ተማሪዎች ለመምህራን ፣ ሰራተኞች ለቅርብ የስራ ባልደረቦቻቸው የስኳር ህመም እንዳለባቸው ቢያሳውቁ ችግር ሲገጥማቸው እርዳታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡
ማንኛውም የስኳር ህመምተኞች የስኳር ህመም እንዳለባቸው ፣ የሚወስዱትን መድኃኒት ዓይነትና መጠን የሚገልጽ መታወቂያ እንዲይዙ ይመከራል። ይህም በአጋጣሚ ህሊናቸዉን ቢስቱ የህክምና እርዳታ በአፋጣኝ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡
እንክብልም ሆነ ኢንሱሊን የሚወስዱ ህመምተኞች ሁል ግዜም ቢሆን ስኳር /ከረሜላ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡የስኳር ማነስ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ሲሰማዎት በቶሎ እራስን ለመርዳት ይህ ይጠቅማል፡፡
የስኳር ህመምተኞች በተደጋጋሚ የስኳር ማነስ ምልክቶች ከተሰማቸዉ የሚወስዱትን የመድኃኒት መጠን መቀነስ ስለሚያስፈልግ ክትትል ወደሚያደርግላቸው ባለሙያ በመሄድ ምክር ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
✍️ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሄልዝ ሊትረሲ ክፍል የተዘጋጀ ©
▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"