዐብደላህ

የተወለዱት በ161 አሂ በቱርክመኒስታን ነበር።

🤌ኢብን ረሀዋይ የተባሉት ምክንያት ሲወሳ አባታቸው በመንገድ ላይ ስለተወለዱ ረሀወይ ተባሉ. ይላሉ።                                                                               
ዒልምን ከታላላቆች ወስደዋል ኢብኑ ሙባረክ፣ ሱፍያን ቢን ዑየይና ፣ ፋደይል ኢብኑ ኢያድ ፣ ወኪዕ ቢን ጀራህን ተጠቃሾቹ ናቸው።

🤛ሀዲስን ከሳቸው ቡኻሪ ፣ ሙስሊም ፣አቡ ዳውድ ፣ አህመድ ዘግበዋል።


🤜ኢማም ቡኻሪ ሰሂህ ሀዲስን ለመዘገብ ያነሳሷቸው ኢስሃቅ ቢን ራሀወይ ነበሩ። እንዲህ ይላሉ ''ኢስሀቅ እኛ ዘንድ ነበር  እንዲህ አለ ''የመልዕክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰሂህ ሀዲስ ብቻ የያዘ ኪታብ ብታዘጋጁ'' ይህም ንግግር ልቤ ላይ ቀረ ሰሂሁል ጃሚዕ ሰሂሁል ቡኻሪን መሰብበሰብ ጀመርኩኝ'''

🤏ካዘጋጇቸው ኪታቦች መካከል ሙስነድ ፣ ጃሚዑል ከቢር፣ ጃሚዑ አስሰጊር ፣ ተፍሲሩል ከቢር ይገኙበታል።

👌አቡ ዙርዐ ረሂመሁላህ  እንዲህ ይላሉ ''ከኢስሀቅ የበለጠ የሚሀፍዝ አላየሁም''


👌አሊ ቢን ሀጀር ረሂመሁላህ  እንዲህ ይላል ''ኢስሀቅ የሞተ እለት በኹራሳን በዒልም በፊቅህ እሱን የመሰለ አልተወም''

👉በ238 አሂ ዱንያ ተሰናብተዋል ረሂመሁላህ ረህመተን ዋሲዓ

ሱናህ(السنة)

27 Sep, 06:43


የለስላሳ ቆርኪዎች ላይ የሚገኙ ሽልማቶችን መውሰድ እንዴት ይታያል።
---------------------------------
#ሸይኽ_ሙሓመድ_ሓሚዲን

★★★★★
©Daewa TV

ሱናህ(السنة)

27 Sep, 04:27


የኦቶማን ሱልጣኔት ገዥዎች ለምን ነበር ትልቅ ጥምጣም የሚለብሱት? ከትላልቅ ጥምጣሞች በስተጀርባ ያለው ጥልቅ ሚስጥር ምን ነበር?

   ብዙ ጊዜ የኦቶማን ኸሊፋዎችን በጣም ትላልቅ እና ከባባድ ጥምጥም ለብሰው የሚያሳዩ ምስሎችን እንመለከታለን። ብዙውን ጊዜ ሰዎች እኒህን ነገር ባዩ ቁጥር ይደነቃሉ። አንዳንዶችም እነዚህን ጥምጣሞች “የሽንኩርት ጭንቅላት” ብለው በመጥራት ይቀልዳሉ።

   ሆኖም ግን ነገሩ እንዲህ ነው። የታላቋ ኦቶማን ሱልጣኔት አስተዳደር ገዥዎች ከሞት በኋላ ስለሚኖራቸው ሕይወት ሁል ጊዜ ይጨነቁ ስለነበር ለጂሃድ ትልቅ ግምት ይሰጡ ነበር። ድል ​​ለመንሣት ወይም በአላህ መንገድ ላይ ሸሂድ ለመሆን ካላቸው ጉጉት በተጨማሪ አላህ ፊት ትሑት ሆኖ ለመቅረብ ራሳቸውን ተጠያቂ ያደርጋሉ። በዚህ ምክንያት አብዛኞቹ የኦቶማን ኸሊፋዎች ለሰዎች ትሁት እንዲሆኑ እና ሞትን ለማስታወስ ይረዳቸው ዘንድ ሁልግዜም በራሳቸው ላይ የጀናዛ መጠቅለያ ከፈንን እንደ ጥምጣም ይለብሱ ነበር።

ምስሉ ላይ ያሉት ግርማዊ ሱልጣን ሱለይማን ኻን ናቸው።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

ሱናህ(السنة)

