የተሰባበሩ ፊደላት @yetesebere Channel on Telegram

የተሰባበሩ ፊደላት

@yetesebere


👉ግጥም
👉ወግ
👉የተሰበረ የልብ ቃላት
👉ጠቃሚ ፅሁፎች

አናግሩኝ 👉 @Tiya67

Join አድርጉን...

ሰላማችን ይብዛ ...
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት።

የተሰባበሩ ፊደላት (Amharic)

የተሰባበሩ ፊደላት በሰላም በተለያዩ እና በሰው ልጆች በተሞላም ተመቻችሁ ሩካ ቀንድ ሃገርን እና ኢትዮጵያን ያሳዩት ነው። ፊደላት ሆነን አስተማሩን እና የትምህርትን በማስመልከት ምን እንደመና ለማብረመሰረት በማንኛውም ቤት ላይ በነበሩ መረጃዎች ውስጥ እንዴት እና እንፈልግም የሚችሉ ሰዎችን ለመከታተል በነበሩበት እጅግ እንቆጠቅናለን። በዚህ እንዳላሰራን ታዳጊ ፊደላትን አልመረጡትም።

የተሰባበሩ ፊደላት

03 Nov, 19:32


ታሳቢ ዋጋዎች
1ኛ  ተገጣጣሚ ጠረጴዛ 1 ሜትር 3ሺ ብር አንዱ
2ኛ ኮፒ እና ፕሪንት ማሽን 65,000(ስልሳ አምስት ሺ)
3ኛ ፕሪንተር ቀለሞች እና ካርቲሌጅ ሁሉም አዲስ ናቸው የ1ዱ ዋጋ 1ሺ ብር ::
4ኛ የከባድ መኪና ፊልትሮ ሁሉም አዲስ ናቸው የ1ዱ ዋጋ 1200
5ኛ ጀነሬተሩ 7500

ሁሉም ድርድር አላቸው ::



👉👉👉 @Tiya67 በውስጥ አውሩኝ ።

የተሰባበሩ ፊደላት

03 Nov, 19:31


65,000( ስልሳ አምስት ሺህ ብር)
ይሄን ኮፒ እና ፕሪንት ማሽን ከፈለጉ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸጣል ::
አሁኑኑ ማናገር ይችላሉ ::

የተሰባበሩ ፊደላት

31 Oct, 21:03


Re-P (ንጉሡ ተሰማ (ጢያ) )
____
እውነት ካንቺ ካራራቀኝ ፥
ምን አገባኝ...?
***
ጠማማ ልብ : መቅናት ቢችል...
ግመል መርፌ ... መች ሊጠበው..? ፣
የካብኩት ቤት : በፍቅር ሥም ...
አሸዋ ነሽ... : አፈረስሽው...? ።
***
ባላይ ኖሮ ባልተከፋሁ...
ለጥላቻም... ባልተጋፋሁ ።
ልብሽ ክፉ : ሆኖ ያድራል ፣
ከ ባቄላም ይጠጥራል ።
***
ፍቅር ክፉ ... መውደድ ጠላት ፣
ውሸት ብዬ ... እንዳልክዳት ፣
ምርኮኛ ነኝ...
አልጠላትም ... በሰው አልጋም : ዓይኔ ቢያያት።
***
እውነት ካንቺ ካራራቀኝ ፥
ምን አገባኝ...!!!

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

29 Sep, 09:12


✍️ ንጉሡ ተሰማ (ጢያ)
       (ይፈግግልሻል )
**********

አምና በሆነልኝ ....
እንደዚህ ፈገግታ : ልክ እንደ ደስታዬ ፣
ስቄ አልፈው ነበር : ባንቺ መገፋቴን :  ደብቄው ዕንባዬ (ን) ።

አምና በሆነልኝ ....
የደስታዬ ምንጩ : እኔው እንደነበርኩ ፣
ስትገላመጪኝ...
አትችልም ስትዪኝ ... እንደዚህ በሳኩኝ ።

ዘንድሮ ሆኖልኝ ...
ባህር ሆኖ ልቤ : አንድ ጋር የረጋ ፣
በያንዳንዱ ድርጊት : ይፈግግልሻል ... ሲመሽም ሲነጋ ።

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

27 Sep, 07:39


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !!!
መልካም በዓል ...!!!!


t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

15 Sep, 07:52


መልካም መውሊድ

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

10 Sep, 21:11


🇪🇹🇪🇹🇪🇹እራሳችንን የምናንፅበት ዘመን ይሁንልን 🥰🥰🥰🇪🇹🇪🇹🇪🇹

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

10 Sep, 21:08


መልካም አዲስ ዓመት !!!! (2017🇪🇹)
የሰከነ ዘመን ይሁንልን........!!!!!!!!!!!!!!!! 🇪🇹🇪🇹

የተሰባበሩ ፊደላት

24 Aug, 15:51


✍️ንጉሡ ተሰማ(ጢያ)
*

እውነት አላጣችም :
ተመረጠች
እንጂ ...
ደርሳ ለመከፋት ፣
እውነት እሱ ካለ :
ከምትቦርቅ ልጇ...
እንደምን ለያያት ? !

ዝም አይሉት ነገር :
አይዘልቁትም ችለው :
ሰውነት አለና ...፣
*
የማይታይ ግዙፍ
ከሚታየው ቅንጣት
ከቶ አይበልጥም እና ...
*
ሰውነትን ገንቡ
ቤተ- እምነት ተው... ና ።


ማስታወሻነቱ ፦.... ለህፃን ሔቨን እና ለእኩዮቿ (ተመሳሳይ ጥቃት ላስተናገዱ !

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

17 Aug, 19:27


ዛሬም ሙዳችን ተደክሏል.... #በ7_ዓመት ህፃን ልጅ በመደፈሯ 😭😭😭😌😫😫😭

የተሰባበሩ ፊደላት

11 Aug, 18:27


አይገርምም ግን ???
🥰(ነገሮች ሁሉ ዛሬም አሉ ... እሳት ባቀጣጠልኩ ቁጥር የከንፈርሽ እስትንፋስ ይመስለኛል)
🥰 አካል እና ስሜት እንዴት የተለያዩ ሆኑ ?🤔
🥰እስትንፋስ ፣ ጠረንሽ ፣ ድምፅሽ ፤ ሹክሹክታሽ... በየምክንያቱ ይመጣሉ ፤ መጥተው መች ይቀራሉ... ከንፈሬን ከንፈርሽን ይነካል ፣ አፍንጫዬ ጠረንሽን ይምጋል ፣ ጆሮዬ ዜማ ድምፅሽን እና ሹክሹክታሽን ይቋደሳል።

እኛ የመራቅ አቅም እንደሌለን ሲያሳየኝ ... እሩቅ ሳለሽ ከእኔው ጋር ያኖርሻል ። አይገርምም !!!???!!!

t.me/yetesebere

የተሰባበሩ ፊደላት

07 Aug, 10:05


t.me/yetesebere