የምማርበት ግቢ አጥር የለውም ግን ስንት እና ስንት ሚሊዮን ብር ፈሶበት Functional ያልሆነ ሴኩሪቲ ካሜራ የሌለበት ኮርነር የለም ።
ጥበቃዎች መሳሪያ ተነጥቀዎል። ከኮማንድ ፓስቱ ጀምሮ...
ታዲያ ምን ቢሆን ጥሩ ነው...
አጥር የለም...
በየትኛውም አቅጣጫ ማንኛውም ሰው ወደ ዩኒቨርስቲው እና ሆስፒታሉ በቀላሉ መግባት ይችላል ።
ከወራቶች በፊት...
ኢንተርን መዘረፍ ተጀመረ...ዝም...
ሬዚደንት መከራውን በላ...ዝም...
አንዳንድ ሲኒየሮች ተሯሩጠው አመለጡ...ዝም...
በመጨረሻም ዝርፊያው ባለስልጣናቱ ጋ ደረሰ ...በመሳሪያ የታገዘ ዝሪፊያ ...
አሁን ሲኒየሮች አመፅ ላይ ናቸው 😁
ሞርኒንግ አይገቡም...
OPD አይገቡም...
የሲኒየር አመፀኛ ማየት ህልሜ ነበር። እንዴት ደስ እንደሚሉ😊
እናንተ አንድ ብትሆኑ ታናናሾቻችሁ ባልተሰቃዩ ።
ለማንኛውም ችግርን በእንቁላሉ ...ነግ በኔ... ብለን መፍታት የግቢያችን ብቻ ሳይሆን የሀገራችን ችግር ነው ። ሁሉም የሚነቃው በሩ ሲንኳኳ ነው። እናም ትንሿ ኢትዮጲያን እዚህ አየኃት ።
በተረፈ Prioritization የሚባል ነገር አለ ...
በሚሊየንስ ፈሰስ አርጎ የማይሰራ ካሜራ ከመግጠም አጥር ማጠር...
ከአጥር ባልተናነሰ የታጠቀ ዘብ ማቋቋም...
ነበር...🥹
ለማንኛውም በዙሪያዎ ያሉ አጥር የሆኑ ክልሎች እየታመሱ ፈንጠዝያ ውስጥ ያለችው ...
ራሷን ከፓሪስ የምታነፃፅረዎ አዲስ አበባም እንዲሁ ናት...
ከታካሚው የታክሲ 10ብር ብሎ መቀበል የቀረው የጤና ባለሙያ ይዛ የምታሸበርቀው አዲስ 😊...
Priority Matters
ብቻ ጭፍን ደጋፊዎችም...ጭፍን ተችዎችም አደብ ግዙ...
Priority Matters
@debolteam