26 Sep, 11:53


ኢማም አድዳሪሚ

ሙሉ ስማቸው ዑስማን ቢን ሰዒድ ቢን ኻሊድ ቢን ሰዒድ አትተሚሚ አድዳሪሚ አስሲጂስታኒ

የተወለዱት በ200 አሂ በኹራሳን ነው

👌አረብኛን ከቋንቋው ሊቅ ኢብኑል ዐረቢ ወስደዋል። ሀዲስን ከያህያ ቢን መዒን ዓሊ ቢን መዲኒ እና አህመድ ቢን ሀንበል ከመሳሰሉ ታላላቆች ወስደዋል።

ብዙ ታላላቆችንም አፍርተዋል።

👊በአህሉል ቢድዐ ላይ እጅግ ብርቱ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል አህባሾችና መሰሎቻቸው ዘንድ እጅግ የተጠሉ ናቸው።

🤌ካበረከቷቸው ግሩም ስራዎች መካከል ሀዲስን የሰበሰቡበት ሱነኑ አድዳሪሚ እና በ ጀህሚያዎች ላይ የፃፏቸው ሁለት ድንቅ ኪታቦች "አርረድ አለልጀህሚያ" እና "ነቅድ ቢሽሪል ሚሪሲ" ይገኙበታል።

👉ኢብን ሂባን ከዱንያ ኢማሞች ነው ብለዋቸዋል።

👉ኢማም አህመድ ስለ ዳሪሚ "ዱንያ ቀረበችለት እንቢ አለ" ብለዋል

👉በ280 ሂጅራ ወደአሂራ ሄደዋል። ረሂመሁላህ ረህመተን ዋሲዓ   
https://t.me/Hassendawd

ሱናህ(السنة)

26 Sep, 11:33


ሰአት እና ቀጠሮ

ايام العسبع አያሙል ኡስቡእ
የሳምንቱ ቀናት

1,እሁድ፦ አል አሀድ/እልአህድ/ኢልአህድ
2,ሰኞ፦አል ኢስነይን/አልእትኔን/እእቲኔን/እተኔን
3,ማክሰኞ፦አልሱላሳ/እሰላስ/ኢተላት/አልተላታ/እተሌታ
4,ሮብእ፦አል አርቢአ/አዕርቢአ/አል አርበአ/እልእርበእ
5,ሀሙስ፦አልኸሚስ/እልኸሚስ/ኢልኸሚስ
6,ጁምአ፦አልጁምአ/እልጁምአ/ኢልጁምአ/ኢልዩምአ
7,ቅዳሜ፦አስሰፕት/እልሰፕት/አልሰብት

ሰአት
አል ሰአ ወህዴ/ወህዳ አንድ ሰአት
አል ሰአ እስኔን /እትኔን/ተኔን ሁለት ሰአት
አለሰአ ሰላሳ/ተላታ/ተሌታ ሶስት ሰአት
አል ሰአ አርበአ/እርበእ አራት ሰአት
አል ሰአ ኸምሳ/ኸምሴ አምስት ሰአት
አል ሰአ ስታ/ስቴ/ሲታ ስድስት ሰአት
አል ሰአ ሰብአ/ሰብኤ ሰባት ሰአት
አል ሰአ ሰማንያ/ተማንያ/ትማንዬ ስምንት ሰአት
አል ሰአ ትስአ ዘጠኝ ሰአት
አል ሰአ አሸር አስር ሰአት
አል ሰአ እህዳ አሸር/ህዳእሽ አስራ አንድ ሰአት
አል ሰአ እስና አሸር/እትናአሽ አስራ ሁለት ሰአት

"بل مثال تتدح المقال"
" ነገር በምሳሌ ይብራራል"

ምሳሌ፦1، አል አሀድ አል ሰአ ወህድ
እሁድ አንድ ሰአት
እተሌታ አሰሰአ ትማንዬ
ማክሰኞ ስምንት ሰአት
3 ،ኢልዩምአ አልሰአ ሰብኤ
ጁምአ ሰባት ሰአት
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0940866666 ወይም
☎️ 0935033426 ይደውሉ

በአካል መምጣት ከፈለጉ
ጎሮ አደባባይ ቤተልሔም ህንፃ 4ተኛ ፎቅ

Freedom Training center
በነፃነት ለማውራት ትክክለኛው ቦታ


ለመመዝገብ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ👇👇

https://forms.gle/q2qGoYBQKkZcZCMz6

📱Tiktok  📱Telegram  📱Community

ሱናህ(السنة)

26 Sep, 10:32


አድ ዶማኢር / الضماعر/ ተውላጠ ስም
1,አና፣አናህ...................እኔ
2,አንታ/ኤንታ/ኢንት .........አንተ
3,አንተ/ኢንቲ/እንቲ ...........አንቺ
4,አንቱም/ኢንቱም/እንቱ ......እናንተ
5,ነህኑ/ኢህና/ነህን/ኒህና ......አኛ
6,ሁዋ/ሁ/ሁዌ ...................እሱ
7,ሂያ /ሂ/ህዬ.......................እሷ
8,ሁም/ሀማ/ህኔ ..................እነሱ

