የጤና ወግ - የጤና መረጃ @yetenaweg Channel on Telegram

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

@yetenaweg


ይህ የጤና ወግ ነው።
Yetenaweg.com
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።
በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።

የጤና ወግ ቀጥተኛ ህክምና አይሰጥም። ሰለ መድሀኒትዎ ወይም ህክምናዎ ጥያቄ ካለዎት ሀኪምዎን እንዲያናግሩ እንመክርዎታለን።

የጤና ወግ - የጤና መረጃ (Amharic)

የጤና ወግ - የጤና መረጃ ለመደገፍ በልዩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጥታ የእውነትን አስማምን እንዲቀርቡ የጤና ወግ በቀጥታ በመሆኑ እንዲቀርቡ ይመልከቱ። ማለትም ከሌሎች ጥናት በአንፃሩ ደምር ያደረገ መረጃዎችን ዳታ የማውጣት ብቻ ማድረግ ከታገቡን በኋላ በግዜ ተጨማሪ መረጃዎች ይምረጡ። ይህ የጤና ወግን መፅሀፍትን ማየት የሚያስፈልግዎት ህክምና አይሰጥም። ነገር ግን ከዚህ በፊት በመሆኑ የሚፈቃደን ጥያቄዎችን ለመልከት የሚያረጋግጥ እንዲሆን የሚቀመጥ ነገርን ማሳሰብ አለበት። ወደ ጤና ስነልቦች ምንጭ እና ሌሎች ብቻ መረጃዎች ለመስራት ምን ያደረጉት ነገር ማስተዋወቅ እንዲችልን በማስመልከት መቸምን እንሰጣለን።

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

24 Nov, 04:55


በየአመቱ በ ፈረንጆች November 18-24 የፀረ-ተሕዋስያንን መቋቋም (AMR)  ሳምንት  ታስቦ ይውላል።

👉ፀረ-ተህዋሲያንን መቋቋም (ኤኤምአር) የሚከሰተው ባክቴሪያ፣ ቫይረሶች፣ ፈንገሶች እና ጥገኛ ተውሳኮች በጊዜ ሂደት ሲለዋወጡ እና ለመድኃኒት ምላሽ መስጠት ሲሳናቸው ኢንፌክሽኑን ለማከም አስቸጋሪ እና የበሽታ መስፋፋት፣ ከባድ ህመም እና ሞትን ሲያስከትል ነው።

👉 ይህም የሚከሰተው መድሀኒቱን ደጋግሞ በመውሰድ፣በሀኪም ያልታዘዘ መድሀኒት በመወሰድ ፣ ለበሽታው ከሚመጥነው መድሀኒት በላይ መውሰድ ና በሀኪም የታዘዘን መድሀኒት ባለመጨረስ ሊሆን ይችላል።

👉ይህን የAMR ሳምንትን በቃላት ሳይሆን በተግባር እናክብረው ፣ እራሳችንን እና ሌሎችን እናስተምር፣ ፀረ-ተህዋሲያን መቋቋምን ለመዋጋት እና የወደፊት የጤና እንክብካቤን ለመጠበቅ በጋራ እንሟገት፣ አብረን  እንስራ።

ለበለጠ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ።

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

14 Nov, 04:50


በየአመቱ በፈረንጆች November 14 አለም አቀፍ የ ስኳር በሽታ ቀን  ታስቦ ይውላል። በሃገራችንም ለ34ኛ ጊዜ ህዳር 5 "የስኳር ህመምና ምሉዕ ደህንነት፡- ለስኳር ህመም ህክምና እና ክብካቤ ተገቢውን ተደራሽነት ካገኙ ሁሉም የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች በተሟላ ጤንነት የመኖር እድል አላቸው!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል::

የስኳር በሽታ ስጋቶችን ለመቀነስ እና በስኳር በሽታ የተያዘ ማንኛውም ሰው ፍትሃዊ ፣ አጠቃላይ ፣ ተመጣጣኝ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ህክምና እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል።

በሃገራችን ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር እንደሚኖሩ ሲገመት ከነዚህም 50 በመቶ የሚሆኑት ህሙማን ምንም አይነት የስኳር ምርመራ ያላደረጉ በመሆናቸው የህክምና እርዳታ እያገኙ አይደለም፡፡

💥የስኳር በሽታ ምርመራዎች ምንድን ናቸው?

💥 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?

💥የስኳር በሽታ የሚያስከትላቸው ችግሮች ምንድን ናቸው?

💥 የስኳር በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?

እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ
🔸ለበለጠ መረጃ: https://yetenaweg.com/tag/diabetes/

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

10 Nov, 16:55


Live stream finished (1 hour)

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

10 Nov, 14:59


Live stream started

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

06 Nov, 06:36


🤰🏽በዚህ እሁድ በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት አዲስ ውይይት ይዘን ቀርበናል።

ርዕሳችን: 💥የስነ ወሊድ ዝግጅት💥

የስነ ወሊድ ዝግጅት በውስጡ ብዙ ክፍሎች ሲኖሩት ከነሱም መሃል የተወሰኑት:


🤰🏽የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ

🤰🏽ለእናት እና ለልጅ አስፈላጊ ነገሮችን ማዘጋጀት


🤰🏽 የቤተሰብ እና ማህበረሰብ ድጋፍ ማጠናከር

🤰🏽እህት እና ወንድሞች ካሉ የልጆች ማቆያ ማዘጋጀት

🤰🏽የገንዘብ ዝግጅት ማድረግ

🤰🏽 ለህፃኑ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ማደራጀት

🤰🏽 የአዕምሮ እና የስሜት ዝግጅት

🤰🏽ስለ ድኅረ ወሊድ እንክብካቤ መማርን ያካትታል።



🗣እንግዳችን:
👉 ዶ/ር ቅድስት ገ/ጻዲቅ ደበሌ (የፅንስ እና የማህፀን ሐኪም በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል)

🗓እሁድ ህዳር 1 2017

ከምሽቱ 12 ሰዓት (በኢትዮጵያ)

⚡️ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yetenaweg?voicechat

⚡️የውይይት ቻናላችንን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ: https://t.me/+dl4juoncBxMyODVh

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

10 Nov, 15:00


Live stream scheduled for

የጤና ወግ - የጤና መረጃ

30 Oct, 08:21


✍️✍️ በየአመቱ በ ፈረንጆች ጥቅምት 29 (በትላንትናው እለት) አለም አቀፍ የ ስትሮክ ቀን  ታስቦ ይውላል።

✍️ ቀኑም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስትሮክን ለመከላከልና ከስትሮክ ለማገገም ያለውን ሚና አጉልቶ የሚያሳይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለተውጣጡ ሰዎች በማዳረስ ና በማሳተፍ ይከበራል።

💥የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስትሮክን በመከላከል ረገድ ያለው ጠቀሜታ ምንድነው?

🔸ለበለጠ መረጃ: 👉እዚህ ይጫኑ