የዴል ካርኔጊ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
ዕውቁ ዴል ካርኔጊ #ጠብታ_ማር ከተሰኘው መጽሐፉ ቀጥሎ አለም አቀፍ እውቅናን ያገኘበት #HOW_STOP_WORRYING_AND_START_LIVING የተሰኘው ድንቅ መጽሐፉ #ሕይወት_ቀላል_ናት_አታወሳስባት በሚል ርዕስ ተተርጉሞ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ 7 ምርጥ ትምህርቶችን እነሆ ለቅምሻ ብለናል።
#1_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_ከልክ_በላይ_በማሰብ_ነው!
ከልክ በላይ ማሰብ የአእምሮ ድራማ ነው። ከልክ በላይ ማሰብ መቆጣጠር የማትችለውን ለመቆጣጠር እየሞከርክ እንደሆነ የሚያሳይ ምልክት ነው።
ከአእምሮህ ወጥተህ ዙሪያህን ብትመለከት ግን ሁሉም ነገር አእምሮህ ውስጥ እንዳለው አይደለም። ሰዎች የራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ ነው።
ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ። መሞከር የምትችለውን ሞክር። ተንፍስ፣ ውሃ ጠጣ፣ ስፖርት ስራ፣ ስራህን ስራ፣ ለወዳጆችህ ጊዜ ስጥ። ቀሪውን ለፈጣሪህ ተውለት!
#2_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_ከልክ_በላይ_በመጨናነቅ_ነው!
ጭንቀት የዛሬ ደስታህንና የነገ ተስፋህን የሚሰርቅ ሌባ ነው። ሕይወትህ ውስጥ ጥሩም፣ መጥፎም ነገሮች ይፈጠራሉ። ይህን እውነት መቀየር ትችላለህ?
አትችልም። ያንተ ድርሻ መኖር ነው። ካንተ የሚጠበቀው አስልተህና አቅደህ መኖር ነው።
መለወጥ ለማትችለው አትጨነቅ። እየተጨነቅክ ቀላሏን ሕይወት አታወሳስባት።
#3_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_ከልክ_በላይ_ተሸክመሃት_ነው!
ሕይወት ቀላል ናት፤ የሚያቀላት እና የሚያከብዳት ግን አሸካከምህ ነው። የታላቁ ሳይንቲስት ቶማስ ኤዲሰንን አንድ ታሪክ ልንገርህ። አንድ ቀን ለዓመታት የለፋበት ግዙፍ ላብራቶሪው ሙሉ በሙሉ ተቃጠለ። ሰዎች ደነገጡ። ራሱን የሚያጠፋም መሰላቸው፤ የእሱ መልስ ግን የተለየ ነበር "አያችሁ ስህተቶቻችን ሁሉ ሲወድሙ! አሁን የተሻለ ትክክለኛ ነገር የምንፈጥርበት ልምድ አገኘን" አለ።
አሻካከምህን አክብደህ አታክብዳት። ቀለል አድርገህ ያዛት፤ ትቀልልሃለች።
#4_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_በጨለምተኛ_አመለካከትህ_ነው!
ጨለማ ጨለማውን መርጠህ እያየህ ለምን ብርሃን አይታየኝም ማለት አትችልም። አንተ ጨለማ ጨለማው ስለታየህም ሕይወትም ብርሃን የላትም ማለት አይደለም።
የምታየው ማየት የምትፈልገውን ነው። አእምሮህ ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። መልሶ የሚሰጥህ አንተ በሐሳብ የምትመግበውን ነው።
ብሩህ ሁን ሕይወት ትበራልሃለች።
#5_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_እንደ_እገሌ_ካልሆንኩ_ብለህ_ነው!
ንጽጽር የደስታ ጸር ነው። አንተ እንደ አንተ እንጂ እንደ እገሌ መሆን አትችልም። ይህን ጥበብ ያወቅክ ቀን የሕይወት ቀላልነት ይገባሃል።
ምክንያቱም የምትሰራው የምትወደውንና የምትችለውን ነው፤ የምትኖረውም እንደ ራስህ ነው።
#1_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_የምትፈልገውን_ባለማወቅ_ነው!
ዓላማ ላለው ሰው ሕይወት ግልጽና ውስብስብ ያልሆነች መንገድ ናት። ምን እንደምትወድ፣ በሕይወትህ ምን ማሳካት እንዳለብህ፣ ልብህ የሚቃጠልለት ነገር ምን እንደሆነ ካላወቅክ ግን እንደ መንገድ ዳር ቆሻሻ የመጣ ነፋስ ሁላ ይወስድሃልና ሕይወት ከባድ ትሆንብሃለች።
ግብና ዓላማህን ለይ። መንገድህና አኗኗርህ ሁሉ ከእሱ ጋር የተስማማ ይሁን። ያኔ ሕይወት ቀላል ናት።
#7_ሕይወት_ቀላል_ናት
#ያወሳሰብካት_ከአምላክህ_ይልቅ_በሰው_ላይ_በመተማመህን_ነው!
ሰው መቼ እንደሚጥልህ የማታውቀው ስር የሌለው ዛፍ ነው። ሕልምህ፣ ደስታህ፣ ዋስትናህ ሰው ላይ ከተደገፈ ባልጠበቅከውና ባልተዘጋጀህበት ጊዜ አሸዋ ላይ እንደተሰራ ቤት ይፈራርሳል።
መተማመኛህ መቼም የማይጥልህ፣ ሲደክምህ ማረፊያ ጥላ የሚሆንህ አምላክህ ብቻ ከሆነ ግን ቢነቀንቁህ የማትወድቅ ትሆናለህ።
ከአምላክህ ጋር ስትጓዛት ሕይወት ቀላል ናት፣ አታወሳስባት።
አዲሱ የዴል ካርኔጊ #ሕይወት_ቀላል_ናት_አታወሳስባት መጽሐፍ በገበያ ላይ።
ዕውቁ ዴል ካርኔጊ #ጠብታ_ማር ከተሰኘው መጽሐፉ ቀጥሎ አለም አቀፍ እውቅናን ያገኘበት #HOW_STOP_WORRYING_AND_START_LIVING የተሰኘው ድንቅ መጽሐፉ #ሕይወት_ቀላል_ናት_አታወሳስባት! በሚል ርዕስ ተተርጉሞ፣
እንዲሁም
#THE_LEADER_IN_YOU የተሰኘው ደግሞ #ራስን_መምራት በሚል ርዕስ ተተርጉሞ 3ተኛው ዕትም በገበያ ላይ ውሏል።
ሁለቱም የዴል ካርኔጊ መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።
📕📕📕
@getmnaleloch