فصل  الخامث
ዶማኢር/pronouns/ተውላጠስም
" خير الكلام من دل وقل "
"The best words are those that are little and kind"

ሱናህ(السنة)

26 Sep, 03:03


#......⁉️
#ለሰው ልጆች መልካም መዋል፣ በመልካም ስራ መጥቀም፣ ችግራቸውን ማቃለል፣ ሀዘናቸውንና ሀሳባቸውን መጋራት፣ የተዘጉ ልቦችን ወደ ኢስላም ብርሀን ይከፍታል ።

( ﺃﻋﻈﻢ ﺃﺳﺒﺎﺏ ﺍﻧﻔﺘﺎﺡ ﺍﻟﻘﻠﻮﺏ ﻟﻺﺳﻼﻡ )

#የፍትህ፣ መልካምነትና የእዝነት መንገድ የሆነውን የአላህ ሸሪዓ ሰዎች በቀላሉ እንድቀበሉ ይረዳል።

ለሰዎች መልካም መዋልን አስመልክቶ ነብዩ እንድህ ይላሉ።

ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ (ﷺ) :- ‏" ﺃَﺣَﺐُّ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪِ ﺃَﻧْﻔَﻌُﻬُﻢْ ﻟِﻠﻨَّﺎﺱِ، ﻳَﻜْﺸِﻒُ ﻋَﻨْﻪُ ﻛُﺮْﺑَﺔً، ﺃَﻭْ ﻳَﻘْﻀِﻲ ﻋَﻨْﻪُ ﺩَﻳْﻨًﺎ، ﺃَﻭْ ﻳَﻄْﺮُﺩُ ﻋَﻨْﻪُ ﺟُﻮﻋًﺎ‏) 📚 ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻄﺒﺮﺍﻧﻲ، ﻭﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ‏

አብደላህ ኢብኑ ዑመር ረ.ዐ እንድህ ሲሉ ከነብዩ ﷺ ዘግበዋል:

" አላህ ሱ.ወ ዘንድ በጣም ተወዳጁ ሰዉ ለሰዎች ጠቃሚ ( መልካም የሚውል)፣ ችግር የሚቀርፍ፣ እዳን የሚከፍል ወይም ረሀብን የሚያስወግድ ሰው ነው ብለዋል።"

قال رسول الله ﷺ :-" ﺃَﺣَﺐُّ ﺍﻟْﻌﺒﺎﺩِ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪِ , ﺃَﻧْﻔَﻌُﻬُﻢْ ﻟِﻌِﻴَﺎﻟِﻪِ" 📚 ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺑﻮ ﻳﻌﻠﻰ ، ﻭﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ .

"አላህ ሱ.ወ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ለቤተሰቡ ጠቃሚው ነው"
#አላህ በእርግጥ መልካም መስራትን አዟል። #ስኬትንም ከመልካም ስራ ጋር አቆራኝቶታል።

{ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩ } [ الحج :77]

" በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡ "

ﻭﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻣﻮﺳﻰ ﺍﻷﺷﻌﺮﻱ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ - ﻗﺎﻝ : "ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ (ﷺ) :- ‏( ﺃَﻃْﻌِﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺠَﺎﺋِﻊَ، ﻭَﻋُﻮﺩُﻭﺍ ﺍﻟﻤَﺮِﻳﺾَ، ﻭَﻓُﻜُّﻮﺍ ﺍﻟﻌَﺎﻧِﻲَ" 📚 ‏ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ‏.

አቡሙሳ ረ.ዐ እንድህ ሲሉ ከነብዩ ﷺ ዘግበዋል:

" የተራበን አብሉ፣ የታመመን ጠይቁ፣ እስረኛንም ፍቱ !"

👉 ከነዚህ ሀድሶች የምንረዳው ቁምነገር ለሰው ልጆች መልካም መዋል ( ኢህሳን ኢላ ኸልቂላህ) እየተረሳ የመጣው ኢስላማዊ_እሴታችን ነው።

#በእኛ ቦታ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተቸገሩትን እንርዳ በሚል ሰበብ በሰፊው የተሰማሩበት የእለት ተለት ተግባራቸው አድርገውታል።በእርዳታም ምክንያት ብዙ ወገኖቻችንን ከእምነታቸው እያስወጧቸው ነው።

#የነብዩን ﷺ አስተምሮ በመተግባር የመልካም ስራ ቁንጮ የሆነውን የተቸገረን የመደገፍ ስራ እናዘውትር

ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል
አዋቂዎች አይደለንም አህለል ቢደአ ግን አይሸውደንም
[]~ ሰለፍያ~[]
የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና
መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና
በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ
ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ
ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ
መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ‼️
https://t.me/Hassendawd

1,307

subscribers

139

photos

25

videos